ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

الذهاب إلى القناة على Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
193
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-530 أيام
أرشيف المشاركات
رسالة صوتية07:20

የእንቁላል የጤና ጥቅሞች 🥚ሙሉ ፕሮቲን ይሰጣሉ፡-አንድ እንቁላል ሁሉም ዘጠኙ "አስፈላጊ" አሚኖ አሲዶችን ይይዛል፤ እነዚህ ፕሮቲንን ለመገንባት የሚያስፈልጉ ሰውነት በራሱ ሊሰራቸው የማይችለው የአሚኖአሲድ አይነቶች ናቸው፡፡ 🥚 ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው፡- ይህ ማለት እንቁላሎች ከአብዛኞቹ ምግቦች የበለጠ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች አሏቸው፡- •  ሴሊኒየም •  ፎስፈረስ •  ቫይታሚን B12 •  ብዙ አንቲኦክሲደንትስ ይህም የሴሎችን ጤናማነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ 🥚በሰውነት ውስጥ 'ጥሩ' ኮሌስትሮል እንዲጨምር ይረዳሉ፡፡ 🥚የስትሮክ የመከሰት እድልን ዝቅ ያደርጋል። 🥚ለልብ ጤናማ ናቸው፡- በቀን አንድ እንቁላል የሚበሉ ሰዎች እንቁላል ካልበሉ ለልብ ሕመም የመጋለጥ እድላቸው በ20 በመቶ ያነሰ ነበር። 🥚ዓይንዎን ይረዳሉ፡- ሉቲን እና ዜአክሳንቲን የተባሉት አንቲኦክሲደንትስ እንደ የዓይን ሞራ ግርዶሽ እና ከእድሜ ጋር ተዛማጅነት ያለው ማኩላር ዲጄኔሬሽን ባሉ የአይን በሽታዎች እንዳይያዙ ይረዳል፡፡ 🥚የነርቭ ሴሎችን ጤና ይጠብቃሉ፡- በውስጣቸው የነርቭ ሴሎች (ኒውሮኖች) እርስ በርስ እንዲነጋገሩ የሚረዳ ኮሊን የሚባል ነገር አላቸው። ኮሊን ለነፍሰ ጡር ሴቶች እና ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ነው ምክንያቱም በአንጎል እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። እንቁላል ብዙ ጠቀሜታ ያለው ቢሆንም አብዝቶ መጠቀም ግን ሌሎች ችግሮችን ሊያባብስ ይችላል ስለሆነም ሳምንታዊ የእንቁላል ፍጆታን መገደብ ያስፈልጋል፡፡ የኮሌስትሮል እና የልብ በሽታ ካለ መጠኑን ከመቀነስ በተጨማሪ የውጨኛውን(ነጩን ክፍል) ብቻ መጠቀም ያስፈልጋል፤ በተጨማሪም የስኳር በሽታ፣ የፕሮስቴት ፣ የፊኛ እና የጡት ካንሰሮች ካሉ እንቁላል መጠቀምን መቀነስ ይመከራል።                                                                               

