Sinksar tube(ስንክሳር)
الذهاب إلى القناة على Telegram
እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 981
المشتركون
-224 ساعات
+507 أيام
+18430 أيام
أرشيف المشاركات
2 982
2 982
2 982
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
2 982
"ወደ ምድረ አግዓዚ ሒድ"
ሰማዕቱ አቡነ ቡሩከ አምላክ ገዳማቸው ልዩ ስሙ መራጉዝ በሚባል ቦታ የሚገኘው ‹‹ሙራደ ቃል ደብረ ኮል አቡነ ቡሩከ አምላክ ገዳም›› ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በዱር የተሸፈነ በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ አስደናቂ ነው። ገዳሙን የመሠረቱት አቡነ ቡሩከ አምላክ ሲሆኑ እርሳቸውም ከታላቁ ጻድቅ ከአቡነ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም ተምረው በዚያም ሲያገለግሉ ከኖሩ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ መራጉዝ ሔደው ገዳማቸውን ገድመዋል። ገዳሙ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት የሚደረጉበት፣ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትንና መምህራንን ያፈራ፣ የበቁ ባሕታውያንም መናኸሪያ ነበር። ጻድቁን የታዘዘ መልአክ "ወደ ምድረ አግዓዚ ሒድ" ከነገራቸው በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት። አቡነ ቡሩከ አምላክ ከሴም ወገን ሲሆኑ የትውልድ ሀገራቸው ሮም ነው። አባታቸው ቴዎቅሪጦስ እናታቸው ሚሊዳማ የሚባሉ ከነገሥታት ወገን ሲሆኑ ኹለቱም እንደ አብርሃምና ሣራ በቃል ኪዳን የጸኑ ነበሩ። እነርሱም ብዙ ሀብትና ንብረት ቢኖራቸውም ልጅ ስለሌላቸው ሁልጊዜ እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ይለምኑ ነበር። ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ወደ ሚሊዳማ በመላክ እንዲያበሥራት አዘዘው። ሚሊዳማ ዕድሜዋ እንደ ሣራ ገፍቶ ስለነበር ብሥራቱን ስትሰማ መልአኩን ‹‹…በዚኽ ዕድሜዬ እንዴት ይሆንልኛል?›› አለችው። ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም›› አላት፤ እርሷም እመቤታችንን አብነት አድርጋ ‹‹…እሺ እንደ ፍቃዱ ይሁንልኝ›› አለች። አባታችን አቡነ ቡሩክም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በዕለተ ጽንሰቷ ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሰው በዕለተ ልደቷም ግንቦት 1 ቀን 1290 ዓ.ም ተወለዱ። ጻድቁ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉም ድዉይ እንደፈወሱ በገድላቸው ላይ ተጽፏል።
አቡነ ቡሩከ አምላክ ገና በተወለዱ በ5ኛ ቀናቸው ‹‹አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን›› ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል። ዳግመኛም ‹‹ለድንግል ማርያም ምስጋና፤ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይሁን›› እያሉ ከእናታቸው ማሕፀን ጀምሮ የጠበቃቸውን አምላካቸውን አመሰገኑ። ከመነኮሱም በኋላ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት በመጾም ሥጋቸውን በረኀብና በውኃ ጥም ቀጡ፤ ከሰንበቶች በስተቀር ምንም አይቀምሱም ነበር። ከብዙ ተጋድሏቸውም በኋላ በዚኽች ዕለት ነሐሴ 14 ቀን 1415 ዓ.ም በክፉዎች ሰዎች እጅ በሰማዕትነት ዐርፈዋል። ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን!\
2 982
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
🔐ከስር ክፈት የሚለውን
በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
................💚💛❤️...............
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
...............💚💛❤️................
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
2 982
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
2 982
2 982
"ሰማይ ታላቅ ነው ቢሉ ከአንቺ ጋር አይስተካከልም፤ ሰማይና ምድርን የሞላው በማሕፀንሽ ሞልቶአልና። ሰዎች ከአንቺ ይልቅ ምድርን ታላቅ ናት ቢሉኝ ምድርማ የእግሩ መረገጫ ብቻ ናት እላቸዋለሁ።
የኖኅ መርከብ ነሽ ይሉሻል፤ የኖኅ መርከብ ግን ያዳነችው ኖኅንና ቤተሰቦቹን ነው። በአንቺ ግን ዓለም ዳነ። ታቦት ነሽ ይሉሻል ታቦቱ የያዘው በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ሁለት ጽላትን ነበር። አንቺ ግን የዓለማትን ጌታ በኃይሉ ቃል ጸነስሽው!"
(ቅዱስ ዲሜጥሮስ)
2 982
2 982
2 982
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
2 982
††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ †††††† ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር:: ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና በሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም:: በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ:: ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል: ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም:: በጊዜው (በዘመነ ሰማዕታት) የነበሩ ካህናት የቤት ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ:: ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ ስጥኑፍ (የግብፅ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ: ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ:: አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን::" ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ:: ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር: በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም ከበው ይነጋገሯቸው ነበር:: ሥጋውን ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ (ሰማዕትነት) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና ከቤተ ክርስቲያን ወጡ:: በቀጥታ የሔዱትም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምሥክርነት አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "ክርስቶስ አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው::" ሲሉ በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ አባ ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በኋላም ወደ ጨለማ እሥር ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል:: በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በኋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን አግኝተዋል:: በአክሊለ ጽድቅ ላይ አክሊለ ካህናትን: በአክሊለ ካህናትም ላይ አክሊለ ሰማዕታትን ደርበዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን በአባቶቻችን ጽናት ያጽናን:: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: ††† ነሐሴ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ (ሰማዕት) 2.አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" ††† (፩ቆሮ. ፲፥፲፬-፲፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
2 982
Repost from Sinksar tube(ስንክሳር ቲዩብ)
"የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ቤት እግሩን ማራቅ ሲጀምር፣ ፍቅርም ከእርሱ ፈቀቅ ትላለች፤ ያን ጊዜ ከሚያየውና ከሚዳስሰው ሁሉ ጋር መጋጨት ይጀምራል። ግጭቱም ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ከተፈጥሮ፣ ከአካባቢው፣ ከማኅበረሰቡና ከራሱ የሕሊና ሙግት ጋር እንጂ።
ፍቅር በሌለበት ምድር ባዶነት ትነግሣለች፤ ፍቅር በሌለበት ልብ የውስጥ ሰላም አይገኝም። ፍቅር ከራቀ ደግሞ ሁሉ ነገር ድቅድቅ ጨለማ ይለብሳል።
ስለሆነም የሰው ልጅ ሆይ! ሙሉ ፍቅርን ታገኝ ዘንድ ሁልጊዜም እግሮችህ ወደ አምላክህ ቤት ይፋጠኑ። ያኔ ለሕሊናህ ፍጹም ሰላምና ፍቅር ታገኛለህ፤ ያን ጊዜ ባዶነትህ ይሞላል፣ ጨለማህም በብርሃን ይተካል።"
2 982
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
