ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ወደ ኢየሱስ ደረት

ወደ ኢየሱስ ደረት

الذهاب إلى القناة على Telegram

Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
276
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-630 أيام
أرشيف المشاركات
photo content

#ቀን:2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ። #ለከንቱ ነገር ያልሰሰትነውን #ጊዜና #ጉልበት #ለወንጌል #ሥራ #አንቆጥበው። #ለ50 ተከታታይ ቀናት #ወንጌልን በድፍረት #በሥራ ቦታ፣ #በትምህርት ቤ
#ቀን:2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ። #ለከንቱ ነገር ያልሰሰትነውን #ጊዜና #ጉልበት #ለወንጌል #ሥራ #አንቆጥበው። #ለ50 ተከታታይ ቀናት #ወንጌልን በድፍረት #በሥራ ቦታ፣ #በትምህርት ቤቶች፣ #በታክሲ ስፍራ፣ #በቤተሰብ መካከል፣ #በባልንጀሮቻችን ፊት እና #በማህበራዊ ሚድያ ገጾች መመስከር      #Share በማድረግ #ለሌሎችም በማድረስ በዚህ የወንጌል ሥራ አብረውን #እንዲጠመዱ እናድርግ። #ፀጋ ይብዛላችሁ ! 🙏

ቀን:1 ለ 50 ተከታታይ ቀናት #ወንጌልን በድፍረት #በሥራ ቦታ፣ #በትምህርት ቤቶች፣ #በታክሲ ስፍራ፣ #በቤተሰብ መካከል፣ #በባልንጀሮቻችን ፊት እና #በማህበራዊ ሚድያ ገጾች መመስከር ፀጋ ይብዛላ
ቀን:1 ለ 50 ተከታታይ ቀናት #ወንጌልን በድፍረት #በሥራ ቦታ፣ #በትምህርት ቤቶች፣ #በታክሲ ስፍራ፣ #በቤተሰብ መካከል፣ #በባልንጀሮቻችን ፊት እና #በማህበራዊ ሚድያ ገጾች መመስከር ፀጋ ይብዛላችሁ ! 🙏

ለአሁኑ ወጣት በጣም አስፈላጊ ምክር ነው። ተባረኪ

ከዘመኑ ደሊላ መሸሽ መሣፍንት16÷1-31 ↔አንድ በመፅሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ በመሣፍንት ጊዜ የተነሳ የመጨረሻው ትልቅ መስፍን አለ እሱም ሶምሶን ነው። ↔ሶምሶን ናዝራዊ ሆኖ እንደሚወለድ እግ/ር ለቤተሰ
ከዘመኑ ደሊላ መሸሽ መሣፍንት16÷1-31 ↔አንድ በመፅሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ በመሣፍንት ጊዜ የተነሳ የመጨረሻው ትልቅ መስፍን አለ እሱም ሶምሶን ነው። ↔ሶምሶን ናዝራዊ ሆኖ እንደሚወለድ እግ/ር ለቤተሰቦቹ  ተናግሮ ነበር።ሳምሶን ሲወለድ ለ እግ/ር    የተለየ እንደሆነ እናስታውሳለን።አንድ ናዝራዊ ሰው ማድረግ የሌለበትን ነገር ይህ ክፍል ይናገራል፦ (ዘኁ 6÷1-21) ሶምሶንም እነዚህ ነገሮችን አለማድረግነበረበት.....ግን አደረገው ↔አንድ ናዝራዊ የሆነ ሰው የወይን ፍሬ ውጤት የሆነ ማንኛውንም ነገር የማይበላ፥ ምንም ዓይነት ሬሳ የማይነካና ጠጉሩን የማይቆረጥ ነበር፤ (ዘኁ. 6፡1-21)። የሚያሳዝነው ግን ሶምሶን እነዚህን ትእዛዝት ሁሉ አፍርሷል። ↔ዛሬ ልላችሁ የምፈልገው ነገር ደሊላ ከምትባል አሳሳች እንድትጠበቁ ነው በርግጥ ከምታሳሳስት ሴት ሳይሆን ወደ ህይወታችን ተስማምተን የምናስገባቸው ከዘመኑ ደሊላዎች ከመሸሽ አንፃር ነው ፣የሶምሶን ብረቱነቱን ታውቁታላችሁ ግን ባልጠበቀው እና ባላሰበው ደግሞ እርሱ በወደደው ነገር ተሰናክሎ ወደቀ የእግ/ርም ሀይል ከእርሱ ተለየ። ↔በዘመናችን ወደን ወደ ህይወታችን የምናስገባቸው ብዙ ደሊላዎች አሉ ።ከእግ/ር ሊያርቁን ከጥልቁ መንግስት ጋር ቃልኪዳን የገቡ ቅድስናችንን ሊበሉ ተከፍሎዋቸው ወደ ህይወታችን የሚመጡ አሉ። ↔ ምንድነው ወጣቶች የምንወደው ነገር ወደ ህይወታችን ያስገባነው ነገር?።ግን  የእግ/ርን ቦታ  ሊወስድብን እና ሊነጥቅብን ያለ ነገር በእውነት እራሳችንን እንጠይቅ ??? ↔መቼም ቢሆን ሰይጣን የሚመጣብን እያስፈራራን ሳይሆን እየተቅለሰለሰ ነው።ይልቁን የምንወደው ነገር ሲታይ ከሚያምር ነገር ግን የእግ/ርን መንፈስ ከውስጣችን የሚወስድ  ከይወታችን እንዲሸሽ ትኩረታችን ሁሉ ወደ እየሱስ  ይሁን። ↔ከዘመኑ ደሊላዎች እንሽሽ❗❗❗ ✍️Betsinat

