cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Show more
Advertising posts
122 597
Subscribers
-24924 hours
-1 2337 days
-6 01830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻሚዮንስ ሊግ ፍጻሜ ቦሪስያ ዶርትመንድን በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ። ቡድኑ በታሪኩ ይህን ዋንጫ ሲያሸንፍ 15ኛ ጊዜ  ነው። @Yenetube @Fikerassefa
Show all...
👍 33👎 8 8😁 3🔥 1
የሞቃዲሾ መንግስት #በሶማሊያ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በቀጣይ ታህሳስ ወር ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል ብሎ እንደሚጠብቅ ተገለጸ! ሶማሊያ በሀገሯ በሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ የሚገኙ ሁሉም የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣይ አመት 2017 ታህሳስ ወር ላይ ጠቅልለው ይወጣሉ ብላ እንደምትጠብቅ ቪኦኤ በዘገባው አስታውቋል። የቪኦኤ ጋዜጠኛ የሆነው ሃሩን ማዕሩፍ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ሼክ አሊን ጠቅሶ ትላንት ባሰራጨው ዘገባው የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (ATMIS) በቀጣይ አመት ታህሳስ ወር ተልዕኮው ካበቃ በኋላ “የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሃይል አባል አይሆኑም” ብሏል። የቪኦኤው ሃሩን የፕሬዚዳንቱን አማካሪ ጠቅሶ እንደዘገበው ከቀጣይ አመት በኋላ በሶማሊያ በሚሰፍረው ጦር ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደማይኖሩ እና ከሌሎቹ የሰላም አስከባሪ ሀይል ካበረከቱ አራቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ የተውጣጡ ብቻ እንደሚሆኑ ጠቁሟል። በሶማሊያ ሰላም በማስከበር ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቀጣይ አመት 2017 ታህሳስ ወር ላይ በሶማሊያ የሰፈረው የሰላም አስከባሪ ጦር ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል። ይሁን እንጂ የሰላም አስከባሪው ሀይሉ ለቆ ከወጣ በኋላ ዋና ዋና የህዝብ ማዕከላትን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን እና የሀሪቱ መንግስት ቁልፍ ተቋማትን በመቆጣጠር ጸጥታ የሚያስከብር ሀይል ለማቋቋም እዕቅ መኖሩ ተጠቁሟል። በያዝነው አመት የታህሳስ ወር መጨረሻ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ ይታወቃል። @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 37😁 3👎 2👀 1
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹 ውድ ኢትዮጲያውን IELTS Official የእንግሊዘኛ ቋንቋ ከመፈተናችሁ በፊት በነፃ ተለማመዱ ይጠቅማቹሀል፣ ለሚጠቅመው ሰውም ሼር አድርጉላቸው እና የተሻለ ውጤት ያምጡ። Free Online IELTS Practice Tests by the British Council 💠 Host Organization: British Council. Offered By: The IELTS learning materials are offered by the British Council 🔺Free IELTS Practice Tests Includes: 🔺Free online IELTS Listening practice tests 🔺Free online IELTS Reading practice tests 🔺Free online IELTS Academic Reading practice test – paper 🔺Free online IELTS General Training Reading practice test – paper 🔺Free online IELTS Speaking practice tests 🔺Free online IELTS Writing practice tests 🔺Free online IELTS Academic Writing practice tests – paper Link: https://takeielts.britishcouncil.org/take-ielts/prepare/free-ielts-english-practice-tests #free #education #practice #ethiopia #africa
Show all...
👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ ማንኛውም መልዕክት ይላኩ ይቀበሉ 22 ጎላጎል አከባቢ ኳሊቲ ህንፃ ስልክ :- 0980526262
Show all...
