ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

❝ ዳሩል ቁርአን ❞ የ አጫጭር ኪታቦች መድረሳ

❝ ዳሩል ቁርአን ❞ የ አጫጭር ኪታቦች መድረሳ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይኽ ግሩፕ አላማው የ አሏህን ﷻ ሸሪዐ እንዲሁም የነብዩን ﷺ ሱና አጥብቆ የሚይዝ ወንድምና እህቶችን ማፍራት ነው ⌚️የቂራአት ሰዐት ከቀኑ፦           ➜  በኢትዮ    10:20           ➜  በሳዑዲ     4:20

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
736
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ወአላ ተሰረቢቀሃ

Repost from N/a
ዐብዱረሕማን አልአውዛዒይ (157 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:- اصْبر نفسك على السُّنَّة، وقفْ حيثُ وقفَ القوم، وقُلْ بما قالوا، وكفّ عمَّا كفّوا عنه، واسْلك سبيل سلفك الصَّالح، فإنَّهُ يسعك ما وسعهم “እራስህን በሱና ላይ አፅና፡፡ ሰዎቹ (ሶሐቦቹ) ከቆሙበት ቁም፡፡ እነሱ ያሉትን በል፡፡ ከታቀቡት ታቀብ፡፡ የመልካም ቀደምቶችህን መንገድ ተከተል፡፡ ለነሱ የበቃቸው ይበቃሀልና!”

"የ19 ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ወደ ህክምና ማዕከል በሄደችበት ማደንዘዣ በመውጋት አስገድዶ መድፈር የፈፀመው ዶ/ር በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ" የሚል ዜና አየሁኝ። "በሃኪም እንዴት ይሄ ይፈጸማል?" ማለት ሞኝነት ነው። በሃኪም ቀርቶ በሃይማኖት አስተማሪም ይፈጸማል። መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው። ማንኛዋም ሴት ከባዳ ወንድ ጋር ተገልላ ልትገኝ አይገባትም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ لا يخلوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ فإنَّ الشيطانَ ثالثُهما "አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋር ብቻውን አይነጠል፤ ምክንያቱም ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነውና።" [ቲርሚዚይ፡ 2165] "ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነው" የሚለው አጉል መልካም እምነት እንዳያዘናጋን ጥብቅ ማሳሰቢያ ነው። ስለዚህ ያልታሰበ ከባድ ጥፋት የመድረስ እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት ነው። ህክምናን በተመለከተ ሴቶች አማራጭ ካለ በሴቶች ታከሙ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ ከቤተሰብ ጋር እንጂ ብቻችሁን ወንድ ሃኪም ዘንድ አትግቡ። ወይም ሴቶች ነርሶች ካጠገባችሁ እንዲሆኑ አናግሩ። እዚህ ላይ "ውጭ ቆዩ" የሚሉ ሃኪሞች ይኖራሉ። (መግቢያየ ላይ የጠቀስኩትም ክስተት በዚህ መልኩ የተፈፀመ ነው።) እንዲህ አይነት ሃኪም ሲገጥመን ቢቻል ማስረዳት፣ ካልሆነ መጋፈጥ ይገባል። ፈቃደኛ የማይሆኑ ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ዘንድ አትሂዱ። ቆራጥ ከሆንን ለራሳቸው ሲሉ ያስተካክላሉ። ለሃኪሞች ማሳሰቢያ፦ ከባዳ ሴት ጋር ተገልሎ መቆየት እንደማይቻል አትዘንጉ። ስለዚህ ስታክሙ ቤተሰብ በቅርብ እንዲኖር አድርጉ። ወይም ረዳቶች ባቅራቢያችሁ ይኑሩ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠማችሁ የምትሰሩበትን ክፍል በሩን ክፍት አድርጉት። በነገራችን ላይ እንኳን ባዳ የሆነ አካል በቤተሰብ መሀል ራሱ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል። ለዚያም ነው ኢስላም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥብቅ መመሪያ ያስቀመጠው። ነብያችን ﷺ ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ለአስር ዓመት ልጆች! ስለዚህ ቤተሰብ አላህ ባገራለት ልክ መኝታቸውን ሊለያያቸው ይገባል። ሁሉም አንድ ክፍል ውስጥ የሚተኙ ከሆነ ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ደግሞ ሌላ ጥግ ማድረግ ይገባል። በቂ ክፍሎች ካሉ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን የብቻ ሌላ ክፍል ማድረግ ይገባል። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው። አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም። "የዘመድ ልጅ ነው"፣ "ቤተሰብ ነው"፣ "ሸይኽ/ ኡስታዝ ነው"፣ "የጎረቤት ልጅ ነው"፣ "እንግዳ ነው"፣ "ስርአት ያለው ጨዋ ልጅ ነው"፣ "ትልቅ ሰው ነው"፣ የመሳሰሉ የዋህ ድምዳሜዎች ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ። እንኳን ሴቶችን ከወንድ፣ ወንዶችን ከወንድም መኝታቸውን መለየት ይገባል። ሌላው ቀርቶ አባት ወይም ወንድም ቢሆኑ እንኳ ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ የሚያሳዩ ከሆነ የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ©: ኢብኑ ሙነወር

ለተዉኪድ(ለማጠናከር