ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

ጲንኤል

ጲንኤል

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጲንኤል ...አንዳንድ ጦርነቶች በውስጣችን ይካሄዳሉ። ይህ ቻናል እነዚያ ጦርነቶች በቃላት የሚገለጹበት፣ ሰው ከራሱ ጋር የሚገናኝበት፣ ሀሳብ፣ ትዝታ እና ውስጣዊ ግጭቶች የሚጻፉበት ገጽ። ✍️ እስራኤል ሰይፉ

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
194
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
ምን ስጦታ ልስጣት ብዬ ብዙ ተጨነኩ 🤔 ላንቺ የሚሆን ምንም ላገኝ አልቻልኩም 😞 ሻኪሶ ወርቅ ተይዞ ይኬዳል? 🤔 ...ለውቂያኖሶ ውሀ ይሰጣል? 💧 ያሰብኩት ስጦታ ሁሉ በርበሬ ይዞ ማረቆ እንደ መሄድ ሆነብኝ 🌶️ ቅጠል ለዛፍ እንደመስጠት ልቤን ወይም ፍሴን ብሰጥሽም ጥቅም የለውም 🥀 ሁለቱንም ይዘሻቸዋል..... ስለዚህ ፍቅሬ መስታወት ይዤልሽ መጥቻለሁ ❤️ ራስሽን እያየሽ ሀልጊዜ አስታውሽኝ 😊

እንደ መፍትሔ የሚቀመጡ ነገሮች ወደኋላ ለመዘርዘር እሞክራለሁ 😊

ሰው ለምንድነው እራሱን የሚያጠፋው? ሰሞኑን እራሱን አጠፋ የሚል ወሬ trend ይመስል በየቀኑ መስማት እየተለመደ እየመጣ ነው በግሌም ብዙ እየሰማሁ ነው ጥያቄው ግን ለምን የሚለው ይመስለኛል ለምን እራሳቸው ለማጥፋት ወሰኑ ?¿? እራስን ማጥፋት ብዙ ጊዜ የችግር ማምለጫ ወይንም ካጋጠመን ፈተና መውጫ መንገድ አድርጎ መውሰድ ወንይንም እንደ አንድ መፍትሄ መመልከታችን በጣም እየተለመደ የመጣ መንገድ ነው። የሰው ልጅ እራሱን ለማጥፋት ከሚነሳባቸው የመጀመሪያዎቹ ምክንያቶች አንዱ ለ አእምሮው የሚሰጠው ምክንያት ይመስለኛል አእምሮ አንድን የምንሰጠው ነገር እውነት ነው ብሎ ከተቀበለው ለሱ ያ ነገር ትክክል ይሆናል ለምሳሌ 1+1=2 ነው ይሄ ሁላችንንም የሚያስማማ እውነት ነው ነገር ግን አንድን ሰው 1+1=3 ነው ብለን ካመነው ለዛ ሰው 1+1=3 እንጂ 2 ብሎ በምንም መልኩ አይቀበለንም ስለዚህ ለ ራሳችን የምንወስዳቸውን ነገሮች በጣም መጠንቀቅአለብን። 2 ሰሚ ማጣት( ብቸኝነት ) ይሄ ደሞ ሌላው ለራስን ማጥፋት እንደምክንያት ሊሆን የሚችል ነገር ነው ብዙውን ጊዜ ብቻውን የሚቀመጥ ሰው እራሱን ለማጥፋት በጣም ቅርብ ነው አእምሮአችን ብቻችን ስንቀመጥ ብዙ ነገሮችን ማሰላሰል ይጀምራል ለዛም ነው በተለምዶ በአካባቢያችን ሰዎች ብቻቸውን ከምትሆኑ ውጡና ከሰው ተገናኙ የሚባለው ለብቻ መቀመጥ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን ሲበዛ የሚያስከትለው የአእምሮ ጤና ጉዳት ከባድ ስለሆነ ነው። እንደ 3ተኛ ምክንያት የምወስደው ደሞ የልጅነት ጠባሳ ወንም በሳይኮሎጂው ( early childhood experience )የምንለው ነገር ለዚሁ ምክንያት ይሆነናል በልጅነታችን የምናያቸው እና የምንመለከታቸው እያንዳንዱ ነገር ለዛሬ ማንነታችን አንዱ መሰረት ድንጋይ ናቸው ልጅ ሳለን ያደግንበት አስተዳደግ የነበረን ማንነት እያንዳንዱ እኛ ላይ ተፅእኖ አለው ለዛም ነው ልጆችን በልጅነታቸው ልዩ ክትትል ልናደርግላቸው የሚገባው። እንደ 4ተኛ ምክንያት የምወስደው ደሞ ምርጫ ማጣት ይሆናል የሰው ልጅ ስንባል ነገሮችን በቀላሉ ማለፍ የውስጥ ፍላጎታችን ነው በአቋራጭ ሀብታም መሆን በሆነ መንገድ የሆነ ቦታ ላይ መድረስ ብቻ የሆነ አጭር መንገድ መከተል እንደ አንደ አንድ ቀላል መፍትሄ እየተመለከትን ነው በተለይ ይሄ ያሁኑ ጀነሬሽን ነገሮችን መጋፈጥ በጣም ነው የምንፈራው ያንን ከምንጋፈጥ ቢቀርብን የምንመርጥ ብዙዎቻችን ነን ከዛ ይልቅ ግን አጠገባችን ያለን ሰው ማማከር በገጠመን ችግር ውስጥ ያለፉ ሰዎችን መጠየቅ ነገሩን ከማቅለል በተጨማሪ ብዙ መንገዶችን እንድንመለከት ይረዳናል። ይሄንን ጉዳይ ያነሳሁት ሰሞኑን እያነበብኩ ከነበረው መፅሀፍ ተነስቼና በዚሁ ሳምንት ከገጠመኝ የራሱን አጠፉ ሀዘን ተነስቼ ነው ለማጠቃለል በተለይ ወንድ ልጆች ህመማችንን ደብቀን ማሳለፍ ልምድ ብናስቀር ባይ ነኝ ብዙ ጊዜ ዝምታን መምረጥ እና ከሰው አለማውራት በኋላ ላይ ለከፋ ጭንቀትና እራስን ወደ ማጥፋት ይመራናል ስለዚህ የ ሀገሬ ሰው እንደሚለው “ ሳይቃጠል በቅል” እንዲሆን ነገሩ ሳይረፍድ በፊት እንጠንቀቅ አጠገባቹ ላሉ የቅርቤ ለምትሉት ሰው የገጠማችሁን አውሩላቸው በተቻለ መጠን በውስጣችሁ ለማቆየት አትሞክሩ አውሩላቸው መፍትሔ አታጡለትም ሌላው ደሞ ወደ ፈጣሪያቹ ፀልዩ ከኛ በላይ የሆነን ነገር እሱ ነው የሚፈታልን ወደ ፈጣሪያቹ በየ እምነታችሁ ፀልዩ እሱ መፍትሔ አለውና። ሁላችንም የአእምሮ ጤንነታችን እንጠብቅ እወዳችኋለሁ 😊 ✍ እዝራ

