75 105
Obunachilar
-3824 soatlar
-2827 kunlar
-1 04230 kunlar
Ma'lumot yuklanmoqda...
O'xshash kanallar
Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
June '25
June '250
1
1 kanaldaMay '250
4
4 kanalda Get PRO
April '250
3
3 kanalda Get PRO
March '250
3
2 kanalda Get PRO
February '25
+215
5
4 kanalda Get PRO
January '25
+11
7
5 kanalda Get PRO
December '24
+890
32
8 kanalda Get PRO
November '24
+80
12
4 kanalda Get PRO
October '24
+181
5
2 kanalda Get PRO
September '24
+25
2
2 kanalda Get PRO
August '24
+106
@0
0 kanalda Get PRO
July '240
1
1 kanalda Get PRO
June '24
+2
@0
0 kanalda Get PRO
May '24
+24
@0
0 kanalda Get PRO
April '24
+28
@0
0 kanalda Get PRO
March '24
+17
2
2 kanalda Get PRO
February '24
+108
5
5 kanalda Get PRO
January '24
+13
2
2 kanalda Get PRO
December '23
+4
5
2 kanalda Get PRO
November '23
+7
8
5 kanalda Get PRO
October '23
+13
@0
0 kanalda Get PRO
September '23
+8
@0
0 kanalda Get PRO
August '23
+4
@0
0 kanalda Get PRO
July '23
+8
@0
0 kanalda Get PRO
June '23
+24
@0
0 kanalda Get PRO
May '23
+26
@0
0 kanalda Get PRO
April '23
+13
@0
0 kanalda Get PRO
March '23
+23
@0
0 kanalda Get PRO
February '23
+8
@0
0 kanalda Get PRO
January '23
+17
@0
0 kanalda Get PRO
December '22
+4
@0
0 kanalda Get PRO
November '22
+2
@0
0 kanalda Get PRO
October '22
+5
@0
0 kanalda Get PRO
September '22
+3
@0
0 kanalda Get PRO
August '220
@0
0 kanalda Get PRO
July '22
+3
@0
0 kanalda Get PRO
June '220
@0
0 kanalda Get PRO
May '22
+4 859
@0
0 kanalda Get PRO
April '22
+5
@0
0 kanalda Get PRO
March '22
+2 698
@0
0 kanalda Get PRO
February '22
+16 917
@0
0 kanalda Get PRO
January '22
+14 889
@0
0 kanalda Get PRO
December '21
+5
@0
0 kanalda Get PRO
November '21
+2
@0
0 kanalda Get PRO
October '21
+5 239
@0
0 kanalda Get PRO
September '21
+7 282
@0
0 kanalda Get PRO
August '21
+13
@0
0 kanalda Get PRO
July '21
+8
@0
0 kanalda Get PRO
June '21
+114
@0
0 kanalda Get PRO
May '210
@0
0 kanalda Get PRO
April '21
+4
@0
0 kanalda Get PRO
March '21
+3
@0
0 kanalda Get PRO
February '210
@0
0 kanalda Get PRO
January '21
+88
@0
0 kanalda Get PRO
December '20
+316 116
@0
0 kanaldaSana | Obunachilarni jalb qilish | Esdaliklar | Kanallar | |
16 June | 0 | @0 | 0 | |
15 June | 0 | @0 | 0 | |
14 June | 0 | @0 | 0 | |
13 June | 0 | @0 | 0 | |
12 June | 0 | @0 | 0 | |
11 June | 0 | @0 | 0 | |
10 June | 0 | @0 | 0 | |
09 June | 0 | @0 | 0 | |
08 June | 0 | @0 | 0 | |
07 June | 0 | @0 | 0 | |
06 June | 0 | @0 | 0 | |
05 June | 0 | @0 | 0 | |
04 June | 0 | @0 | 0 | |
03 June | 0 | 1 | ||
02 June | 0 | @0 | 0 | |
01 June | 0 | @0 | 0 |
