cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Більше
Рекламні дописи
34 394Підписники
+524 години
+1087 днів
+1 83730 днів
Архів дописів
የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦን ላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ብለዋል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኛች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 14👎 6😁 4
የእንግሊዘ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ    ዌስትሃም ዩናይትድ 2-2 ሊቨርፑል      ቦውን ⚽️            ሮቦርትሰን ⚽️       አንቶኒዮ ⚽️       አርዮላ (OG) ⚽️ ጎሎቹን 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 21👎 4 3🤬 2
የእንግሊዘ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ                 የጨዋታ አጋማሽ    ዌስትሃም ዩናይትድ 1-0 ሊቨርፑል      ቦውን ⚽️ ጎሎቹን 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
5👍 1👎 1
የተአምራት  የበረከት   የፈውስ ቦታ የሆነው የፃድቁ አቡነ ሐራድንግል አንድነት ገዳም የህልውና አደጋ የፈጠረበትን የገዳሙን ርስት  መሬት ለማስመለስ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ተጠይቋል ለዚህም ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር በካፒታል ሆቴል ለማካሄድ ቀን ተቆርጧል በሐገር ቤትም በውጭም ያላችሁ የፃድቁ ወዳጆችና ህዝበ ክርስቲያን  እንድትረባረቡ ገዳሙ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጠይቋችሗል። የገዳሙ ሂሳብ ቁጥር ንግድ ባንክ 1000610362463 አባይ ባንክ 9221111060954312 ጎ ፈንድ ሚ አካውንት 634110814 account 021 000 021 Routine #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 35😁 11👎 7 6
ሰላም                                                                                                                                አሁን የተዘጋጀው ማለትም 6ተኛ ዙር  ከዚህ በፊት ከነበሩት የDropshipping  online ስልጠና ለየት ባለ መልኩ(master class) አዘጋጅተናል የሚቆይለ 1 ወር ሲሆን 2 ሳምንቱን THEORY ሲሆን የ ቀሩትን 2 ሳምንት ደግሞ practical ይሆናል ይህም ደግሞ ኮርሱን እየወሰዳችሁ  በ Dropshipping ገንዘብ መስራት ያስችላችዋል ። በተጨማሪም ስራውን ለመስራት ምንም አይነት investment እንደማያስፈልግ ትምህርቱን በተመለከተ በ online በ  Telegram ሲሆን በሳምንት 5 ቀን የምትማሩ ይሆናል። ከዚህ በፊት ከ 3000 ተማሪ በላይ በ 5 ዙሮች እንዳስተመ‍ኣርን ሶስቱ ቀን የተዘጋጀ video ሲለቅላቹ ሁለት ቀን ደግሞ በlive ቀጥታ ስርጭት ከvideo ያልገባቹ ነገር ካለ ወይንም በግል መጠየቅ ምትፈልጉትን ጥያቄ በቀጥታ ከ አስተማሪዎቹ ጋር የምትወያዩበት ይሆናል። 👉ኮርሱን ለሚወስዱ ተማሪዎች በሙሉ በነፃ የትኛዉንም የ online payment መፈፀም እና መቀበል የሚያስችል Mastercard የምንሰጥ ይሆናል። 👉ስልጠናዉን ሙሉ ለሙሉ ለጨረሱ ተማሪዎች certificate የሚሰጥ ይሆናል።እናም ደግሞ ከ Dropshipping በተጨማሪም እንደ bounes ሌሎች online business እንደሚያዩ 👉 በተጨማሪም ኮርሱን ወስደዉ አሪፍ ዉጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎቹ በኮርሱ መጨረሻ ላይ የ 100,000 ብር giveaway ይኖራል። 👉 ኮርሱም ከለቀ በሁዋላም በ Dropshipping lifetime guide ከAfro dropshipping ይሰጣችዋል። 👉ከ Afro dropshipping private community ጋር አብራቹ የምትሰሩበት እድል ይመቻቻል። 👉 ኮርሱን ተመዝግበዉ ኮርሱን ከልወደዱት በመጀመሪያዎቹ 3 ቀናቶች የከፈሉትን ገንዘብ ማስመለስ ይችላሉ። 👉 ለአእያንዳንዳቸው ስለ Dropshipping guide ሚያደርጋቸው ሰው እንደሚኖር 👉 የ 6ተኛ ዙር ምዝገባውም የሚቆየዉ ለ2 ሳምንታት ማለትም እስከ ሚያዚያ 28 እንደሆነ ና በመጀመሪያው ሳምንት ለሚመዝገቡ ታላቅ ናሽ እንዳዘጋጀን ለመመዝገብ በዚ User name [ @Afrodropshipping ] እንዲያዋሩን እና ብዙ Fake account ስለተከፈቱ የኛ afro dropshipping ትክክለኛ Telegram account verified የሆነው እንደሆነ በ channel ደረጃ ደግሞ ከ 26000 subscriber belay yalew endehone ለበለጠ መረጃ Telegram channel ላይ ስለ coursu ሙሉ መረጃ በ video መልኩ ማግኘት ይችላሉ። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 9👎 3 2
👍 2 1
ህወሓት በዝግ የተደረጉ ስብሰባዎች መረጃ ከየት ነው የምታገኙት በማለት ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶችን እያስፈራራ ነው ተባለ ህወሓት ባለፈው የካሄደው 60 ቀን የፈጀ ዝግ ስብሰባን ጨምሮ በሌሎች ስብሰባዎች የተነሱ ጉዳዮችን የተመለከ መረጃ ለጋዜጠኞችና ለአክቲቪስቶች ማን ነው አሳልፎ እየሰጠ ያለው የሚለውን ለማወቅ ያለመ ኮሚቴ በማቋቋም ምርመራ መጀመሩን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። በትናንትናው ዕለት አንድ የቀድሞ የድምፂ ወያነ ጋዜጠኛና የተለያዩ ህወሓትን የተመለከቱ ጉዳዮች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በማጋራት የሚታወቅ ጋዜጠኛ በዚሁ መርማሪ ኮማቴ ጥሪ ቀርቦለት በመቀለ ከተማ በመገኘት ከኮሚቴው አባላት ጋር ቆይታ እንዳደረገ ተናግሯል። በቆይታውም በቅርቡ የተካሄደው 60 ቀናት የፈጀውን ስብሰባ ላይ የተነሱ ጉዳዮች የተመለከቱ መረጃዎች እንዴትና ከማን ነበር ስታገኝ የነበረው የሚሉ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት የገለፀ ሲሆን ጥያቄዎቹም ከትብብር ይልቅ በማስፈራራትና ለማወጣጣት በመሞከር የተቃኙ እንደነበሩ ተናግሯል። ዳጉ ጆርናል የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም በጦርነቱ ወቅት የህወሓት ጦር ቃል አቀባይ የነበረው ገብረ ገብረፃዲቅና የቀድሞ የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ የነበረው ሃይለ አሰፋ የዚህ መርማሪ ኮሚቴ አባላት እንደሆኑ ነው። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😁 38👍 19🕊 4👎 3😢 2 1🤬 1