ግቢያችን ውስጥ ያበደ መቀመጫ ያላት የአቅም ማሻሻያ (remedial)ተማሪ ነበረች። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች አሉ ሲባል የሷን መቀመጫ ብቻ መዝግበው ይመስለኝ ነበር። ማን ሚሉት ፀሀፊ እንዳለው "አቦም አይቆጡ ኪዳነምህረት ደጁ ተረማማጅ አይቼው ልሙት" ተብሎ የተገጠመለት መቀመጫ ነበር ያላት። በዚህ በረሀ በሆነ በሚያቃጥል ግቢ ውስጥ የእሷ መቀመጫ ለተማሪው ሁሉ መጠለያ ዋርካ ነበር። እሷን ስታይ ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ሰቀቀን የለም ታድያ፤ ምክንያቱም ሰው ሁሉ እሷ ላይ ስለሚያፈጥ ምን ሰአት አግኝቶ እርስ በእርስ ይተማማል። አንድ ዕለት ቡና ልጠጣ በሚል ተልካሻ ምክንያት ግቢ ውስጥ ወዳለ ቡና ቤት ጎራ አልኩኝ። ዘወትር በዚህ ሰአት ተንቀሳቃሽ ቅርሱ "ለኤግዚቢሽን" ክፍት ሚሆንበት ሰአት ነው። እኔም ቡናውን ወድጄ ወይ ደግሞ እሷን ላይ ቦታው ላይ ታድሚያለሁ። እሷም እግዜር ይስጣት ብዙ አላስጠበቀችንም(ብዙ የኔ ቢጤዎች ነበሩ ፤ተደራጆተን ነበር ምንጠብቃት )አንድ ሁለት ሰአት ቆይታ ብቅ አለች። እውነቱን ለመናገር ከቡናው በላይ የእሷ መምጣት ነበር እንዳለ ህዝቡን ያነቃቃው። እንደው እንደ ሀሳብ እነ ማንያዘዋል የተለያዬ ሀሳብ እያመጡ "ብሮ" ምናምን ከሚሉ እሷን ከጎን አድርገው "ተኙ፣ ምንም ነገር አይቻልም" እያሉ ቢናገሩ ራሱ ህዝቤ ሚነቃቃ ነው ሚመስለኝ። ብቻ እሷ ስትመጣ ሁሉም ፀጥ በሉ የተባሉ ይመስል ሁሉም በተመስጦ እሷ ላይ ማፍጠጡን ተያያዘው። እኔም ጉዱን ልዬው እስኪ ብዬ ቀስ ብዬ ግራ ቀኜን አየሁና (ዳኛም አይደለሁ 😂) ዳሌዋ ላይ አይኔን ሰየምኩ። የሆነ ጎጃምኛ ሚጨፍር ጎረምሳ ከኃላ ያዘለች ነው ሚመስለው። ተንቀጥቅጦ አንቀጠቀጠን እኮ ጎበዝ። ጭኔ አካባቢ የሆነ ነገር እየሞቀኝ ነው። መጀመሪያ ጀግናው ይሆናል ብዬ በቸልታ አለፍኩት እሱስ ዛሬ አይደል ቀን የወጣለት የታባቱ ብዬ ትቸው ነበር። በጣም ሲያቃጥለኝ ጊዜ ምንድን ነው ብዬ ዝቅ አልኩኝ። ለካስ ነጭ ሱሪዬ ላይ የያዝኩትን ቡና እየለቀኩት ነበር ወይኔ ሰውዬው ብዬ ስኒውን ቀና አድርጌ ዕድሉ እንዳያመልጠኝ ተጣድፌ አይኔን ወደሷ መለስኩት። ደግነቱ ያዬኝ አልነበረም እነሱ ሱሪ ላይ እንኳ ብለቀው ማንም ዞር ብሎ አያዬኝም። ሞንደል ሞንደል እያለች ስትመጣ ሳይ የስንት ዘመን የሳይንስ ግኝትን ፉርሽ እንዳደረገችው ልብ አልኩኝ። ማን ነበር "ምድር በፀሀይ ዙሪያ ትዞራለች" ያለው?  የለም የለም ምድርማ ምትዞረው በዚች ልጅ መቀመጫ ዙሪያ ነው። እሱን ብሎ ተመራማሪ ። ይሄ ቅሪላ ሳይንቲስት ትክክል ሚሆነው የዚች ልጅ ስም ፀሀይ ከሆነ ብቻ ነው mr.x ይሙት። ቡና ምታፈላው ሴት እንኳ ከንፈሯን ነክሳ ልጅቱን እያዬቻት ነው። ይሄኔ ዕድሏን እያማረረች እኮ ነው። ለምን እግዜር በመቀመጫ ፋንታ ጉንጭ እንደሰጣት ትንግርት ሆኖባት ይሆናል። ይሄኔ እግዜር ለእኔ የእንጀራ አባቴ ነው እንዴ እያለችም ይሆናል። ዞር ብዬ ህዝበ አዳምን ሳዬው ክተት የተባለ ሰራዊት ይመስል በተጠንቀቅ ነቅቶ የሷን መቀመጫ እያየ ነው። ሚኒሊክ አድዋ ላይ ህዝቡን አንድ አድርጎ ካዘመተ ዘመናት በኃላ ከአራቱም አቅጣጫ የመጣ ኢትዮጵያዊን አንድ ሚያደርገን ነገር ተገኘ፣ የሷ መቀመጫ!!! የዚህኛው ልዩነቱ ባልተነገረ አዋጅ እና ባልተነፋ ጥሩንባ ነው የዘመተው ህዝቡ። አዋጁም ጥሩምባውም የሷ መቀመጫ ነበር። ዞር ብዬ ከጎኔ የተቀመጠውን ሰው ሳይ እሱም እንደኔ ሲያያት ኖሮ አይን ለአይን ተገጣጠምን "ሰላም ነው" አለኝ "ሰላም" አልኩት። ከዚህ በፊት ግቢ ጎሪጥ (በአይን ቂጣችን) ነበር ምንተያዬው። እኔ በበኩሌ "ሙሴ" ብየዋለሁ። ለምን አትሉኝም ባህር ባይከፍልም ይሄው ልባችንን ከፍሎ አንድ አርጎናል። ጀግናው የድር ድንኳን መሰሎ ቁጭ አለ ቀስ ብዬ Flight mode አድርጌ(እኛ ወንዶች ነው ምናቃት😂) የጀመርኩትን ቡና ጨርሼ ወደ ዶርሜ ተመለስኩ።

ከአባት የተሰጠ ምክር ለልጅ ! ልጄ ሆይ፣ በጣም ግልጽና ያልተሸፋፈነ ነገር ነው የምነግርህ!! ስለ ሴት መቀመጫ ወይም ጡት መጠን አትጨነቅ፤ ነገር ግን ስለ ልቧና አእምሮዋ መጠን ተጨነቅ። ስለ ፍቅሯና ስለ ትዕግስቷ መጠን ተጨነቅ። ምክንያቱም ከአምስት ወይም ከአሥር ዓመት በኋላ ዋናው ነገር ጡት ወይም መቀመጫ አይሆንም። እንደምታየው፣ እናትህ አሁን ጠፍጣፋ ደረትና ጠፍጣፋ ለማለት የሚቻል መቀመጫ ነው ያላት፤ ነገር ግን አሁንም በደስታ አብረን እንኖራለን፣ አሁንም እወዳታለሁ እሷም አሁንም ትወደኛለች። ገንዘብ የምትወድ ሴትን ተጠንቀቅ። ማለቴ 'ሁልጊዜ' ስለ ፀጉሯ፣ ልብሷ፣ ጫማዋ፣ ቦርሳዋ፣ የውስጥ ልብሶቿና ሜካፕ የምታወራ ሴትን ነው። ጋብቻ ሙሉ በሙሉ ስለ እነዚህ ነገሮች አይደለም። ያለ ሜካፕ፣ ልብስ፣ ጫማና የውስጥ ልብስ ጥሩ ትዳር ይቆማል፤ ነገር ግን ያለ ፍቅር ምንም ትዳር ሊቆም አይችልም። እናትህን ሳገባ መኪናም ሆነ የራሴ ቤት አልነበረኝም። የተማርኩም እንኳን አልነበርኩም። ነገር ግን ህልሞች ነበሩኝ እሷም አደንቃ ደግፋኛለች። ህልምህን የማትደግፍ ማንኛዋም ሴት ለአንዲት ደቂቃ እንኳ ልታስብላት አትገባም። ካንተ በተሻለ ህልምህን የሚያዩ ሴቶች አሉ፤ አንዷን ካገኘህ እድለኛ ነህ! ልጄ ሆይ፣ ጆሮህን በደንብ ክፈት፤ ልትርቃት የሚገባ አይነት ሴት አለች፤ እንዲህ አይነቷን ሴት የማግባት ስህተት እንዳትሠራ፤ አለበለዚያ ትጸጸታለህ። ማለቴ ሁልጊዜ ስለ ሁሉም ሰው መጥፎ ነገር የምትናገር ሴት ናት። እንዲህ አይነቷን ሴት ካየህ ሽሽ። ልታገባቸው ከምትችላቸው እጅግ መጥፎ ሴቶች መካከል አንዷ ስለ ሁሉም ነገር የምታማርር ናት። ይህን ከገዛህ ያኛውን መግዛት ነበረብህ ትላለች፤ ይህን ካደረግክ ያኛውን ማድረግ ነበረብህ ትላለች። እባክህን ራቅ! አብዛኞቹ ሴቶች ማውራት ያስደስታቸዋል፤ ነገር ግን ለሁለት ሰዓት አውርታ ለሁለት ደቂቃ የምታዳምጥ ሴት ለወደፊቱ 'አደጋ' ልትሆን የምትችል ናት። ብልህ ሁን! አስመሳይ አጋርን በጣም ተጠንቀቅ። አስመሳይ ሴትን ማወቅ ከባድ አይደለም። ሁልጊዜ ስለ ሁሉም ነገር ሁሉን አውቃለሁ ትላለች፤ ጥንቁቅ ትሆናለች። አይንህን ዝም ብለህ ዝጋና ልብህን ክፈት፤ ታያለህ! ፍጹም የሆነች ሴት የለችም። በህልምህ የምታምን፣ የምታከብርህ፣ ቁርጠኛ የሆነች እና ስለ ራሷ ብቻ የማታስብ ሴት ካገኘህ አትልቀቃት። ነገር ግን አስታውስ፣ አንተም ባለጌ ወንድ መሆን የለብህም። አሰልጥኜሃለሁ! ጥሩ ሴት አግኝተህ አንተ ግን መጥፎ ወንድ ከሆንክ ጥሩ ትዳር አይኖርህም! ሚስት አልመርጥልህም፤ ነገር ግን ምክሬን ሰጥቼሃለሁ። ስታገኛት ለምርቃቴ አምጣት። የምትጨምርልህን እንጂ የምትቀንስብህ ያልሆነች ሴት ያጋጥምህ .. ስለጋብቻ አባት ለልጅ የሰጠው ምክር!

