cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Більше
Рекламні дописи
1 356 686
Підписники
+66024 години
+3 8857 днів
+17 06330 днів
Архів дописів
" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች። የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ ሕግ ትላንት አጽድቋል። ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ፥ " በቀጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን " ብለዋል። ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል። 52,000 ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሩዋንዳ ይዘዋወራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቅርብ አመታት ፦ - #ከአፍሪካ ፣ - ከመካከለኛው ምስራቅ - ከኢስያ ጦርነት እና ድህነት የሚሸሹ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል። እነኚህ ስደተኞቹ በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በትንንሽ ጀልባዎች ተጉዘው ነው የሚገቡት። #ሮይተርስ @tikvahethiopia
Показати все...
😭 601 107😡 58👏 33🕊 28😱 26🤔 20🥰 14🙏 11😢 6
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አፏል። አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 " ጠሮ መስጂድ " አካባቢ ነው። ለሊት 11 ሰዓት ገደማ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ከላይ ወደ ታች (ወደ ቤቱ) ተንዶ 3 ክፍል ያለው ቤት ላይ አደጋ ደርሷል። በዚህም ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሟቾቹ ፦ ➡ የ4 ዓመት ህጻን ፣ ➡ ሶስት የ11 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች  ➡ ከ25 እስከ 30 ዓመት ያሉ 3 ወጣቶች ናቸው። ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ አደጋው የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ላይ ነው። መረጃው የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ነው። @tikvahethiopia
Показати все...
😢 1112😭 518 86😡 51🕊 28🙏 16😱 13🤔 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከፊታችን ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ጀምሮ ወደ ሶማሌ ክልል #ቀብሪደሃር ከተማ በሳምንት ሁለት ቀን የበረራ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል። አየር መንገዱ በሶማሌ ክልል ከጅግጅጋና ጎዴ ቀጥሎ #ቀብሪደሃር ሶስተኛው መዳረሻው ይሆናል። @tikvahethiopia
Показати все...
278👏 100🙏 13🤔 11🥰 8🕊 7😡 7😱 6😭 1
“ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” - አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዙራያው በሰፈሩ ሰዎች የታዘ መሬቱን ለማስመለስ የካሳ ክፍያ መጠየቁን አስታወቀ። በአማራ ክልል የሚገኘው ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ከ30,000 እስከ 50,000 የሚሆኑ ፀበልተኞች እንደሚጸበሉበት ይሁን እንጂ የገዳሙ መሬት ሰዎች ስለሰፈሩበት እንኳን ለጸበልተኞች ለመነኮሳቱም እጅግ በመጣበቡ፣ “ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” ተብሏል። የገዳሙ ይዞታ የጠበበው ከበርካታ ዓመታት ጀምሮ ለመፈወስ ወደ ስፍራው የሚሄዱ ፈውስ ያገኙ ጸበልተኞችና አርሶአደሮች ከሕመማቸው ከተፈወሱ በኋላ በገዳሙ መሬት ቤት እየሰሩ እዚያው በመኖራቸው መሆኑን የገዳሙ መነኮሳት አስረድተዋል። ሰዎቹ በአንድ ሳይሆን ቀስ በቀስ እዛው መኖር እንደጀመሩ ጠቁሟል።   በገዳሙ ይዞታ የሰፈሩ ከ250 በላይ አባውራዎች ይነሱ ዘንድ ለጠየቁት ካሳና ለሌሎች አገልግሎቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል። ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም በካፒታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ግብር እንደተዘጋጀ፣ በመሆኑም በውስጥም በውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እርብርብ እንዲያደርጉ ገዳሙ ጥሪ አቅርቧል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
🙏 717 121😭 61😡 33🤔 15😢 15👏 12🕊 6😱 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#SafaricomEthiopia መልካሙን ዜና ከሳፋሪኮም ሰምተዋል?! 🎁ዕለታዊ የዳታ ጥቅል ስንገዛ ቀኑን ሙሉ፣ ሳምንታዊ የዳታ ጥቅል ስንገዛ ሳምንቱን በሙሉ እንዲሁም ወርሃዊ የዳታ ጥቅል በምግዛት ወሩን ሙሉ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም መስመር በነጻ እንደዋወል! ዳታ እንግዛ! በነጻ እንደዋወል! የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ  እንጋብዛለን። 👉 Facebook 👉Telegram 👉 Twitter 👉Instagram 👉 YouTube
Показати все...