🍃 ጥርስን ጤናማ ለማድረግ የሚረዱ መንገዶች ጤናማ ጥርስ ማግኘት የህይወት ዘመን እንክብካቤን ይጠይቃል፤ ጤናማ ጥርሶች እንዲኖሩ መንከባከብ እና ችግሮችን ለመከላከል በየቀኑ ትክክለኛውን እርምጃ መውሰድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ትክክለኛ የአፍ እንክብካቤ ምርቶችን ማግኘትን እንዲሁም የእለት ተእለት ልማዶችን ማስታወስን ያካትታል፡- 👉ጥርስህን ሳይቦርሹ አለመተኛት፡- እንደ አጠቃላይ ምክር ጥርስን በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ መቦረሽ አስፈላጊ ነው ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ ጠዋት ላይ ብቻ የመቦረሽ ልምድ ይስተዋላል፤ ከተቻለ ሁለቱንም ጊዜ የሚመከር ነው ካልተቻለም ግን ከመተኛት በፊት መቦረሽ ቀኑን ሙሉ የሚከማቸውን ጀርሞች እና ንጣፎችን ስለሚያስወግድ ከመተኛት በፊት ጥርስን ማፅዳት የተሻለ ልምድ ነው፡፡ 👉ምላስን ማጽዳት፡-በምላስ ላይ የምግብ እና የመጠጥ ንጣፍ ሊገነባ ይችላል፤ ይህ ወደ መጥፎ የአፍ ጠረን ብቻ ሳይሆን ወደ ሌሎች የአፍ ጤንነት ችግሮች ሊያመራ ይችላል ስለሆነም ጥርሶችዎን በሚቦርሹበት ጊዜ ሁሉ ምላሶን በቀስታ ይቦርሹ። 👉የፍሎራይድ የጥርስ ሳሙና ይጠቀሙ፡-የጥርስ ሳሙናን በተመለከተ ኃይልን እና ጣዕሞችን ከማጥራት የበለጠ አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች መኖራቸውን ማየት ምንም አይነትሳሙና ቢሆንም ፍሎራይድ መያዙን ያረጋግጡ። 👉ተጨማሪ ውሃ ጠጡ፡-ውሃ ለአጠቃላይ ጤና አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል፤ የአፍ ጤንነትን ጨምሮ። ከእያንዳንዱ ምግብ በኋላ ውሃ መጠጣት ይመክራል ይህም በቀላሉ የጥርስን ጤና የሚጠብቅ ነው፡፡ 👉የስኳር እና አሲዳማ ምግቦችን ይገድቡ፡-ውሎ አድሮ ስኳር በአፍ ውስጥ ወደ አሲድነት ይቀየራል፣ ይህ ደግሞ የጥርስህን ገለፈት ሊሸረሽር ይችላል። እነዚህ አሲዶች ወደ መቦርቦር ያመራሉ፡፡ አሲዳማ ፍራፍሬዎች፣ ሻይ እና ቡና የጥርስ መስታወትን ሊያደበዝዙ ይችላሉ፤ እንደነዚህ ያሉትን ምግቦች ሙሉ በሙሉ መተው ባይኖርብዎትም ጥንቃቄ ማድረግ እነ መጠኑን መቀነስ ይመከራል፡፡

👉ወንድማችን ሁሴን ይምጡና ሰበቡን ያድርሱ ይለናል። ታላቅ የምስራች! ፈውስ ለጠማችሁ እና መፍትሄ ለሻታችሁ እህትና ወንድሞች ሁሉ! 📢 በተለያዩ ህመሞች እየተሰቃያችሁ መድኃኒት ፈልጋችሁ ላጣችሁ፣ በዓለም ዙሪያ ለምትገኙ እህት እና ወንድሞች በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የፈውስ ጥሪ! ከአስ-ሱና ሸሪዓውን የጠበቀ የዋግምትና የቁርኣን ህክምና መስጫ ማዕከል! 🛡 ለታላላቅ መንፈሳዊ ህመሞች ፍቱን መፍትሄ አለን! የምንሰጣቸው ሸሪዓዊ መድኃኒቶች ለሚከተሉት ችግሮች ፈጣን መፍትሄ ናቸው፡- ✅ ለሲህር (ድግምት)፡ ለተበላ፣ ለተጠጣ፣ ለተረገጠ፣ ለተነካ እና ለየትኛውም የሲህር ዓይነት። ✅ ለጅን ጥቃት፡ በአፍቃሪ ጅን እና መሰል መንፈሳዊ ተጽዕኖዎች። ✅ ለዓይነ-ናስ እና ቡዳ፡ በሰው ዓይን እና በክፉ መንፈስ ለታመሙ። ✅ በህክምና (Medical) ብዙ ተሞክሮ ለውጥ ላጡ ታካሚዎች። 🏥 ለአካላዊና ውስጣዊ ህመሞች ከመንፈሳዊ ህክምና በተጨማሪ ለሚከተሉት የጤና እክሎች ተፈጥሮአዊ እና ሸሪዓዊ መድኃኒቶችን እናቀርባለን፡- 🔹 ለሆድ ህመሞች፡ ለሆድ ቁርጠት፣ መነፋት፣ ማቃጠል፣ ሆድ መጮህ፣ መገለባበጥ እና የምግብ ፍላጎት መዘጋት። 🔹 ለራስ እና ፀጉር ችግር፡ ለከባድ ራስ ምታት፣ ለፀጉር መርገፍ፣ መሰባበር እና ለመርሳት ችግር። 🔹 ለዓይን ጤና ችግር፡ ለዓይን ማቃጠል፣ ማሳከክ፣ መደፍረስ እና መቅላት። 🔹 ለአጠቃላይ ሰውነት ችግር፡ ለሰውነት ቁርጥማን፣ ማቃጠል፣ መዛል (ድካም) እና ማሳከክ። 🔹 ለሴቶች ጤና (ማህፀን)ችግሮቸ፡ ለማህፀን ህመም፣ ውጋት፣ ፈሳሽ፣ ለወር አበባ ህመም እና የወር አበባ መዛባት። 🔹 ለወገብ እና መገጣጠሚያ ችግሮች፡ ለወገብ ህመም፣ ለእግር እና እጅ ቁርጥማን እንዲሁም ማቃጠል፡፡ 🧠 ለስነ-ልቦናዊ ችግሮች 🔹 ለጭንቀት፣ ለፍርሃት፣ ለልብ ማፈን (Palpitations)። 🔹 እንቅልፍ እምቢ ላላቸው እና ለከባድ ቅዠት። 🌍 ልዩ አገልግሎቶቻችን 1️⃣ መድኃኒት መላክ፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር (በየትኛውም የዓለም ክፍል) ለምትገኙ መድኃኒቶቻችንን እንልካለን። 2️⃣ የማማከር አገልግሎት፡ ታካሚዎች ባሉበት ሆነው እንዴት በራሳቸው ላይ ሩቃ (Ruqyah) መቅራት እና ራሳቸውን በዚክር ማከም እንዳለባቸው ሙያዊ ምክር እንሰጣለን። 3️⃣ ጅምላ አቅርቦት፡ ለሩቃ ቤቶች (ለህክምና ማዕከላት) መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በብዛት እናከፋፍላለን። 📜 መድኃኒቶቻችን ምንጫቸው ምንድን ነው? ሁሉም መድኃኒቶቻችን ከቁርኣን፣ ከሀዲስ እና ከታላላቅ የኢስላም ሊቃውንት (አኢማዎች) ኪታቦች የተገኙ፣  ሸሪዓን የጠበቁ ናቸው። 📞 አሁኑኑ ይደውሉልን፣ ያማክሩን፣ ይዘዙን! 👤 ወንድማችሁ፡ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ኢስማኢል (ከደሴ) 📲 ስልክ/ 0930320504 0942819970 የቴሌግራም/አድራሻ @Abu_Hibetilah_hussen @Abu_Hibetillah_Al_aseriy የዋትስአፕ አድራሻ፡ [0930320504 📍 አድራሻ፡ ደሴ፣ ከአስ-ሱና የዋግምትና የቁርኣን ህክምና መስጫ ማዕከል ፈውስ ከአላህ ነው፤ እኛ ሰበቡን እናደርሳለን! የቴሌግራም አድራሻችን ይቀላቀሉ ይጎብኙ

