cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

TenaSeb - ጤና ሠብ

ሠላም- 👋 ይህ በጤና ዙርያ መረጃ የምታገኙበት ቻናል ነው:: ለበለጠ መረጃ 👉🏽 https://youtube.com/@tenaseb-?si=TAxp4fhX-YijtoJn

Больше
Рекламные посты
4 880
Подписчики
Нет данных24 часа
+57 дней
+6330 дней
Архив постов
Показать все...
👍 2
Attention Health Professionals! Enhance your career and make a meaningful impact by joining TenaSeb Media! We are seeking health professionals passionate about health education and media to be part of our dynamic team. If you’re interested, apply here: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf0XVjVjKUQSBloMsOMR2WRFjf7qQeL75c4q7WF3NIHkuQXag/viewform?usp=pp_url
Показать все...
ከማህፀን ውጭ እርግዝና መንስኤ ህክምና እና ቅድመ ጥንቃቄ - Dr. Zimare @tenaseb - Ectopic pregnancy https://youtu.be/tK9t-lyEOvY
Показать все...
በ "አራስ ቤት" ቆይታ ማወቅ ያለብሽ ነገሮች - ዶ/ር ፅዮን / Early days of motherhood- #mothersday https://youtu.be/DHjD3CCArFs
Показать все...
6👍 2
ከ ወሲብ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎችን ምንም እንኳን በግልፅነነት ለመነጋገር የተለመደ ባይሆንም በርካታ ሰዎች ለራሳቸው የያዙት ችግሮች አላቸው። በዚህ ቪድዮ ከ ዶ/ር ሸምስ ጋር የናንተን ጥያቄዎች አንስተን ተወያይተናል እንድትከታተሉ ጋበዝን። የ ስነ ሩካቤ ጥያቄዎች እና መፍትሄያቸው - ክፍል 1 / top questions about sexual and reproductive health - part 1 https://youtu.be/CPFSbFN52yk
Показать все...
👍 12
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።
Показать все...
👍 23 6👏 1
ሰላም ሴቶች እነዚህን ምልክቶች በእርግዝና ወቅት ብታዩ ችላ ማለት የለባችሁም። 👉🏼 ⚠️በእርግዝና ወቅት ችላ ማለት የማይገባን ዘጠኝ ምልክቶች | Nine signs that we should not ignore during pregnancy https://youtu.be/GLiRAelrIEc
Показать все...
👍 6 2
https://youtu.be/Ixzq6Ut4ETU?si=aoyYNGO1PeWiulck የዶር ዘይኑ ዙቤር የአጥንት ህምና ፈጠራውን ይከታተሉ 800 ላይ NG2 በመላክ ይምረጡት።
Показать все...
5
Фото недоступноПоказать в Telegram
Показать все...
6
Показать все...
👍 4
በቀዶ ጥገና ከወለድሽ በኋላ ማድረግ ያሉብሽ ጥንቃቄዎች 📌 ከቀዶጥገናው 48 ሰዓት በኋላ ቁስሉ መድረቅ ስለሚጀምር ሻወር መውሰድ ትችያለሽ። 📌 ከወሊድ በኋላ አነስተኛ የደም መፍሰስ ይኖራል ይህም እየቀነሰ እና እየነጣ ወደሚሄድ ፈሳሽ እየተቀየረ ይመጣል። ነገር ግን ከዚህ የተለየ መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ አይነት የደም መፍሰስ ካጋጠመሽ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ አለብሽ። 