🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷
ጨረቃ 🌕 ጨረቃዋ ሆና የልቤ ጓደኛ እጠብቃታለሁ እንቅልፌን ሳልተኛ ደሞ ነግራታለሁ አንደናፈቀቺኝ አዘነች መሰለኝ አቀርቅራ አየቺኝ ቀና ብዬ አይቻት ስላንቺ ነገርኳት ተከፍች መሰለኝ አንባ አመለጣት አይ የኔ ጨረቃ የዋህ ደግ እኳ ናት For any Promotion DM 👇👇 ☎️ = +251931374891 📩 = t.me/Abate_Hiwote = t.me/Abenag
Показати більше📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу 🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷
Канал 🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷 у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 216 790 підписників, посідаючи 96 місце в категорії Релігія і духовність та 70 місце у регіоні Ефіопія.
📊 Показники аудиторії та динаміка
З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 216 790 підписників.
За останніми даними від 05 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -6 535, а за останні 24 години на -313, загальне охоплення залишається високим.
- Статус верифікації: Не верифікований
- Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 0.34%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 0.80% реакцій від загальної кількості підписників.
- Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 745 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 744 переглядів.
- Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 18.
📝 Опис та контентна політика
Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“ጨረቃ 🌕
ጨረቃዋ ሆና የልቤ ጓደኛ
እጠብቃታለሁ እንቅልፌን ሳልተኛ
ደሞ ነግራታለሁ አንደናፈቀቺኝ
አዘነች መሰለኝ አቀርቅራ አየቺኝ
ቀና ብዬ አይቻት
ስላንቺ ነገርኳት
ተከፍች መሰለኝ አንባ አመለጣት
አይ የኔ ጨረቃ የዋህ ደግ እኳ ናት
For any Promotion DM
👇👇
☎️ = +251931374891
📩 = t.me/Abate_Hiwote
= t.me/Abenag”
Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 06 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.
Триває завантаження даних...
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 06 червня | 0 | |||
| 05 червня | 0 | |||
| 04 червня | 0 | |||
| 03 червня | 0 | |||
| 02 червня | 0 | |||
| 01 червня | 0 |
| 2 | ፍቅር እና ፊልም
እውነተኛ ታሪክ
የመጨረሻው ክፍል 3