👍 12
የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ፤ ስለ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ኃላፊነት ምን ይላል? በ1995 ዓ.ም. የወጣውን የኢሚግሬሽን አዋጅ የሚያሻሽል የህግ ረቂቅ በትላንትናው ዕለት ለፓርላማ ቀርቧል። አዋጁን ለማሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች “አንዱ የተቀናጀ ድንበር ቁጥጥር አስተዳደርን” አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ተግባራዊ ካደረገው መመሪያ ጋር የኢትዮጵያን ስርዓት ማጣጣም በማስፈለጉ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። የዓለም አቀፉ ድርጅቱ ተግባራዊ ያደረገው መመሪያ፤ ሀገራት የመንገደኛ ቅደመ ጉዞ መረጃ እና ምዝገባ ስርዓትን እንዲዘረጉ የሚያስገድድ ነው። ኢትዮጵያ የዚህ መመሪያ ፈራሚ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ፤ ይህንኑ ስርዓት በኢሚግሬሽን ማሻሻያ አዋጅ ላይ እንዲካተት መደረጉ በአዋጅ ማብራሪያው ላይ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት “ማንኛውም አጓጓዥ መንገደኛን ወደ ሀገር ለማስገባት ወይም ከሀገር ለማስወጣት ከማጓጓዙ ከሶስት ሰዓት በፊት፤ የመንገደኛውን ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ስም ዝርዝር ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት የማሳወቅ ወይም የመላክ” ግዴታ እንዲኖራቸው ተደርጓል። “ይህ መሆኑ መረጃውን በመለዋወጥ የሚፈለጉ አደገኛ ወንጀለኞች በተለይም ሽብርተኞችን ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ ያስገንዝባል። “ሀገርን የደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ሰዎች ከአየር ጉዞ ውጪ ሌሎችም የትራንስፖርት ዘዴዎች ሊጠቀሙ የሚችሉ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ”፤ ለሌሎች አጓጓዦችም የሚሆን አንቀጽ በአዋጅ ማሻሻያው ላይ እንዲካተት መደረጉ በማብራሪያው ላይ ሰፍሯል። “ማንኛውም ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አጓጓዥ፤ በሀገራት መካከል በሚኖር በእንካ ለእንካ መርህ ወይም በሚደረግ ስምምነት መሰረት፤ የመንገደኞችን ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ስም ዝርዝር ወደሚሄድበት አገር ከመውሰዱ በፊት እንዲያሳውቅ” በአዋጅ ማሻሻያው ግዴታ ተጥሎበታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 20 5👎 1
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ! የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ። በሥራ ላይ ባለው “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ” ላይ የተደረገው ይህ ማሻሻያ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተሰረዘበትን የፓርቲነት ሕጋዊ እውቅና መልሶ እንዳያገኝ ያደረገውን የሕግ ጥያቄ የሚመልስ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጅ ማሻሻያውን ተቀብሎ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው ዛሬ አርብ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ያወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ከእነዚህ ረቂቆች መካከል በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ስለማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው አዋጅ ይገኝበታል። በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ አዋጅ እና የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው አዋጅም ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሕጎች ናቸው። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፤ በዛሬው ስብሰባ ውሳኔ እንደተላለፈበት በቀዳሚነት የጠቀሰው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጅ ነው። ማሻሻያ የቀረበበት በ2012 ዓ.ም. የወጣው የምርጫ ሕግ፤ እውቅና የተነፈጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልሶ ከመመዝገብ ጋር በተያያዘ ክፍተት ያለበት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቅሷል። “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ሥርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም” ሲል በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ላይ የታየውን ክፍተት ይገልጻል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የመራው ማሻሻያ ላይ የፖለቲካ ቡድኖች “በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ” መልሰው ለመመዝገብ የሚችሉበትን ሥርዓት የሚዘረጋ እንደሆነም ተጠቅሷል። ዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የፖለቲካ ቡድኖች መልሶ የመመዝገብ ጉዳይ ከህወሓት ዳግም ሕጋዊ እውቅና የማግኘት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ፈጥሮ ነበረ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