ወደ ፀያፍ ምስሎች እና ቪዲዮዎች መመልከት መርከስ ነው ! እስኪ ቆም ብላችሁ አስቡት ! የተራቆቱ ርካሾችን መመልከት ጥቅሙ ምንድን ነው ?!  ማን እንዲህ አይነቱን ርካሽ ነገር ያሰራጫል ?! ... ለምን ?! እወቁ ! ሙስሊሞችን ማርከስ ትልቁ ግባቸው እንደሆኑ እንዳትዘነጉ - ሌላውንማ አጭደው ከጨረሱት ቆይተዋል ! # ወሏሂ ! ወደ ረከሱ ነገሮች መመልከት አይንና አካላችሁ አድክሞ ልቦቻችሁን ይገድላል ! # ጉዳዩ ለዘመናት አብሮ የኖረን የሃፍረት መጋረጃ ቀስ በቀስ በማንሳት ከዘመኑ እንስሶች ጋር ይቀላቅላል - ከወቅቱ ሃፍረት ቢስ የሰው እንስሶች ጋር ! # ወደ እንዲህ አይነቱ ርካሽ ነገር መመልከትኮ ይቅርና ሙስሊሞች ዘንድ በሌሎችም ቤት ነውር ነው ! በነገራችን ላይ - አንዳንዶች .... ወደ እንዲህ አይነቱ ፀያፍ ነገር መመልከት ከተለመና በሽታ ከሆነ በኋላ በሽታውን መላቀቅ የሚቻል አይመስላቸውም ! ... ወሏሂ ይቻላል ! ብቻ ....  ፀያፉን ለመራቅ የልብ ቁርጠኝነት እና እውነተኛ ፀፀት ይኑር .. በአሏህ ታገዙ ... አካባቢ እና  ጓደኛን  ቀይሩ ... መጥፎውን ቦታ በመልካም ፀያፉን ስራ በደጉ ለውጡ ..... https://t.me/msirage4

ደርስ 001👇 العقيدة الطحاوية 🎤በ ኡስታዝ ኢድሪስ መሀመድ ዳርሳ                 VIEW CHANNEL @t.me/ustazidrisfantirasu

