uz
Feedback
avatar

ETV.News

Kanalga Telegram’da o‘tish

@etv_newss (tikvah news)

Ko'proq ko'rsatish
10 687
Obunachilar
+224 soatlar
+117 kunlar
+9730 kunlar
Postlar arxiv
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተነገረ። ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ወንጀል ምርመራ በማጣራት ለፌደራል ዐቃቤ ህግ በማስተላለፍ ክስ እንዲመሰረት ማድረጉን አመልክቷል። ‎ ‎ተከሳሾቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሌሎች የግል ባንኮች የሚደውሉ በማስመሰል እንዲሁም የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀሉን እንደፈጸሙ ፖሊስ ገልጿል። ‎ ‎የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያብራራው፣ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመሰወር፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን እና መታወቂያዎችን በማዘጋጀት እና በመጠቀም የተበዳዮችን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው  ማዋላቸው በምርመራ ተረጋግጧል። ‎ ‎በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረበው ክስ በዋናነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን እንዲሁም የብሄራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003ን የተላለፉ መሆናቸውን ይገልጻል። ‎ ‎ለወንጀል ድርጊቱ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ፦ - በርካታ የባንክ አካውንቶች፣ - የሞባይል ቀፎዎች፣ - ሲም ካርዶች እና ኮምፒውተሮች የተያዙ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል። ‎ ፖሊስ ፥ ህብረተሰቡ ከማያውቋቸውና አጠራጣሪ ከሆኑ የስልክ ጥሪዎችና መልዕክቶች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል። (በክሱ ከተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች መካከል የተወሰኑት ስም ዝርዝራቸው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
2👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ከ3 ጊዜያት በላይ ሲራዘም የቆየዉ ቶምቦላ ሎቶሪ ዛሬ ይወጣል ተባለ። የሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን ለማጠናቀቅ ታስቦ ለሽያጭ የቀረበዉ ቶምቦላ ሎተሪ ከሶስት ጊዜያት በላይ ሲራዘም ቆይቶ ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አደራሽ እንደሚወጣ የሀዋሳ ከተማ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ፈንድ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል። አስቀድሞ ጥር ‎20/2017 ዓ/ም ከዚያም ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ዕጣዉ እንደሚወጣ ተገልፆ ሲራዘም የቆየዉ ሎተሪ 500 ሺህ ትኬቶች ለገበያ የቀረቡ ሲሆን 1 መቶ ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብም ዕቅድ ተይዞበት ነበር። " ሶስቱንም ዙሮች ትኬቶቹ በበቂ ሁኔታ ስላልተሸጡና በተለያዩ አከባቢዎች የተሰራጩ የቲኬት ወረቀቶችም ተሰብስበዉ ስላላለቁ " በሚል መውጫው ሲራዘም ነበር ተብሏል። 250 ካ.ሜ ለንግድ እና 200 ካ.ሜ ለመኖሪያ የሚሆን መሬትን ጨምሮ ኩዊት ባጃጅ፣ ሞተር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ ዕጣ የሚወጣባቸው ሲሆኑ 14 ዕድለኞች ይታወቃሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ #TikvahEthiopiaFamliyHawassa @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ #ጥቆማ_ለሚመለከተው_አካል! አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የኢሚግሬሽ እና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ ከሰሞኑን የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል የዘረፋ ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎች የተሞከረባትን የዘረፋ ሙከራ አንድ የቤተሰባችን አባል ለጥንቃቄ አጋርታለች። የጎተራው አገልግሎት መ/ቤት የውጭ ዜጎች አገልግሎት ፣ የቪዛም አገልግሎት የሚገኝበት በመሆኑ ብዙ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለአገልግሎት ይሄዳሉ። በባለፈው ሳምንት ለዚሁ የውጭ አገልግሎት የሄደች አንዲት ከአሜሪካ የመጣች የቤተሰባችን አባል የዘረፉ ሙከራ ተፈጽሞባታል። ነገሩ እንዲህ ነው ... ቦታው እንደልብ ትራንስፖርት የማይገኝበት እና ጭር ያለ ነው። ልክ ከአገልግሎቱ መ/ቤቱ ስትወጣ በቦታው ቀድሞውንም የነበሩ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የሚመስሉ ሰዎች " ይኸው ነይ የሜትር ታክሲ አገልግሎት " ይሏት። እሷም ወደ መኪናው ትገባለች። ብዙ ሳይጓዙ መኪናውን የሚያሽከረክረው ሰው መኪናውን ያቆመውና አንድ ሰው ገቢና ይጨምራል። " ለምን ሰው ትጨምራለህ ? " ብትለውም " ምን አገባሽ ዝም ብለሽ ቁጭበይ " የሚል መልስ ይሰጣታል። ነገሩ ያላማራት ይህች እህታችን ሁኔታውን በንቃት መከታተል ትጀምራለች። አሁንም ትንሽ ከተጓዙ በኃላ መኪናውን አንድ ግብረአበራቸው ጋር ያቆሙና እሷ በተቀመጠችበት በር በኩል እንዲገባ ይነግሩታል። በዚህ ወቅት እሷ " እኔ አልከፍትም በዛኛው ተቃራኒ በኩል ከፍቶ ይግባ " የሚል ምላሽ ትሰጣለች። ልክ ሰውየው በዛኛው በር ለመግባት ሲሄድ የነበረችበትን በር በመክፈት ወርዳ ወደ ኃሏ ሩጣ ማምለጥ ችላለች። ሰዎቹ መንገዱ ወደፊት እንጂ ወደኃላ መመለስ የማያስችል በመሆኑ ሊከተሏት አልቻሉም። በኃላም አካባቢው ግር ስላለባት በጎተራ ድልድይ አድርጋ ወደ ሳሪስ አቅጣጫ በእግር እየሮጠች ራሷን አትርፋለች። በሩጫ በምታመልጥበት ወቅት ሰዎቹ " ነቃሽብን አይደል " እንዳሏት ታስታውሳለች። ታርጋውን ለማየት ባትችልም የመኪናው ቀለም ' ብሉብላክ ' ቶዮታ ቪትዝ እንደነበር አስተውላለች። አካባቢው ጭር ያለም ስለሆነ ብዙ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የሚስተናገዱበት በመሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ መከታተል ይገባል። የሜትር ታክሲ አገልግሎት የምትጠቀሙም " ኑ ታክሲ ይኸው " ብትባሉ እንዳትገቡ። ይልቁም ወደ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶቹ ስልክ በመወደል እና የተመዘገበ ህጋዊ መኪና ወደእናተ እንዲመጣ ማስደረግ አለባችሁ። በማንኛውም ሁኔታ ስልካችሁ ባልተመዘገበበት እና ባለመኪናውም በድርጅት በህጋዊነት የተመዘገበ መሆኑን ሳታረጋግጡ ትራንስፖርት ለመጠቀም አትሞክሩ። መንገድ ላይ የምትገቡም ከሆነ ስልካችሁን የግድ አስመስግባችሁ መልዕክት ሲመጣላችሁ ብቻ ተንቀሳቀሱ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamliyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Mesebo የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሁለት ወራት በላይ ከስራ ገበታ ውጪ ሆኗል። ስራ ባቆመባቸው ቀናት 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ሳያመርት ቀርቷል። ፋብሪካው ከማምረት ውጪ ሊሆን የቻለው ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር  በተፈጠረ አለመስማማት ነው። የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ክብረኣብ ተወልደ ምን አሉ ? " የላይምስቶን ጥሬ እቃ የሚያገኝበት አከባቢ የሚኖረው ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳው ጥያቄ  በጊዜ ባለመመለሱ የተነሳ ፋብሪካው ላለፉት 65 ቀናት አላመረተም።  ባለፉት 65 ቀናት ውስጥ 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ማምረት ይችል ነበር በመጋዘን የነበረው ክምችት ባለፉት 30 ቀናት ተሽጦ አልቋል። ፋብሪካው ማምረት በማቆሙ የስሚንቶ መወደድ አስከትሏል። ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር  ህዝብ የተፈጠረው አለመግባባት ተፈትቶ ፋብሪካው በቅርቡ ወደ ስራ ይመለሳል። " #DemtsiWeyane @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ዓባይ ባንክ የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት በይፋ ማክበር ጀመረ ------------------------------------------- ዓባይ ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ የግል ባንክ ዘርፍ በመቀላቀል የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በይፋ ማክበር ጀመረ፡፡ ባንኩ የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በይፋ ማክበር መጀመሩን አስመልክቶ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደገለጹት፣ ባንኩ በተመሰረተ አጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎች እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን እና ለተገኘው ሁለንተናዊ የሥራ ስኬት የባንኩ ደንበኞች፣ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ባለአክሲዮኖች፣ የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበረ አውስተዋል፡፡   የምስረታ በዓሉ በአጠቃላይ ለደንበኞች እና ለመላ የባንኩ ቤተሰቦች መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ብሩህ አጀማመራችንን የሚዘክር እና የከፍታ መዳረሻችንን የሚያመላክትም ይሆናል ብልዋል፡፡   ባንኩ በ823 መስራች ባለአክሲዮኖች በብር 125 ነጥብ 8 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ የባለአክሲዮኖችን ቁጥሩ 4 ሺህ 500 እንዲሁም የተከፈለ ካፒታሉን ብር 7 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልጿል፡፡ ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🚨 ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መልዕክት ! በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ለአብነትም አዋሽ ወንዝን ተከትሎ የሚኖሩ ከመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል ከኦሮሚያ ክልል ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወረዳዎች ጀምሮ እስከ ታችኛው አዋሽ አካባቢዎች በተለይም ፦ - በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ዳር የሚገኙ ወረዳዎች፣ - በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰች ወረዳ ሆሞራቴ ከተማን ጨምሮ፣ - በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ እና ሌሎች በባሮ ወንዝ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉት ወረዳዎች፣ - በዋቤ ሸበሌ ወንዝ ሊጠቁ የሚችሉ የሶማሌ ክልል ወረዳዎች፣ - በአማራ ክልል በጣና ሀይቅ አቅራቢያ የሚገኙ አንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በዚህ የክረምት ወቅት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ እና የተጎጂ ይሆናሉ ተብሎ ተለይቷል፡፡ በተጨማሪም የክረምት ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አከባቢዎችና ከተሞች በሙሉ ከባድ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት በየትኛዉም ጊዜ በቅፅበታዊ ጎርፍ አደጋ ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ባልታሰቡ ክስተቶች እና ትናንሽ ወንዞች ምክንያት የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡ የ2017 ክረምት ወቅት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና ዓለም አቀፍ ትንበያዎች እንደሚያመለክቱት በእነዚህ ክልሎች እና ሌሎችም ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ የሚጠበቅ ነዉ፡፡ የጎርፍ አደጋ ስጋት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው ? ➡️ በተፋሰስና ወንዝ ዳርቻ (አዋሽ ፣ ዋቤ ሸበሌ፣ ተከዜ፣ ባሮ፣ ኦሞ፣ የከተሞች ወንዞች፣ ወ.