Kanal postlari
ላባቴ
በእውቀቱ ስዩም
ሰው ብቻ አይደለህም፥ ካፈር ወጥተህ ላፈር
ክብርህ ማንነትህ ባመጽ የሚታፈር የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዘፋን፥ በርጩማ የምትመርጥ፤
ያለ ባሕር ሰርጓጅ፡ ያለ ሙሴ በትር በመታገስ ብቻ፡ ባሕር የምትመትር
ካዘልከኝ ጀምር ፥ እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጅ ፥ ዝቅታውን ሳላይ
እንደነስር መጠቅሁ፥ እንደ ምስራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን ፥ እንደ ዳንቴል ሰራሁ
በርግጥ ድሀ ነበርክ
ከሰላምታ በቀር፥ የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፥ ሰውነትህ የክት፤
በርግጥ ድሀ ነበርክ፥ የነጣህ የጠራህ ከጦር ሜዳ ይልቅ፥ ገበያ ሚያስፈራህ ቤሳ ባታወርሰኝ፥ አወረስከኝ ትግል የትም እንዳይጥለኝ፥ ሕይወት እንደ ፈንግል፤
አባየ ብርሃን
አባ የምሥራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፥ እንደ ካባ ገበር አባቴ አባቴ ባትሆን፥ ምን ይውጠኝ ነበር።
2 351220
2 | Man's Search For Meaning - Viktor E. Frankel.pdf | 5 511 |
3 | Man's Search For Meaning
ከናዚ ጭፍጨፋ(Holocaust) የተረፈውና ቀሪ ዘመኑን መኖር የቻለው ሳይኮቴራፒስቱ ቪክቶር ፍራንክ- Viktore Frankl በናዚ ጀርመን የማሰቃያ እና ማጎሪያ ካምፕ (Auschwitz concentration camp) ውስጥ ሆኖ የነበረውን የሕይወት ገጠመኝ(ልምድ) ተመርኩዞ "መቆጣጠርና መለወጥ በምንችለው ጉዳይ ብቻ ማተኮር" ስላለው ጠቀሜታ "Man's Search For Meaning" በሚል መፅሐፉ አስፍሯል።
Frankl ማተኮር ያለብን "ማድረግ፣ መቆጣጠር እና መለወጥ" በምንችለው ጉዳይ ላይ እንዲሆን ይመክራል። መለወጥ በማንችለው ነገር ብዙ ጊዜ ሰጥተን ከቆየን "መለወጥ የማንችለው ነገር" ሳያገኘንም "ጭንቀት፣ ፍርሃት ወደ ከፋ ጉዳት" እንደሚወስደን ያሳስባል።
Frankl በናዚ በአሰቃቂ ሁኔታ እንገደል ይሆን በሚል ጭንቀት ብቻ አይሁዶች እስር ቤት ውስጥ እያሉም ሲታመሙ፣ ሲሞቱ ያየውን ፅፏል። Frankl ራሱ ግን በናዚ ጀርመን እገደል ይሆን ወይም ስለ ሞት(መገደል) ማሰብ ትቶ በተስፋ ተሞልቶ አንድ ቀን ከእስር ሲፈታ ስለሚፅፈው መፅሀፍ፣ ስለሚሰራቸው በጎ ስራዎች ብቻ አተኩሮ ሙሉ ጊዜ ወስዶ ማሰቡ ከጭንቀትና ከፍርሃት እንደገላገለው(እንደታደገው) ፅፏል።
በሕይወት ቆይቶም 2ኛው የአለም ጦርነት ሲያልቅ ነገሮች ተቀይረው ሳይገደል ከእስር ለመለቀቅ በቅቶ ለሰው ሁሉ የሚጠቅም በርካታ ስራ ሰርቷል። Frankl በናዚ መገደልን እያሰበ በፍርሀት ቢኖር ግን በህይወት እያለ ከእስር ቤት የመውጣት እድሉ አናሳ ነበር።
ስለዚህ በበርካታ ፈተናዎች ታጥረን ቢሆንም እንኳን ራዕይ፣ መልካም አስተሳሰብ፣ ህልም እና ልንኖርለት የምንችለው አለማ ሊኖረን እንደሚገባ የስነልቦናው ዘርፍ ይመክረናል። [ ቢኒያም ቢኑ ] ✍
©️ከፍልስፍና አለም | 5 152 |
4 | ከተደበቀባችሁበት ውጡ!!
አንዳንድ ሰዎች የሚተኙት እረፍት ለማግኘት አይደለም፤ ካለባቸው የስሜት ስቃይ፣ ኃዘን፣ ድብርትና ይህችን አለም ለመጋፈጥ አቅም የማጣት ስሜት ለመደበቅ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ጓደኛም ሆነ ፍቅረኛ የሚይዙት የትክክለኛን ግንኙነት ጣእም ለማጣጣምና አብሮ ለማደግ አይደለም፤ ካለባቸው የብቸኝነት፣ ተቀባይነት የማጣትና ለብቻ የመቅረት ፍርሃት ለመደበቅ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ለሁሉም ሰውና ነገር “እሺ” በማለት ሁል ጊዜ ተባባሪና ተሳታፊ የሚሆኑት ያንን ማድረግ ደስታ ስለሚሰጣቸውና የሕይወታቸው መርህ ስለሆነ አይደለም፤ የራሳቸውን አመለካከት፣ ትክክለኛ የሆነውን ነገርና እነሱን ደስ የሚያሰኛቸውን ነገር ካደረጉ ሰዎች በእነሱ ላይ ሊኖራቸው ይችላል ብለው የሚያስቡትን አመለካከት ስለሚፈሩትና ከዚያ ለመደበቅ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ቀን-ከሌት ካለማቋረጥ በማሕበራዊ ግንኙነት እና በማሕበራዊ ሚዲያ ታጅበው የሚኖሩት በዚያ ሁኔታ ውስጥ የሚያከናውኑት አንድ ጠቃሚ ዓላማ ስላላቸው አይደለም፤ ከራሳቸው አመለካከትና መቀበል ካቃታቸው የራሳቸው ማንነትና ሁኔታ ለመደበቅ ነው፡፡
ከተደበቀባችሁበት ውጡ!
ትክክለኛውን የሕይወት መስክ ፈልጉና ድረሱበት!
ማንነታችሁን ተቀበሉ!
ያንንም ሕይወት በነጻነት ኑሩ!