የሴት ልጅ ነኝ ሴት ወልዶ ሴት ያሳደገኝ ‎የሴትን ክብር ከሴት እናቴ የተማርኩ ሙሉ ሴት ‎ታሪኬ እንዲ ነበር አባቴን ያጣሁት ገና የቅፍ  ልጅ ሁኘ ነው። ከስሙ እና ከጠይም ቆዳ ዉጭ ሌላ ከሱ አላውቅም ሙሉ ለሙሉ የናቴ ልጅ ነኝ ‎ ‎አግቢ ቢሏት አሻፈረኝ ለምን ልጄ የሠው አባት ታያለች ብላ ትኩስ ስጋዋን ውበቷን ማቅ አልብሳ ነው ያሳደገችኝ ‎ግን  ቀላል አልነበረም። ‎ላለማግባቷ የደነቀው ህዝቤ ምን ይላታል ‎ ሟች ሞቱ ሲገባው አስተብትቦባታል ፤ ‎ሌላ አግብቼ ቢሞትስ ብላ ነው ገደ ቢስ ናት ፤ የዘመኑ በሽታ አለባት፤ ልጇ አመሏ ግም ነው ምን ያላሏት አለ በነፃነት እንድትወሰልት ነው ያላትን ቤት ይቁጠረው ‎ይሄ ሁሉ ልጄን  ላሳድግ ባለች ስጋዋን በቀጣች ፤ በተራቦች ፤ በተጠማች ፤ ብዙ አሏት ‎ለምለም ፊቷ በእንባ እርሶ ፀሐይ የነካው እደሁ ጥቁር ማህተም ጉንጮቿ ላይ ይታተማል ‎ ‎ያኔ ".....እ...... ታብሌቱ እቺ ወስላታ ‎ኧረ ስንቱ ‎አብባ ሳታበቃ የከሠወችዋ እናቴን የሚያስጨንቁ ሴሰኛ ባለጌዎች ሂወቷን የበለጠ ሲኦል አረጉባት ‎ ‎እናቴ ማለት  ለኔ ሲኦል የታጠረች   የገነት ቦታየ ናት ‎ ‎ከዛ.......ይሄ ባለ ባለጌ ወና አፍ ሠፈርተኛ ‎እኔን ምን አለኝ ‎"የሴት ልጅ "አወ የሴት ልጅ ነኝ ማን ነው ስድብ ያረገው ‎የአንድ  ቆንጆ እድሜ የተገበረልኝ የሴት ‎ልጅ ነኝ እንደ እየሱስ ❤️‍🩹የሴት ልጅ ነኝ ። ‎ ✍️ድንቡሎ

በመካከለኛው ዘመን ይጠቀሙበት ነበር ተብሎ የሚነገር የቅጣት መሣሪያ ነው። "Shrew’s Fiddle" በመባል ይታወቃል። ሁለት ሰዎች በተደጋጋሚ ሲጣሉ ፊት ለፊት በዚህ መሣሪያ ውስጥ ያስቀምጧቸው እን
በመካከለኛው ዘመን ይጠቀሙበት ነበር ተብሎ የሚነገር የቅጣት መሣሪያ ነው። "Shrew’s Fiddle" በመባል ይታወቃል። ሁለት ሰዎች በተደጋጋሚ ሲጣሉ ፊት ለፊት በዚህ መሣሪያ ውስጥ ያስቀምጧቸው እንደነበር ታሪካዊ መረጃዎች ያሳያሉ። ዓላማውም ግጭታቸውን እንዲያቆሙና እንዲስማሙ ማድረግ ነበር ተብሎ ይገለጻል። ይህ ታሪካዊ መረጃ ነው የዛሬን እሴቶች ወይም አመለካከቶች አይወክልም። እርስዎ ስለዚህ ምን ያስባሉ? 🤔