እውነትሽ ነው በሥጋ ቀርበን በልብ መራቅ ሳይሆን፤ ከእውነተኛ ልብ መቅረብ ነው🛐🛐

ወደ ደረቱ መመጠጋት ና የልብ ምቱን መስማት ✧“ደረት” ብንል በመጀመሪያ የሰውነት ክፍል ይመስለናል፤ ግን በእውነቱ ከዚያ  ያለፈ ትርጉም አለው  ደረት የፍቅር፣ የመቀራረብ እና የእረፍት ቦታ ነው ሰው በሰው ደረት ላይ ሲጠጋ ምን ያሳያል? መታመን፣ መረጋጋት እና ያለ ፍርሃት መቀመጥ ✧ይህን ሀሳብ መፅሐፍ ቅዱስ በግልፅ ያሳያል። በዮሐንስ 13፡23 አንዱ ደቀ መዝሙር፣ ኢየሱስ የሚወደው፣ በእርሱ ደረት ላይ ተጠግቶ እንዳለ ይናገራል ይህ ቀላል ተግባር አይደለም፤ ቅርብ ግንኙነትን ያሳያል። እርሱ በጌታው ዘንድ ያለውን ፍቅር ተረድቶ በዚያ እረፍት አግኝቶ ነበር። ✧እኛም በኢየሱስ ደረት መጠጋት ማለት እንዲሁ ነው፤ በእርሱ መታመን፣ ጭንቀታችንን መተው እና በእርሱ ውስጥ እረፍት መፈለግ። “እናንተ የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ” የሚለው ቃል (ማቴዎስ 11፡28) ይህን ግንኙነት ያብራራል። ✧“የልብ ምት መስማት” ሲባል ደግሞ የአካል ድምፅ ብቻ አይደለም፤ መንፈሳዊ ነገር ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ቅርብ ስንሆን ፈቃዱን እንረዳለን፣ ድምፁን እንሰማለን። ይህ በጸጥታ የሚደረግ ነው “ዝም በሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ” (መዝሙር 46፡10) የሚለው እንደሚያሳየው፣ በጸጥታ ስንቀመጥ የልቡን ምት መስማት እንጀምራለን ✧እንግዲህ በኢየሱስ ደረት መጠጋት ማለት በፍቅሩ ውስጥ መኖር ነው፤ የልቡን ምት መስማት ደግሞ ፈቃዱን መረዳት ነው በዚያ ውስጥ እረፍት፣ ሰላም እና እውነተኛ ቅርብነት አለ           ተፃፈ:- በአፅናኝ

ሰላም ወዳጆቼ እንደምን ቆያችሁ🙌 ከላይ የተለቀቀውን ✨ወደ ደረቱ/ወደ ፀጋው ዙፋን✨ የሚለውን ትምህርት እንዳነበባችሁ በጣም እርግጠኛ ነኝ እና እኔስ ወደማን እየተጠጋው ይሁን??🤔 እያላችሁ በምናባችሁ እያሰባችሁ ይሆናል።እናም ወዳጆቼ ይህ ቻናልም የተከፈተበት አላማ ያ ነው በምንም አይነት ጉዳይ፣ሁኔታ፣ድካም፣ውድቀት ውስጥ ልንሆን እንችላለን ግን ምንም ቢመጣ ቅድምያ ለኢየሱስ/ ወደ እየሱስ፤አሁንም ነጌም መቼም ወደ እየሱስ ደረት ፈጥነን እንጠጋ🫂 እንቅረብ በፀጋው ባለጠጋ የሆነ አምላክ እየሱስ አቅፎ ይቀበለናል🙌።በእኔ እና በእናንተ ቤት እየሱስ ይቅደም🙌
ይህንን እውነት ሌሎችም እንዲረዱት shere አድርጉ🙏
https://t.me/wedeysusedert

