cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
Advertising posts
196 433
Subscribers
-4524 hours
-1107 days
+7230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸውም ይገልጻል። አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል። በተጨማሪም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ የሃይማኖት ተቋማቱ ጨምርው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ @TikvahethMagazine
Show all...
👏 186😡 110🤔 36 14😨 4
Photo unavailableShow in Telegram
#EthiopiaEducationCluster ° በኢትዮጵያ 8.85 ሚሊዮን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል። ° 10 ሚሊዮን ህፃናት የትምህርት ድጋፍ ይፈልጋሉ። በኢትዮጵያ በተባባሱ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት 8.85 ሚሊዮን ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የትምህርት ክላስተር ባወጣው የሩብ አመት ሪፖርት አመለከተ። ሪፖርቱ በ2024 አመት 10 ሚሊዮን ህፃናት ተማሪዎች ድጋፍ እንደሚፈልጉ ያመለከተ ሲሆን ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ወዲህ ባሉት ጊዜአት ከትምህርት ገበታቸው ውጭ የሆኑ ህፃናት ቁጥር፣ በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። በክረምቱ ዝናባማ ወቅት የተከሰተው ጎርፍ በስድስት ክልሎች ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑን ያመለከተው ሪፖርቱ 2024 ከገባ ጀምሮ ባሉት 3 የበልግ የዝናብ ወቅቶች በአስር ክልሎች ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ትንበያውን አስቀምጧል። በሰባት ክልሎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት እስከ መጋቢት ድረስ 1ሚሊዮን የተጎዱ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል። በ3 ወራት ውስጥ የወደሙ ትምህርት ቤቶች በ4.5 በመቶ የጨመረ ሲሆን የተዘጉ ትምህርት ቤቶች 18 በመቶ መጨመራቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። በ2024 የፈረንጆች ዓመት ለ3 ሚሊዮን ህፃናት የትምህርት ድጋፍ ለማድረግ ቢታቀድም እስካለፈው መጋቢት ወር 356 ሺህ ህፃናት ብቻ ድጋፍ አግኝተዋል። በተያያዥ ቀውሶች ምክንያትም ችግሩ ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችልም ነው የተገለፀው። @TikvahethMagazine
Show all...
😢 17
Photo unavailableShow in Telegram
#Tecno #Camon30Pro5G Tecno Camon 30 pro 5G በአስገራሚ ቴክኖሎጂዎች እና በአገልግሎቱ ልቆ የቀረበ የዘመኑ ምርጥ ስልክ! #Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
Show all...
😢 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
አያት አክሲዮን ማህበር በሪል እስቴት ፣ በፋይናንስ ፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት ፣ በማዕድን እንዲሁም በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፎች የተሰማራ ግዙፍ ትርፋማ ድርጅት ነው። እርስዎም የአያትን አክሲዮን ገዝተው ዘላቂ ስኬትን እውን ያድርጉ! ለበለጠ መረጃ: በ 0921138613 / 0915922176 ይደውሉ 👉telegram - @Netsanet_Realestate 👉Whatsapp - https://wa.me/251921138613
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
#እንድታውቁት የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በማዕከል ደረጃ ሲሰጥ የነበረውን የማስረጃ ማረጋገጥ ስራ ለየካ፣ ለቦሌ እና ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተገልጋዮች አገልግሎት የሚሰጥ የማስረጃ ማረጋገጫ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገናኛ ከፍቷል። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሶስት ክፍለ ከተሞች አማካይ ቦታ መገናኛ አማረ አብርሀም እና ቤተሰቡ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ላይ ለአገልግሎት ክፍት ሲያደርግ ለተገልጋዮች ከ13/9/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥ የኤጀንሲው የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀሚላ ረዲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል። ከዚህ ቀደም ኤጀንሲው የማስረጃ ማረጋገጥ ስራን የሚከውን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከፍቶ የነበረ ሲሆን ጽ/ቤቱ ለኮልፌ ቀራንዮ፣ ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ ለልደታ እና ለአቃቂ ቃሊቲ ተገልጋዮች አገልግሎት እየሰጠ ነው ተብሏል። @TikvahethMagazine
Show all...
