cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

God is Good 🇪🇹 🌏

GOD IS GOOD በዚህ ቻናል(Channel):- 📖የየዕለቱ ጥቅስ 🔊 በየዕለቱ የእግዚ/ርን መልካምነት ከቃሉ እናያለን 🎹መንፈሳዊ መዝሙሮች 🎤ስብከቶችና ትምህርቶች. እግዚአብሄር መልካም ነው በመከራ ቀን መሸሸጊያ ነው! 💻ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ https://t.me/Surafelfikre 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Lordisgood2

Більше
Рекламні дописи
196Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
“የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።” — ገላትያ 5፥24
Показати все...
(መዝሙረ ዳዊት 91 ) ------------ 1፤ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። 2፤ እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ። 3፤ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። 4፤ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። 5፤ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ 6፤ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። 7፤ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። 8፤ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። 9፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። 10፤ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። 11፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ 12፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። 13፤ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። 14፤ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። 15፤ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። 16፤ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
Показати все...
“ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤” — ሐዋርያት 2፥5
Показати все...
❝በሌላ ስፍራ ሺህ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣ በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።❞ መዝሙር 84: 10 “ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።” — መዝሙር 84፥10 “For a day in thy courts is better than a thousand. I had rather be a doorkeeper in the house of my God, than to dwell in the tents of wickedness.” — Psalms 84:10 (KJV)
Показати все...
“ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤” — 1ኛ ዮሐንስ 1፥6
Показати все...
ከፈቃድህ ስር ይሁን መቃብሬ ከዚህ ሌላ ህይወት አይታየኝ ለኔ::
Показати все...
“ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።” — 2ኛ ቆሮ 9፥15
Показати все...
“እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚያደርግ እርሱ ኃያል ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?” — ኢዮኤል 2፥11
Показати все...
ምነው መውጣት ባይኖር ከዚህ መንፈስ ምነው መውጣት ባይኖር ከዚህ ቦታ ሳመልክ ሳመሰግን ልኑር ሲያንስብህ ነው ነው የእኔ ጌታ-2 ሺህ ዘመናትን በኃጣን ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ እንኳን እድሜ ልኬን አንዲትን ቀን በእግዚአብሔር ቤት እርሱ መሚመለክበት ከቅዱሳኑ ጋር መሆን እንደሚበልጥ አስቤ በልቤ ይህ ዝማሬ በመንፈስ ቅዱስ ፈሰሰ: ወገኖቼ እናንተና የትውልድ ትውልዳችሁ የእግዚአብሔርን ቤት ይውደድ ዘመኑም በዚያ ይለቅ :... መዝሙረ ዳዊት 27 4፤ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። Pastor Endale W/G