በኮሪደር ልማት 1 ሺህ 135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ 👉🏼 ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸዉ አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም ብለዋል በትናንትናው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ጥያቄ ካቀረቡ የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፤ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች መካከል “1,135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸውን” በማንሳት ጥያቄ አቅርበዋል። “1,135 ሰው ማለት ቀላል አይደለም። በዚህ ወቅት፣ በዚህ የኑሮ ውድነት፣ በዚህ ጊዜ ተረጋግቶ የሚኖርበት አጋጣሚ ካልተፈጠረ፤ የሚሰራውን ስራ ሁሉ በዜሮ ድምር የሚያባዛ ነው የሚሆነውና እርሱ ለምን ግምት ውስጥ አልገባም?” ሲሉ መጠየቃቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በ90 ቀናት እንዲጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘለት በመጥቀስም፤ “የግድ በዚህ ሶስት ወር ውስጥ ስራ ማለቅ አለበት ወይ?” ሲሉ ተጨማሪ ጥያቄ አስከትለዋል። “በጊዜ ተለክቶ ስራ መሰራት አለበት፤ ልክ ነው። አምናም የ90 ቀን እቅድ ተብሎ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል። ሁልጊዜ ግን በዚህ መልክ በዘመቻ መሰራት አለበት ወይ? የሚል ጥያቄ ይስነሳል” ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ “ነገሮች በተረጋጋ እና በታቀደ መልኩ እንዲሄዱ ለማድረግ መሰራት የለበትም ወይ?” ሲሉ አስተያየት አዘል ጥያቄ ማንሳታቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የምክር ቤት አባሉ ከጠቀሷቸው የልማት ተነሺዎች ውስጥ “አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም። በተለይ የመንግስት ቤት ተከራይ፣ የቀበሌ፣ የኪራይ ቤቶች፣ የቤተክህነት ጭምር ማለት ነው” ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የልማት ተነሺዎችን በዚህ መልኩ የማስተናገድ አካሄድ ሲከተል “ለመጀመሪያ ጊዜ” መሆኑንም ጠቁመዋል። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 31👎 3 3
የፌይኖርዱ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ፥ በቀጣይ የርገን ክሎፕን በሊቨርፑል ቤት ለመተካት ከስምምነት መድረሳቸው በስፋት እየተዘገበ ይገኛል #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 29 2
የኤርትራ ጦር ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ የዛላአንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል ብለዋል፡፡ ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች ፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮብ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮ ኤፍኤም ዘገባ ተመልክቷል። አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡ የኤርትራ ጦር የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ተነግሯል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል። በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ 30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ  አቶ ብርሀነ ገልፀዋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 31🤬 11 3🕊 1
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩት የራያ አካባቢዎች ያለ አስተዳዳሪ ወደ ሁለተኛ ሳምንታቸው እየተሻገሩ ነው ከየካቲት ጀምሮ አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረው “በህወሓት ታጣቂዎች” እና “በአካባቢው ሚሊሺያዎች” መካከል ሲደረግ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍ ባለ ሁኔታ ተካሂዶ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወዲህ የነበረውን መዋቅር ቀይሮታል። ላለፉት ሦስት ዓመት ገደማ አካባቢዎቹን ሲመሩ የነበሩት ከአማራ ክልል በኩል የተሾሙ አስተዳዳሪዎች፤ ከሚመሯቸው የራያ ወረዳ እና ከተሞች ሸሽተው ቆቦ ከተማ እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ውስጥ ተጠልለዋል። በቆቦ ከተማ የሚገኙት ከራያ አካባቢዎች የሸሹት የመንግሥት ሹመኞች ብቻ አይደሉም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በወጣው ሪፖርት 50 ሺህ ሰዎች ከራያ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች እንደተፈናቀሉ አስታውቋል። ከተፈናቃዎቹ ውስጥ 42 ሺህ ያህሉ የሚገኙት በሰሜን ወሎ ዞን ስር በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። ሌሎች የራያ አካባቢዎች ነዋሪዎች ግን አሁንም ባሉበት ኑሯቸውን ቀጥለዋል። የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች የተሾሙላቸው የአላማጣ እና የኮረም ከተሞች ያለምንም አስተዳዳሪ ከቀሩ ሁለት ሳምንታት ተቃርበዋል። ከሁለቱም ክልሎች የተሾሙ አመራሮች የሚገኙት በየክልላቸው ውስጥ በሚገኙ አጎራቦች አካባቢዎች ውስጥ ነው። በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች ውስጥ የፌደራል እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱ ከተማዎች አምስት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በከተሞቹ ውስጥ የሚገኙት የፌደራል መንግሥት እንዲሁም የአካባቢ አስተዳደሮችን ተቋማት እና ቢሮዎች እየጠበቁ ያሉት በሁለቱ የፀጥታ አካላት መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ ውስጥ አንጻራዊ ሰላም እንዳለ ጠቅሰዋል። ባንኮች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቢሮዎች እንዲሁም የተወሰኑ መደብሮች መከፈታቸውን ሦስት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች ያልተከፈቱት አካባቢዎቹን ላይ አስተዳዳሪ አለመኖሩ በፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት መሆኑን የሚናገሩ አንድ የአላማጣ ነዋሪ፤ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተንቀሳቀሱ ያሉት በዋና የአስፓልት መንገዶች ላይ እንደሆነ አስረድተዋል። ከትግራይ ክልል በኩል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ዝናቡ ደስታም በተመሳሳይ በከተማዋ ሁለቱ የፌደራል መንግሥት ኃይሎች ቢኖሩም የፀጥታ ሁኔታው በበቂ ሁኔታ እየተሸፈነ አለመሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአማራ ክልል በኩል የተሾሙት የአላማጣ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋ ውስጥ መኖራቸውን አንስተው በአሁኑ ሰዓት ስላለው ሁኔታ ግን “ዝርዝር መረጃ” እንደሌላቸው ጠቅሰዋል። ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የመንግሥት ኃላፊዎች ከአላማጣ መውጣታቸውን ተከትሎ በመንግሥት ተቋማት ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች እስካሁን ድረስ እንደቆሙ መሆኑን ሦስት ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማዋ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነም ጠቅሰዋል። አንድ የከተማዋ ነዋሪ*፤ “[የጤና አገልግሎት] የለም ማለት ይቻላል። አሁን በቅርብ አንዲት ወላድ ነበረች፤ ደም [ያስፈልጋል] ተብላ ወደ ወልዲያ ሄዳለች። ምንም ዓይነት አገልግሎት የለም። በጣም ተቸግራ እዚህ ያሉ ዶክተሮች በግል ተባበሯት፤ …ወደ ቆቦ በትራንስፖርት ሄዳ፣ ከቆቦ ወደ ወልዲያ ወሰዷት” ሲል በከተማዋ ላለው ሁኔታ ማሳያ ጠቅሷል። በኮረም ከተማም በተመሳሳይ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቀድሞ አስተዳዳሪዎች ለቀው በወጡባት ኮረም ከተማም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ተቋማት እየተጠበቁ ያሉት በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ሠራዊት አባላት መሆኑን ተናግረዋል። ይሁንና ከአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ሦስት ነዋሪዎች ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ታጣቂዎቹ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ “ዝርፊያ ፈጽመዋል” ሲሉ ከሰዋል። ታጣቂዎቹ የሰፈሩት በከማው ውስጥ በሚገኙት ስድስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ መሆናቸውን የሚናገሩ አንድ ነዋሪ፤ “የትምህር ቤት መጽሐፍት ‘የአማራ ክልል ናቸው’ በሚል ተቀድደዋል” ሲሉ በትግራይ ታጣቂዎች ተፈጽሟል ያሉትን ድርጊት ጠቅሰዋል። ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው፤ በከተማዋ ውስጥ በታጣቃዎቹ በሚፈጸሙት ድርጊቶች ሳቢያ ነዋሪዎች አሁንም ወደ ቆቦ ከተማ እየሸሹ መሆኑን ተናግረዋል። በቆቦ ከተማ የሚገኙት በአማራ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉም የኮረም ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ወደ ቆቦ ከተማ እየገቡ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በትግራይ ክልል በኩል የራያ አካባቢ ወረዳ እና ከተማዎችን በስሩ የያዘው የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀፍቱ ኪሮስ፤ በኮረም ከተማ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ገብተዋል ስለመባሉ እና ታጣቂዎቹ ፈጽመዋቸዋል ስለተባሉ ድርጊቶች ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በኮረም “በጣም የተረጋጋ ሰላም እና ደኅንነት” መፈጠሩን የሚናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፤ “ኮረም እና አላማጣም ላይ በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ኃይሎች የፀጥታ እና ሰላሙን የመጠበቅ ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈጸሙ ነው” ብለዋል። አቶ ሀፍቱ፤ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ስለመግባታቸው እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ መስረፈራቸው ማረጋገጫ ከመስጠትም ሆነ ከማስተባበል ተቆጥበዋል። እንደ ራያ ባሉ አካባቢዎች ላይ ከዚህ ቀደም በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳደር መካከል የነበረው “ከመከላከያ ሠራዊት ውጪ ሌላ ታጣቂ ኃይል አይኑር” የሚለው “ንግግር” በአሁኑ ሰዓት “መቀየሩን” ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል። የፕሪቶሪያ ስምምነትን የተፈራረሙት የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ከስምምነቱ በታች ያሉ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ንግግር እየፈቱ እና “እያሻሻሉ” እየሄዱ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሀፍቱ፤ “ለምሳሌ አሁን ማሻሻያዎች አሉ። በዚያ አካባቢ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፌደራል ፖሊስ ውጪ ማንኛውም ታጣቂ መኖር የለበትም የሚል የውይይት ሀሳብ እንደነበር ይታወቃል። አሁን እሱ ተቀይሯል። ሌላ እድገት አለው” ብለዋል። ዋና አስተዳዳሪው “ተቀይሯል” ያሉት የታጣቂዎች ጉዳይ የሚወያዩት አካላት ይፋ እንደሚያደርጉት በመጥቀስ ዝርዝሩን ከመናገር ተቆጥባዋል። ሁለቱ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ባለፉት ሳምንታት የተፈጠረውን ሁኔታ የአፍሪካ ኅብረት እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ተወካዮች እንዳሰሰባቸው እና ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። የአማራ እና የትግራይ ክልሎች በይገባኛል በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ላይ የህወሓት ታጣቂዎች ወረራ ፈጽመዋል ብሎ ባለፈው ሳምንት የአማራ ክልል መንግሥት መክሰሱ ይታወሳል። ለወሰን እና ለማንነት ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት እየሠራ መሆኑን የገለጸው የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ሲል ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። Via ቢቢሲ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 23🕊 7😢 2
👍 1
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተነገረ ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ብለዋል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ አመራር ነግረውኛል ሲል አል አይን መዘገቡን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😁 27🤔 11👍 10 2😢 2🙏 1
