ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም 2ተኛ ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
1 841
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+227 أيام
+12330 أيام
أرشيف المشاركات
በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ የሚሰጠው የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህ
+8
በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ የሚሰጠው የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ትምህርት ስኬታማ እንዲሆን በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ቢሮ በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ በ2019 የትምህርት ዘመን እየተሰጠ በሚገኘው የመማር ማስተማር ስራ ላይ ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲና ከኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ አመራሮችና ወላጆች ጋር ውይይት አድርጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ በሳይንስ ዘርፍ ፍላጎት ያላቸዉ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስታውሰው በትምህርት ቤቱ በ2019 የትምህርት ዘመን በመሰጠት ላይ የሚገኘው ትምህርት ውጤታማነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትጋት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ ሀላፊ አክለዉም የትምህርት ልማት ስራ በአንድ ወገን ብቻ የሚከናወን ተግባር ባለመሆኑ ወላጆች ከትምህርት ቤቱ አመራሮች ጋር በትኩረት በመሰራት የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲጎለበት የሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ትምህርት ቤቶች የትምህርት በሬዲዮ ፕሮግራምን በአግባቡ ተግብረው ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡ (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ
+8
ትምህርት ቤቶች የትምህርት በሬዲዮ ፕሮግራምን በአግባቡ ተግብረው ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡ (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የትምህርት በሬዲዮ ሰርጭት አተገባበር ውጤታማነትን መሰረት በማድረግ በአንደኛ በረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትል ለሚያካሂዱ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የውብዳር አያሌው በከተማ አስተዳደሩ የትምህርት በሬዲዮ ተደራሽነት እየጨመረ መሆኑን አስታውሰው ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት የ2019 ዓ.ም ትምህርት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በትምህርት ቤቶች የትምህርት በሬዲዮ ስርጭት አተገባበር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ታስቦ እንደሚካሄድ አመላክተዋል ። ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም በድጋፍና ክትትል ስራው የሚሳተፉ ባለሙያዎች በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት የትምህርት በሬዲዮ ስርጭቱ በተተዘጋጀው መርሀግብር በአግባቡ ተግባራዊ በመሆን ላይ እንደሚገኝ በተጨባጭ መረጃ በማረጋገጥ ትክክለኛ ግብረመልስ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡ በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ፕሮግራም አዘጋጅ አቶ ፀጋዬ አጋጨው ለድጋፍና ክትትሉ የተዘጋጀውን ቼክሊስት በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የማህበረሰብ ክፍሎች መንግስት ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍንላቸው ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰብ የመሰረታዊ ቤተሰቡን 50 ፐረሰንት መዋጮ ይከፍላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተማ አስተዳደሩ በ 2018 ዓ.ም ለማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት አመታዊ መዋጮ ብር 1.3 ቢሊዮን ብር ድጎማ ያደረገ ሲሆ በ 2019 ዓ.ም ለዚሁ ተግባራት የሚውል 2.3 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙም ተገልጻል ፡፡ የጊዜ፣ የወጪና የሰው ኃይል ብክነት ለመቀነስ፣ የመዋጮ አሰባሰብ ሂደትን ሲስተም ጋር በማቀናጀት የተሻሻለ የክፍያ አሰራር ተዘርግቶ እተሰራ መሆኑም የነጋዴው ማህበረሰብ ወደ ተለያዩ ተቋማት በአካል መሄድ ሳያስፈልገው የመዋጮ ክፍያውን በኦንላይን በቀላሉና በፍጥነት በመፈጸም ማረጋገጫ ማግኘት ማስቻሉ የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽነት ለማሳደግ፣ የክፍያ መረጃዎችን በተገቢው ሁኔታ ለመመዝገብና ለመከታተል፣ የአሰራር ቅልጥፍናን ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል ። ዋናው ነገር ጤና ነውና ህብረተሰቡ ራሱንና ቤተሰቡን ካልታሰበ የድንገተኛ ወጪ ለመጠበቅ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆን እንዳለበት እና አባላት ወደ ምዝገባ ሲሄዱ መሟላት የሚገባውን በሙሉ በሟሟላት ስራው የተቀላጠፈ እንዲሆን ማገዝ xንዳለባቸው ዶክተር ዮሃንስ አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ2019 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ምዝገባ ከጥቅምት አንድ ጀምሮ እስከ ህዳር 30/2019 ዓም እንደሚሰጥ ገለጸ ፡፡ (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም)
+2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ2019 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ምዝገባ ከጥቅምት አንድ ጀምሮ እስከ ህዳር 30/2019 ዓም እንደሚሰጥ ገለጸ ፡፡ (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ምዝገባ ከጥቅምት አንድ ጀምሮ እስከ ህዳር 30/2019 ዓ.ም ለተከታታይ 2 ወራት እንደሚሰጥ የቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል ፡፡ ከተማ አስተዳደሩም ሆነ ቢሮው የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ፍትሀዊነት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ እና ዋነኛ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ተፈጻሚነት ያለው የጤና መድህን አዋጅ ቁጥር 1273/2014 አንቀጽ 15 (6) የመክፈል አቅምን መሠረት ያደረገ የመዋጮ አከፋፍል ስርዓት እንደሚደነግግም ተናግረዋል ። በ2018 በጀት አመት ከ 2ሚሊዮን 750 ሺህ ዜጎች በላይ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል የሆኑ ሲሆን ከ 3ሚሊዮን 200ሺህ በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ባሉት የመንግስት ጤና ተቋማት የጤና አገልግሎት በድግግሞሽ ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉም ጠቁመዋል ፡፡ የ2019 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ነባር አባላቶች ሙሉ ለሙሉ እድሳታቸውን እንዲያሳድሱ እና ከ10 ፐርሰንት በላይ አዲስ አባላቶችን በአጠቃላይ ከ 3 ሚሊየን በላይ የከተማችን ነዋሪዎችን አባል በማድረግ ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝና በገቢ እርከን ደረጃ የክፍያ መጠን ከፍተኛ 10ሺህ 500 ብር መካከለኛ 2ሺህ 500 ዝቅተኛ ደግሞ 1ሺህ 500 እንዲሁም በጣም ዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ 892 ሺህ በክፈል ለማይችሉ የማህበረሰ