ልጁ ብቸኝነት ያጠቃው አይነት ስለሆነ ከፓርቲው ውስጥ ያለው ጫጫታና የሰው ጋጋታፈሪ አድርጎታል ። እሷም እጁን ይዛው ከፊት ሆና ትመራዋለችና ወደ ቤቱ ገቡ ። እንደገቡም ሰላም ከተባባሉ በኋላ ፓርቲው ውስጥ የነበሩት ጓደኞቿ ከሷ ጋር ትንሽ ማውጋት ፈልገው ነበርና ነገርግን እሷ ብቻውን ልተወው ስላልፈለገች ቶሎ ለመመለስ አስባ ልጁን ውስጥ አስቀምጣው ወጣችና ከጓደኞቿ ጋር ማውጋትን ጀመረች ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ጨዋታውን አቋርጣ ወደ ልጁ ልትመለስ አስባ " ቆይ ቆይ " ብለው ያዟትና ስለልጁ የሆነ ነገር ማወቅ ፈልገው ነበርና ጥያቄያቸውን ጀመሩ ። ያው በቀልድና በፉገራ ነበር የጀመሩት ነገር ግን ወዲያው አስቆመቻቸው
። " እረፉ በእሱ ቀልድ የለም " አለች ። የምሯን ነበር የተናገረችው ። አነሱ እንደሚያስቡት አይነት ልጅ እንዳልሆነና ከዛ ይልቅ ንፁህነቱንና የዋህነቱን ልትገልፅላቸው ሞከረች ። የሷን ያህል አልተረዱም ሆኖም ግን አፋቸውን አሽጋለች ። የልጁ ክብር እንዲነካ አልፈለገችም ። ማንም ሰው እንዲነካው ማትፈልግ ትመስላለች ። ከሆነማ ልጁ ከፈጣሪው ልዩ ስጦታ አገኘ ማለት ነው ። ጨዋታቸውን ጨርሰው ወደፓርቲው ቤት እየተመለሱ ቀድማ ከፊት ሆና የፓርቲውን ቤት መግቢያ በር የከፈተችው ልጅቷ ነበረች እና ድንገት ከውስጥ ያየችው ነገር ወዲያው ሁኔታዋን ቀያየረው ። ስትስቅ ነበር ግን አሁን በቅፅበት የንዴት ፊት ሆኖ ተቀየረ ። የፓርቲው ልጆች በሙሉ ክብ ሰርተው ጥጋቸውን ይዘዋል ነገር ግን አንድ ሰው በመሀላቸው ቆሞ መድረኩን ተቆጣጥሮታል ። በጉ ነው የተቆጣጠረው ። እነሱም ደስተኛ ነበሩ እሱም ደስተኛ ነበር ። ነገር ግን ሁኔታው የገባት ልጅ ጓደኛው እንዳየችው ጊዜ አላጠፋችምና በፍጥነት ወደውስጥ ገብታ ከዛ ከመድረኩ ውስጥ ጎትታ አስወጣቸው ። ሁኔታዋ የንዴት ነገር ስለሚመስል ልጁ ደንግጧል እናም ግራ ገብቶታል ። እጁን ይዛው ስትወጣ በመሀል ልጁ ጭራሽ መቆም አቅቶት አዙሮት ይወድቃል ነገር ግን ልጅቷ ደግፋው ስለነበር እየደገፈችው መቀመጫ ወዳለበት ቦታ ወስዳው ወደ ጥግ ቦታ አስቀመጠችው ። ወዲያው ውሀ ይዛለት መጥታ በእጇ አያስነካች ፊቱን መደባበስ ጀመረች ። ልጁ ተሽሎት ወደራሱ ተመለሰ ። ከዛም እሷ ቆማ ወደታች ታየዋለች እሱ ደግሞተቀምጦወደ ላይ ያያታል እና በውስጧ የነበረው ንዴትቁጣዋን አስነሳውና ልጁን መቆጣት ጀመረች ። እንዳጠፋ ፣ ለምን ይሄ ሁሉ እንደጠጣና ጭራሽ ማይችለው ዳንስ ውስጥ ለምን እንደገባ ጠየቀችው በንዴት ውስጥ እንዳለች ። ልጁ በድንጋጤና ሀዘን ፀጥ ብሏል ። " ይሄን ደሞ ምነግርህ ለራስህ ብዬ ነው እሺ !.........እሺ አሁን እንሂድ ! " ብላ ቀድማው እንደተነሳች " እኔም ላንቺ ብዬ ነው " ብሎ አስቆማት ። ንዴቷ አልበረደም ነበር ነገር ግን የልጁ ሁኔታና ንግግር ንዴቷን አረጋጋው ። ለሷ ብሎ ያ ሁሉ እንደጠጣና ዳንሱንም ለሷ ሲል ሲደንስ እንደነበር ፣ ጓደኛሽ መጠጥ አይጠጣምና ጓደኛሽ ዳንስ አይችልም ብለው እንዳይሰድቧት ብሎ አስቦ ነው እንደዛ ያደረገው ። ልጅቷ ንዴቷን ወደ ጓደኞቿ አዞረችው ። ልጁን ባለበት ትታው ወደጓደኞቿ ወደፓርቲው ትመለሳለች ። አናግራቸው በፍጥነት ከቤቱ እየወጣችሳለ አንዷ ጓደኛዋ ሁኔታዋ ገርሟት እየተከተለቻት አብራት ወጥታ " እና ለሱ ብለሽ ነው " ስትላት ልጅቷ በግትርነትና በንዴት ድምፅ ፊቷን አዙራው " አዎ ለሱ ብዬ ! " ትላታለች ። ታዳሚውም እነሱን ተከትለው ወጥተው የነሱን ሁኔታ በዝምታ መከታተል ይጀምራሉ ፣ በመሀከላቸው ለቅፅበት ያህል ፀጥታ ይሰፍናል ። ልጅቷ ለማስረዳት ሞክራ ግን ከንዴቷ አንፃር መናገር ስለከበዳት ትታቸው ነገርግን ልጁ እዛው ከተቀመጠበት እጁን ይዛው ተነሳች ። እናት ልጇን እንደምትይዘው አይነት ፤ እሷ ከፊት እሱ ከኋላ እጇን ይዞ እየተከተላት ከግቢው ተያይዘው እየወጡ ነው ። ታዳሚው እነሱን በአግራሞት ይመለከታል ። በሩን በሀይል ዘግታው ወጣች ከልጁ ጋር ። ልጁ ግን ታድሎ !
