SU|ኤስዩ
الذهاب إلى القناة على Telegram
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
666
المشتركون
-124 ساعات
+27 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
669
የደቡብ ምዕራብ (ጅማ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!
የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በጅማ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።
በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የተማሪ መሪዎችና አገልጋዮች በንቃት ተሳትፈዋል። የተሳታፊዎቹ ስብጥርም ከሚከተሉት ከተሞች እና አካባቢዎች የመጡ ነበሩ፦
▪️ ከጋምቤላ አካባቢ፦ ጋምቤላ እና ጋምቤላ ቦንጋ ▪️ ከጅማ እና ኢሉባቦር አካባቢ፦ ጅማ፣ አጋሮ እና በደሌ ▪️ ከካፋ እና ቤንች ሸኮ፦ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ሚዛን አማን እና ሚዛን ጋቸብ ▪️ ከሸካ ዞን፦ ቴፒ፣ ቴፒ ኩቢቶ እና ቴፒ/ኮርቻ
📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦ በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) ከነበረን ጥናት በተጨማሪ፣ የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ የሚከተሉት ስልጠናዎች (Seminars) ተሰጥተዋል፦ 🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method - BSM) 🔹 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ራዕይ (Highschool Vision) 🔹 ተልዕኳዊ ህብረት (Missional Fellowship) 🔹 የቤተሰብ ቡድን (Family Group)
🚀 ቀጣይ ርምጃችን፦ በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ይህንኑ ጉባኤ ይዘን ወደ ሌሎች ክልሎች እናመራለን! 📍 በሰሜን ምዕራብ፡ ባህር ዳር 📍 በምዕራብ፡ ነቀምቴ
በባህር ዳር እና በነቀምቴ ለሚካሄዱት ለእነዚህ ቀጣይ ጉባኤዎች በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
🌐 @suethio #LeadershipSummit2018 #Jimma #ጅማ #StudentLeaders #YouthEmpowerment #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት