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጫወታ የማስተማር ስነዘዴን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው በ2019 ዓ.ም የትምህርት አመት የተቋማቱን ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። በከተማ አስተዳደሩ 25 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ 4 ለማስገባት በትኩረት በመሰራት ላይ መሆኑን የቢሮው የቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ባለሙያ አቶ አቤል ኤፍሬም አስታውቀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ቢሮው በ2019 የትምህርት አመት 25 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደረጃ 4 እንዲገቡ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑ ተገለጸ። (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም
+7
ቢሮው በ2019 የትምህርት አመት 25 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደረጃ 4 እንዲገቡ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑ ተገለጸ። (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማዊ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት እና አጠቃቀም ማኑዋል እንዲሁም ተቋማቱን ሞዴል ለማድረግ መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ለተመረጡ የቅድመ አንደኛ ደረጃ አስተባባሪዎችና መምህራን መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላዬ ዘውዴ ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስትና የግል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶችን ሞዴል ለማድረግ ባከናወናቸው የተለያዩ ተግባራት አብዛኛዎቹ ተቋማት በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ ትራንስፎርም ማድረጋቸውን ጠቁመው ሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሞዴል ሆነው የተማሪዎቻቸውን ሁለንተናዊ እድገት እንዲያስቀጥሉ ከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ በጀት ያቀረባቸውን ግብአቶች ለታለመለት አላማ ማዋል እንዲችሉ ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማዊ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ስራ ክፍሉ

ማስታወቂያ! (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
+2
ማስታወቂያ! (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ልምዱን አካፈለ፡፡ (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ለ
+9
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ልምዱን አካፈለ፡፡ (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ለመጡ ልዕካን ቡድኖች በትምህርት ዘርፉ እያከናወናቸዉ በሚገኙ ስራዎች ላይ ልምድን አካፍላል፡፡ በልምድ ልውውጡ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የቢሮ ዳይሬክተሮችና ከሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመጡ ልዕካን ቡድኖች ተሳተፉ ሲሆኑ በዋናነት ቢሮ ከስርዓተ ትምህርት ዝግጀትና ትግበራ ፣ ከትምህርት ቴክኖሎጂ መሰረት ልማትና ትምህርት ረገድ ፣ ከትምህርት ቤት መሻሻልና ግንባታ ስራዎች አካያ እንዲሁም ከለውጥ ስራዎች ትግባራ አንጻር የተከናወኑ ስኬታማ ስራዎች ለልዑካን ቡድኖች እንዲቀርብ ተደርጋል፡፡ በልምድ ልውውጡ የተካፈሉ ልዑካን ቡድኖች ለተደረገላቸው አቀባበልና ላገኙት ተምክሮ ምሰጋና አቅርበው ቢሮ በትምህርት ዘርፍ ስራዉ ላይ እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች አመርቂና ውጤታማ መሆናቸዉን ብሎም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገሩና ትልቅ አሻራን እያሳረፉ የሚገኙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

