قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
الذهاب إلى القناة على Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
898
المشتركون
-224 ساعات
-167 أيام
+2730 أيام
أرشيف المشاركات
አዝነንም፣ተደስተንም፣አግኝተንም አጥተንም፣ከስረንም እንድሁም አትርፈንም.. ... ሁሌም አልሐምዱሊላህ!!!
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
✍ እናቱን ለሚወድ ብቻ
🎂ደርሰሽ ለጡረታ
የዘጠኝ ወር ቤቴ
ኑሪልኝ እናቴ
የደስታ ማጀቴ
ውስጤ ነሽ አንጀቴ
🍢 እማየ🍢
ችግር አይቅረብሽ ኑሪ በደስታ
ተፈጥሮሽ ልዩ ነው የጀሊል ስጦታ
ሀቅ፣ሽን መጠበቅ ዛሬ ላይ ብረታ
በእጀ ላንከባክብሽ ደርሰሽ ለጡረታ
⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤
🎤 በወንድም አቡ ሹራ አህመድ ካሳየ
ቻናሏን እናሳድጋት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4645
https://t.me/Sobabilalmesjid/4645
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
🌹 ፈገግ በሉልኝ 🌹
በበፊቱ ግዜ ነው ይባላል። ታሪኩ እናም አራት የገጠር ሰዎች በጀመዓ እየሰገዱ ነበር ከዛም ልክ ሩኩዕ ሲያረጉ አንዱ ወይኔ ወገቤን አለ ሁለተኛው ደሞ የወግብን ነገር አታንሳው ይለዋል። ንግግራችውን የሰማው ሶስተኛ ሰው ሶላት ላይ አይወራም ይላቸዋል ከሁሉም የባሰው አራተኛዉ አንተ ራስህ ሶላት ላይ አኮ ነህ ብሎት እርፍ
አውነተኛ ታሪክ የሆነ ነው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሑሴን ባይኖር ኖሮ አላህም አይመለክ፣ ነብዩም አይታወቁም ነበር ይላል ይሄ ሺዒ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
إياكم والغلوَّ في الدينِ فإنما أهلَك مَن كان قبلَكم الغلوُّ في الدينِ
"በሃይማኖት ውስጥ ድንበር ማለፍን ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም ከእናንተ በፊት የነበሩትን ያጠፋቸው በሃይማኖት ውስጥ ያለው ድንበር ማለፍ ነው።" [አን-ነሳኢይ፡ 3057]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ስለ ክብርህ ስትል ተዋቸው
~
የሰው ልጅ አመል እንደ መልኩ ብዙ አይነት ነው። ብዙ ደግ የመኖሩን ያህል በየትኛውም ሁኔታ መጥፎህን ብቻ ለማውራት ያሰፈሰፈ አለ። ልቡ በክፋት የተሞላ። በጎህን ሲያይ ይከፋዋል። ሰዎች በመልካም ቢያነሱህ ያመዋል። ያለ ስምህ ስም ይሰጥሃል። ያለ ግብርህ ያሸክምሃል። በሌለህበት ያውልሃል። ያለህን መልካም ይገፍሃል። ክፉህን ቢያይ ይቦርቃል። ሰዎች ቢያወግዙህ አታሞ ይመታል። ይቅርታህ አይዋጠውም። ዝምታህ አይጥመውም። ምላሽህም አይመቸውም። የቱንም ብታደርግ አታስደስተውም። ስህተት ቢያገኝ ጭራና ቀንድ አውጥቶለት ቆርጦ፣ ቀጣጥሎ ጭራቅ ያደርግሃል። ንግግርህን ፈፅሞ ባላሰብከው መልኩ ተርጉሞ ራሱ አጣሞ በተረዳው ላይ ተመርኩዞ ነብር ግስላ ሆኖ ይነሳብሃል።
በቃ! አንዳንዱ ባህሪው የውሻ አይነት ነው። ባለፍክ ባገደምክ ቁጥር ይጮሃል። "ዋው!" ማለትን የመተንፈስ ያህል ኖርማል አድርጎታል። ብትነካውም ይጮሃል። ብትተውም ይጮሃል። እንዲያውም ውሻ ሲያይህ ነው የሚጮኸው። ይሄኛው ሳያይህም ይጮሃል። "አትርሱኝ" ባይ ነገር ነው። በሌለህበትም፣ ሳታስታውሰውም ይጮሃል። በየትኛውም ሁኔታ ሊነድፍህ ስለተዘጋጀ ተያያዥ ጉዳይ እስከሚያገኝ አይታገስም። ይበላዋል። ያሳከዋል። ስለ ጦሃራ ስታወራ "ዋው!" ስለ ተውሒድ ስትናገር "ዋው!" ስለ ራስህ ብታነሳ "ዋው!" ራሱ የሚደግፈውን ሃሳብ ብታነሳም "ዋው!" ከማለት አይመለስም። ብትመልስለት አገር በጩኸት ያቀጣጥላል። ዝም ስትለውም ወይ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ወይ "አሸነፍኩ" ብሎ ይጮሃል።
