cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
13 457
Obunachilar
+12124 soatlar
+8597 kunlar
+3 24430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

​​✞ ምስጋና ላቅርብ ✞ ምስጋና ላቅርብ ለሥላሴ (፪) በእጅህ በረከት ተባረከች ነፍሴ ምስጋና ላቅርብ ለሥላሴ      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኸኝ እግዚአብሔር ከፍጥረታት አከበርከኝ በአምሳልህ እኔን ፈጠርከኝ ከፍጥረታት አከበርከኝ በአርአያህ እኔን ፈጠርከኝ      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ለፈጣሪ ለሥላሴ ሳትሰለች ትዘምር ነፍሴ ስሙን ጠርታ እረክታለች እንደ መልካም ዛፍ ለምልማለች፪      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የምወጣው የምገባው ሁሉን ነገር የማደርገው ጀምሬም የምቋጨው እግዚአብሔርን ጠርቼ ነው ሥላሴንም ጠርቼ ነው፪      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ስሉስ ቅዱስ ያከብራሉ ባመሟልም ያደርጋሉ በሥላሴ ከብሬያለሁ ልጅነትን አግኝቻለሁ፪            መዝሙር| ዲ/ን ልዑልሰገድ ጌታቸው ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Hammasini ko'rsatish...
3🙏 2
🧡 ሼር 🧡
Hammasini ko'rsatish...
YEZEMARIT BEZAWORK asfaw MEZMUROCHI SBISBI /የዘማሪት ቤዛወርቅ አስፋው መዝሙሮች ስብስብ@YESAGIDULOTU

suscribe THIS CHANNAL FOR ORTHODOX ANS ERITIRAN MEZMUR

2
ዐሥራ ሦስት የአብነት ደቀ መዛሙርት ዲቁና ተቀበሉ | ጃንደረባው ሚድያ | ግንቦት 6 2016 ዓ.ም.| አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በጃን እስጢፋኖስ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአዳር የአብነት ትምህርት ያስተማራቸውንና መሥፈርቱን ያሟሉ ዐሥራ ሦስት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሄኖክ አንብሮተ ዕድ ማዕረገ ዲቁናን ተቀብለዋል:: የኢጃት ቦርድ ሰብሳቢ ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት "ኢጃት ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በጃን ማዕተብ ከሰባ በላይ ንዑሰ ክርስቲያንን ለምሥጢረ ጥምቀት ፣ ብዙኃንን በጃን ዮሐንስ ለምሥጢረ ንስሓና ቁርባን ፣ በጃን ቃና ዘገሊላ ደግሞ ለምሥጢረ ተክሊል ያበቃ ሲሆን አሁን ደግሞ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ለምሥጢረ ክህነት አብቅቶአል" ብለዋል:: "ዲያቆናቱ በአግባቡ የተማሩና ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ናቸው" ያሉት የጃን እስጢፋኖስ ሰብሳቢ መምህር ኤፍሬም ሲሳይ ሲሆኑ "ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት ትምህርት ሳይኖራቸው ወደ ኢጃት መጥተው በአግባቡ ተምረው ለዚህ በመብቃታቸው እጅግ ደስ ብሎናል:: ትምህርት ሳይጨርሱ ወዴትም እንዳይሔዱ በማስገደድም በአበው ልማድ መሬት ላይ እየተኙ በሌሊት እንዲማሩና ከአብነት ትምህርቱ ጋር መሠረታዊ ነገረ ሃይማኖትም እንዲማሩ ተደርጓል" ብለዋል:: በማያያዝም "በቅርቡ ሱባኤ እስጢፋኖስ የተሰኘ የዲያቆናት ብቻ ሱባኤ ጉባኤ ለማካሔድም ዝግጅታችንን ጨርሰዋል ብለዋል" ዲያቆናቱን አስተምረው ለዚህ ካበቁ መምህራን መካከል አንዱ የሆኑት መምህር ኃይለ ኢየሱስ ተሻለ በበኩላቸው "ወደ አገልግሎት ለመግባት በአግባቡ ደጅ ጸንተውና የአገልግሎቱን ምንነት ተረድተው ለዚህ መብቃታቸው ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ ለማገልገል ያስችላቸዋል:: ለዚህ ደርሰው ማየታችን ለኢጃት ትልቅ ደስታ ነው" ብለዋል::
Hammasini ko'rsatish...
7👍 2🙏 1😘 1
✞ ድንቅ አድርጎልኛል ✞ ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ (፪) አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ (፪)             አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ ድንቅ አድርጎልኛል ረክሼ ሳለሁ ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምጻቱ ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ             አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ ድንቅ አድርጎልኛል እንዲ ለወደደኝ             አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Hammasini ko'rsatish...
🙏 3👍 2 2
🧡 ሼር 🧡
✝️ በታላቅ ሥልጣን ተነሳ ✝️ እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት የኔታ #አባ_ገብረኪዳን_ግርማ https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1
Hammasini ko'rsatish...
4👍 1
✞ ሞት ይደንግጥ ✞ ሞት ይደንግጥ የአንተን ስም ሰምቶ ይሰንጠቅ ቀላዩ በግርማ ተረትቶ ቁጣውም ጸጥ ይበል ይራቅ አለማመን አሸናፊ ጌታ አንተ ብቻ ግነን(፪) ስምህ ላላመኑት የሚያፍገመግም ነው ሞትና ጨለማን ረትቶ የሰቀለው ድንጋያችንን ሰብረህ ጥለኸዋልና ድል መንሳቱ የለም ተሸንፏልና(፪)      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ሞትን እንቅልፍ አርገህ ቀይረህልናል እረፍት የምናልፈው ድልድያችን ሆኗል ትንሳኤህ ሰበረው መቃብሩን ሁሉ ቢሞቱ ያው ናቸው ያመኑ በሙሉ(፪)      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አለን በእምነት የምንወርሰው ስምህን ተሸክመን ነፍሱን ለአንተ የሚያኖር አያጣትምና ልባችንን ሰጠን ቀድሰው ግባና(፪)      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የአንተ ስም ሲሰማ ፈታኙ ደንብሯል ጌርጌሴኖን ያለው ሌጌዎን ተሰዷል ስንቱን አሳረፍከው ከከሳሹ እጆች አይደፍርም ከእንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጆች(፪)                   መዝሙር|      ዘማሪት| ፋንቱ ወልዴ "..ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።"                 ኢሳ ፳፭፥፰ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 2
🧡 ሼር 🧡
✝️ ሲጨንቃችሁ እንዲህ በሉ ✝️ እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት የኔታ #አባ_ገብረኪዳን_ግርማ https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1
Hammasini ko'rsatish...
3