ዶ/ር እዮብ ማሞ
@enlighten_ethiopia | 7 959 |
5 | "የሆነ ነገር ስራ" መመሪያ
"ድርጊት የመነሳሳት(motivation) ምክንያት ነው።"
ማርክ ማንሶን
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ የሂሳብ አስተማሪዬ የነበረው ሚስተር ፓክውድ፤ “በአንድ ችግር ላይ ከተያዝክ፣ እዚያው ቁጭ ብለህ ስለእርሱ አታስብ፤ ለመፍታት መስራት ጀምር፡፡ የምትሰራው ምን እንደሆነ ባታውቅ እንኳን በዚያ ነገር ላይ መስራት መጀመር በመጨረሻ ትክክለኛው ሀሳብ በጭንቅላትህ እንዲመጣ ያደርጋል፡” ይለን ነበር፡፡
የራሴን ስራ በጀመርኩበት ወቅት፤ በየቀኑ በምታገልበት፤ ሙሉ በሙሉ ምን መስራት እንዳለብኝ ፍንጭ የሌለኝ በሆንኩበት ወቅት፤ የምሰራው ስራ የሚያመጣውን ውጤት በፈራሁበት ጊዜ የሚስተር ፓክውድ ምክር በአእምሮዬ ውስጥ መምጣት ጀመረ፡፡
“ዝም ብለህ አትቀመጥ፡፡ የሆነ ነገር ስራ ከዚያ መልሶቹ ይከተላሉ” ሲል ሰማሁት፡፡
የሚስተር ፓክውድን ምክር ተግባራዊ በማደርግበት ጊዜ ስለ መነሳሳት አንድ ኃያል ትምህርት ተማርኩ፡፡ ይህ ትምህርት ዘልቆ እስኪገባኝ ስምንት አመታት ገደማ ወስዷል፡፡
"ድርጊት የመነሳሳት ውጤት ብቻ ሳይሆን ምክንያትም ነው፡፡"
አብዛኞቻችን ለድርጊት የምንዘጋጀው የሆነ የመነሳሳት ደረጃ እንዳለን ሲሰማን ብቻ ነው፡፡ መነሳሳት የሚሰማን ደግሞ በቂ የሆነ ስሜታዊ መቀስቀስ ሲሰማን ነው፡ እነዚህ ደረጃዎች በሰንሰለታዊ መያያዝ አይነት እንደሚከሰቱ እንገምታለን፡፡
ስሜታዊ መነቃቃት → መነሳሳት → ተፈላጊ ድርጊት
የሆነ ነገር ማከናወን ፈልገህ ነገር ግን መነሳሳት ወይም የስሜት መቀስቀስ ካልተሰማህ እንደወደቅህ ይሰማሀል፡፡ ስለዚያ ልታደርገው የምትችለው ነገር የለም፡፡ በቂ መነሳሳት ተፈጥሮ ከተኛህበት ተነስተህ የሆነ ነገር ለመስራት የምትችለው የሆነ ከፍተኛ ስሜታዊ የሕይወት ክስተት ሲከሰት ነው፡፡
ስለ መነሳሳት ያለው ነገር ባለ ሶስት ክፍል ሰንሰለት ብቻ ሳይሆን መጨረሻ የሌለው ቀለበትም ነው፡፡
የመንፈስ መነቃቃት > መነሳሳት > ድርጊት > የመንፈስ መነቃቃት> መነሳሳት > ድርጊት > ወዘተ
ድርጊቶችህ ተጨማሪ ስሜታዊ ምላሾችና የወደፊት ድርጊቶችህን ለማነሳሳት የሚያንቀሳቅስህን ተጨማሪ ስሜታዊ ምላሾች እንዲሁም የወደፊት ድርጊቶችንህ ለማነሳሳት የሚያንቀሳቅስህን መንፈሳዊ መነቃቃት ይፈጥራሉ፡፡ በዚህ እውቀት በመጠቀም በሚከተለው መንገድ አስተሳሰባችንን እንደገና ማስተካከል እንችላለን፡፡
ድርጊት > የመንፈስ መነቃቃት → መነሳሳት
በሕይወትህ ውስጥ አስፈላጊ ለውጥ ለማድረግ መነሳሳት ካጣህ፣ የሆነ ነገር ስራ ፤ ስለምትሰራው ስራ መነሳሳቱ እስኪመጣ አትጠብቅ ፤ምን መስራት እንዳለብህም አብዝተህ አትጨነቅ።የሆነ ነገር በመስራት ራስህን ማስገደድ ጀምር።መነሳሳቱ እንዲቀጥል መንፈስን ለማነሳሳት የሚያስፈልገው ድርጊት ያ ነው፡፡ የራስህ መንፈስ መነሳሳት ምንጭ ራስህ መሆን ትችላለህ፡፡
@enlighten_ethiopia | 7 140 |
6 | ጠቅላይ ሚኒስትሩ -" የምግብ ክምችታችን በምን ያህል ደረጃ ይገኛል?" ሲል ይጠይቃል
የግብርና ሚኒስተሩ- "እምብዛም የሚያሳስብ አይደለም ጌታዬ " ይመልሳል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ -" ምንያህል ስንዴ አለን?"
የግብርና ሚኒስተር- "ለ5 አመት የሚበቃ አለን"
ጠ/ሚኒስትሩ- "ጤፍስ ?"
የግብርና ሚኒስትሩ -"ከ4 አመት በላይ የሚሆን አለን"
ጠ/ ሚኒስትሩ- "ስኳር እና ዘይትስ?"
የግብርና ሚኒስትሩ- "በቂ ነው እሱም መጪዎቹን ሶስቱን አመታት ይሸፍናል"
ጠ/ሚኒስትሩ - "ምንሆነው ታዲያ ህዝቡ አስከፊ የምግብ እጥረት በሀገሪቱ ተከስቷል በማለት ሰልፍ የሚያካሄደው?"
የግብርና ሚኒስትሩ- "ጌታዬ በጣም አዝናለሁ የሚጠይቁኝ ስለሀገሪቱ የምግብ ሁኔታ አልመሰለኝም ነበር ሰለእኛ እና ስለ ቤተሰቦቻችን የምግብ ክምችት የጠየቁኝ መስሎኝ ነበር"
😂😂😂
@enlighten_ethiopia | 9 417 |
7 | ጊዜን ማስተዳደር
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ነብስ ካወቅንበት ጀምሮ ያለውን ዘመን እናስላው። ጊዜው እንደሸማኔ መወርወሪያ ይሮጣል። በአይን ጥቅሻ ዘመን ይከንፋል። እድሜ ይጣደፋል።
ቅርብ ጊዜ አይደል ልጆች የነበርን?
ጊዜን እንዳይባክን የሚያደርገው ምን ይሆን?
ጊዜ የላቀው ሀብት ነው። አያያዙን ላወቁበት በስኬት የሚመነዘር፥ ላላወቁበት የነገ ውድቀትን የሚያዋልድ ነው።... ጊዜን እንዴት እናስተዳድር?