እና ምን ይሻላል? ጩኸቱን ላታስቆመው ነገር አትጨነቅ። እርሳው። ሰላምህ ያለው እሱን ከመርሳት ነው። ሊፈትንህ ይችላል። ከዚህ ውጭ ያለው ምርጫ ግን የበለጠ ፈታኝ ነው። አሕመድ ሻኪር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"የማያውቅ ሁሉ ይወቅ! ምድር ላይ ሞኞች ብዙ ናቸው። እና አንድ ሰው ከሞኝ ለሚንፀባረቅ ሞኝነት ሁሉ የሚበሳጭ ከሆነ በብስጭቱ ሰበብ ብሶት መከፋቱ ይራዘማል። ሞኞችን ያሻቸውን ይበሉ ተዋቸው። ለክብርህ ስስት ይኑርህ። ክብርህ ለሞኞች ምላስ ተብሎ የሚመነዘር ከመሆን በላይ ውድ ነውና።"
[መጅሙዑል መቃላት፡ 1/579]
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (አቡ ሁዘይፋ)
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
‘ሸይኽ ኢብኑ ባዝና አልባኒይ ይጋሩታል ወይስ ይቃረኑታል?’ ስለተባለው ጉዳዩ እኔ የሸይኽ ረቢዕን ኪታቦች በብዛት አላነበብኩም። ይሄ አንድ ነገር ነው። እንደገና ሌላው ነገር እንዳልነው የሱና ሰዎች ከፊሉ ከፊሉን በጭፍን አይከተሉም። እሱን ቢሀይሱና ከልክ እንደወጣ ቢያዩ ኖሮ የሚለውን ለማረም ፅሁፎችን ባወጡ ነበር። የሚለውን ለመመለስ ኪታቦችን ባዘጋጁ ነበር። ምንም ይሁን ምን ሁላችንም እናገኛለን፣ እንስታለን። እንዘነጋለን፣ እናውቃለን። ወላሁል ሙስተዓን።”
ምንጭ፦ https://www.muqbel.net/fatwa.php?fatwa_id=4330
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"መድኸሊዮች አይደለንም፣ ግን መድኸሊዮች ነን"
~
በኢማሙ ሻፊዒይ ላይ ድንበር የሚያልፍ ሻፊዒይ አትሁን፣ በአልባኒይ፣ በኢብኑ ባዝ ላይ ድንበር አትለፍ ስትል ኮሽታ አያሰማም። በረቢዕ ላይ ድንበር አትለፍ ስትል ግን "ሸይኽ ረቢዕን ሰደብክ" ብሎ አገር ምድሩን ያቃጥላል። ይሄው ነው በቃ የማሰብ አቅማችሁ? ረድ ማለት እናንተ ዘንድ የሰውን ንግግር እያጣመሙ በመተርጎም መጮህ ነው? እናንተ አስተማሪዎቻቸው የሆኑ ሰዎች ምንኛ ያሳዝናሉ?!
ድንበር ማለፍኮ ይሄው ነው። እንጂማ ድንበር አላፊዎችኮ "ልክ ነው እኛ ድንበር እናልፍለን" ብለው አያውቁምኮ። ብቻ ቢኮሰኩሳችሁም ዋጡት። በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር የሚያልፉ ሰዎች በተጨባጭ አሉ። ለዚህም እናንተ ተግባራዊ ማሳያ ናችሁ። ደግሞም "ረቢዕን መልእክተኛ አደረጉትን?" ያልኩት እኔ ሳልሆን ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ ናቸው። ብልግናችሁ ለከት አጥቷልና ዝመቱባቸው። ሸይኽ አዝሀር ሲነይቆራም "የሸይኽ ረቢዕ ንግግር ወሕይ ነው ወይ?" ብለዋል። በቀጣይ ዑለማኦች ለሸይኽ ረቢዕ የሰጡትን አድናቆት መዘርዘር ላይ ትጠመዱ ይሆናል። አንድ ትልቅ ዶሴ ብታቀርቡም እውነታው አይቀየርም። በማንም ላይ ድንበር ማለፍ ባጢል ነው። "የጀርሕና ተዕዲል ሰንደቅን ተሸካሚው ረቢዕ ነው" የሚለው የሸይኽ አልባኒይ ንግግርም "ሸይኽ ረቢዕ የተናገረውን ሁሉ ውሰዱ" ማለት አይደለም። በዚህ መልኩ የሚረዱት ማሰቢያቸው የተደፈኑ በቀቀኖች ናቸው። ይሄኮ አይን ያወጣ ድንበር ማለፍ ነው። በፈውዛን ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም ሲባል ምንም አይሉም። እንዲያውም በትልልቅ የሰለፍ አኢማዎች ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም ሲባልም ምንም አይሉም። በረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም ሲባል ግን ይጮሃሉ። አይ ድንበር ማለፍ በረቢዕ ላይ ሲሆን ይፈቀዳልi "ረቢዕን በጭፍን የምትከተል መድኸሊይ አትሁን" ስትባል ከጮህክ መድኸሊይነትህን እያረጋገጥክ ነው ያለኸው።