ብቻ አትጠይቁኝ ! ፊልሙን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ወደድኩት ። ያ የኔ ቢጤ መስሎ የሰራውን ተዋናይ አደነኩት ። ፊልሙ ስሜት ውስጥ ከቶኝ እንደነበር አስታውሳለሁ ። ልጁ ሲያለቅስ ሊያስለቅሰኝ ይሞክር ነበር ። ሲደሰትም እስቃለሁ ። ብዙ ነገር ሊመሳሰልብኝ ችሏልና ። ልጅቷን ብታዩዋት አዛኝ ትመስላለች ። ትወናዋን አሪፍ አርጋዋለች ። ውበቷስ ብትሉ !..........የምሬን ነው በጣም ታምራለች ። መልኳም ትወናዋም አንድ ላይ ሆኖ ትማርካለች ። እኔ አንድ ነገር ከተመቸኝ መደጋገም ፀባዬ ነው ። ግን " ሙድ አንዴ ነው " ስለሚባል በአራዶች ህግ እኔ ግን አራዳ መሆን አልቻልኩም ። " ሞኝና ወረቀት የያዙትን አይለቁም " አይነት ሆንኩ ። ፊልሙን መደጋገም ይዣለሁ ። ሞኝ ሆንኩ እንዴ..........እኔንጃ ግን ምንም ይሁን ምን ራሴን ሞኝ ብዬ ለመጥራት አልፈቅድም ፣ ነኝ ብዬም አላስብም ። ራስን እንደሞኝ ማሰብ ልክ ነው ብዬ አልገምትም ። ነገር ግን አንዴ አይቼ ገብቶኝ የጨረስኩትን ፊልም ለምን እደጋግመዋለሁ ? ለምሳሌ የሚያውቁት ወይም አንዴ የሰሙት ታሪክ ሲደጋገም መሰልቸቱ የማይቀር ነው ። እርግጥ ፊልሙን እንደመጀመሪያ ተመስጬ አላይም አሁን ፤ ምክንያቱም የታየ ስለሆነ ። ግን አንዳንድ ቦታ ላይ ሌላ ስሜት ውስጥ ይከተኛል አሁንም ። የሆነ ነገር ውስጤን ሰርስሮት የገባ ይመስለኛል ። የልጁ ሁኔታ ነው ?.........ብቻ ሁኔታዬ ተቀይሯል ። የሆነ ስሜት አለና ልቤ ውስጥ እንደሆነ አግኝቼዋለሁ ። ታዲያ ልቤ ምን ሆኖ ነው ? ፣ ምን ጎሎብኝ ?.............ከብቸኝነት ሌላ ስሜት ተደርቦ መጥቷል ብቻ ። ልቤ ውስጥ ነው ። ልቤ የሆነ ነገር ወዷል ። እና ፊልም ውስጥ ብዙ ነገር አለ እኮ.......... ፦ ታሪክ አለ ፣ ትወና አለ ፣ ተዋናዮቹም አሉ ። ብቻ ብዙ ነገር አለና ፊልሙ ውስጥ ሁሉን ነገር ነው የወደድኩት ። በተለይ በተለይ ተዋናይቷን ፦ ያቺ የወንደሰን ጓደኛ ፣ ምትንከባከበው ፣ ምትጠብቀው ፣ ምታዝንለት ፣ ምትወደው ወ.ዘ.ተ
አንድ ነገር ልንገራችሁ ፦ ፊልሙን እያየሁ ድንገት የሷን መልክ ሲያመጣው ልቤ በጣም SENSE አያረግም መሰላችሁ ። እኔንጃ ምን እንደሆነ። ብዙም ሳይቆይ ነው ልቤን ያገኘሁት ። ከመቼው ወደዛእንደሄደ ! ምን ልሁን ብሎ ነው ? ፣ ምን ሊሰራ ?.......አላዘዝኩትም ። ስልጣን የሱ ይመስላል የኔ ልብ ቢሆንም ። ብቻ ልቤ አዘዘኝ ። አርቲስት ከመሆኗ አንፃር ሌሎች ስራዎቿንም ማየቱን ቀጠልኩበት ፤ በፎቶም ፣ በቪዲዮም እና እሷን እሷን ነው ሚለኝ ። በነገራችን ላይ ፊልሙ የ 2001 ዓ.ም ነው ። እኔ 2001 ላይ 6 አመቴ ነበርኩኝ ። አሁን 22 አመቴ ነው ። የዛሬ 16 አመት የተሰራ ፊልም ። ብቻ አሁን ልጅቷ የት ነች ? ፦ ያቺ የወንደሰን ጓደኛ ፣ ያቺ ምትወደውና ምትጠብቀው ልጅ ? ፣ የት ነች አሁን ? ፣ ከማን ጋር ነች ? ፣ ምን እየሰራች ነው ? ........ያለኝ መረጃ ቢኖር 39 አመቷ መግባቷ ብቻ ነው ።
አመሰግናለሁ !
2017 ዓ.ም | 1 722 |
| 3 | ጥቆማ‼️
ምንም ውሸት አልተቀላቀለበትም!!
በትኩሱ ስለወቅታዊ ጉዳይ ፈጣን እና ታማኝ መረጃ ለማግኘት ይሄንን ቻናል ዝምብላቹህ ተቀላቀሉ!!
አሁኑኑ ይቀላቀሉ...አሁኑኑ...‼️
በጥቆማዬ ሙሉ በሙሉ እተማማናለሁ 👌"የመረጃ ቋት ቻናል ነው "በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇 👇👇
https://t.me/+J1IotGE22aE3ZGY0
https://t.me/+J1IotGE22aE3ZGY0 | 248 |
| 4 | አሪፍ አሪፍ የቴሌግራም ቻናሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት የምትፈልጉ እኛጋ ያገኛሉ አናግሩን ።
📩 @Abate_Hiwote
☎️ 0931374891 | 2 622 |
| 5 | አባቷን ያጠባችው ልጅ
በጥንት የሮማዊያን ታሪክ ውስጥ የተፈፀመ እስካሁን ድረስ የፍቅርና መስዕዋትነት መገለጫ ተደርጎ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ነው የአባት ሲመንና የሴት ልጁ ፔሮ ታሪክ
ሲመን በእድሜ ማምሻቸው ለእስር ተዳርገው የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል፡፡ ፍርዱ ግን በስቅላት ወይም ጥይት ተተኩሶባቸው አልነበረም እንዲሞቱ የተወሰነባቸው፡፡ በራብ እንዲሞቱ ነበር።
በዚህን ግዜ ሞታቸውን በጥብቅ ቁጥጥር ስር ባለው እስር ቤት ሆነው እንዲጠብቁ ተደረጉ። በዚህ መሀል ልጃቸው ፔሮ አባቷን ከሞት የመታደግ ሀቅም ባይኖራትም ቢያንስ አባቷ አስኪሞት እየተመላለሰች እንድትጠይቃቸው አዛዦችን ተማፀነች። እነሱም ለአባቷ ያላትን ጥልቅ ፍቅር አይተው ፈቀዱላት ነገር ግን ምግብ በምንም መልኩ ይዛ ብትገባ የአባቷ እጣ እንደሚደርሳት አስጠነቀቋት። በርግጥ ፍተሻውም ሊያሳልፋት የሚችል አልነበረም።
በዚህ ሁኔታ ሳምንታት አለፉ፡፡ ጠባቂዎች ቢጠብቁ ሲመን ሊሞቱ አልቻሉም፡፡ ይባስ ብለው ያብረቀርቁ ጀመር። በዚህን ጊዜ ተደብቀው ነገሩን መከታተል ጀመሩ። ከዚህ በኋላ ነበር ለሰው ልጅ የፍቅርና መስዕዋትነት መለኪያ ሁኖ በታሪክየተሰነደውን ነገር የደረሱበት።
ለካስ ልጅ አባቷን ጡቷን እያጠባቻቸው ነበር ይህን ታክል ጊዜ ያቆየቻቸው።
ጠባቂዎች ይዘው ለአለቃቸው አቀረቧት። ለምን እንዳደረገች ስትጠየቅም እድሜ ልኬን እንዳልራብና እንዳልጠማ ያደረገኝ አባቴ እያየሁት በራብ ሲሞት እንዴት ይቻለኛል፡፡ ቀድሜው ብሞት እመርጣለሁ አለች።
በዚህን ጊዜ አለቆች ልባቸው ተሰበረ። ለአባቷ በከፈለችው መስዕዋትነት ግድያ ሳይሆን ክብር ነው የሚገባት ብለው አባቷንም በምህረት ፈቱላት ።
#ሰላም_ለሀገራችን_ሰላም_ለሕዝባችን
ይ🀄️ላ🀄️ሉ
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8 | 2 975 |
| 6 |
ፍቅር እና ፊልም
እውነተኛ ታሪክ
ክፍል 2
ሰው ሚስቅበት ምክንያት ይኖረዋል ። እየተግባቡ እኩል መሳቅ መጫወት እንለዋለን ። ግን እኔን ሳይገባኝ እነሱን ምን ገብቷቸው ነው ሚስቁት ? ፣ ለምንስ አብሬያቸው መሳቅን አልቻልኩም ? ብቻ አዝናናቸዋለው ። ግን እኔ እነሱን ለማዝናናት ሞክሬም ሆነ አስቤም አላውቅም ። ብቻ እዛው ስብሰባ ውስጥ የኔ መገኘት ብቻ ለነሱ በቂ ነው ። ግራ ገባኝ ። ከሰው ጋር ሆንኩም አልሆንኩም ያው ህመሙ እንዳለ ነው ። ማለት አሁንም ብቸኝነት ነው ሚሰማኝ ። ምንም ለውጥ የለም ።
አንዳንድ ልጆች አሉ ፣ ማለት ከሳቅ ሚቆጠቡ ። እነሱስ ለምን አልሳቁም ?..............ከሳቅ ይልቅ ዝምታን እና ችላ ማለትን ይመርጣሉ ። እኔንጃ ። እነሱን ግን ስቀርባቸው ጥሩ ስሜትን ይፈጥርብኛል ። ግራ ገብቶኝም አያውቅም ። በተቻለን አቅም እኩል ተግባብተን እንለያያለንና ደግሞ ሰላምታቸው ራሱ ልዩነት አለው ከነዛ ጋር ። የማይስቁት ሰላምታቸውን ሰጥተውኝ ሲያልፉ የሚስቁት ግን ሰላምታ አይበቃቸውም ። ሌላም ነገር ይጀምራሉ ። ያቺ ቦታ አብረን ምንሰባሰብበት ላይ የሚያደርጓትን ነገር ይደግሙታል ። ያው ይስቃሉ ማለቴ ነው ። እኔ ግን አሁንም አልስቅም ። ለነሱ ገብቷቸው ለኔ ያልገባኝ ነገር አለ ማለት ነው ። የሆነ ከኔ በላይ የሆኑ ነገር ይሰማኛል ።የበታችየሆንኩኝ አይነት ስሜትን ይፈጥርብኛል። እኔንጃአልወዳቸውም ግን። የቀሩት ልጆች ግን ይመቹኛል ምክንያቱም ትህትና አላቸው እና ምናገረውን ሊረዱኝ ይሞክራሉ ። የሆነ ጊዜ ጅቦች አይቼ በእንቅልፍ ልቤ ጅብ ደግሞ በህልም ምን ሊሰራ መጣ ብዬ ፤ ህልም ማለት የሆነ መልዕክትን ያዘለ ይመስለኛል ። ህልሜን አይቼ ችላ ማለት አልፈለኩም እና አንዱ ተርጓሚ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው ?............የሆኑ ሰዎች በኔ ድክመት እየተጠቀሙ እንደሆኑና የኔን አቅመቢስነት ገለፀልኝ ። አሁን ሁሉ ነገር ገባኝ ። ለካስ ከጅብ ጋር ነበርኩ ፣ ለካስ እየበሉኝ ነበር ። ምን ያድርጉ ? ፤ በግ የሆንኩት እኔ ። እንግዲያውስ ያለኝ አማራጭ መሸሽ ነበር ። በግ ከጅብ መሀል ምን ይሰራል ? ፤ ዳይ ወደ ቤቴ..........