ርዕሱን የዘነጋሁት ፀሐፊ ራስን ማስተዳደር የሚል መፅሐፍ አለው። ጊዜ አጠቃቀምን በተመለከተ ጠቃሚ ትምህርት አስፍሮ አንብቤ ነበር። (መፅሐፉን 2010 አከባቢ ነው ያነበብኩት)
ጊዜያችንን የሚበለው ድርጊታችን ነው። ድርጊታችንን ደግሞ በአራት መደብ መክፈል እንችላለን።
በወፍ በረር እንያቸው።
ሀ፥ አጣዳፊ ያልሆነ ፥ ደግሞም የማያስፈልግ።
ይህን በተመከተ ማብራሪያ ያስፈልግ ይሆን? አንድ ጉዳይ አስፈላጊም አስቸኳይም ካልሆነ ጉልበታችንን ልናባክንት እንደማይገባ ነጋሪ አያስፈልገንም። ይልቅ ወደ ቀጣዩ..
ለ፥ አጣዳፊ የሚመስል ዳሩ ግን የማያስፈልግ
እንዲህ ያለው ነገር የብዙ ወጣቶችን ጉልበት ይበላል። ጊዜን ያበክናል። ሱስ አይነተኛው ምሳሌ ነው። አስፈላጊነቱ ምንም ነው። ነገር ግን ያጣድፋል፥ ያቻኩላል። "አሁን ካልሆነ" ይላል። ለእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ ካልተሰጠው እድሜን ያበክናል። እርጅናን የምሬት ያደርጋል።
ሐ፥ አጣዳፊ ደግሞም አስፈላጊ
ይህች ጉዳይ ሁሉንም የምትሸውድ ናት። ጊዜን ለማስተዳደር የላቀው መንገድ እንዲህ ባለው ጉዳይ ላይ ማተኮር ይመስላል። አስገራሚው ነገር ግን አጣዳፊ ጉዳዮች ጊዜን አባካኝ መሆናቸው ነው።
አጣዳፊ እና አስቸኳይ ጉዳዮች በእለት ተዕለት ጉዳዮች ቢዚ ያደርጉናል። በጥቃቅን ነገሮች እንድንወጠር ያስገድዱናል። ጊዜያችንን የሩጫ ያደርጉታል። እንደባከንን ዘመናችንን ሊጨርሱት ይችላሉ።
መ፥ አጣዳፊ ያልሆነ ነገር ግን የሚያስፈልግ
በዚህ ነጥብ ላይ ማተኮር የሚችሉ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። አስተዋዮች ዋነኛ ትኩረታቸው አጣዳፊ ያልሆኑ ነገር ግን አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ነው። ይህ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል። ደግሞም ስኬታማ ያደርጋቸዋል።
የመጨረሻዎቹን ሁለት ነጥቦች (ሐ እና መ) ግልፅ የሚያደርግ ምሳሌ እናምጣ
በትምህርት መጀመሪያ ለፈተና መዘጋጀት አስፈላጊ ነገር ነው። ነገር ግን አጣዳፊ አይደለም። በአመቱ መጨረሻ ላይ ለሚደረግ ፈተና መስከረም ላይ መዘጋጀት አስቸኳይ ጉዳይ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን አስፈላጊ ነው። (አጣዳፊ ያልሆነ ነገር ግን አስፈላጊ)
በአመቱ መጨረሻ ለፈተና መዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ደግሞም አጣዳፊ ነው። (አስፈላጊና አጣዳፊ)
ከላይ እንዳነሳነው ለስኬት የሚረዳው እና የተሻለ የጊዜ መጠቀሚያ መንገድ አጣዳፊ ያልሆነ ነገር ግን አስፈላጊው ላይ ማተኮር ነው።
የላቀው ተማሪ በአመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለፈተና ይዘጋጃል። የፈተናው ወቅት ሲደርስ ለክለሳ የሚሆን የተትረፈረፈ ጊዜ ይኖረዋል። ራሱን ጫና ውስጥ አይከትም። ተረጋግቶ ለፈተና ይቀመጣል።
ፈተና ሲደርስ የሚያጠናውስ? ሩጫ ይበዛበታል። ለክለሳ የሚሆይ ጊዜ አይኖረውም። ውጥረት ውስጥ ስለሚገባ መረጋጋት ሊቸገር ይችላል።
(በእርግጥ ልዩ ሁኔታዎች ከግምት ይገባሉ)
ብዙ ሰው አጣዳፊ እና አስፈላጊ በሆነው ጉዳይ ላይ ሲዳክር ጊዜ ያመልጠዋል። አጣዳፊ እና አስፈላጊ ነገሮች ደግሞ ያደረ የቤት ስራ ውጤት የመሆን እድላቸው ቀላል አይደለም። አስፈላጊ ነገር ግን የማያስቸኩሉ በሆኑበት ወቅት ላይ "ጊዜ አለኝ" በሚል መዘናጋት ሳይሰሩ ይቀራሉ። በመጨረሻም ሩጫ ያስከትላሉ።
ተጨማሪ ምሳሌ፥
ስፖርት መስራት ለጤና አስፈላጊ ነው። ግን ደግሞ አጣዳፊ አይደለም።
አንድ ወጣት ዛሬ ስፖርት ሳይሰራ ቢቀር በማግስቱ ደም ግፊት አይዘውም። ስለዚህ አስቸኳይ አይደለም።
አንድ ወጣት ስፖርት ሳይሰራ ፥ እንቅስቃሴ ሳያደርግ እድሜውን ቢገፋ እና ለአላስፈላጊ ውፍረት ቢዳረግስ? ከዛጋር ተያይዞ የጤና መታወክ ቢከተልስ? ያኔ ስፖርት መስራት አጣዳፊም አስፈላጊም ጭምር ይሆናል ማለት ነው። ብዙ ጫና ተከትሎ ይመጣል። ምናልባትም ኢኮኖሚ ይናጋል።
ወጣቱ ቀድሞ ስፖርት የሚሰራ ቢሆን ቀጥሎ የሚመጣውን ቀድሞ ያግደዋል። ጊዜውም በአግባቡ ተጠቀመ ማለትም አይደል?