በካፋ ዞን አንድት ሴት ህፃን ጫካ ውሰጥ ተጥላ ተገኘች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ  ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት በ01 ቀበሌ ልዩ ስፍራው እግዚአብሔር አብ ተብሎ በሚጠራበት ጫካ ዉስጥ ተጥላ መገኘቷን ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስም ህፃኗን በማንሳት ወደህክምና ተቋም በመውሰድ አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ እንድታገኝ የተደረገ ሲሆን ህፃኗ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የደብቡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን የህፃኗን ቤተሰብ በአከባቢው ባህል መሰረት ኦቶ ወይም በአፈርሳታ እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗን ከሺሾ እንዴ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በጊዜያዊነት ለአንድ ግለሰብ እንድታሳድጋት መሰጠቷን ተገልጿል። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
የካሊፎርኒያ ኮሌጅ በጋዛ ያለውን ጦርነት በመቃወም የተነሳውን ውጥረት ተከትሎ ተጠባቂውን የተማሪዎች የምረቃ ስነስርአት ሰረዘ በሎስ አንጀለስ የሚገኘው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የደህንነት ስጋት በመጥቀስ ዋናውን እና በግንቦት 10 እንዲካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ሰርዟል። ይህ እርምጃ የተወሰደው በእስራኤል እና በጋዛ ጦርነት ምክንያት በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ካምፓሶች ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት ወቅት ነው። በአትላንታ ኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ 28 ተቃዋሚዎች ግቢውን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሐሙስ ዕለት ተይዘዋል ። በኒውዮርክ ከተማ፣ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በግቢው ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ለማስቆም ቀነ ገደብ ተጥሏል።ተማሪዎች ግን ድንኳን ሰርተው ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል። በመግለጫው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ እንዳስታወቀው 65,000 ተማሪዎች፣ ቤተሰብ እና ጓደኞቻቸው የሚታደሙበት የምረቃ ሥነ ሥርዓት ግቢው ማስተናገድ እንደማይችል ይፋ አድርጓል። እሮብ እለት፣ ፖሊስ ግቢውን ጥሶ በመግባት ከ93 ያላነሱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ተቃውሞ የፍልስጤም ኬፊህ ወይም ሻርፕ እና በፍልስጤም ባንዲራ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የጆርጅ ዋሽንግተን ሀውልት ለብሶ ታይቷል። በሌላ በኩል በጋዛ በቀጠለው ውጊያ ዙሪያ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ወታደሮቹ በታቀደው የምድር ጦር ዘመችም መሰረት “ወደ ፊት እየገሰገሱ ነው” ነው ብለዋል። የራፋህ ምስራቃዊ ክፍል በየጊዜው በመድፍ እየተደበደበ ይገኛል። ከደቡብ ሊባኖስ በተነሳው የሂዝቦላ የሚሳኤል ጥቃት አንድ እስራኤላዊ የጭነት መኪና ሹፌር መገደሉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። የእስራኤል ሚዲያዎች አካባቢው በተመታበት ጊዜ ሰውዬው ወደ እስራኤል ሰሜናዊ ድንበር አቅራቢያ ለወታደሮች የመሠረተ ልማት ስታዎችን ሲያከናውን ነበር ብለዋል ። በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ በሄዝቦላህ እና በእስራኤል ጦር መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በኢራን የሚደገፈው ቡድን ከጋዛውያን ጎን መቆሙን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 50 13👏 5👎 1
"እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው።" መዝሙር 68፤35 ገዳመ ወንያት መንታዎቹ ደብር አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ወር በገባ በ11ኛው ቀን ጻድቁ አቡነ ሐራ መታሰቢያ በዓላቸው ነው።ገዳሙ የተአምራት የበረከት የፈውስ ቦታ ነው።ከጻድቁ መቃብር ተዝቆ በማያልቅ ሞልቶ በማይፈስ አፈር እጹብ ድንቅ ተአምራት ይደረጋል። በጻድቁ መካነ መቃብር ላይ የሚገኘውን ቤተክርስቲያን ያሰሩት አፄ ዮሐንስ፬ኛ በጽኑ ነቀርሳ በሳይንሳዊ አጠራር ካንሰር በሽታ ተይዘው የእግዚአብሔር ቸርነት የጻድቁን አማላጅነት ተስፋ አድርገው ከመቀሌ ድረስ ገስግሰው መጥተው በጻድቁ ጸበል ድንቅ ስለተደረገላቸው ፈውስን ስላገኙ የክብር አልጋና ዘውዳቸውን ሰጥተዋል ቤተክርስቲያኑንም አሰርተዋል። ጻድቁ ዛሬም ውሉደ ጥምቀትን ሁሉ ከክፉ ደዌ በጸበላቸው ይፈውሳሉ።ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር መንገድ ስንወጣ ዘንዘልማ የምትባል አነስተኛ ከተማ አለች ከዘንዘልማ በስተቀኝ ታጥፎ በ12ኪሎሜትር ላይ ይገኛል።ብዙዎች በጻድቁ አማላጅነት ከደዌ ስጋ ድነዋል መካኖች ወልደዋል እውሮች በርተዋል ለምጻሞችም ነጽተዋል። የጻድቁ በረከት ይደርብን በቃልኪዳናቸው ይጠብቁን ከእለት እኪት ከቀሳፊ ነገር ይሰውሩን ከፍቅር ረሐብ ከዘረኝነት ደዌ ከዝሙት እሳት ከምንፍቅና አሽክላ ይታደጉን።የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዓላውያን መንግስታት ዘመን በደረሰበት መከራና ፈተና የተነሣ ተዳክሞ በመቆየቱ የገዳሙ የይዞታ ቦታ በመሉ በአካባቢው አርሶ አደር እና በሌሎች ጥቃቅን ነጋዴዎች እጅ ከገባ አያሌ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ገዳሙ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ተከትሎ በርካታ አባቶች መነኮሳትና እናቶች መነኮሳይያት ወደ ገዳሙ በመግባት በመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ቢሆንም የገዳሙ ይዞታ ለረጅም ዘመናት በሌሎች ግለሰቦች እጅ ተይዞ በመቆየቱ ምክንያት እንኳንስ ለገዳሙ ልማት ይቅርና ለመነኮሳቱ መጠለያ ቤት መሥሪያ ቦታ በመጥፋቱ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል፡፡ ይህን መሬት ለማስመለስ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ተጠይቋል።ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ታላቅ የገቢ ማሰባሰብያ መርሀ ግብር በካፒታል ሆቴል ለማካሄድ ቀን ተቆርጧል በሐገር ቤትም በውጭም ያላችሁ የፃድቁ ወዳጆችና ህዝበ ክርስቲያን እንድትረባረቡ ገዳሙ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጠይቋችኃል #ዳጉ _ጆርናል
Показати все...
