✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
الذهاب إلى القناة على Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
195
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-730 أيام
أرشيف المشاركات
⇛በሚያፈጥሩበትም ሆነ ፆም በሚይዙበት ጊዜ ዱዓ ይወደዳል። ረመዷን ዉስጥ ከልቡ የለመነ ሸዋል ላይ፣ ከሸዋልም በፊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በርግጠኝነት ዉጤቱን ያያል።
⇛በረመዷን በቀንም ይሁን በማታ፣ በአፍጥር ይሁን በሱሑር በማንኛዉም ሰዓት ከዱዓ አትዘናጉ። የፆመ አንጀት ዱዓ ቢያደርግ ምላሽ አይነፈገዉም። የረመዷንን ዱዓ ችላ ያለ በርግጥ በራሱ ላይ ሰሰተ።
አቡ ሱፍያን
ከመስጂድ አደቦች መካከል፦
1. ወደ መስጂድ ሲሄዱ ያማረ ልብስ መልበስ።
2. ጥሩ ሽታ ያላቸውን ነገሮች መጠቀም።
3. በመኝታና በስራ ልብስ መስጂድ አለመሄድ።
4. በእርጋታ መሄድ። ችኮላንና እሩጫን መተው።
5. ሲገቡ ዱዓ ማድረግ፣ ቀኝን ማስቀደም።
6. ተሕየተል መስጂድ ረክዓተይን መስገድ።
7. መጥፎ ሽታ ያላቸውን ነገሮች መራቅ።
9. ጀናባ ሁኖ መስጂድ አለመግባት።
10. ቦታ ይዞ ከመስጂድ አለመውጣት።
11. ጫማዎችን ከቦታቸው ማስቀመጥ።
12. ስልክን መዝጋት ወይም ሳይለንት ማድረግ።
13. እየሰገዱ እያለ ከተደወለ ተሎ መዝጋት።
14. ወደ ሶፉ በእርጋታ መግባት።
15. ወደ መስጂድ በጊዜ መሄድ።
16. የመስጂዱን ንፅህና መጠበቅ።
17. መስጂድ ውስጥ አለመፍሳት
18. ጥፍር አለመቁረጥ።
19. ወረቀት አለመቀዳደድ፣ ሶፍት አለመጣል።
20. መናፈጥና አክታ መጣል ክልክል ነው።
21. ድምፅን ዝቅ ማድረግ።
22. መስጂድ ውስጥ አለመገበያየት።
23. የጠፋ እቃን ማፈላለጊያ አለማድረግ።
24. የልመና ቦታ አለማድረግ።
25. የነሺዳ መባያ አለማድረግ።
26. መመገቢያ እና መጠጫ አድርጎ አለመያዝ።
27. አደብን የሚያጎድል ቀልድን መተው።
28. ያለ ሐጃ መሳሪያ ይዞ አለመግባት።
29. ኢማሙ ሲያጠፉ በድብቅ መምከር።
30. የሚሰግድ ካለ ድምፅን ዝቅ አድርጎ መቅራት።
31. የራስን ሃሳብ በሰዎች ላይ አለመጫን።
32. የመስጂድ ወቅፎችን አለመውሰድ።
33. መስጂድን የፓለቲካ ቦታ አለማድረግ።
34. አዛን ከተባለ በኋላ ያለምክንያት አለመውጣት።
35. ከመስጂድ ሲወጡ ጫማን ተሎ ማንሳት።
36. ሚስትን ወይም ሌላ የሴት ቤተሰብን ሲጠብቁ ከሌሎች ሴቶች አይንን መስበር።
=
[ሑስኑል አደብ 157 - 161]
[ሸይኽ ሙሐመድ አልኢማም]
ባለችን እንሰድቅ
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን ከእሳት ተጠበቁ።"
[ቡኻሪና ሙስሊም]
ታጋሽ ሆኖ ለመገኘትም የአላህ እገዛ ያሻል። ታጋሽነት በራስ ክህሎትና በልምምድ ብቻ የሚገኝ የትግል ፍሬ አይደለም። አላህን በመማጽንም ጭምር እንጂ።
ኻቲማ•••••••••[መጨረሻ]‼
ወደ አላህ መንገድ የሚገቡ ሰዎች መጀመርያ ላይ ብዙ ናቸው፤ ከዚያ በሂደት እየቀነሱና እየተንጠባጠቡ ይሄዳሉ፡፡ በመጨረሻም ጥቂቶች ብቻ ይቀራሉ፡፡ የአላህ መንገድ ትዕግስትን፣ ፅናትንና ተውፊቅን ይፈልጋል፡፡ ጌታዬ ከጥቂቶቹ ባሮችህ አድርገን፡፡
አምላኬ ሆይ የኻቲማዬን ነገር
አቡ ሱፍያን
ወንድሜ/እህቴ
ከአባትህ ውጭ ባለ አካል አትጠራ
የራስ ባልሆነ አባት/ጎሳ ሙግት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“እያወቀ ያለ አባቱ ሌላን የሚሞግት (በሌላ የሚጠራ) ሰው አይኖርም፣ የካደ ቢሆንጂ። ከነሱ ሳይሆን ወደሆኑ ወገኖች እራሱን በማስጠጋት የሞገተ መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 3508