የአንዳንድ ሰው ጠላቱ ጭንቅላቱ ነው🙌 መልካም ሰንበት😊

ዝም ብሎ ብቻዬን ያስቀኛል ዛሬ 3ቀን ሞላኝ ችግር የለውም አይደል 😭

ህእ! +++++++ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ትዳር ነው። ባል ስቅታ ይዞታል። ከነጋ ለሶስተኛ ጊዜ እንደ አዲስ ሲጀምረው ክፉኛ ተበሳጨ። “አረ ማናባቱ ነው ስሜን ሲያነሳና ሲጥል የዋለው? ህእ! ” አለ ለሚስቱ። “ስኳር ቃምክበት?” አለችው። “አዎ።” “ደረቅ እንጀራ በላህበት?” “ህእ! አዎ” “ቀዝቃዛ ውሃ ጠጣህበት?” “አዎ” "በረዶ ያለው?" "ህእ! አዎ አልኩሽ እኮ" “እሺ ትንፋሽህን ይዘህ ሞከርከው? ” “አዎ ” “እና አሁንም አልቆመልህም?” “ህእ! አልቆመልህም? እያየሽኝ አይደል? አሁንም እያነቀኝ? ህእ! " ትኩር ብላ አየችው። ከቅድሙ አሁን ንጭንጭ አብዝቷል። “እንጃ እንግዲህ” አለች። “እስቲ የፈረደበትን ቻት-ጂፒቲን ሌላ መፍትሄ ጠይቀው?” “አይ! እሱማ ‘ልትሞት ነው’ ብሎ ነው የሚያስበረግገኝ። ህእ! ካንሰር ነው ምናምን ብሎ ቆሌዬን እንዳይገፈው። ጉግል ይሻለኛል።” “እሺ ጉግል አርገዋ” ስልኩን አነሳ። በፍጥነት ተየበ። የስልኩ ሰማያዊ ብርሃን ፊቱ ላይ አርፎ ይታያል። ህእ! ህእ! ህእ! “ኦ!” አለ ከደቂቃዎች በኌላ። “ምነው? ምን አለህ?” ጠየቀችው “ለካስ ያልሞከርኩት ነገር አለ” “ምንድነው?” “ብነግርሽም አታምኚኝም” “ተናገር እንጂ። ለምንድነው ማላምንህ?" “መፍትሄው ላይ ትረጂኛለሽ?” “እንዴ! የምችለው ከሆነ ለምን አልረዳህም? ቀኑን ሙሉ አሸህ እኮ! ድምፅህ ራሱ ያሳዝናል፤ በዛ ላይ ነገ ስራ ነው። በጊዜ መተኛት አለብን።” ዝም ብሎ ቆየ። ከዚያ ደግሞ ህእ! አለ። "ንገረኝ እንጂ" “ያ ነገር ስቅታን ቶሎ ያስቆማል ይላል” አላት። ጮክ ብላ ሳቀችና... “አትለኝም?!” አለችው በለበጣ። “በእውነት!" " አታሹፍ" " እውነቴን ነው ስልሽ?" " ውይ አንተ! ቀልድና ቁምነገርህ አይለይ!" " እውነቴን ነው እያልኩሽ?" “አንተ ከምር አንበበኸው ቢሆን እንኴን አንድ ሰው ለቀልድ የጻፈው ይሆናል ።” “አይደለም፤ ‘ስዊዲሽ ጆርናል’ ነው ይላል፤ ሳይንሳዊ ጥናት ነው። ህእ!" “በእውነት?” “እውነት" አስተዋለችው። መኝታ ክፍላቸው ያው እንደተለመደው ነው። ሰላላ ብርሃን፣ አልጋ፣ ልብስ የተከመረበት ወንበር... “የሚገርም ነው” አለች ሰረቅ አድርጋ እያየችው። “እሱስ አዎ። ህእ! እና ታዲያ...?” አላት። ተጠጋችው። የሚደረገውን ካደረጉ በኋላ... ትሄዳለች ብሎ የሰጋ ይመስል እርቃን ገላዋን ከእርቃን ገላው አጣብቆና አጥብቆ አቀፋት። ፈገግ ብላ አየት አደረገችውና፣ “እሺ በል፤ ደህና እደር የኔ ጌታ” አለችው። “ደህና እደሪ የእኔ እመቤት” መለሰላት። “ሳመኛ” ሳማት። ጀርባዋን ሰጥታው ተኛች። ከኋላዋ አቀፋት። “ባሌ..” አለች ፀጉሯ ውስጥ ተደብቆ ሙቅ ትንፋሹ በአንገቷ በኩል ሽው ሲላት ደስ እያላት። " ሚስቴ" “ኢንተርኔቱ ምንም ይበል ምን” አለች ፊቷም ባዞረችበት ፈገግ ብላ። “በበኩሌ ስቅታ ስላስቸገረህ ደስ ብሎኛል።” ከት ብሎ ሳቀ። ተቃቅፈው ባሉበት ብዙ ደቂቃዎች በዝምታ አለፉ። ከዚያ ግን ባል እንዲህ ብሎ ዝምታውን ረበሸ.... "ህእ!"

