cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Show more
Advertising posts
1 363 265
Subscribers
+79424 hours
+3 1577 days
+16 87630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ ተገኝተው ነበር ? #አልተገኙም " ውይይት መደረጉን የሰማነው እራሱ በሚዲያ ነው " - ኦፌኮ በኦሮሚያ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግሥት አድርጎታል በተባለው ውይይት ላይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) #አልተሳተፉም። የኦፌኮ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቪኦኤ ሬድዮ ፥ " ውይይቱ መደረጉን የሰማነው ከብዙሃን መገናኛ ነው። እንደ ግለሰብ ይሁን እንደ ተቋም የደረሰን ጥሪ የለም የኮሚኒኬሽን ክፍተቱ ከማን በኩል እንደሆነ አላውቅም " ብለዋል። ኦፌኮ የክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ቢሆንም ባለው ቅሬታ ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል። አቶ ጥሩነህ ፤ ለውይይት በም/ቤት ይሁን በመንግስት ጥሪ አልደረሰንም ብለዋል። የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በበኩላቸው ፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ #እንዳልተሳተፈ ገልጸዋል። " ለውይይቱ ጥሪ ሊደረግ ይችላል እኛ ግን የምንፈልገው በአንድ አካል አቅራቢነት የሚደረገውን ውይይት ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ውይይት ነው። " ብለዋል። " የምንፈልገው አንድ ሀገርን የሚያስተዳደር መንግሥት በሚሰጥህ ቦታ ተወስኖ መወያየት ሳይሆን እራሳችንን የመፍትሄ አካል ነን ብለን የምናይ አካላት በአንድ ላይ ሆነን በተመሳሳይ ድምጽ ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ የምናስቀምጥበት ካልሆነ ኦነግ በአንድ አካል ጥሪ የሚሳተፍበት መድረክ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል። የኦሮሞን ችግር የሚፈተው በእውነታ ላይ የተሰመሰረተ አካታች ውይይት እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሚ ፤ ውይይት ሂደቱን ጠብቆ አካታች በሆነ መልኩ መከናወን አለበት አሁን ያለው አካሄድ ሂደቱን ያልጠበቀ ቅንነት የሌለው በአንድ አካል ብቻ ተጎትቶ እየሄደ ያለ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ም/ቤት ሰብሳቢ እና የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ኦነግ እና ኦፌኮ ከውይይት መቅረታቸውን አረጋግጠዋል። " በድረገጻችን ላይ ለቀናል፣ በዋትስአፕ ላይ ተለቋል። እንደምንሄድ ኮሚቴው ሲወስን ተለቋል። በአካል አነጋሬያለሁ የሚመለከታቸውን ኦሮሚያ የኢትዮጵያ እምብርት ናት እናተ ስለሚመለከታችሁ ለምን አብረን አንሄድም? ብዬ ነግሬያቸዋለሁ። ተጋብዘዋልም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። #Ethiopia #Oromia #VOA #OFC #OLF @tikvahethiopia
Show all...
#OROMIA #PEACE " የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል። በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል። በውይይቱ ፦ - የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤ - ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል። " ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል። " መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል። " በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ብፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል። " የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል። #Ethiopia #Oromia #VOA @tikvahethiopia
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ኤርፖርት የሚመጡ ሁሉ የመንገድ መዘጋቱን ታሳቢ እንዲያደርጉ አሳሰበ። የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በመንገድ ኮሪደር ልማትና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም መንገደኞች ለበረራ ወደ ኤርፖርት በሚሄዱበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳቸው እንዲጠብቁ አሳስቧል። የሚዘጉት መንገዶች #የትኞቹ_ናቸው ? በዚህ ሊንክ ይመልከቱ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88048 #EthiopianAirlines @tikvahethiopia
Show all...
👏 256😡 95 64😭 48🙏 39🤔 14🥰 11🕊 11😢 10😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹 ➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡ በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል። #ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡ የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል። " ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡ Credit - Sheger FM 102.1 @tikvahethiopia
Show all...
27😡 21👏 7🙏 1
ፎቶ ፦ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ ፍትሃትና ባህላዊ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ ፈጽመዋል። ሁለቱ ወጣቶች ማለትም ፦ - ናሁሰናይ አንዳርጌ - አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጥ ከተገደሉ በኃላ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ፌደራል ፖሊስ ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ 2 ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን እና በመጨረሻም ተስፋ መቁረጣቸውን ተናግረዋል። ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ የናሁሰናይ አንዳርጌ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብና በወዳጆች ፍትሃቱና የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ በአባ ጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። አንድ የቤተሰብ አባል ደግሞ " ለቀስተኛው ካለ አስከሬን በተካሄደው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ወደ ቤተ-ክርስቲያን እያመራ ሳለ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የናሁሰናይ ፎቶ እና ስም ያለበትን 2 ባነር በኃይል ተቀብለዋል። ከዚህ ውጭ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ብለዋል። የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል። #Credit - BBC AMHARIC @tikvahethiopia
Show all...
