cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Show more
Advertising posts
122 215
Subscribers
-22424 hours
-1 1317 days
-5 68430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ሊገነቡ ነው፡፡ ከፍተኛ የአውሮፕላን ማረፍያ በሌለባቸው ነገር ግን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አሉባቸው በሚባልባቸው አካባቢዎች ትናንሽ አየር ማረፍያዎች እንደሚገነቡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስትክስ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በእጅጌ የኢትዮጵያ መንግስት ለአዳዲስ የአውሮፕላን ማረፍያዎች ግንባታ የሚሆን በጀት አለመያዙን ተናግረው አሁን የሚገነቡ ትናንሽ አየር ማረፍያዎች በተለያዩ ወጪዎች የሚሸፈኑ ይሆናል ብለዋል፡፡ በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የሚገነቡት 23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ተለይተው መታወቃቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ የአዋጭነት ጥናት የመሬት ጥናት እና ሌሎችም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡እነዚህ ግንባታዎች በራሳቸው ወጪ ለማከናወን የክልል መንግስታት ፍላጎት ማሳየታቸው የተነገረ ሲሆን ባለሃብቶችም ጭምር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተነገረው፡፡ Via Ethio FM @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 27 15😁 8
Photo unavailableShow in Telegram
79 አባላት ያሉት የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የተመራ 79 አባላትን የያዘ የሳዑዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለጹ። ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን አምባሳደር ነብዩ ገልጸዋል።ቡድኑ ዛሬ ማታ አዲስ አበባ እንደሚገባና በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎች ይጎበኛል ብለዋል። በሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች በኢትዮጵያ ስላሉት ምቹ የኢንቨስትመንትና ንግድ አማራጮች ለባለሀብቶቹ ገለፃ የሚደረግበት የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል። የልዑካን ቡድኑ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በሀይል ማምረት፣ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንዲሁም በሌሎች ቁልፍ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ያሉትን እድሎች ለመገንዘብ እንደሚፈልግም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳውዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል። @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 18👎 7😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
የተወካዮች ምክር ቤት ህወሓት ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን የአዋጅ ማሻሻያ አጸደቀ! የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አጸደቀ። በ2011 ዓ.ም. የወጣውን “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን” የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በሁለት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው። “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ፤ “ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል” በሚል “ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ” የተደረገው ህወሓት በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል። “አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” ሲል ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
😁 41👍 21👎 6 4
ትግራይ ክልል እየተጠቀመበት ባለው ዐዲስ ደንብ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ታዘዘ! የትግራይ ክልል፣ ካለፈው ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ እንዲኾን ያጸደቀው ደንብ ቁጥር 4/2016 እንዲሻር በቀረበው አቤቱታ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ መታዘዙን፣ ሂዩመን ራይትስ ፈርስት የተባለ፣ ሀገር በቀል የመብቶቸ ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ። የድርጅቱ ምክትል ዲሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የወጣው ደንብ፥ በጦርነቱ ወቅት ለወጡትና ከሕገ መንግሥቱ ጋራ ለሚቃረኑት ሕጎች እውቅና የሚሰጥ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ድርጅታቸው፣ ዐዲሱ ደንብ እንዲሻር፣ ለፌደራል የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ማቅረቡን አመልክተዋል፡፡ጉባኤውም አቤቱታውን በመመልከት፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ማዘዙን ተናግረዋል፡፡ፍትሕ ሚኒስቴርም በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ታዟል። [VoA] @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 16