86😡 22🙏 9🥰 7👏 5🕊 2😱 1😭 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Addis Ababa University- Cisco Networking Academy @CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com Online Live class - Cybersecurity Training & Certification Preparation. Registration Date: April 22 to May 26, 2024 Class start date: May 27, 2024. Course Recognitions:- Trainees will receive 4 certificates of training completion; 4 digital badges & 32% discount for LPI Linux Essentials and 58% discount for CyberOps Associate Certification exam voucher. Mobile 0902-340070/ 0935-602563/ 0945-039478 Office : 011-1-260194 Follow our telegram channel: @CiscoExams
Показати все...
40🙏 6🕊 3🥰 2😱 2
#ቱርክ #ሶማሊያ ከጥቂት ወራት በፊት በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል የወታደራዊ ትብብር ስምምነት መደረጉ ይታወሳል። ይህ ስምምነት ተከትሎ የቱርክ ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ መድረሷን ቢቢሲ ዘግቧል። ሁለቱ አገራት ባለፈው የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ትብብር ለማድረግ ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል። የዚህ ስምምነት ዝርዝር ይፋ ባይሆንም ቱርክ የሶማሊያን ባሕር ኃይልን #ለማሠልጣን እና #ለማስታጠቅ እንዲሁም በአካባቢው ያለውን የባሕር ላይ ደኅንነት ለማስጠበቅ ተስማምታለች ተብሏል። በአንጻሩ ቱርክ ከሶማሊያ የባሕር የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ እንደምትሆን ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙ በቢቢሲ ዘገባ ላይ ሰፍሯል። @tikvahethiopia
Показати все...
490😡 312🤔 72😢 50🕊 29👏 24🥰 17🙏 17😭 15😱 4
" ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ፤ ይህም ይቀጥላል " - የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት የብሔራዉ የደኅንነት ምክር ቤት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባጋጠመ ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዳሉ ገልጿል። " እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው " ብሏል። " የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል " ሲልም ገልጿል። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል፤ #በራያ እና #አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው እየገቡ እንደሆነ አመልክቷል። በዚህ ሂደት " የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል " ብሏል። ም/ቤቱ እነዚህ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልጽ በስም ጠርቶ ባይገልጽም " ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ " ብሏል። " አንዳንዴም #በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። " ሲል ገልጿል። " መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል " ሲል አሳውቋል https://t.me/tikvahethiopia/87168?single @tikvahethiopia
Показати все...
😡 484 214👏 45🤔 23😭 22🕊 17🥰 11😢 9🙏 9😱 5
#Ethiopia ዛሬ የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ፤ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩን አሳውቋል። ይህ ተከትሎ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫ ፦ - ስለ ሀገራዊ ምክክር - ስለ ሽግግር ፍትሕ - ከመንግሥት ውጭ ታጥቀው ስለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች - ስለ ተሃድሶ ኮሚሽን - ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት - ስለ ህወሓት ታጣቂዎች - ስለ ተፈናቃዮች መመለስ ... ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተውበታል። ምክር ቤቱ፥ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሀገረዊ ምክክር ኮሚሽን በክልል ደረጃ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ ይጀምራል ብሏል። ሀገራዊው የምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል ሲል ገልጿል። ም/ቤቱ፤ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መፅደቁን አስታውሷል። እንደ አግባብነቱ፦ ° የወንጀል ምርመራ እና ክስ ° እውነት ማፈላለግ ° ዕርቅ ° በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት ° ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ ብሏል። " የመንግሥት አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም " መሆኑን ገልጾ በሀገራችን በተወረሰ የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል ብሏል። የሀገሪቱን ሰላም የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው ብሏል። " የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ " ሲል ገልጿል። ለዚህም የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም፦ ° መሣሪያ ማስፈታት ° የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ነው ብሏል። መንግሥት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበር ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበና የሚመጋገብ እንዲሆን ኃላፊነቱን ይወጣል ብሏል። ምክር ቤቱ በመግለጫው፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል ሲል ገልጿል። የሰላም ስምምነቱ ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ ውሳኔ እንደሆነ ገልጿል። የሰላም ስምምነቱ እስካሁን ብዙ ውጤት እና እፎይታ ቢያስገኝም ቀሪ ሥራዎችም አሉ ብሏል። በተለይ በስምምነቱ መሠረት " የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው " ሲል ገልጿል። የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት ብሏል። " ካለፈ ስሕተተ አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው " ያለው ም/ቤቱ ፤ ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉ አሉ ሲል ጠቁሟል። እነዚህን ሁሉም ተባብሮ አደብ ማስገዛት ይኖርበታል ብሏል። " ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባል" ሲል አሳስቧል። ም/ ቤቱ ፤ መንግሥት በትግራይ ክልል አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ እንደሆነ ገልጿል። " ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም " ብሏል። " በፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትና በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንደ ሀገር የሚኖረው አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው ክልሎች በክልል ከፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም " ብሏል። በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታትና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስቧል። ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል። ያንብቡ👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-24 (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
Показати все...
