ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 298
المشتركون
+124 ساعات
-157 أيام
-8430 أيام
أرشيف المشاركات
+2
🇺🇸 'ዶናልድ ትራምፕ ኔታንያሁን አምባረቀበት …ተቆጣው …ዘለፈው' የምትለውን የ Axiosን ዜና ሳነባት የተሰማኝን ስሜት እነዚህ በደንብ ገልፀውታል። እስራኤል እና ኔታንያሁ በአሜሪካ እና በትራምፕ ላይ፣ በተለይ በውጭ ፖሊሲያቸው፣ አዛዦች ናቸው። አሜሪካም ትራምፕም ለአይሁዳዊያን ታዛዦች ናቸው። ይህን ሁሉም ያውቃል። ትራምፕ በሀገር ቤት በዚህ ሲከሰስ እና ሲወነጀል ሰንብቷል። ዛሬ ተነስቶ በአክሲዮስ በኩል አዛዡ እሱ እና አሜሪካ እንደሆኑ ለማሳመን ጥሯል። ፉገራዊ እና ማስመሳያ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ናት!

🇺🇦🇷🇺 የሩሲያን ጥቃት በመሸሽ የኪይቭ ነዋሪዎች  አዳራቸውን በምድር ሥር በሚገኙ ባቡር ጣቢያዎች ተጠልለው አሳልፈዋል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 የሩሲያን የማጥቃት ዘመቻ ተከትሎ፣ በዚህ ሰዓት በኪየቭ ያልተቋረጡ ፍንዳታዎች እየተሰሙ ናቸው።

— 🇺🇸/🇮🇷/🇮🇱 ኢራን ከድርድሩ ለመውጣት ካስፈራራች በኋላ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በፍጥነት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን በቤሩት ላይ የታቀደውን ጥቃት እንዲያራዝም እየጮኸ ነግሮታል
— 🇺🇸/🇮🇷/🇮🇱 ኢራን ከድርድሩ ለመውጣት ካስፈራራች በኋላ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በፍጥነት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን በቤሩት ላይ የታቀደውን ጥቃት እንዲያራዝም እየጮኸ ነግሮታል፣ በአክስዮስ ዘገባ መሠረት በጥሪው ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኔታንያሁ ላይ በግልጽ ተቆጥቶ እንዲህ ብሏል፦
አንተ እብድ ነህ። እኔ ባልሆን ኖሮ እስር ቤት ውስጥ ትሆን ነበር። ሰምተሃል! እየታደግኩህ ነው። አሁን ሁሉም ሰው ጠልቶሃል። በዚህ ምክንያትም ሁሉም ሰው እስራኤልን ጠልቷል። ምን እየሰራህ ነው?'
አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ትራምፕ ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ያለውን ዲፕሎማሲ ለማበላሸት እየሞከረ እንደሆነ ስለተረዳው፣ በሁለቱ መሪዎች መካከል ከመቼውም ጊዜ የከፋው ጥሪ እንደነበረ ተናግሯል። 

🇺🇸🇮🇷🇮🇱🇱🇧 ትራምፕ ለ ABC፦ ዛሬ ትንሽ ችግር ነበር — ኢራናውያን እስራኤል በሊባኖስ ላይ ባደረገችው ጥቃት ተበሳጭተው ነበር። ስለዚህ ሂዝቦላ ጋር ደወልኩኝ፣ እንዳይተኩሱ ነገርኳቸው
🇺🇸🇮🇷🇮🇱🇱🇧 ትራምፕ ለ ABC፦ ዛሬ ትንሽ ችግር ነበር — ኢራናውያን እስራኤል በሊባኖስ ላይ ባደረገችው ጥቃት ተበሳጭተው ነበር። ስለዚህ ሂዝቦላ ጋር ደወልኩኝ፣ እንዳይተኩሱ ነገርኳቸው፣ ቢቢ ጋርም ደወልኩኝ፣ ተነጋግሬ እንዳይተኩሱ ነገርኩት፣ እና ሁለቱም አንዱ አንዱ ላይ መተኮስ አቁመዋል።

—❗️🇮🇷/🇱🇧/🇮🇱 አዲስ፦ የኢራን የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሞሃመድ ባቂር ቃሊባፍ፣ ኢራን የውይይት ሂደቱን ማቆም ብቻ ሳይሆን በሊባኖስ ውስጥ የሚደረጉትን ጥቃቶች ካላቆመች እስራኤልን በቀጥታ ት
—❗️🇮🇷/🇱🇧/🇮🇱 አዲስ፦ የኢራን የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሞሃመድ ባቂር ቃሊባፍ፣ ኢራን የውይይት ሂደቱን ማቆም ብቻ ሳይሆን በሊባኖስ ውስጥ የሚደረጉትን ጥቃቶች ካላቆመች እስራኤልን በቀጥታ ትገጥማለች ብለዋል