የፃፍኩት ግልፅ ነው? ዝም ብዬ ዘበዘብኩ ወይስ ሃሳቤን በትክክል ገለፅሁ?
ማለት የፈለግሁት በአጭሩ ልድገመው።
ጥሩ ጊዜ ማስተዳደሪያው መንገድ አስቸዃይ እና አስፈላጊ የሆነው ላይ ማተኮር አይደለም። የተሻለው መንገድ አስፈላጊ ነገር ግን አስቸኳይ ያልሆነውን በአግባቡ መስራት ነው። ያኔ አስፈላጊ እና አጣዳፊ በሆኑ ነገሮች የመዳከር እድል ይቀንሳል
@Tfanos | 9 394 |
8 | አሌክስ አብርሀም | 1 |
9 | የጤና ባለሞያዎችን መደገፍ ለምን....
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ዜጎች የሃኪሞችን ጥያቄ መደገፍ የውዴታ ግዴታችን ነው።
ላስረዳ
ምክኒያት አንድ፥
እውቀት ሊከበር ይገባል። ታታሪነት ተገቢውን እውቅና ማግኘት ይኖርበታል። ታታሪዎች ሲገፋ፥ አዋቂዎች ሲዋረዱ መጥፎ መልእክት ይተላለፋል።
አንድ ዶክተር የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ በብዙ መትጋት ግዴታው ነው። ደግሞም ጎበዝ ተማሪ መሆን ይጠበቅበታል። እኩዮቹ በሸነና ሲሉ አንገቱን ቀብሮ ለማንበብ ይገደዳል። ከዚህ ሁሉ በኋላ መሰረታዊ ፍላጎቱን ማሟላት የማይችል ሲሆን ሌሎች እውቀትን እንዲንቁ ይገደዳሉ።
"ጠንክሬ ብማር ፥ ታታሪ ብሆን ፥ ሰቃይ ተማሪ ሆኜ ብገኝ ምን ጥቅም?" የሚል ትውልድ ይበዛል። ትምህርትን የማያከብር ዜጋ በበዛ ቁጥር የሀገር ነገ ፥ የማህበረሰብ እጣ ፋንታ ይኮላሻል።
የሃኪሞችን ጥያቄ መደገፍ ለእውቀት እና ታታሪነት ተገቢውን ክብር መስጠት ነው
ምክኒያት ሁለት
"የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመፅ በሮች ይከፈታሉ" ይባላል። እንዳለመታደል የሐገራችን ፖለቲካ ከአመፅ የተጋባ ነው። የመብት ጥያቄዎች በአመፅ ይታጀባሉ። መንግስት ሃይል ካልተጠቀመ ሐገር ያስተዳደረ አይመስለውም። ይህ ዋጋ ሲያስከፍለን ኖሯል።
የጤና ባለሞያዎች የመብት ጥያቄ አንስተዋል። ጥያቄያቸው እጅግ ተገቢ ነው። ተገቢ ብቻ ሳይሆን እስከአሁን አለመመለሱ እንደ ሐገር ያሳፍራል። ሐኪሞች ተገቢ ጥያቄ በማንሳት ብቻ አልተገደቡም። ጥያቄያቸውን ያቀረቡበት መንገድ ስልጡን ነው። ይህ ብዙ ያስተምራል።
ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ፥ በብዙ የሚያስፈልገን ባህል ነው። ሃኪሞች የተከተሉት መንገድ አረዓያነት ያለው በመሆኑ የተነሳ ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል።
ምክኒያት ሦስት፥
ከአጀንዳ ፖለቲካ ጋር ፀበኞች ነን። እንደ ህዝብ መሰረታዊ የሆኑ አጀንዳዎች ቢኖሩንም ትኩረታችን ሌላ ነው። በብሔር እና በሃይማኖት ተከፋፍለናል። ከጋራ ጉዳያችን ይልቅ ከፋፋይ ነገሮች ይስቡናል።
በቡድን መከፋፈላችን ሐገራዊ አንድነትን ጭምር ለአደጋ የሚዳርግ ሆኗል።
ዶክተሮች ድጋሚ አርዓያ ሆነውናል።
ብሔር ዘለል መተባበር ፥ ሃይማኖት ተሻጋሪ ግኑኝነት ማድረግ እንደሚቻል አሳይተውናል። የጋራ አጀንዳን በሃይማኖት አሊያም በብሔር ሳይከፋፈሉ ማቅረብ እንደሚቻል አስተምረውናል።
ፖለቲካችን አጀንዳ ተኮር እንዲሆን ፥ የመብት ጥያቄዎቻችንም በመተባበር መከወን እንደሚችል ላሳዩት አረዓነት ሲባል ሊደገፉ ይገባል።
ምክኒያት አራት፥
"ትውልዱ ሐገሩን አይወድም" የሚል ወቀሳ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ይሰነዘራል። ሐገር መውደድ የፖሊሲ ውጤት ጭምር ነው።
ዜጋ ሐገሩን እንዲጠላ ከሚያደርጉት የተለያዩ ምክኒያቶች መካከል አንዱ በሐገር የመገፋት ስሜት ነው። "ያገለገልኳት ሐገር ገፍታኛለች" ብሎ የሚያስብ ሰው በልቡ ጥላቻ ሊወለድበት ይችላል። በእርግጥ አንዳንድ ሰው ሐገር እና መንግስትን ለዩ የሚል ክርክር እንደሚገጥም ይገባኛል። ነገር ግን ይህ ንግግር መሬት ላይ ያለውን እውነታ አይቀይረውም።
ሰዎች በአገዛዝ ሲበደሉ ፥ ሐገር አገልግለው ሲያበቁ ተገቢውን ክብር ሳያገኙ ሲቀሩ ለሐገራቸው ያላቸው ፍቅር ይሸረሸራል። ይባስ ብሎ ለሌላው መጥፎ ምሳሌ ይሆናል። ሌሎች ሰዎች ጭምር "ሐገራችንን ብናገለግል አንመሰገንም" የሚል አደገኛ ስሜት ይፈጥርባቸዋል። ይህ ስሜት ሲጎለብት የገዛ ሐገራቸውን የሚመዘብሩ ፥ ለወገናቸው ርህራሄ የሌላቸው ሰዎች ይበዛሉ። ይህ ምን እንደሚያስከትል ማብራራት አይጠበቅብኝም።
ለሃኪሞች ጥያቄ ተገቢውን ድጋፍ ለመስጠት ከምንገደድበት ምክኒያቶች መካከል አንዱ ብሔራዊ ስሜትን መጠበቅ ነው። ሃኪሞች ለህዝብ ላደረጉት አገልግሎት የሚመጥን ክፍያ ይሰጣቸው ማለት ዜጎች የሐገር ፍቅር ስሜታቸው እንዳይሸረሸር መታገል ጭምር ነው።