አሁን ተሽሎኛል ። እንደ በፊቱ ያህል መቸገር ቁሟል ፣ ራሴንም መጠበቅ ችያለሁ ። ግን አሁንም ብቸኝነቱ አለ ፤ ሆኖም ይመስገነው ! ካለፈው ዘንድሮ ይሻላል ። ተመስገን !
ደብሮኝ ቤት ብቻዬን ፊልም ባይስ የሚል ሀሳብ መጣልኝ ። በነገራችን ላይ ታሪኩ አሁን ይጀምራል እና አሁን ወረቀቱን ድብቁን ነገር ላስይዘው ነው ። ሚስጥሬን !
እርግጥ ፊልሙን ከዚህ በፊት አውቀዋለሁ አይቼዋለሁም ግን ለማስታወስ ያህልና ካየሁትም ስለቆየሁኝ ፤ በብዙ ሰዎች ዘንድም ጥሩ አስተያየት ስላለው ደግሜም ባየው አይደብረኝም አልኩ ። ፊልሙን ለማውረድ ተጫንኩት ። ፊልሙም ወርዶ አለቀ ። የቀረኝ ከፍቶ ማየት ብቻ ነበር ። ምሽት ላይ ላፕቶፔን ይዤ አልጋዬ ላይ ተጋደምኩና PLAY የሚለውን ተጫንኩት ። ፊልሙም ጀመረ ። የፊልሙ ዋና ገፀባህርይ ስለ አንድ ብቸኛና ትንሽ የ MENTAL DISORDER ያለበት የ ሀያ አመት ወጣት ነው ። ልክ እንደኔው ወጣት ነው እንዲሁም ተማሪ ነው ። ብዙ ነገራችን ተመሳሰለብኝ ከልጁ ጋር ፦ እንደኔው ተማሪ ነው ፣ ወጣት ነው ፣ ብቸኛ ነው ፣ ጓደኛም የለውም ። ብቻውን ከቤቱ ወጥቶ ብቻውን ሄዶ ብቻውን ተምሮ ብቻውን ሚመለስ በግ ነው ። አያሳዝንም !
ጊዜው የፈተና ቀንነበር ።ልጁ ጎበዝ ተማሪ ቢሆንም ግን በግ መሆኑ ሳይጎዳው አልቀረም። መቼም ከዛ ሁሉ ተማሪ ጅብ አይጠፋምና የክፍሉ ጉልቤዎች የፈተና መልስ እንዲልኩለት አስጠንቅቀው ነገሩት ነገር ግን በጉ አስተማሪውን ፈርቶ መልሱን ሳይልክላቸው ይቀራል ። ጠበቁት ከትምህርት ቤቱ እስኪወጣ ። እዛው ትምህርት ቤት ግንብ አጥር ስር ትቦ ውስጥ ቀጥቅጠው ትተውት ሄዱ ። ደግነቱ ሰው አይቶት ዝም አላለምና በሰው እገዛ ወጣ ። እዛው አካባቢ ከሚገኘው ከአንድ የካፌ ባለቤት ልጅ ጋር እንደ አጋጣሚ ተገናኘ ። ገፅታውን አይታ ተረድታው ነው መሰለኝ ልትረዳው ፈልጋ ነበርና በጓሮ በኩል ወስዳው ልብሱን ማራገፍ ጀመረችለት ። ጥያቄም ትጠይቀው ነበርና በጭውውታቸው መሀከል ስለሱ የጀርባውን ታሪክ ሲነግራት አዘነችለት ። ልብሱን አፅድታለት ፊቱንም አጥባለት ነገር ግን የልጁን የእጅ ሰዓት በጀርባዋ በኩል ደብቃበት ፣ ቦርሳውን ብቻ መልሳ ቻው ተባባሉ ። ልጁ ተስተካክሎ ወደቤቱ ሄደ ነገር ግን የእጅ ሰዓቱን አልሰጠችውም ።
የተማሪዎች መውጫ ሰዐት ነው ፣ ልጁም ከተማሪዎች እኩል እየወጣ ነው ። እሷም የመውጫ ሰዓቱን አውቃ ከካፌው በረንዳ ላይ የልጁን ሰዐት በጀርባዋ ደብቃው ልጁ በሷ በኩል እስኪልፍ እየጠበቀችነው ። ልጁ ቦርሳውን እንደተማሪ አንግቦት እየተጓዘ ከካፌው አጠገብ ደረሰ ። ሊያልፍ ሲል ቆማ እየጠበቀችው እንደነበር አየ ። አስታወሳት ። ፈገግ ብላ ታየዋለች ። ከጀርባዋ የሆነ ነገር የደበቀች ትመሰላለች ። ቀስ ብላ የእጅ ሰዐቱን አውጥታ እያሳየችው መሳቅ ጀመረች ። ተሸውደህ ነበር ማለቷ ነው ። ልጁም