ለማንኛውም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
وكلام يحيى بن معين والبخاري ومسلم وأبي حاتم وأبي زرعة والنسائي وأبي أحمد بن عدي و الدارقطني وأمثالهم في الرجال وصحيح الحديث وضعيفه هو مثل كلام مالك والثوري والأوزاعي والشافعي وأمثالهم في الأحكام ومعرفة الحلال من الحرام
"የሕያ ብኒ መዒን፣ ቡኻሪይ፣ ሙስሊም፣ አቢ ሓቲም፣ አቢ ዙር0፣ ነሳኢይ፣ አቢ አሕመድ ብኒ ዐዲይ፣ ዳረቁጥኒይ እና መሰሎቻቸው በዘገባ ሰዎች ላይ እና በሶሒሕና ዶዒፍ ሐዲሥ ብይን ላይ የሚናገሩት ንግግር ልክ ማሊክ፣ ሠውሪይ፣ አውዛዒይ፣ ሻፊዒይና መሰሎቻቸው በፊቅህ ህግጋትና የሐላልና ሐራም እውቀት ላይ እንደሚናገሩት ንግግር ነው።" [ረድ ዐለል በክሪይ፡ 1/72]
ስለዚህ! ልክ በፊቅህ ርእስ ላይ የአንድን ኢማም ንግግር በጭፍን መውሰድ እንደማይገባው በሐዲሥ ብይን ላይ፣ በአስተላላፊዎች ትችትና ሙገሳ ላይ የአንድን ኢማም ንግግር በደፈናው መውሰድም ግዴታ አይሆንም። ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም። ይልቁንም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ናቸው ረሒመሁላህ። ይሄ ቋሚ መርህ ከሺ ዘመናት በኋላ ሸይኽ ረቢዕ ላይ ሲደርስ አይቀየርም። አሁንም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ፦
لا يجوز لأحد أن يجعل الأصل في الدين لشخص إلا لرسول الله ﷺ ولا لقول، إلا لكتاب الله عز وجل ومن نَصَّب شخصاً كائناً من كان فوالى وعادى على موافقته في القول والفعل، فهو (من الذين فرقوا دينهم وكانوا شيعاً)
"በዲን ጉዳይ ላይ መሰረትን ለግለሰብ ሊያደርግ ለአንድም ሰው አይፈቀድም፤ ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ቢሆን እንጂ። ለየትኛውም ንግግርም እንዲሁ፤ ለአላህ - ዐዘ ወጀል - መፅሐፍ ቢሆን እንጂ። አንድን ሰው መድቦ - ያ ሰው ማንም ይሁን ማን - በንግግርም ይሁን በተግባር እሱን በመግጠም ላይ ወዳጅነትና ጠላትነት የሚመሰረት አካል እሱ 'ከነዚያ ሃይማኖታቸውን በመለያየት ጭፍራዎች ከሆኑት ነው።' " [አልመጅሙዕ፡ 20/8]
በመጨረሻም ፅሑፌን በሸይኽ ሙቅቢል ረሒመሁላህ ንግግር እዘጋለሁ። እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፦
“በሂስና ሙገሳ (ጀርሕ ወተዕዲል) ዘርፍ ላይ በሸይኽ ረቢዕ የሂስ ፅሁፎች ላይ እንዲሁም በሚጓዙበት መንገድ ላይ ይስማማሉ ወይስ ይቃረናሉ? ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚንና አልባኒይ እንደሚጋሯቸውስ ያውቃሉን?”
የሸይኽ ሙቅቢል መልስ ይሄውና :-
أهل السنة منبعهم واحدٌ - الذي يشربون منه -؛ وهو: كتاب الله وسنة رسوله ﷺ؛ فعقيدتهم واحدة، واتجاههم واحد في جميع البلاد الإسلامية.
نحن متفقون على جرح أصحاب البدع والحزبيين، متفقون على هذا، بقي في أناس هم عند شخص من المجروحين، وعند آخر ليسوا من المجروحين، هذا حدث على عهد السلف؛ فرُبّ راوٍ يقول فيه أحمد بن حنبل: ثقة، و يقول فيه يحيى بن معين: كذاب، أو العكس، وهكذا البخاري وأبو زُرعة وأبو حاتم.
والمهم: لا يقلّد بعضهم بعضاً؛ فإذا اختلفنا في توثيق شخص وتجريحه: فليس معنى هذا أننا مختلفون في العقيدة! وليس معنى هذا أننا مختلفون في الاتجاه.