ዘ.ተ….)፣ ➡️ በግድቦች ማስተንፈሻ አካባቢዎች (ተንዳሆና ቀሰም፣ ግልገል ጊቤ ፣ ተከዜ፣ ገናሌ፣ ዳዋ ፣ ፊንጫ፣ ቆቃ ወ.ዘ.ተ...)፣ ➡️ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆነ አከባቢዎችና ከተሞች ሙሉ በሙሉ ከባድ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት በየትኛዉም ጊዜ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ። ማህበረሰቡ፣ የሚመለከታቸው ተቋማት እና የአስተዳደር መዋቅሮች አስፈላጊውን ጥንቃቄና በክትትል ላይ ተመሰረተ እርምጃዎች እንዲወስዱ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል። (ዝርዝር መረጀዎች ከላይ ተያይዟል) ⚠️መልዕክቱን ለሌሎች ያጋሩ! #EDRMC #TikvahEthiopiaFamliyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
3👍 2
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ሸዉደዉናል 5ዐ ሰዉ መርጣችሁ ስጡን ብለዉ ካስነሱን በኋላ የተወከሉትን ስብሰባ ጠርተዉ አስፈራርተዋል " - ነዋሪዎች ➡️ " የኛ ጥያቄ የወረዳውን የተወሰኑ ቀበሌያት ወደ ሀዋሳ ከተማ ክፍለ ከተማነት ለማጠቃለል መወሰኑ ተገቢነት የለዉም የሚል ነው ! " የሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ  አከባቢ ነዋሪዎች ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዲስ ተዋቀረ በተባለው የክፍለ ከተማ አደረጃጀት ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ 5 ቀበሌያትን ብቻ ነጥሎ መወሰዱን በመግለፅ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵየ ገልጸው ነበር። ነዋሪዎቹ የተመረጡት ቀበሌያት ምርታማና የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸዉ በመሆኑ የወረዳዉን የመልማት አቅም ያዳክመዋል፤ ከዚህ ቀደም የተገባልንም ቃል ተግባራዊ አልተደረገም ሲሉ አደባባይ በመዉጣት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ወደ ቤታችን አንመለስም " ማለታቸው አይዘነጋን። " በዕለቱ ሕዝቡ ከሜዳ ላይ አልነሳ በማለቱ ምሽት ከ2 ሰዓት በኋላ የዞንና የወረዳ አመራሮች መጥተዉ 'ለነገ 50 ተወካዮችን መርጣችሁ ዉይይት እናድርግ' ብለዉ ሕዝቡ እንዲበተን ካደረጉ በኋላ በማግስቱ የተመረጡትን ተወካዮች ሰብስበዉ አስፈራርተዋቸው ስብሰባዉን ረግጠዉ ወጥተዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። " አመራሮች ሸዉደዉናል 50 ሰዎችን መርጣችሁ ወክሉና እናንተ ወደ ቤት ተመለሱ እነሱ ነገ ከኛ ጋር ይወያዩ ብለው በሽማግሌዎች በኩል ሕዝቡ እንዲበተን ካደረጉ በኋላ በማግስቱ የተወከሉትን ሰዎች ' እናንተ ናችሁ ሕዝቡን የሚታሳምፁት ' ብለዉ በማስፈራራት ስብሰባዉን ጭምር ረግጠዉ ወጥተዋል " ሲሉ ገልፀዋል። ዶሬ ባፋናና አከባቢዉ ያሉ ሌሎች ቀበሌዎች ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ ስር ከመካለል ጋር ተያይዞ አንድ ላይ ዉሳኔው ያለ ልዩነት ተግባራዊ እንደሚደረግ እየተነገራቸዉ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ በወረዳው የተሻለ አቅም ያላቸው የተባሉ 5 ቀበሌያትን ብቻ ነጥሎ ' በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዋሳ ላንጋኖ ክፍለ ከተማ ' በሚል ሊደራጅ እንደሆነ መነገሩ ሕዝቡን ማስቆጣቱን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ የወረዳዉ አስተዳዳሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ #TikvahEthiopiaFamliyHawassa @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
2👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ሞሐመዱ ቡሃሪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ82 ዓመቱ ቡሃሪ በብሪታኒያ ዋና ከተማ ለንደን በሚገኝ ክሊኒክ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የቀድሞ ቃል አቀባያቸው ገርባ ጋሹ ገልጸዋል። ሁለት የፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ያገለገሉት ቡኻሪ ሥልጣን ያስረከቡት እኤአ በ2023 ነበር። በናይጄሪያ ታሪክ ቡሃሪ በምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኝ ፕሬዝደንት ያሸነፉ የመጀመሪያው የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ነበሩ። እኤአ 2015 ሥልጣን የያዙት የቀድሞውን ፕሬዝደንት ጉድላክ ጆናታን በምርጫ አሸንፈው ነው። ይሁንና ናይጄሪያን የመሩባቸው ዓመታት በጤና ዕክል ምክንያት አሉባልታ በብዛት ይናፈስባቸው ነበር። ቡሃሪ ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ አድርገው ከመቀየራቸው በፊት በ1980ዎቹ ጠንካራ አምባገነን ሆነው ናይጄሪያን መርተዋል። ቡሃሪ ከሦስት ያልተሳካ ሙከራ በኋላ ጉድላክ ጆናታንን