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
Show all...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
“በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ “በልዩ ሁኔታ” ለመመዝገብ ማመልከቻ ባቀረበ “በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ምዝገባው እንዲፈጸም” የሚያደርግ አዋጅ ነገ በፓርላማ ሊጸድቅ ነው። ➡️ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ ምዝገባ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ምርጫ ቦርድ የሚኖረውን ስልጣን የሚወስኑ ድንጋጌዎች የተካተቱት፤ ይህንኑ በተመለከተ በ2011 ዓ.ም የጸደቀን አዋጅ ለማሻሻል በቀረበ የህግ ረቂቅ ላይ ነው። ➡️ የተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ ግንቦት 26 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው ከሚመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ ይኸው የአዋጅ ማሻሻያ እንደሆነ በስብሰባ አጀንዳ ማሳወቂያ መልዕክቱ ላይ አስፍሯል። ➡️ የተወካዮች ምክር ቤት አዋጁ ለውይይት እንዲቀርብ ቀጠሮ የያዘው፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራሩ ወጣ ባለ መልኩ የህግ ረቂቁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተመራለት በ3 ቀናት ጊዜ ውስጥ ነው። ➡️ ይህ የአዋጅ ረቂቅ፤ በነባሩ አዋጅ የተካተቱ 3 አንቀጾች ላይ ብቻ ማሻሻያ የሚያደርግ ነው። ከማሻሻያዎቹ መካከል፦ ⭕️ “አንድ የፖለቲካ ቡድን ሀይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” የሚለው ይገኝበታል። ⭕️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ መልኩ የቀረበለትን ማመልከቻ ውድቅ የማድረግ አማራጭ በአዋጁ ባይሰጠውም፤ በፓርቲው ላይ ለሁለት ዓመታት “ክትትል እና ቁጥጥር” የማድረግ ስልጣንን ግን ያገኛል። 🔴ዝርዝሩ 👉 https://ethiopiainsider.com/2024/13159/ Via Ethiopia Insider @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
😁 47👍 28👎 3 3
Photo unavailableShow in Telegram
በኮሬ ዞን በልጃገረዶች ጠለፋ ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ሰዎች በፖሊስ መያዛቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በተደረገ ህዝባዊ ንቅናቄ ሁለት ታዳጊ ሴት ተማሪዎች ከጠላፊዎቻቸው ነጻ መውጣታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።በዞኑ በታዳጊ ሴቶች ጠለፋ ላይ የተሳተፉ 12 ሰዎች በቁጥጥር መዋላቸውን ደግሞ ፖሊስ ገልጿል። በዞኑ እየተባባሰ መጥቷል የተባለውን የታዳጊ ሴቶች ጠለፋ ለመግታት ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ መጀመሩን ዶቼ ቬለ ከአካባቢው ባለስልጣናት ተረድቷል። ህዝባዊ ንቅናቄው እንዲጀመር የምክር ቤት አባላት እና እና የህግ አካላት ትኩረት መስጠት መጀመራቸው በምክንያትነት ተጠቅሷል። በዞኑ በተለይ ችግሩ ጎልቶ በሚታይበት የጎርካ ወረዳ አሁንም ድረስ በጠላፊዎች እጅ የሚገኙ ጥቂት የማይባሉ ታዳጊ ሴት ተማሪዎች እንደሚገኙ ዴቼ ቬለ ከአካባቢው ማህበረሰብ ያሰባሰበው መጃ ያመለክታል። ተማሪዎቹን ለማስለቀቅም ብርቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም እንዲሁ። የኮሬ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠለፋ ጥቃት ያደረሱ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ ለወረዳዎች በደብዳቤ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ መሻሻሎች መታየት መጀመራቸው የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ Via DW @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 19 4
