cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tikvah-University

Show more
Advertising posts
215 763
Subscribers
+5024 hours
+6237 days
+2 13930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#MoE የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚወስዱ ተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀ ማስፈንጠሪያ (URL) ላይ በመግባት እንዲለማመዱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። ከስር የተቀመጡት ማስፈንጠሪያዎች ተፈታኝ ተማሪዎች የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው ዕለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናሉ። Note: እስካሁን Username እና Password ያለገኛችሁ ተፈታኞች፤ ከትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ➧ ክላስተር አንድ አዲስ አበባ፦ https://c2.exam.et ሲዳማ ክልል፦ https://c2.exam.et ትግራይ ክልል፦ https://c2.exam.etክላስተር ሁለት ደቡብ ም/ኢ/ክልል፦ https://c3.exam.et ጋምቤላ ክልል፦ https://c3.exam.et አማራ ክልል፦ https://c3.exam.etክላስተር ሦስት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ https://c4.exam.et ሀረሪ ክልል፦ https://c4.exam.et አፋር ክልል፦ https://c4.exam.et ኦሮሚያ ክልል - 1 • አዳማ ከተማ፦ https://c4.exam.et • አጋሮ ከተማ፦ https://c4.exam.et • አምቦ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ አርሲ፦ https://c4.exam.et • ምዕራብ አርሲ፦ https://c4.exam.et • አሰላ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ባሌ፦ https://c4.exam.et • ባቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ቤሾፍቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ቦረና፦ https://c4.exam.et • ቡሌ ሆራ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ቡኖ በደሌ፦ https://c4.exam.et • ዶዶላ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ ባሌ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ ቦረና፦ https://c4.exam.et • ጉጂ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et • ምዕራብ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et • ሆለታ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ሆሮ ጉዱሩ፦ https://c4.exam.et • ኢሉባቦር፦ https://c4.exam.etክላስተር አራት ድሬዳዋ ከተማ፦ https://c5.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2 • ጅማ፦ https://c5.exam.et • ጅማ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ቄለም ወለጋ፦ https://c5.exam.et • ማያ ከተማ፦ https://c5.exam.et • መቱ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሞጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሞያሌ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ነጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ነቀምት ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሮቤ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሰንዳፋ በኬ፦ https://c5.exam.et • ሻኪሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሻሸመኔ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሸገር ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሸኖ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ምስራቅ ሸዋ፦ https://c5.exam.et • ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ)፦ https://c5.exam.et • ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et • መዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et • ምስራቅ ወለጋ፦ https://c5.exam.et • መዕራብ ወለጋ፦ https://c5.exam.et • መዕራብ ጉጂ፦ https://c5.exam.et • ወሊሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et @tikvahuniversity
Show all...
👍 54😢 10 3
Photo unavailableShow in Telegram
👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ለማስፈተን ፍላጎት ያለው ማንኛዉም የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የተደራጀ የኮምፒውተር ላብራቶሪ ሊኖረው እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። በዚህም የትኛውም ትምህርት ቤት፦ 1. ዴስክቶፕ ወይም ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች 2. የውስጥ ኔትዎርክ (Local Area Network) 3. የኢንተርኔት መስመር ከበቂ ባንድዊድዝ ጋር (ከመፈተኛ የኮምፒውተር ብዛት አንጻር) 4. የመጠባበቂያ ኃይል (ጄኔሬተር) ጋር ማሟላትና ለትምህርት ቢሮዎች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህም በቢሮዎች በኩል መሟላቱ ሲረጋግጥ የፈተና ማዕከል በመሆን ተማሪዎቹን ማስፈተን እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ለፈተና የሚዘጋጁት ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ማሟላት ያለበቸቅ ዝቅተኛ ስፔስፊኬሽን፦ 1. RAM --------------- 4GB or higher 2. Storage --------------250GB or higher 3. Processor Speed -------- 2.5GHZ or higher 4. Processors ---------- Intel Core i3 or higher 5. OS --------------- Windows 10 6. Browsers ---------------Safe Exam Browser and other 7. Accessories ---------- Keyboards and Mouse for desktop computers. @tikvahuniversity
Show all...
👍 204👎 54 16👏 16😢 13🙏 7😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በክልሉ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚወስዱ ከ53 ሺህ በላይ ተማሪዎች የቲቶሪያል ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ጥራት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡ በክልሉ በሁለት ኮዶች የሚሰጠው የ2016 ዓ.ም ፈተና፤ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና ዘንድሮ ትምህርታቸውን ተከታትለው የሚፈተኑትንም ያካተተ መሆኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር ታደሰ ካሕሳይ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ከ53 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ተፈታኞችን በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለመፈተን ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይ በክልሉ ለሚሰጠው የስምንተኛ ክፍል ፈተና 123 ሺህ ተፈታኞች በሁለት ባች ተከፍለው ከሰኔ 11-13/2016 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ጠቁመዋል፡፡ #ኢፕድ @tikvahuniversity
Show all...