وأما هل الشيخ ابن باز والشيخ الألباني يوافقونه أم يخالفونه؟ فالمسألة أنني أنا ما قرأت كثيراً من كتب الشيخ ربيع، هذا أمر، أمر آخرأيضاً كما قلنا: إن أهل السنة لا يقلِّد بعضهم بعضا، ولو انتقدوا عليه ورأوه خرج عن الصواب لأخرجوا المنشورات في رد ما يقول، وأخرجوا الكتب في دفع ما يقول. وعلى كُلٍّ: كلنا نصيب ونخطئ، ونجهل ونعلم. والله المستعان.
“የሱና ሰዎች የሚቀዱበት ምንጫቸው አንድ ነው። እሱም የአላህ ኪታብና የመልእክተኛው ﷺ ሱና ነው። በሁሉም ኢስላማዊ ሃገራት ዐቂዳቸውም አንድ፣ መንገዳቸውም አንድ ነው። አዎ እኛ የቢድዐ ሰዎችንና ቡድንተኞችን በመሀየስ ላይ እንስማማለን። በዚህ ላይ እንስማማለን። የሚቀረው፡ አንዱ ዘንድ የተተቹ ሌላኛው ዘንድ ግን ያልተተቹ የሆኑ ሰዎች ጉዳይ ነው። ይሄ በሰለፎችም ዘመን ተከስቷል። ምናልባትም አንዱን ዘጋቢ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ‘ታማኝ ነው’ ብሎት የሕያ ኢብኑ መዒን ግን ‘ውሸታም ነው’ ያለው ወይም በተቃራኒው የሆነ ስንት ዘጋቢ ያጋጥማል። ቡኻሪ፣ አቡ ዙርዐና አቡ ሓቲም ዘንድም ተመሳሳይ ነገር ያጋጥማል።
ቁም ነገሩ ከፊላቸው ከፊሉን በጭፍን አይከተሉም። በአንድ ሰው ታማኝነት ወይም ብልሹነት ላይ ብንለያይ ይሄ ማለት ዐቂዳ ላይ ተለያይተናል ማለት አይደለም። በአካሄድ ላይ ተለያይተናል ማለት አይደለም።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
⚠️ አቋም የቀየረው ማነው?
~ ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ
~ ሸይኽ ሀሰን
~ ኡስታዝ ዩሱፍ
እና መሰሎቻቸው? ወይስ ....?
መልሱን ለግልፀኛ አድማጭ እተወዋለሁ።
ያኔ አምነንበታል ተስማምተናል ካሉ በኋላ ዛሬ በዚህ መልኩ በውሸት ማጭበርበር እና ፊትናን ማቀጣጠል ከዱዓት አይጠበቅም። የሙስሊም ባህሪም አይደለም።
ወንድሞች ወሏሂ ወቢላህ የእልህ ጉዞ አያዛልቅምና ከወዲሁ ቆም ብለን እናስብ።
መረጃ የፈለገ ድምፁን ያድምጥ!!
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
🔖 እነዚህ አኢማዎች ዓብዱል ሐሚድ ዘንድ ጃሂል ይሆኑ ወይስ ሙብተዲዕ!?
🔖 አባ ደፋር ዘንድ'ስ ኢኽዋኖች ይሆኑ ይሆን!?
https://t.me/Multeka_Selefiyin
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
የሱና አንበሳ ወይስ የፊትና ሸይኽ!?
~ የሱና ዑለማኦች የማያቁትን አዲስ ነገር አምጥቶ የፊትና ጠንሳሽና አራጋቢ የሆነ የሱና አንበሳ!
~ ሸፍጥና ከዳተኝነት የማይጎረብጠው፣ የሱና አንበሳ!?
~ ትላንት ቁጭ ብሎ ተወያይቶ የተስማማበትን ነጥብ ዛሬ ጥሶና ተገልብጦ በኔ ሳንባ ካልተነፈሳቹህ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል የሱና አንበሳ!
~ ቅጥረኛ፣ ቆሻሻ፣ ሸይጣን፣ ቡችላና መሰል በሆኑ ቀፋፊ ስድቦች ያለ ሐያእ የሚያቀረሽ የሱና አንበሳ!
~ ተግባሩ እና ንግግሩ እንደ ምስራቅ እና ምዕራብ የተራራቀበት የሚጮኸውን የማኖር የሱና አንበሳ!
~ መርቀን ሲልና የእርሱን የተሳከረ አካሄድ የሚቃወሙ ከመሰለው ታላላቅ የሱና ዑለማኦችና የዲኑ ባለውለታዎችንም ሳይቀር "ከመንሀጅ ውጭ ናቸው" ከማለት የማይሳቀቅ የሱና አንበሳ!?
