cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Більше
Рекламні дописи
1 341 538Підписники
-17824 години
+2 7687 днів
+25 84930 днів
Архів дописів
#ጥንቃቄ🚨 " ማህበረሰቡ ያለበትን #የቤት_እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ - ቴሌኮም ጋር በመተባበር 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው " እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም #ሀሰተኛ ነው። በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወረው መልዕክት አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን #ለማጭበርበር የፈጠሩት ነው። " ሼር ብቻ እያደረጋችሁ የቤት ባለዕድለኛ ሆኑ ፣ ተሸለሙ " የሚሉት መልዕክቶች በሁለቱም ተቋማት እውቅና የሌላቸው የአጭበርባሪዎች ስራ ናቸው። " ቤት ታገኛላችሁ ሼር አድርጉ " እንዲህ የሚባል ነገር የለም። ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፤ መሰል #በውሸት የተሞሉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን እንድትጠነቀቁ ከዚህ ቀደም በዛ ያሉ መልዕክቶች ተለዋውጠናል ፤ በቂ እውቀትም አላችሁ። ምናልባት እንዲህ ያለን ሀሰተኛ መልዕክት አምኖ የሚጭበረበር ወዳጅ ዘመንድ እንዳይኖራችሁ አስገንዝቧቸው። #TikvahFamily @tikvahethiopia
Показати все...
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉም አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትም ፈተና በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብሏል። ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጿል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸው ተገልጿል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ተብሏል። #MoE @tikvahethiopia
Показати все...
" ኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ይሻል። መፍትሄ እንሻለን " - የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ  የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የስራ ግብር እንዲቀነስ ፤ የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ከኑሮ ውድነቱ አንፃር የዘገየው የሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እና የግብር ቅነሳ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። " አሁንም #በቀን_አንድ_ጊዜ ብቻ በልቶ ለመዋል የሚቸገር ሰራተኛ ነው ያለው " ያሉት አቶ ካሳሁን ሰራተኛው ካለው ገቢ አንፃር ችግሩ የሰፋ እንደሆነ አስረድተዋል። እነዚህ ጥያቄዎች #በአዎንታዊ_መልኩ መታየት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። አቶ ካሳሁን " ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል በሚመለከት ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የሚወስን ቦርድ የሚቋቋምበት ደምብ ላይ ጥናት ማድረጋቸውን በቅርቡ አሳውቀውናል " ሲሉ ተናግረዋል። የኑሮ ውድነት በጣም አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ሰራተኛው ችግር ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ " ትክክለኛ ግብር ከፋይ ሰራተኛው ነው። ለመንግስት ቀኝ እጁ በሚከፍለው ግብር ሰራተኛው ነው። የግብር ቅነሳው አንድ እና ሁለት የለውም ዘግይቷል " ሲሉ ጠቁመዋል። አቶ ካሳሁን ፤ ሚያዚያ 23 ቀን በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በሚከበረው ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን (ሜይዴይ) አዳራሽ ውስጥ እንደሚከበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል። " አሁንም ቢሆን ባልተመለሱልን ጉዳዮች ላይ ነው የምንወያየው። የቀኑ መሪ ቃል ' ለሰላም እና ለኑሮ ውድነት መፍትሄ እንሻለን ' የሚል ነው  ብለዋል። " የሰላም ችግር አለ። ሰራተኞች በአንዳንድ ቦታዎች ይታገታሉ ፣ ይሞታሉ " ያሉት አቶ ካሳሁን ፎሎ ፤ " ይሄ እስከ መቼ ይቀጥላል ? ማንኛውም ማህበረሰብ ላይ እንደሚደርሰው ጉዳት ሁሉ ሰራተኛውም ላይ እየደረሰ ነው ፤ ስለዚህ ለሰላም መፍትሄ መምጣት አለበት " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