😡 579 290🕊 58🤔 31🙏 22😢 16😱 15👏 12🥰 11😭 5
#Update ቀሲስ በላይ መኮንን በሃሰተኛ ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። በተጠረጠሩበት ወንጀል ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል። ከእሳቸው ጋር ሌሎች ሁለት ግለሰቦች (ያሬድ ፍስሃ እና ጣባ ገናና ) ቀርበዋል። ከዚህ ቀደም ለፌዴራል መርማሪ ፖሊስ 7 ቀን መሰጠቱ ይታወሳል። በዚህ ጊዜ መርማሪ ፖሊስ ምን እንደሰራ አስረድቷል። ፖሊስ ምን አለ ? - " የምስክሮችን ቃል ተቀብያለሁ። " - " በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም ጠይቂያለሁ። " - " የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። " - " ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለአፍሪካ ህብረት የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሰጠኝ ጠይቂያለሁ። " - " ተጠርጣሪዎቹ በስማቸው የሚገኙ ሂሳቦችን ለማጣራት ማረጋገጫ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። " - " በወቅቱ የነበረ የካሜራ ቅጂ ጠይቂያለሁ። " - " ለወንጀል ተግባር የዋለ ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ከሚመለከተው ተቋም ጠይቂየለሁ። " - " በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ አድርጌ በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራሁ ነው። " ... ብሏል። የቀሩ ስራዎች ፦ - " ከተለያዩ ተቋማት የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ። " - " ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል። " - " ግብረአበሮችን ተከታትሎ መያዝ። " - " ተጨማሪ ሀብት የማፍራት ተግባሮች ላይ የማጣራት ስራ መስራት ሌላም ሰፊ የምርመራ ስራ ስለሚያስፈልግ ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ " ብሏል። የተፈጸመው ድርጊት " ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ጥላሸት የሚቀባ ተግባር ነው " ብሏል። ተጠርጣሪው ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ነው የቀረቡት። ጠበቆቻቸው ምን አሉ ? ° " ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያቶች ደንበኞቻችን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም " ብለዋል። ° " ቀሲስ በላይ የተገኘው የጦር መሳሪያ ህጋዊ ነው። ሀብት ማፍራት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ሊገናኝ አይገባም " ብለዋል። ° " የሃይማኖት አባት መሆናቸው ፣ የልማት ስራ አስተባባሪ በመሆናቸው ፣ ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ ቢወጡ ከመንግስት ተቋማት የሚመጡ ማስረጃዎችን የማጥፋት አቅም የላቸውም " ብለዋል። ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። ቀሲስ በላይ መኮንን ምን አሉ ? ➡ ወንጀል አለመፈጸማቸውን ገልጸዋል። ➡ ለሀገር እና ለፖሊስ ተባባሪ መሆናቸውን ገልጸዋል። " ምሽት ላይ #እቤቴ እየሄድኩ ጠዋት ልምጣላችሁ " በማለት ፖሊስን መጠየቃቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል። ➡ አብረዋቸው የታሰሩት ሹፌራቸውና አጃቢያቸው እንደሆኑ ገልጸው ምንም የወንጀል ተሳትፎ በሌለበት ሁኔታ ከኔ ጋር ተጨማሪ ጊዜ በእስር ማቆየት ተገቢ አይደለም በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ቢወጡ ማስረጃ ሊሰወር ይችላል በማለትም የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል። የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ( ኤፍ ቢሲ) መሆኑን ያሳውቃል። @tikvahethiopia
Показати все...
