የቀጠናው ተመልካች
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 327
المشتركون
+2824 ساعات
+307 أيام
-4230 أيام
أرشيف المشاركات
4 328
🇮🇷⚡️🇮🇱 ኢራን ዛሬ በቁጥጥር ሥራ ያዋለቻቸውን፣ የእስራኤል እና የጠላት ጎረቤት አገር ናቸው ያለቻቸውን፣ መርከቦች እንዴት እንደያዘቻቸው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቃለች።
4 328
- ❗️🇮🇷❌🇬🇷 አስቸኳይ፡ የግሪክ FM ዛሬ በሆርሙዝ ወሽመጥ ሲያልፍ በኢራን አብዮታዊ ጠባቂ (IRGC) ጥቃት የደረሰበት መርከብ ባልቤትነቱ የግሪክ እንደሆነ አረጋግጧል። ሁሉም መርከበኞች በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ያለ ሲሆን፣ የኢራን ባለስልጣናት መርከቡን እንዲለቁ ተማጽኖአል።
4 328
+2
🇦🇪🇸🇾⚡️ - የሶሪያው ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ፣ ዛሬ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ ጋር በአቡ ዳቢ ተገናኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች (ኢራን) ላይ ተወያይተዋል።
4 328
ሱማሊያ ለእስራኤል ከልክያለሁ የምትለው የባሕር መስመር፣ ሱማሌላንድ በምትቆጣጠረው ግዛት ያለውን የውሃ ክፍል ነው። ሱማሌላንድ ደግሞ ከእስራኤል ጋር ሸሪኮች ናቸው። ያው፣ 'ለማለት ያህል' እንጂ ሱማሊያ በዚያ በኩል የምትቆጣጠረው ውሃ እንደሌለ ልብ ሊባል ይገባል።
4 328
❗️🇮🇱/🇸🇴 ሰበር፡ ሶማሊያ በቀይ ባሕር ላይ፣ በባብ አል-ማንዳብ ወሽመጥ፣ በሚያልፉ የእስራኤል መርከቦች ሁሉ ላይ እገዳ ማድረጓን አስታውቃለች።
4 328
🇮🇷🇺🇸⚡️ ትራምፕ፣ ኢራን በስቅላት ሞት ልትሰቅላቸው የነበሩትን 8 ሴቶች ይቅር ብላቸዋለች- በምትኩ- በአንድ ወር እሥራት ቀይራላቸዋለች፣ ሲል ተናገረ።
"ኢራን ጥያቄዬን ስላከበረችልኝ በጣም አድርጌ ላመሰግናት እወዳለሁ።"
4 328
ፔንታገን ለኮንግረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ ፈንጂዎችን ለማጽዳት በትንሹ 6 ወራት ሊወስድ እንደሚችል ተናግሯል - WaPo
"አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገው ጦርነት እስኪያበቃ ድረስ፣ እንዲህ ዓይነቱ ዘመቻ ሊከናወን አይችልም።"
ቪዲዮው የ CENTCOM ሲሆን፣ መትረየስ የደገነ የሄሊኮፕተር ወታደር በባሕር ወሽመጡ የሚያልፈውን መርከቡ እንዲመለስ ሲነግረው ያሳያል።
4 328
+1
🇮🇷❗️ የዛሬ የ Sentinel-2 የሳተላይት ምስሎች፡ በአካባቢው ጥበቃ ካደረጉ በኋላ ከሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በስተሰሜን ወደሚገኝ ሰፈራቸው እየተመለሱ ያሉ የ IRGC ን የባሕር ላይ ፈጣን አጥቂ መንጋ ጀልባዎችን ያሳያል። እነዚህ ጀልባዎች፣ ዛሬ በኢራን ቁጥጥር ሥር ወደቁ ተብሎ ከተዘገቡት ኮንቴይነር ጫኝ መርከቦች ጋር የተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ።
4 328
— 🇺🇸⚡️🇮🇷 Financial Times: በደርዘን የሚቆጠሩ የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች፣ እገዳው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፍ ችለዋል - ምንም እንኳን ትራምፕ እገዳውን 'ትልቅ ስኬት' ብሎ ቢገልጸውም።
4 328
- 🇺🇸 /🇮🇷/ 🇵🇰 ኢራን በድርድር ላይ ካልተሳተፈች የተኩስ አቁም ስምምነቱን በማራዘም ላይ ዋስትና እንደማትሰጣት ፓኪስታን አስጠንቅቃታለች። ኢራን የአሜሪካ የባሕር ሃይል እገዳ ሙሉ በሙሉ ከመነሳቱ በፊት፣ በማንኛውም አዲስ ዙር ውይይት እንደማትገኝ መልሳላታለች። ይህም፣ የፓኪስታን ሸምጋዮችን በንዴት 'እንዲናደዱ' እና 'እንዲግሉ' አድርጓቸዋል ተብሏል። - አል አረቢያ
4 328
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 አዲስ፡ ትራምፕ ለኢራን የተኩስ አቁም ከማብቃቱ በፊት 'ጠባብ መውጫ ጊዜ' ብቻ ሰጥቷል - Axios