ምክኒያት አምስት፥
የነገ መብታችን በዛሬው የሃኪሞች ጥያቄ ውስጥ ተሸሽጓል። ዛሬ የጤና ባለሞያዎች ያቀረቡትን ተገቢ ጥያቄ መንግስት በሃይል ሊደፈጥጠው ይችላል። "ዶክተሮች እንደጀመሩት እነሱው ይወጡት" ብለን ዝም ብንል እና ጥያቄው በመንግሥት ቢደፈጠጥ የነገ እጣፈንታችን ለከፋ አደጋ ይጋለጣል።
ነገም በተራችን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ብናነሳ የድፍጠጣ ትምህርት ይሆናል። "ትላንት ዶክተሮችን እንደደፈጠጥኩት ዛሬም ሌላውን እደፈጥጣለሁ" የሚል መንግስታዊ ትምክህት ይፈጠራል።
ይህ ነገረ ረዘመ፥ እዚህጋ እናብቃ።
ከጤና ባለሞያች ጥያቄ ጋር መተባበር የውዴታ ግዴታችን ነው!
@Tfanos | 10 217 |
10 | “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!”
#repost
ከአሌክስ አብርሀም
መፅሀፍ-አልተዘዋወረችም
በአገራችን ባህል የዝምታ ትርጉም ግራ የገባው ነው፡፡ እውነት በአደባባይ ሲደፈጠጥ እያዩ አፍን መሸበብ፤ ግን ደግሞ በስሚ ስሚ ለመጣ አሉባልታ ነፍስን ጭምር መስጠት። ጮኾ የማያወራ፣ ሐሳቡን የማይገልጽ ሕዝብ የሐሜት ጫካ ነው። በየጋራና ሸንተረሩ ጥይት ከማስጮኸ የበለጠ፣ ጮኽ ብሎ ያመኑበትን መናገር የሚከብደው ሕዝብ ጀግንነቱ ከባድ ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ በዝም አይነቅዝም ብሒል የነቀዘ ሕይወት እንመራ ዘንድ የፈቀድን ሕዝቦች መሆናችን ሳያንስ ይኽንንም ባህል አድርገን ልንኮራበት ይዳዳናል፡፡
ይኼ ተወልጄ ያደግሁበት ሕዝብ በሹክሹክታ ያወራል፣ ጓዳ ለጓዳ ያወራል፣ እውነት ይሁን ውሸት አግበስብሶ ያወራል፣ እንደ ወረርሽኝ ወሬ በብርሃን ፍጥነት ያዛምታል፣ በአደባባይ ግን ዝምተኛን ያደንቃል- ያበረታታል፡፡ በተረቱ “ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም” እያለ ዝንብ ፈርቶ ዝም (እንዴት _ ለዝንብ ዝም ይባላል? ለምን ሰፈራችሁን አጽድታችሁ እንደልባችሁ አታወሩም? የሚል የማሪያም ጠላት ነው!) መንግሥትን ፈርቶ ዝም (እንዴት ዝም በሉ ለሚል መንግሥት ዝም ይባላል አፋኝ መንግሥት እጁን ከአፋችን ላይ እንዲያነሳ መንገር የለብንም ወይ? የሚል የአገር ጠላት ነው) ይሉኝታን ፈርቶ ዝም (እንዴት በይሉኝታ እንለቅ? ብንል የባህል ጠላት መባል ይመጣል፡፡)
ሁሉም ስሕተትና ፍርኃታችን እንደ ትልቅ ሐብት በእሳት ሰይፍ ተከቦ የሚጠበቅ ቅርስ ነው፤ እውነት ብቻ ነው ራቁት፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም እውነት የእብዶችና ሰካራሞች ልፈፋ ተደርጋ በየመድረኩ የምትሳለው፡፡ እብዶች እውነቱን እንዲናገሩለት “ጤነኛው' ከፍሎ ይታደማል፡፡ ይኼ ባህላችን ሲሆን ከያኒ የነፍሱን ጥሪ ጥሎ የጅሎች አፈቀላጤ ይሆናል፡፡ ታዲያ የዚህ ሁሉ ምክንያት ፍርኃታችን ቢሆንም፣ ይኼንንም በሰበብ ስንጀቡነው (መቼም ሰበብ አናጣ) “ዝምታችን ትዕግስት የወለደው፤ ትዕግስታችንም አምላካችንን የምንፈራ ሕዝቦች ስለሆንን የተጎናጸፍነው ጸጋ ነው” እንላለን፡፡ እውነታው ግን አምላክን መፍራታችን ሳይሆን ፍርኃትን ማምለካችን ነው።
በዚህ ሁሉ ዝምታ ውስጥ የታቀፈ ጅልነት ድርጊት ሆኖ ሲፈለፈል ከግለሰብ እስከ አገር ስንት የጨነገፈ ኑሮ ፈጠረ!? ታዲያ የራሳችን ዝምታ ተጠራቅሞ ሲከብደንና አላራምድ ሲለን፤ በየዘመኑ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቅን በጋራ እንጮኻለን። የጨረባ ተዝካር! ይኼን ዓይነቱን ጩኸት አብዮት እንለዋለን (የታዘዙትን ሁሉ እሺ! እያሉ አብዮት አለ ወይ?!) ነገሩ ልክ ውሃ ውስጥ የተነከረ ውሻ፣ ውሃውን ከላዩ ላይ ለማራገፍ በደመነፍስ እንደሚርገፈገፈው ዓይነት ነው፤ ውሃው ቢራገፍም ውሻው ያው ውሻ ነው፡፡ አጯጯኻችን በአንድ ላይ በየአፋችን ስለሆነ ማንም ማንንም አይሰማም፤ ማንም የማይሰማው ጩኸት ደግሞ ከዝምታ እኩል ነው፡፡
ይኼ ዝምታ፣ የጅል ባንዲራ እንጂ ጨዋነት አይደለም። ባንዲራችን ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ለዘመናት በተከመረና በደደረ ጅልነታችን ላይ ይመስለኛል፡፡ የባንዲራችንን ቀለም እየጠቀስን የማንሰጠው ትርጉም የለም። ሁሉንም ቀለም እንደ ዳማከሴ ጨቅጭቀን ብንጨምቀው ከጀግንነታችንም በፊት፣ ከኩሩነታችንም በፊት፣ከአገር ፍቅራችንም በፊት የሚንጠባጠበው ጅልነታችን ሳይሆን ይቀራል?!