👏 718 176😱 64🤔 43😢 37🕊 27😭 26🙏 24😡 18🥰 4
#Update ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " #አራ " ከሚባል ስፍራ 77 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መገልበጧ መገለጹ ይታወሳል። በዚህም አደጋ የ5 ዓመት #ሕጻናት እና #ሴቶችን ጨምሮ 16 ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ መገለጹ አይዘነጋም። የIOM የጅቡቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ታንጃ ፓሲፊክ ፤ የሟቾች ቁጥር ቀደም ሲል ከሰጠው መረጃ ማለትም 16 ከፍ ማለቱንና 21 መድረሱን ተናግረዋል። የሞቱት ሁሉም #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጸዋል። 23 ሰዎች አሁንም ድረስ የት እንደገቡ እንኳን አይታወቅም ብለዋል። 33 ሰዎች ከአደጋው እንደተረፉ ገልጸዋል። ይህ አደጋ #38_ኢትዮጵያውን ከሞቱበት አደጋ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተከሰተ ነው። በርካታ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ህይወታቸውን ለመቀረ ሲሉ በአደገኛው እና ህገወጥ በሆነው መንገድ ሀገራቸውን ጥለው ይሰደዳሉ ፤ በዚህም ህይወታቸውን ባህር ላይ ያጣሉ ፣ ይታሰራሉ፣ በየበረሃው ይንገላታሉ ፣ በደላሎች ታግተው ይሰቃያሉ ። ሀገር ጥለው በህወጥ መንገድ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም። @tikvahethiopia
Показати все...
😭 853😢 106 59🙏 17🥰 11😡 10🕊 5😱 4
#Update ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " አራ " ከሚባል ስፍራ 77 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መገልበጧ መገለጹ ይታወሳል። በዚህም አደጋ የ5 ዓመት ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ 16 ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ መገለጹ አይዘነጋም። የIOM የጅቡቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ታንጃ ፓሲፊክ ፤ የሟቾች ቁጥር ቀደም ሲል ከሰጠው መረጃ ማለትም 16 ከፍ ማለቱንና 21 መድረሱን ተናግረዋል። የሞቱን በሙሉ #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጸዋል። 23 ሰዎች አሁንም ድረስ የት እንደገቡ እንኳን አይታወቅም ብለዋል። 33 ሰዎች ከአደጋው እንደተረጉ ገልጸዋል። ይህ እጅግ አሰቃቂ አደጋ 38 ኢትዮጵያውን ከሞቱበት አደጋ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተከሰተ ነው። በርካተ ወጣቶች ህይወታቸውን ለመቀረ ሲሉ በአደገኛው እና ህገወጥ በሆነው መንገድ ሀገራቸውን ጥለው ይሰደዳሉ፤ በዚህም ህይወታቸውን ባህር ላይ ያጣሉ፣ በደላሎች ታግተው ይሰቃያሉ። ቁጥሩ ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም። @tikvahethiopia
Показати все...
#Update የአሜሪካ #ሴኔት በመላው አሜሪካ " ቲክቶክ" ን ሊያግድ የሚችል አዋጅ ትላንት ለሊት አጽድቋል። ከቀናት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት " ቲክቶክ " እንዲታገድ ረቂቅ ሕግ ማጽደቁ ይታወሳል። ትላንት ለሊት የአሜሪካ ሴኔት ተሰብስቦ " ቲክቶክ " ከቻይና ካልተፋትና ድርሻው በ9 ወር ውስጥ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያግድ አዋጅ አጽድቋል። ቀጣዩ ሂደት ፕሬዜዳንቱን ይመለከታል። ይህ አዋጅ ወደ ፕሬዝዳንት ጆ  ባይደን የተመራ ሲሆን እሳቸው ቀደም ሲል " ይህ አዋጅ እኔ ጋር ይድረስ እንጂ ፊርማዬን አኑሬበት ሕግ ሆኖ ይተገበራል " ብለው ነበር። አሁን አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮ ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " የመታገዱ ነገር እውን እየሆነ የመጣ ሲሆን ሂደቱ ረጅም ወራትን ሊወስድ ይችላል። በሌላ በኩል ፥ ሴኔቱ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል አፅድቆታል። @tikvahethiopia
Показати все...