+2
Ustaz idris Daqwa Qafar Afat

+1
Ustaz idris Daqwa Qafar Afat

حرمة الغلو فى القبور وخطره.m4a45.78 MB

ተቀሪኦም ዝተወድኡ ደርስታት ማውጫ 📚ዓቂዳ 1,ኡሱሉ ሰላሳ 2,ሓጀቱል ኡማ ሊመንሃጁ ሰለፊ 3,ሚን ኡሱሊ ዓቂደቱ ኣህሊ ሱነቲ ወል-ጀማዓ 4,ኩሉ ቢድዐቲን ደላላ 5,ሸርሑ ሱና ሊል ኢማም ኣል-በርበሃሪ 6,ከሽፉ ሹቡሃት 7,ዓቂደቱ ኣህሊ ሱነቲ ወል-ጀማዓ 8,ፈድሉል ኢስላም 9,ነዋቂዱል ኢስላም 10,ቀዋዒዱል ኣረበዓ 11,ተዕሊሙ ሲብያኑ ተዉሒድ 12,ኡሱሉ ሲታ 13,ኣልሙዕተቀዱ ሰሒሕ 14,ኡሱሉ ሱና 15,ሃዚሂ ዳዕወቱና ወዓቂደቱና 16,ኣል-ዋጂባቱ ሙተሓቲማት 17,ማሂየ ሰለፍያ 18,ዓቂደቱል ዋሲጢያ 19,መሳኢሉ ጃሂልያ 20,ፈትሑ ረቢል በርያ 21,ኪታቡ ተውሒድ ናይ ሸኽ ፈውዛን 22,ሙኽተሰር ፊኡሱሊል ዓቃኢድ 23,ዓቂደቱ ኣህሊ ሱነቲ ወል-ጀማዓ ብሸኽ ሙሓመድ መኪን 24,ኡሱሉ ሱና ሊል ሑመይዲ 25,ኣልከሊማቱ ሒሳን ፊ በያኒ ዑሉዊ ራሕማን 26,ዓቂደቱ ጠሓዊያ 27,ዓቂደቱል ዋሲጥያ ብሸኽ ሙሓመድ መኪን 📚ሓዲስ 1,ዒሽሩን ሓዲስ 2,ኣረበዒኑ ነወውያ 3,ሙኽተሰር ቡኻሪ 📚ፊቕህ 1,ኣሕካሙል ሓይዲ ወኒፋሳ 2,ሹሩጡ ሰላት ወኣርካኒሃ ወዋጂባቲሃ 3,ሙኽተሰሩ ሲያም ሚን ፊቅሂል ሙየሰር 4,ኣኽጣኡ ለዚ የቀዑ ፊ ባዕዲ ሳኢሚነ ወሳኢማት 5,መትኑ ቓየቱ ወተቅሪብ (ኣቢ ሱጃዕ) 6,መትኑ ቓየቱ ወተቅሪብ (ኣቢ ሱጃዕ) ብሸኽ ሙሓመድ መኪን 7,ዱሩሱል ሙሂማ 📚ኣዳብ 1,ሲፈቱ ዘዉጀቱ ሳሊሓ 2,ተጥሪዙል ወሳኢሉል ሙፊዳ ሊልሓያቲ ሰዒዳ 📚ኡሱሉል ፊቅህ 1,መትኑ ወረቃት 2,ኣል ኡሱል ሚን ዒልሚል ኡሱል 📚ተጅዊድ 1,ተይሲር ፊ ኣሕካሚ ተጅዊድ ➷➴➷ ናይ ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/Alikhlasderstat

ዲን እና እድብቲ ዘለዋ ጓል ምምራዓው ዓወት ንሓደር ቁርፂን ዓንዲን ማእገር ኢዩ መብዛሓትኡ ሰብ ኣብ ላዕሊ ገፅ ዒላማ እና ውሽጣዊ ባህርያት ሸለል ብምባል ኢዩ። መልእክተኛ ዲን ዘለዋ ቀልጢፍካ ተመረዐዋ ዝብል መምርሒ አመሓላሊፎም። ዲን እና አኽላቅ ያላትን ሴት ማግባት የስኬታማ ትዳር ቁርጠኝነትን ምሶሶ እና ማገር ነው አብዛኛው ሰው በውጫዊ ገጽታ ላይ ማተኮር እና ውስጣዊ ባህሪያትን ችላ በማለታቸው የተነሳ ነው። መልክተኛው፦ "…ዲን ያላትን ፈጥነህ አግባ" የሚል መመሪያ ያስተላለፉት። t.me/Tewjihat ©Tewjihat

አንተ ነጋዴ ሆይ! በዚህ የኑሮ ውድነት ወቅት አዛኝ ሁን! ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿التجّارَ يُحشرونَ يومَ القيامةِ فجّارا إلا من اتقّى برّ
አንተ ነጋዴ ሆይ! በዚህ የኑሮ ውድነት ወቅት አዛኝ ሁን! ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿التجّارَ يُحشرونَ يومَ القيامةِ فجّارا إلا من اتقّى برَّ وصدقَ.﴾ “ነጋዴዎች በትንሳኤ ቀን አመፀኞች ሆነው ነው የሚቀሰቀሱት። አላህን የፈራ፣ መልካምን የሰራ እና እውነትን ያወራ ሲቀር።” ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 1458

ኢስላም በመልካም ስነምግባራት ያዛል። በነገራቶች ላይ ጋጥ ወጥነትን፣ አይና አውጣነትን ሳይሆን ቁጥብነትን፣ ጨዋነትን፣ አይናፋርነትን ያስተምራል… ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ لِكُلِّ دينٍ خُلُقًا، وخُلُقُ الإسلامِ الحياءُ.﴾ “ሁሉም እምነት የራሱ የሆነ የስነምግባር መገለጫ አለው። የኢስላም መገለጫው ሐያዓ ‘ዕፍረት’ ማድረግ ነው።” ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 940