#ICS የሕዝብ ተ/ም/ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ9 ወር አፈጻጸም ትላንት ገምግሟል። ኮሚቴው ከዚህ ግምገማ በፊት ማለትም ሚያዚያ 3/2016 ላይ #ድንገተኛ ምልከታ አድርጎ ነበር። ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ? - ምንም እንኳ የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና የተገልጋይን ቅሬታ መፍታት አልተቻለም። - ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ብለው በሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ምክንያት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ በድንገተኛ ምልከታ መመልከት ተችሏል። - በዋና መ/ ቤቱ ተገልጋይ በተቋሙ ሠራተኞች ፦ ➡️ #መሰደብ፣ ➡️ #መመናጨቅ ➡️ #መገፍተር_ጭምር የሚደርስበት በመሆኑ ተገልጋይ በሥነ ምግባር መስተናገድ አለበት። - በአዲስ አበባ " ካሳንቺስ አካባቢ " የሚገኘዉ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ምቹ ያልሆነ እና የንጽህና ጉድለት ያለው ነው። ይህ መታረም አለበት። - ዋናው መስሪያ ቤት ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ፣ ሕንፃው የቆየ እና አስፈላጊዉን የማሻሻያ ጥገና ያላገኘ ነው። ሕንፃው ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስሪት ያለው ነው። - በዋና መስሪያ ቤት ያለው መጨናነቅ እንዲቀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ከአምስት ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ የመፍትሔ ሃሳብ ቢሰጥም አልተፈጸመም። በተለይ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማስፋፋት ሥራዎች መሠራት አለበት። - የደላላ ሰንሰለት በመለየት ማቋረጥ ያስፈልጋል። - አሁንም ከደላሎች ጋር የሚመሳጠሩ የተቋሙ #ሠራተኞች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት። - የሠራተኛ ባጅ አለመኖሩም ሊታሰብበት ይገባል። በምክር ቤቱ የተገኙት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል። ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/EPA-04-27-2 #EPA @tikvahethiopia
Показати все...
#Update በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ጀርመን ኤምባሲ አካባቢ የሚገኘውና በ1979 ዓ/ም ለ “ አዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ቤት ሥራ ማኀበር ” ተሰጥቶ ነበር የተባለ 1,500 ካ/ሜ መናፈሻ መሬት የመከነ ማስረጃ ባቀረቡ ሰዎች መታጠሩን ማኀበሩ መግለጹን መረጃ አጋርተናችሁ ነበር። ከዚያ ወዲህ ምን ተፈጠረ ? የማኀበሩ አባላት ትላንት (ዓርብ ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ/ም) ከምሽቱ 3 ገደማ በሰጡት ቃል፣ “ ጨለማን ተገን አድርገው የግንባታ እቃዎች አስገብተዋል ” ብለዋል። “ ደንቦች ቢባል፣ ሰላምና ጸጥታ ቢባል ምንም ሊፈይድልን አልቻለም። አሁን ለሕይወታችን ሁሉ እየፈራን ነው። የ70 ዓመት አረጋዊ ገፍትረው ጣሉ አታስገቡም ብሎ ሲከለክላቸው ” ሲሉም ወቅሰዋል። የጸጥታ አካላት መፍትሄ እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ፈቃደኛ እንዳልሆኑላቸው ገልጸው፣ “ የለፋንበት፣ ወጪ ያወጣንበት ቦታ ነው። ኃላፊነት የጎደለው ነገር እየተሰራ ነው ” ብለዋል። ታጠረ የተባለው ግሪን ኤሪያ ጀርመን አደባባይ አካባቢ የተባበሩት ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 300 ሜትር ገባ ብሎ መሆኑን አመላክተዋል። ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቅናቸው አንድ የደንብ ማስከበር አካል፣ ጉዳዩን በዝርዝር ከሰሙ በኋላ ምላሽ ለመስጠት የማይመች ቦታ ላይ እንደሆኑና ከቆይታ በኋላ እንዲደወል ቢጠይቁም ፣ በድጋሚ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
😡 1
ከባንክ ወደ M-PESA ገንዘባችንን እናስተላልፍ እስከ 50ብር ሽልማት እናግኝ! M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ! 🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል! #MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
Показати все...
1
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች  ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
Показати все...
11😱 4👏 1
#RoseWood ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ ሼልፎችን ከሮዝዉድ ፈርኒቸር  ይዘዙ 👌 ለ ወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉልን  🙌 ሮዝዉድ ፈርኒቸር  📲 0905848586 ኣድራሻ  :  📍4ኪሎ ኣምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ                   📍 እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል Showroom Location 👇 https://goo.gl/maps/X6Q2exa7dfvjBPvWA ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ  👇 https://t.me/R0seWood https://t.me/R0seWood
Показати все...