~ "ኢብኑ መስዑድ ችግር የለበትም እያሉ ነው አይደል!? ኢልያስ ችግር የለበትም እያሉ ነው አይደል!? ፍፁም ናቸው ነው አይደለ!? ፍፁም ናቸው መቶ በመቶ እንከተል እያሉ ነው! ከአንደበታቸው የተወራ ነው።" በሚልና መሰል በሆኑ ግልፅ ቅጥፈትና ውሸቶች የታወቀ፣ የሱና አንበሳ!?
ለማንኛውም የለተሞው መንጋ غሉው እዚህ ደርሷል።
الله المستعان! وعليه التكلان!
بئس العصر كان هذا الرجل فيه أسد السنة!
بئست الجماعة كان هذا إمامها قائدها!
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
በኢኽዋነል ሙስሊሚን ዘንድ ለምን ይጠላላሉ???
ያለ ግንዛቤ መፈክሮችንና ቃላትን ለሚያስተጋቡ ሁሉ.. ያሻቸውን የፓለቲካና የቡድን ፍላጎት ለማራመድ ለሚፈልጉ ሰዎች ስማቸው ሲነሳ ለሚያንቀጠቅጣቸው ለሶስቱ ስሞች እውነተኛው "ማብራሪያ" እነሆ።👇👇
እነዚህን ስሞች ያወጡት "ስድብና ማጣጣያ" መስሏቸው ነበር ነገር ግን እነዚህ መሻይኾች (ዑለማዎች) በቢድዓና (በሃይማኖት አዲስ ፈጠራ) በአመፅ (ኹሩጅ) ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ የክብር ማዕረግ ሆነላቸው!
1️⃣ ወሃቢያ (ሼክ ሙሐመድ ቢን አብዱልወሃብ)
ሼይኹ ማን ናቸው?
ኢማም ሙሐመድ ቢን አብዱልወሃብ (አላህ ይዘንላቸውና) በ18ኛው ክፍለ ዘመን በዓረብ ባሕረ ሰላጤ የተውሂድን ጥሪ ያደሱ (ሙጀዲድ) ናቸው።
እውነተኛው አነሳስ፦ ጥሪው (ዳዕዋው) በነጅድ የበቀለው በወቅቱ ተስፋፍተው የነበሩትን ሽርኮች፣ የቁብር አምልኮዎችን፣ ቢድዓዎችንና አጉል እምነቶችን ለመዋጋት ሲሆን ጥሪውም ወደ ንፁህ እስልምና ልክ በነቢዩ ﷺ እና በሶሃቦቻቸው ዘመን እንደነበረው ለመመለስ ነበር።
ባላንጣዎቻቸው ለምን ይጠሏቸዋል? ምክንያቱም የሳቸው ጥሪ የማጭበርበርን፣ በሃይማኖት የመነገድን፣ የሱፊያና የፖለቲካ ቢድዓዎችን ዙፋን ስላፈራረሰ ነው። ባላንጣዎቻቸው በእውቀት መመከት ሲያቅታቸው ተራውን ህዝብ አዲስ ሃይማኖት እንደሆነ አድርገው ለማሳሳት "ወሃቢያ" የሚለውን ቃል ፈጠሩ እውነታው ግን እሱው ንፁሁ እስልምና ነው።
2️⃣ ጃሚያ (ሼክ ሙሐመድ አማን አል-ጃሚ)፦
ሼኩ ማን ናቸው?
ታላቁ ሊቅ ሼክ ሙሐመድ አማን አል-ጃሚ (አላህ ይዘንላቸውና) በመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ የዓቂዳ (የእምነት) ክፍል ዲን ነበሩ።
እውነተኛው አነሳስ፦ ይህ ስያሜ ጎልቶ የወጣው በ90ዎቹ (በገረፍ ጦርነት ወቅት) ነው። ሼይኹ ከታላላቅ ዑለማዎች ጋር በመሆን ህዝቡን ለማነሳሳት፣ ስሜትን ተጠቅመው በገዢዎች ላይ ለማምፅና ሁከትን ለመፍጠር ይሞክሩ የነበሩትን ቡድኖችን (እንደ ኢኽዋንና ሱሩሪያ ያሉትን የፖለቲካ ቡድኖች) በፅኑ በተቃወሙበት ወቅት ነው።
ባላንጣዎቻቸው ለምን ይጠሏቸዋል? ምክንያቱም ሼክ ጃሚ በየመጅሊሱና በየደርሱየ ኹዋሪጅአል-ቀዕዲያህ (በንግግር አመፅን የሚያነሳሱ) እና የፖለቲከኞችን ሴራ ስላጋለጡና የሃሳብ ዝቅጠታቸውን ስላሳዩ ነው። ባላንጣዎቻቸው በዕውቀት ምላሽ መስጠት ስላቃታቸው እሳቸውን ለማጠልሸትና በመልካም ነገር ላይ መሪዎችን የመታዘዝንና ጀመዓን የመከተልን አካሄድ ሰዎችን ለማስጠላት "ጃሚያ" የሚል ቃል ፈጠሩ።
3️⃣ መድኸሊያ (ሼክ ረቢዕ ቢን ሃዲ አል-መድኸሊ)፦
ሼኩ ማን ናቸው?