📌 ከቀዶ ጥገና በኋላ ሃኪም ፈሳሽ ነገር እንድትወስጂ ሲያዝዝልሽ እንደ ሻይ፣ አጥሚት ያሉ ቀላል ፈሳሽ መጠጦችን መውሰድ መጀመር ይኖርብሻል። ነገር ግን የታሸጉ ጋዝ ያላቸው መጠጦችን በዚህ ሰአት ባትወስጂ ይመከራል። 📌 ትኩሳት፣ የሆድ ውስጥ የህመም ስሜት፣ የተለየ ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ፣ እየጨመረ የሚሄድ የደም መፍሰስ ካስተዋልሽ ጊዜ ሳታባክኚ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ አለብሽ። 📌 ከወሊድ በኋላ የምትወስጃቸው መድሃኒቶች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ምክንያቱም ህፃኑ ጡት በሚጠባበት ወቅት ወደ ህፃኑ ስለሚተላለፉ እንዲሁም የወተት ምርት ላይ ተፅእኖ ሊፈጥር ስለሚችል። 📌 የተሰፋውን ቁስል እና አጠቃላይ የጤናሽን ሁኔታ ለማረጋገጥ በቀጠሮ ቀንሽ ሃኪም ቤት መሄድ ይኖርብሻል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 11
ኢንዶሜትርዮሲስ(Endometriosis) ኢንዶሜትርዮሲስ ምንድን ነው? ይህ ችግር ለወር አበባ መዛባት፣ መካንነት እንዲሁም በወርአበባ ወቅት ለሚከሰት ከፍተኛ ህመም(Secondary dysmenorrhea) መከሰት አንድ ምክንያት ሆኖ የሚጠቀስ የጤና እክል ነው። ይህ ችግር የሚከሰተው የማህፀን ግድግዳ የውስጠኛው ክፍል(Endometrial tissue)በተለያዩ ምክንያቶች ከማህፀን ውጭ ካለ ቦታው ወደሌሎች አካላት በሚሄድበት ጊዜ ነው። ለምሳሌ: እንደ ማህፀን በር(cervix), የእንቁላል አስተላላፊ ቱቦዎች( Fallopian tubes),እንቁልጢ(Ovary), ሳንባ፣ የሽንት ፊኛ እና የመሳሰሉ የሰውነት ክፍሎች ላይ ካለ ተፈጥሯዊ ቦታው ሲገኝ ነው። 📌የዚህ ችግር ትክክለኛ መንስኤው አይታወቅም። ምልክቶቹ 📌ይህ ችግር ያለባቸው ሴቶች: በወር አበባ ወቅት ሌላ የሰውነት ክፍል ላይ ደም መፍሰስ፣ በተደጋጋሚ የሚኖር የህመም ስሜት፣ እንዲሁም ለማርገዝ መቸገር ወይንም መካንነት ሊኖራቸው ይችላል። ምርመራው 📌ይህ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ የተለያዪ ምር መራዎች ይታዘዛሉ ከነዚህም ውስጥ: የአልትራሳውንድ፣ ኤምአርአይ(MRI) እንዲሁም ላፓራስኮፒ ምርመራ ተጠቃሽ ናቸው። ህክምናው 📌አንድ ሴት ኢንዶሜትርዮሲስ እንዳለባት በምርመራ ከታወቀ በኋላ የተለያዩ የህክምና አማራጮች አሉት እነዚህም: የመድሃኒት ህክምና ወይም ቀዶጥገና ናቸው። የህመም ማስታገሻዎች እና የተለያዩ አይነት የሆርሞን ማስተካከያ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። የመድሃኒት ህክምናው ለውጥ ካላመጣ ቀዶ ጥገና አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 4 1
ልጅ ከተወለደ በኋላ የሚያስፈልጉ እንክብካቤዎች 📌ጨቅላ ህፃናት እንደተወለዱ ለቅዝቃዜ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ወዲያው በፎጣ መጠራረግ እና መጠቅለል ያስፈልጋል። 📌 ተጨማሪ ሙቀት እንዲያገኙ ሌላ ችግር ካላጋጠመ በስተቀር እንደተወለዱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ጡት ማጥባት አስፈላጊ ነው። 📌 ከ ተወለደ ከ 24 ሰዓታት በኋላም ለብ ባለውሃ በስፓንጅ ውይም በፎጣ እየነከርሽ መጠራረግ ትችያለሽ የእትብቱ ቁስለት ቶሎ እንዲድን እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር ውሃ እንዳይነካው መጠንቀቅ አለብሽ። 📌ከዚህም በተጨማሪ ለክትባት ቀጠሮ በሚሰጥሽ ቀን ህፃኑን በመውሰድ ማስከተብ ይኖርብሻል። 