"ትራምፕ ኢራናውያን 'ቆሻሻቸው' በአንድ አድርገው እንዲሰበስቡ ለማስቻል፣ ሌላ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት የተኩስ አቁም ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው" ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናግረዋል። "በሩ እንደተከፈተ አይቆይም"።
4 328
🇮🇱🤝🇱🇧❌🇮🇷🇱🇧 - የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር Gideon Saar አገር የሊባኖስ መንግሥት በኢራን ወረራ ላይ ከእስራኤል ጋር ሽርክና እንዲፈጥር ጥሪ አቅርቧል
- እንደ አለመታደል ሆኖ ሊባኖስ ያልተሳካለት ሀገር (Failed State) ናት፣ በሂዝቦላህ በኩል በኢራን ቁጥጥር ሥር ያለችም ሀገር ናት። ይህ ጉዳይ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ መደምደሚያው ሊያመራ ይገባል። ሂዝቦላህ የእስራኤል እና የሊባኖስ የጋራ ጠላት ነው። የእስራኤልን ደህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል ሁሉ የሊባኖስን ሉዓላዊነት የሚጎዳ እና የወደፊት ዕጣ ፋንታዋን የሚያበላሽ ነው። ከሊባኖስ ጋር ምንም አይነት አለመግባባት የለንም። ሊፈቱ የሚችሉ ጥቂት ጥቃቅን የድንበር አለመግባባቶች አሉ። በአገሮቻችን መካከል ለሰላምና ለጥሩ ጉርብትና እንቅፋት የሆነው አንድ ቡድን ነው፣ ሂዝቦላህ!
4 328
🇺🇸🇮🇷⚡Senator Chris Murphy,
የባሕር ኃይላችንን በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ለማቆየት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣን ነው። የትራምፕ ትርጉም የለሽ የምርጫ ጦርነት እስኪዘጋው ድረስ ያልተዘጋውን የውሃ መንገድም መክፈት አቅቶን፣ እየተንደፋደፍን ነው።
4 328
- 🇺🇸 / 🇮🇷 የኢራን አንዳንድ ምንጮች፡ አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ዘመቻ ከመክፈቷ በፊት፣ USS George H.W Bush አይሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ አረብ ባሕር እስኪደርስ ድረስ እየጠበቀች ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ይህ መርከብ በአሁኑ ጊዜ በታንዛኒያ ወይም በኬንያ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን፣ ከ3-5 ቀናት ውስጥ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚደርስ ይሆናል። በዚያም፣ USS Abrham Lincoln እና USS Gerald Ford ን በመቀላቀል፣ ወደ ጦርነት የሚገባው ሦስተኛው መርከብ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
4 328
🇬🇧 የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር፡ "ከ30 አገራት የተውጣጡ ወታደራዊ ስትራቴጂስቶች፣ ረቡዕ፣ በለንደን የሆርሙዝን የባሕር ወሽመጥ ለመርከብ ትራፊክ በማስከፈት ዙሪያ ይሰባሰባሉ።
4 328
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ተደርሶበት የነበረው የ 2 ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት፣ አሁን አበቃ።
ኢራን፣ ፕሬዚዳንት Trump በተናጠል ስምምነቱን ለማራዘም ስለወሰደው እርምጃ ይፋዊ ምላሽ እስካሁን አልሰጠችም።
4 328
🇮🇷❌🇺🇸 - በርካታ የኢራን ሚዲያ ጣቢያዎች፣ ኢራን የተኩስ አቁም ማራዘሚያውን ላታከብር እንደምትችል እየዘገቡ ነው። ምክንያቱም፣ "አሜሪካ እና እስራኤል ለድንገተኛ ጥቃት ጊዜ ለመግዛት የሚያደርጉት ሙከራ ነው" ብለው ያምናሉ።
4 328
🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን መንግሥት ዜና ወኪል TASNIM፡ "ትራምፕ ያራዘመው የተኩስ አቁም፣ ኦፊሴላዊ መግለጫ እስካልሰጠንበት ድረስ፣ እኛን አይመለተንም።