ታላቁ ሊቅ ሼክ ረቢዕ ቢን ሃዲ አል-መድኸሊ ሲሆኑ፣ ሼክ አል-አልባኒ (አላህ ይዘንላቸውና) "በዚህ ዘመን የጀርሕ ወተዕዲል (የሰዎችና የቡድኖች ሂስ) ባንዲራ ተሸካሚ" ብለው የገለጿቸው ናቸው።
እውነተኛው አነሳስ፦ በሃይማኖት ሽፋን የሚደረገውን የፓለቲካ መገለባበጥና የቡድንተኝነት አካሄድን በዕውቀት የመመከት ቀጣይነት ሲሆን በተለይም እንደ ሰይድ ቁጥብና መሰል አንቀሳቃሽ መሪዎች መጽሐፍት ውስጥ ያሉትን የዓቂዳና የመንሃጅ (የአካሄድ) ስህተቶች ማጋለጥ ነው።
ባላንጣዎቻቸው ለምን ይጠሏቸዋል? ምክንያቱም የሼይኽ ረቢዕ ትችት ለቡድኖች መገለባበጥና መዘበራረቅ ምሕረት የሌለው ስለነበር በሙናፊቅነት የሰለፊያ ልብስ የለበሰውን የ"አብዮታዊ አስተሳሰብ" ምሽግ ስላፈራረሰ ነው። በመሆኑም የሰለፎችን (የቀደምቶቹን) ጥብቅ አካሄድ የያዘውንና አብዮቶችንና መፈንቅለ መንግስታትን የማይቀበለውን ሁሉ ለመወረፍ "መድኸሊያ" የሚለውን ቃል ፈጠሩ።
ይህ ሶስቱ ስያሜዎች (ወሃቢያ፣ ጃሚያ፣ መድኸሊያ) ራሳቸውን የቻሉ አዳዲስ ቡድኖችም ሆኑ የተፈጠሩ መዝሃቦች አይደሉም።
ይልቁንም በቢድዓ፣ በአመፅ (ኹሩጅ) እና አጥፊ በሆኑ የፓለቲካ ቡድኖች ፊት እንደ ጅራፍ ሆነው የቆሙ የሱና ዑለማዎች ስሞች ናቸው።
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abulabas1444
t.me/Abulabas1444
ተውሂድ፣ ከዚያም ተውሂድ!
የሚገርመው ነገር፣ አንዳንዶች ስለ ሸሪዓ ጥቃቅን ሕጋጋትና ዝርዝር ጉዳዮች ይጠይቃሉ የተጠሉ ነገሮችን (መክሩሃትን) ሲጠነቀቁ አልፎ ተርፎም ከአንዳንድ የተፈቀዱ (ሙባህ) ነገሮች እንኳ ሲታቀቡ ታያቸዋለህ።
ነገር ግን የዲኑ መሠረት (አስል አድ-ዲን) ላይ ሲደርስ፣ አንዳንዶቹ የተፈጠሩለትን የተውሂድ ምስክርነት (ሸሃዳ) ትርጉም እንኳ አያውቁም። ስለ መስፈርቶቹ (ሹሩጥ) ወይም ስለሚያፈርሱት ነገሮች (ነዋቂድ) ምንም የሚያውቁት ነገር የለም።
በዚህም ምክንያት በትልቁ ሽርክ (አሽ-ሽርክ አል-አክበር) ላይ ወድቀው ታገኛቸዋለህ፤ ወይም የአላህን ስሞችና ባህሪያት የሚያጣምሙ የጀህምያህ እምነት ተከታዮች ናቸው ወይም ደግሞ አላህ በፈጠረው ፍጡር ውስጥ ይሟሟል ወይም ይዋሃዳል (አህሉል ሑሉል ወል-ኢቲሓድ) በሚሉ የጥመት እምነቶች ያምናሉ።
አንዳንዶቹ በኢማን ጉዳይ ወይ ኻዋሪጆች ወይም ሙርጂአዎች ናቸው (ቀድር) ጉዳይም ወይ የፍፁም ነጻ ፈቃድ (ቀደርያህ) ወይም የጅብሪያህ (አስገዳጅነት) አራማጆች ናቸው።
ይህ ሁሉ የሆነው በጃሂልነት (ባለማወቅ) እና ለተውሂድ እምነት (ዓቂዳህ) ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠት ነው!
የአላህ ባሮች ሆይ! በዱንያም በአኺራም ሰላም እንድታገኙና እንድትደሰቱ፡ ተውሂድ፣ ከዚያም ተውሂድ፣ ከዚያም ተውሂድ!