ፈገግ አለና ቀስ ብሎ ወደሷ ተጠጋና ወደ ካፌውም ይዛው ገባች ። ተመቻችተዋል ። እሱም እሷም ደስተኛ ናቸው ። ልጁ ግን ድብቅ ነገር ነው ። ልጁ ጥሩ ጓደኛ ሳያገኝ አልቀረም ። እንዲሁ በየጊዜው መገናኘታቸው እየቀጠለ ተስማምተዋልና የልጁን ፀባይ ወደዋለች ። ታዝንለታለችና ቦታ የሰጠችው ትመስላለች ። የሆነ ቀን አብረው ተጫውተው ሊሰነባበቱ ሲሉ " ነገ የለሁምና ከነገ ወዲያ የሆነ ፕሮግራም ስላለ ጓደኞቼ ጋር እንሄዳለን " ትለዋለች ። እንዲሁም ዘንጦ እንዲመጣ መክራው ቻው ተባባሉ ።
በቀጣዩ ቀን ልጁ ከፊቱ ባለው መስታወት ቆሞ የመዘነጫ ልብሶቹን እየቀያየረ ይመለከታል ። ከልብሶቹ መሀከል አንዱን መርጦ ለብሶ ልጂቷ ወዳለችበት ወደ ወደካፌው ሄደ............... አላያትም ነበርና እሷ ግን አይታው ስለነበር እንዳየችው " ወንድዬ " ብላ ጠራችው ። የልጁ ስም ወንደሰን ነው ግን እንደዛ ነው ምትጠራው ። በሙሉ ስሙ ስትጠራው ሰምቼ አላውቅም ። ደስ ብሏት እየሳቀች ቀርባው ያደረገው ከረባት ትንሽ ያስፎግራል መሰለኝ አነሳችለት ። ከረባቱ ሲነሳ አሁን ያማረ ይመስላል ። ተያይዘው ሄዱዋ ወደ ፓርቲው !
ክፍል 3 ይቀጥላል ..... | 3 130 |
| 7 | ለ Pp የሚሆን ጥቅስ አጥተው ያውቃሉ? ወይስ ለፍቅረኛዎ የሚልኩት የፍቅር መልዕክት ይፈልጋሉ?❤️ ተቀላቀሉን👇🏼👇🏼👇🏼 | 349 |
| 8 | የማንን ስልክ መጥለፍ ይፈልጋሉ ?🤔
የፍቅረኛዉን ፣የልጆን ወይስ የጓደኛዎን
እንግዳዉስ መፍትሄዉ ትልቁን የ HACKING ቻናላችንን መቀላቀል ነዉ።👩💻🧑💻
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/addlist/ywaPLkXhze04NGY0 | 309 |
| 9 | 😆😂🤣በ10ጣቴ እፈርምልሀለው የምር እዚህ ቻናል ላይ ገብታችሁ ካልሳቃችሁ የምር ጥርስ ስለሌላችሁ ነው😆😂🤣
🤣🤣እውነት ዝም ብላቹ JOIN በሉ 😂😂😂ጥርሳችሁ እስኪ ሰበር ነዉ ምትስቁት ግን በዋላ ጥርሳቹ ተሰብሮ ክፈል የለም 😁😁JOIN ብለው አብረን እንሳቅ😂😂😂👇👇👇👇
https://t.me/+_7b2Tn3bu9RmMGFk
https://t.me/+_7b2Tn3bu9RmMGFk | 248 |
| 10 | የምትወዳትን ልጅ ስታገኝ የምታወራው ይጠፋብሀል ⁉️
👉ከስር ነበብ ነበብ አርገህ ፍጠንባት‼️
⚜ወንድ እስከሆንክ ድረስ ቀልጠፍ ማለት አለብህ‼️
😋 ከስር view የሚለውን በመጫን ያገኙታል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 | 323 |
| 11 | ፍቅር እና ፊልም
እውነተኛ ታሪክ
ክፍል 1
2017 ዓ.ም
እስክሪብቶና ደብተር (አጀንዳ) ይዤ ተቀምጫለሁ ቤቴ ። ጻፍ ጻፍ ሲለኝ እንግዲህ ለመፃፍ ተነሳሁኛ ። ታዲያ ምን ሊፃፍ ነው ?.......... ልቦለድ ነው ? ፣ ግጥም ? ፣ ተረት ? ፣ ወግ ወይስ እውነተኛ ታሪክ ?