እሱን እየተቀባን ስንት ጊዜ ከዘመን በሽታ ተፈወስን ብለናል?! ፈውሳችን ሐሰት ነበርና ምስክርነታችን የታተመበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ብዙዎች በነጠላም በጅምላም የጅል በትር ሰለባ ሆነው ወደ መቃብር ወርደዋል፡፡
የተረፍነው እንዴት ተረፍን? እያልኩ ሳስብ፣ አንዳንዶች “ምሕረቱ በዝቶልን'' ቢሉም እኔ ግን ፈጣሪም ከዚህች ከኛ ምድር በተዋሰው ተረት “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!” ብሎ ለአጫዋችነት ትቶን ይሆናል እላለሁ፡፡ አገሬ ጨዋታና ተጨዋች ይበዛታል፡፡ እንደ አገር ልጅነታችንን አልጨረስንም ይሆን? እስከምል ድረስ የአገሬ ጨዋታ ወዳድነት ያስደምመኛል፡፡
ጅልነቴ ከሕዝብ ባሕር የተቀዳ ነው ስል፣ ለጥፋቴ ሌላ የሕዝብ ክንብንብ ውስጥ መደበቄ አይደለም፤ ምንስ ቢሆን ሕዝብ የሚባለው አጀብ ለሚሊዮኖች ቢሰነጣጠር አንዱ ስንጣሪ መሆኔ አይቀር፡፡ ሕዝባዊ ጀግንነት፤ ሕዝባዊ ታሪክ እንዳለ ሁሉ ከየቤታችን አዋጥተን አገራዊ ያደረግነው ሕዝባዊ ጅልነት አለመኖሩን ማን አጥንቶ ነገረን?! ጅልነት ቀለም ነው፤ ታሪካችን እኛም በግልና በጅምላ አማርን ብለን የተቀባነው የተኳኳልነዉ ጠይም ቀለም፡፡
@enlighten_ethiopia | 10 524 |
11 | ዳግም ውልደት
ንስር 40 አመት ሲሞላው የህይወት ወይም የሞት ምርጫ ይገጥመዋል ይህም የሚሆነው ማንቁሩ በጣም በመርዘሙና በመጣመሙ ማደንም ሆነ መመገብ ባለመቻሉ ነው።
በተጨማሪም የደረት እና የክንፍ ላባዎቹ በጣም በመክበዳቼው ለመብረር የማይቻል ያደርጉታል፡፡ ስለዚህ አሁን ንስሩ ሁለት አማራጭ ብቻ ነው ያለው "መሞት"... ወይም ረጅምና አሳማሚ ለውጥን መታገስ ፡፡በመቀጠል ወደ ተራራው ጫፍ ይሄድና የጭካኔው ወይም የዳግም ውልደት ሂደት ይጀምራል ይህም የሚሆነው ማንቁሩ እስኪሰበር ድረስ ድንጋይ ላይ ይፈጠፈጣል።
ከዚያም ይጠብቃል ቀስ በቀስ እያመመው አዲስ ማንቁር ይበቅላል እንደ አዲስ የድሮ ማንቁር ያወጣል እናም አንድ በአንድ ንስሩ ከባዱን ላባ ከደረቱ እና ከክንፉ ለማውጣት ይጠቀምባቸዋል።
ከ150 ቀናት ትግል፣ ህመም፣ዝምታና መገለል በኋላ ሂደቱ ሲያልቅ እንደገና ይበራል።ዳግም ንቁና ጠንካራ ኾኖም ይወለዳል። እናም... ለተጨማሪ 30 ዓመታት ይኖራል ፡፡
አንዳንዴ የእውነት ለመኖር መለወጥ አለብን ለውጥ የሚመጣው ከፍርሃት፣ አለመመቸትና የልብ ስብራትም ጭምር ነው።
ነገር ግን ከዚህ በኋላ የማያገለግለንን ነገር ላይ አንጣበቅ የድሮ ልማድ፣ ስንፍና፣ጊዜው ያለፈባቸው እምነቶች . . .
ያለፈውን ቀንበር ስናስለቅቅ ብቻ ነው ወደ ፊት ከፍ ማለት የምንችለው።
የለውጥ ህመም እውነት ነው — የዳግም ልደት ሃይል !