ሸይኽ ዐብዱሰላም አስ-ሱሐይሚ
ያልበሰለ ደዕዋ
👉በጉራጌው አብሬት ደግሞ በሸከና፤
👉መርሳ አባጌትዬ እንዲሁም በዳና፤
👉በትግራይ ነጃሺ በወሎ ቦረና፤
👉የሸሆቹ ቀብር ሲመለክ በጠና፤
👉ዝም አለ አንደበትህ ህዝብህ እያለቀ፤
👉ተውሒዱን ከሽርኩ እየደባለቀ፤
👉አኽላቅ ትሰብካለህ ጧት ማታ ሰደቃ፤
👉ያላወቀው ወገን በሽርክ እያበቃ፤
👉በመከራው ዘመን ሰው ለዛፍ ተስሎ፤
👉ቃል ለሱ እየገባ ብጣሽ አንጠልጥሎ፤
👉የሞተን ሲማጸን ፈጽምልኝ ብሎ፤
👉ዝም ሲል ገረመኝ አንደበትህ ችሎ፤
👉ተው እንደሱ አይደለም የረሱሎች ጥሪ፤
👉ተውሒድን መስበክ ነው የደዕዋው ጅማሪ፤
👉ግባና ተከተል በረሱሎች ሱና፤
👉ባልበሰለው ደዕዋ ውጤት የለምና፤
✍️ ኡስታዝ አቡ ዒምራን ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ሐፊዘሁላህ
Repost from ስለ ቀልባችን
ለተማሪዎች የተለገሰ ድንቅ ምክር!
በፈገግታ የታጀበው፣ ማራኪው የሸይኽ አል-ባሲጢይ ምክር-አላህ ይዘንላቸው-
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ፍቅር
-----
الأصيل حتى في عداوته شريف
وقليل الأصل حتى قي صداقته خبيث.!
ብዙዎች አፍቃሪ ነን ይላሉ እንጂ ፍቅርን አያውቁትም።
ወደናል ይላሉ እንጂ መውደድን አይኖሩትም።
አወ ብዙ ሰዎች ፍቅርን በሒሳብ ይለካሉ።
በፍቅር ስም ገንዘብ ያመልካሉ።
...ምን ሰጠኸኝ⁉️
ምን አደረክልኝ⁉️
ምን ዋጋ አለህ⁉️...ይሉሀል።
...ይህንን አይተሀል....!?
...ግና እውነተኛ ፍቅር በመለየት አይቋጭም፡፡
ከእውነተኛ ፍቅር ውስጥ ጥላቻ መቼም አይመነጭም።
እውነተኛ መውደድ በግጭት አይቆጭም።
የሀቂቃ ሙሀባ በክስተቶች አይጋጭም።
...ምክንያቱም...
The meaning of love is not limited to the relationship between two individuals of opposite sexes.
የፍቅር ትርጉም በሁለት ተቃራኒ ፆታ ባላቸው ግለሰቦች መካከል ባለው ግንኙነት ብቻ የተወሰነ አይደለም።
እውነተኛ ፍቅር
ከሒሳብ በላይ ፣
ከምክንያት በላይ ፣
ከመለኪያ በላይ ነው።
✅እሱ ልክ ነውና መለኪያ የለውም።
ፍቅር ፓወር ነው It has interchangeable lenses አለውና በአፍቃሪ አይን ላይ የተፈቃሪን ስህተትና ጥፋት በመልካም ቀይሮ የሚያሳይ መነፀር አለው።
ለዛም... እውነተኛ ወዳጆች በፈተናዎች አይናወጡም፣ በችግር አይተጣጡም፣ በማገኘት አይላላጡም የሆነ ክስተት ሲያንዣብብ ወደ ወዳጃቸው የበለጠ ይጠጋሉ፣ እጂግ በጣም ይረጋጋሉ፣ይታገሳሉ በሚከፍሉት ዋጋ ደስተኛ የጉዟቸው ነገን የሚመለከቱ ተስፈኛ ናቸው።
✅ምክንያቱም ለመለያየት አልተገናኙም።
አወ ፍቅር ሰበብ አይጠይቅም።
መውደድ ጥላቻን አያውቅም፡
ሙሀባ ፀብን አያፀድቅም፡፡
ፍቅር ማብራሪያ አይፈልግም፡፡
ሁብ ክፉ አያደርግም፡፡
መውደድ በጀርባ አያመልጥም፡፡
ፍቅር ደረጃ አይሰጥም።
«እውነተኛ ፍቅርን አብራራዋለሁ ባልክ ቁጥር ክብሩን እየቀነስከው ትሔዳለህ ፍቅር ትርጉመ ጥልቅና ሚስጥረ ረቂቅ ነው የንግስና ቦታው ምላስ ሳይሆን ልብ ላይ ነውና አይረሳም።
👉አሏህ እውነተኛ አድርጎ እውነተኛ ፍቅር ይወፍቀን አሚን ሰላም ዋሉልኝ።
....ኑር.....✍️
t.me/nuredinal_arebi
Repost from موقع فضيلة الشيخ رسلان
--🎤من روائع التراث 🎤--
(كل بدعة ضلالة)
🌷فضيلة الشيخ الدكتور🌷
💐محمد بن سعيد رسلان (حفظه الله) 💐
