cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Більше
Рекламні дописи
1 362 620
Підписники
+31824 години
+3 6717 днів
+17 17430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Update " በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ #ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ምንድናቸው ? በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው። በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ #ጣልቃ_መግባት_እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦ ° የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣ ° የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ #በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ #ተካቷል፡፡ ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል #አለባበስን እና የተማሪዎች #አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡ የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ምን አሉ ? የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ #የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም #በመንግሥት እና #በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል። አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት #ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡ Credit - Reporter Newspaper @tikvahethiopia
Показати все...
409😡 162🤔 48🕊 43😭 39🙏 27😱 25👏 23🥰 22😢 21
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Update " በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩም የሃይማኖት ተቋማት ቅሬታ ማቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ተቋማቱ ረቂቅ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት የሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት መብትና ክብር የሚጠብቅ መሆኑ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። በአብዛኛው ተከብሮ የቆየው የሃይማኖቶች ነፃነት ላይ ገደቦችን እንዳይጥል ሥጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። የቀረቡ ቅሬታዎች ምንድናቸው ? 1ኛ. ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች የተነሳው ቅሬት፦ በረቂቁ አዋጁ ላይ የአደባባይ በዓላትን በሚመለከት " የአደባባይ ኩነት " ተብሎ መቀመጡን በማንሳት ይህ ትክክለኛ ትርጉም አይደለም ብለዋል፡፡ ለዚህ በማሳያ " የአደባባይ ኩነት በተፈቀደው ቦታ ብቻ መደረግ አለበት " በሚል በረቂቁ ላይ የተቀመጠውን ነው። ለአብነት #የጥምቀት_በዓል የአደባባይ ሃይማኖታዊ በዓል ቢሆንም ፤" ከተፈቀደለት አደባባይ ውጪ መንገዶች ላይ መካሄድ አይፈቀድም " የሚል ትርጓሜ እንዳይሰጠው #ያሠጋል ብለዋል፡፡  ሌላው " የሃይማኖት ተቋም የሚይዘው ስያሜ፣ ዓርማ ወይም ምልክት ቀድሞ ከተቋቋመ ተቋም ስም፣ ዓርማ ወይም ምልክት ጋር ተመሳሳይ መሆን የለበትም " በሚል ረቂቁ ላይ የተቀመጠው ነው። ይህ ፤ " #በከፊልም ሆነ #ሙሉ_በሙሉ ተመሳሳይ መሆን የለበትም " በሚል ሊስተካከል እንደሚገባው ገልጸዋል። ለዚህ ምክንያቱ " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ስያሜ የኢትዮጵያ የሚለውን ብቻ በማውጣትና የራሳቸውን በመተካት አገልግሎት ላይ ሲያውሉ የሚታዩ አካላትን ስለተመለከትን ነው " በማለት አስረድተዋል፡፡ 2ኛ. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤትን በመወከል የተገኙ ተሳታፊዎች ያቀረቡት ቅሬት ፦ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሚከለክለው የረቂቅ አዋጁ ክፍል " በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች መፈጸም የተከለከለ ነው " በሚል የቀረበው ሊስተካከል ይገባል ብለዋል። #ሶላት_የደረሰበት_ሙስሊም በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች እንዳይሰግድ መከልከል እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ " በከተሞች ውስጥ ለአምልኮና መቃብር የሚሰጥ ቦታ የከተማውን የዕድገትና የልማት ዕቅድ ወይም ማስተር ፕላን የማይቃረን መሆን አለበት " በሚለው ረቂቁ ላይ ይህ ወደ ተግባራዊነቱ ሲገባ አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልጸዋል። መጀመሪያ የተገነባ ቤተ እምነት " ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የሚቃረን ነው " በሚል እንዳይፈርስ ዋስትና የማይሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች ሁሉ እምነት እንዳላቸው፣ ለአብነትም አንድ ሙስሊም በመንግሥት ተቋም ተቀጥሮ ሲሠራ ሶላቱን በሚሰግድበት ወቅት፣ በተቋሙ ውስጥ ሃይማኖታዊ ክንውን አድርጓል ሊባል መሆኑንና ረቂቁ ይህን እንዴት ማስታረቅ እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል፡፡ 3ኛ. የወንጌል አማኞች ካውንስል ተወካዮች ቅሬታ ፦ ረቂቅ አዋጁ በወንጌላውያን ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል። " በተለይ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ የሚከለክሉ የረቂቁ ክፍሎች፣ ወንጌል መስበክ መሠረታዊ አስተምሯችን ለሆነው ለወንጌላውያን ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል ነው " በማለት ተናግረዋል፡፡ ይህ ' መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ' በሚል የተቀመጠውን መርህ የጣሰ እንዳይሆን ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡  Credit ➡️ Reporter Newspaper @tikvahethiopia
Показати все...