" ... ትጥቅ ሙሉ በሙሉ የማስፈታት ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው " - አቶ ኢያሱ ተስፋይ ከቀናት በፊት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፥ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከመከረ በኃላ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በመግለጫው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ብዙ ውጤቶች እና እፎይታን ያስገኘ ቢሆንም አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር። ከነዚህ ቀሪ ስራዎች አንዱ የ ' ህወሓት ' ትጥቅ መፍታት እንደሆነ ጠቁሞ ፤ " በሰላም ስምምነቱ መሰረት ህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ፤ በብሄራዉ ተሃድሶ ኮሚሽን እቅድ መሰረት በፍጥነት መተግበር አለበት " ብሎ ነበር። በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ህወሓት በስምምነቱ መሰረት " ከኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ / የፌዴራል ጸጥታ ኃይል ውጭ ያለ ማንኛውም ኃይል ከትግራይ የአስተዳደር ወሰን እንዲወጡ መደረግ አለበት " ብሏል። የህወሓት የፕሮፖጋንዳ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ኢያሱ ተስፋይ ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥  " ' ለዘላቂ ሰላም ትጥቅ መፍታት አለባቸው የሚለው ችግር የለውም እንደ ትግራይ ህዝብ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻችን ከተመለሱ ወደ ልማት እና ወደ የዴሞክራሲ ግንባታ ስራችን መሸጋገር እንፈልጋለን " ብለዋል። " ለሰላም ከማንም በላይ ጥብቅና እንቆማለን ስትራቴጃካዊ ፍላጎታችን ነው ግን ደግሞ ያ ሰላም ከጥያቄዎቻችን መመለስ ጋር በቀጥታ መያያዝ አለበት እንጂ ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ መብታችን ሳይከበር ዝም ብሎ ሰላም የሚመጣ ነገር አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል። " ለሰላም ብለን ቀደም ብለን ትጥቅ ማስፈታት ጀምረናል። የከባድ ማሳሪያም ርክክብም ከአመት በፊት አድርገናል፣ ከዛ አልፎ ከነበረን ሰራዊት በርካታውን demobilize አድርገናል ፤  " ሲሉ አክለዋል። " ትጥቅ #ሙሉ_በሙሉ_የማስፈታት_ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ከፌዴራል ኃይል ውጭ ያሉ የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ አሉ ህዝባችንን ለብዙ መከራ እየዳረጉ ያሉ በጸለምትም ፣ በደቡብ ትግራይም ስለዚህ አሁን ፌዴራል በጀመረው ነገር እነዚህን ኃይሎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱና ወደ ሌላ ስራቸው እንዲሄዱ የማድረግ ኃላፊነት አለበት " ብለዋል። ለDDR የሚያስፈልገው ሁሉ በጀትም መመደብ አለበት ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልጸዋል። @tikvahethiopia
Показати все...
106😡 49🕊 20👏 15🙏 6😭 5😱 2
“... ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም ” - አቶ ንጋቱ ማሞ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፥ በከተማው በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ዘንድሮ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነተ ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ? - “ ከተማው ውስጥ ብዙ የግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ። በተለይ አሁን ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት በኮንክትራክሽን / በግንባታ ዘርፉ ያሉ የቀን ሠራተኞች ናቸው። ” - “ የቀን ሠራተኞች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ብዙ ጊዜ ጉልበታቸውን ነው ይዘው የሚገቡት፤ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ቴክኒካል እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የላቸውም።  እንዴት የሥራ ላይ አደጋን መከላከል እንደሚችሉ ስለጠና እንኳ አይሰጥም። ” - “ ' #የቀን_ሠራተኞች_እንፈልጋለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችን የኮንስትራክሽን ሳይቶች ላይ እናያለን። በዚያው ሥራ ያጣ መንገደኛ ይገባል ግን ሥራውን ለመከናውን ምን ሊያጋጥም ይችላል ? ብሎ አስቀድሞ የመገመት እውቀት አይኖርም። ” - “ ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች ላይ ትልቁ ኃላፊነት ይወድቃል። እነርሱ ደግሞ በሚፈለገው ደረጃ ለዘርፉ ትኩረት እየሰጡ አይደለም። አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም። ” - “ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የደህንነት መርሆዎችን ያለመከተል ሁኔታ አለ። ” Q. መፍትሄውን ምንድነው ? - “ መፍትሄውማ ፈቃድ ሰጪው አካልም ፈቃድ ከሰጠ በኋላ በየጊዜው ጠብቅ ቁጥጥር በማድረግ ለአደጋ የተጋለጡ አሰራሮችን እየለዩ በህንጻ አዋጁ መሠረት እርምጃዎችን ቶሎ ቶሎ መውሰድ ያስፈልጋል። ” ሰሞኑን የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የድንጋይ እና አፈር ናዳ አደጋ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች ላይ ባለመድረሱ ለየት ያለ ቢሆንም ይህንኑ አደጋ ጨምሮ በ2016 ዓ/ም እስካሁን 12 ሰዎች በተለያዩ ጊዜዎችና አደጋዎች ሞተዋል። የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጨምሯል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @thikvahethiopia
Показати все...