📌ልጅሸ ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ ትኩሳት ካለው፣ ሰውነቱ ቢጫ የሚሆን ከሆነ፣ እትብቱ እየደማ የሚያስቸግር ከሆነ ወይም ለየት ያለፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ፣ በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ እና በማባበል ያለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ፣ በ 48 ሰዓት ውስጥ እንደ ካካ ነገር ምንም  የማይወጣው ከሆነ፣ በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ ፈፅሞ ችላ ሳትይ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 7
ጨቅላ ህፃናት ላይ እነዚህን ምልክቶች ስታዪ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ አለብሽ። 📌በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ እንዲሁም ምንም ነገር ባፉ አልወስድ ካለ። 📌ንቃቱ የቀነሰ ከሆነ፣ ለመጥባት እንዲሁም ለማልቀስ የሚደክመው ከሆነ 📌ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ ከሆነ እንዲሁም እያባበልሽውም ካለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ   📌ቆዳው እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ እንደሆነ ካስተዋልሽ።  📌 ከተወለደ በ 2 ቀናት ውስጥ ምንም ካካ ነገር ከሌለው፣ ሆዱ እየተነፋ የሚሄድ ከሆነ  📌እትብቱ የተቆረጠበት ቦታ የሚደማ ከሆነ እንዲሁም ሌላ ፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ 📌ጡት ሲጠባ የሚያቆራርጥ ከሆነ፣ ከንፈሩ እንዲሁም እጆቹ የሚጠቁሩ ከሆነ  እነዚህን ምልክቶች ካስተዋልሽ ቶሎ ልጅሽን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 4
ጥያቄ: የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምልክቶቹ ምንድን ናቸው? መልስ: የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምልክቶች እንደ በሽታው የደረሰበት ደረጃ ይለያያሉ። አንዳንድ ሴቶች ላይ ምንም  ምልክት ሳያሳይ መጥፎ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል። ዋና ዋና ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው : 📌ከወር አበባ ጊዜ ውጭ የሚኖር ውይም ከእርጣት በኋላ የማህፀን ደም መፋሰስ ወይም የወር አበባ ከተለመደው በተለየ መብዛት፣ ለረጅም ጊዜ መፍሰስ ወይም መዛበት 📌የተለየ ጠረን ያለው የማህጸን ፈሳሽ 📌ከግንኙነት በኋላ የሚኖር የደም መፍሰስ 📌በታችኛው የሆድ ክፍል የሚሰማ ህመም ፣ የወገብ ህመም 📌ሽንት ለመሽናት መቸገር ፣ የሽንት መጠን መቀነስ 📌የድካም ስሜት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ክብደት መቀነስ ወዘተ። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 9
Показать все...