👍 101😱 6 5🙏 3👎 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ2016 ዓ.ም የትክክለኛነት ማረጋገጫ ከተሰራላቸው 10,238 የትምህርት ማስረጃዎች 1 ነጥብ 6 በመቶዎቹ ትክክለኛውን መስፈርት #የማያሟሉ ሆነው መገኘታቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለፀ። ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ የዜጎችን የተወዳዳሪነት አቅም በማሳጣት፣ በተቋማት ላይ ብልሹ አሠራሮች በማስፈን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ተናግረዋል፡፡ ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ የብቃት መመዘኛና የመቁረጫ ነጥብ ያላሟሉ፣ ተዛማጅ ባልሆኑ የትምህርት ዘርፍ እና ፍቃድ በሌለው ኮሌጅ ማስረጃ የሚያገኙ መሆናቸውን ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡ በ2016 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የትክክለኛነት ማረጋገጫ ከተሰራላቸው 10,238 የትምህርት ማስረጃዎች 1 ነጥብ 6 በመቶዎቹ ትክክለኛውን መስፈርት #የማያሟሉ ሆነው መገኘታቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ በፌዴራል እና የክልል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ላይ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ በትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ የማጣራት ሥራው ሲጠናቀቅ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 35 5👏 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔔 አሁን የሚያገግኙትን ገቢ በሦስት እጥፍ ማሳደግ ይፈልጋሉ? በሁለት ወራት ውስጥ በተከታዮቹ መስኮች ስልጠና በመውሰድ ባለፀጋ ይሁኑ! 🌟 ሴልስ እና ማርኬቲንግ - ለሁለት ወር 🌟 ዲጂታል ማርኬቲንግ - ለሁለት ወር 🌟 ኢቨንት ኦርጋናይዚንግ - ለሁለት ወር 🌟 የብቃት ሰርተፊኬት (COC) እንሰጣለን! በሦስት ፈረቃ፦ | ጠዋት | ቀን | ማታ 📣 አሁኑኑ ይመዝገቡ! ለመመዝገብ እና ለተጨማሪ መረጃ፦ 0963454545 ቦሌ ቅርንጫፍ 0978230000 ሜክሲኮ ቅርንጫፍ 0978200000 መገናኛ ቅርንጫፍ 0978250000 ፒያሳ ቅርንጫፍ 0978201111 አዳማ ቅርንጫፍ አድራሻ፦ ጎልደን ዋና ቢሮ፣ ቦሌ መድኃኒዓለም ትራፊክ መብራት፣ ሒድሞና ሕንፃ ቢሮ ቁ. 604 Golden Sales and Marketing
Show all...
👍 21 3👎 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይለማመዱ! የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀምን ይለማመዱ! ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀምና እንዴት ፈተናውን መውሰድ እንደሚቻል ለማሳየት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተዘጋጀን የአራት ደቂቃ ገላጭ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ይመልከቱ፡፡ ራስዎን ለፈተናው ያዘጋጁ! ቪዲዮውን ይመልከቱ 👇 https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M @tikvahuniversity
Show all...
👍 70 9👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program) በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡ የታለንት መስኮች፦ ➧ Cyber Security ➧ Cyber Development ➧ Embedded Systems ➧ Aerospace ምዝገባ የሚያበቃው 👇 ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ለበለጠ መረጃ👇 0904311833 0943579970 0904311837 ለመመዝገብ፦ https://talent.insa.gov.et
Show all...
👍 50 8🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#የቻናል_ጥቆማ 🔔 ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ‼️ የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት? 📚 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀት ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን! 👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ 👉 አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣ 👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣ 👉 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡ Join Us :- ✅on Telegram 👇 https://t.me/ethioengineers1 https://t.me/ethioengineers1 ✅on TikTok tiktok.com/@ethiocons tiktok.com/@ethiocons
Show all...
👍 9 2🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የምትወስዱ ተፈታኞች ምዝገባ እስከ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ በዚህም፦ ➧ በሰኔ 2015 ዓ.ም እና በየካቲት 2016 ዓ.ም ተፈትናችሁ የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለምትፈልጉ እንዲሁም ➧ ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት የሕግ መውጫ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያላገኛችሁና አሁን በድጋሜ ለመውሰድ የምትፈልጉና ስም ዝርዝራችሁ ከቀድሞው ዩኒቨርስቲያችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላችሁ አመልካቾች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ምዝገባ እንድታጠናቅቁ ተብሏል፡፡ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ በሰኔ 2015 ዓ.ም እና በየካቲት 2016 ዓ.ም ተፈተናችሁ የማለፊያ ውጤት ያልመጣላችሁ አሁን በድጋሜ መፈተን ለምትፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባችሁን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ብቻ የምትፈጽሙ ይሆናል፡፡ ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጣችሁ በድጋሜ ለመፈተን የምትፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራችሁ ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያችሁ መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባችሁን የአገልግሎት ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ ስካን ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንድትልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 93 7🥰 2