cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ቢቢሲ አማርኛ

@desalegntemesgen.com

Більше
Ефіопія6 193Амхарська5 824Категорія не вказана
Рекламні дописи
786
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступне
Фото недоступне
ሰላም የፀደይ ኒውስ ቤተሰቦች✋ ፀደይ ኒውስ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች በማጠናቀር ወደ እናንተ ወድ ቤተሰቦቹ የሚያቀርብ ምርጥ እና አማራጭ የዜና ቻናል ነው። በቻናላችን:- 1. የሀገር ውስጥ ዜናዎች 2. የውጪ ዜናዎች 3. ትምህርት ነክ መረጃዎች 4. የጤና መረጃዎች 5. የስራ ማስታዎቂያዎች 6. አስተማሪ፣ አዝናኝ እና ቁምነገር ያላቸው ዝግጅቶችን የምናቀርብ ይሆናል። እናንተም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በተለያዩ መድረኮች በመሳተፍ፣ ኮሜንት ላይ ሀሳብ አስተያየት በመስጠት፣ ዜናዎቻችንን ሼር በማድረግ እና ሌሎችን በመጋበዝ በንቁ እንድትሳተፉ እንጠይቃለን። ---ፀደይ ኒውስ - Tsedey News--- "ተመራጭና ተአማኒ የመረጃ ምንጭ"       "T.me/tsedeynews"
Показати все...
Фото недоступне
የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ በሥራ ላይ እንዲውል ተወሰነ‼️ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎች በሕገወጥ መንገድ ይፋ እንዳይሆኑ፣ እንዳይጠፉ፣ እንዳይለወጡ እና እንዳይተላለፉ ለመጠበቅ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን በማስተዳደር እና ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት፣ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያየ መልኩ መረጃው ተደራሽ የሆነላቸው አካላት መብትና ግዴታዎች በግልፅ መደንገግ በማስፈለጉ፤ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴዎች ለመለዋወጥ የተዘረጋ ስርዓት ባለመኖሩ በየደረጃ ያሉት የመንግሥት አመራሮች እና ሰራተኞች እራሳቸው በመረጡትና ደህንነታቸው ባልተረጋገጠ መረጃ መለዋወጫ ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙ በመሆኑ የአገሪቱን ደህንነትና ሉዓላዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ እንዳይሆን መከላከል በማስፈለጉ፤ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመደብ የሚያስችል ግልፅ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሠራር ስርዓት መዘርጋት እንዲሁም መረጃዎቹ በህገወጥ መንገድ ይፋ እንዳይሆኑ፣ እንዳይጠፉ፣ እንዳይለወጡ እና እንዳይተላለፉ ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ ---ፀደይ ኒውስ - Tsedey News--       "T.me/tsedeynews"
Показати все...
ለልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት የተላከን ዱቄት ሸጠው ለግላቸው ጥቅም ያዋሉ የጎንደር ከተማ የሥራ ሃላፊዎች በጽኑ እሰራት ተቀጡ ለአማራ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ኃይል ፓሊስ አባላት የተላከን ዱቄት ሸጠው ለግላቸው ጥቅማቸው ያዋሉ የጎንደር ከተማ የሥራ ሃላፊዎች በጽኑ እሰራት መቀጣታቸው ተገለጸ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ሀይል ፓሊስ መምርያ የሚኒሊክ ክፍለጦር የሎጀስቲክ ኃላፊ የሆነው 1ኛ/ተከሳሽ ኮማንደር ኡስማን መሐመድ፤ ለልዩ ኃይል ፓሊስ አባላት አገልግሎት የሚውል 199 ኩንታል  “የፊኖ ዱቄት” ከፓሊስ ኮሚሽን ከልዩ ሀይል መምርያ ዘርፍ ይረከባል፡፡ ከዚህም ውስጥ 129 ኩንታል ዱቄት በሲኖትራክ የጭነት መኪና በመጫን፤ ጭልጋ ሰራባ ልዩ ኃይል ካንፕ ማድረስ ሲገባው፤ መስከረም 25/2015 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ከተጫነው ዱቄት ውስጥ 80 ኩንታል ለአንዱ ኩንታል 4 ሺሕ አምስት መቶ ብር በመተመን፤ 80 ኩንታሉን በጎንደር ከተማ ለሚገኘው ለሐሮን ዳቦ ቤት በ360 ሺሕ ብር መሸጡ ተገልጿል። ከኮማንደሩ በተጨማሪም፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምርያ የ3ኛ ፓሊስ ጣቢያ ትራፊክ ፓሊስ ሆኖ የሚሰራ ዋና ሳጅን እንድሪስ ሐሰን ወንጀልን የመከላከል ኃላፊነት እያለበት ከሕዝብና ከመንግሥት የተሰጠውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው የዳቦ ቤቱን ባለሀብት ሻጭ እና ገዥን በስልክ ያገናኘ እና ያስማማ በመሆኑ ወንጀለኛ ተደርጓል። በዚህም የመንግሥት ንብረት የሆነው የዳቦ ዱቄት እየተራግፉ ባሉበት በአካባቢው በነበሩ የጸጥታ ሃይሎች እጅ ከፈንጅ መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምርያ የሙስና ነክ ወንጀሎች ምርመራ ዋና ክፍል እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የሥራ ሒደት በጋራ በተቋቋመ የምርመራ ቡድን ምርመራው ተጣርቶ ለዞኑ ፍትህ መምርያ መላኩ ተገልጿል። የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ በ10 የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አስደግፎ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ለ/33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 31/2/ስር የተመለከተውን የመሰረተ ሲሆን፤ ክሱንም ለማዓከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል። ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ ሰኔ 15 /2015 በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው፤ አንደኛ ተከሳሽ ኮማንደር ኡስማን መሐመድ በአምስት ዓመት ጽኑ እሰራትና በ3 ሺሕ ብር፤ ዋና ሳጅን እንድሪስ ሐሰን በሦስት ዓመት ከሦስት ወር ጽኑ እስራትና በኹለት ሺሕ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን ገልጿል። t.me/TsedeyNews t.me/TsedeyNews
Показати все...
👍 1
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ፣ “ነብዩ መሐመድን ተሳድቧል” የተባለ ግለሰብ፣ በድንጋይ ተወግሮ እንደተገደለ፣ ባለሥልጣናት እና የመብት ተሟጋች ቡድኖች አስታወቁ። ድርጊቱ፥ በአካባቢው የሃይማኖት ነፃነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፤ ያሉት የመብት ተሟጋቾቹ፣ ጉዳዩ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል። ኡስማን ቡዳ የተባለው ሟቹ ሉካንዳ ነጋዴ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ፣ በሶኮቶ ግዛት ጉዋንዱ ወረዳ የተገደለው፣ በገበያ ሥፍራ ከሌላ ነጋዴ ጋራ ሲከራከሩ፣ “ነብዩ መሐመድን ተሳድቧል፤” በሚል እንደሆነ፣ የፖሊስ ቃል አቀባይ አሕመድ ሩፋ፣ በአወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ከግድያው ስፍራ የተወሰዱና ነዋሪዎች ያጋሯቸው የቪዲዮ ምስሎች፣ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው፣ መሬት ላይ የወደቀውን ኡስማን ቡዳን ሲራገሙ እና ድንጋይ ሲወረውሩበት ያሳያሉ። የፖሊስ ቃል አቀባዩ ስለጉዳዩ ሲያብራሩ፣ በሥፍራው የፖሊስ ኃይል ሲደርስ፣ “ሕዝቡ ተበትኖ፣ ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ ራሱን ስቶ” እንዳገኘው ገልጸው፣ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሕይወቱ እንዳለፈ አብራርተዋል። በአብዛኛው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሚበዙበት ሰሜናዊ ናይጄሪያ የተፈጸመው ይኸው የደቦ ግድያ፣ የእምነት ነፃነትን አደጋ ላይ ይጥላል፤ በማለት፣ የመብት ተሟጋቾች ድምፃቸው እያሰሙ ነው። ናይጄሪያ የሚገኘው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ “መንግሥት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት አልሰጠም፤” ብሎ በመክሠሥ ባወጣው መግለጫ፣ እንደዚኽ ዐይነት ግድያዎች፣ ፍትሕ ሳያገኙ ከቀሩ፣ ሕግ ፊት ሳይቀርቡ በመንጋ የሚፈጸሙ ግድያዎችን ያበረታታል፤ ብሏል።
Показати все...