393👏 69😡 38🕊 24🙏 20😭 18🤔 7🥰 6😱 6😢 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Tigray ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት አገልግሎት መስጠት የጀመረው በመቐለ ከተማና አከባቢዋ ነው። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎት መስጠት ስለመጀመሩ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በ2 ምዕራፎች 16 የትግራይ ከተሞች የ4G እንዲሁም የ5G የሞባይል ዳታ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብሏል። #TikvahEthiopiaFamilyMekelle @tikvahethiopia            
Показати все...
336👏 78🕊 28🥰 20😡 10😭 9😢 7🤔 3🙏 1
#Amhara የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ። በወረዳው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ትለንትና በምሽት በመግባት እንደገደሉት ተሰምቷል። ወረዳው ባወጣው የሀዘን መግለጫው ፥ " አቶ አልብስ ለዓመታት በቀውስ ነጋዴዎች ለችግር ተጋልጦ የሴራ ፖለቲካ መሸቀጫ የተደረገውን የጀውሃና አካባቢው ማህበረሰብ ቀርቦ በማወያየት መተማመን ፈጥሮና አደራጅቶ ወደ ቀደመ አካባቢውና ኑሮው እንዲመለስ በማድረግ ላይ ነበሩ " ሲል ገልጿል። አክሎ " የወደሙትን የጤናና ሌሎች ተቋማትንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመስራት መልሶ እያቋቋመ የነበረ ደከመኝን የማያውቅ፣ ለእውነት የቆመ ንፁህ የሕዝብ ልጅና አገልጋይ፤ እውነተኛ የአማራ ጀግና ነበር " ብሏል። አቶ አልብስ አደፍራሽ ትላንትና ምሽት ቤታቸው በገቡ ታጣቂዎች ተገድለዋል። @tikvahethiopia
Показати все...
👏 467😭 376 59🕊 46😢 32🙏 17😡 15🥰 13😱 10🤔 2
#AddisAbaba በጀኔቭ የመኪና አስመጭና በቤቶች ኮርፖሬሽን መካከል የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው ? በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ደንበል አደባባይ አካባቢ " ጄኔቭ የመኪና አስመጪና ሻጭ ድርጅት " የተከራየው ህንፃ የኪራይ ውሉ እንዲቋረጥ ሊደረግ በመሆኑ ያለውን ቅሬታ እያቀረበ ይገኛል። የጀኔቭ ዋና እና ምክትል ማናጀሮች ቅሬታቸው ፦ - ህንፃው ለMixed አገልግሎት ሆኖ ሳለ ለሆቴል ማስፋፊያ ይሰጥ መባሉ፣ - እኛ እራሳችን ከፍተኛ ግብር ከፋይ ሆነን ለሌላ ለሆነ አካል ይሰጥ መባሉ፣ - ቤቱ ለልማት ይሰጥ ተብሎ የካቢኔ ውሳኔ ባለማግኘታቸው፣ - ለልማት ይሰጥ የተባለው በ2013 ዓ/ም ሆኖ ሳለ አሁን ውሉ ይቋረጥ መባሉ፣ - ቤቶች ኮርፖሬሽን ሊሟገት ሰገባው የኪራይ ውሉ እንዲቋረጥ የድጋፍ ደብዳቤ በመፃፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ራሱ ኮርፖሬሽኑ ቢያለማው እኛ መልቀቅ እንችላለን የመንግስት ቦታ ስለሆነ ግን ለምንድነው ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ የሚሰጠው ? ያውም ሆቴል ሳይሆን ሆቴል ተብሎ ሲሉ ጠይቀዋል። የቤቶች ኮርፖሬሽን የፃፈው የድጋፍ ደብዳቤ ላይ፥ ምክንያቶቹን በዝርዝር ካብራራ በኋላ፣ የተከራይ ውል እንዲቋረጥ ያዛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ኮርፖሬሽኑን ጠይቋል። የኮርፖሬሽኑ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አማኑኤል አያሌው፣ “ የመጀመሪያ ስህተቱ ሰዎቹ ልክ እንደ ግል ይዞታ አድርገው እያቀረቡ ነው። ይዞታው የቤቶች ኮርፖሬሽን ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ ደግሞ የንግድ ቤት ተከራይ ናቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ ከተማ አስተዳደሩ ‘እዚያ አካባቢ የሆቴል ዲዛይን ነው’ አለ። እኛ ሆቴል አንገነባም። ስለዚህ እኛ ይዞታ አናስተላልፍም ለግለሰብ። እሳቸውም ለእኛ ቅሬታ ቢያቀርቡ መስጠት አንችልም ” ብለዋል። አቶ አማኑኤል፣ “ ቅሬታ ካላቸው ለከተማ አስተዳደሩ ነው ማቅረብ ያለባቸው። ቦታው ለእኔ ይመደብ ብለው ማቅረብ ይችላሉ ” ነው ያሉት። ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ቦታው ለልማት እንዲነሳ በካቢኔ ስለመወሰኑ እንደማያውቁ ላነሱት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ አቶ አማኑኤል፣ “ የካቢኔ ውሳኔ ተለጥፏል ያውቃሉ። በ2013 ዓ/ም የተለጠፈ የካቢኔ ውሳኔ ነው ” ብለዋል። (ይህን የሚገልጽ ዶክመትም አሳይተዋል) ለቲክቫህ የላኩት ሰነድም ህንፃው ለልማት እንዲነሳ በከተማ አስተዳደሩ በ2013 ዓ/ም መወሰኑን ያትታል። እንዲሁም፣ ቦታው ለMixed አገልግሎት ሆኖ ሳለ ለምን ለሆቴል ማስፋፊያ ይሰጥ በመባሉ ጀኔቭ ላነሳው ቅሬታ፣ “ ይህ ሰው ተከራይ ነው። ይህን ያህል ቅሬታ ማንሳት የለበትም፣ ተቀባይነት የለውም ” ብሏል ኮርፖሬሽኑ። “ ተከራይ ነው፤ በንግድ ህጉ መሠረት ይህ ሰው ሲዋዋል መንግስት ወይም ኮርፓሬሽኑ ቤቱን ለልማት  ሲፈልገው ውል ያቋርጣል ይላል ” ነው ያለው። ተወሰነ የተባለው በ2013 ዓ/ም ሆኖ ሳለ ለምን አዘግይቶ አሁን መጠየቅ አስፈለገ ? ሲል ጀኔቭ ላነሳው ጥያቄ አቶ አማኑኤል፣ “ አብዛኛውን ውሳኔ አንቀበልም። መሬቱን ማቆየትና ማልማት ስለምንፈልግ ” ሲሉ መልሰዋል። አክለው፣ “ ግን አሁን የአዲስ አበባ ከተማ መልሶ ማልማት ላይ ያለው ‘ ከመንግሥት እንቅፋት እየሆነናችሁ ነው ’ የሚል ቅሬታም እየመጣ ስለሆነ ማልማት በምንችለው መንገድ እኛ እናለማን። ባለሃብቱ ማልማት ባለበት ደግሞ ባለሃብቱ ” ነው ያሉት። የጄኔቭ ማናጀር አቶ አብርሃም ለማ በበኩላቸው፣ “ ራሳቸው ተጠይቀው የሰጡት መልስ አለ። ‘ ራሱን ችሎ የሚገነባ ቦታ ስለሆነ ራሳችን እንገነባለን። ካልሆነ ደግሞ ተከራዩ ማልማት የሚችል ከሆነ ቅድሚያ እንሰጣለን’ ” የሚል ምላሽ ከከተማ ከንቲባ ለቀረበላቸው ጥያቄ እንደሰጡ ተናግረዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
91😡 24🕊 15😱 12😭 8🤔 7😢 7🥰 6👏 2🙏 1
“ እናቴን አድኑልኝ፣ የልቧ ሁለቱ ቱቦዎች በመጥበባቸው ደም እየመለሱ ነው ” - ልጅ የእናቱ ሁለት የልብ ቱቦዎች ጠበው ወደ ሰውነት አካል ክፍላቸው መተላለፍ ያለበት ደም ወደ ኋላ እየተመለሰ በመሆኑ በአስቸኳይ መታከም እንዳለባቸው ሀኪም ማዘዙን የታማሚዋ ልጅ ገልጿል። የታማሚ ወ/ሮ ትዕግስት ነብሮ ልጅ ናትናኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ እናቴን አድኑልኝ፣ የልቧ ሁለቱ ቱቦዎች በመጥበባቸው ደም እየመለሱ ነው ” ይላል። “ እኔ የአምስተኛ ዓመት አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ነኝ። እናቴን ለማሳከም 760,000 ብር ተጠይቀናል። የተገኘው 192,000 ብር ብቻ ነው ” ብሏል። “ ልቧ ሲመታ ስለሚያማት እናቴ አሁን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አታደርግም ” ያለው ተማሪ ናትናኤል፣ “ ኬዙ ቆየት ብሏል፤ ከአንድ ወር በፊት ግን በጣም አሟት ለ17 ቀናት ሆስፒታል ተኝታ ነበር ” ሲል ሁነቱን አስረድተዋል። ለህክምና 760,000 ብር እንደሚያስፈልግ ከሆስፒታል የተጻፈ ማስረጃ ደብዳቤ አለ ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ፣ “ አዎ አለ ” ብሎ የላከ ሲሆን፣ ደብዳቤውም ከላይ ተያይዟል። ተማሪ ናትናኤል ባስተላለፈው መልዕክት፣ “ከአቅም በላይ ስለሆነ ነው እንጂ እርዳታ አልጠቅም ነበር። ግን ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር አቅም ጠፍቶ ነውና እርዳታ አድርጉልኝ” ሲል ተማጽኗል። መርዳት ለምትፈልጉ 1000298948935 የNatnael Demelash አካውንት ቁጥር ነው። እንዲሁም 1000032440324 የTigst Nebro አካውንት መጠቀም ይቻላል። መደወል ለምትፈልጉ 0993655876 ናትናኤል ደመላሽን ማግኘት ይቻላል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