Показати все...
ድንቅ አባባሎች 1."መፍራት ያለብህ ቀስ ብለህ ማደግህን ሳይሆን ከአለህበት ቁመህ እንዳትቀር ነዉ፡፡ተራራን ከቦታ ወደቦታ የሚያንቀሳቅሰዉ ሰዉ ትንንሽ ድንጋዮችን ያለመታከት የሚያጓጉዝ ሰዉ ነዉ፡፡"   ቻይናውያን 2."በምስጋና የተከፈተ ዘመን አስደሳች ነው፤ በፀሎት የተከፈተ ቀን መልካም ነው፤ በእምነት የሆነ ኑሮ ረፍት ነው፤ በይቅርታ የሆነ ጉዋደኝነት ዘላቂ ነው፤" አቡነ ሺኖዳ 3."ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡" አልበርት አንስታይን 4. “በከተማው ግንብ እጥሮች ውስጥ ቤት ከመገንባታችሁ በፊት በአእምሮአችሁ ዋሻ ውስጥ ያለውን ጎጆ ስሩ፡፡” ካህሊል ጅብራን 5."ስለራስዎ ጥሩ ስሜት እስኪሰማዎት ድረስ አንድ ሰው ስለራሱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ማድረግ አትችሉም ፡፡" ሮቢን ሻርማ 6."ዘላለም እንደምትኖር ሆነህ ስራ፤ ነገ እንደምትሞት ሆነህ ኑር" ጀርመኖች 7. “ልባችሁ በዝምታ ውስጥ የቀኖችንና የሌሊቶችን ሚስጥሮች ያውቃሉ፡፡ ይሁንና ጆሮዎቻችሁ የልባችሁን እውቀት ድምፅ ይጠማሉ፡፡ ምክንያቱም በሃሳብ የምታውቁትን ሁሉ በቃላትም ልታውቁ ትወዳላችሁና፡፡” ካህሊል ጅብራን 8.“በአንተ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ደስታ በፈረስ እንደሚጎተት ጋሪ ዘወትር ስቃይን ማስከተሉ አይቀርም፡፡” ሪንፓቼ 9.“ለማንኛውም የሰው ልጅ የምግባር በሽታ ጠንካራው መድኃኒት ፍቅር ብቻ ነው፡፡” ራማያና 10."ጊዜ በረረ፣ጊዜ አለፈ፣ ጊዜ ሄደ የሚሉ አገላለፆች በሙሉ መፅናኛ ናቸው፡፡ እውነቱን ካየነው እያለፍን ያለነው  እኛው እራሳችን ነን፡፡" ያልታወቀ 11." ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ " አልበርት አንስታይን 12."ነፃነት ማለት ሀላፊነትን በራስ እጅ መቀበል ማለት ነው።ሀላፊነትን ለመሸሽ ነፃነትን ብትሻ በአጉል ምኞት ታሰርክ እንጂ ነፃ አይደለህም!" ያልታወቀ 13."በራስዎ ውስጥ ኢንቬስት ማድረግ እርስዎ የሚያደርጉት ምርጥ ኢንቬስትሜንት ነው። ሕይወትዎን ማሻሻል ብቻ አይደለም ፣ በአጠገብዎ ያሉትን ሰዎች ሕይወትም ያሻሽላል ፡፡" ሮቢን ሻርማ 14."በሰዎችና በመላዕክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሸው ጸናጽል ሆኛለሁ::" ጳውሎስ 15."በገንዘብህ የጥቅም ጓደኞችን ልታፈራ ትችላለህ በውበትህ የስሜት ጓደኞች ልታፈራ ትችላለህ በእምነትህና በስነምግባርህ ግን.. የህይወት ጓደኞችን ታፈራለህ።" ያልታወቀ 16."ያለፈው ጊዜዎ እስረኛ መሆን የለብዎትም። የወደፊትዎ አርክቴክት ይሁኑ ፡፡" ሮቢን ሻርማ ሌላውን ለማስተማር ሼር አድርጉ!! #Abel
Показати все...
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ አንድ ቀን በድንገት በህዝብ መጓጓዣ ባቡር ላይ ሲሳፈሩ አንድ መንገደኛ በጊዜው አሸልቦት ስለነበር ለብዙ ጊዜያት በቴሌቪዥን መስኮት አልያም በጋዜጣ እያየ ሲያደንቃቸው የነበሩትን ክቡር ፕሬዚዳንት እርሱ ወዳለበት ሥፍራ መጥተው አጠገቡ ቢቆሙም እርሳቸውን የማናገር ወይም ሰላም የማለት ዕድልን በእንቅልፉ ምክንያት ሊያገኝ አልቻለም። ውድ ጓደኞቼ በዚህ በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ በሚከሰት አጋጣሚ ተኝቶ ያመለጠውን ሰው ታሪክ ሳነብ የተማርኩትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ የሰው ልጆችን ለማዳን ወደ ዓለም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን እና በደላችንን በመሸከም በመስቀል ላይ አስወግዶ ሞቶ በመነሳት ከፍ ብሎ ወደሰማይ ሲያርግ ተመልሶ በቅዱሳን መላዕክት ታጅቦ እንደሚመጣ እና እንደሚወስደን መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል ታዲያ መቼ ነዉ ይህ የሚሆነው ብለን ስንጠይቅ ቃሉ እንደዚህ ይለናል ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። ማቴዎስ 24÷42-44 ስለዚህ የጌታ መምጫው በድንገት ስለሆነ በስሙ በማመን ንስሐ በመግባት ዘወትር ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ ቃሉ ይመክረናል “ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤” ሉቃስ 21፥34 “ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።” ማቴዎስ 25፥13
Показати все...
“#ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።” — ፊልጵስዩስ 4፥6
Показати все...