🇺🇦⚡️🇷🇺 በአሁኑ ሰዓት ወደ 40 የሚጠጉ የሩሲያ ድሮኖች በዩክሬን ሰማይ ላይ እየበረሩ ናቸው።
🇺🇦⚡️🇷🇺 በአሁኑ ሰዓት ወደ 40 የሚጠጉ የሩሲያ ድሮኖች በዩክሬን ሰማይ ላይ እየበረሩ ናቸው።

🇷🇺❌🇺🇦— እስከ 16 የሚደርሱ የካሊብር ክሩዝ ሚሳይሎች ከካስፒያን ባሕር ወደ ዩክሬን ተተኩሰዋል። ➡️ ሚሳይሎቹ በሚቀጥሉት 40-60 ደቂቃዎች ውስጥ ወደ ዩክሬን አየር ክልል ይገባሉ። ይህ የሩሲያ ጥቃቱ ሲጠበቅ የከረመው ነው፣ ተብሎ ይጠበቃል።

🇮🇱⚡️🇺🇸 የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ግቪር፦ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ጠንካራ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት በሚቻልበት ጊዜ 'እሺ' እና አስፈላጊ ሲሆ
🇮🇱⚡️🇺🇸 የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ግቪር፦ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ጠንካራ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት በሚቻልበት ጊዜ 'እሺ' እና አስፈላጊ ሲሆን 'እምቢ' ይላል ብለው ተናግረዋል። ለአጎታችን፣ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ—'እምቢ' ለማለት ጊዜው አሁን ነው። ሂዝቦላን ለመምታት፣ የተዋጊዎቻችንን የእጅ መቅሰፍት ሊዘረጉባቸው ይገባል። በሰሜን ደህንነትን ለመመለስ የሚያስፈልገውን እና አስፈላጊውን ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው።

🇺🇸🇮🇷 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ከዋሽንግተን ጋር የምታደርገውን ውይይት ልታቋርጥ እንደምትችል የሚገልጹ ዘገባዎች እውነት እንደሆኑ ሲጠየቅ፡ “ችግር የለውም” ብሎ ለ NBC News
🇺🇸🇮🇷 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ከዋሽንግተን ጋር የምታደርገውን ውይይት ልታቋርጥ እንደምትችል የሚገልጹ ዘገባዎች እውነት እንደሆኑ ሲጠየቅ፡ “ችግር የለውም” ብሎ ለ NBC News ተናግሯል፦ “እንዲያውም ንግግሩን በጣም ያበዛነው ይመስለኛል።” “ይህ ማለት እኛ ሄደን ቦምብ መወርወር እንጀምራለን ማለት አይደለም። ዝም ብለን እንቀመጣለን። እገታውን እንቀጥላለን።”

🇺🇸 የኢራን ማስፈራሪያዎች ሠርተዋል። ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስለሰጡ እናመሰግናለን!
🇺🇸 የኢራን ማስፈራሪያዎች ሠርተዋል። ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስለሰጡ እናመሰግናለን!

🇺🇸 ሰበር ዜና! ትራምፕ በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እንዳደረገ ተናገረ።
🇺🇸 ሰበር ዜና! ትራምፕ በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እንዳደረገ ተናገረ።

—❗️🇮🇱/🇱🇧/🇺🇸/🇮🇷 የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን (Kann)፦ 'ከፕሬዝዳንት ትራምፕ አስቸኳይ የስልክ ጥሪ በመነሳት፣ ኔታንያሁ በዳሂዬ እና ቤሩት ላይ ሊያደርግ የነበረውን ትልቅ ጥቃት ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል።'

— 🇮🇱/🇱🇧/🇮🇷 አዲስ፦ የኢራን ማስፈራሪያዎችን ተከትሎ፣ እስራኤል ቤሩትን ለመምታት ያላትን እቅድ 'እንደገና እያሰበችበት' ነው – ዕብራይስጥ ሚዲያዎች

—❗️🇮🇷 የኢራን ካታም አል-አንቢያ (ማዕከላዊ ማዘዣ ጣቢያ) እስራኤላዊያን ሰሜን እስራኤልን ለደህነታቸው ሲሉ እንዲለቁ አስጠነቀቀ። 'ኔታንያሁ፣ በቀጠናው የጥቃት ድርጊቶቹን በመቀጠል፣ ዳሂየህን
—❗️🇮🇷 የኢራን ካታም አል-አንቢያ (ማዕከላዊ ማዘዣ ጣቢያ) እስራኤላዊያን ሰሜን እስራኤልን ለደህነታቸው ሲሉ እንዲለቁ አስጠነቀቀ።
'ኔታንያሁ፣ በቀጠናው የጥቃት ድርጊቶቹን በመቀጠል፣ ዳሂየህን እና ቤሩትን በቦምብ ለመደብደብ ማስፈራሪያ አውርዷል እና ለነዋሪዎቻቸው የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። እስራኤል በተደጋጋሚ በጋዛ የተደረሰውን ተኩስ አቁም በመጣስ ሕዝብ ስትጨፈጭፍ ከርማለች። አገዛዝ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በተደጋጋሚ በመጣሱ ምክንያት እና አሁን ሊባኖስን እያስፈራራበት ያለውን ከፈጸመ፣ የኢራን ጦር ሠራዊት በተያዙት ግዛቶች ውስጥ የሚገኙትን የሰሜን አካባቢዎች እና የወታደራዊ ሰፈሮችን ስለሚያጠቃ ነዋሪዎችን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለቅቀው እንዲወጡ ያስጠነቅቃል'