😭 91🙏 10 7😡 7😢 6🥰 5🕊 5👏 1🤔 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#WKU " አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል። ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው። ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል። በየጊዜው እንዲህ ያለ ነገርም እንሰማለን ነው ያሉት። ከጠቆሙት አንዱ ጉዳይ በመምህሯ የተደፈረችን ተማሪ የሚመለከት ነው። በተማሪዎች ስለሚነሳው ጉዳይ ተቋሙ ምን ይላል ? በማለት ጥያቄ አቅርበናል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው አመራር የመምህሩ ጉዳይ #ከ2_ወራት_በፊት መከሰቱን እና ከአስገድዶ መድፈር ጋር በተያያዘ በቅርብ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን ገልጸዋል። " ወንጀሉን ከ2 ወራት በፊት እንደፈጸሙ የተጠረጠሩት መምህር በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ነው " ብለዋል። ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ ? በወቅቱ አንድ የሂሳብ መምህር በክፍል ውስጥ ሆነው ከተማሪዎቻቸው አሳይንመንት በመቀበል ላይ ነበሩ። የአንደኛዋን ተማሪያቸውን ወረቀት ግን ሳይቀበሉ ነበር የወጡት። ይሁንና " #አልቀበልሽም " የተባለችው ተማሪም ምን አድርጌ / ምንስ አጥፍቼ ነው ? ብላ በምትጨነቅበት ሰአት ከክፍሉ ተጠሪ ያገኙትን ስልክ ተጠቅመው የደወሉላት መምህር  " አሳይመንትሽን ቤቴ መጥተሽ ማስረከብ ትችያለሽ " ይሏታል። ተማሪዋም በተሰጣት አድራሻ ተመርታ ወደተባለችው ቦታ ትሄዳለች። የጠበቃት ግን አሳይመንቱን መቀበል ሳይሆን ሌላ ነበር። ተማሪዋ እያነባች ጓደኛዋን ይዛ ወደሆስፒታል ካመራች በኃላ በሆስፒታል ህክምና አግኝታለች። የሆስፒታል ማስረጃዋን ይዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሂዳ አመልክታቸለች። በወቅቱ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዋ አቤቱታና በቀረበዉ የህክምና ማስረጃ  መሰረት ጉዳዩን ወደ #ዲስፕሊን በመዉሰድ በፍጥነት መምህሩን ከስራ ሊያግድ ችሏል። መምህሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ #ራሱን_ደብቆ እና ስልኩን አጥፍቶ ቆይቷል ተብሏል። የዩኒቨርስቲው አስተዳደር #የስራ_እግድ ማሳለፉንም ተከትሎ ከተደበቀበት በመዉጣት ሲመለስ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው በመረከብ ይዞ መምህሩን ሲያፈላልግ የነበረው ፖሊስ #በቁጥጥር_ስር ሊያውለው ችሏል። አሁን ላይ የምርመራ ሂደቱ አልቆ ፍርዱን እየተጠባበቀ ሲሆን ወደፊት የፍርድ ሂደቱ የሚገለጽ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ከሰሞኑ በዚሁ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት ተማሪና አንድ መምህር መጉዳቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል👉 https://t.me/tikvahethiopia/88025 @tikvahethiopia
Show all...
😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ሰዓት! ሕብር ሞባይል ባንኪንግን በማውረድ ሂሳብዎን በቅርበት እና በቀላሉ ይከታተሉ፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ! https://www.hibretbank.com.et/hibir-mobile-landing-page/ ሕብረት ባንክ በሕብረት እንደግ! ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡     ቴሌግራም- https://t.me/HibretBanket     ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/     ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/ #Hibretbank
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#SouthAfrica ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪቃ " የ2024 ምርጫ " ተደርጎ ነበር። በምርጫው ማንም አሸናፊ አልሆነም። የዘንድሮ ምርጫ ገዢው ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት / ANC / 40.18 በመቶ ድምጽ በማግኘት ቀዳሚ ቢሆንም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምጽ ግን አላገኘም። ፓርቲው በ30 ዓመታት የመሪነት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አብዛኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ተነጥቋል። በዚህም መንግሥት ለመመስረት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መጣመር ግድ ይለዋል። ፓርቲው ምክር ቤቱ ካለው 400 መቀመጫዎች 159 ብቻ ነው ያሸነፈው። የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ መንግሥት ለመመስረት #ከተቃዋሚዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አመልክተዋል። በምርጫው 87 መቀመጫዎችን ያሸነፈው የመሃል ቀኝ ዘመሙ ዴሞክራሲያዊ ጥምረት (DA) ነው። ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ንግግር ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል። ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የቀድሞ ፕ/ት ጃኮብ  ዙማ ፓርቲ MK ሲሆን ከገዢው ፓርቲ ጋር የመነጋገር ፍላጎት ቢኖረውም " ራማፎዛ ሥልጣን ላይ እያሉ ንግግር አላደርግም " ማለቱን ዶቼ ቨለ ዘግቧል። በዘንድሮ ሀገር አቀፍ ምርጫ እጅግ በርካታ #ወጣቶች ድምፅ መስጠታቸው የተሰማ ሲሆን ገዢውን ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት /ANC/ በድምጻቸው #ቀጥተውታል። ለዚህ ደግሞ  ፦ - የከፋ ሙስና - የመልካም አስተዳደር ችግር - ስራ አጥነት መፋፋት - የወንጀል መባባስ ... ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተነግሯል። @tikvahethiopia
Show all...
👏 393 111😢 33🙏 26😱 23🕊 16🤔 13🥰 12😭 11😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
#እንድታውቁት #AddisAbaba በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ መዚህ መሰረት ፡- - ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ እንዲሁም #በውስጥ_ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ #በየዕለቱ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ። አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ #AddisAbabaPolice @tikvahethiopia
Show all...
😡 419 146👏 59🙏 49😢 21😭 17🤔 14🕊 14🥰 10
Photo unavailableShow in Telegram
#Axum #Tigray " በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! " ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦ " ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው።  ብርሃን አየን። በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው። ብዙ ለውጥ ነው ያለው። በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን  መተኛት እንችላለን። ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። " #Ethiopia #TigrayRegion #Peace @tikvahethiopia
Show all...
😢 404😭 86🕊 39 34🤔 10🥰 3😱 3