ልቦለድ ፅፌ አላውቅም ግን አንድ ቀን የፊልም ደራሲ ለመሆን አስቤ የሆነ ታሪክ ለመፃፍ ስሞክር እንደነበር ትዝ ይለኛል ። ግን አላለቀም ። ልቦለድ ማለት ፈጠራ ነው ። ሰው ከአእምሮ ወይም ከራሱ የሚያወጣው የፈጠራ ታሪክ ነው ። ውሸት ቢሆንም ። ግጥምም ሞክሬያለሁ ። ትቤት ውስጥ አስተማሪያችን የክፍልስራ ብላን ያው የተማሪ ግዴታዬ ስለሆነ ነበር የፃፍኩላት ። ተረት አንድም ቀን ፅፌም ሆነ ሞክሬም አላውቅም። ወግን ተዉት ፤ ጭራሽ አስቤም አላውቅም ። ያወኩት ራሱ አስራአንደኛ ወይ አስራሁለተኛ ክፍል ስገባ ነበር ።
እና ስነፅሁፍ ላይ ያለኝ ተሞክሮ እንዴት ነው ? ፣ የደከመ አይመስልም ?............ለስነፅሁፍ የነበረኝ አቋም ወይም ፍላጎት ያን ያህል ከፍተኛ ነው አያስብልም መሰለኝ ። ታዲያ ዛሬ ምን አነሳሳኝ ?
ስነፅሁፍ ተሞክሮ ላይ ከነበርኩኝ ቆይቻለሁ ። እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 2012 ዓ.ም ላይ ነበር ተሞክሮዬ ። ዛሬ 2017 ከገባ ቆየ ። ታዲያ ምን ልፅፍ ነው ይሄ ሁሉ ጊዜ ቆይቼ ? ፣ እና ልፃፈው ወይስ አልፃፈው ? እሱንስ ወስኛለሁ ለመፃፍ እና ውሳኔዬም ልክ ነው ብዬ አምናለሁ ። ለምን ግን ውሳኔዬን ልክ ያልኩት ይመስላችኋል ?..........እርግጥ ልክ ነው ምክንያቱም በወረቀት ላይ ባሰፍረው ችግር አለው አንዴ ? የለውም ምክንያቱም ወረቀት ሊፅፉበት ነውና የተፈጠረው ስለዚህ ፅፍበታለው ምናባቱ !
እና ብፅፈው ይሻላል አይደል ?..........ለነገሩ ወረቀትኮ ካላዩት አያሳይም። ይቺን ወረቀቴን ማንም ሰው እንዲያይብኝ አልፈልግም ። ማንም ! የታየ ቀን ማሳየቱ አይቀርምና ወረቀቱ ከእኔ ውጭ ማንም ሰው እይታ እንዲሰጠው አልፈቅድም ። በጭራሽ ። ለምን ግን ከእኔ ውጭ ሌላ ሰው እንዳያየው ፈለኩኝ ? ፣ ለምን ? ፣ ለምን መደበቁን ፈለግኩኝ ? ፣ ወረቀቱ ምን ይዞ ነው ባካችሁ ? ፣ ከተደበቀማ ሚስጥር ተባለ አይደል እንዴ ?...........እንግዲያውስ ሚስጥር ነው ። ሚስጥር ካልኳቹማ ልቦለድ መሆን አይችልም ። ተረትም አይሆንም ፣ ወግም አይሆንም ፣ ግጥምም አይሆንም ። ግን እውነተኛ ታሪክ ብንለውስ ?...........ያው ሚስጥር ከተባለ ድብቅ እውነት የሚል ፍቺን ስለሚይዝ አዎ እውነተኛ ታሪክ ነው ያስኬዳል ። እና ምን አይነት እውነት ይዤ ነው ? ብዙ እውነቶች አሉ ለምሳሌ " ፀሀይ በምስራቅ ወጥታ በምዕራብ ትገባለች " ይሄ ግልጽ እውነት ነው ማንም የሚያውቀው ። የኔም እውነት ነው ነገር ግን ማንም የማያውቀው ።
እንግዲያውስ እውነቴን ለራሴ ልናገር ። እኔ ብቸኛ ሰው ነኝ ። አማካሪ የሌለኝ ወይም ምግባባው አይነት ጓደኛ የሌለኝ ሰው ፣ ከራሴ ጋር እንኩዋን መግባባት ያልቻልኩኝ ሰው ። ነገሮች ይወሳሰቡብኛል ። በብዙ ሰዎች ዘንድ ቀላል እና የተለመደ ነገር ለኔ አዲስና ገና ለመልመድ ጥረት ላይ ነኝ ። እርግጥ ብቸኝነት ጥቅም አለው ። ብዙ ነገሮችን ቢያስተምረኝም ግን ጎድቶኛል ። ሰውን ለምን እንደምፈራ አላውቅም ። መፍራቱስ ለምን አስፈለገ ?...............ብቻ ፍርሀት ይይዘኛል ። ብቸኝነቴን ያበዛሁት መሰለኝ እና ለመድኩት ፣ ሰዎችንም ረሳሁ ። ጓደኛ ፣ ጎረቤት ፣ ዘመድ ወ.ዘ.ተ