አሸንፈው ፕሬዝዳንት ሲሆኑ በናይጄሪያ ፖለቲካ የለውጥ ዕድል ተፈጠረ ተብሎ ተስፋ ተሰንቆ ነበር። ይሁንና በስልጣን ዘመናቸው በናይጄሪያ የበረታውን ሙስና እና የመረጋጋት እጦት መቅረፍ ተስኗቸዋል። የሥልጣን ዘመናቸው ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና የጤና ዕክል የበረታባቸው ነበሩ። መንግሥታቸው በተቃዋሚዎች ላይ በወሰዳቸው ርምጃዎች ከፍተኛ ትችት ይሰነዘርባቸው ነበር። በሰሜናዊ እና ደቡባዊ ናይጄሪያ ከፍተኛ ፉክክር ባለባት ሀገር ቡሃሪ የትውልድ አካባቢያቸውን ሰዎች እና ዘመድ አዝማዶቻቸውን ለከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን በመሾም አለመተማመን እና ጥርጣሬ እንዲነግስ አድርገዋል እየተባሉ ይተቻሉ። Credit - DW @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው። አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል። በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማት የትኞቹ ናቸው ? - ንግድ ቢሮ፣ - ገቢዎች ቢሮ፣ - መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣ - መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣ - ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣ - ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል። @TikvahethMagazine @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" አንዱ መኪና ተገኝቷል " - ባለንብረቶች ከቀናት በፊት ለሊት 9 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቃሊቶ ቶታል ኮንዶሚየም ግቢ ውስጥ የቆሙ ሶስት 5L ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ እንደተወሰዱ፣ አንደኛው እንደተገኘ ሌሎቹን ያየ ሰው እንዲቆጥማቸው ባለንበረቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች አሳውቀው ነበር። መልዕክቱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ አንዱ መኪና ማለትም ኦሮ ኮድ 03 34021 ጀሞ 2 አካባቢ መገኘቱን ገልጸዋል። " መረጃዉን አይቶ ለደወለልን ግለሰብ እንዲሁም ለአቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ አባላት ምስጋናችንን አድርሱልን " ብለዋል። አሁን ላይ ተሽከርካሪውን በእጃቸው ለማድረግ ከፖሊስ እየጠበቁ መሆናቸውን አመልክተው " ተሽከርካሪዎቹን ይወስዳሉ ተብለው የተጠረጠሩት አልተያዙም ክትትል እየተደረገ ነው " ሲሉ ጠቁመዋል። አሁንም ቀሪ አንዱን ተሽከርካሪ ኦሮ ኮድ 03 41867 ያየ እንዲጠቁማቸው ተማጽነዋል። ከዚህ ቀደም ባለንብረቶቹ በጥበቃና ቀጣሪ ኤጀንሲው ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸው የነበረ ሲሆን በዚህ ላይ ገና ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamliyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👏 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያን ይፋ አደረገ ! ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ ይፋ ባደረገው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ ውስጥ ካቀዳቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የሆነውን ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ የማብሰሪያ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡ ይህ ለደንበኞች የተሟላ፣ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ንብተራ ኦንላይን ሱፐር አፕ መተግበሪያ ከሐምሌ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ መተግበርያው ደንበኞች ከባንክ አገልግልት በተጨማሪ ግብይቶችንና ክፍያዎችን በቀላሉ የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም መፈጸም እንደሚያስችላቸው በዚሁ የማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጻል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት ባንኩ ለደንበኞቹ ዘመኑ የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በውጤት የታጀበ አገልግልት ለመስጠት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን አዲሱ የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድም ከባለድርሻ አካላትና ከመላው ደንበኞቹ ጋር በመሆን የላቀ ውጤት የሚመዘገብበት ይሆናል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ይህ በውስጥ አቅም በልጽጎ ወደ ተግባር የገባው ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያና አዲሱ የሶስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማበልፀግና ወደ ሥራ እንዲገባ ላደረጉ የባንኩ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ምሰጋና ያቀረቡት የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሊ/መንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ አዲሱ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምክክር አድርገውበትና ጸድቆ ወደ ሥራ መግባቱን አመልክተዋል፡፡ በይፋዊ የንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፣ ደንበኞች፣ የባንኩ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- https://www.nibbanksc.com/wp-content/uploads/2025/07/Press-release-NIB-Tera.pdf ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ! #Nib #DigitalBanking #Nibinternationalbank #nibbank #nibtera #nibsuperapp Facebook  / Instagram / linkedin / X / Youtube / Tiktok / Website