ትልቁ ኪሳራ! ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿رَغِمَ أَنْفُ، ثُمَّ رَغِمَ أَنْفُ، ثُمَّ رَغِمَ أَنْفُ ". قِيلَ : مَنْ يَا رَسُولَ
ትልቁ ኪሳራ! ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿رَغِمَ أَنْفُ، ثُمَّ رَغِمَ أَنْفُ، ثُمَّ رَغِمَ أَنْفُ ". قِيلَ : مَنْ يَا رَسُولَ اللَّهِ ؟ قَالَ : " مَنْ أَدْرَكَ أَبَوَيْهِ عِنْدَ الْكِبَرِ، أَحَدَهُمَا أَوْ كِلَيْهِمَا فَلَمْ يَدْخُلِ الْجَنَّةَ﴾ “በአፍንጫው ላይ አፈር ይደፋ፣ አሁንም በአፍንጫው ላይ አፈር ይደፋ፣ አሁንም በአፍንጫው ላይ አፈር ይደፋ። ማንን ነው? አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሲባሉ። እንዲህ አሉ፦ ወላጆቹን ትልቅ ሆነው አግኝቶ አንዳቸውን ወይም ሁለቱንም እነሱን በመንከባከብ ጀነት ያልገባ ሰው።” ሙስሊም ዘግበውታል: 2551