#ርዕስ ፦  የእውነተኛ አምልኮ የትኩሬት አቅጣጫዎች                  ኢሳ 6፥1~13 ድረስ       1ኛ) እግዚ/ር ተኮር ነው (ኢሳ 6፥1-5)               2ኛ) ራስ ተኮር ስሆን ቅድሚያ ለላውን ሣይሆን ራስን ማየት ነው (ኢሳ 6፥5-)  * እኔም ፦ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ ከንፈሮቻቸውም  በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ  እግዚ/ርን ስለአዩ ጠፍችያለሁና ወዮልኝ አልሁ ይላል።        ንጉሱን      3ኛ) ተልዕኮ ተኮር ነው (ኢሳ 6 ፥ 8- 11) .. የጌታንም ድምፅ ማንን እልካለሁ ? ማንስ ይሄድልናል? ስል ሰማሁ ። እነሆኝ እኔን ላከኝ አልሁ። እርሱም ሂድ .....           )# ወደ ዓለም ሁሉ የማትሄድና ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ የማትናገር ቤ/ክን ቸልተኛና ንጽህ የጌታ ፍቅር የለላት ቤ/ክን ነች።        የምገርመው አብ የነበረው አንድ ልጅ ቢቻ ስሆን እርሱንም ሚስዮናዊ አድርጎ ወደዚህ ምድር ላከው።        የአንድ ጤናማ አማኝ የመጨረሻ ግቡ ዶክተር ወይም ሳይንትስት ሆኖ መሞት ሣይሆን ወንጌልን እየተናገረ ኢየሱስን ገልጦ መሞት ነው።           ከዚህ የወጣ ህይወት ኖሬና ሞቴ እንጅ በጌታ ፍት ምንም ዋጋ የለውም።         ወንጌልን ከማትናገር ቤ/ክን ጋር እግዚ/ር አብሮ አይቆምም።        ወንጌልን አለመናገር ማለት ልሞት ከተቃረበው ህመምተኛ ፍት መዲሃኒት እንደመደበቅ ነው።         መቼስ አንድ ትክክለኛ ራዕይ ያለው ሰው ዘመኑን የሚመራበት ዓላማ አለው።ዓላማውም የወንጌልን ተልዕኮ ይዞ መሮጥ ነው።           Oh ተልዕኮዋን ረስታ ዓላማዋን የጣለች ቤ/ክን ምድራዊ ተቑም እንጅ ሰማያዊ አካል አይደለችም ።          ቤ/ክን በምድር ላይ የምትኖርበት ሁለት ቁልፍ ዓላማ ስናይ       1ኛ) የጠፍትን ነፍሳት ማዳንና        2ኝ) የዳኑትን ደቀመዝሙር ማድሬግ ነው።        & ኢየሱስ የሞተው ማንንም ሃብታም ወይም ድሃ ለማድረግና የምታየውን ህንፃ ለመገንባት ሣይሆን ነፍሳትን ለማዳን ነውና ወጌኖች ሆይ የመኖራችን ትልቁ ዓላማ ለሎችን ለማዳን ስለሆነ የኢየሱስን የደም መስዋዕትነት የጠየቀው የለሎች መዳን ጉዳይ ነውና፦      ~ወንጌልን እንናገር       ~ ራሳችንን ሣይሆን ኢየሱስን እንስበክ        ~ ጠበቃዎቹ ሣይሆን ምስክሮቹ እንሁን         ~ መንግሥቴ ሰማያትን የምወርሰውን የሰውን ነፍስ ቸል ብለን በምድር የምቀረውን ህንፃ ብቻ እየገነባን ዘመናችን አይለቅ           ~ ስንት ግዜ church ተመላልሼ መጣሁ ሣይሆን ስንት ነፍስን ወደ ጌታ መንግሥት ጨምርያለሁ ብለን እንጠይቅ         @ሳጠቃልለው በወጣ መልኩ እግዚ/ርን ሳናይ፥ራሳችንን በጌታ ዓይን ሳንመረምርና፥ይልቅ በለሎች ላይ እየፈረድን ዋናውን ተልዕኮ መጣል እርሱ የእውነተኛ አምልኮ ትኩሬት ሣይሆን ምድር ተኮር የሆነ ከንቱ አምልኮ ወይም የአምልኮ መልክ ቢቻ ይሆናል።     From ወንድማችN ታምራት ኃይለማርያም      Wolayta areka
Показати все...
" በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። " (መዝሙረ ዳዊት 65:11) አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅር፣የደስታ፣የስኬት፣የመታደስ፣የጤና፣የመጨመር፣የድልና የመዉረስ ዘመን ይሁንልዎት። መልካም አድስ ዓመት ይሁንልን 2015!!! GOD IS GOOD 🙏 ይወዳጁን 🙏   ♦♦♦♦♦♦       🔑 @Lordisgood2       🔑 @Lordisgood2🔓 ❤Join and share Us🙏  Please 🙏 Join 🈴 Us!!
Показати все...
“እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።” — ሐዋርያት 14፥15 መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻2015🌻🌻አመቱ ከያለንበት ቦታ ወዴ#ጌታ ዘወር የሚንልበት ይሁን!! Be with God! Happy new year 🌻🌻🌻🌻🍸💐
Показати все...