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ትናንሽ አውሮፕላኖች እናስመጣለን "-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያዊ አየር መንገድ መጋቢት 17/2017 ዓም ላይ አርቸር አቪዬሽን ከተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ጋር ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል። ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አርቸር አቪዬሽን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋል ሲሆን በመኪና ከ60-90 ደቂቃ የሚወስድ ጉዞን ወደ 10 ደቂቃ ዝቅ የሚያደርግ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። የዚህ ስምምነት ትግበራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጥያቄ አቅርቧል። ዋና ስራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ " በፈርንጂዎቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ትናንሽ አውሮፕላኖች እናስመጣለን በዋነኛነት የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ እንጠቀምባቸዋለን ብለን አቅደናል " ብለዋል። የኢ-ኮሜርስ ንግድን ከማስፋፋት አኳያ አየር መንገዱ ከአለም አቀፎቹ አማዞን እና አሊባባ እንዲሁም ከሃገር ውስጡ " ዘመን ገበያ " ጋር በአጋርነት ለመስራት አስቧል ወይ ? ምን አይነት እንቅስቃሴዎችንስ እያደረገ ይገኛል ? የሚል ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ መስፍን ፤ አየር መንገዱ የተወሰነ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሚገኝ ነገር ግን ገና በሚባል ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን በተጨማሪ ምን አሉ ? "እኛ እስካሁን ድረስ ኢ-ኮሜርስን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመስራት የሚያስችለንን ፋሲሊቲ ገንብተናል። ይህ ፋስሊቲ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አካሉን ብቻ ነው የሚሰራው እኛ ኢ-ኮሜርስ ውስጥ አንገባም ኢ-ኮሜርስ ንግዱን የሚሰሩት ሌሎች ድርጅቶች ናቸው እኛ ትራንስፖርቱን ነው የምናቀላጥፈው። ከመነሻው ማጠናቀቁን እና መዳረሻውን ላይ ደግሞ የመጨረሻውን ከሚያከፋፍሉ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅተን ቦሌ ኤርፖርት ካርጎ ተርሚናላችንን ተጠቅመን ይህንን ለማሳለጥ ነው የምንሰራው የተወሰነ የተጀመረ ስራ አለ ነገር ግን ገና መሰራት ያለበት ነው " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamliyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅሬታችንን ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት አስገብተናል " - የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የ‎ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ በመቃወም ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል። ‎ ክለቡ ቅሬታዉን በየደረጃ ለፌዴሬሽኑም አስገብቶ ምላሽ ባለማግኘቱ ወደ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ማለፉን የገልጿል። ሲዳማ ቡና ከወላይታ ዲቻ ጋር ባደረጉት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጫወታ የሲዳማ እግር ኳስ ክለብ 2ለ1 አሸንፎ ዋንጫዉን ቢያነሳም " ያለ አግባብ ተጫዋቾችን አሰልፏል " በሚል ፌዴሬሽኑ ቡድኑ የወሰደዉን ዋንጫ ለወላይታ ዲቻ ተመላሽ እንዲያደርግ የሚል ዉሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ #TikvahEthiopiaFamilyHawassa ‎@tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
3👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አ/አ ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር የመብራት ኮንክሪት ፖል ለመውደቅ ጫፍ ላይ መድረሱን በመጠቆም መፍትሔ ይፈለግለት ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች መጠየቃቸው ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደረሰው መረጃ መሰረት ይህንን ፖል የመቀየር ሥራ በምሽት እየተሰራ ይገኛል። " ባለሞያዎቻችን አሁንም እዛው ሳይት ናቸው " ሲል ጥገናው ምሽቱን እየተከናወነ መሆኑን የገለጸልን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፥ ፖሉ ተበልቶ ሳይሆን በመኪና ተገጭቶ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር መረጃውን አጋርቶናል። @eeuethiopia ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
14.68 MB