ብቸኝነት ህመም ነው ። ህመም ማለት ከሰውነታችን ላይ ወይም ከሆነ ነገራችን ላይ የሆነ ነገር ሲጎድል ነው ። እኔም ብቸኝነትን ህመም ያልኩበት ምክንያት የሰው ማጣት ይመስለኛል ። የማማክረው ወይ አንድ ነገር አርግልኝ የምለው ጓደኛ ወይም ሌላ ሰው አለመኖሩ ፣ ችግሬን ለራሴና ለራሴ ብቻ ማማከሬ፣ ድብቅ ሰው መሆኔ እንዳልታወቅ አድርጎኛል ። ምን ብቸኝነት ውስጥ እንደከተተኝ ! እስቲ ይለፍልኝና ከሰው ጋር ልሁን ብዬ ሰዉ ወዳለበት ስገባ አዳማጭ ብቻ እንጂ ተናጋሪ አይደለሁም ። ኸረ አዳምጬም አላውቅም ! እሱንም አንዳንዴ ካዳመጥኳቸው ነው ። እና ምንም ለውጥ ሊያመጣልኝ አልቻለም ። እዛው ቤቴ ብቻዬን ተቀምጬ ከራሴ ጋር የማወጋው ሳይሻለኝ አይቀርም ብዬ ወደ ቦታዬ ( ወደ ቤቴ ) እመለሳለሁ ። ነገር ግን ወደዛው ስብሰባ መሄዱን አላቆምኩም ። መቼም እንደነሱ ተናጋሪ የመሆን ፣ አብረው መሳቅና አብሮ መጫወት ለኔ አዲስና ብርቅ ነገር ነውና ሳያቸው አብሮ ለመሳቅ ለመጫወት ካለኝ ጉጉት የተነሳ ልቀላቀላቸው እሞክርና ፊቴን አንዴ አይተውት ወዲያው ወደ ጨዋታቸው ይመለሳሉ ። ሙከራውን አላቆምኩም ። በየቀኑ እዛው መመላለስ ነበርና ጭራሽ ክብ ከሰሩ በኋላ እኔን መሀል አስገብተው ሌላ ነገር ጀመሩ ። እነሱ አንድ ሆነው ተያይዘው ክብ ሰርተዋል ፣ ተግባብተዋል ። እኔ ግን ከማናቸውም ጋር አልተያያዝኩም ። ነገር ግን በመሀከላቸው አስገብተውኝ እነሱ ይዝናናሉ ።
ለምን ግን ብቻዬን መሀል አስገቡኝ ? ፣ ለምን ብቻዬን ሚመለከቱኝ አይነት ሆንኩኝ ? ፣ ቆይ በምን ተለየሁ ? ምን አዲስ ነገር ተገኘ ?..............ይስቃሉ ያወራሉ ። ደግሞም የኔም ስም ወሬው ላይም አለበትና ለምንድነው ሚስቁት ? ሳላውቀው ተጫዋች ሰው ሆኜ ነው ? ፣ ወደውኝ ? ፣ ወይስ የሆነ የተለየ ነገር ኖሮኝ ? ፣ ተጫዋች ሰው ብሆን ኖሮ ታዲያ ለምን እጄን አልያዙትም ? ፣ እሺ ወደውኝ ቢሆን ኖሮ እጄን መያዝ ነበረባቸው አይደለምን ? እኔ ኮሜዲያን የመሆን ሀሳብም የለኝ ። ሳቁልኝ ሳልል ይስቃሉ ብቻ ። እኔ ግን የማውቀው NORMALLY ACT ማድረጌን ነው ። ለነሱ ግን ኖርማል አይደለም ። ይስቃሉ !
ክፍል 2 ይቀጥላል .........
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA | 4 699 |
| 12 | 1GB ስንት MB ነው? | 289 |
| 13 | Single ከሆንክ/ሽ ወይም ድብርት ውስጥ ከሆናችሁ ይህ ቻናል ለእናንተ ነው እመኑኝ ዝም ቢላችሁ Join በሉ 😍👇👇 | 507 |
| 14 | እንዴዴዴዴዴዴዴ ኧረ ፍጠኑ ጥያቄና መልስ ጀምረናል🔥🔥
✔️ ቀድሞ ለመለሱ 5 ሰዎች የካርድ ሽልማት አለ Request to Join ያድርጉ
🚛 የአለማችን ብዙ ህዝብ ያላት ሀገር ማን ነች? | 150 |
| 15 | የትምህርት ሚኒስተር ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ📝📝📝📝📝📝
https://t.me/+o3lMojCM02NjOTE8 | 350 |
| 16 | 😔ከፍቶኛል🥺 | 269 |
| 17 | ◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በለው ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇 | 296 |
| 18 | የፍቅረኛችሁን ሰው ስም የመጀመርያ ፊደል በመጫን ስለ ፍቅረኛዎ ይወቁ ❣︎❣
😍😍😍
ዳይ ለሁላችሁም ነው እንዳያመልጥዎ!!!!👇👇👇👇👇 | 125 |
| 19 | 🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ ‼️
ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇 | 199 |
| 20 | የትምህርት ሚኒስተር ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ📝📝📝📝📝📝
https://t.me/+o3lMojCM02NjOTE8 | 251 |
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
