✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
الذهاب إلى القناة على Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
195
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-730 أيام
أرشيف المشاركات
27ኛዋ ሌሊት!
ስማ/ስሚ!!
ዛሬ አይተኛም
~
ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል። ከየትኛውም ሌሊት በተለየ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣታል። ስለሆነም ለዚችኛዋ ሌሊት የበለጠ ትኩረት መስጠት ይገባል። ሶላት፣ ቁርኣን መቅራት፣ አዝካር፣ ድምፅን ዝቅ፣ ቀልብን ስብር አድርጎ ደግሞ ደጋግሞ በዱዓእ የሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል። ኢኽላስ እና ኹሹዕ መዘንጋት የሌለባቸው ትጥቆች ናቸው። ባይሆን የሱብሕን ነገር አደራ! ብልጥ ነጋዴ ትርፍ ፍለጋ ወረቱን አይጥልም።
ከኢብኑ ሙነወር የተወሰደ
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በዚህ ታላቅ ሌሊት የሚፈፀም አንድ ታላቅ ዒባዳ ልጠቁማችሁ!
~
ወንድማችን ሰዒድ ኢብራሂም የበለጠ ለዲን፣ ለወገን ለመስራት ብሎ የመንግስት ስራውን ትቶ በአፋር ክልል ሎግያ ከተማ በሚገኘው "ተቅዋ መስጅድ" ውስጥ ቁርዓንና ኪታብ በማስተማር እንዲሁም በዳዕዋ ስራ ላይ ሙሉ ትኩረቱንና ጊዜውን ሰጥቶ እየሰራ ነበር። ይሄ ብርቱ ወንድማችን አምስት ህፃናት ልጆችን ጥሎ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በሞት ተለይቶናል።
ስለዚህ የዚህን የዲን፣ የወገን ባለውለታ ወንድም ልጆች ለማቋቋም አነሰ በዛ ሳንል በምንችለው እንድንተባበረው ጥሪ እናደርጋለን። አላህ ሶደቃችሁን ይቀበላችሁ፣ ለይለተል ቀድርን ይወፍቃችሁ። ከእሳት ጠብቆ ጀነትን ያድላችሁ።
የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000751636238
ስም፦ Nesrddin, Seid and Yimam
ለበለጠ መረጃና ተሳትፎ
ወደ ቴሌግራም ግሩፑ በመቀላቀል የበኩላችሁን ተወጡ፡
👉 https://t.me/+MxnYwRWJtaI5YmFk
"የየቲሞችን እንባ አብረን እናብስ!"
ይህንን መልእክት ሼር (Share) በማድረግ የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ።
27ኛዋ ሌሊት!
~
ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል። ከየትኛውም ሌሊት በተለየ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣታል። ስለሆነም ለዚችኛዋ ሌሊት የበለጠ ትኩረት መስጠት ይገባል። ሶላት፣ ቁርኣን መቅራት፣ አዝካር፣ ድምፅን ዝቅ፣ ቀልብን ስብር አድርጎ ደግሞ ደጋግሞ በዱዓእ የሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል። ኢኽላስ እና ኹሹዕ መዘንጋት የሌለባቸው ትጥቆች ናቸው። ባይሆን የሱብሕን ነገር አደራ! ብልጥ ነጋዴ ትርፍ ፍለጋ ወረቱን አይጥልም።
=
ቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
( ربي إني لما أنزلت إلي من خير فقير)
«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ»።
•እንደ ኢብኑ ዐሹር ተፍሲር፤ከላይ የተጠቀሰችው የቁርአን አንቀፅ ሶስት መልእክትን ይዛለች።እነሱም ምስጋና ውዳሴ እና ዱዓእ ናቸው።እንደሚታወቀው አላህን አመስግኖ እና አወድሶ ዱዓእ ማድረግ ፈጣንና ሰፊ ተቀባይነት አለው።ለዚህም አላህ ለ ነብዩሏህ ሙሳ አስደሳችና ፈጣን ምላሽ ሰጥቶታል።
① ሚስት የለውም ነበር። ሚስት አገኘ።
② መጠለያ ቤት አልነበረውም ከደጉ ሰውዬ ቤት ተጠጋ።
③ ስራ የለውም ነበር ስራ አገኘ።
ብዙዎች ግን ይችን አንቀፅ ሲያስታውሱ ሚስትን ብቻ ያስታውሳሉ። እውነታው ግን ነብዩሏህ ሙሳ ከሚስት በተጨማሪ ቤትና ስራም አትርፎበታል።
አቡ ሱፍያን
"ዲን መያዝ ፍም የመጨበጥ ያህል ከባድ ይሆናል" የተባለው ዘመን ይህ ነው እንዴ!"ብሎ ጠየቀ አንድ ወጣት አላህን አብዝተው የሚፈሩትን አንድ ዓሊም።
ዓሊሙም " ያ ዘመንማ ካለፉ ቆይቷል፤ አሁን ያለንበት ዘመን አንድ ሰው ሙስሊም ሆኖ ያነጋል፣ ካፊር ሆኖ ያመሻል፤ ሙእሚን ሆኖ ያመሻል ካፊር ሆኖ ያነጋል፤ በጥቂት ዱንያዊ ጥቅም ዲኑን ይሸጣል።" የተባለው ዘመን ነው። አሉት።
አቡ ሱፍያን
"በፈለግከው ነገር ብትቀልድ በእምነትህ ግን ፈፅሞ እንዳትቀልድ!!"