👍 45 19👎 7🔥 1
አሜሪካ ወታደሮቿን ከቻድ በጊዜያዊነት ልታስወጣ መሆኑ ተነገረ ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉንም ወታደሮቿን ከጎረቤት ኒጀር ለማስወጣት ከተስማማች ከቀናት በኋላ የተወሰኑ ወታደሮቿን ከቻድ በጊዜያዊነት እንደምታስወጣ ተሰምቷል። የዩናይትድ ስቴትስ የፔንታጎን ፕሬስ ሴክሬታሪ ሜጀር ጄኔራል ፓት ራይደር እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ አንዳንድ ወታደራዊ ኃይሎቿን ከቻድ “ለመቀየር” አቅዳለች፣ ነገር ግን ምን ያህሉ እንደሚወጡ እና ወደየት እንደሚዘዋወሩ ግን አልገለጹም። "ይህ ከቻድ የግንቦት 6 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ የሚቀጥል የፀጥታ ትብብር ግምገማ አካል የሆነ ጊዜያዊ እርምጃ ነው" ብለዋል ። ይህ መረጃ የተሰማው የቻድ አየር ሃይል አዛዥ ዩናይትድ ስቴትስን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በዋና ከተማዋ ኒጃሜና አቅራቢያ የሚገኘውን የአየር ጦር ሰፈር እንቅስቃሴ እንድታቆም ማዘዛቸውን ተከትሎ ስለምሆኑ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ጄኔራል ራይደር በተጨማሪም ከኒጀር ገዥው ወታደራዊ መንግስት፣ የሀገር ውስጥ ጥበቃ ብሔራዊ ምክር ቤት ጋር ውይይት የጀመረው እሮብ እለት ሲሆን ዓላማውም “ሥርዓት እና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ የአሜሪካ ኃይሎች ከአገሪቱ መውጣታቸውን” ለማረጋገጥ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ በቀጠናው የሚገኙ ታጣቂዎችን እንቅስቃሴን ለመከታተል እንደ ቀዳሚ ቦታዋ ኒጀርን ትመለከታት ነበር። ነገር ግን ካለፈው ሀምሌ ወር ጀምሮ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው ወታደራዊ መንግስት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በሀገሪቱ ላይ እንዲሰማሩ እና የፈረንሳይ ወታደሮችን እንዲቆዩ የፈቀደውን ወታደራዊ ስምምነት ወረቀት ቀዷል። ይህ ውሳኔ የኒጀር ወታደራዊ መንግስት ከምዕራባውያን ጋር ያለውን ግንኙነት ለመቁረጥ የጀመረው ጥረት አካል ነው። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 17🔥 1
👍 1🔥 1
በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ውስጥ ከ230 ኩንታል በላይ ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፅ እንዲወገድ ተደረገ በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ በቁጥጥር ስር የዋለ ከ230 ኩንታል በላይ የሚገመት ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፅ እንዲወገድ መደረጉን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል።የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዶ/ር ደረጄ ኢተና በሻላ ወረዳ በተለያዩ ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ 230 ካናቢስ ከፍተኛ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ተናግረዋል:: በአርሲ ዞን እንደ ሻላ ያሉ ጥቂት ወረዳ ውስጥ አርሷአደሩ ከበቆሎ እና ከማሽላ ምርቶች ጋር አደንዛዥ እፅን እንደሚያመርት የጠቀሱት ኃላፊው ህብረተሰቡ በተለያዩ ጊዜያት መድረክ በመፍጠር አስፈላጊውን የግንዛቤ ማስጨበጫ  ትምህርት በመስጠት የምርቱን ስፋት በሂደት መቀነሱን ተናግረዋል። የአደንዛዥ እፅ ንግድ እና ዝውውር የተደራጀ የቡድን ሰንሰለት ያለው በመሆኑ በከፍተኛ ገንዘብ በመደለል በድብቅ የሚመረት የሚደረግ ቢሆንም የተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ተቋማት ጋራ በመስራት የአደንዛዥ እጹን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።በቅርቡ በተደረገ የተቀናጀ አሰሳ በሻላ ወረዳ ላይ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲወገድ መደረጉን ገልፀዋል። አደንዛዥ እፅ የወጣቶችን አዕምሮ ለወንጀል ድርጊት የሚያነሳሳና ሀገር ተረካቢ የሆነውን ወጣት ለሞራል መላሸቅ እንዲገጥመው እና ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር የሚያገልጥ በመሆኑ የአደንዛዥ እፅ ዝውውር እና ንግድ ላይ ከመስራት ባሻገር በዚህ ተግባራት የተሰማሩ በርካታ ግለሰቦችን ለፍትህ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ረ/ኮሚሽነር ደረጄ ኢተና ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 16👏 5 1😁 1
የኬንያ አየር መንገድ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሰራተኞቼ ላይ ተፈፅሟል ያለውን እስር ተቃወመ የኬንያ አየር መንገድ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ሰራተኞቼ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ቢወስንም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሁለት ሰራተኞቹን በቁጥጥር ስር አውሏል ሲል ከሷል። ሁለቱ የአየር መንገዱ ሰራተኞች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ መረጃ ክፍል ባለፈው አርብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን “በጣም ጠቃሚ” ጭነት ላይ ያለ የጉምሩክ ሰነድ ጠፍተዋል በሚል ነው ሲል የኬንያ አየር መንገድ በመግለጫው ገልጿል። አየር መንገዱ ጭነቱን ወደ ኪንሻሳ ያላነሳው ባልተሟላ ሰነድ የተነሳ ነው ብሏል። "የኬንያ አየር መንገድ የጭነት ንብረቱ ያልተሟላ ሰነድ ስለ መኖሩ ለወታደራዊ መኮንኖች ለማስረዳት የተደረገው ጥረት ሁሉ ከንቱ ሆኖ ተገኝቷል" ሲል አክሏል። ወታደራዊ መኮንኖቹ የኬንያ ኤምባሲ ባለስልጣናት እና የአየር መንገዱ ቡድን ለአጭር ጊዜ ሁለቱን ሰዎች እንዲጎበኟቸው የተፈቀደላቸው እስከ ማክሰኞ ድረስ ብቻ ነው። ሐሙስ እለት የኬንያ አየር መንገድ እንደገለፀው ፍርድ ቤት ሰራተኞቹ ላክ ምርመራ እንዲጥል በመወስን ከእስር እንዲፈቱ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሏል። "ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ቢሰጥም የወታደራዊ መረጃ ክፍል አሁንም በድብቅ እንደያዛቸው ይገኛል፣ ሆኖም እነዚህ በወታደራዊ መረጃ ተቋም ውስጥ የታሰሩ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው" ሲል አየር መንገዱ አክሎ ተናግሯል። በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የሰራተኞቹ ስልኮች መያዛቸውን የኬንያ አየር መንገድ ገልጿል። የተጠቀሰው ጭነት ምን እንደያዘ ግልፅ ያልተደረገ ሲሆን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለስልጣናት ዘንድ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 7🔥 1
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 244 የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ ሰራተኞቹን መቅጣቱን እና በህግ ተጠያቂ ማደረጉን ገለፀ 👉 አገልግሎቱ አመራሮቹ እና ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ሰራተኞቹ ሀብታቸዉን እንዲያስመዘግቡ አድርጓል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትከዚህ በፊት ይነሳበት የነበረዉን የሙስና ተግባር ለመከላከል የተለያዩ ለዉጦችን እየከወንኩኝ እገኛለሁ ማለቱን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ለዚህም በማሳያነት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከወናቸዉን ተግባራት በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል። በተመሳሳይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 244 ሰራተኞቹን ከስራ እንዲታገዱ ፣ ከሀላፊነት እንዲነሱ እና በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉንም አሳዉቋል። አገልግሎቱ ይህንን ያለዉ በዛሬዉ እለት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸምን በገመገመበት ወቅት ነዉ። የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ - ፓስፖርት (E-passport) ለመቀየር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየከወነ መሆኑንም ብስራት ከሪፖርቱ ሰምቷል። በተመሳሳይ በዉጪ የሚታተመዉን ፓስፖርት በሀገር ዉስጥ ለማድረግ የዲዛይን ስራዎች ተጠናቅቀዋል የተባለም ሲሆን ህትመቱን ከሚሰራዉ ተቋም ጋር ዉል መታሰሩን እና ህትመቱን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ለመጀመር ማቀዱንም ይፋ አድርጓል። ተቋሙ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ስራዎቹን ለመከወን እንዳልቻለ የገለጸ ሲሆን በአንጻሩ በትግራይ ክልክ ተቋርጦ የነበረዉን አገልግሎት ለማስጀመር የዳሰሳ ጥናት መስራቱን አስታዉቋል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 17👏 7🔥 2
የሜክሲኮ የምግብ አቅራቢ የአይጥ መረቅን ከ50 ዓመታት በላይ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታወቀ በሜክሲኮ ሜርካዶ ሪፐብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ በሚሰኘው ገበያ ውስጥ በርካታ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይቻላል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልዩ የሆነው የአይጥ ስጋን በመሸጥ የሚታወቅ የቆየ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ታዋቂ ነው። ለበርካታ የዓለም ህዝብ የአይጥ ስጋ በፍፁም የማይለመድ እና ነውር ቢሆንም በሜክሲኮ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ክልል ውስጥ ግን ለየት ያለ ጣዕሙ እና ለመድኃኒትነት ይውላል በሚል ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአይጥ ሥጋ የሚሸጡባቸው ሱቆች እና አከፋፋዮች ከአካባቢው ገበያ እየጠፉ ይገኛል። በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ ግን አንዱ አከፋፋይ አሁንም ሁለቱንም ማለትን ጥሬ የአይጦች ስጋ እና የአይጥ መረቅ ከተለያዩ አትክልቶች እና ቅመማ ቅመም ጋር አዋህዶ መሸጡን ቀጥሏል። እያንዳንዱ የአይጥ መረቅ አንድ ሙሉ ሳህን የሚይዘው  በ100 የሜክሲከ ፔሶ ወይም በ5.80 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል።በሜርካዶ ሪፑብሊካ የመጨረሻው የአይጥ ስጋ ሻጭ ሆሴ ሬሜዲዮስ ሄርናንዴዝ "ካሚሎ" በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየችው ወላጅ እናቱ ይህንኑ ንግድ ወርሷል። በአንድ ወቅት በገበያው ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይጥ ስጋ ሻጮች እንደነበሩ ያስታውሳል፣ ነገር ግን ሁሉም ጡረታ ወጥተዋል አልያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሁን ላይ በገበያው ውስጥ ብቸማ አቅራቢ ሆኖ ቀጥሏል። ስራው እየተቀዛቀዘ በርካቶች ከዘርፉ ቢወጡን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰብን ንግድ ለመተው እቅድ የለኝም ሲል ይናገራል። ይህው የቤተሰቡ ንግድ ለ52 ዓመታት ዘልቋል። በተቻለም መጠን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ለማድረግ የአቅሜን ያህል መስራቴን እቀጥላለሁ ሲል ይደመጣል። ካሚሎ የሚያቀርበውን የአይጥ ሾርባ ለማዘጋጀት  በሳን ሉዊስ ፖቶሲ ዙሪያ ካሉ የከተማ አካባቢ እና በዙሪያው ክሚገኙ ገጠራማ ስፍራዎች ተይዘው ይመጣሉ። የአይጥ ሥጋ በተለይ የደም ማነስ፣ የስኳር በሽታ ወይም ካንሰር ላለባቸው ሰዎች ጠቃሚ ሲሆን የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር እና የምግብ ፍላጎትን ለመጨመር ይረዳል ተብሎ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ይታመናል። በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ በሚገኘው ካሚሎ ሁለቱንም የአይጥ መረቅ በ100 ፔሶ የሚሸጥ ሲሆን ጥሬ አይጥ ገዝተው ቤት ይዘው ለሚሄዱ በ90 ዋጋ ይቀርባል።የስጋውን ጣዕም በትክክል ለማሟላት በአትክልቶችና ቅመማ ቅመሞች ለማብሰል ይመክራል ሲሉ የሬስቶራንቱ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😁 28👍 17🤬 13👎 4🤯 4😱 4🤔 2 1
🤯 6
ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት እና መታወቂያ በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር  ዋለ ረቡዕ ሚያዚያ 16/2016ዓ.ም  በየካ ክፍለ ከተማ  በሀሰተኛ  ማስረጃ  አገልግሎት  ለማግኘት የሞከሩ አራት ደንበኞች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን  የአዲስ አበባምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሁለት ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው አገልግሎት ለማግኘት የቀረቡ ተገልጋዮችን ጨምሮ  ሌሎች ሁለት በወንጀል ተግባሩ የተጠረጡ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አግልግሎት ኤጀንሲ  ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ ዓለማየሁ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ። አንደኛው ግለሰብ ሃሰተኛ የመታወቂያ እና ያላገባ ህገ ወጥ ማስረጃ በመያዝ ለጽ/ቤቱ ሰራተኛ ጉቦ በመስጠት አገልግሎት ለማግኘት የሞከረ ሲሆን   ከዓመታት በፊት ማስረጃውን በሌላ አገናኝ ደላላ ያገኘው መሆኑን ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም  ደላላው እና  ሁለተኛው ተጠርጣሪ የቂርቆስ ክ/ከተማ ነዋሪነት መልቀቅያን አስመስሎ በማሰራት አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ ሲያደርግ ሃሰተኛ ሰነዱን ካዘጋጀው አስመዝጋቢ የቤት ባለቤት ነዋሪ ግለሰብ ጋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በአንደኛው ወንጀል የተጠረጠረው የጽ/ቤቱ ሰራተኛ ከዚህ ቀደም በወንጀል ተጠርጥሮ በኤጀንሲው ታግዶ የፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ያለ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡  ሁለተኛው  ድርጊት ሃሰተኛ መልቀቅያ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ነዋሪነት ስም አስመስሎ ለመገልገል ሲቀርብ በማስረጃው ላይ በጽ/ቤቱ ጥርጣሬ በማደሩ  የቂርቆስ ክ/ክተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ድርጊቱ ለፖሊስ እንዲተላለፍ በየካ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት  ጽ/ቤት መደረጉን አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 19 1
የበዓል ቅርጫ ቤትዎ ድረስ ብናመጣልዎትስ? አጋፔ online ቅርጫዎች ነን። ለገና በዓል እምነት የጣሉብን ደንበኞቻችን ሁሉ አስደስተናል!ለመጪው ፋሲካ ደግሞ ከቀድሞው በላይ ተዘጋጅተናል።የበዓል ቅርጫ በአቅራቢያዎ ካላገኙ የስራ ሁኔታዎ ለሊት ተነስቶ በቅርጫ ስራ ለመሳተፍ ካልፈቀደልዎ ሳይደክሙና እንቅልፎን ሳያጡ ድካምና ጊዜዎን ቆጥበን ማለዳ ከወፏ ዜማ ቀድመን ትኩስ ስጋ ከቤትዎ እናደርሳለን። ውጪ ሀገር ሆነው አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቾን በአውድ ዓመት ቅርጫ ሰርፕራይዝ ማድረግ ከፈለጉም ይዘዙን! ለመመዝገብ ☎️ 09-20-80-98-21 09-20-72-91-52 ወይም 0913552085 ይደውሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ደግሞ የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ፡፡ https://t.me/+HRT-JSbRFPQ3MzVk #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 15 3