መንገድ ላይ 😀 በመንገድ ላይ እየሄዳቹ ድንገት አንድ በምንም አይነት መልኩ የማታውቁት ሰው ወደናንተ መቶ ከ32ቱ ጥርሶቻቹ  ውስጥ  2 ጥርሶች የኔ ናቸው ቢላቹ ምን ትሉታላቹ?😀 በርግጠኝነት በደንብ ስቃቹ ነው ይህንን ሰው የምታልፉት፤ ነገር ግን በመንፈስ አለም ይህንን ሰው በሴጣን ብንተካው አሪፍ ይመስለኛል፤ በቃ ሴጣን እንደዚ ነው፤ ምንም ሳይኖረው በንግግርና በሀሳብ ብቻ ሊያሳምነን ይሞክራል፤ ከሰማቹትና ትኩረት ከሰጣቹት ልክ እንደዚያ ሰው 2ቱ ጥርሶች የእርሱ እንደሆነ አሳምኗቹ  በ 2ቱ ጥርሶች ላይ ንጉስ ይሆናል። ከሴጣን ጋር አታውሩ የሚላቹንም መስማት አቁሙ፤ እናታችን ሄዋን ትኖርበት ከነበረው ከኤደን ገነት የተባረረችው ከሴጣን ጋር አጉል ክርክር ውስጥ ገብታ ነው፤ ከሄዋን ተማሩ😍 From thedayofpentecost
Показати все...
እንደዚህ ብንፀልይስ? መንፈስ ቅዱስ ሆይ: በኔ ውስጥ የሚቆረቁርህ ነገር ካለ አውጣው! ያልተመቸህ ነገር ካለ አውጣው! ንፅህና የጎደለው የውስጥ ሞቲቭ (motive)ካለ አውጣው! ያልተፈወሰ አስተሳሰብ ካለ አውጣው! የተሰወረ ሃጢአት ካለ አውጣው! ድብቅ የዓመፅ ስር ካለ አውጣው! የእኔነት እንክርዳድ ካለ አውጣው! የማትደሰትበት የልብ ዝንባሌ ካለ አውጣው! ከፈቃድህ የተጣረሰ ከሃሳብህ የተፃረረ ምኞትና ፍላጎቴን አውጣው! ኢየሱስን የማያከብረውን ሁሉ አውጣው!! አውጣው አውጣው አውጣው!! በመለኮት ፈቃድ በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በነበረው ሃሳብ በመንፈስ ቅዱስ ክቡር ህላዌ ለውጠው !! አሜን!!! ወንድማችሁ ላሊ
Показати все...
#የእግዚአብሔር ሰው ሆይ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። ¹¹ #አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።
Показати все...
ኢሳይያስ 46 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፥ ስሙኝ። ⁴ #እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።
Показати все...
🙏 ልጅነት🙏 ♨️ልጅነት የህብረት ውጤት ነው። ወንድና ሴት ህብረት ሲያደርጉ ልጅ ይወለዳል። የቃሉ ዘርና መንፈሱ ሲገናኙ መንፈሳዊ ልጆች ይገኛሉ። ከእግዚአብሄር ለመወለድ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት ያስፈልጋል። ♨️ልጅነት ጥልቅ የሆነ ማሰሪያ ነው። የልጅነትን ማሰሪያ በፍቃድ መቁረጥ አይቻልም። መሰረቱ ተፈጥሮ እንጂ ፍላጎት አይደለም። አባት የቀየረ ሰው አለ? እርግጠኛ ነኝ ማንም የለም። እኛም እግዚአብሄር በቃኝ ማለት አንችልም። ♨️ልጅነት ጥልቅ ፍቅር ነው። የልጅነትን ፍቅር መሰረቱን ማግኘት አይቻልም ጥልቅ ነው። ልጆች አድካሚ ናቸው አይደል? የወለዳችሁ ወላጆች ታውቁታላችሁ ግን ፍቅር ድካሙን እንኳ እንዳትቆጥሩት አድርጓችኃል። ♨️ልጅነት በነፃ መወደድ ነው። እግዚአብሄር በነፃ ሲወደን ልጆቹ አደረገን። ልጅነት የቤተሰብና የአለም አባል የምንሆንበት ነው። አንድ ልጅ በተወለደ ቅፅበት ለቤተሰቡ አባል ለአለም ደግሞ ዜጋ ይሆናል። ከእግዚአብሄር ስንወለድ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባል በአለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን ደግሞ ዜጋ እንሆናለን። ♨️ልጅነት የእምነት ኑሮ ነው ልጆች ከቤተሰብ ጋር የሚኖሩት በእምነት ነው ቤተሰቦቻችን ቢያጡ፣ ቢነጡ ፣ ቢቸገሩ ብለው አይሉም ። በባዶ ካዝና ብዙ ነገር ያዛሉ። የነርሱ ቤተሰብ በአለም ላይ ካሉ ቤተሰብ ባለፀጋ ሁሉን ማድረግ የሚችሉ የመጀመሪያ አድርገው ነው የሚያስቡት። አባታቸውን አውሮፕላን ግዛልኝ የሚሉ ልጆች አሉ አባትዬው ትንሽዬ ነገር የመግዛት አቅም አይኖረው ይሆናል እኮ ልጆቹ ግን የኔ አባት የሚነሳው የለም ብለው ያስባሉ። እግዚአብሄርም እንደ ልጆች ካልሆናችሁ የሚለው ይሄንን ነው የኔ አባት እግዚአብሄር ምንም አይሳነውም እንዲህ ብለን እንድናምን እግዚአብሄር ይፈልጋል። የማንታመነውን እኛን ልጆቻችን ይሄን ያህል ካመኑን እኛስ እግዚአብሄርን ይሄን ያህል እናምነው ይሆን። ብዙ ጊዜ የተለያዩ ዜናዎችን ስትሰሙ ከመርከብ ከአውሮፕላን አደጋ የሚተርፉት ብዙ ጊዜ ህፃናት ናቸው። በዛ አደጋ ወቅት ራሳቸውን ለማዳን የሚያደርጉት ሁኔታ የለም ጥረት በማያድንበት ሁኔታ ትልልቁ ሰው ጥረት ሲያደርግ መስኮት ከፍቶ በር ከፍቶ ራሱን ይጥላል ህፃናት ግን በአደጋ ውስጥ እንኳ በእምነት በሰላም ነው ያሉት በአደጋ ውስጥ በእናት እቅፍ ውስጥ እንደተኛ ህፃን በብዙ አደጋም መከራ ውስጥ በእግዚአብሄር እቅፍ መሆን ያስፈልጋል። GOD IS GOOD 🙏 ይወዳጁን 🙏   ♦♦♦♦♦♦       🔑 @Lordisgood2       🔑 @Lordisgood2🔓 ❤Join and share Us🙏  Please 🙏 Join 🈴 Us!!