2. #ቆዳዎ_እንደረጠበ_ያቆያል ====== ታላቅ የተፈጥሮ እርጥበት የሚፈጥረው እሬት የራስ ቆዳ ድርቀትን ይከላከላል እና የፀጉር እድገትን የሚያሻሽል ነው፡፡ በጥሩ ሁኔታ የራሰ እና የረጠበ ቆዳ ጤናማ እና ለስላሳ ይሆናል፡፡ ቆዳ ላይ ሲደረጉ በቀላሉ ወደ ቆዳ ዘልቀው የሚገቡ ሲሆኑ የቆዳን የፒ ኤች መጠን ለመመለስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም እሬት ቅባታማ ሆነው እንዲታዩ አያደርግም፤ ይህም ቅባታማ ቆዳ ላላቸው ጥሩ አማራጭ ናቸው፡፡ 3. #ብጉርን_ይቀንሳል ===== እሬት የተፈጥሮ ፀረ ባክቴሪያን የያዘ ሲሆን ብጉር እንዲከሰት የሚያደርገውን ባክቴሪያን ለመዋጋት ይረዳል፡፡ አዲስ ህዋሳትም እንዲያድጉ ያነቃቃል፡፡ በተጨማሪም የማድያት እና የቆዳ መቆጣት የመከላከል ባህርያት ያሉት ሲሆን ቆዳ በፍጥነት እንዲድን እና የቆዳ መቆጣትን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ 4. #በፀሀይ_የተጎዳ_ቆዳን_ያክማል ===== የእሬት የማቀዝቀዝ እና ቆዳን ከመቆጣት የመከላከል ባህርያቶች የቆዳን የፀሀይ ቃጠሎን ለማከም ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የቆዳን የፀሀይ መጎዳት ለመፈወስ አስፈላጊ የሆነውን የቆዳ የእርጥበት ደረጃ ለማቆየት ይረዳል፡፡ እሬት የማይፈለጉ በፊት ላይ የሚወጡ ጥቁረቶችን ይከላከላል። 5.#የፀጉርን_እድገት_ይጨምራል ====== እሬት የእራስ ቅልላይ ሲደረግ ከሌሎች ተፈጥሯዊ ቅባቶች በተሻለ ሁኔታ ወደቆዳ ውስጥ ዘልቆ በመግባት የፀጉር ስር የሚገኙትን ሴሎችን በማነቃቃት ጤናማ እና ረጅም ፀጉር እንዲኖረን ይረዳል። የፀጉር መነቃቀልን እንዲሁም የእራስ ቅል ድርቀትን ተከትለው ለሚከሰቱ እንደፎሮፎር  እና ፈንገሶችን የፀጉር መበጣጠስ እና መነቃቀልን ይከላከላል። 6. #የቁስል_መዳንን_ያፋጥናል  ===== ብዙ ሰዎች እሬት በቆዳ ላይ ቀጥታ በመቀባት (topical use) እንጂ በመመገብ አይጠቀሙበትም።  ጥናቶች አሎዌ ቬራ ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ደረጃ የቃጠሎ ቁሶች (burns) ውጤታማ ህክምና እንደሆነ ያሳያሉ። 7. #የጥርስ_መበላሸት (dental plaque) #ይቀንሳል  የጥርስ ቀለም መለወጥ እና የማስተንፈሻ ችግሮች በጣም የተለመዱ የጤና ችግሮች ናቸው። ከነዚህ ህመሞች ለመከላከል ዋየኛው መንገድ የጥርስ ላይ የሚፈጠረውን ባክቴሪያል ንብርብር (plaque) መቀነስ ነው። 8. #አንቲ_ባክቴሪያል #ባህሪያት_አሉት ====== አሎዌ ቬራ አንቲባክቴሪያል፣ አንቲቫይራል እና አንቲሴፕቲክ ባህሪያት አሉት። ይህም ለቁስል መዳን እና የቆዳ ችግሮችን ለማከም የሚረዳውበት ምክንያት ነው።  አሎዌ ቬራ የተለያዩ የባክቴሪያ ዓይነቶችን (ለምሳሌ *Staphylococcus aureus* እና *Pseudomonas aeruginosa*) እንዳያድግ ይከላከላል። 9. #የአፍ_ውስጥ_ቁስሎችን (canker sores) #ለማከም_ይረዳል  ==== ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የአፍ ውስጥ ቁስሎች (mouth ulcers/canker sores) ይገጥማቸዋል። እነዚህ በተለምዶ ከከንፈር በታች፣ በአፍ ውስጥ ይፈጠራሉ እና ለ1 ሳምንት ያህል ይቆያሉ።  ጥናቶች እሬት የአፍ ውስጥ ቁስሎችን ከሌሎች ሕክምናዎች በበለጠ ፍጥነት እንደሚያዳልስ ያሳያሉ።  ለምሳሌ፣ በ2022 የተደረገ ግምገማ ጥናት (9 የተለያዩ የሙከራ ጥናቶችን በመመርመር) እሬት የአፍ ቁስሎችን በፍጥነት እንደሚያድን እና የህክምና ጊዜን እንደሚቀንስ አረጋግጧል። #አጠቃቀም ☑️እሬት(አሎዌ ቬራን) በፋብሪካ የተዘጋጁ እንደ ጄል፣ ኦንትመንት፣ሳሙና : የአፍ ማጠቢያ(teeth paste) ወይም ፈሳሽ መልክ መጠቀም ይቻላል።  ☑️በቆዳ ላይ ለሚደረግ አጠቃቀም የተክሉን ቀጥተኛ ፈሳሽ(raw juice) በመቀባት መጠቀም ይቻላል። #የጎንዮሽ_ጉዳቶች ===== 👉 የቆዳ ላይ መጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። 👉ከዚህ ተጨማሪ እሬትን ለጨጓራ አሲድ መብዛት : ለሆድ ድርቀት ህክምና በአፍ በመውሰድ የሚያገለግል ሲሆ በአፍ በመዋጥ መጠቀም የሆድ ህመም፣ ምግብ አለመፈጨት ወይም የጉበት ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።  በዚህ መንገድ ለመጠቀም ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል።