cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Deleted channel

WeCare is Ethiopia’s digital healthcare platform where treatment seekers can discover practitioners to directly book appointments for online consultation or in clinic visits. [email protected] https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
5 069
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-130 kunlar
Postlar arxiv
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የኢሬቻ በዓልን ለምታከብሩ በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን እንመኛለን። Paartiin Lammiilee Itiyoophiyaa Haaqa Hawaasummaaf kabajoota ayyaana Irreechaa baga nagaan geessan jechaa ayyaanni kan nagaa fi jalaala akka ta’u ni haawwina. #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የኢሬቻ በዓልን ለምታከብሩ በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆንልን እንመኛለን። Paartiin Lammiilee Itiyoophiyaa Haaqa Hawaasummaaf kabajoota Ayyaana Irreechaa Baga Nagaan Geessan Jechaa Ayyaani Kan Nagaa fi Jalaala Akka Nuu Ta’u Ni Hawwina. #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Repost from WeCare ET
የዊ ኬር ዲጂታል ሄልዝ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ቤቴል ደረጀ በኒውዮርክ በተካሄደው የዓለም ዓቀፉ የማሕጸን ካንሰር ማህበር (IGCS) ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከ Global fellowship program በመመረቃቸው ደስ ብሎናል። በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ዶ/ር ዳዊት ካሳና ዶ/ር ብሩክ ጋሻውበዛ ከኢትዮጵያ ሌሎቹ ተመራቂዎች ነበሩ። በዚህ ፕሮግራም እንደ ሀገር ከፍተኛውን ቁጥር ያስመረቀችውም ኢትዮጵያ ናት። ዊኬር ዲጅታል ሄልዝ ለሁላችሁም ተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልዕክቱን ያስተላልፋል።
Hammasini ko'rsatish...
Well deserved! Congratulations, Madame.
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅን ኅልፈት ስሰማ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ሥራዎቹ ለሀገር ፍቅር እና ለወገን ክብር የነበረውን ተቆርቋሪነት አንረሳውም። ሀገራችን ስትደፈር በየማሰልጠኛዎች እና ግንባር ድረስ በአካል በመገኘት ለሠራዊቱ ደጀንነቱን አሳይቷል። ነፍስህ በሰላም ትረፍ።
Hammasini ko'rsatish...
00:30
Video unavailableShow in Telegram
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
5.98 MB
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ ይሁንላችሁ !
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የወጣቶች መምርያ እሑድ መስከረም 08/ 2015 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት የፓርቲው ህገ ደንብ እና ፕሮግራም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ስለሚሰጥ የፓርቲያችን ወጣት አባላት እንድትገኙ ጥሪ እናቀርባለን። የኢዜማ ወጣቶች መምርያ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
ዴሞክራሲን እውን ማድረግ የሚቻለው የጠንካራ ተቋማት ግንባታ ሲኖር ብቻ ነው! ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም ዓለምአቀፉ የዴሞክራሲ ቀን ለ15ኛ ጊዜ ታስቦ ይውላል፡፡ ዴሞክራሲ የአንድ ሀገር ማህበረሰብ ራሱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ እንዲወስን ዕድል የሚሰጥ ሥርዓት ነው፡፡ በተጨማሪም ዴሞክራሲ ስህተትን ለማረም ያለው ጠቀሜታም ከፍተኛ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የህግ የበላይነት እንዲሰፍን በማድረግ የቁጥጥር እና ግምገማ ሂደትን የሚያሳልጥ ለተጠያቂነት አመቺ የሆነ ሥርዓት መሆኑንም የተለያዩ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚጨነቅ የትኛውም ማህበረሰብ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባው ጉዳይ የተቋማት ግንባታ ዕውን መሆንን ነው፡፡ ዴሞክራሲ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ጠንካራ ተቋማት በሌሉበት ሁኔታ ዕውን ሊሆን አይችልም፡፡ የአንድ ሀገር የፍትሕ ሥርዓት ህግን ብቻ መሰረት አድርጎ ከመስራት ይልቅ የጥቂት ግለሰቦችን ፍላጎት ለማስፈፀሚያነት የሚያውል ከሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቅዠት ሆኖ ይቀራል፡፡ ሚዲያዎች በሙያዊ ሥነምግባር ታንፀው ማህበረሰባቸውን ከማገልገል ይልቅ የጥቂቶች የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ከሆኑ ዴሞክራሲ ትሞታለች፡፡ ሀገራዊ ምርጫዎች ጊዜያቸውን ጠብቀው ከመደረጋቸው ባለፈ ለተወዳዳሪዎች ሁሉ እኩል ሜዳ የማይመቻችባቸው ከሆነ በዴሞክራሲ ስም አምባገነንነት ይነግሳል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከልባቸው ለንፁህ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት ታምነው ፓርቲና መንግስትን ካልለዩ፤ በውስጣቸውም ዴሞክራሲን ካልተለማመዱ ሀገር የጥቂቶች መቀለጃ ትሆናለች፡፡ የሲቪል ማህበራት ህብረተሰቡ በጥቅሞቹ ዙሪያ እንዲደራጅ ካላነቁ፤ መብቱን የማይጠይቅ እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ በንቃት የማይሳተፍ ትውልድ ከተፈጠረ፤ ዴሞክራሲ ቅንጦት ይሆናል፡፡ በመሆኑም፤ በዛሬው ዓለምአቀፍ የዴሞክራሲ ቀን የምናስተላልፈው መልዕክት  የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ትኩረት እንዲሰጠው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ብዙ ትግሎች ተደርገዋል፡፡ “ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም” በሚል መርህ የህይወት መስዕዋትነት ጭምር ያስከፈሉ ትግሎች  እንደነበሩም ታሪክ የመዘገበው ሀቅ ነው፡፡ ይህ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕውን መሆን በትውልድ ቅብብሎሽ የተደረገ ትግል እና የተከፈለ መስዕዋትነት ፍሬ የሚኖረው ነፃ፤ ገለልተኛ እና ጠንካራ ተቋማት ሲኖሩ ብቻ መሆኑን ኢዜማ አጥብቆ ያምናል፡፡ በሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ገና በጅምር ደረጃ ላይ ያለ በመሆኑ፤ ከዚህ አኳያ በሀገር ደረጃ  ብዙ ስራዎች ይቀራሉ፡፡ ላለፉት አራት ዓመታት በሀገራችን የፖለቲካ ለውጥ እንደሚመጣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በስፋት ቃል ቢገባም፤ የቃሉን ያህል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቀናዒነት በተግባር አላሳየም፡፡ ይህም በሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕውን እንዲሆን ለሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ቅሬታን የፈጠረ ነው፡፡ በተለይ በመንግስት በኩል ይህ አዝማሚያ በፍጥነት ተስተካክሎ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ሂደት ከልብ በመነጨ ተነሳሽነት እንዲከወን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲም ሆነ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለዴሞክራሲ ያላቸውን ተነሳሽነት ቢያንስ በፓርቲ ውስጠ ዴሞክራሲ ሊያሳዩ እንደሚገባ ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡  በመጨረሻ  የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ሲቪክ ማህበራት፤ ማህበረሰብ አንቂዎች፤ ሚዲያዎች፤ የሚመለከታቸው ተቋማት ሁሉ ለዴሞክራሲዊ ተቋማት ግንባታ ዕውን መሆን በትኩረት እንዲሰሩ እንጠይቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
1) የኢዜማ ብሔራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሳፍንት የውጪ ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ ላይ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከ EBC ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://fb.watch/fqQJpiBnxK/ እና https://fb.watch/fqQPDxBd4H/ 2) የኢዜማ ም/መሪ ዮሐንስ መኮንን ከእንደገና ባገረሸው የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት ዙርያ በአሃዱ FM አሃዱ መድረክ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://fb.watch/fwDhlHOT_E/ እና https://fb.watch/fwDobzeZDz/ 3) የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አንድነት ሽፈራው ከእንደገና ባገረሸው የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት ዙርያ ከ ኢ.ፕ.ድ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ https://www.press.et/?p=80726 4) የኢዜማ ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) የ 2014 ዓ.ም ሀገራዊ ኩነቶች እና የፓርቲያችንን ኢዜማ እንቅስቃሴ አስመልክቶ እንዲሁም በ 2015 ዓ.ም ምን ሊሰራ ይገባል የሚለውን አስመልክቶ ከአ.ሚ.ኮ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ይመልከቱ https://youtu.be/t0WJPce4tvM 5) የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ መምርያ ሐላፊ አቶ ዋስይሁን ተስፋዬ የ 2014 ዓ.ም ሀገራዊ ኩነቶች እና የፓርቲያችንን ኢዜማ እንቅስቃሴ አስመልክቶ እንዲሁም በ 2015 ዓ.ም ምን ሊሰራ ይገባል የሚለውን አስመልክቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ https://www.ethiopianreporter.com/110453/ 6) የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ መምርያ ሐላፊ አቶ ዋስይሁን ተስፋዬ የ 2014 ዓ.ም ሀገራዊ ኩነቶች እና የፓርቲያችንን ኢዜማ እንቅስቃሴ አስመልክቶ እንዲሁም በ 2015 ዓ.ም ምን ሊሰራ ይገባል የሚለውን አስመልክቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://fb.watch/fwDLopyaWi/ _____ #ኢዜማን_ይወዳጁ 👉 ቴሌግራም: https://t.me/ethzema 👉 ፌስቡክ: facebook.com/ethzema 👉ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@ethzema?_t=8VTdYbWGIK6&_r=1 👉ትዊተር: twitter.com/ethzema 👉ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCi-FE-Khv-f1hE4ieyjoEIA #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
➔ በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በህወሓት ልክ የኢትዮጵያን ህልውና የተፈታተነ የውስጥ ኃይል የለም። ➔ ህወሓት ... በተለመደ ባህሪው የሰላም ድርድሩን እንደ ጊዜ መግዣ ወስዶ ቀጣይ ጥቃት ለመክፈትና ለጥፋት ዝግጅት እንዳይጠቀምበት እንሰጋለን። ➔ ይህ የሠላም ድርድር ጥያቄ በተራዘመ ጦርነት የሀገርን ኢኮኖሚ በማዳከም፣ ማኅበረሰቡን የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ በመክተት፣ ሕዝባዊ ስልቹነት ውስጥ ለማስገባት ታስቦ የሚደረግ ደባ እንዳይሆን በጥንቃቄ ልናየው ይገባል፡፡ ➔ የሀገርን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስከበር ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስን ኃይል የማዘዝ ሥልጣን ሊኖረው የሚገባው የፌደራል መንግሥት ብቻ ነው። ህወሓት ትጥቁን እንዲፈታ ሊደረግ ይገባል፡፡ ➔ በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚገኙ የፌደራል ተቋማትንም ሆኑ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የመጠበቅና የአየር ክልሉን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር ሥልጣን በብቸኝነት የፌደራል መንግሥቱ መሆኑን ህወሓትም ሊገነዘበው፤ መንግሥትም ሊዘነጋው አይገባም፡፡ ➔ የትግራይ ህዝብ በድርብርብ መከራ ውስጥ እንዲኖር ያደረገው ህወሓት መሆኑ አያነጋግርም፤ ➔ የትግራይ ሕዝብ የሰላም አየር እንዲተነፍስ እና አስፈላጊው ሰብዓዊ እርዳታና መሠረታዊ አገልግሎቶች ማግኘት እንዲችል፤ ህወሓት ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስድ እንደመሆኑ፤ ... ሰላምን እመርጣለሁ ማለቱን መልካም ጅምር አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ➔ ሀገራችን የሉዓላዊነት እና የህልውና ስጋት ተጋርጦባት እንዳትቀጥል በየትም ቦታ በህወሓት የሚመራ ምንም ዓይነት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይገባም። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
<<ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚችለው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በምንም መልኩ ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ ሊሆን ይገባል ብሎ ኢዜማ በጽኑእ ያምናል>> በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በህወሓት ልክ የኢትዮጵያን ህልውና የተፈታተነ የውስጥ ኃይል የለም። የፌደራል ሥልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ በነበረበት የሥልጣን ዘመኑ ልዩነትን የሚያጎላ የብሔርና የቋንቋ ልዩነትን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ተክሎብናል። በዚህም እንደ ሀገር አሁን ለገባንበት ውስብስብ ቀውስ ጥንስሱን የጠመቀው መራራ የልዩነት ድንበር አስምሮ እያገዳደለን ያለው ይኸው የጥፋት ኃይል ነው፡፡ ህወሓት ለሰላማዊ ድርድር ተስማምቼያለሁ ብሎ ጥያቄ ማቅረቡ መጥፎ ባይሆንም በተለመደ ባህሪው የሰላም ድርድሩን እንደ ጊዜ መግዣ ወስዶ ቀጣይ ጥቃት ለመክፈትና ለጥፋት ዝግጅት  እንዳይጠቀምበት እንሰጋለን። መንግሥት እና ሕዝባችን ይህንኑ በመረዳት አስፈላጊውን ዝግጅትና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አጽንኦት ሰጥተን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ይህ ቡድን  "የኃይል የበላይነት አለኝ" ብሎ ባመነበት ጊዜ ሁሉ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያደረሰው ሰቆቃ መቼም የሚረሳ አይደለም። የፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ንፁሀን ዜጎችን ገድሏል፣  እናቶችን፣ ሕጻናትን እና መነኮሳትን ሳይቀር ደፍሯል፣ ንብረት ዘርፏል፤ መዝረፍ ያልቻለውን ሀገራዊ ተቋማትን አውድሟል፡፡ ወቅት እየጠበቀ በተደጋጋሚ አውዳሚ ጦርነትን ከለኮሰ በኋላም ቢሆን አሁን ላይ ለሰላም ዝግጁ ነኝ ማለቱ መጥፎ አይሆንም። ኢዜማ መቼም ቢሆን ለእውነተኛ ሰላም የሚረፍድ ጊዜ የለም ብሎ ያምናል፡፡ ነገር ግን ይህ የሠላም ድርድር ጥያቄ በተራዘመ ጦርነት የሀገርን ኢኮኖሚ በማዳከም፣ ማኅበረሰቡን የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ በመክተት፣ ሕዝባዊ ስልቹነት ውስጥ ለማስገባት ታስቦ የሚደረግ ደባ እንዳይሆን በጥንቃቄ ልናየው ይገባል፡፡ እንደ ኢዜማ እምነት ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንዲቻል የክህደት በሮች ሁሉ መዘጋታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ከዚህም አንዱና ዋነኛው የሀገርን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስከበር ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስን ኃይል የማዘዝ ሥልጣን ሊኖረው የሚገባው የፌደራል መንግሥት ብቻ ስለመሆኑ ሀገራዊም ሆነ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን አስረግጦ በማስገንዘብ ህወሓት ትጥቁን እንዲፈታ ሊደረግ ይገባል፡፡ እኛ ሰላምን የምንናፍቀው ለአጭር ግዜ መፍትሔነት ሳይሆን በዘላቂነት ነው፤ ዘላቂ ሰላም ደግሞ መረጋገጥ የሚችለው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ፍፁም ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ መሆን አለበት። ስለሆነም በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚገኙ የፌደራል ተቋማትንም ሆኑ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የመጠበቅና የአየር ክልሉን ሙሉ ለሙሉ  የመቆጣጠር ሥልጣን በብቸኝነት የፌደራል መንግሥቱ መሆኑን ህወሓትም ሊገነዘበው፤ መንግሥትም ሊዘነጋው አይገባም፡፡ በዚህ ግዜ የትግራይ ህዝብ በድርብርብ መከራ ውስጥ እንዲኖር ያደረገው ህወሓት መሆኑ አያነጋግርም፤ የትግራይ ሕዝብ ለመጨረሻ ጊዜ ከጦርነት እራሱን ነፃ እንዲያወጣ ጠንክሮ መታገል ያለበት ሲሆን፤ በዚህ ትግል ውስጥም ኢዜማ ከህዝቡ ጎን እንደሚቆም ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ፤ በተለይ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የትግራይ ሕዝብ የሰላም አየር እንዲተነፍስ እና አስፈላጊው ሰብዓዊ እርዳታና መሠረታዊ አገልግሎቶች ማግኘት እንዲችል፤ ህወሓት ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስድ እንደመሆኑ፤ ከጀርባ ያለው ምክንያት መጠናት ያለበት ሆኖ ሰላምን እመርጣለሁ ማለቱን መልካም ጅምር አድርጎ መውሰድ ይገባል፡፡  ከዚህ በኋላ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ከዛሬ ነገ ጥቃት ደረሰብን፣ ንብረታችን ተዘረፈ፣ ሰላማችን ደፈረሰ፣ ልጆቻችን ተደፈሩ፣ ተቋሞቻችን ሊፈራርሱ ነው እያሉ በስጋት ውስጥ እንዳይኖሩ ሀገራችንም የሉዓላዊነት እና የህልውና ስጋት ተጋርጦባት እንዳትቀጥል በየትም ቦታ በህወሓት የሚመራ ምንም ዓይነት የታጠቀ ኃይል አለመኖር እጅግ ወሳኝ ተግባር መሆኑን በአጽንኦት ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ኢዜማ የመከላከያ ሠራዊታችን እና የህወሓትን አጉራ ዘለል ወረራ በተግባር ለመመከት የተሰለፉ ኢትዮጵያዊ ኃይሎች ሁሉ የሚከፍሉትን የአካል እና የሕይወት መስዋዕትነት በታላቅ ክብር የሚመለከተው ነው፡፡  ይህ መስዋዕትነት በከንቱ መሆን እንደሌለበት አጽንኦት ሊሰጠው እንደሚገባ ለማሳሰብ ይወዳል፡፡ ማንኛውም የሰላም ውይይት እና ድርድር ቢኖር እንኳን የሀገር ህልውና አደጋ ላይ በወደቀ ቁጥር ከፊት ተሰልፎ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚዋደቀውን ኃይል ለሁለተኛ ዙር መስዋዕትነት በማይዳርገው መልኩ መከወን ይገባዋል፡፡ ይህ ሊረጋገጥ የሚችልበት ብቸኛ መንገድ በህወሓት የሚታዘዝ ምንም አይነት የታጠቀ ኃይል በየትም ቦታ እንዳይኖር በማድረግ ብቻ ነው፡፡ የማንኛውም የሰላም ንግግር ቁልፉም ይሔንን ማረጋገጥ ሊሆን ይገባል፡፡ አንዳንድ ሀገሮችና  ዓለም አቀፍ ተቋማት የህወሓትን ባህሪ እና በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በቀጠናው ላይ የሚጋርጠውን ስጋት በመረዳት ከኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት  ጎን ቆመው ሊሠሩ ሲገባቸው በተቃራኒው ሀገራችንን ያልተገባ ጫና ውስጥ በማስገባት የውስጥ ጉዳያችን ላይ ጭምር ጣልቃ በመግባት የሁለት መንግሥታት ድርድር እንዳልሆነ እያወቁ እንኳ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነትን በሚጎዳ መልኩ የሚደረግን ድርድር ሲያበረታቱ ይታያል። ይህን መሰል ድርጊት የኢትዮጵያ ህዝብ በፍፁም የማይቀበለው መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል። ይህን መሰል አድሏዊነት እና ሉዓላዊነታችንን መዳፈርን ፓርቲያችን በጽኑእ ያወግዘዋል፡፡ እንደ ኢዜማ ይህን ዓይነት የሰላም ድርድር ጥያቄን በመልካም ጎኑ የምናይበት ዋነኛው ምክንያት "የፖለቲካ ልዩነቶች ሁሉ ከጠረጴዛ ዙሪያ ውጪ ሊሆኑ አይገባም" ከሚል የጸና እምነት ነው፡፡ መጪው ሀገራዊ ምክክርንም በተስፋ የምንጠብቀው አሉ የምንላቸው ልዩነቶችን ሁሉ በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ እና ብቻ በምክክር እና ውይይት ወደ መፍትሔ በማምጣት ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህል እንድንመሠርት ይረዳል ብለን በማመንም ጭምር ነው፡፡ የሰላም ድርድር ሃሳቡ ስኬታማ ሆኖ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሰላም ሕይወት የሚኖሩበት አዲስ ዘመን እንዲሆን እየተመኘን፤ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚችለው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በምንም መልኩ ጥያቄ ውስጥ ሳያስገባ ሊሆን እንደሚገባው ለማስገንዘብ አንወዳለን፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መስከረም 03 ቀን 2015 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ሁሉም ክልሎች እውቅናቸው ከፌደራሉ መንግሥት ሥር እና ከሉዓላዊ የሀገር ግዛት አንድነት ውስጥ ነው። ስለዚህም "የትግራይ ክልላዊ መንግሥት" እንጂ "የትግራይ መንግሥት" በመባል የሚታወቅ መዋቅር በሕግም በታሪክም የለም።
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
02:43
Video unavailableShow in Telegram
የኢዜማ አመራር ለ 2015 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምርያ ሐላፊ _________________________________ #ኢዜማን_ይወዳጁ 👉 ቴሌግራም: https://t.me/ethzema 👉  ፌስቡክ: facebook.com/ethzema 👉ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@ethzema?_t=8VTdYbWGIK6&_r=1 👉ትዊተር: twitter.com/ethzema 👉ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCi-FE-Khv-f1hE4ieyjoEIA #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
42.37 MB
01:01
Video unavailableShow in Telegram
የኢዜማ አመራር ለ 2015 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) የኢዜማ ሊቀመንበር #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
2.86 MB
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ ዓመት አዲስ ተሥፋ ------------------ በግል ጠባዬ ግጭት አልወድም። ጦርነት ደግሞ ያሳቅቀኛል። ይልቁንም የአንድ ሀገር ልጆች ሆነን ችግሮቻችንን በውይይት እና በድርድር መፍታት ሲገባን የእርዳታ እህል እየበላን ጦር መማዘዛችን ያሳፍረኛል። ኢትዮጵያውያን ወደን እና ፈቅደን ጦርነት ውስጥ አልገባንም። ጦርነት የሚያስከትለውን ሞራላዊ፣ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት በውል እንገነዘባለን። ለጦርነት የሚውለውን ሀብት ልማት ላይ አውለነው ቢሆን ኖሮ ህዝባችንን ከማይምነት እና ከጉስቁልና ለመታደግ የሚኖረውን ፋይዳም እንረዳለን። "አንድ በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል?" እንዲሉ፤ ህወሓት እና ተባባሪዎቹ "ሲኦልም ቢሆን ወርደን፤ ከሰይጣንም ጋር ቢሆን ተባብረን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርን እንበትናታለን" ብለው ጦር ሰብቀው መከላከያ ሠራዊታችንን ሲወጉ ሀገርን ከማዳን የሚቀድም ሌላ ምን አማራጭ ነበረን? ምንም። በአዲሱ ዓመት ተገደን የገባንበትን የህልውና ጦርነት በድል ደምድመን፣ የግጭት መንስኤ የሆኑ አጀንዳዎቻችንን በሀገራዊ ምክክር ጠረጴዛ ላይ አቅርበን፣ ሕገመንግሥታዊ ማሻሻያ በማድረግ ለዘላቂ ሰላማችንን እንሥራ! በመጪው ዘመን ኢትዮጵያችን ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት እና ዜጎቿ የክብር ሕይወት የሚኖሩባት የሰላም ምድር እንድትሆን እመኛለሁ !
Hammasini ko'rsatish...
01:30
Video unavailableShow in Telegram
የኢዜማ አመራር ለ 2015 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሰላማዊት ገ/እግዚአብሔር የኢዜማ ሕግ እና ደንብ ትርጉም ኮሚቴ አባል #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
4.22 MB
01:31
Video unavailableShow in Telegram
የኢዜማ አመራር ለ 2015 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አበበ አካሉ የኢዜማ ዋና ፀሐፊ ______________________________________________________________ የተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በመወዳጀት የኢዜማን እንቅስቃሴዎች እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የፓርቲውን አቋም በተመለከተ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ። 👉 ቴሌግራም: https://t.me/ethzema 👉  ፌስቡክ: facebook.com/ethzema 👉ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@ethzema?_t=8VTdYbWGIK6&_r=1 👉ትዊተር: twitter.com/ethzema 👉ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCi-FE-Khv-f1hE4ieyjoEIA 👉 ስለፓርቲያችን ማንኛውንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ወይንም መስጠት ቢፈልጉ በቢሮ ስልክ ቁጥራችን +251944107661 በሥራ ሰዓት ይደውሉልን። ወይንም በኢሜይል አድራሻችን [email protected] መልዕክትዎን ያድርሱን። @ethzema #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
23.76 MB
03:04
Video unavailableShow in Telegram
የኢዜማ አመራር ለ 2015 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማዕረጉ ግርማ የኢዜማ አካል ጉዳተኞች መምርያ ሐላፊ የተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በመወዳጀት የኢዜማን እንቅስቃሴዎች እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የፓርቲውን አቋም በተመለከተ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ። 👉 ቴሌግራም: https://t.me/ethzema 👉  ፌስቡክ: facebook.com/ethzema 👉ትዊተር: twitter.com/ethzema 👉ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCi-FE-Khv-f1hE4ieyjoEIA 👉 ስለፓርቲያችን ማንኛውንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ወይንም መስጠት ቢፈልጉ በቢሮ ስልክ ቁጥራችን +251944107661 በሥራ ሰዓት ይደውሉልን። ወይንም በኢሜይል አድራሻችን [email protected] መልዕክትዎን ያድርሱን። @ethzema #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
47.88 MB
01:03
Video unavailableShow in Telegram
የኢዜማ አመራር ለ 2015 ዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን የኢዜማ ምክትል መሪ የተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በመወዳጀት የኢዜማን እንቅስቃሴዎች እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የፓርቲውን አቋም በተመለከተ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ። 👉 ቴሌግራም: https://t.me/ethzema 👉  ፌስቡክ: facebook.com/ethzema 👉ትዊተር: twitter.com/ethzema 👉ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCi-FE-Khv-f1hE4ieyjoEIA 👉 ስለፓርቲያችን ማንኛውንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ወይንም መስጠት ቢፈልጉ በቢሮ ስልክ ቁጥራችን +251944107661 በሥራ ሰዓት ይደውሉልን። ወይንም በኢሜይል አድራሻችን [email protected] መልዕክትዎን ያድርሱን። @ethzema #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
16.63 MB
ድህነት በወለደው ረሃብ እና ድንቁርና ለተጎሳቆለችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በእርግጥም ሰላም ከማንም በላይ ያስፈልጋታል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሀገራችንን ሰላሟን ቀምቶ በጦርነት እና በኋላ ቀርነት እንድትማቅቅ የፈረደባት ማነው ? በጥላቻ እና በዘውግ ቅራኔ የተጠመቀው ቋንቋን መሠረት ያደረገው የዘር ፖለቲካ አይደለምን? ለዚህስ ዋንኛው አጋፋሪ ከቀዳማይ እስከ ሳልሣይ ሀገራችንን ነክሶ የያዛት ህወሓት የተባለው የሽብር ቡድን አይደለምን? እነኚህ ሁለቱስ እያሉ በምድራችን ዘላቂ ሰላም ሊገኝ ይችላል?
Hammasini ko'rsatish...
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች ከፓርቲው ወጣት አባላት እና ደጋፊዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። የተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በመወዳጀት የኢዜማን እንቅስቃሴዎች እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የፓርቲውን አቋም በተመለከተ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ። 👉 ቴሌግራም: https://t.me/ethzema 👉 ፌስቡክ: facebook.com/ethzema 👉ትዊተር: twitter.com/ethzema 👉ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCi-FE-Khv-f1hE4ieyjoEIA 👉 ስለፓርቲያችን ማንኛውንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ወይንም መስጠት ቢፈልጉ በቢሮ ስልክ ቁጥራችን +251944107661 በሥራ ሰዓት ይደውሉልን። ወይንም በኢሜይል አድራሻችን [email protected] መልዕክትዎን ያድርሱን። @ethzema #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ከሀገር መከላከያ ጎን ! እንደ ሀገር የደኅንነታችን ዘብ እና የሉዓላዊነታችን የመጨረሻው ምሽግ ከሆነው የሀገር መከላከያ ጎን መቆም የሁሉም ዜጎች የማይናወጽ አቋም መሆን አለበት!!! ከመከላከያ ጎን መቆም ስንል ምን ማለታችን ነው ? - በወታደራዊ ሳይንሥ እና መርኅ ሥራውን እንዲሠራ የመከላከያ ሥራን ለመከላከያ መተው! - የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን በሞራል፣ በቁሳቁስ እና በገንዘብ መደገፍ ! - የሠራዊቱን ክብር በሚነኩ እና በሚከፋፍሉ አሉባልታዎች ፈጽሞ አለመተባበር! - እርሱ ድንበር ሲጠብቅ እኛ ሠፈር መጠበቅ ስንችል! ... ያኔ እውነትም ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ቆመናል። ዘላለማዊ ክብር ወድቀው ሀገር ለሚያቆሙ የሠራዊት አባላት !
Hammasini ko'rsatish...
የቅድሚያ ቅድሚያ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለሕዝቦች ሠላም ! https://m.youtube.com/watch?v=snG4iVU1eUQ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
"በአዲስ ዓመት ለዜጎች ገፀ በረከት" የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እሁድ ነሐሴ 22/ 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምርያ "በአዲስ ዓመት ለዜጎች ገፀ በረከት" በሚል የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ስታዲየም በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ብሔራዊ ዋና መስርያ ቤት አዘጋጅቷል። የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎች በዚህ መርኃግብር በመካፈል ሰብዓዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
ጦርነትን እያወገዝን ሰላምን ብናስቀድምም የሀገር ህልውናና ቀጣይነት ግን በፍፁም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አንፈቅድም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን! ሁላችንም ለጊዜው የሃሳብ ልዩነቶችን ወደ ጎን አድርገን፣ ባልተረጋገጡና አሉታዊ ፕሮፓጋንዳዎች ሳንረበሽ፣ በየተሠማራንበት የሥራ መስክ የዕለት ተዕለት ሥራችንን በትጋት እየከወንን ከሀገራችን እና ከመከላከያ ኃይላችን ጎን የምንቆምበት ትክክለኛ ሰዓት ላይ መሆናችንን በመረዳት በምንፈለግበት ቦታ ሁሉ ከፊት መሰለፍ ይኖርብናል !!! #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
ጦርነትን እያወገዝን ሰላምን ብናስቀድምም የሀገር ህልውናና ቀጣይነት ግን በፍፁም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አንፈቅድም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በነሐሴ 13/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በግልፅ እንዳስቀመጠው የፌደራል መንግስት ከግማሽ ርቀት በላይም ቢሆን ተጉዞ ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጥ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ ይህ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተጀመረው ጦርነት እንዴት እንደተጀመረ ምን ያህል የሰላም መንገዶች ተዘግተው አሁን ለደረስንበት ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ እንደገባን የምንዘነጋው አይደለም፡፡ በዘውግ ማንነት ላይ የተመሠረተው ፖለቲካችን ተመሳሳይ ግጭቶችን እየጠመቀ ካሁን በኋላም እንደሚያቀርብ ሳይታለም የተፈታ ነው። የሀገራችን የፖለቲካ ሥሪት ሁላችንን እኩል በሚያደርገን የዜግነት ምሶሶ ላይ ካልቆመ ዋስትና ያለው ሰላምም ሆነ ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ እንደምንቸገር የተረጋገጠ ነው። ይህ ሆኖ የሠላም ችግራችን በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስ የሚፈጠሩ መሰል ግጭቶችን ለመከላከል መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ንግግር የሚሻል መንገድ እንደሌለ እምነታችን ጽኑእ ነው። ህወሓት በተደጋጋሚ ከሰላም በተቃራኒ እየቆመ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመከራ መዳረጉን እንደቀጠለ ነው፤ የትግራይ ህዝብም እየደረሰበት ላለው መከራ ሁሉ ዋነኛ ተጠያቂው ይኸው የሕወሓት አክራሪ ቡድን መሆኑን በመረዳት ለተጨማሪ መከራና ብሶት ልጆቹን መገበር፣ ሀብት ንብረቱን ለእኩይ ዓላማው እንዳያውልበት በመከላከል ህወሓትን በቃህ በማለት ጦርነትን እምቢኝ ብሎ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመቆም ህወሓት ተገድዶም ቢሆን ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጣ ማስገደድ ይኖርበታል፡፡ እንደ ሀገር የጦርነትን ጉዳት በተግባር የምናወቀው ነው፤ የደረሰብን ቁስል ገና አልደረቀም፤ ከህመማችን አላገገምንም፤ ያሳለፍነው ጦርነትም የዜጎቻችንን ሕይወት፣ አካል እና ንብረት እሳት ውስጥ ከመማገድ ያለፈ ይህ ነው የሚባል ፍሬ እንደሌለው ግልፅ ነው፡፡ በተደጋጋሚ የሚቃጣብንን ትንኮሳ በመከላከል ብቻ ከልክ ያለፈ ትዕግስት ማሳየት ህዝብን ለመከራ፣ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለድቀት፣ የማኅበረሰቡን ሥነልቦናም ለቀውስ የሚዳርግ እንዳይሆን መንግሥት በቁርጠኝነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሁሉ እንዲወጣ በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ተደጋጋሚ ጦርነቶች እንዳይከሰቱ ማስቆም የሚቻለው በቂ ዝግጅት አድርጎ የጥፋት ኃይሎች ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ሲቻል ብቻ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሁሌም ቢሆን ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተን የምንሠራውን ያህል ሀገራችንን የሚነካ አንድነታችንን የሚያደፈርስ ጉዳይ ሲመጣ ግን በሕብረት መቆም የምንታወቅበት ታሪካችን ነው። ይህ ደግሞ ዛሬም አብሮን እንዳለ በተደጋጋሚ ያረጋገጥነው እሴታችን ነው። ሁላችንም ለጊዜው የሃሳብ ልዩነቶችን ወደ ጎን አድርገን፣ ባልተረጋገጡና አሉታዊ ፕሮፓጋንዳዎች ሳንረበሽ፣ በየተሠማራንበት የሥራ መስክ የዕለት ተዕለት ሥራችንን በትጋት እየከወንን ከሀገራችን እና ከመከላከያ ኃይላችን ጎን የምንቆምበት ትክክለኛ ሰዓት ላይ መሆናችንን በመረዳት በምንፈለግበት ቦታ ሁሉ ከፊት መሰለፍ ይኖርብናል፡፡ ፓርቲያችን ኢዜማም የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚጠበቅበትን ኃላፊነትና ግዳጅ ሲወጣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኑ ተሰልፎ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ በመቋጨት ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማትና ሰላም እንድንመለስ የሚጠበቅብንን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን፣ ክብር ለሀገራችን ኢትዮጵያ! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
ከአርክቴከት ዮሐንስ ጋር የተደረገ ቆይታ "... በፍጥነት ፖለቲካቸውን በማዘመናቸው ... ወደ ስልጣኔ ሄደዋል፤" ክፍል አንድ https://youtu.be/D5eXzBwDYJw
Hammasini ko'rsatish...
በአፋር እና ሱማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የእርስ በእርስ ግጭት  የፌደራል  መንግሥቱ በቂ ትኩረት በማድረግ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጠው እንጠይቃለን! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)  የአፋር እና የሱማሌ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ከሕብረተሰቡ ጋር በመሆን  በንቃት ከፊት ተሰልፈው እየከፈሉ ላለው መስዋዕትነት ልዩ ክብር አለው፡፡ ክልሎቹን ከሽብርተኞች በመጠበቅና  በሃገር ህልውና ላይ የተቃጣን ትንኮሳ በመመከት እንደወትሮው ሁሉ ታሪክ የሚያስታውሰው ገድል እየፈፀሙ እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ፓርቲያችን ኢዜማ የክልሎቹ አመራሮች ከህወሓትና አልሻባብ በኩል የተሞከረባቸውን ጥቃት ለመመከት ባሳዩት ትዕግስት እና ቁርጠኝነት ልክ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ ለሚፈጠሩ ችግሮች ልዩ ትኩረት ሰጥተው ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እንዲሰሩ ጥሪያችንን ማቅረብ እንፈልጋለን፡፡ በአካባቢው የተከሰቱት የጎርፍ አደጋዎች፣ ጦርነት ያስከተላቸው መፈናቀሎች፣ በድርቅ ሳቢያ የተፈጠሩ ችግሮች፣ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት እና የመሳሰሉት ጫናዎች በማሕበረሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የፈጠሩት እንቅፋቶች ውስብስብ በሆነበት በዚህ ወቅት በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ የሚገባው የአስተዳደር ወሰን ጉዳይ ዜጎችን ለተጨማሪ የሰላም እጦትና የደኅንነት ችግር እንዲዳርግ መፍቀድ የሚያሳድረው ጉዳት ከክልሎቹ አልፎ ለአጠቃላይ ሀገሪቱ ስጋት ከመሆን በተጨማሪ ለውጭ ሀይሎች መግቢያ ቀዳዳ እንደሚከፍት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የፌደራሉ መንግሥት የክልሎቹን ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪነት በመረዳት ለጉዳዩ ከፍተኛ አትኩሮት ሰጥቶ በአካባቢው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የጎሣ መሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና የሚመለከታቸው አካላትን ሁሉ በማስተባበር ዘላቂ ሰላም የሚሰፍንበትን መንገድ በአፋጣኝ ማፈላለግ ይኖርበታል፡፡ የክልሎቹ አመራሮችም የማሕበረሰቡን ጥቅም እና የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ቅድሚያ በመስጠት ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዘው ለጋራ ሰላምና ተጠቃሚነት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
1) የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ ከአባይ ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/YW8HOMDYTp4 2) አንድነት ሽፈራው የኢዜማ ትሬዠረሪ በሕዳሴው ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ስራ መጀመር እና 3ኛው ዙር ውሃ ሙሌት መጠናቀቁን አስመልክቶ ከፋና ብሮድካስት ጋር ያደረጉት ቆይታ ለመስማት 6:14-11:55 ደቂቃ ዜና ያደምጡ - Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C https://www.fanabc.com/%E1%8B%9C%E1%8A%93-%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88%9D%E1%8C%A1/ 3) የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሀገራዊ ምክክሩ ጉዳይ ከፋና ብሮድካስት ጋር ያደረጉት ቆይታ https://www.facebook.com/123960474361367/posts/5436729363084425/?app=fbl 4) የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሕዳሴው ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ስራ መጀመር እና 3ኛው ዙር ውሃ ሙሌት መጠናቀቁን አስመልክቶ ከፋና ብሮድካስት ጋር ያደረጉት ቆይታ https://www.facebook.com/123960474361367/posts/5421845427906152/?app=fbl 5)  የኢዜማ ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) በሕዳሴው ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ስራ መጀመር እና 3ኛው ዙር ውሃ ሙሌት መጠናቀቁን አስመልክት ከኢፕድ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://www.press.et/?p=79101 6) የኢዜማ ም/መሪ ዩሐንስ መኮንን(አርክቴክት) በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ VOA ጋር ያደረጉት ቆይታ https://amharic.voanews.com/a/addis-ababa-/6704142.html 7) የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ አብርሃም በርታ (ዶ/ር) በፓርላማው ስነምግባር ደንብ ላይ  ከአሐዱ ሬድዮ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://fb.watch/eYxM5IcuRJ/ 8) የኢዜማ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የገንዘብ ሚኒስቴር ትይዩ ካቢኔ ግርማ ሰይፉ በሀገራዊ ምክክሩ ጉዳይ ከአሚኮ ጋር ያደረጉት ቆይታ ከ 08፡51ደቂቃ ጀምሮ https://fb.watch/e-8xClYXvE/   9) የኢዜማ ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቆይታ ከ 02፡55 ደቂቃ ጀምሮ https://youtu.be/j8InK4CxFjA   10) የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ ከሸገር 102.1 FM ጋር ያደረጉት ቆይታ https://t.me/ShegerFMRadio102_1/11908 11) የኢዜማ ትሬዠረሪ አንድነት ሽፈራው በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://fb.watch/eZYilkBUpx/ 12)  የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ ከባላገሩ ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/OiruqLkzDpw 13) የኢዜማ ም/መሪ ዩሐንስ መኮንን(አርክቴክት) በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን ማካለል ጉዳይ ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/HZ95HkcC6MI
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የፖለቲካ አለመግባባቶች መፈታት ያለባቸው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው !!! መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት እና የሀገርን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ላይ ቁርጠኛ አቋም ይዞ መሥራት ተቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን ይገባል። በአሸባሪነት የተፈረጁ ቡድኖች ለሀገር ህልውናና ቀጣይነት እንቅፋት እየሆኑ  የዜጎችን ደኅንነት እና ሰላም ጥያቄ ውስጥ እየከተቱ ህዝብን በስጋት እና ፍርሃት ውስጥ እንዲኖር ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ፈጽሞ መፍቀድ አይኖርበትም፡፡ ፓርቲያችን ኢዜማ ከጦርነት የሚገኝ አንዳችም ትርፍ እንደሌለ በፅኑእ ያምናል። የፖለቲካ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች ሁሉ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ማድረግም የሰለጠነ አካሄድ መሆኑን ይገነዘባል። ለዚህም ነው ለሀገራዊ ምክክሩ የተለየ አትኩሮት ይገባዋል የሚለውን እምነቱን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አፅንኦት ሰጥቶ የሚያስረዳው። ሁሌም ቢሆን ሰላምን ቅድሚያ መስጠት አግባብ ነው፡፡ ለሰላም ሲባል የሚደረጉ ድርድሮችም ሆኑ ስምምነቶች ግን ሕወሓት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ በፈጸመው ክህደት ተገድደን የገባንበትን ጦርነት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጡ መሆናቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ በሂደቱም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ በዋነኝነት የህዝብን ጥቅም ከፊት ያስቀደመ የሀገርን ህልውና እና ቀጣይነት የሚያረጋግጥ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሰሞኑን እንደሚወጡት መረጃዎች ህወሓት የሰላም ድርድሩን አማራጮች እየገፋ እራሱን ለጦርነት እያዘጋጀ እና በተለመደው አውዳሚ መንገድ የጥፋት ነጋሪት እየጎሰመ መሆኑን በአደባባይ እያወጀ ይገኛል።  በትግራይ የሚኖሩ ዜጎቻችን ለህወሓት የጦርነት ቅስቀሳ ጀርባቸውን በመስጠት ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለሰላም እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። እንደሚታወቀው እስካሁንም በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ሕይወት ከመቅጠፍ ያለፈ ይህ ነው የሚባል ውጤት አለመገኘቱን ሁላችንም ልብ ልንለው ይገባል።  የህወሓት መሠረታዊ ባህርይ ሰላም ጠል መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ቢሆንም የእውነት ለትግራይ ህዝብ  የሚቆረቆር ከሆነ ከጦርነት ይልቅ የሰላም አማራጮችን ከልቡ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግን የቅድሚያ ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅበታል። መንግሥትም ለሰላም እያሳየ ያለውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉ የሚበረታታ ሆኖ በአካባቢው ያለውን ማኅበረሰብ በድጋሚ ለከፋ ሰብአዊ ጉዳትና መፈናቀል እንዳይዳርግ ወቅታዊ ሁኔታውን ያገናዘብ ጥንቃቄ ሊወሰድና የሚገባውን አሰፈላጊ ዝግጅት ሁሉ ሊያደረግ እንደሚገባ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) 13 ነሐሴ 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
<<ወጣቶች በሃገራቸው ጉዳይ ላይ በንቃት አለመሣተፍ የነገው ትውልድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሣድራል!>> ውድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንኳን ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አደረሳችሁ! ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዘንድሮ "INTERGENERATIONAL SOLIDARITY: CREATE A WORLD FOR ALL AGE" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 25ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡ እኛ ወጣቶች በእያንዳንዱ የሀገራችን ኩነቶች ከፊት ተሰልፈን፣ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ በእውቀት እና ምክንያት ላይ ተመስርተን የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል፤ በተለይ ሀገራዊ ጉዳዮችን በዝምታ መመልከት አቅመ ደካሞች እና ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ላይ የራሱን የሆነ አሉታዊ ችግር እንደሚያሣርፍ ተገንዝቦ በንቃት መሳተፍ ከወጣቱ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ልናስገነዝብ እንወዳለን፡፡ ወጣቱ ሀገራችን የምትገኝበትን እጅግ አስቸጋሪና ውስብስብ ሁኔታ ከመሠረታዊ ምክንያቶቹ አንጻር በመረዳት፣ ተጨንቀውና ተጠበው ለችግሮቹ መፍትሔ ለመፈለግ ፍቃደኛ ሆኖ፣ አስቸጋሪውን ሀገራዊ ሁኔታ ለመለወጥ ግንባር ቀደም ሊሆን ይገባል። የዛሬውን ቀንም ለሀገራችን ልናበረክት የምንችለውን መልካም ተፅእኖ እያሰብን ወደ ተግባር ለመሰማራት ዝግጁ የምንሆንበት ቀን እንዲሆን እንመኛለን፡፡ ወጣቶች ያለምንም ተፅእኖ በነጻነት ሊሳተፉባቸው የሚገቡ ማህበራትና ሌሎች የወጣቱን ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተው የሚሰሩ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን በማስጠበቅ የተቋቋሙበትን ዓላማ ማሳካት እንዲችሉ በማድረግ የወጣቱ ድምፅ ማሰሚያ ቦታዎች ብቻ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ መልካም የወጣቶች ቀን! #ኢዜማ #ኢትዮጵያ የኢዜማ ወጣቶች መምርያ
Hammasini ko'rsatish...
00:23
Video unavailableShow in Telegram
ዓባይ ነሀገር አድባር የሀገር ሲሳይ
Hammasini ko'rsatish...
5.89 MB
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ተርባይን ሃይል ማመንጨት በመጀመሩ የተሰማንን ደስታ እየገለፅን፤ ይህ ግድብ የሀገር ህልውና ማረጋገጫ፣ የጋራ ማንነታችን መገለጫ የመተባበራችን ፍሬ ነው፡፡ የህዳሴው ግድብ እውን ሆኖ እንድናይ ቀን ከሌት እየለፉ ላሉ ዜጎች ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
አስቸኳይ የጥቆማ ማስታወቂያ!! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከታች በተጠቀሱት አምስት አበይት ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅሬታዎች የደረሰው ሲሆን ጉዳዩን በሰፊው አጠናቅሮ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ እየደረሱ የሚገኙ አስተዳደራዊ በደሎችን ለመለየት እና በጉዳዮቹ ላይ አቋም ለመያዝ እየሰራ ይገኛል። 1) በመሬት ምሪት ሽፋን የሚፈጸም ወረራና ዝርፊያን አስመልክቶ 2) በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዋሳኝ አካባቢዎች በግልጽ እየተስተዋሉ የሚገኙ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነቶችን እንደዚሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን 3) በየትምህርት ቤቶቹ ከሰንደቅ ዓላማ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ፖለቲካዊ አምባጓሮዎችን 4) የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችንና ኢፍትሃዊ አሰራሮችን 5) የውሃ፣ የመብራትና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና የፍስሽ ማስወገጃ ችግሮች ጋር በተያያዘ የከተማዋ ነዋሪዎች ከላይ ከተዘረዘሩ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎችንና ጥቆማዎችን ስታዲየም ግዮን ሆቴል አከባቢ የቀድሞው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ህንጻ ላይ የሚገኘው ዋና ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክና በኢሜል አድራሻችን ከሃምሌ 23 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 03 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ጥቆማ እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን። ስልክ 0944107660 +251115258025 0904302314 @WhatsApp @Telegram ኢሜል [email protected]
Hammasini ko'rsatish...