#የቱንም ቢሆን መልካም ስራን አትናቅ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لقَدْ رَأَيْتُ رَجُلًا يَتَقَلَّبُ في الجَنَّةِ، في شَجَرَةٍ قَطَعَها مِن ظَهْرِ الطَّرِيقِ، كانَتْ تُؤْذِي النّاسَ﴾
“አንድን ሰው በመንገድ ላይ ሰዎችን ያስቸግር የነበረን ዛፍ ቆርጦ በማስወገዱ ምክንያት በጀነት ውስጥ ሲጣቀም አየሁት።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1914
ጣፋጭ የቁርኣን ቲላዋ
الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَى جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ آل
(عمران191)
(እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡
ቃሪዕ ሸይኽ አሊ ጃቢር
📌 የጁሙዓ ቀን ቁርአን መክፈት ⁉️
📌ጥያቄ📌
📌 በእኛ አካባቢ ዘወትር ጁሙአ ጁሙአ አብዛህኛው መስጂድ ውስጥ በማይክራፎን ቁርአን ይከፈታል ፣ ይህን የሚያደርጉት ሰውን ወደ መስጂድ ለመጥራት ወይም ጁሙአ ቀን ስለሆነ ብለው ነው። ይህ በሸሪዓችን እንዴት ይታያል⁉️
✅መልስ✅
✅ ቁርአን የወረደው ተገንዝበነውና አስተንትነነው እንድንሰራበት እንጅ ልክ እንደ አዛን ሰዎችን ወደ መስጂድ መጥሪያነት እንድንጠቀመው አይደለም። ነብየም ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱናቸውን አጥብቀን ይዘን እሳቸውን ከመፃረርና በዲናቸው ላይ አዲስን ነገር ከመፍጠር እንድንቆጠብ አዘውናል።
❌ በሀገራችን በበርካታ መስጂዶች እንደሚስተዋለው ጁሙአ ቀን በማይክራፎን ቁርአን መክፈት በሸሪዓችን መሰረት የሌለውና ነብዩም ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ያላዘዙት ፣ ሰለፎችም የማያውቁት ቢድአ የሆነ ተግባር ነው። በዚህ መልኩ የጁሙአ ቀን ሁሉም ሙስሊም በግሉ ቢቀራቸው የሚወደዱ የቁርአን ምእራፎችን እንጅ መስጂድ ላይ ቁርአን መክፈት የተወደደ መሆኑን የሚያመለክት ሸሪዓዊ ማስረጃ የለም።
❌ ሰዎችን ወደ መስጂድ ለመጥራት ታስቦበትም ከሆነ በጁሙአ አዛን እንጅ በቁርአን መጥራት አልተደነገገም። የጁሙአ ቀን ስለሆነ ተብሎም ከሆነ በዚህ መልኩ ጁሙአ ቀንን በሸሪዓችን ባልተደነገገው መልኩ መለየትም አይፈቀድም።
♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ መጅሙዑል ፈታዊ ፣ 16/128 ፣📚የሳኡዲ የኢልም ጥናትና የፈትዋ ቋ
ሚ ኮሚቴ ፣ 4/40
ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~~~
የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:–
(إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ)
"ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አትተውባ: 60]
መጠነኛ ማብራሪያ
① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም።
③ ዘካ ላይ የሚሰራ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑም ዘካ ይሰጣቸዋል።
ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።
④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው።
አንደኛ/ ካፊር (ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው): –
– ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣
– የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ
ሁለተኛ/ ሙስሊም:–
– በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ
– በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290]
⑤ እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው።
የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል።
⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አልሞ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል።
⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል።
⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል።
ጉዞ ወደ አብሬት! ❌
ጉዞ ወደ ነጃሺ ! ❌
ጉዞ ወደ ዲያና ! ❌
ጉዞ ወደ ጌታው ሸህዬ ! ❌
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لا تُشَدُّ الرِّحالُ إلّا لِثَلاثَةِ مَساجِدَ: مَسجِدِ الحَرامِ، ومَسجِدي هذا، والمَسجِدِ الأَقصى.﴾
“ወደ ሶስት መስጂድ ካልሆነ በቀር ለአምልኮት እንዳትጓዙ። እነሱም፦ መስጂዱል ሐራም፣ መስጂዱል አቅሷ ይሄ መስጂዴ መዲና የሚገኘው የሳቸው መስጂድ ናቸው።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1189
#የሰማህውን ሁሉ አታውራ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
كَفى بالمَرْءِ كَذِبًا أنْ يُحَدِّثَ بكُلِّ ما سَمِعَ
“ለአንድ ሰው ውሸታም ለመባል በቂው ነው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ።”
📚 ሙስሊም
የበሽታ ደምን የሚመለከት አጭር ማስታወሻ
- የወር አበባን መለየት ሲያስቸግር የሚያግዙ ነጥቦች -
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"በረመዳን የሚፈፀም ኃጢአት በሌላ ጊዜ ከሚፈፀም ኃጢአት ወንጀሉ የከፋ ነው።"
[መጅሙዑ ፈታዋ ወመቃላት፡ 15/446]
ሲጋራ
~~~
"ለማንም ሰው ሲጋራ መሸጥ አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ሲጋራ የተከለከለ ነውና። አላህ አንድን ነገር ክልክል ካደረገ የሽያጭ ዋጋውንም ከልክሏል። እንዲሁም እሱን መሸጥ በወንጀልና ወሰን በመተላለፍ ከመተባበር ነው።" [አሊቃኡ ሸህሪይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፡ 3/ 597]
-
ጫትም ላይ ተመሳሳይ ብይን ነው ያለው። መሸጥም፣ መግዛትም፣ ማጓጓዝም፣ መሸከምም፣ ማሸከምም፣ ሱቅን ለጫት ንግድ ማከራየትም፣ ... በየትኛውም መልኩ መተባበር አይፈቀድም።
=
IbnuMunewor
ከሰለፎች አንደበት!
ኢብኑ ዑሰይሚን (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿فكل إنسان يكــره النساء ويعاملهــن معاملة سيئــة ففيــہ شبــہ من أهل الجاهلية﴾
“እያንዳንዱ ሴቶችን የሚጠላና፤ መጥፎ አያያዝን የሚይዛቸው ሰው ከጃሂሊያው ዘመን ሰዎች ጋር መመሳሰል ያለበት ሰው ነው።”
📙 ኑሩን ዐለ ደርብ፡ 314
ከነብዩ ﷺ ድንቅ ስብዕናዎች ውስጥ፦
•የአላህ ክብር ሲነካ ይቆጣሉ፣
•ለተሳሳተ ይቅርታ ያደርጋሉ፣
•የቀረበውን ይመገባሉ፣
•ምግብ አያነውሩም፣
•ካልተመቻቸው ይተውታል።