15😡 3👏 2🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
የስራ አጥ ቁጥር በተበራከተባት ኬንያ የወንጀል ምጣኔ በ19 በመቶ መጨመሩ ተነገረ በዋጋ ግሽበት በተቸገረችው እና የስራ አጥ ቁጥር በተበራከተባት ኬንያ በተያዘው አመት የተፈጸሙ እና የተመዘገቡ ወንጀሎች ቁጥር በ19 በመቶ ማደጉን ኢስት አፍሪካ ጋዜጣ ዘግቧል። በሀገሪቱ የተመዘገበው የወንጀል ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ 104,842 መድረሱ ሲነገር ባለፈው አመት ከነበረው 19 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል። እንደ ኬንያ ስታትስቲክስ ቢሮ መረጃ በሀገሪቱ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ሁሉም አይነት የስርቆት ወንጀሎች ሲጨምሩ በኬንያ የሚፈጸሙት ወንጀሎች ማጭበርበር፣ ንጥቂያ፣ ስርቆት እና የቡድን ዝርፍያን እንደሆኑም ተገልጿል። በሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ እንደሆኑ ሲገለፅ የንግድ ድርጅቶች መንግስት የታክስ ጭማሪ ሊያደርግ እንደሆነ ካሳወቀ በኋላ የሰራተኛ ቅነሳ በማድረግ ላይ ናቸውም ነው የተባለው። @TikvahethMagazine
Show all...
🤔 23😢 11😡 2
በአዲስ አበባ በአካል ጉዳተኞች የተሰሩ የቆዳ ውጤቶችና የተለያዩ አልባሳት የቀረቡበት ባዛር ተከፈተ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ "አካል ጉዳተኞች መስራት ይችላሉ " በሚል መሪ ሃሳብ በአካል ጉዳተኛ ማህበራት የተመረቱ የተለያዩ የቆዳ ውጤቶችና አልባሳት የቀረቡበት ባዛር ተከፈተ። በአዲስ አበባ 4 ኪሎ አካባቢ የተዘጋጀው ባዛር እስከ ግንቦት 17 ቀን 2016 እንደሚቆይ ሲገለፅ 14 ማህበራት እና 36 በግል በድምሩ 50 አምራች የሆኑ አካል ጉዳተኞች ያሳተፈ ነው ተብሏል። ይህ የንግድ ትርኢት የተዘጋጀው አካል ጉዳተኞች ምርታቸውን በማቅረብ የገበያ ዕድል እንዲያገኙ እድል ለማመቻቸት ሲሆን ህብረተሰቡ ያቀረቡትን ምርት በመግዛት አካል ጉዳተኞችን እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል። @TikvahethMagazine
Show all...
👏 39 6
00:35
Video unavailableShow in Telegram
ሁሉንም የግንባታ ባለሙያዎች እየጠራን ነው። በቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2016 ለይ የሚሳተፉ ከ150 በላይ የግንባታው ዘርፍ ብራንዶችን ይተዋወቁ። ዩናይትድ አረብ ኢምሬት፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ኢትዮጵያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ህንድ፣ ቱርክና ኦስትሪያን ጨምሮ ከተለያዩ 20 ሃገራት ተወክለው ከሚመጡ ተሳታፊዎች(አቅራቢዎች) ጋር ይገናኙ። የአቅራቢ ድርጅቶችን ዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/44BfWyw ይህ በዘርፉ መልካም ስም ካተረፉ ድርጅቶች ጋር የመገናኘት አስደሳች አጋጣሚ አያምልጥዎ! በነጻ ለመግባት እዚህ ይመዝገቡ https://bit.ly/3UsrL5I በቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ
Show all...
4
🔥🔥 እንኳን ደስ አሎት ለGamezoneኦች ✓for school ✓Home use ✅ imported Table tennis Size=international standard ✅Family entertainment Price=26500 birr ❐ስልክ፡ 0944311523 0973379551   Join https://t.me/mame321a
Show all...
🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስር አመታት የምታስመዘግባቸውን ቅርሶች የሚለይ ኮሚቴ መቋቋሙ ተጠቆመ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው የቱሪዝም ሚኒስቴር የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቅርስ ማስመዝገብን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስር አመታት የምታስመዘግባቸውን ቅርሶች የሚለይ በብሔራዊ ደረጃ የሚመራ ኮሚቴ መቋቋሙ ተጠቆመ። የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብረት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከዚህ ቀደም የቅርስ ምዝገባ የሚደረገው አካባቢዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ እና አጥኚዎች በሚያጠኑት ጥናት መሰረት እንደነበር ገልፀዋል። አሁን ግን አዲስ ባሉት አሰራር ከዱር እንስሳ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባለሙያዎች የተካተቱበት በብሄራዊ ደረጃ የሚመራ ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል። የዚህ ኮሚቴ ስራ ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስርት አመታት የምታስመዘግባቸውን ቅርሶች መለየት ሲሆን የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ቅርሶች በልዩ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ገልፀዋል። በዚህም ማህበረሰቡንና የተለያዩ አካላትን የሚያሳትፍ በመሆኑ ለሚቀጥሉት አስርት አመታት የሚመዘገቡት የትኞቹ ናቸው የሚለውን ህዝቡም ያውቀዋል በማለት ጠቁመዋል። @TikvahethMagazine
Show all...
😡 37👏 15🤔 7 5😢 3😨 1