cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

THIQAH

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
11 695
Obunachilar
+14324 soatlar
+3757 kunlar
+20030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
የእስራኤሉ ጠ/ሚ ኔታንያሁ እሁድ በራፋህ የተፈፀመው የአየር ጥቃትን " አሳዛኝ ስህተት ነው " ማለታቸው ተሰምቷል። ጉዳዩ እንደሚጣራም ገልጸዋል። በእስራኤል የራፋ ጥቃት 45 ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾቹ ጦርነት ሸሽተው በራፋ መጠለያ የተጠለሉ ተፈናቃይ፣ ሴቶች ፣ ህጻናት ይገኙበታል። @thiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
😡 34😭 12😱 2
“ከ2,000 የሚበልጡ ዜጎች ከነሕይወታቸው ተቀብረዋል“ - ተ.መ.ድ ሰሞኑን የመሬት መንሸራተት አደጋ ባጋጠማት በፓፑዋ ጊኒ ከ2,000 የሚበልጡ ሰዎች ከነሕይወታቸው መቀበራቸውን የተ.መ.ድ አስታውቋል፡፡ በኢንጋ ግዛት የሚገኘው የማንጎሎ ተራራ ተንዶ በአካባቢው ያሉ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ተብሏል። የመሬት መንሸራተት አደጋው አሁንም መቀጠሉና ችግሩን ለመቆጣጠር አዳጋች መሆኑን ተነግሯል። #Gulftoday @thiqaheth
Hammasini ko'rsatish...
😱 14😭 10👍 1 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፒርስ ሞርጋን ፦ " በራፋ የታዩት ክሰተቶች እጅግ አሰቃቂ ናቸው። ከኦክቶበር 7 በኋላ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብቷን ደግፊያለሁ ነገርግን በስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚገኙ እጅግ ብዙ ንፁሀኖችን መግደል ተቀባይነት የለውም። ይህንን ልከላከል አልችልም። ኔታንያሁ አሁኑኑ ማቆም አለባቸው። " @tiqhaEth
Hammasini ko'rsatish...
😭 24👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል ትናንት ምሽት ራፋ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 35 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በተጠጉበት መጠለያ ስፍራ መሆኑ ነው የተገለጸው። ከሟቾቹ የሚበዙት ሴት እና ህጻናት ናቸው። ድርጊቱ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እጅጉን አስቆጥቷል። እስራኤልም ጥቃቱን እንድታቆም እየተጠየቀ ነው። @thiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
😭 57👍 7😡 4🤔 2
“ከ2,000 የሚበልጡ ዜጎች ከነሕይወታቸው ተቀብረዋል“ - ተ.መ.ድ ሰሞኑን የመሬት መንሸራተት አደጋ ባጋጠማት በፓፑዋ ጊኒ ከ2,000 የሚበልጡ ሰዎች ከነሕይወታቸው መቀበራቸውን የተ.መ.ድ አስታውቋል፡፡ በኢንጋ ግዛት የሚገኘው የማንጎሎ ተራራ ተንዶ በአካባቢው ያሉ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ተብሏል። የመሬት መንሸራተት አደጋው አሁንም መቀጠሉና ችግሩን ለመቆጣጠር አዳጋች መሆኑን ተነግሯል። #Gulftoday @thiqaheth
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በቴክሳስ፣ ኦክላሆማ እና አርካንሳ በጣለው ዓውሎ ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ 20 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ዓውሎ ነፋሱ መኖሪያ ቤቶችን እና የከባድ መኪና ሾፌሮችን መጠለያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ቤቶችን ፓርክ አውድሟል። በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች ካለ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል። ማዕበሉ ዛሬ ሰኞ ወደ ምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል በማምራት ከአላባማ እስከ ኒው ዮርክ ያሉ ግዛቶችን እንደሚመታ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች በመናገር ላይ ናቸው። በኬንተኪ አገር ገዢው ዛሬ ማለዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። አውሎ ነፋሱ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም አስተውቀዋል። በቴክሳስ ግዛት 100 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ከ200 በላይ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎችም ሕንጻዎች ወድመዋል። #ቪኦኤ @thiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
👍 7😢 5🤔 1
#Scholarship የጣልያን መንግሥት ለውጭ ሀገራት ተማሪዎች ያመቻቸው የ2024 -2025 ስኮላርሺፕ የማመልከቻው ቀን በቀጣይ ወር ሰኔ 14 /2024 ያበቃል። ፍላጎት ያላችሁ ከላይ PDF ፋይሉን ክፈቱና ዝርዝሩን ተመልክታችሁ በቀረው ጊዜ ውስጥ ማመልከት ትችላላችሁ። የኢትዮጵያ 🇪🇹 ተማሪዎች የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተመላክቷል። በማስተርስ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በPhD ፣ ለሪሰርች ፕሮጀክት ... ማመልከት ይቻላል። ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች እና የማመልከቻ አድራሻዎችን ከላይ ካለው ፋይል ማግኘት ይቻላል። መልካም ዕድል ! @thiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
👍 33 21🙏 4😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ከቀናት በፊት የመሬት መንሸራተት አደጋ በገጠማት ፓፑዋ ጊኒ የሟቾቹ ቁጥር በትንሹ 670 ደርሷል። 1,182 ቤቶች የመስመጥ አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል። በኢንጋ ግዛት የደረሰው አደጋው 6 የገጠር ቀበሌዎችን ማካለሉ ተነግሯል። @ThiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
😭 17👍 5😢 4
04:21
Video unavailableShow in Telegram
በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚፈጸመው የግድያ መጠን ባለፉት ሃያ አመት ከታየው እጅግ ከፍ ብሏል። ከዓለም ከፍተኛውን ደረጃም ይዟል። ባለፈው አመት ብቻ ከ27,000 በላይ ግድያዎች ተፈጽመዋል። ማህበረሰቡ በፖሊስ ላይ ያለው እምነት እየተመነመነ ይገኛል። #BBCAfricaEye በሀገሪቱ ወንጀለኞችን የሚዋጉትን ​​የማህበረሰብ ክፍሎች በተመለከተ የሰራውን ዶክመንተሪ እንድታዩት ጋበዝናችሁ  youtu.be/Qk9HEzcFiZ4 @thiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
👍 11😢 7 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፎቶ፦ ዛሬ ይህ የኳታር አየር መንገድ የሆነው " ቦይንግ 787 ድሪምላይር " በረራ ቁጥ QR017 አውሮፕላን ከዶሃ ወደ አየርላንድ ሲበር አየር ላይ መነዋወጥ አጋጥሞታል። 12 ሰዎች ላይ ተጎድተዋል። ከተጎዱት 6ቱ መንገደኞች ቀሪዎቹ የበረራ አስተናጋጆች ናቸው። ክስተቱ ለ20 ሰከንድ የቆየ ሲሆን ለመንገደኞዥ ምግብ እና መጠት ሲቀርብ ነው የተፈጠረው። ክስተቱ ከተፈጠረ በኃላ ደብሊን ኤርፖርት አርፏል። የኳታር አየር መንገድ ስለ ክስተቱ ማረጋገጫ ሰጥቷል። ጥቂት ቁጥር ያላቸው መንገደኞች አየር ለይ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና የህክምና ላይ እንዳሉ ገልጿል። ምርመራ እንደሚደረግም አመልክቷል። ከቀናት በፊት 211 ሰዎችን ባሳፈረ የሲንጋፖር አወሮፕላን ላይ ተመሳሳይ ክስተት ገጥሞ አንድ መንገደኛ ህይወቱ ሲየልፍ 30 ተጎድተዋል። መረጃው የአልጀዚራ ነው። @thiqahEth
Hammasini ko'rsatish...
😱 25👍 12😭 6😢 4 1