👏 738😡 200 67😱 36🙏 23🤔 20🕊 19😭 19😢 17🥰 13
" ሕግ ፊት እናቀርበዋለን " - ፌዴራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፤ በሃይማኖታዊ ስፍራ ላይ ጥይት ወደ ላይ ሲተኩስ የነበረው አባሉ በቁጥጥር ስር እንደሚኝ ገልጿል። ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሰ ግለሰብ በቤተክርስቲያን ውስጥ እየተዘመረ በነበረበት ሰዓት ወደ መድረክ ወጥቶ በተደጋጋሚ ሲተኩስ የሚያሳይ ቪድዮ ተሰራጭቷል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባሉ ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ እንደሚባል ገልጿል። ክስተቱ የተፈጸመው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተላከበት ወቅት መሆኑን አመልክቷል። " ጥር 5/2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት ነው የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ የነበረው " ያለው ፖሊስ ይህ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ ነው ብሏል። አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ አመልክቷል። ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት ያቀርበዋል ሲል አሳውቋል። @tikvahethiopia
Показати все...
😡 1282👏 883 118🙏 61😢 41🕊 33😭 28🤔 24😱 9🥰 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ሴጅ_ማሰልጠኛ የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም 20ኛ ዙር የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ይጀምራል። ቀድመው ይመዝገቡ! 👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና 👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ 👉 ከ15 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት 👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት ስልክ፦ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
Показати все...
23🙏 13😱 4🕊 3😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች  ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
Показати все...
30😱 4🥰 3🙏 3😢 2🕊 1😭 1
#እንድታውቁት #ሀዋሳ #ክልከላ በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ ባለ ሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና የሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር #ተከለከለ። ሰሞኑን በሀዋሳ ከመዝናኛ መልስ እየደረሰ ያለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሲባል ከምሽቱ 3:00 በኃላ ባለሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪው ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦ °  ምክንያት ? °  ክልከላው ለምን አስፈለገ ? ° በማህበረሰቡ የእለት ተእለት ህይወትስ ላይ የሚያሳድረዉ ጫና አይኖርም ? ወይ ስንል ኢንስፔክተሩን ጠይቋል። ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፤ " ሁሉንም ያደረግነው ለማህበረሰቡ ደህንነት ነው " ብለዋል። " አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እየተስተዋለ ነው " ሲሉ ገልጸው ከአደጋዎቹ አብዛኛዉ በባለሦሰት እግር ባጃጅና በባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል የሚደርስ እንደሆነ አስረድተዋል። " በዚህ አመት ብቻ በምሽት በሞተር ሳይክል የደረሰዉ አደጋ የሚያስገርም ቁጥር ያለው ነው " ያሉት ኢስፓክተር ተስፋዬ በቁጥር ስንት ? የሚለውን ወደፊት ዳታውን አጠናቅረዉ ለማህበረሰቡ የማሳየት እቅድ እንዳለቸዉ ጠቁመዋል። ከአደጋዎቹ ውስጥ በአብዛኛው የሚከሰቱት በምሽት መሆኑን ጠቅሰው ፤ " ጠጥቶ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር  ትልቁ ምክኒያት ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም በመንግስት ሞተር ሳይክሎች ሳይቀር ሶስትና ከዚያ በላይ ሆኖ መንቀሳቀስ አደጋ እየፈጠረ ነው ይህን ችግር ለመቀነስ ሲባል #ክልከላው ወጥቷል " ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ፤ " የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የወንጀል መፈጸሚያ እየሆኑ ነው " ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ " ለአብነት ኮንትራት ተብለዉ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ እና የሌሎችም ወንጀሎች ምንጭ ሆነው ተገኝተዋል " ብለዋል። " ጥንቃቄ ለራስ በመሆኑ ማህበረሰቡ ለራሱ ሲባል የወጣዉን ክልከላ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ " ሲሉ አሳስበዋል። " እለት ተእለት የሚከሰተው ዘግናኝ የትራፊክ አደጋ እንዲቆም የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል " ብለዋል። ክልከላው የሚያበቃበትን ጊዜን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም። #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
Показати все...