  • Файл недоступний
  • Файл недоступний
  • Файл недоступний
  • Файл недоступний
  • Файл недоступний
ሰመመን - ክፍል 1 ❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥 ━━━━━━━━ ከ ጸጋዬ አብራር ━━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦⇨ @Ethio_Tereka@Ethio_Tereka ━━━━✦✗✦━━━━
Показати все...
ጀርመን የሩሲያ ባለስልጣናትን "በጅምላ" ለማባረር መወሰኗን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ገለፁ። ዛሬ ከሞስኮ ሆነው ይህንን የገለፁት ዛካሮቫ ሩሲያ አፀፋዋን እንደምትመልስ አክለው ገልፀዋል። በዚህም መሠረት ከ 20 በላይ የጀርመን ባለስልጣናት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይደረጋል።ሞስኮ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ስለ ጉዳዩ በጎርጎሮሲያኑ ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ተነግሮታልም ተብሏል። ባልስልጣናቱ ሀገር ለቀው ይሁን አይሁን ግን ግልፅ እንዳልሆነ የጀርመን ዜና ምንጭ ዲፒኤ ዘግቧል። ጀርመን እና ሩሲያ በየፊናቸው ከዚህ ቀደምም ባለስልጣናት ተወካዮቻቸውን ያባረሩ ሲሆን ውጥረቱ ሩሲያ ዩክሬይንን ከወረረች በኋላ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ጠዋት አንድ የሩሲያ የመንግሥት አይሮፕላን በርሊን እንዲያርፍ ልዩ ፍቃድ አግኝቷል። ሩሲያ ላይ በተጣለው ማዕቀብ የተነሳ በአውሮፓ ህብረት እና በሩሲያ መካከል ያለው የአየር ክልል አሁንም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት እንደተዘጋ ነው። አይሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሩሲያ ተመድበው የነበሩ የጀርመን ባለስልጣናት ይሁኑ አይሁኑ እስካሁን ይፋ አልሆነም።
Показати все...
👍 2
ጃፓን ወታደሮቿ የሰሜን ኮሪያን የባልስቲክ ሚሳይልን መትተው ለመጣል ዝግጁ እንዲሆኑ አዘዘች። ጃፓን ይህን ያዘዘችው ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ የስለላ ሳተላይት ለማምጠቅ ዝግጁ መሆኗን ከገለጸች በኋላ ነው ተብሏል። የጃፓን የመከላከያ ሚኒስትር ዛሬ ባስተላለፉት ትዕዛዝ የሰሜን ኮሪያ የባልስቲክ ሚሳኤል አደጋን ለመቀነስና ለማክሸፍ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ወታደሮቻቸው እንዲዘጋጁ አስጠንቅቀዋል ሲል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት ሰሜን ኮርያ የመጀመሪያዋን አህጉር አቋራጭ የባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አከናውናለች። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቀኑን ሳይጠቅሱ የመጀመሪያው ወታደራዊ ሰላይ ሳተላይት በታቀደበት ጊዜ ወደ ህዋ እንደሚልኩ ተናግረዋል። እያደገ የመጣውን የሰሜን ኮሪያ የሚሳይል ስጋት በተሻለ ብቃት ለመከላከል በሚል ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የሚሳይል ጥቃት የመከላከል ልምምድ እንዲሁ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ማካሄዳቸው ይታወሳል። የሦስቱ ሃገራት ወታደራዊ ትብብር የሚቀጥለው ሳምንትም መቀጠሉን ተንተርሶ ሰሜን ኮርያ በበኩሏ ቀጣይ ሙከራዎችን እንደምታካሄድ ይጠበቃል።
Показати все...