😢 872🙏 293 60😭 56🕊 15🤔 4🥰 3😱 3😡 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#DStv ✈️ አውሮፓ እንሂድ ⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው! በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይከታተሉ! 🏆የምትወዱዋቸውን የአውሮፓ ታላላቆችን ዋንጫ ፍልሚያ በወር 350 ብር! የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ። የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ! 👇 https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2 #Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Показати все...
24😢 5😱 4🥰 3🤔 1🕊 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✈️ አውሮፓ እንሂድ ⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው! በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይከታተሉ! 🏆የምትወዱዋቸውን የአውሮፓ ታላላቆችን ዋንጫ ፍልሚያ በወር 350 ብር! የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ። የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ! 👇 https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2 #Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Addis Ababa University- Cisco Networking Academy, @CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com Online Live class - Cybersecurity Training & Certification Preparation. Registration Date: April 22 to June 07, 2024 Class start date: June 08, 2024. Course Recognitions:- Trainees will receive 4 certificates of training completion; 4 digital badges that recognized and accepted in USA, Canada, and Europe, and you will get 32% discount for LPI Linux Essentials and 58% discount for CyberOps Associate Certification exam vouchers. Mobile #: 0945-039478/ 0902-340070/ 0935-602563 Office : 011-1-260194 Follow our telegram channel: @CiscoExams
Показати все...
20🙏 4😭 2
#ስፖርት : ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻሚዮንስ ሊግ ፍጻሜ ቦሪስያ ዶርትመንድን በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ። ቡድኑ በባለፈውም ዓመትም እጅግ ጠንካራ ነው የሚባለውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፎ ነበር። ይህ የእግር ኳስ ፍልሚያ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለተለይ በወጣቶች ዘንድ እንዲሁም በመላው ዓለም በርካታ ሚሊኒዮን ተመልካች ያለው ሲሆን ምርጥ የሚባሉት የአውሮፓ ክለቦች የሚሳተፉበት ነው። @tikvahethiopia
Показати все...
1523👏 278😡 159🥰 70😭 63🙏 43🕊 29🤔 28😢 28😱 15