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ከግዛቷ እንደምታስወጣ ካሳወቀች በኋላ አሜሪካ ውጥረት እንዲረግብ ጠየቀች! የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር በነበራቸው የስልክ ንግግር በቀጠናው ያለው ውጥረት መርገብ እንዳለበት አሳስበዋል። ብሊንክ ቅዳሜ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም. ከሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ጋር በነበራቸው ውይይት ቀጠናዊ ውጥረትን መቀነስ አስፈላጊነት ለፕሬዝዳንቱ መናገራቸው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። የብሊንከን እና የፕሬዝዳንት ሐሰን የስልክ ውይይት የተደረገው፤ የሶማሊያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማስወጣት የመወሰኑ ዜና ከተሰማ በኋላ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት መፈረሟ ይታወሳል።ይህ የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መንግሥታት ሰምምነት ሶማሊያን እጅጉን ከማስቆጣቱ ባሻገር በሞቃዲሾ እና አዲስ አበባ መካከል ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ውጥረት አስከትቷል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት ሑሴን አሊ በሶሻል ሚዲያ የውይይት መድረክ ላይ በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በአውሮፓውያኑ 2024 ማብቂያ ላይ ከሶማሊያ ጠቅልለው ይወጣሉ ብለዋል። በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር ተሰማርቶ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ትራንዚሽን ሚሽን ኢን ሶማሊያ (አትሚስ) (የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ተልዕኮ) በ2024 መጨረሻ ቆይታው ይጠናቀቃል። ይሁን እንጂ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪው ዓርብ ምሽት በነበረ የኤክስ ውይይት ላይ ሶማሊያ የአትሚስ ኃይል ተሳታፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ከተልዕኮው ወጪ ሆነው ከኬንያ፣ ከጂቡቲ፣ ከኡጋንዳ እና ከቡሩንዲ በተወጣጡ ወታደሮች ተልዕኮው በአንድ ዓመት እንዲቀጥል ፍላጎት አላት ብለዋል። “የኢትዮጵያ ሠራዊት የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ እንደማይካተት እና በአገሪቱ እንደማይቆይ ግልጽ ውሳኔ አሳልፈናል” ያሉት ሑሴን አሊ፤ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአገሪቱ እንዳይቆይ ውሳኔ ያስተላለፈችው በሁለቱ አገራት መካከል በተፈጠረው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሠራዊት ለአካባቢው አደገኛ ነው ተብሎ የነበረውን የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ቡድንን ዛቻ ተከትሎ ወደ ሶማሊያ ዘልቆ በመግባት የቡድኑን መዋቅር በማፈራረስ ለሶማሊያ መንግሥት መጠናከር ድጋፍ አድርጓል። ከዚያም በኋላ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተልዕኮዎች ስር በመሆን አል ሻባብ በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ላይ የደቀነውን አደጋ ለመግታት ከፍተኛ ሚና ሲጫወት መቆየቱ ይነገርለታል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 39😁 11 2🔥 2👀 1
ኢሕአፓ ያስቀመጥኳቸው ቅደመ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ከሀገራዊ ምክክሩ ራሴን አግልያለሁ አለ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ( ኢህአፓ ) ያስቀመጣቸው ቅደመ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሀገራዊ ምክክር ሂደት ራሱን ማግለሉን ለአሻም በላከላት መግለጫ አመልክቷል። ይህ በስድስት ገጾች የተቀነበበው መግለጫ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የኮሚሽነሮች ጥቆማ፣ ገለልተኝነት፣ የኮሚሽኑ ተጠሪነት በአንድ ፓርቲ የበላይነት ለተያዘ ምክር ቤት መሆኑና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ጠቅሶ ዳራውን ያስታውሳል። ከወቅታዊ ሁኔታም አንፃር ያሉትን የሰላምና ፀጥታ፣ የሰላማዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አስቻይ ሁኔታ አለመኖርን አትቶ፣ በዝርዝር ቅደመ ሁኔታዎቹን አስቀሞጦ ከዛሬ ጀምሮ ከሂደቱ ራሱን እንዳገለለ በይፋ አረጋግጧል። Via Asham @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👏 23👍 10😁 9 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ሥራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ! ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ሥራ ምክንያት ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየዕለቱ የልማት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በመንገድ ኮሪደር ልማትና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል። በዚህ መሰረትም፤ 👉 ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ 👉 ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ 👉 ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየዕለቱ የልማት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
👍 29👎 8 4