Показати все...
ap
Показати все...
#የት እንደተሸሸግን እንወቀው ዘፍጥረት 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ፦ ወዴት ነህ? አለው። ¹⁰ እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም
Показати все...
“አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።” — መዝሙር 71፥8 GOD IS GOOD 🙏 ይወዳጁን 🙏   ♦♦♦♦♦♦       🔑 @Lordisgood2       🔑 @Lordisgood2🔓 ❤Join and share Us🙏  Please 🙏 Join 🈴 Us!!
Показати все...
የዘሩ ምሳሌ የዘሩ ምሳሌዎች በማቲ 13:3-23 ማር 4: 3-13 ሉቃ 8: 5-13 ተጠቅሰዋል:: በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ዘሪው አንድ አይንት ዘርን በአራት የተለያዩ መሬቶች ላይ እንደዘራ ይናገራል :: መሬቶቹም -የመንገድ ዳር መሬት - ጭንጫ መሬት - እሾሃማ መሬት እና - መልካም መሬት ናቸው:: (የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 4) 2፤ በምሳሌም ብዙ ያስተምራቸው ነበር፥ በትምህርቱም አላቸው። ስሙ። 3-4፤ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት። 5፤ ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ 6፤ ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። 7፤ ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም። 8፤ ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ። . . . 14፤ ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥ 15፤ በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል። 16፤ እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፥ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፥ 17፤ ለጊዜውም ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም፥ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ። 18፤ በእሾህም የተዘሩት ሌሎች ናቸው፥ ቃሉን የሰሙት እነዚህ ናቸው፥ 19፤ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። 20፤ በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው። *እነዚህ መሬቶች አንድ አይንት ዘር ቢዘራባቸውም በሚገባ ያፈራው መልካሙ መሬት ብቻ ነበር እዚህ ላይ ማብቀል ብቻ በቂ እንዳልሆነ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ያሳየናል :: ታዲያ አንቺም ልቧሟ እህቴ ይህ መልካሙ የወጣትነት ጊዜሽ ~የልዩ ልዩ የሰይጣን ሃሳብ መተላለፊያ መንገድ ሳይሆን ~በልዩ ልዩ እሾክ በሆነ በዚህ ዓለም ሃሳብ ያስታንቅ ~ጭንጫ ሆኖ በያዝ ለቀቅ እና በለብታ ሂወት ፍሬ ቢስ እንዳይሆን ፍሬ ለማፍራት የአዝመራው ጊዜ ሳያልፍ እድሜሽ በጨለማው ኃይል ሳይታንቅ እና የቀኑ ክፋት ሳይጫንሽ በጉብዝናሽ ወራት በመልካሙ ልብሽ ላይ መልካሙን ዘር ዝሪበት:: *ዘሪ ዘርን የሚዘራው በወቅቱ ነው ያለወቅቱ ከዘራ ትርፉ ድካም ነው ማለትም ሰኔ ላይ ካልዘራ ምስከረም ላይ አረም ያጭዳል በውቅቱ ከሆነ አመርቂ እና ያማረ ፈሬ ያፈራል :: ታዲያ አንቺም እህቴ ይህ ያማረው እግዚአብሔርም አለምም የሚፍልገው የወጣትነት ጊዜሽ ሳያልፍ በወቅቱ መልካሙን ዘር ዝሪበት :: ደግሞም የምታጭጂውን የምታጭጂውን በአንቺ ውሳኔ ሳይሆን በምትዘሪው ዘር አይንት ነው ስለዚህ ምትዘሪውን በጥንቃቄ ምረጪ:: °°የዘሩም ምሳሌ ይህ ነው እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው°° " ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።"(ሉቃ8-11) ~ለመንገዳችን መብራት ~ለነፍሳችን መድሃኒት ~ ራሳችንን እንድናይ መስታወት የሆነውን የአምላካችንን ቃል በዘመናችን ላይ እንዝራ እጥፍ ምናፈራ ትውልዶች እንሁን:: 🙏ጌታ በፍሬያማ ሂወት የባርከን 🙏
Показати все...
ባልሽን ታድኚው እንደሆነ ምን ታውቂያለሽ⁉️ በዚህ ዘመን በእምነት የሚለያዩ ጓደኛማቾች በጣም እንዋደዳለን ግን ትዳር መመስረት እንችላለን ወይ ? ቃሉም 1 ቆሮንቶስ 7 -16 ላይ አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ? ይላል ማንያውቃል ጌታ እኔን ተጠቅሞ ያድነው( ያድናት) ይሆናል የሚሉ በዝተዋል መብዛት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ የሆነ ነገር ይመስል በብዙ ሰዎች ሕይወት ላይ ይታያል :: በመጅመሪያ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ብሎም ትዳር ለመመስረት የመጀመሪያውና ቁልፉ መስፈርት የእምነት (የሃይማኖት) መመሳሰል ነው። • ይህም ማለት ወንዱም ሴቷም ተመሳሳይ እምነት ሊኖራቸው ይገባል (ሁለቱም ዳግም የተወለዱ መሆን ይኖርባቸዋል)።በ 2 ቆሮንቶስ 6-14 ላይ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ብሎ በግልፅ ይናገራል ይህን ሲል ከማያምኑ ጋር ማህበራዊ ሕይወት ምንም አይስፍልግም እያለ ሳይሆን ለሚሰሩት ለእንደዚህ አይነት ትልቅ ስህተት እኛም ተባባሪ ሆነን እውቅና መስጠት እንደሌለብን ይነግረናል:: ብዙዎች በ1ኛ ቆሮ 7-16 ላይ ያለውን ቃል የቃሉን አውድና መልዕክት በሚገባ ባለመገንዘብ ጌታ እኔን ተጠቅሞ ያድነው( ያድናት) ይሆናል ብለው ሊወጡበት ወደማይችሉት ሕይወት ውስጥ ይገባሉ :: 1 ቆሮ 7 ከ13-16 ብናነበው 13፤ ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው። 14፤ ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። 15፤ የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። 16፤ አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ? • ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ሊነግረን የፈለገው ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ ሃይማኖታቸውን ስለሚቀይሩ የትዳር አጋሮች እንጂ ገና ወደ ትዳር ለሚገቡ በጓደኝነት ላይ ስለሚገኙ የተለያየ እምነት ስላላቸው ሰዎች አይደለም። ማለትም ሁለት የማያምኑ ሰዎች ቢጋቡና ከጊዜ በኋላ አንደኛው አካል ጌታን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ ቢቀበል በማያምነው ሰው ምክንያት ትዳራቸው መፍረስ እንደሌለበትና ወደጌታ በመጣው ሰው ህይወት ምክንያት የማያምነው ሰው ወደ ጌታ ሊመጣና ሊድን እንደሚችል ወይም ክርስቲያን የሆኑ ተጋቢዎች ቢኖሩና አንደኛው አካል ወደኋላ ቢመለስ በእምነት ልዩነት ምክንያት ትዳራቸውን ማፍረስ እንደሌለባቸው በተለይ ደግሞ ያላመነው ካመነው ጋር መኖር እየፈለገ መለያየት እንደሌለባቸው ይገልፃል:: ብዙ ወጣቶች በእምነት ከማይመሳሰላቸው ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ይገኛሉ። ሁለቱም በተለያየ ዓለም ውስጥ ስለሚገኙ አብረው መፀለይ ቃል ማንበብ አንድ ላይ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማሳደግ በፍፁም አይቻሉም። እንደውም አንደኛው ሌላኛውን ሰው ወደ ራሱ ሃይማኖት ለመሳብ ይጥራል እንጂ ምናልባትም አንደኛው ሌላኛውን ላለማጣት ሲል ብቻ ውስጡ ያላመነበት እምነት ውስጥ ይገባል :: 🚫 ትልቁ ስህተት! በጣም ስለሚወደኝ እምነቱን አስቀይረውና አገባዋለሁ የሚለው ሃሳብ ነው። አንድ አፍቃሪ ወደ ጌታ መምጣት ያለበት ፍቅረኛውን ፈልጎ ሳይሆን እውነቱ ገብቶት እውነትም ጌታ ኢየሱስ ሞቶልኛል የዘላለም ህይወት የማገኘው በእርሱ ነው ብሎ በማመን እና ከእጮኛው/ዋ በፊት ህይወት እንደሚቀድም በመረዳት መሆን አለበት። • እህቴ እጮኛሽ የዘላለም ህይወት ከሰጠሽ ጌታ በላይ በልጦብሽ እሱን ላለማጣት ስትይ የበራልሽን እውነት( እምነት ) የምትተይ ከሆነ እመኚኝ ትልቅ ኪሳራ ውስጥ ነሽ አስቢበት ዛሬ መንገድሽን አስተካክይ:: ለአንዷ እህትሽ አጋሪያት ምናልባት ይጠቅማት ይሆናል 👇 @lebamnegn @lebamnegn
Показати все...
#ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል። ኢሳይያስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። ² በዙሪያው ቈፈረ፥ ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ፥ ምርጥ የሆነውንም አረግ ተከለበት፥ በመካከሉም ግንብ ሠራ፥ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማሰበት፤ #ወይንንም ያፈራ ዘንድ #ተማመነ፥ ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ። ³ አሁንም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሆይ፥ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል እስኪ ፍረዱ። ⁴ ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን ስለ ምን #ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ? ⁵ አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፥ ለማሰማርያም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፥ ለመራገጫም ይሆናል። ⁶ #ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይቈረጥም፥ አይኰተኰትም፤ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ዳመናዎችን አዝዛለሁ። ዮሐንስ 15 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። ² #ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል። ³ እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤ ⁴ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። ⁵ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ⁶ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።
Показати все...
“ማን ነህ?........ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።” — ዮሐንስ 1፥22        ሰው መዝፈን የሌለበት ለምንድነው? የአንድ መስሪያ ቤት እቃዎች ከጀርባቸው የድርጅቱ መለያ ቁጥር ይጻፍባቸዋል። ይህ የሚሆነው እነዚህ እቃዎች የተመዘገቡና ከዚህ ድርጅት ውጪ ሌላ ቦታ ላይ አገልግሎት መስጠት አይችሉም ማለት ነው። እኛም በእግዚአብሔር የታተምን ነን ከእግዚአብሔር ውጪ ሌላ መንግስትን፣ ሌላ ተቋምን፣ ሌላ ፍጥረትን ማገልገል አንችልም። ስለዚህ አንደበታችን እግዚአብሔርን ብቻ ለማክበር ከፍ ከፍ ለማድረግ የተቀባ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ባመለክንበት፣ በዘመርንበት አንደበታችን ለሌላ አንዘምርም። የተቀባነው እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ለማድረግ እንጂ ሰዎችን ለማወዳደስ አይደለም።       እንኳን ስለሌላው ልንዘፍን ቀርቶ ስለራሳችን እንኳን መናገር ያለብን ከፍ ከፍ የሚያደርጉንን፣ ራሳችንን የሚገነቡ ንግግሮችን ሳይሆን እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሰዎችን ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ የሚመራውን ሕይወት ያለበትን ነገር ነው። “እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።” እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።”   — ዮሐንስ 1፥22-23 በረሃ ደረቅ ቦታ ነው። እዚያ ቦታ ላይ ብዙ ነገር ለምለም ሆኖ አያድግም። ዮሐንስ ሕይወት ለሌላቸው ሰዎች ሕይወት የማምጣት ሥልጣን ነበረው፣ እናንተም እንዲሁ ምድረበዳ ውስጥ ላሉ ሰዎች ሕይወትን የማሳየት ስልጣን አላችሁ።    