“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናት ልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዟቸው ተማጽኑ። ወ/ሮ መባ አላምረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሊያ የ3ኛ ክፍል ተማሪ 2ኛ ልጄ ናት። #ልቧ 15 ሚሊ ሜትር #ክፍተት አለው ” ብለዋል። የልብ ስፔሻሊቲ ዶክተርም፣ “ ‘ችግሩ ክፍተት መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን የቀኝ ልቧ አቅጣጫውን በመሳት ወደ ሳምባዋ ክፍል ደም እየረጨ ነው። ሳምባዋም ወደ ማበስበስ ደረጃ እየደረሰ ነው። በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት’ ” እንዳሏቸው አስረድተዋል። “ በፊት ላይ ‘#የሳንባ #ምች ነው’ እየተባለ ነበር። አሁን ‘የልብ ክፍተት ነው’ ተባለች። #እጇንም #እግሯንም #መሸምቀቅ ጀመራት። ትምህርቷን አቋርጣ ቤት ከተቀመጠች 1 ወር ሆናት ” ብለዋል። “ ‘ሳንባዋ ለንቅለ ተከላ የሚደርስ ነው’ አሉኝ ” ያሉት እኝሁ እናት፣ ለሰርጀሪው ብቻ 595 ሺሕ ብር፣ የሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ 700 ሺሕ ብር ለቀዶ ጥገና እንደተጠየቁ አስረድተዋል። የታዳጊዋ እናት፣ “ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ። ሁሉም ያቅሙን በገንዘብም በጸሎትም እንዲተባበረኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳኝ እለምናለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል።  እናት መባ አላምረውን በስልክ ለማግኘት በ +251939665539 መደወል ይቻላል። የባንክ የሒሳብ ቁጥራቸው 1000470071536 ነው። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Показати все...
" የፀጥታ አካላት ነን ፤ #በወንጀል_ትፈለጋለህ " በማለት አስፈራርተው ከኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ ገንዘብ የተቀበሉ ግለሰቦች በእስራትና ገንዘብ መቀጣታቸው ተነገረ። የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው። ተከሳሾች ፦ 1ኛ. ጫላ መገርሳ፣ 2ኛ. ለሊሳ በቀለ፣ 3ኛ  ዳዊት ጉደታ፣ 4ኛ. ዮሃንስ ደረጄ 5ኛ  ብርቱካን ለታ ናቸው። ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በመጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ገፈርሳ ክ/ ከተማ አካባቢ በሚገኝ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ የሆነን የግል ተበዳይን " የፀጥታ አካላት ነን ፣ በወንጀል ትፈለጋለህ " በማለት መንገድ ላይ ያስቆሟቸዋል። በኃላም ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳይታይ አድርገው በስቲከር ሸፍነው ወደአዘጋጁት የቤት መኪና ውስጥ በማስገባት ወደ መልካ ናኖ ክ/ከ አንፎ ወደ ተባለ አካባቢ ይወስዷቸዋል። ከዚህም በኋላ የሞተ ሰው ፎቶ ለግል ተበዳዩ በማሳየትና በመሳሪያ በማስፈራራት ግማሽ ሚሊየን ብር እንዲያመጣና እንደሚለቁት ይገልጻሉ። ገንዘቡን ካልከፈለ ደግሞ " ወደ ጦር ኃይሎች እንወስድኃለን " በማለት ገንዘብ እንዲከፍል ያስፈራሩታል። ይህን ተከትሎ የግል ተበዳዩ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ 100 ሺህ እንዳለው ይገልጽላቸዋል። በዚህም ጊዜ 1ኛ ተከሳሽ ባለቤቱ በሆነችው በ5ኛ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ የግል ተበዳዩ 100 ሺህ ብር እንዲያዘዋውር ያደረገና ቀሪውን 400 ሺህ ብር እንዲያመጣ በማስጠንቀቅ ይለቁታል። በህገወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ደግሞ 5ኛ ተከሳሽ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ምንጩን ለመደበቅ በማሰብ በተለያዩ መጠኖች ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅም እንዳዋሉት የክስ መዝገቡ ያስረዳል። ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ያሉትን የሰው ምስክሮች ፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል። ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ስላልቻሉ ፍ/ቤቱ  የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል። በዚህም ፦ ➡ 1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፤ ➡ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ➡ 5ኛ ተከሳሽ በ1 ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኗል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ቢ ሲ (ታሪክ አዱኛ) መሆኑን ይገልጻል። @tikvahethiopia
Показати все...