‎↪️ ወደ ደረቱ/ ጸጋው ዙፋን ቅረቡ🛐 ‎ ‎✍️ የብርታታችን ምንጭ ወደ ጸጋው ዙፋን ወይም ወደ ደረቱ መቅረብ ስሆን የድካማችን ምንጭ ከደረቱ ከጸጋው መራቅ ነው። ‎ ‎✍️ አማኝ ከሆንን ከደረቱ ውጭ ለላ ምንም አይነት መበርቻ የለንም‼️ ‎ ‎✍️ ደክሞሀል መጸለይ፣ ቃል ማጥናት ፣ መንፈሳዊ ሕብረት ማድረግ አቃተክ አይዞክ የእግዚአብሔር ፀጋ አለልክ ወደ ፀጋው ዙፋን በእምነት ብቻ ቅረብ የምያበረታን ጸጋን ትቀበላለ ከዚያማ ኃይላችን ይታደሳል እንደ ንስር 🦅🦅 እንበራለን፣ እንሮጣለን አይታክተንም፣ እንሄዳለን አይደክመንም ሀሌሉያ ‼️ 👉 በደከምን ሰዓት በምንም ተአምር አማራጫችን ከእርሱ መሸሽና መራቅ ሊሆን አይገባም ወደ ፍቅሩ ደረት መጠጋት አለብን🛐 ‎ ‎#ጸጋው_ሁልጊዜ_ዝግጁ ‎(available)ነው‼️ ‎ ‎"እንግዲህ #ምሕረትን_እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ #የሚረዳንን_ጸጋ እንድናገኝ ወደ #ጸጋው_ዙፋን_በእምነት #እንቅረብ።"  (ዕብራውያን 4:16) ‎     ‎♨️አሁን በእምነት ወደ ጸጋው ዙፋን ቅረቡ በኢየሱስ ስም ዛሬ የምያበረታችሁን ጸጋ በእምነት መቀበል ይሁንላችሁ‼️ ‎ 👉 ሁል ጊዜ እንቅረብ የለመለመ ሕይወት ይኖረናል🛐🛐🛐

ሲሞላ ዘምሬ ሲጎድል አላለቅስም በምንም ሁኔታ አምልኮ አልቀንስም አንተ ከሁሉ በላይ ነህ እታመንሃለው በምስጋና ሆኜ ድል እንደምትሰጠኝ በስምህ አምኜ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ

Repost from N/a
የትንሳኤው በዓል ግብዣው የሚያስጨንቅበት፣ ምኞት የሚጎርፍበት፣ ሆድ የማይታመምበት፣ ደስታ የሚጠገብበት፣ ሳቅ የሚረክስበት፣ ጥላቻ የሚሞትበት፣ ፍቅር የሚዘንብበት፣ ተስፋ የሚታደስበት፣ እግዚአብሔር surprise የሚያደርግበት፣ መንፈስ ቅዱስ የሚደሰትበት... ብቻ ደስ የሚል... እኔንም የሚታስታውሱበት በዓል ይሁንላችሁ! I love y'all! Happy Easter!

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ሞትና ትንሳኤ መታሰብያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። ሉቃ 24:5 ይህ ቀን በሞቱ እና ሞትን ድል በመንሳቱ ጌታ ያደረገላችሁን እያሰባችሁ ጌታን የምታከብሩበት በዓል ይሁንላችሁ ። መልካም የትንሳኤ በዓል !

“በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም፦ ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው።”   — ሉቃስ 24፥33-34 ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ በክብር ተነስቷል! ይህ ትንሳኤ የሞት መጨረሻ መሆኑን ያበሰረና ለሰው ልጅ ሁሉ አዲስ ተስፋን የሰጠ ታላቅ የምስራች ነው። ​በመቃብር አለመቅረቱ ፍቅር ከጥላቻ፣ ሕይወትም ከሞት እንደሚበልጥ በተግባር ያሳየበት የድል አዋጅ ነው። ዛሬም እርሱ ሕያው ስለሆነ በሕይወታችን ላለው ጨለማ ሁሉ ብርሃን፣ ለጭንቀታችንም እውነተኛ ሰላም ይሆንልናል። እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስትቶስ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ!"✨

“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።”   — 1ኛ ጴጥሮስ 1፥3-5 👉ስለዚህ ደሰ ይበላችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከሞት በመነሳቱ ሁሉ ነገር ተለውጧል እኛም አምነናል የሕያው ተሰፋ ቃል ወራሾች ሆነናል ። #ክብር #ለትንሣኤው #ንጉሰ #ይሁን!! እንኳን ለኢየሱስ ክርሰቶስ ትንሣኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን።🙏

አዲሱን የ ዘማሪ Bereket Tesfaye መዝሙር ለማግኘት👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻

☑️የሚከተለው መዝሙር የማን ነው? የጥሉን ግድግዳ ላያዳግም አንዴ አፈራርሶ ጣለው ይህ የመዳን ቀንዴ ለእኔም ሆኖልኛል ታዳጊና ቤዛ በእውነት ኢየሱሴ ሃያል ነው ሲበዛ
Anonymous voting

#በርባን_እኔ_ነኝ 🎤: ዘማሪት ኤደን አብርሀም ⏰: 5:32 ተባረኩበት https://t.me/wedeysusedert https://t.me/wedeysusedert

ወዳጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተ ውብ ነህ፥ የኔ ናርዶስ ትለያለህ። የመረጥኩህ ከእልፉ መሀል፥ ጠረንህ ይናፍቀኛል። ላፍታም ባጣህ ካላየሁማ፥ እንዴት ችዬ ያን ጨለማ፥ ናልኝ ልዋል ቀን ታቅፌህ፥ ማታም ዳብሰኝ በእንቅልፌ። አስከትለኝ እጄን ይዘህ፥ እንዳትለቀኝ በምንም ግዜ፥ ካንተ ጋር መሆን ሁሌ ያምረኛል፥ ደስታ አለበት ይመቸኛል። ✍Alazer Teshome

Too panful!

‎     ፈሶ ወደ ሰማይ ‎**** ‎የተላጠ ጀርባህ፣ የተገሸለጠው ‎ለጨካኞች ጅራፍ፣ ታልፎ የተሰጠው ‎የተተለተለው፣ በደም አሸብርቆ ‎የሚታይ ገላህ፣ ከገላዎች ልቆ ‎በኃጢአተኞች እጅ፣ እየተዋረደ ‎ምህረት አዝንቦ፣ ፍቅር ያዥጎደጎደ ‎ጭንቀትና ስቃይ፣ ዝምታ በአንድ ላይ ‎የተቆለለብህ ፣ በማይስብ መልክህ ላይ ‎ወደኸኝ ነውና ፣ ልሙትለት ብለህ ‎እንኳን ስቃይ ገባህ ፣ እንኳን ጭንቅ አለህ ‎አባትህ ነውና ፣ ጨክኖ የገደለህ ‎ኤሎሄ ኤሎሄ ፣ ስትለው ዝም ያለህ ‎ምነው የዛን ጊዜ ፣ በሰማህ አልልም ‎አንተ ባትሞት ኑሮ ፣ እኔ ልጅ አልሆንም ‎ምነው የዛን ጊዜ ፣ ወይ ባለህ አልልም ‎አንተ ባትቆስልልኝ ፣ የኔ ቁስል አይድንም ‎እንደውም እንደውም ፣ እንኳንም አልሰማህ ‎እንኳንም ተላጠ ፣ እንኳን ደማ ጀርባህ ‎እንደውም እንደውም ፣ እንኳን ወይ አላለህ ‎እንኳን አደቀቀህ ፣ እንኳን አቆሰለህ ‎ባትጨነቅ ኑሮ ‎ባትወጋ ኑሮ ‎ባትገረፍ ኑሮ ‎ባያደቅህ ኑሮ ‎አንተ ባትሰቀል ፣ ተተክተህ በ'ኔ ‎አንፋታም ነበር ፣ እኔና ኩነኔ ‎ይብላኝ እንጂ ለሞት ፣ አንተ እንኳን ተሰቀልክ ‎መልክህን እንድይዝ፣ እንኳን መልኬን መሰልክ ‎ከአባትህ ዕቅፍ ፣ እንኳን ወ'ተህ መጣህ ‎እንኳን ባልሰራኸው ፣ ቅጣቴን ተቀጣህ ‎በፍቅር እያየህ ፣ ወንድሜ ልትለኝ ‎ከወዳጅ የሚበልጥ ፣ ወዳጅ ልትሆነኝ ‎እዛ መስቀሉ ላይ ፣ ተቸንክረህ ሳለ ‎እዛ መስቀሉ ላይ ፣ ደምህ ሲፈስ ሳለ ‎እዛ መስቀሉ ላይ ፣ እያማጥክ ሳለ ‎እዛ መስቀሉ ላይ ፣ ዝለህ ደክመህ ሳለ ‎ይቅር በለው እያልክ ፣ የበዛ በደሌን ‎የጠራኸው አንተ ፣ አቤት ያለው እኔን ‎በእኔ ህመም ቆስለህ ፣ እያከምክ ቁስሌን ‎ኤሎሄ ያልከው አንተ ፣ አቤት ያለው እኔን ‎ ‎እናማ ምን ሆነ...... ‎በእርግማን ሞትህ ፣ በረከት ሆነኸኝ ‎ከጽዮን መጥተህ ፣ ከሲዖል ነጥቀኸኝ ‎በአብ ቀኝ ተገኘሁ ፣ ሞትን ዳግም ላላይ ‎የደምህ ጅረቱ ፣ ፈሶ ወደ ሰማይ ‎