በአንድነትና በልማት ዛሬም እንደትናንቱ ከፍ ልናደርገው ይገባል ብለዋል። ብሔራዊው የሰንደቅ አላማ ቀን በየአመቱ የጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያው ቀን በተለያዩ መርሀግ ብሮች እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነታችን" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከበረ፡፡ (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢ
+9
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነታችን" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከበረ፡፡ (ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሰራተኞች በጋራ ባከበሩት 19ኛው ሰንደቅ ዓላማ ቀን የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር እና ሰንደቅ ዓላማን በክብር በመሰቀል ተከብሩዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልእክት የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የህዝቦቿን አንድነት የሚገልጽ የኩራታችን ምንጭ መሆኑን ገልጸው ቀኑ ሲከበር ሁሉም ሰራተኛ በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ሀገሪቱ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ በተጨማሪም የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓዋጅ ቁጥር 863/2008 በህግ ተደንግጎ የሚከበር በዓል መሆኑንም ገልጸዋል። አክለውም ሰንደቅ ዓላማችን የሀገር ዳር ደንበር ያስከበሩ አባት እናቶቻችን በክብር ያስረከቡን የሁላችንም የወል ምልክት መሆኑንም አብራርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ኤልያስ ከበደ በበኩላቸው የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ጥልቅ የብሔራዊ ስሜት የሚቀሰቀስበትና የጋራ ቃልኪዳን የሚታደስበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ሰንደቅ ዓላማችን የጽናታችን የነጻነታችን የሉዓላዊነታችን የተስፋችን ምልክት ነው። የአባት እናቶቻችን የአጥንታና የደም የታተመበት ልዩ የኩራት ዐይከናችንን በቃል ብቻ ሳንወሰን

ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን! 🇪🇹 እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን! የ2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን
ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን! 🇪🇹 እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን! የ2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነው። ልዩነቶቻችንን በውይይት እንፍታ፤ አንድነታችንን በመግባባት እናጠናክር፤ ሀገራችንንም በጋራ ጥረት እንገንባ! ዛሬ ሰንደቃችንን ከፍ ስናደርግ፣ ነገ የኢትዮጵያን ክብር፣ ሰላምና ብልጽግና ከፍ ለማድረግ ቃል እንግባ! ኢትዮጵያ በዜጎቿ አንድነት ትጠናከራለች፤ በጋራ ቁርጠኝነታችንም ለትውልድ ትጸናለች! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‎ ‎“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአ
+1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‎ ‎“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” ‎ ‎ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችንና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው። ‎ ‎በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል። አባቶቻችን በፈተናዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ይህ በጋራ የመቆም ጥሪ መቼም ቢሆን ተቋርጦ አያውቅም፤ እያንዳንዱም ትውልድ ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። ‎ ‎መደመር ሁላችንንም አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀናል፤ እኛ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ከዳር ቆመን የምንታዘብ ተመልካቾች ነን? ወይንስ “ይህች ሀገሬ ናት፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም ያሳስበኛል” ማለት የምንችል ባለቤቶች? ‎ ‎ቋንቋዎቻችን፣ ሃይማኖቶቻችን እና ማንነቶቻችን ለዘመናት በጋራ በምናልፍበት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ አብረው ተሰናስለው የተሸመኑ የአንድ ሸማ ክሮች ናቸው። ለሀገር መቆም ከትንንሽ የድፍረት እርምጃዎች ይጀምራል፤ ከራስ አልፎ ሰፊ ርዕይ ይዞ መሥራትንም ይጠይቃል። ያለፉት ትውልዶች ሀገሪቱን እንድንረከብ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ዛሬ በጋራ የምናጸናትን ሀገር ነው ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው። ‎ ‎ስለሆነም ዛሬ ራስዎን ይጠይቁ፤ ለሀገርዎ አንድነትና ብልጽግና ምን አበረክታለሁ?

+7
💥Bio grade 12 shortnote and practice questions ✅@addis_ababa_education_bureau2