የዎላይታ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በአጭሩ (ዎሕነን) የተሰኘ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ዛሬ ወላይታ ሶዶ ውስጥ ተመሠረተ። ንቅናቄው በፓርቲ ደረጃ እንዲመሰረት ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባገኘው ጊዜያዊ የምስረታ ፍቃድ መሠረት ላለፉት ሶስት ወራት ሲሰራ እንደነበር ዛሬ በምስረታ ጉባኤው ላይ ተገልጿል። ከንቅናቄው ስራ አስፈፃሚዎች አንዱ የሆኑት አቶ አማኑኤል በላቸው ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት የንቅናቄው ዋንኛ አጀንዳ የወላይታን ሕዝብ መብት እና እኩልነት በኢትዮጵያ ማስከበር ነው። የዎላይታ ሕዝብ የራስ በራስ አስተዳደር ለመመሥረት ያነሳው ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ፓርቲው በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገል አክለው የገለፁት አቶ አማኑኤል የፖርቲው ስያሜ ብሔር ተኮር መሆኑ እና በሀገራዊ ፓርቲነት መሰየሙ «ምንም ግጭት አይፈጥርም» ሲሉ ለሐዋሳው የዶይቸ ቬለ ወኪል ሸዋንግዛው ወጋየሁ ገልፀዋል።
Показати все...
ከ1000 በላይ ሰዎችን አሳፍራ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሰመጠች አንዲት የጃፓን መርከብ በፊሊፒንስ የባህር ዳርቻ ተገኘች። ፍለጋውን ያካሄዱ የጥልቅ ባህር ተመራማሪዎች እንደገለፁት የመርከቧ ፍርስራሽን ከ4000 ሜትር ጥልቀት በኋላ በደቡብ ቻይና ባህር ውስጥ ለማየት ችለዋል። ፍለጋው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ከተጀመረ 12 ቀናት በኋላ መርከቢቱ መገኘቷን በተልዕኮው የተሳተፈ «ሳይለንት ወርልድ ፋውንዴሽን» የተባለ የአውስትራሊያ ድርጅት ዛሬ አስታውቋል። «ሞንቴቪዲዮ ማሩ» የሚል መጠሪያ የነበራት መርከብ እጎአ ሀምሌ 1 ቀን 1942 ዓ.ም የሰመጠችው በዩናይትድ ስቴትስ ሰርጓጅ መርከብ ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ነው። 1060 ገደማ ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር የሚነገረው ይህቺው መርከብ ከዚያን ጊዜ በኋላ የደረሰችበት አይታወቅም ነበር። አብዛኛዎቹ ሰዎች በጃፓን ቁጥጥር ስር የዋሉ የአውስትራሊያ የጦር እስረኞች የነበሩ ሲሆን በጠቅላላው የ 14 ሀገራት ዜጎች በመርከቧ ላይ ይገኙ እንደነበር እና እድሜያቸውም ከ 15 እስከ 60 እንደሚደርስ ተዘግቧል። ለሟች ቤተሰቦች ክብር በሚል መርከቢቱ ሰምጣ ከተገኘችበት ቦታ በስተቀር ከሰው ቅሪት ምንም የተወሰደም ይሁን በቪዲዮ የተቀረፀ ነገር እንደሌለ የጀርመን ዜና አገልግሎት አክሎ ዘግቧል።
Показати все...