😁 31👍 24 8🔥 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ “በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎችን” ጨምሮ ለስምንት አካላት የዕውቅና ሽልማት አበረከተ! በአዲስ አበባ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የተለያዩ እስር ቤቶቸ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ለስምንት ግለሰቦች እና ተቋም የአመቱን የህብረቱን የሹመን የሰብአዊ መብት ሽልማትን (EU Schuman Human Rights Award) አበረከተ። በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት እንዲከበረ እና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በማሰማት አስተዋጽኦ አበረክተዋል በሚል ስድስት ግለሰቦች የተሸለሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ይገኙበታል፤ ተቋማቸውን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን አስችለዋል የሚል አድናቆት ተችሯቸዋል። በሽልማቱ ስነስርአት ወቅት ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር፣ ሽልማቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ እንደባህል በየአመቱ በኢትዮጵያ ሽልማቱ በቀጣይ አመታት ይተገበራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ሃ/ማርያም፣ በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሰው የሆርሙድ የሴቶች ማህበር ሊቀመንበሯ ጋሪ ኢስማኤል ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች ሊግ መሥራች ጌቱ ሳከታ፣ ከሰብአዊ መብት በተጨማሪ በአከባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ መሆኑ የተገለጸው የቁም ለአካባቢ ሊቀ-መንበር መልካሙ ኦጋ፣ የኢትዮጵያ ሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበር፣ የፈንዲቃ የባህል ማዕከል መሥራች የሆነው አርቲስት መልካሙ በላይ እና በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሽልማቱ የተበረከተላቸው ናቸው። Via Addis Standard @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 29👎 5 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዶናልድ ትራምፕ በታሪካዊው የክስ ሂደት በቀረቡባቸው ክሶች በጠቅላላ ጥፋተኛ ተባሉ! የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሁሉም ጥፋተኛ ተብለዋል።ትራምፕ ከንግድ ሰነድ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ በቀረቡባቸው ክሶች ከ2016 ጀምሮ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት በእርሳቸው ፊርማ ተፈርመው የወጡ የገንዘብ ሰነዶች እና ቼኮች እንደማስረጃ ቀርበውባቸዋል። ስቶርሚ ዳንኤልስ የተባለችው የወሲብ ፊልም ተዋናይት ከምርጫው በፊት ከትራምፕ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት እንደፈጸመች እና ስለዚህ ጉዳይ እንዳታወራም የ130ሺ ዶላር ክፍያ እንደተፈጸመላት በኒውዮርክ ፍርድ ቤት ቀርባ መስክራለች። የቀድሞ የፕሬዝዳነቱ ጠበቃ ማይክል ኮሀን ይህንኑ ፍርድ ቤት ተገኝተው አረጋገረጠዋል፡፡ ጠበቃው ለዳንኤልስ በትራምፕ አዛዥነት እንዲከፈል የተጠየቀ 130 ሺ ዶላር ክፍያን አስፈጽሚያለሁ ብለዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኒውዮርኩ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ላይ ያለም ሆነ የቀድሞ ፕቴዝዳነት በወንጀል ጥፋተኛ ሲባል የመጀመርያው ሆነዋል፡፡ ትራምፕ የፍርድ ውሳኔውን የተጭበረበረ እና አሳፋሪ ነው በሚል ሲገልጹት ጠበቆቻቸቸው በበኩላቸው ውሳኔውን እንደማይቀበሉ እና የይግባኝ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ከሰአት ላይ ኒውዮርክ በሚገኝው ትራምፕ ታወር መግለጫ እንደሚሰጡ የሚጠበቁት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ የምርጫ ቅስቀሳ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተነግሯል፡፡ጥፋተኝነት ውሳኔው በትራምፕ ቀጣይ የፖለቲካ ጉዞ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እስከሁን ግልጽ የሆነ ነገር ባይኖርም የሚያሳድረው ተጽዕኖ ግን ቀላል የማይባል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለሀምሌ 11 የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ቀጠሮ የሰጠው ፍርድ ቤት ውሳኔ የትራምፕን የፖለቲካ ህይወት የሚወስን ነው፡፡ በእርግጥ ፍርድ ቤቱ ጥፈተኛ ናቸው ባላቸው ትራምፕ ላይ የሚያሳልፈው ቅጣት አልታወቀም፡፡ ሮይተርስ ያነጋገገራቸው የህግ ባለሙያዎች ግን የእስር ቅጣት ከአማራጮቹ መካከል ቀዳሚው ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ለዚህም የንግድ ሰነዶችን ማጭበርበር ለአራት አመታት በእስር እንደሚያስቀጣ የሚደነግገውን ህግ በማሳያነት ጠቅሰውታል፡፡ [Al ain] @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 44 10👎 4