5🤔 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ባለቤቴንና አምስት ልጆቼን ነው ያጣሁት " - ተጎጂ አባት ➡️ " ጥቃቱን ያደረሱት ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ታጣቂዎች ናቸው ! " - የአካባቢው ነዋሪ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ቆንዳላ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ተገደሉ። ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ሃምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ነው የተፈጸመው። የታጠቁ አካላት በመደዳው አንድ መንደር ላይ አነጣጥረው የዘፈቀደ ጥቃት ማድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡ ብርሃኑ ሸምሰዲን የተባሉ ተጎጂ በጥቃቱ ሙሉ የቤተሰቦቻቸውን አባል አጥተዋል፡፡ ባለቤታቸውን እና አምስት ልጆቻቸውን ድንገት ከቤት በወጡበት አጋጣሚ አልቀው ማግኘታቸውን ተናግረዋል። አደጋው ዱብ እዳ እንደሆነባቸው በደከመና በሚቆራረጥ ድምፅ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ተናግረዋል። " ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል አከባቢ ነው ስድስት የቤተሰቤ አባላት በሙሉ የጨረሱብኝ፡፡ የሁለት ዓመት ጨቅላ ህጻንና ባለቤቴን ጨምሮ ሶስት ወንድ ልጆቼን እና ሁለት ሴት ልጆቼ አልቀውብኛል " ብለዋል። " የአምስት ዓመት፣ የ11 እና 12 ዓመት እንዲሁም የ14 ዓመት እድሜ ልጆች ናቸው ያለቁብኝ፡፡ ገዳዮች ከኔ የተለየ ቂም የላቸውም፤ #ጽንፈኛ የሚባሉ በአከባቢያችን የደቡብ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ሸምቀው ያሉ መሆናቸው ብቻ ነው የተነገረን " ሲሉ አክለዋል። " በመንደራችን በመደደው በተወሰደብን ድንገተኛው ጥቃት እንደ እኔ ሙሉ ቤተሰቦቻቸው አልቆባቸው ባይጎዱም እንደ እኔ ሁሉ ዉዶቻቸውን ያጡ አራት ቤቶች ግድም ጎረቤቶቼም አሉ " ብለዋል። ጥቃቱ ድንገተኛና ምንም በማያውቁ ንጹሃን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህ ሁሉ አደጋ በመላው ቤተሰቦቻቸው ላይ የደረሰው እሳቸው ድንገት ለጉዳይ ወደ ጎረቤት ብቅ ባሉበት ሰዓት መሆኑን ገልጸዋል። " ጥቃቱ የተፈጸመው ሁሉም በማታው ቤቱ ቁጭ ባለበት ሰዓት ነው፡፡ አንዳንዶቹ እራት እየበሉ ሌሎችም ቴሌቪዢን እየተመለከቱ ባሉበት ነው ድንገት ገብተውባቸው የጥይት እሩምታ በማዝነብ ህጻናት እና ሴት ሳይሉ ያገኙትን ሁሉ የገደሉዋቸው " ብለዋል። " የተኩሱን ድምጽ ሰምቼ ከነበርኩበት ጎረቤት ቤት ልወጣ ስል በግድ አስቀመጡኝ፡፡ በኋላ ሮጬ ቤቴ ስደርስ ግን አንድም የተረፈልኝ የለም፤ ስድስት የቤተሰቤ አባላት በሙሉ አልቀው ጠበቁኝ " ሲሉ ሀዘናቸው መሪር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመበት ቦታ የምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጋር በምታዋስን ቆንዳላ ቀበሌ ዳርጌ ከተማ ነው ያሉት የአይን እማኝየአከባቢው ነዋሪ፤ በተለይ ይህ ጥቃት የተፈጸመው በከተማዋ ዳር ላይ በሚገኙ መንደሮች ነው ብለዋል፡፡ ለደህንነታቸው ስባል ስማቸውን ሳይገልጹ አስተያየታቸውን ብቻ ያጋሩን እኚህ አስተያየት ሰጪ፤ " በሰዓቱ ሁላችንም በዚያችው ከተማ ውስጥ ነበርን፡፡ ጥቃቱ በደረሰበት በዚያ አከባቢ የከባባድ መሳሪያዎች ድምጽ ጨምር ስንሰማ ስለነበር ተኩሱ ሲቆም 2፡30  አከባቢ ወደ ቦታው ስናመራ ብዙ አስከሬን አገኘን " ብለዋል። " የተጎዱትን ወደ ሆስፒታል ብንወስዳቸውም ሆስፒታልም ደርሰው ያለፉብን አሉ፡፡ አሁን ባጠቃላይ 14 ሰዎች ስሞቱ ሶስት ሰዎች በከባድ ሁኔታ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል። " ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው በር እየከፈቱ እየገቡ የአንድ ዓመት ህጻን ጨምሮ አዛውንትና ሴት ሳይሉ ያገኙት ሁሉ ላይ ጥይት አርከፍክፈው የወጡት " ብለዋል፡፡   በወቅቱ የከተማዋን ጸጥታ የሚያስጠብቁ የፀጥታ አካላት በቦታው እንደሌሉ የገለጹት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ወደ 40 የሚጠጉ ናቸውም ብለዋል፡፡ " የፀጥታ መዋቅር በሰዓቱ ወደ ሌላ ስፍራ ተንቀሳቅሶ ነበር ነው የሚባለው፡፡ ይህን ክፍተት በመጠቀም ይመስላል ታጣቂዎቹ ዘልቀው ገብተው እንዲህ ያለ ዘግናኝ ጥቃት ያደረሱት፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ሲሆን ከተማ ውስጥ ገብተው ጥቃቱን ያደረሱም በቁጥር ከ35 እስከ 40 እንደሚሆኑ ከጥቃቱ የተረፉ ነግረውናል፡፡ መሰል ድርጊቶች በዚህ ቀበሌና አከባቢው ተደጋግሞ የተፈጸመ ሲሆን አሁንም ልቆም አልቻለም " ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል፡፡ አከባቢው አሁን ተረጋግቶ እንደሆነ የተጠየቁት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ፤ " ለአሁኑማ ምን መረጋጋት አለ፤ ሰው የሞተበትን ቀብሮ ሀዘን ተቀምጠዋል፡፡ የህግ አካላትም መጥተው ' ድርጊቱን የፈጸመውን አካል እያደንን ነው ' ብለዋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
😭 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" አንድ ካህንና ወንድሙ፤ ሁለት ሰዎች ናቸው ታግተው የተወሰዱት። አንድ አባት እስከ ልጃቸው ተገድለዋል " - የወረዳው ቤተ ክህነት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሶኮራ ቀበሌ የ"ሸኔ" ታጣቂ ቡድን በአንድ ቤተሰብ አባላት የግድያ እና እገታ ጥቃት መፈጸሙን የወረዳው ቤተ ክህነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ቤተ ክህነቱ የሆነውን ሲያስረዳ፣ " ሁለት ሰዎች ተገድለዋል፤ ትላንት 3 ሰዓት ከሩብ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ የሟች አባትና ልጅ ቀብር ተፈጽሟል። ካህንና ምዕመን ወንድማማቾች ታግተው ተወስደዋል፤ የተወሰዱትም የሟች ወንድም ናቸው " ሲል ተናግሯል። " አንድ ካህንና ወንድሙ፤ ሁለት ናቸው ታግተው የተወሰዱት። አንድ አባት እስከ ልጃቸው ተገድለዋል " ብሎ፣ ታጋች ካህን የሰኮራ ኪዳነ ምህረት አገልጋይ መሆናቸውን ገልጿል። ቤተ ክህነቱ፣ " ህዝቡ ሁሌም በልቅሶ ነው፤ ሁሌ መገደል ነው ማን ይደርስለታል " ሲልም በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚፈጸምን ጥቃት አስከፊነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። " ታጣቂ ቡድኑ 3 ሰዓት ይመጣል፤ ምሽት 11 ሰዓት ይመለሳል፤ በሌሊትም የፈለገውን ይፈጸሰማል" ብሎ " መንግስት የህዝቡ ድምጽ እንዲሰማና ህዝቡን እንዲጠብቅ አሳስቧል። " መንግስት ቢደርስ ጥሩ ነው በወረዳው ከ2014 ዓ/ም ጀሞሮ ያለማቋረጥ ነው ግድያ እየተፈጸመ ያለው። ህዝቡ እየተፈናቀለ ነው፤ ተፈናቅሎም የሚገባበት የለም። ይህ የሆነው መንግስት ሃይ ባለማለቱ ነው " ሲልም ወቅሷል። እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በበዞኑ ሶኮራ ቀበሌ ሐምሌ 4/2017 ዓ/ም አባትና ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ ገልጾ፣ " የሟች ወንድሞችና የአጥቢያው  አገልጋይ ካህን ቄስ አድማሱ ጌታነህና ወገኔ ጌታነህ ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን፣ የደረሱበት አልታወቀም " ሲል አስታውቋል። " ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ኃይል በዞኑ በሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ እየተንቀሳቀሰ ከፍተኛ ሰቆቃ የሚፈጽም ሲሆን፣ ከፌዴራሉም ሆነ ከክልሉ መንግሥት በኩል ነገሩን ከማድበስበስ ያለፈ እስካሁን ይህ ነው የሚባል እርምጃ ሲወስዱ አልታየም። ይህም ለሌላ ጥርጣሬ የሚጋብዝ ነው " ብሏል። " ፓርቲያችን ግድያውን በጽኑ ያወግዛል፤ ታፍነው የተወሰዱ ካህንና ወንድማቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ይጠይቃል " ሲል ገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
😭 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ዙሪያ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይዘዋቸው የምናያቸውን በርካታ ፖስ ማሽኖች በማስቀረት ወደ አንድ የተቀናጀ ስርአት እንዲገቡ ያስችላቸዋል የተባለ ሲስተም ይፋ ተደርጓል። ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከዳሽን ባንክ እና ኤታ ሶሉሽንስ በአጋርነት በጋራ በመሆን የቀረበው "ዙሪያ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲስተም  በአስመጪና ላኪ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና ችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን ያግዛቸዋል ተብሏል። "ዙሪያ" የኢ.አር.ፒ (ERP)፣ የፒ.ኦ.ኤስ (POS) እና ካሽ ሬጂስተር (Cash Register) አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ለመስጠት የሚያስችል የቢዝነስ አውቶሜሽ ሶሉሽን የያዘ ሲስተም ነው፡፡ መተግበሪያው የተለያየ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይዘዋቸው የምናያቸውን በርካታ ፖስ ማሽኖች በማስቀረት ወደ አንድ የተቀናጀ ስርአት እንዲገቡ የሚያስችል ነው። "ዙሪያ" ሁሉንም የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ካርዶች መቀበል እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና እንደተሰጠው ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ላይ ተገልጿል። ይህ ሲስተም የሂሳብ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ነጋዴዎች የሚያንቀሳቅሱትን ሃብት ለማስተዳደር እና ማንኛውንም የክፍያ መረጃዎች በአንድ ያካተተ ደረሰኝ ለማግኘት ያስችላል ነው የተባለው፡፡ አገልግሎቱን ለማቅረብ ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌክላውድ (TeleCloud) መሠረተ ልማት በማቅረብ የተሳተፈ ሲሆን ለዚህ አገልግሎት የሚውለውን ማሽን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በማመቻቸት ዳሽን ባንክ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተነግሯል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👏 1🕊 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#EFFORT " ነባሩ ቦርድ ህጋዊ ነው ፤ በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " የሚል ውሳነ መሰጠቱ ተሰማ። የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታማኝ ምንጮች በላኩት መረጃ ነባሩ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር " ህገ-ወጥ የምክር ጉባኤ አካሂዶ ህገ-ያልተከተሉ አመራሮች መርጦ በተቋሙ ላይ የጀመረው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ይታገድልኝ " ሲል ለክልሉ የፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት አግኝቷል። " በስራ ላይ ያለው ህጋዊ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር ነኝ " የሚል አካል ለፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ምን ይመስላል ? በአቶ ቴድሮስ ሓጎስ የሚመራው የትእምት ባለ አደራ ቦርድ አመራር " በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህገ-ወጥ ነው ፤ በጉባኤው  የተመረጠ በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራ ቦርድ በተቋሙ ላይ እያካሄደ የሚገኘው እንቅስቃሴም ህገ-ወጥ መሆኑ ተጣርቶ ይታገድልኝ " ሲል ለፍትህ ቢሮ አቤታቱ አቅርቧል። ሦስት አጣሪ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም  ላለፉት 10 ቀናት የቀረበለት አቤቱታ ሲመረምር የቆየው የፍትህ ቢሮ " በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራ ቦርድ ህጋዊ  አይደለም " በማለት በትእምት ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንዲያቆም የእግድ ውሳኔ ሰጥቷል። " የትእምት ምክር ቤት ባለፈው የካቲት 2017 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ መርጦኛል " በሚል በመንቀሳቀስ ላይ ያለውና  የተቋሙ ዋና ስራ  አስፈፃሚ በየነ መክሩ ህጋዊ ርክክብ ባላካሄዱበት ሁኔታ በላያቸው ላይ አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለመቅጠር በሚድያዎች እስከማስነገር የደረሰው በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራው አካል " ህጋዊ  አይደለህም " የሚል የፍትህ ቢሮ ውሳኔ ያከብር ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው። ባለፈው መጋቢት 2017 ዓ.