አልኢማም ማሊክ ረሒመሁላህ
(ተርቲቡል መዳሪክ: 2/65)
በጤናው ዘርፍ ተመረቃችሁ ስራ ለሌላችሁ ሙስሊም እህት እና ወንድሞች ይህ የስራ ማስታወቂያ ስለወጣ መወዳደር ትችላላችሁ።
Repost from 🔹قَناةُ أبي جُلَيبيب الأثري
የእርዳታ ጥሪ ለሱመያ ኢድሪስ👆👆
👂👂መልእቱን በደንብ አዳምጡት 4 ደቂቃ አካባቢ ነው አጭር ነው ባረከሏሁ ፊኩም።
ከላይ የምትመለከቷት ታዳጊ ህፃን ልጅ ከ4አመት በላይ በከባድ ህመም ውስጥ እየተሰቃየች ትገኛለች ።
የሱና ወንድማቺን ልጅ ነች በደካማ ቤታቸው የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል
ዛሬ ግን ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የውንድሟቻቸውንና የእህቶቻቸውን ትብብርን ሽተዋል።
መቼም የልጂን ነገር የወለደ ያቀዋል።ስለዚህ የምንቺለውን እናግዛቸው።
~~~
እኔ በደንብ ቀርቤ ነው የማቃቸው በጣም ጥሩ ሰዎች ናቸው እናስደስታቸው። የተከበራችሁ ውንድሟቼና እህቶቼ
ሼር ሼር ሼር አድርጉት
አንተ የሐጃ(የጉዳይ) ባለቤት!
➰ አዎ... አንተን ነው! ያ የከበደህ ነገር፣ ያ ሌሊት እንቅልፍ የነሳህ ጉዳይ፣ ያ ማንም የማያውቅብህ የልብህ ስብራት... ዛሬም አብሮህ አለ?
ለመሆኑ... ዛሬ ላይ ቆመህ አላህን ካለመንከው፣ መቼ ልትለምነው ነው?"
➰"እስኪ አስበው... አንተ ፆመኛ ነህ። ሆድህ ለጌታህ ሲል ተርቧል፣ ከንፈርህ ደርቋል። ይህ ድካምህ ግን አላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው።
➰የአንተ ውዱ ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ምን አሉ መሰለህ? 'የፆመኛ ዱዓ በፍጹም አይመለስም!' ይህ ማለት በአንተና በጌታህ መካከል ያለው በር ወለል ብሎ ተከፍቷል ማለት ነው።
●አላህ 'ለምነኝ ልስጥህ' እያለህ... አንተ ግን በዝምታ ታልፈዋለህ? 'አይ ቆይ ነገ እለምናለሁ' ትላለህ? የነገ ሰው መሆንህን ማን ነገረህ?➰ለውጥ የሚጀምረው ከልመና ነው። ● ዱዓ ማለት 'አልቻልኩም' ብሎ ለቻይ ጌታ እጅ መስጠት ነው። ●ዱዓ ማለት 'ደካማ ነኝ' ብሎ ወደ ብርቱው ጌታ መጠጋት ነው።" ➰"ስማኝ! ዛሬ ላይ ቆመህ ካልተለወጥክ፣ ዛሬ ካለመንክ፣ መቼም አትለምንም። ያንተ ሐጃ ለአላህ ቀላል ነው። አንተ ተራራ የምታየው ለእሱ ቅንጣት ታክል ነው። ወንድሜ/እህቴ ሆይ "አትጠራጠር/ሪ! ጌታህ/ሽ ሰሚ ነው። ጌታህ/ሽ ሰጪ ነው። ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት፣ ያንተ/ቺ የለውጥ ፀሐይ እንድትወጣ ተማጸነው/ኝው። ዛሬ ካልሆነ... መቼ?" ያአላህ! ዛሬ የሁላችንም የሐጃ (የጉዳይ) በር የሚከፈትባት፣ የጨለመው የሚበራባት፣ የራቀው የሚቀርብባት ልዩ ቀን እንድትሆንልን ዱዓዬ ነው። ያ አላህ! ለሁላችንም እንደየልባችን መሻት፣ እንደ ሐጃችን ስፋት ሳይሆን እንደ አንተ ቸርነትና ሰጪነት መልስልን። አሚን!
ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለተል ቀድር ዙሪያ
~
ለይለቱል ቀድር ማለት ትልቅ ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው። ከፊል ዓሊሞች ዘንድ ደግሞ ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት ነው።
የለይለተል ቀድር ደረጃዎች፦
1. ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተል ቀድር አወረድነው”ብሏል። [አልቀድር፡ 1]
2. በሷ ውስጥ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች ምንዳው የበለጠ ነው። አላህ “ለይለተል ቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት” ይላል። [አልቀድር፡ 3]
3. በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ። ጌታችን “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ” ብሏል። [አልቀድር፡ 4]
4. ለሊቷ ዒባዳ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት። ጌታችን “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት” ብሏል። [አልቀድር፡ 5]
5. የተባረከች ለሊት ናት። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው” ብሏል። [ዱኻን፡ 3]
6. በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል። “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል” ብሏል አላህ። [ዱኻን፡ 4]
7. በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው። [አልባኒ ሐሰን ብለውታል]
8. ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር። በ(ረመዳን) አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!)” [በዳኢዑል ፈዋኢድ፡ 1/55]
ለይለቱል ቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው። ከረመዳንም በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ። ነብዩ ﷺ “ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ አለኝ” ማለታቸው ይህን ያስረግጣል።
ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል። ነብዩ ﷺ በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች። የሷን ኸይር የተነፈገ በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2247]
መቼ እንፈልጋት?
ይበልጥ የሚገመተው ጊዜ 27ኛዋ ለሊት ናት። ይሁን እንጂ “ለይለተል ቀድርን በ23ኛዋ ለሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም “ለይለተል ቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) ፈልጓት። ከተረታችሁ በመጨረሻዎቹ 7 ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተል ቀድር ሁሌ በአንድ ለሊት ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል። በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው። ይህን አስመልክተው ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) በዊትሮቹ ፈልጓት” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሸፍዕ ለሊቶችም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ፈልጓት። ዘጠኝ ሲቀረው፣ ሰባት ሲቀረው፣ አምስት ሲቀረው” ብለዋልና። ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ ሲቆጠር ነው። ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው የሚሆኑት። ይህም ሸፍዕ ለሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል። ቢሆንም ግን “ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ዊትሩ ላይ ይበልጥ ማተኮር ይገባል።
በለይለተል ቀድር ምን ይጠበቅብናል?
ዒባዳ ማብዛት። ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል” ይላሉ። [ቡኻሪና ሙስሊም] እናም በዚች ለሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለመታየት ለጉራና መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው።
ምልክቶቿ
1. “በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች።” [ሙስሊም]
2. በዚያን ለሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል። ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች። [ሶሒሑል ጃሚዕ]
እነዚህ ምልክቶች ግን አንፃራዊ ናቸው ይላሉ ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ። በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል። ስለሆነም በትክክል ለይለተል ቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው ሊኖር ይችላል።
ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!
የወር አበባ ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች… የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም። ማስረጃው ጠቅላይ ነውና። ባይሆን ከሶላት ውጭ ባሉ ዒባዳዎች ላይ ሊበራቱ ይገባል። በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው። እንዲያውም ሱፍያኑ ሠውሪ ረሒመሁላህ “በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ።
ለይለተል ቀድር በአይን ትታያለች?
አንዳንዶች እግራቸውን ዘርግተው፣ እያወሩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ። የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው። እሱን ሲያዩ “አኑረን አክብረን” ብለው ይንጫጫሉ። ይሄ ባዶ እምነት ነው። ለይለተል ቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም። የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም። ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም።
ለይለተል ቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?
በተለይ ደግሞ ለሊቱ ለይለተል ቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አሏሁመ ኢነከ ዐፉውዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው። [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ስለዚህ ዋናው ትኩረታችን የአላህን ይቅርታ ለማግኘት ይሁን።
ግን ለምን አላህ ለይለተል ቀድርን ስውር አደረጋት?
ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ለሊት ስውር ያደረጋት። እናም ለይለተል ቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ለዒባዳ ይተጋሉ። በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ። ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹ ለሊቶች ላይ ይዘናጉ ነበር። እናም መሰወሯ ነብዩ ﷺ እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው። [ቡኻሪ]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 29/2007)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