👏 663 174😡 149🤔 63🙏 39🕊 25😭 19😢 17😱 13🥰 12
“ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ” - ነዋሪዎች በኮሬ ዞን ፤ #በታጣቂዎች አማካኝነት ንጹሃን ላይ የሚደርስ ጥቃት በእርቀ ሰላም ተፈቶ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ከ4 ወራት ወዲህ በማገርሸቱ የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል። ባለስልጣናቱና ነዋሪዎቹ ለድርጊቱ  የ " ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች " ን ተጠያቂ አድርገዋል። የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ ምን አሉ ? ➡️ “ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች በቀጠናው ላይ ገብተው 4 ሰዎችን በአንድ ቀን ገድለዋል። ” ➡️ “ የመንግሥት መዋቅር እዛ አካባቢ ላይ Functional ስላልሆነ ኦነግ ሸኔ በነጻነት ተንቀሳቅሰው በቀጠናው ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ። ” ➡️ “ እርቅ ተፈጽሞ ከኀዳር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ወዲህ ከጉጂ ዞን ጋ መልካም ግንኙነት ተፈጥሮ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከ4 ወራት ወዲህ ታጣቂዎቹ እንደገና ጥቃት እያደረሱ ነው። ” ቃላቸውን የሰጡን የቆቦ ቀበሌ ነዋሪ ምን አሉ ? 👉 “ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ተገድለዋል። 4ቱ የቆቦ ቀበሌ ነዋሪዎች እሁድ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከብት በሚጠብቁበት ነው የተገደሉት። " 👉 “ከዚያ በፊት ዳኖ ቀበሌ 2 ሰዎች ተገድለዋል። ሌላም የሞተ አለ። ” 👉 “ ታጣቂዎቹ #ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ጥቃት ያደርሱ ነበር በዚህም ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ” 👉 “ በ2015 ዓ/ም እርቅ ተፈጽሞ ጥቃቱ ቆሞ ነበር። ከወራት ወዲህ ጥቃቱ አገርሽቶ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ” 👉 “ በቆቦ ቀበሌ እርቁ ከተፈጸመ ወዲህ ብቻ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ” ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን አካል ምን አሉ ? ▪️ “ በቀን 08/08/2016 የሁለት አርሶ አደሮች ሕይወትም አልፏል። እስከ ሚያዚያ 8/2016 ብቻ 19 ንጹሐን ከህዳር 1/2015 ዕርቅ በኋላ ተገድለዋል። ” ▪️ “ ከ19ኙ ሟቾች በተጨማሪ እሁድ ሚያዚያ 13 በቆቦ ቀበሌ፦ - ተመን እንግዳ ሶልዳንቶ - ይርጋ ሚትኩ ሶልዳንቶ  - ነብዩ ቡና - አባይ ፍቅሬ የተባሉ ሰዎች ተገድለዋል። ” ▪️ “ ንጹሐንን የገደሉ ለሕግ ይቅረቡ። ” ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
😢 297😭 112 92🕊 37😡 24🙏 15😱 9🤔 8🥰 7👏 6
" ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው " - ህወሓት ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድር እያደረገ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር። ህወሓት ግን " ይህ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው " ብሏል። ህወሓት ፥ " ከብልጽግና ጋር በተከታያይ እየተካሄደ ያለው ውይይት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው " ሲል ገልጿል። ከብልጽግና ፓርቲ ጋር #መሰረታዊ የሆነ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳለው የገለጸው ህወሓት ፤ " ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች አሉ " ብሏል። " ህወሓት ከብልጽግና ጋር ሊቀላቀል / ሊዋሃድ ንግግሮች ተጀምረዋል " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው ሲል አሳውቋል። @tikvahethiopia
Показати все...
👏 956😡 175 151🕊 146🤔 72😱 37🙏 32🥰 29😢 27😭 13
" የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል " - በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጀልባ መገልበጥ አደጋ #የ16_ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲጠፋ አብረው የተሳፈሩ 28 ዜጎችን እስካሁን ማግኘት አልተቻለም። ትላንት ምሽቱን ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " አራ " ከሚባል ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ " ጎዶሪያ " በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን ድረስ የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል። እስካሁን አብረው ተሳፍረው የነበሩት ውስጥ 28 ፍልሰተኞችን ማግኘት እንዳልተቻለ እና 1 ሴትን ጨምሮ 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። ከ2 ሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በደረሰ አደጋ የ38 ፍልሰተኛ ዜጎች ሕይወት አልፎ ነበር። ከጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው የዜጎችን ሕይወት እያሳጣ እንደሆነ በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል። በዚህም ዜጎች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለከፋ አደጋ እየዳረጉ ይገኛሉ ብሏል። ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ እና የፍትህ አካላትም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ከገጠራማ የአገራችን አካባቢዎች ዜጎቻችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል። @tikvahethiopia
Показати все...
😭 625 78😢 39🕊 11😱 9🤔 6🙏 4🥰 3