#ኢትዮ_ቴሌኮም የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችን ይታወቃል። በማስከተል ምዝገባ በተጀመረባቸው ማዕከላት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተገኝተው አተገባበሩን ተመልክተዋል። በዚህም ወቅት ለምዝገባው አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸው እና የምዝገባ አገልግሎቱ በላቀ ፍጥነት መስጠት መቻሉን በተግባር መመልከት ችለዋል፡፡ አገልግሎቱ በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት የሚስፋፋ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ተገልጋዮች ስለዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ እንዲረዱ የማድረግ ሥራ በስፋት እንደሚከናወን ተነግሯል። ዜጎች በአቅራቢያቸው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንበትን የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከል ለማወቅ ቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ውስጥ የተካተተውን አዲስ የአቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ ዳታ በማብራት ብቻ በነጻ መጠቀም ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ፦ https://t.me/telebirr https://t.me/ethio_telecom #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #NIDP
Показати все...
12👏 4🤔 3😡 2🙏 1🕊 1
#አቢሲንያ_ባንክ ከዘመናዊ የATM ማሽኖቻችን ብር ለማውጣት ካርድዎን ወደ ማሽኑ በማስጠጋት እና የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት መገልገል ይችላሉ። አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ! #BoAATM #ATM #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #contactless #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
Показати все...
124👏 38😡 17🥰 14😭 8🕊 6😢 1
#ጥቆማ (ለተማሪዎች እና ለወላጆች) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወር የሚቆይ የAI ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጀቱን ገልጿል። በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ናቸው። ተማሪዎቹ ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን አለባቸው። ለተከታታይ 2 ወራት ለሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ። ስልጠናው የሚያተኩርባቸው ፦ ➡️ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ➡️ ሮቦቲክስ፣ ➡️ ፕሮግራሚንግ፣ ➡️ ማሽን ለርኒንግ ➡️ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT) እንደሆኑ ተገልጿል። በስልጠናው መሳተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች ፦ 👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8 👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ ላይ መመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪ እውቀትና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ፦ 👉 www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/ 👉 forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6 ላይ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። #AI #ETHIOPIA @tikvahethiopia
Показати все...
#Wolaita ➡ " መምህራኑ በተራበ አንጀት አንሰራም በማለት ስራ አቁመዋል " -  የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ➡ " መምህራኑ ወደስራ ያለተመለሱት የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ላይ በመሆናቸዉ ነው " - የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች መምህራን ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ስራ ማቆማቸው ተነግሯል። መምህራኑ በተለያየ ጊዜ ደሞዝ ሲዘገይና ሲቆራረጥ መቆየቱ ለስራቸው እንቅፋት ለህይወታቸውም አደጋ መሆኑን በመግለጽ ለሚመለከታቸዉ አካላት በተለያየ መልኩ ለመግለጽ ሲሞክሩ መቆየታቸውን ይገልፃሉ። ከነዚህ መምህራን ውስጥ አንዱ የሆኑት መምህር አሸብር ፤ እርሳቸዉና በዳሞት ገሌ ወረዳ ያሉ መምህራን በደሞዝ መቆራረጥና የእርከን ጭማሪ እጦት ምክኒያት ምሬት ውስጥ እንደገቡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በተደጋጋሚ የግማሽ ወር ደሞዝ ሲወስዱ መቆየታቸዉን የሚገልጹት መምህር አሸብር አሁን ላይ ጉዳዩ ለመምህራን በህይወት የመኖርና ያለመኖር መሆኑን ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንቱ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በተደጋጋሚ " ችግሩ ይቀረፍ " በማለት በደብዳቤም ሆነ በውይይት ባለስልጣናትን ስናናግር ቆይተናል ብለዋል። ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ መምህራኑ " በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም " በሚል ስራ ማቆማቸዉን ገልጸዋል። መምህራን በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸዉ ደሞዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን መዘግየቱን ተከትሎ ስራ እንዳቆሙ አስረድተዋል። " ችግሩ ከደሞዝም በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ማለትም የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን እድገት መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል " ብለዋል። በሌላ በኩል አሁን ላይ እንደ ሶዶ ባሉ ከተሞች ብቻ ደሞዝ መከፈሉ ወረዳ ላይ ካሉ መምህራን በላይ የገጠር ተማሪ ወላጆችን ልጆቻችን በዚህ ምክኒያት ከትምህርት ራቁ በሚል እያናደደ መሆኑን በመግለጽ ይህን አሳሳቢ ችግር የዞኑም ሆነ የክልሉ መንግስት በአፋጣኝ ሊቀርፈዉ እንደሚገባ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመምህራኑን ቅሬታ ተከትሎ ምላሽ እንዲሰጡ የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ ታደሰ ኩማን አነጋግሯል። እሳቸውም ፤ " ነገሩ እንደሚባለዉ ሳይሆን ክፍያዉ የዘገየዉ በ8 መዋቅሮች ብቻ ነው " ብለዋል። " አሁን ላይ ደሞዙ በመከፈሉ ችግሩ ተቀርፏል " ሲሉ ገልጸዋል። ለቀናት የዘገየዉ ደሞዝ ከተከፈለ በኋላ መምህራን በአመጽ ሳይሆን በነበረባቸዉ የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ምክኒያት ወደስራ አለመግባታቸውን አስረድተዋል። ከዚህ ዉጭ አንዴ ብቻ በተፈጠረ የደሞዝ እጥረት ለአንድ ወረዳ ብቻ ስልሳ ፐርሰንት እንደተከፈለ በመግለጽ ከዛ ውጭ ምንም አይነት የደሞዝም ሆነ የጥቅማጥቅም ችግር እንደሌለ ምላሽ ሰጥተዋል። #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
Показати все...
' በረራው እንዴት ጨመረ ? ' " ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራ መጨመር የሚገልጸውን መረጃ በእጅ ስልኬ ላይ ደረሶኝ አየሁት። እንዲያው ዝም ብሎ የሀገረ ውስጥ በረራ ጨመረ ብሎ የሚታለፍ መስሎ አልተሰማኝም። በእርግጥ አየር መንገዳችን ገቢ ማግኘቱ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም ሰዎችን በዚህ ያህል ልክ የአየር ትራንስፖርት እንዲጠቀሙ ያደረጋቸው ምንድ ነው ?  ብሎ ጥናት ማድረግ ይገባል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን የየብስ ትራንስፖርት ማድረግ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎችን የሚያሰጋ ሆኗል። በተለያየ ጊዜ የሚሰማው የእገታ ወንጀል ፣ ጥቃት ሰዎች ቅርብ ከተሞች ሳይቀር በአየር እንዲጓዙ እያደረጋቸው ነው። ለአብነት እኔ ከዚህ ቀደም ለስራ የግል መኪናዬን ይዤ ከከተማ ውጭ እስከ ድሬዳዋ ድረስ እየነዳው ሄጄ እመለስ ነበር ዛሬ ላይ ያን ለማድረግ አልችልም። የሆነ ነገር ብሆንስ ብዬ እፈራለሁ ስለዚህም በየጊዜው የአየር ትኬት መቁረጥ ግድ ብሎኛል። እኔ ስላለኝ ነው ይህ ያደረኩት አቅሙ የማይፈቅድ ደግሞ የግዴታ ሆኖበት የየብስ ይጠቀማል። እኔ እንኳን የማውቀው ብዙ ሰው ተቸግሮም ቢሆን በአየር ትራንስፖርት ለመጠቀም ሲገደድ ብዙ ጊዜ አይቻለሁ። ወደ ሰሜኑ ክፍልም ብንመለከተ ካለው ጸጥታ ጋር በተያየዘ ሰዎች ከየብስ ትራንስፖርት ይልቅ አቅማቸው ባይፈቅድ እንኳን ተቸግረው የአየር ትራንስፖርት ይጠቀማሉ። ስለዚህ የሀገር ውስጥ በረራ ቁጥሩ የመጨመሩ ብቻ ሳይሆን በዚህ ልክ እንዴት ሊጨምር እንደቻለ ምክንያቱ ቢታወቅ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። " (Ato Solomon K. Tikvah Family Addis Ababa) @tikvahethiopia
Показати все...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ገልጿል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡ ይህ መጠን ከ2015 ዓ.ም በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ ይኖረዋል። በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ " ካፒታል ጋዜጣ " አየር መንገዱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። @tikvahethiopia
Показати все...
😡 772 145😭 73🤔 52👏 39🕊 36😱 25😢 25🥰 12🙏 12