ዮሐንስ ድምጹ ተራ ድምፅ አልነበረም። ይልቁንም  ነገሮችን በተሻለ መልኩ ለመለወጥ የተቀየሰ ድምጽ ነበር። በክርስቲያኖች መሐል እንኳን በጣም ብዙ ድምፆች አሉ። ነገር ግን አንዳንድ ድምጾችን በጥሞና ብታዳምጡ ራስን ከፍ ለማድረግ እንጂ አድማጭን ለመጥቀም የተነደፉ እንዳልሆኑ ትገነዘባላችሁ።  አድማጮችን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ለመጠቆም ሳይሆን ወደ ራሳቸው ለመጠቆም የታሰቡ ናቸው።  አንዳንድ ድምጾች ነፍሳትን ለመግደል የተነደፉ ናቸው። ይህንን ማየት በእውነት በጣም ያሳዝናል!     መጥምቁ ዮሐንስ ለአድማጮቹ ሕይወትን ለመስጠት የፈለገው "እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ አለ" ብሎ ለሙታን ሕይወት ወደሚሰጠው ወደ ክርስቶስ በመጠቆም ነው።   መጥምቁ ዮሐንስ እርሱ ክርስቶስ እንዳልሆነ መስክሯል። አንዳንዶች ይህን እድል ቢያገኙ ክርስቶስ ነኝ በማለት ዕድሉን ተጠቅመው ተመልካቾችን ሊያሳስቱ ይችሉ ነበር። ቀጥሎ መጥምቁ ዮሐንስ አድማጮቹን ወደ ክርስቶስ አመለከተ። አንዳንዶች ራሳቸውን ብቻ በማሳየት ይጠመዱ ነበር።      ወዳጆቼ እኛ ከክርስቶስ ውጪ የሚታይ ውበት የለንም። ሕይወት ለሌላቸው ሰዎች ሕይወትን መዝራት በእውነት ከፈለጋችሁ ወደ ክርስቶስ ጠቁማችሁ። እናንተ ድምጽ ናችሁ። ሁሌም ሰዎች ከእኛ ስለሚያገኙት መልዕክት ልንጠነቀቅ ይገባል። ክርስቶስ በፍቅር የሚታይ ነውና በፍቅር ለሰዎች እንግለጠው።   ✍አዶኒ ነሐሴ 14/2014 ዓ.ም 👇 @adonigospel @adonigospel
Показати все...
#የፈራሃው ነገር ምን እንደሚያደርሰበህ ሳይሆን እግዚአብሔር የት እንደሚያደርሰህ አሰብ🙏
Показати все...
ኢየሱስ መልካም ነው። ኢየሱስ መልካም ነው። ኢየሱስ መልካም ነው። ኢየሱስ መልካም ነው። ኢየሱስ መልካም ነው። ጌታ መልካም ነው። GOD IS GOOD 🙏 ይወዳጁን 🙏 ♦♦♦♦♦♦ 🔑 @Lordisgood2 🔑 @Lordisgood2🔓 ❤Join and share Us🙏 Please 🙏 Join 🈴 Us!!
Показати все...
ፍቅራችን በምን ይገለጥ                       ክፍል ሶስት       👉  ደግነትን በማሳየት       እግዚአብሔር ደግ ነው። እኛም ደግ መሆን ምርጫችን ሳይሆን ክርስቲያናዊ ህይወታችን ነው። ለወለዳችሁ ቤተሰብ ደግ መሆን ቀላል ነው፤ ለጓደኞቻችሁ ቸር መሆን ቀላል ነው። ደግነት ግን ለማያውቃችሁ ማንኛውም ሰው የምታሳዩት ፍቅር ነው። ደግነት ማሳየት ማለት ስለራሳችን ከምናስበው በላይ ስለሌላው ሰው ማሰብ ማለት ነው። ፍላጎታቸው ምንድን ነው? ሕይወታቸውን የተሻለ የሚያደርገው ምንድን ነው? ብሎ ማሰብ ነው። ሃሳባችን የግድ ትልቅ መሆን የለበትም ነገር ግን ሊታሰብበት ይገባል። አሳቢና ደግ መሆን ለሌላው ሰው ያላችሁ ፍቅር ከራሳችሁ በላይ ከፍ አድርጋችሁ እንደምትመለከቱት ትልቅ መልዕክት ያስተላልፋል።    ለማናውቀው ሰው፤ ውለታ መመለስ ለማይችሉ ምስኪኖች ደግ ስንሆን ከእነርሱ መልሰን ጥቅም እናገኛለን ብለን ሳይሆን ነፃ ፍቅር መስጠታችን ነው። ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ፍቅር ራስን መፈለግ አይደለም ይላል። (1ኛ ቆሮንቶስ 13:5)     ወዳጆቼ ፍቅራችን ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ ለሌሎች ደግ በመሆን ነው። ስለዚህ በሌሎች ላይ ማተኮርን ተለማመዱ። የእግዚአብሔርን ፍቅር በደግነት አሳዩ። ዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፍቅር የምትገልጡባቸው መድረኮቻችሁ ናቸው። ለደግነት ጊዜ አትጠብቁ፤ ለደግነት ስፍራ አትፈልጉ፤ ለደግነት ቀስቃሽ አትፈልጉ። እያንዳንዱን እድል ቸርነት ለማድረግ፤ እያንዳንዱን ጊዜና ቦታ ደግነትን ለመግለጥ ምክንያት አድርጉት። እግዚአብሔር ይባርካችሁ! አሜን ✍አዶኒ ሐምሌ 04/2014 ዓ.ም ይወዳጁን👉 @adonigospel @adonigospel
Показати все...