ـــــ ـــــ ـــــ ـــــ ـــــ ـــــ ـــــ ـــــ
💢احرص على الاشتراك وتفعيل الإشعارات لكي يصلك كل جديد أولا بأول
💢 الموقع الرسمي على الشبكة
╭─═┅┅┅┅┅┅┅═────╮
https://www.rslan.com
╰─═┅┅┅┅┅┅┅═────╯
💢 الموقع الرسمي على اليوتيوب
╭─═┅┅┅┅┅┅┅═────╮
https://www.youtube.com/user/RslanCom
╰─═┅┅┅┅┅┅┅═────╯
💢 الصفحة الرسمية على الفيس بوك
╭─═┅┅┅┅┅┅┅═────╮
https://www.facebook.com/Rslan.Com.Official
╰─═┅┅┅┅┅┅┅═────╯
💢 القناة الرسمية على التليجرام
╭─═┅┅┅┅┅┅┅═────╮
https://t.me/rslancom
╰─═┅┅┅┅┅┅┅═────╯
💢 القناة الرسمية السوند كلاود
╭─═┅┅┅┅┅┅┅═────╮
https://on.soundcloud.com/dw4Hz
╰─═┅┅┅┅┅┅┅═────╯
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
“የልብ ውበት በኢማን ይታያል”
የሰው እውነተኛ ዋጋ በመልኩ አይመዘንም፣ በሀብቱ አይለካም፣ በሰው ዘንድ ባለው ዝናም አይቆምም። እውነተኛ ዋጋው የሚገኘው በልቡ ውስጥ ባለው ኢማን እና ተቅዋ ነው። ልብ ከአላህ ጋር ሲገናኝ ይበራል፣ ሲነጻ ይረጋል፣ ሲጨልም ግን ሕይወት ሁሉ ይጨልማል። የልብ ብርሃን ከጠፋ ሰው ቢኖር እንኳ ውስጡ ባዶ ይሆናል፤ ዓለም ቢያገኝ እንኳ ሰላም አይገኝም።
አላህ ይህን እውነት በጣም ገሳጭ ቃል እንዲህ ብሎ ተናግሯል፦
﴿أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ﴾
“እነዚያ ያመኑት ልቦቻቸው ለአላህ መዘከር እንዲለሙ ጊዜው አልመጣምን?” (الحديد: 16)
ይህ አንቀፅ ልብን ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ ድምፅ ነው። ልብ ተኝቶ ከቆየ ሰው ሕይወቱ ተኝቶ ይቆያል፤ ልብ ከነቃ ግን ነፍስ ትነቃለች፣ ባህሪ ይለወጣል፣ መንገድ ይበራል።
ነብዩ ﷺ ይህን መርህ በግልጽ ቃል አሳይተዋል፦
“إِنَّ اللَّهَ لَا يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ”
“አላህ ወደ መልካችሁና ወደ ገንዘባችሁ አይመለከትም፤ ነገር ግንወደ ቀልቦቻችሁ እናወደስራችዎችሁ ይመለከታል። ” (ሙስሊም)
ይህ ሐዲስ ልብ የክብር መድረክ መሆኑን ይገልጣል። ሰው ቢነጋገር እንጂ ልቡ ከጨለማ ከሆነ እውነተኛ ዋጋ የለውም፤ ግን ልቡ ከበራ ቢያንስ ቢሆን እንኳ አላህ ዘንድ ታላቅ ነው።
ኢማን ልብን ሲገባ ሰውን እንደ አዲስ ይፈጥራል። ውስጣዊ ጨለማን ያጠፋል፣ ተስፋ ይዘራል፣ ሰላም ያስገባል። አላህም እንዲህ ይላል፦
﴿أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ﴾
“በእርግጥ በአላህ መዘከር ልቦች ይረጋጋሉ” (الرعد: 28)
እና እውነት ነው—ልብ ካልረጋ ሰው አይረጋም፣ ልብ ካልበራ ሕይወት አይበራም።
ስለዚህ የልብ ውበት ማለት በዚክር የበራ፣ በተቅዋ የተጠናከረ፣ ከሺርክ የተጠራ ልብ ነው። እንዲህ ልብ ባለቤቱን ወደ አላህ ያቀርባል፣ ወደ ሰላም ይመራል፣ በምድር ላይ ሳለ የጀነት ብርሃን ያሳየዋል።
እውነተኛ ውበት በመልክ አይታይም፤ በልብ ውስጥ ነው። ሰው በሰው ካልታየ እንኳ አላህ ዘንድ ከተቀበለ ያ ብቻ እውነተኛ ስኬት ነው።
https://t.me/A2mnt