@enlighten_ethiopia | 10 486 |
12 | ጥቂቶች...
___
"The axe forgets, but the tree remembers." – African Proverb
___
በታሪክም ሆነ በዕለታዊ የሰው ልጆች መስተጋብር ውስጥ ሁሌም ቢሆን የኑሮን ሸክም የሚሸከሙት፣ የብዙኃኑን ሕማም የሚታመሙት፣ በቅንዋቱ የሚቸነከሩት ጥቂቶች ናቸው...
ጥቂቶች ለጨለማችን ብርሃን ይሆናሉ... ጥቂቶች ለድካማችን ብርታት ይፈጥራሉ... ጥቂቶች ድልድይ ገንብተው ያሻግራሉ...
ምናልባት ስማቸው ተረስቶ ይሆናል... ምናልባት እጃቸው በጉልህ አይታይ ይሆናል... የተግባራቸው ፍሬ ግን በእያንዳንዱ ምቾታችን ውስጥ ይፈሳል... ፈር ቀዳጅ ጥንስሳቸው በየግኝቶቹ መሰረት ስር ይቆማል... የድካማቸው አሻራ በምናጣጥመው መልካም አጋጣሚ ውስጥ ሁሉ ይናኛል...
እኒህ ጥቂቶች ለተግባራቸው ግዴታ የለባቸውም... ተቆጣጣሪና ተቆጭ አያውቁም... ከሚጠበቅባቸው በላይ ቢያበረክቱም የሚያደርጉት ስለ ፍቅር ነው... ድንቅ የሚባል ተግባር ቢፈጽሙም የሚበረቱት ስለ ሰው ልጅ ነው... ስለ ጭብጨባ አይበረቱም... በሙገሳ አዳራሽ አይከሰቱም... ዘመን ሲያጋድል አይነጥፉም... ለነፍስ ተልዕኮዋቸው ታማኝ ናቸው... ተመልካች በሌለበት ጊዜ ብርቱ፣ አይዞህ ባይ ሳይኖር ታታሪ ናቸው...
[Real change is not about being seen; it's about seeing what needs to be done and doing it anyway.]
በእንቅልፋም ዓለም ውስጥ ማልደው ይነሳሉ... በጸጥታ ሆነው ተግባራቸውን ይከውናሉ... እኒህ ጥቂቶች በዝንጋኤ የተውናቸውን ጥያቄዎች የሚያነሱልን አሳቢያን ናቸው... እኒህ ጥቂቶች በከፉ ሁኔታዎች ውስጥ በጽናት የሚቆሙልን ሰራተኞች ናቸው... እኒህ ጥቂቶች አንተኛም ያሉ አላሚያን ናቸው... ለልባቸው ሃቂቃ እንጂ ለውጫዊው እውቅና የማይሽቀዳደሙ ታታሪ ናቸው... ለነፍሳቸው ጥሪ የማያወላውሉ ወታደሮች ናቸው...
ስጦታቸው ከላብ የተላቆጠ ንዑድ ነው - ተራ ስጦታ አይደለም... አበርክቶአቸው ከደም የተለወሰ ክቡር ነው - የይምሰል አይደለም... ሲሰጡ ከራሳቸው የተከፈለውን በልግስና ይሰጣሉ... ሲቸሩ ድንበሩ ሳይፈጥሩ ይቸራሉ...
[You give but little when you give of your possessions. It is when you give of yourself that you truly give. ~ Kahlil Gibran]
እኒህ ጥቂቶች ራሳቸው ይተክላሉ፣ ራሳቸው የአትክልት ቦታውን ይንከባከባሉ፣ ራሳቸው ምርትና ገለባውን ለይተው ከማዕድ ላይ ያኖራሉ... ሲሰሩ ተመልካች ሽተው - ሲከውኑ አድናቂ ማትረው አያውቁም...
ከመኖራቸው ብታተርፍም ዓለም አጀንዳ አድርጋቸው አታውቅም... ልዩነት ፈጣሪ ቢሆኑም ከአደባባይ ሲጎሉ አይታይም... በጸጥታ መሰረት ይጥላሉ... በዝምታ ይገነባሉ... በአርምሞ ዓለምን ይለውጣሉ...
እኒህ ጥቂቶች የፈውስ ምክንያት ናቸው... እኒህ ጥቂቶች ችግር ፈቺ ናቸው... እኒህ ጥቂቶች የፈጠራ ባለሙያ ናቸው...
እኒህ ጥቂቶች ለተሰማሩበት መስክ የታመኑ፣ ለተሰጣቸው አደራ በእምነት የቆሙ ናቸው... ዋጋቸውን የሚያሰሉት በአስተዋጽዎው ልክ ነው... ክፍያቸውን የሚጠብቁት ከደካሞች ፈገግታ ነው... ከስቁይ ኑረታቸው የሚስቁ ልቦች መወለድ ድካማቸውን ያስረሳቸዋል...
“Don’t get lost in your pain, know that one day your pain will become your cure.” ~ Rumi
ሰዓት የማይቆጥሩ - በድካም የማይታክቱ ነርሶች፣ በሕማም ውስጥ ሆነው ውበት የሚወልዱ አርቲስቶች፣ የተማሪዎቻቸውን መድረሻ ከማለዳ የሚተልሙ መምህራን፣ ከስኬቱ በፊት ሺህ ጊዜ ለመውደቅ ያላመነታ ሳይንቲስት...
እና ደግሞ ስም የለሾች...
[ብዙ፣ በጣም ብዙ፣ ብዙ ጥቂቶች...]
___
ምስጋና ለእኒህ ጥቂት እጆች ይሁን!!...
___
"He who plants trees, knowing he will never sit in their shade, has at least started to understand the meaning of life." – Indian Proverb
___
@bridgethoughts | 8 752 |
Boshqa reja tanlang
Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.