በጋዛ የጅምላ መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ 'ግልጽ' ምርመራ እንዲደረግ እስራኤልን ጠየቀች ዋይት ሀውስ በእስራኤል ከበባ ከወደሙ የጋዛ ሆስፒታሎች የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን ተለትሎ ከእስራኤል ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንደሚፈልግ አስታውቋል።ከ300 በላይ ሰዎች በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸው የተረጋገጥው በካን ዮኒስ ናስር ሆስፒታል ተቀበሩ የተባሉ ከ300 በላይ ሰዎች እስካሁን ድረስ በመገኘታቸው ነው።በሰሜናዊው አል-ሺፋ ሆስፒታል ውስጥ ሌሎች የጅምላ መቃብሮችም ይገኛሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ እንፈልጋለን ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።በተጨማሪም ይህንን በጥልቀት እና በግልፅ መመርመር እንፈልጋለን ሲሉ አክለዋል።በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር በኑሴይራት ውስጥ የሃማስ ‘ስናይፐር ሴል’ አጠፍቻለሁ ሲል አስታውቋል።የእስራኤል ጦር ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ጋዛን የሚከፍለው በኔትዛሪም ኮሪደር አቅራቢያ በርካታ ተዋጊዎችን በመግደል እና ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን በማውደም በአካባቢው ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል። ወታደሮቹ በሰሜን በሻቲ የሚገኘውን የሃማስ ማስጀመሪያ ቦታዎችን በመምታታቸው በማዕከላዊ ጋዛ ኑሴይራት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚገኘውን የቡድኑን “ስናይፐር ሴሎች” አንዱን “በትክክለኛ የአየር ድብደባ” በማውደም ላይ መሆናቸውን ጦሩ አስታውቋል።በአጠቃላይ ባለፉት 24 ሰዓታት የእስራኤል ጦር በወሰደው ዘመቻ 30 የሃማስ ኢላማዎችን መምታቱንም አክሏል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የእስራኤል የመጨረሻ የጦር ማዕበል በሆነችው በራፋህ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ቢያንስ አምስት ሰዎችን መግደልን ጨምሮ በሲቪል ዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ሲል የፍልስጥኤሙ ዋፋ የዜና ወኪል ዘግቧል። በሰምሃል አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 31💔 14😢 8😱 3🙏 3👎 2😁 2👏 1
ከኢትዮ ቴሌኮም እውቅና ውጪ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ስልክ ሲያስደውል የነበረ ግለሰብ ተያዘ በሀረሪ ክልል ጀኒላ ወረዳ ጆራ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከኢትዮ ቴሌኮም እዉቅና ውጪ በህገወጥ መንገድ  ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወደ ውጪ ሀገር በማስደወል ህገ ወጥ ተግባር ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ ከግብራበሮቹ ጋር ከነ ቁሳቁሶቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የጅኒላ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሙፍቱ ከድር ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት  በተጠርጣሪነት የተያዘው ግለሰብ ከኢትዮ ቴሌኮም እውቅና ውጪ የስልክ መስመሮችን በመዘርጋት የኢትዮ ቴሌኮምን በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ እና ኪሳራ ላይ የሚጥል ተግባር ፈፅሟል። ግለሰቡ በድብቅ ሰዎችን ወደ ውጪ ሀገር በማስደወል የግል ጥቅሙን በህገ ወጥ መንገድ ሲያካብት እንደነበር እና በዚህ ተግባር ላይ እያለም እጅ ከፍንጅ መያዙን ተናግረዋል።ለዚህ ተግባር አገልግሎት እንዲሁም በህገወጥ ተግባር ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባቸው ብዛት ያላቸው የዋይፋይ ሳጥኖች፣ የተለያዩ ኬብሎች ፣ፍላሾች ፣ አንቴናዎች፣ሲም ካርዶች እና ሞባይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል። በዚህ ተግባር በተባባሪነት ከአንደኛው ተጠርጣሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ እና በቀጣይ ጊዜያት የምርመራ መዝገባቸው ተጠናቆ ለሚመለከተው የፍትህ አካል እንደሚላክ ኮማንደር ሙፍቱ ከድር ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 20 7👏 6😁 6😢 2
የቲክ ቶክ ቻይና ዋና ድርጅት መተግበሪያውን የመሸጥ እቅድ እንደሌለው አስታወቀ የቲክ ቶክ የቻይና እናት ኩባንያ ባይትዳንስ ዩናይትድ ስቴትስ በጣም ተወዳጅ የሆነውን የቪዲዮ መተግበሪያ እንዲሸጥ ወይም በአሜሪካ ውስጥ እንዲታገድ የሚያስገድድ ሕግ ካወጣች በኋላ ንግዱን የመሸጥ ፍላጎት የለኝም ሲል ኩባንያው አስታውቋል። "ባይት ዳንስ ቲክ ቶክን ለመሸጥ ምንም እቅድ የለውም" ሲል ኩባንያው በያዘው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ቱቲያኦ ላይ በይፋ መለያው አጋርቷል። ቴክቶክ ከመገናኛ ብዙሃን አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ቲክ ቶክ “ህገ-መንግስታዊ ያልሆነውን” ህግ በፍርድ ቤት እንደሚቃወም ተናግሯል። የባይትዳንስ መግለጫ የመጣው ቲክ ቶክን ከሚሰጠው ስልተ ቀመር ውጭ ለመሸጥ አማራጮችን እያፈላለገ መሆኑን መገናኛ ብዙሃን ከዘገቡ በኋላ ነው። ባይትዳንስ ቲክ ቶክን እንደሚሸጥ የውጭ መገናኛ ብዙሃን እያጋሩት ያሉት ዘገባዎች እውነት አይደሉም ብሏል ኩባንያው። ባይት ዳንስ ቲክ ቶክን ለመሸጥ ምንም እቅድ የለዉም ”ሲል ኩባንያው በማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም ቱቲያኦ ላይ በይፋ መለያው ላይ ለጥፏል። ቲክቶን በአሜሪካ የማገድ እርምጃ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረቡዕ እለት ተፈርሟል። ቲክ ቶክ የተጠቃሚውን መረጃ ለቻይና መንግስት ጋር ሊያጋራ ይችላል በሚል ስጋት በአሜሪካ የተወነጀለ ሲሆን ኩባንያው ግን ውንጀላውን የሀሰት ሲል አድርጓል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 34 5🤔 2