አይሁኔ የሆነው... (✍️እስራኤል ሰይፉ) ''...ጨረቃ ታሰክራለች ማለት ነው?...'' አልኩኝ ለራሴ ...አጠገቤ የተቀመጠው ሰው የሚያወራው ነገር ከዚህ በፊት የመጋቤ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ መጽሀፍ ላይ ካነበብኩት ጋር ስለተመሳሰለብኝ። ...ከቃሊቲ ወደ አየር ጤና እየሄድን ነው። ራሴን ትንሽ ያዝ ስላደረገኝ በተቻለኝ አቅም ከሽታ ለመራቅ እያሰብኩ ነበር ወደ ታክሲው የገባሁት። ገና ቁጭ ከማለቴም መንገድ ላይ ስለሚገጥመኝ ሽታ እያሰብኩ... "...እንዴት ብዬ ነው ቻይና ካምፕ ጋር ሳልደርስ ያለውን የቆሻሻ መጣያ ቦታ ሽታ የምቋቋመው..?'' የሚል ምናባዊ ሽታ... ድባቴው አላስቀምጥህ ብሎኛል። ምንም ነገር ይለመዳል ሽታ ግን በፍጹም አይለመድም ብዬ ነበር የማስበው ይህን ቦታ እስካይ.... ይህ ሽታ የሸተተኝ የመጀመርያው ቀን እንዲህ ነበር... ወደ አየር ጤና እየሄድኩ በቆሻሻው መጣያ በኩል እያለፍኩ ልክ ቆሻሻ መጣያው ጋር ልንደርስ ስንል የሆነ ሆድና ጀርባን የሚገለብጥ... አፍንጫ ቢያዝ እንኳን በአይን የሚገባ... አስቀያሚ የማይገልጸው ሽታ ጀመረ። ምን ሽታ ቅርናት እንጂ... "... ኤጭ...'' ብዬ እየተበሳጨሁ አፍንጫዬን ያዝኩና መስኮት ያልተዘጋ ካለ በአይኔ ማተርኩ። ነገር ግን አንድም ክፍት መስኮት አይታይም። በየት በኩል እንደሚገባ ግራ እየገባኝ ሰዉን ሳስተውለው አንድም አፍንጫውን የያዘ የለም። ሁሉም በየፊናው ወሬውን ይሰልቃል። ...ግራ እየተጋባሁ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩኝ። እየቀረብን ስንሄድ ሽታው ሊያስቀምጠኝ አልቻለም። ጭራሽ ያቅለሸልሸኝ ጀመር። አለርጂ ስላለብኝ አንዳንዴ ያስነጥሰኝስል። ግራ ሲገባኝ በለበስኩት ጃኬት ሙሉ ፊቴን ከለልኩት። ወይ መከለል ሙሉ ፊቴን ቀርቶ ሙሉ መኪናው ቢከለል ሚቀር አይመስልም። ሰዉ ግን ተስማምቶታል መሰል አንድም የሚከልል የለም። ... ከዛን ቀን በኋላ ግድ ካልሆነብኝ በስተቀር በዛ በኩል ማለፍ አልወድም። ያንን ሽታ ፍራቻ አብዝሀኛውን ጊዜ በሜክሲኮ ነው የምዞረው። ... ዛሬ ግን እቸኩላለሁ ብዬ ብገባም የዛን ቀን ማቅለሽለሽ እየታወሰኝ እንዴት እንደማልፈው አስጨንቆኛል። በዚህ ሁናቴ ሳለሁ ነው አጠገቤ መጥቶ ቁጭ ያለው። ... ለብርድ ብሎ ወፍራም ካፖርት የደረበ ቢሆንም ሙቀቱ አላስቀምጥ ብሎት አስሬ እያወለቀ መልሶ ይለብሰዋል። ደርቦ ስለለበሰ እንጂ ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ተክለ ሰውነት አለው። በርግጥ ቀርቦ ላላስተዋለው እምብዛም ቅጥነቱ አያስታውቅም። እድሜው ወደ 48 አመት ይገመታል። (ቀጫጫ ስለሆነ ከዛም ሊበልጥ ይችላል) ድንገት ወደኔዞሮ ወሬ ሲጀምር ሸበት ባለ ቅንድብ ሊከለል ያለው አይኑን አየሁት። በርበሬ መስሏል። ከነጭ እና ጥቁር ሽፋሽፍቱ ውስጥ ቀልቶ ሲታይ... ወፍጮ ቤት ደክሞ የወጣ ፈጪ አስመስሎታል። (ልጅ እያለሁ ወፍጮ ቤት ገብቼ ዱቄቱ ሽፋሽፍቴን እንዲያነጣው እፈልግ ነበር ከሌሎች አይቼ) ...ምን ሆኖ ነው ብዬ ከማሰቤ ነበር ሽታውን የታጠንኩት። (ደግሞ ሌላ ትኩሳት...) ...ስለ ስካር ነበር የሚያወራኝ (ያው መቼስ ለኔው ነው) ብቻ እሱ ያውራ እንጂ ላዳምጠው አላዳምጠው ግን ግድ ያለው አይመስልም። ምን አልባት ታክሲ ውስጥ ከመግባቱ በፊት "...ስትጠጣ እና ሳትጠጣ ትለያያለህ'' ያለው ሰው እንዳለው ያስገምታል ወሬው። አልኮል መጠጣት ስለሚያመጣው ለውጥ ነው የሚያወራው። ...እንኳን ተወርቶልኝ እንዲሁም አድምጥ አድምጥ ይለኛል። ከልቤ ማድመጥ ጀመርኩ... ''መጠጥ ሰው የሌለውን ነገር ከየት ያመጣዋል?... እ..? '' መልስ ሳይጠብቅ ይቀጥላል። "...ሁሉም ሰው ሲጠጣ ያለው ጠባይ ነው የበለጠ የሚጨምር። እንጂማ ከየት ያመጣል?... አልኮል በራሱ ምን ይፈጥራል?...ምንም! ያለውን ይጨምራል እንጂ። '''እገሌ እኮ ሲጠጣ ቸር ነው ምንም አይሰስት..' ሲባል ሰምተህ አታውቅም?...'' አፈጠጠብኝ። "..መስጠትን የሰጠው ስካር እንዳይመስልህ። ድሮም ሰጪ ነበር። ሲጠጣ ግን ይበልጥ ሰጪ ሆነ። ሀሳብህን ነው የሚያወጣው መጠጥ። የሞት ታናሽ ወንድም እንቅልፍ እንደሆነ ሁሉ... ስካርም የእብደት ታናሽ ወንድም ነው... ምን አልኩኝ? የእብደት ታናሽ ወንድም። ..አው... እብድ ከጤነኛ የሚለየው በምን ይመስልሀል?...'' አፈጣጠጡ ሲያስፈራ። በአስተሳሰቡ ልለው ብዬ ግን ምንም አልመለስኩለትም። መልስ እሚፈልግ አይመስልም። ቀጥሏል.... ''... እብድ ከጤነኛ የሚለየው በአስተሳሰቡ እንዳይመስልህ። አስተሳሰብ እብድ ቢያሰኝማ ማንም ጤነኛ የለም። እብድን እብድ ያሰኘው ድርጊቱ ነው። ቀላል ምሳሌ ልስጥህ... አንድ እብድና አንድ ጤነኛ ሰው አብረው ሰው ቤት ገብተው ተቀምጠው ሁለቱም ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ ምግብ ቢያዩ... ሁለቱም መመኘታቸው አይቀርም። ልዩነቱ ግን ጤነኛው ረሀቡን በይሉኝታ ሸብቦ ቁጭ ሲል እብዱ ግን ተነስቶ ይበላዋል። አየሀ ልዩነቱን? ስካርም እንዲሁ ነው። በፍላጎት ጊዜ ወስኖ ማበድ። ስትሰክር ታድያ ውስጥህን ነው የምትከተለው። ውስጥህ መስጠት ካለ ትሰጣለህ.... ውስጥህ መሳደብም ካለ ትሳደባለህ... መግደልም ካለ.... ሰዉ ወንጀል ሰርቶ ፍርድ ቤት ዳኛፊት ቀርቦ '..ለምን ደፈርክ...' ሲባል '...በሰአቱ አልኮል ጠጥቼ ስለነበር እንጂ አስቤ አላደረኩም...' ምናምን ሲል እውነት እንዳይመስልህ። በርግጥ ጥሩ ምክንያት ቢመስልም ግን በደምብ ነው አስቦ ያደረገው። መጠጡ ሀይል ነው የሆነው። ከፍሎ ስላበደ ያሰበውን እንዲያደርግ ፈቀደለት። አልቃሻ ሰውም እንዲሁ ነው። ሰክሮ አይደለም ያለቀሰው... ውስጡ ነው... ብሶቱን መጠጥ ቀስቅሶት..." ''...ጨረቃ ታሰክራለች ማለት ነው?...'' አልኩኝ ለራሴ ... ሰውዬው የሚያወራው ነገር ከዚህ በፊት የመጋቤ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ መጽሀፍ ላይ ካነበብኩት ጋር ስለተመሳሰለብኝ። ጨረቃ በውሀ ላይ ያላት ሀይል በጥልቀት ታትቷል በመጽሀፉ። በተለይም ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ማዕበል የማስነሳት አቅም እንዳላትና ይህንን ኹነት በባህር ዳርቻ ላይ የሚኖሩ ሰዎች በደምብ ያስተውሉታል። የሰው ልጅም 75% የሚሆነው ሰውነቱ ውሀ ስለሆነ ሙሉጨረቃ ስትሆን የጸባይ መለዋወጥ ይታይበታል ይላል መጽሀፉ። ተናዳጅ የነበረ ሰው ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ይበልጥ ተናዳጅ... ተነጫናጭም ከነበር ይበልጥ የሚነጫነጭ... አፍቃሪም ሰው ጨረቃ ስትሞላ ይበልጥ እንደሚያፈቅር... እና በሌላው ጊዜ የሚሰማንና የምናደርገው ድርጊት ጨረቃ ሙሉ ስትሆን ከሌላ ጊዜው የላቀ እንዲሆን ያነበብኩትን አሁን ሰውዬው ከሚናገረው የመጠጥ ንግግር ጋር ስለተገናኘብኝ ይህንንም እያሰላሰልኩ ሰውዬው የሚያወራውንም እያደመጥኩ አየር ጤና ደረስን... ... ምናለ መንገዱ ባያልቅ ነው ያሰኘኝ የሰውዬው ንግግር። ታድያ ስደርስ ትዝ ያለኝ የሽታው ነገር። ያኔ ሲሸተኝ ሰውን ያልሸተተው የመሰለኝ ለካ በየፊናው የየራሱ አለም ውስጥ ስለነበር ነው። የግድ እንዳይሸተን መሳጭ ሀሳብ መኖር አለበት ማለት ነው? ወይንስ ለምጄው ነው? አይሆን የለ መቼስ። ለምጄው እንኳ ሊሆን አይችልም። ሁሌ እየሸተተኝ ስንት ያለመድኩት ሽታ እያለ በስንት ጊዜ አንዴ የሚሸተኝን እንዴት?... ይህ እየገረመኝ ሰውዬው ''...እኔም እንዲህ ያልኩህ ወድጄ እንዳይመስልህ... ትንሽ ትንሽ እፈላሰፍ ነበር ያው....'' ብሎኝ ወርዶ ሄደ። https://t.me/Oct13wed

#ጥያቄ አንድ በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ ላለ ወጣት ምን አይነት የህይወት ምክር ትሰጡታላቹ?

....20ዎቹ ወይም 30ዎቹ እድሜ ውስጥ ነህ? ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ “ህይወቴ ዘግይታለች” የሚል ስሜት ይሰማሀል? ዙሪያህን ስትመለከት ሁሉም ሰው የህይወቱን መንገድ ያገኘ ይመስልሃል… አንዱ ቢዝነስ ከፍቷል… አንዱ ተጋብቷል… ሌላው አለምን ይዞራል… ሁሉም ደስተኛ፣ ውጤታማ፣ የተሳካላቸው ይመስሉሀል… አንተ ግን እዛው ቆመህ ራስህን “ገና ጊዜ አለኝ…” እደርስባቸዋለህ ብለህ ለማሳመን ትሞክራለህ። ግን ውስጥህ አይቀበልህም… ውስጥህ አልፎብሀል የሚል ጩሀት ያስተጋባል ..... ወንድሜ… ችግሩ ከአንተ አይደለህም። ችግሩ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርህ ነው። Social media ላይ የምታየው ሙሉ ህይወት አይደለም… ሰዎች የሚያሳዩህ ድሎቻቸውን....ስኬታቸውን ብቻ ነው… እንባቸውን፣ ውድቀታቸውን፣ ጭንቀታቸውን አያሳዩህም። በ 23 አመቱ ድርጅት የከፈተውን ወጣት ታያለህ… ከ6 ወር በኋላ መክሰሩን ግን አታይም። በ25 አመቷ አለምን ስትዞር ታያታለህ… በእዳ እንደምትኖር ግን አታውቅም። በ27 አመታቸው በደማቅ ሰርግ የተጋቡትን ጥንዶች ታያለህ… እርስ በእርስ ቀስ ብለው ያለ ጭቅጭቅ መነጋገር እንደማይችሉ ግን አታይም። ወዳጄ… አንተ ዘግይተህ አይደለህም። ህይወት ውድድር አይደለችም። 20ዎቹና 30ዎች “ሁሉን ነገር መጨረሻ” ሳይሆን ሁሉን ነገር የመጀመሪያ ፣ የመሞከሪያ ፣ የመውደቅ፣ የመነሳት ዘመን ናቸው። 20ዎቹን አልፈህ .... በ30ዎቹ መጨረሻ ስራህን ልታገኝ ትችላለህ… በ40ዎቹ ደሞ ራስህን ልታገኝ ራሰህን ልታውቅ ትችላለህ… በ50ዎቹ ፍቅር ውስጥ ልታገባ ትችላለህ… ምንም “ትክክለኛ የህይወት ሰዓት” የሚባል የለም። ላንዱ ቀድሞ የተሳካለት ላንዱ በእስተርጅናው ሊሳካለት ይችላል። ማምሻም እድሜ ነው....የማታ እንጀራ ይስጠኝ የሚባለው ፀሎት የሚፀለየው ለዚህ ነው። ስለዚህ… ዛሬ ከሌሎች ህይወት ይልቅ የራስህን ጉዞ አክብር። ቀስ ብለህ ብትሄድም እየተራመድክ ነው። ውድቀትህ መጨረሻህ አይደለም… የዛሬ ውድቀትህ ለነገ ስኬትህ ምክንያት ነው። አንተ የማትረባ ሰው አይደለህም… አንተ በሂደት ላይ ያለህ ጠንካራ ብርቱ ሰው ነህ!! ፈጣሪ ሀሳብህን በሙሉ ያሳካልህ፣አግኝቶ ከማጣት ይሰውርህ...አሜን 🙏❤❤❤❤

#ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ወደ ሂወትህ ሲመጡ እነዚህን ሶስት ነገሮች አስብ 1. እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደነበር 2. እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ 3. ነገም ሁሌም እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደሚኖር❤️

''የልደትህ ቀን እና የምርቃትህ ቀን አንድ ስለሚሆን ያንተ ምርቃት ከሌሎቹ ተመራቂዎች ለየት ያለ እና ድርብ ደስታ ነው የሚሆነው..'' አልኩት ከአመታት በፊት በወሬአችን መሀል ድንገት ስለ ምርቃት ተነስቶ ስናወራ። ታድያ ልክ የምረቃ ቀን እንደደረሰ ደወለና እንዲህ አለኝ... ''...እስራ ግን ምን ታይቶህ ነው ያኔ እንደዛ ያልከኝ?...." " ምኑን.." አልኩት። ስለምን ማውራት እብደፈለገ ግልጽ እስካልሆነልኝ ድረስ የገባኝ ቢሆን እንኳ ነገሩን ግልጽ እንዲያደርገው ሙሉ እድሉን ለመስጠት። "...ያኔ የልደትህ ቀን ከምረቃህ ጋር አንድ ይሆናል ያልከኝን ነዋ... ወይንስ ማጫጫስ ምናምን የጀመርከው ነገር አለ? ከሆነ ለይልን.." ከት ብዬ ነበር የሳቅኩት። አንዳንዴ የልባችን የሆኑ ሰዎች የሌለንን ነገር እንዳለን አድርገው ሲያወሩን ምን ባያስቅ እንኳ አለመሳቅ ይከብደናል። ስቄ ሳበበቃም ''... ልደትህ ሰኞ አይደል እንዴ? ምርቃትህ ደግሞ ማክሰኞ..መች አንድ ላይ ሆነ?" ''..ጭራሽ አንድ ቀንም ይሁንልህ? ከዚህ በላይ ምን ይሁንልህ? አንድ ያልሆነውም ደግሞ ፈጣሪ ባወቀ ነው። ሊጠብቅህ። እንጂ ይህን ጫፍ ይዘህ ሌላ ነገር ልትጀምርብን? ሆሆሆ..'' ...ሀይስኩል ካገኘኋቸውና የዛን ጊዜን ሳስታውስ ከተማርኩት ትምህርት በላይ ቀድመውና ደምቀው ከሚታዩኝ ወዳጆቼ አንዱ አብርሽ ነው። በተለይ 12ተኛ ክፍል ከያብ እና ከአብርሼ ጋር ያሳለፍናቸውን ነገሮች መቼም አልረሳቸውም። አብዝሀኛው ወዳጅነትና ጓደኝነት ጊዜ እና ቦታ በተራራቀ እና በሄደ ቁጥር ጥላቸውም ይደበዝዛል። የሰው ልጅ ሕይወት እንደ አንድ ረዥም ጉዞ ነው። በአንድ ዘመን የምናገኛቸው ጓደኞች በሕይወታችን የፀደይ ወራት ውስጥ እንደሚያብብ አበባ የሕይወታችንን ማማር እና ጉልበት የሚሰጡን ናቸው። በዚያ የጉርምስና እና የተስፋ ዘመን አንድ ላይ የሳቅንበት ያለቀስንበት እና የሕልም ማማ የገነባንበት ጊዜ ለልባችን እጅግ ቅርብ ነው። ሆኖም በትምህርት ሆነ በሌላ ወደየራሳችን የሕይወት ጎዳና ስንሰማራ፣ የቦታ መራራቅ የጓደኝነትን መውጫ በር ይዘጋው ይመስላል። የጓደኝነት ምስጢር ያለው በስጋዊ ቅርበት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ትስስር ውስጥ ነው። እውነተኛ ወዳጅነት እንደ አንድ የተገጠመ የሙዚቃ ዜማ ነው ድምፁ ቢራራቅም የዜማው ስሜት ግን በውስጥ ይቀራል። ሆኖም የምንለያይበት ዋናው ምክንያት የጊዜ መራራቅ ሳይሆን የልብ መዘንጋት ነው። ሕይወት በኃላፊነት ስትወጠር የየዕለቱን ትግል ስንታገል። ቀስ በቀስ የዚያን የቀድሞ የጋራ መንፈስ እያጠፋን እንሄዳለን። የሚያጠፋፋን ነገር ቢኖር በውስጣችን የሚፈጠረው የግዴለሽነት መጋረጃ ነው። ለረጅም ጊዜ ካልተገናኘን በኋላ "ምን ይሆን የሚለኝ?" ወይም "የሚቀየም ይሆን?" በሚል እሳቤ የምንፈጥረው የስነ-ልቦና እንቅፋት፣ ትናንት በአንድነት የነበርንበትን ድልድይ እንደ ገመድ እንዲበጠስ ያደርገዋል። ይህን አይነት ቸልተኝነቴን አይተው በፊት የነበረንን አጠናክረው ካቆዩልኝ ወዳጆቼ አንዱ አብርሽና ያቡ ናቸው። ጊቢ ውስጥ የሆነ ነገር ልገዛ ፈልጌ ብር ከጎደለኝ ልክ አብረውኝ እንዳሉ ሁሉ አምጡ የምላቸው ያብንና አብርሽን ነው። ከዛ ባለፈ የጊቢ ጓደኞቼ (እነሱ እንኳ አብረውኝ ስላሉ ግዴታቸው ነው😂) አብርሽ ዝም ብዬ ስጠፋ ደውሎ ምን ሆነህ ነው? ሲለኝ አፍራለሁ። አንድ ቀን ደውዬ አላውቅም። እሱ ግን ያንን አያይም። ደግሞ ያንተ ጥላ ነው መሰል በዙርያዬ ሌሎችም አብርሽ የሚባሉ መልካም ሰዎች አሉ። ቸልተኝነቴን የገረሰስከው ዛሬ ልደትህም ምርቃትህም ነውና እንኳን ተወለድክ። እንኳን ተመረቅህ።🥰💐💐💐 ቀጣይ እሁድ የምትመረቁ ወዳጆቼም ቤኪ🥰💐 (ክላስ ውስጥ አመጣቸው የነበሩ ከረሜላዎች አብዝሀኛው ያንተ ስለነበሩ ለዛሬው ይቅርታ ይሁኑልኝ) ጆሲ (ጃ)🥰🥰🥰(ያንተው ሚስጥር ነው በInbox ጠብቅ ምንም አልልም እዚህ) ሜሪ (የክላሳችን ከረሜላ የደረሰሽ ይመስለኛል ካልደረሰሽ ግን አሳውቂኝ) 💐💐 CONGRATULATIONS💐💐 ሁላችሁም ከእናንተ መጥፋቴ ቸልተኝነቴ ነውና ይቅር በሉኝ https://t.me/Oct13wed