ም በተፈጠረው የፓለቲካ ቀውስ ምክንያት የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከትግራይ መውጣታቸው ተከትሎ የትእምት ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስፈፃሚና የባለ አደራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ መክሩና አቶ ቴድሮስ ሓጎስ ከክልሉ ውጪ ናቸው። የትእምት ዋና ስራ ስፈፃሚ በየነ መክሩ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላዛ ትግርኛ ለተባለው ሚድያ ከአዲስ አበባ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ " ህገ-ወጥ ቡድኑ በሃይል ካስቀመጣቸው አመራሮች የተደረገ ርክክብ የለም ፤ ዋና ስራ አስፈፃሚና ቦርድ የነበረው ነው ያለው " ማለታቸው ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ #TikvahEthiopiaFamilyMekelle @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው  መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚያስገነባው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ መገለጹ ይታወሳል። 3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ የአየር ማረፊያ ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አየር መንገዱ አሳውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአሁኑ ሰአት ለ2,500 አባውራዎች መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን እና በመስከረም ወር ለማስረከብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ስለ አዲሱ አየር መንገድ እና በሃገር ውስጥ ያሉ መዳረሻዎችን ለማስፋት እየተሰራ ስላለው ስራ በዝርዝር ምን አሉ ? " አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው እንደተጠናቀቀ ወደ ተሰራላቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ይዘዋወራሉ ስራቸውንም በአዲስ መልክ ይጀምራሉ። ቦታው ሲለቀቅልን የግንባታ ስራ እንጀምራለን የአየር መንገዱ ዲዛይንም በብዙ አድቫንስ አድርጓል እየቆራረጥን በቅደም ተከተል ነው የምንሰራው የመጀመሪያውን ዙር ስራ ህዳር ውስጥ ለመጀመር እቅድ ይዘናል። የሃገር ውስጥ በረራን ለማስፋት እና የአገልግሎት ጥራቱን ከፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ጥቂት አመታት በርካታ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። ከስራዎቹ  መሃል ዛሬ ላይ ያሉን የአውሮፕላን ጣቢያዎች ማሻሻል ነው የአውሮፕላን መንደርደሪያው ጥሩ ካልሆነ እሱን በአዲስ መልክ መስራት። መንገደኞች የሚስተናገዱባቸው ተርሚናሎችም አንዳንዶቹ ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና አሮጌ ፣ ወይም በቆርቆሮ የተሰሩ ነበሩ እነሱን እያፈረስን በዘመናዊ መንገድ እየሰራን ነው ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማይቻል በቅደም ተከተል ነው የምንሰራው። ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ብቻ እንደ ጎዴ እና ጂንካ ያሉ 3 ተርሚናሎችን ሰርተን ስራ ላይ አውለናል። አገልግሎቱን ለማስፋትም አዳዲስ ኤርፖርቶችን በመስራት ላይ እንገኛለን በአሁኑ ሰአት ስድስት ተርሚናሎች እየተሰሩ ይገኛሉ አንዳንዶቹ ለምረቃ ደርሰዋል። ለምሳሌ ፦ ያቤሎ መንደርደሪያው አልቋል በሁለት ወር ውስጥ በረራ እምጀምራለን እሱ 23ኛው የሃገር ውስጥ መዳረሻችን ይሆናል ማለት ነው። ነገሌ ቦረና፣ መቱ ፣ሚዛን አማን እና ደብረ ማርቆስም በመገንባት ላይ ናቸው በሚመጡት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል" - ፖሊስ በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ የጅብ መንጋ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ። የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ስምዖን ለንበቦ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ገደማ የጅብ መንጋ በወረዳዉ ወይደ መላቶ ቀበሌ በሰዎች ላይ ጉዳት ሰንዝሮ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። በአከባቢው ከከተማ በቅርብ ርቀት ጥብቅ ደኖች መኖራቸውን የገለፁት ፖሊስ አዛዡ ጅቦች በጫካዉ ዉስጥ እንዳሉ ቢታወቅም እስካሁን በሰዉ ላይ ጉዳት አድርሰው እንደማያውቅና የትናንት ምሽቱ ጥቃት ድንገተኛ እንደሆነ ገልጸዋል። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አዛዡ ገልጸው ማምሻዉን ጥንቃቄና ጥበቃ ሲደረግ ማደሩንና ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ የፀጥታ አባላት ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አሰሳ እያደረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ #TikvahEthiopiaFamilyHW @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1😱 1