— 🇺🇸/🇮🇷/🇱🇧/🇵🇸 ከፋርስ ኒውስ ጋር የተነጋገረ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን፦ 'የፍልስጤማዊ ደም ከኢራናዊ ደም ጋር እኩል ነው። የሊባኖሳዊ ደም ከኢራናዊ ደም ጋር እኩል ነው። የሙስሊሙ ማህበረሰብ በዚህ ውጊያ ጎን ለጎን የሚቆም አንድ የጋራ ግምድ ነው።' *-- እንዲህ ያሉ ንግግሮች በሳዑዲ እና በጥቂት ገልፍ አረቦች አይወደድም፣ የሙስሊሙ ጠበቃ እኛ ነን ብለው ስለሚያስቡ። ኢራን፣ ሳዑዲና ገልፍ አረቦች በሕዝበ ሙስሊም ላይ አለን የሚሉትን ይህን የጥብቅና ደረጃ የቀማቻቸው፣ እንደ ፈረንጆች 1978 ነበር፣ የኢራን አብዖት የፈነዳ ጊዜ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የኢራን መንግሥት የሙስሊሙ ዓለም ድምፅ በመሆን ኃላፊነቱን እንደተረከበ ያምናል። በእምነታቸውም ቢሆን፣ በታሪክ አብዛኛው የእስልምና ሊቅ የፈለቀው ከፋርስ (የዛሬዋ ኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ኡዝቤኪስታን እና መካከለኛው እስያ ወይም non-arabs) በመሆኑ እንዲህ ያለው የዛሬው የኢራን ንግግር በሳዑዲና በገልፍ አረቦች የበለጠ እንዲጠላ ይሆናል።

🇪🇹⚡️እንደ ምንጮቼ ዘገባ፣ በኢትዮጵያ ተደረገ የተባለው የዛሬ ምርጫ፣ በአብዛኛው ባዶ ነበር። አዲስ አበባን ጨምሮ፣ በሀገሩ በከተሞች ዋና ዋና መንገዶች እና ሰፈሮች፣ የፖሊስና የፀጥታ አስከባሪው
🇪🇹⚡️እንደ ምንጮቼ ዘገባ፣ በኢትዮጵያ ተደረገ የተባለው የዛሬ ምርጫ፣ በአብዛኛው ባዶ ነበር። አዲስ አበባን ጨምሮ፣ በሀገሩ በከተሞች ዋና ዋና መንገዶች እና ሰፈሮች፣ የፖሊስና የፀጥታ አስከባሪው ኃይል ቁጥር፣ ከወጣው መራጭ ሕዝብ ቁጥር በልጦ ታይቶ ነበር ብለውኛል። እነዚህ ምንጮቼ እንደነገሩኝ፣ Turn Outቱ በታሪኩ እጅግ ዝቅተኛው ነበር ብለውኛል። መንግሥት ምርጫውን ያራዘምኩበት ምክኒያት ሌላ ነው ቢልም፣ ይህ የሕዝብ ቤት መቀመጥ እና አለመውጣት፣ ምርጫው እንዲያራዝመው አስገድዶታል።

🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️ — ሰበር ዜና፦ በኢራን የዜና ኤጀንሲ Tasnim መረጃ መሠረት፣ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እና በሊባኖስ የምታካሂደውን ቀጣይ ወታደራዊ ተግባራት ምክንያት በማድረግ፣ ኢራን ከአሜሪ
🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️ — ሰበር ዜና፦ በኢራን የዜና ኤጀንሲ Tasnim መረጃ መሠረት፣ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እና በሊባኖስ የምታካሂደውን ቀጣይ ወታደራዊ ተግባራት ምክንያት በማድረግ፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ድርድር አግዳለች።
እስራኤል የምታካሂደውን ወታደራዊ ተግባር ካላቆመች እና ከተያዙ የሊባኖስ አካባቢዎች ወታደሮቿን ካላስወጣች፣ ድርድሩ አይቀጥልም። ኢራን እና አጋር ቡድኖች የሆርሙዝ ወሽመጥን እና በቀይ ባሕር የባብ አል-ማንደብን ጨምሮ፣ ቁልፍ የባሕር መተላለፊያ መንገዶችን ሊያደናቅፉ በመቻል ጫናውን ለመጨመር እያሰቡ ናቸው።

—❗️🇺🇸/🇮🇷 ሰበር ዜና፦ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ሁሉንም ድርድሮች አግዳለች – የኢራን መገናኛ ብዙሃን Tasnim

🇪🇹⚡️ወቅታዊ የሀገር አቋምን ይገልፃል ይሉታል አንዳንዶቹ።
+2
🇪🇹⚡️ወቅታዊ የሀገር አቋምን ይገልፃል ይሉታል አንዳንዶቹ።