photo content
+3

ሰይፍ ዘክልዔሁ... (✍️እስራኤል ሰይፉ) እስከ ስድስት አመትህ ከተፈጠሩ እና ከምታስታውሳቸው ነገሮች ውስጥ አንድ ነገር ንገረኝ ብባል ልክ እንደ ሩቅና ንጥል ኮከብ ጎልቶ የሚታየኝ ይህ ምክር ነው። ''...ሰይፍ ዘክልዔሁ..." እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ምን ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ አይገባኝም ነበር። ...እንደ ባህራን ደብዳቤ ሳላውቀውም ቢሆን እንድይዘውና የሆነ ሰዓት ላይ ሲገለጥልኝ እንድረዳው ተደርጎ መሆኑን ዘግይቶም ቢሆን የገባኝ ነገር ነው። ...የዚያን ጊዜ የልጅነት ትዝታዬ እንደ አንድ ብሩህ ቀን በህሊናዬ ውስጥ በግልጽ ይታያል። ያኔ አዳሪ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ወቅት ግቢው በሙሉ በታላቅ ድምቀት ይሞላ የነበረው ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ወደ ትምህርት ቤታችን በሚመጡባቸው ቀናት ነበር። አቡነ መልከጼዴቅ ወደ ግቢው ሲገቡ  ርህሩህ አባታችን በፊታቸው ላይ የሚነበበው የሰላም ፈገግታ የሁላችንንም የልጅነት ስጋትና ናፍቆት ይገፍልን ነበር። ...አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ  ወደትምህርት ቤታችን እየመጡ ትራንስፎርመሩ ጋር ትንሽ ዳገት ነገር ስለነበር በዕርጋታ ነበር የሚወርዱት።  በዚያ በስድስት ዓመት እድሜዬ በእሳቸው ግርማ ሞገስና በተረጋጋ አመለካከታቸው በጣም እደነቅ ነበር። ጺማቸው የልጅነት ሽበት ጣል ጣል አድርጎበት ያለ እድሜያቸው እያስረጃቸው እንደሆነ ቢያሳብቅም እኔ ግን የአቡነ ሺኖዳን ጺም እወደው ስለነበር መሸበቱን አልጠላሁትም ነበር። (አቡነ ሺኖዳ ልጆችን ይወዳሉ ስለምንባል ፎቷቸውን የመጽሀፍ የፊት ገጽ ላይ ያየሁት ቀን ተሳልሜዋለሁ) አቡነ መልከጼዴቅን እንዳየሁ እየሮጥኩኝ ወደሳቸው በመሄድ መሀል ዳገት ላይ አስቁሜ ጉልበታቸውን እና መስቀል ተሳለምኩ። (...ከሳቸው መስቀል የተሳለምኩት የመጨረሻ የማስታውሰው የዚህን ቀን ነው...) "...ልጆቼ! እንዴት ናችሁ? ኧይ የልጅ ነገር.. ወርጄም እስክጨርስ አላስችል አላችኋ?!..."   እያሉ አብረውኝ የነበሩትንም ካሳለሙ በኋላ ቁልቁለቱን ወርደው ጨርሰው ቆም አሉ። ወደ እኔና ወደ ጓደኞቼ ዘወር ብለው ያንን የምወደውን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያወሩን ጀመር። ልክ እንደ ትልቅ ሰው ነው ምላሾቻችንን የሚያጤኗት። በትምህርታችን እና በቆይታችን ሁሉ የምናወራቸውን ቅሬታም ሆነ መልካም ነገር መሬት አትወድቅም። መፍትሄ የሚፈልግ ነገር ካለም አይዘገይም። ...የምናወራውን ሁሉ በየተራ ከሰሙን በኋላ ይመክሩናል።    ''...ትምህርታችሁ እንደ ሰይፍ ይሁን፤ ግን በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ! ሰይፍ ዘክልዔሁ!.. ጎሽ ልጆቼ..." አሉን። ሁሌም መጨረሻ ላይ ሰይፍ ዘክልዔሁ ሲሉ እኛ በዚያ እድሜያችን ትርጉሙን ሙሉ በሙሉ ባንረዳውም፣ የቃላቱ ክብደት ልባችን ውስጥ ዘልቆ እንደገባ ይሰማን ነበር። "...በአንድ በኩል አስኳላው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የእግዚአብሔርን መፍራትና ፍቅር የሆነው አብነቱ ይኑራችሁ። አስኳላው እውቀት ከአብነቱ ጋር ሲጣመር ነው ዓለምን የሚለውጥ። እንዲያ እንድትሆኑልኝ ነው የምፈልገው..." ብለው ሲያስተምሩን የነበረው ትምህርት በየጊዜው ሲጎበኙን ይደግሙልን የነበረው መመሪያ ነበር። ... ጠጋ እያሉ ራሴን ሲዳብሱት እጃቸው ላይ የነበራቸውን ሙቀት ሳስታውሰው አሁንም ድረስ ውስጤን ያግለዋል። እሳቸው ሲያበረታቱን "እናንተ የሀገር ተስፋዎች ናችሁ" ሲሉን፣ በእኛ ላይ የነበራቸው እምነት በህይወታችን የውስጥ ጉልበት ሆኖ አለ። ...የገዳሙ ማህበር ስራ ሲኖር እንደማንኛውም መናኝ ወገባቸውን ታጥቀው አብረው ችግኝ እየተከሉና ሌላም ስራ ሲሰሩ፣ ድንገት መምህር እያስተማረ ክፍል ገብተው ልጆቼ እንዴት ናቸው እያሉ ሲጠይቁ፣ ምግብ እየበላን ድንገት ዝምታ ሲሰፍን ዘወር ስል እሳቸው መምጣታቸው መሆኑን ማየቴ.... ልክ ጥር ላይ ሆኖ የሐምሌን የጉም ውስጥ ድብብቆሽ እንደማስታወስ ድብዝዝ ብሎ ይታየኛል። ...እሳቸው ከዚህ ዓለም በስጋ ሲለዩ ገና የስድስት ዓመት ህፃን ብሆንም፣ ታላቅ አባቴን ማጣቴን የሰማሁበት የልጅነት ኀዘን አሁንም ይታወሰኛል። ...ተሰልፈን ጧፍ ይዘን ስንጠብቅ...  ስፍር ቁጥር የሌለው ህዝብ በአንድነት የሚያወጣው ድምጽ... የጉራጌ እናቶች የተወሰኑት ከበሮ ይዘው የተወሰኑት እንደ አሞራ እጃቸውን ዘርግተው እየተቀባበሉ የሚሉት ''ወርኮ ተማነረ'' ዜማ... የሀገር ሽማግሌዎች ፈረስ ላይ ሆነው በአለንጋ ጀርባቸውን እየገርፉ ሲያጉረመርሙ...  መኪናው ሲገባ እነ እማሆይ አናሳልፍ ብለው ሲያስቸግሩ ለምን እንደሆነ ሳይገባን ጧፉን እንደያዝን ቆመን ስናይ... ይመጣሉ ስለተባልን በአካል መስሎኝ ለቀብር የመጡት ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ እሳቸውን ሳጣቸው የተሰማኝን ስሜት... ቃል አጥሮኝ የማልጽፋቸው ብዙ ብዙ ትዝታዎች.... ብቻ ሁሉ ተጽፎ ቃል አይበቃ። ...ታድያ በቅርቡ ለትምህርት ሆሳዕና ሄጄ ከአንድ አባት ጋር ስለ አቡነ መልከ ጼዴቅ እያወራን ያሉኝን ግን መቼም አልረሳውም። ሆሳዕና በነበሩበት ወቅት ያደረጉትን እንዲህ ነበር ያሉኝ... "...ብፁዕነታቸው እኛጋር የሰላምና የእርቅ አባት በመባል ይታወቁ ነበር። አሁን ላይ የተከፋፈሉትን የከምባታ፣ ሃዲያ፣ ስልጤና ጉራጌ ሀገረ ስብከትን በአንድ ላይ ይዘውም በእነዚሁ አካባቢዎች በነበሩ ማህበረሰቦች መካከል የሚፈጠሩትን ግጭቶችና አለመግባባቶች በእርቅና በምክር ለመፍታት ሁሌም ግንባር ቀደም ነበሩ። እሳቸው የነበራቸው የሰላም ስብከትና የእርቅ መንፈስ ህዝቡ በሰላም እንዲኖርና ቤተ ክርስቲያንም የህብረተሰቡ የሰላም ማዕከል እንድትሆን አድርገዋል። በተለይም በችግር ጊዜ ለወደቁና ለተጎዱ ወገኖች የነበራቸው ደግነት፣ የቤተ ክርስቲያንን አባታዊ ተልዕኮ በተግባር ያሳዩበት ነበር። አንድ ጊዜ እንደውም እዚህ ከወልቂጤ ሆሳዕና ስትመጣ አይተኸው ከሆነ መንገድ ዳር ያለ ትልቅ መስጊድ አለ። እዛ መስጊድ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሼሆች ተጣልተው የከረረ ጸብ ነበር። ይህን ሰምተው ብጹዕነታቸው መስጊድ ውስጥ ገብተው ነው ያስታረቋቸው..." ...ስለ አባት እንዲህ መስማት ግን እንዴት ደስ ይላል! ከልቤ ነበር የሰማኋቸው። ለሳቸው ቢገርማቸውም ለእኔ ግን አባቴ ከዚህም በላይ ያደርጉ እንደነበር ስለማውቅ ባልገረምም በታላቅ ሀሴት ነው የሰማኋቸው። ... እሳቸው የዘሩት "ሰይፍ ዘክልዔሁ" ምክር፣ (ቅድሚያ ለራስ) ዛሬ ለሕይወት ፈተናዎቼ የምቆምበት ጋሻና ሰይፍ ሆኖልኛል።  የሳቸው አባታዊ ትዝታ በምሁር ገዳመ ኢየሱስ የ፲፮ኛ አመት መታሰቢያቸው ሰኔ ፲፬ ሲከበር ለእኔ የህይወት መንገድ መብራት ሆኖ ይኖራል። ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ካልዓይ ኢትዮጵያዊ ሊቀ ጳጳስ ከ፲፱፶፪  እስከ  ፳፻፪ ዓ.ም "ስመከ ህያው ዘኢይመውት" https://t.me/Oct13wed

photo content
+3

ቅኝት... ✍️እስራኤል ሰይፉ ...እድል አለመጠቀምን እንዴት ታየዋለህ? ብባል እድልን አለመጠቀም ማለት ከራሳችን ኢጎ ጋር ቅኝት ያለመጨረስ ጉዳይ ነው እል ይመስለኛል። አንዳንድ ልንጠብቃቸው የሚገቡ እና ማንነታችንን እንደ ዘብ ጠብቀው የሚያቆዩልን ኢጎዎች አሉ። የእኛነታችን ኢጎዎች። ማንነታችንን የሚያሳጡንም ኢጎዎች አሉ...  ኢጎ ብዙ ነገር ያሳጣል ጥሩም መጥፎም። የሚያሳጣን ነገር ግን መጥፎ ነገርን ብቻ እንዲሆን አድርገን የምንቃኘው እኛው ነን። ለአስረጅ ይሆነኝ ዘንዳ ይህን ታሪክ ላንሳ... ... ጋዜጠኛዋ በሀብት ከአለም አንደኛ የሆነውን ሰው ቀጥታ ስርጭት ላይ አቅርባ ስለ ሀብቱ ማሳወቅ ፈለገችና መጠይቋን የጀመረችበትና የተሰጣት ምላሽ ትልቅ ትምህርት የሚሆን ነው። ጋዜጠኛ:- ''...በዚህ ልክ ከአለም 1ደኛው ሀብታም እንዴት ልትሆን ቻልክ?..." አለች... ሀብታሙ ከኪሱ ቼክ አወጣና ''... ስንት ልጻፍልሽ..'' አለ ፈገግ እያለች (ቢጽፍላት እኮ ደስታዋ😂) ''...ጥያቄዬ በዚህ ልክ ከአለም 1ደኛው ሀብታም እንዴት ልትሆን ቻልክ?...የሚል ነው...'' ሀብታሙ ሰውዬ እስክሪፕቶውን ለመጻፍ አመቻችቶ ''...የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ መጥራት ትችያለሽ..'' አለ። ጋዜጠኛዋም ግራ በመጋባትና ፈገግ በማለት መሀል ሆና መልሳ ያንኑ ጥያቄ ጠየቀች። ሀብታሙ ሰውዬም በእርጋታ ያመቻቸውን ቼክ ወደ ኪሱ በማስገባት በእስክሪፕቶው እየጠቆመ የመለሰው ድንቅ ምላሽ ይህ ነበር... ''... ያገኘውሁትን እድል በሙሉ ስለምጠቀም። አብዘሀኛው ሰው የገኘውን እድል በሙሉ አይጠቀምም። ቼኩን እንድፈርምልሽ የሰጠሁሽን እድል ተጠቅመሽ ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ምናልባትም ከአለም በሀብት ብዛት ደረጃ ውስጥ የሚያስገባሽን ያህል ታገኚ ነበር..." እና ምን ለማለት ነው... ቅኝታችንን እናስተካክል! https://t.me/Oct13wed

.....በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ስንብት የሚባል ነገር ትልቁ የነፍስ ፈተና ነው። አብዛኞቻችን ቻው ማለት ወይም መሰናበት እንደ ቀላል ጉዳይ ይታያል። ለአንዳንዶቻችን ግን ስንብት ቀላል የቃላት መለዋወጫ ሳይሆን በልብ ውስጥ የነበረን አንድ ውብ ገጽ በግድ የምንዘጋበት ያንኑ ቅርርብ በአንድ ቃል የምናቋርጥበት እጅግ ከባድ ስሜት ነው። ቻው ብለን.... ለሰዎች... መሰናበት ሲያቅተን እንደ መጥፎ ባህሪ ወይም እንደ ቸልተኝነት ሊቆጠር ይችላል። ነገር ግን ይህ ስሜት የሚመጣው ከመውደድ ነው። አንድን ሰው መሰናበት ማለት ያ ሰው በህይወታችን የነበረውን ድርሻ በአንድ ጊዜ የምንገታበት የጋራ ጊዜያችንን ወደ ትዝታነት የምንቀይርበት ሂደት ነው። መለያየትን ለመቀበል የሚከብደን ያንን የፍቅር ወይም የጓደኝነት ትስስር ማቋረጥ ስለማንፈልግ ነው። ስንብትን መሸሽ ማለት የልብን ባዶነት ለመቋቋም መሞከር ነው። ብዙ ጊዜ ዝም ብሎ መሄድ ወይም ሳይሰናበቱ መለየት ያንን የስንበት ሰላምታ ለመናገር የሚጠይቀውን የልብ መፍረስ ላለመጋፈጥ ነው። ያንን ቃል ከተናገሩና ከተቃቀፉ በኋላ የሚመጣው ርቀት ስንብትን ለሚጠሉት ሰዎች እጅግ ይከብዳል። አንዳንዴ ስንብት ሳይደረግ የሚደረግ ጉዞ ለራስ የምናደርገው ጥበቃ ነው። መለያየትን ለመቀበል መቅረት የሚችሉትን የልብ ትስስር ይዞ ለመቀጠል ነው። ቻው ማለት ከባድ ነው ምክንያቱም ልብ ሁሌም አብሮ መኖርን እንጂ መለያየትን ስላልተማረ። ራስ ወዳድነት ሊመስል ይችላል ግን ደግሞ ጠለቅ ብሎ ላየው ከልብ ላለመውጣት የሚደረግ ትግል ነው። ሁሌም አብሮ ያለ አይሰነባበትም😍 https://t.me/Oct13wed