👍 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአይረን እና ፎሌት እንክብሎችን መቼ ነው መጀመር ያለብኝ? * አንድ ነፍሰጡር ሴት ነፍሰጡር በመሆኗ ብቻ ለአይረን እጥረት ተጋላጭ ናት። ይህም የሚሆንበት ምክንያት ለፅንሱ እድሀት እና ኦክስጅን ተሸካሚ የሆኑ ቀይ የደም ህዋሳት ምርት አይረን ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። * ከአይረን በተጨማሪም ቫይታሚኖች ለፅንሱ የስርአተ ነርቭ እድገት እንዲሁም ለእናቲቱ በሽታን የመከላከል አቅም ለማዳበር፣ እንዲሁም አጠቃላይ የ ሰውነት ማብላላት ሂደት(metabolism) ቫይታሚኖች ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። ከነዚህም ቫይታሚኖች አንዱ ፎሊክ አሲድ ነው። * ነፍሰ ጡር መሆንሽ በህክምና ከተረጋገጠ ጀምሮ እነዚህን የአይረን እና ቫይታሚን እንክብሎች መውሰድ መጀመር ይኖርብሻል። * በተለይ የፎሌት እንክብሎችን ለጽንሱ ስርዓተ ነርቭ እድገት ያላቸው ሚና የጎላ ስለሆነ ለማርገዝ ስታስቢ ሃኪም አማክረሽ  ከማርገዝሽ  ከ1 ወር ቀድሞ እስከ 12 ኛ የእርግዝና ሳምንት ድረስ መውሰድ ይመከራል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 1
ጥያቄ: ለምንድን ነው ማር ለህፃናት መስጠት የማይመከረው? መልስ: ማር ለጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ተፈጥሯዊ ምግብ ነው። በውስጡም የተለያዩ ፀረተህዋስ ኬሚካሎች እንዲሁም አንቲኦክስዳንቶችን ይይዛል። ከአንድ አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ማር አትስጡ ይባላል ይህም በምክንያት ነው። ማር የማይበስል ምግብ በመሆኑ ምክንያት ማር በምንመገብበት ወቅት ከማሩ ጋር አብረው የሚገቡ ጀርሞች አሉ። የአዋቂዎች በሽታ የመከላከል አቅም የዳበረ ስለሆነ ብዙውን ጊዜ እነዚህ ጀርሞች አዋቂዎች ላይ ጉዳት ላያደርሱ ይችላሉ። ነገር ግን ከ አንድ አመት በታች የሆኑ ህፃናት በሽታ የመከላከል አቅማቸው በደንብ ያልዳበረ ስለሆነ infantile botulism ለተባለ ከባድ የስርዓተ ነርቭ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ይህ ህመም የሰውነት ጠንቻዎችን እንዲሰንፉ በማድረግ፣ የመተንፈሻ ጡንቻዎችን በማዛል ለሞት ይዳርጋል። ይህ ህመም በጣም ጥቂት ሰዎች ላይ የሚከሰት ችግር ቢሆንም አንዴ ከተከሰተ በኋላ ለማከም አስቸጋሪ ስለሆነ ለህፃናት ማር ባለመስጠት ቀድሞ መከላከሉ የተሻለ ይሆናል። *** በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
👍 16
በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ የደም መፍሰስ (Post partum hemorrhage) በወሊድ ወቅት ለእናት ሞት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች ውስጥ በወሊድ ወቅት የደም መፍሰስ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል። በተለይም ባላደጉ አገራት እናቶች በብዛት በጤና ተቋም ውስጥ ስለማይወልዱ በደም መፍሰስ ምክንያት የብዙ እናቶች ህይወት ይቀጠፋል። በ ወሊድ ወቅት መጠነኛ የደም መፍሰስ የሚጠበቅ ሲሆን ከፍተኛ ደም መፍሰስ ስንል በማህፀን ወይም በኦፐሬሽን ለወለደች እናት ህይወቷን አደጋ ላይ የሚጥል አይነት (hemodynamically unstable) የሚያደርግ አይነት የደም መፍሰስ ነዉ።   📌 አጋላጭ ሁኔታዎች • ካለ ጤና ባለሙያ እርዳታ ቤት ውስጥ መውለድ • የምጥ መርዘም • የእንግዴ ልጅ ሙሉ በሙሉ አለመውጣት፣ ተቆርጦ ማህፀን ውስጥ መቅረት • የመንታ እርግዝና • በእርግዝና ወቅት መድማት (APH) • የፅንሱ ክብደት ከመጠን በላይ መጨመር • የእንሽርት ውሃ መብዛት • በምጥ መርፌ መውለድ • በመሳሪያ ታግዞ መውለድ 📌ህክምናው • ደም መውሰድ ፦ ከሰውነትሽ የወጣው ደም ለመተካት ደም አስፈላጊ ስለሆነ ከለጋሾች የተገኘ ደም እንዲሰጥሽ ይደረጋል። • የተለያዪ ደም ማቆሚያ መድሃኒቶችን በየደረጃው እንዳስፈላጊነቱ ይሰጡሻል። • የኦፕራሲዮን አገልግሎት ፦ በህክምና እርዳታ ደሙ ካልቆመ ህይወትሽ ለማትረፍ ኦፕራሲዮን ሊደረግልሽ ይችላል። ይህም ከቀላል የደም ማቆሚያ መቋጠር (B-lynch suture) እስከ ማህፀን ማውጣት (hysterectomy) የሚደርስ ሊሆን ይችላል። 📌እንዴት መከላከል ይቻላል? • ጤና ተቋም መውለድ • የተነገሩሽ ከፍተኛ ችግሮች ካሉ ከፍተኛ ጤና ተቋማት በመሄድ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ማማከር ደም በመለገስ የብዙ እናቶችን ህይወት መታደግ እንችላለን!!! *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 8🙏 1
ህፃናትን ጡት ማጥባት ከጡት ካንሰር እንደሚከላከል ታውቂያለሽ??  📌አዎ። ጡት ማጥባት ከ ጡት ካንሰር የመከላከል ጥቅም እንዳለው ሳይንስ ያስረዳል። ሌሎች አይነት የካንሰር አይነቶችን እንደ የእንቁልጢ ካንሰር(Ovarian cancer), የማህፀን ካንሰር(Endometrial cancer) የመከላከል ጠቀሜታ አለው። ከዚህም በተጨማሪ ጡት ማጥባት ለእናት የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት። እነዚህም: 🔷ከወሊድ በኋላ ማህጸን ቶሎ ወደቦታዉ እንዲኮማተር በማድረግ ከወሊድ በኋላ ሊያጋጥም ከሚችል ከፍተኛ የደምመፍሰስ ይከላከላል። 🔷በወሊድ ወቅት የእንግዴ ልጁ ከማህጸን ግድግዳ ቶሎ እንዲላቀቅ በማድረግ ከከፍተኛ የደም መፍሰስ(Postpartum hemorrhage) ይከላከላል። 🔷እንደ ተፈጥሯዊ የወሊድ መቆጣጠሪያ ሆኖም ያገለግላል። 🔷እንዲሁም ከደም ማነስ ይከላከላል 🔷 ከወሊድ በኋላ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል። 📌ጡት ማጥባት ለህፃናት እድገት እንዲሁም ለእናት ጤና እነዚህን የመሳሰሉ ከፍተኛ ጠቀሜታዎች ስላሉት በህክምና ጡት ማጥባትን የሚከለክል ችግር እስካላጋጠመሽ ድረስ ጡት እንድታጠቢ ይመከራል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 9
ጥያቄ: ዶክተር ፔሬድ ጨርሻለሁ ግን አሁንም የፔሬድ አይነት ሳይሆን ንፁህ ደም ይፈሰኛል እናም ከእብርቴ በታች በጣም ያመኛል እባካችሁ ተባበሩኝ ? መልስ: አንድ ሴት የማረጥ እድሜ ላይ ከደረሰች በኋላ የአር አበባ ማየት ታቆማለች። ይህም የሚከሰተው ስትወለድ ጀምራ ይዛቸው የእንቁላል ብዛት በቁጥር የተወሰነ ነው። ይህም ቁጥር በየወሩ እየቀነሰ ይመጣል። የማረጥ እድሜ ላይ ስትደርስም ቁጥሩ አነስተኛ ይሆናል በዚህም ምክንያት ለወር አበባ መከሰት ምክንያት የሚሆነው ሆርሞን(ኤስትሮጅን) ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንስ እና በየወሩ እንቁላል ከእንቁልጢ መለቀቅ ያቆማል፣ የወር አበባም ማየት ታቆማለች። 📌አንዴ የወር አበባ በማረጥ(Menopause) ምክንያት ማየት ያቆመች ሴት ከማህፀን የሚወጣ ደም ካስተዋለች ፈፅሞ ችላ ማለት የለባትም። 📌ከማረጥ በኋላ ደም መፍሰስ(post menopausal bleeding) ጤናማ ያልሆነ ክስተት ነው። በተለያዩ የማህፀን እና መራቢያ አካላት ችግሮች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።  📌ይህ ችግር ችላ መባል የሌለበት እና ምርመራ የሚያስፈልገው ስለሆነ የማህፀን ስፔሻሊስት ሃኪም ማማከር እና ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 6
በእርግዝና ወቅት የተለየ ክትትል የሚሹ ሁኔታዎች 1. ቁመታቸው አጭር የሆኑ ሴቶች በተለይም ከ 1.50 በታች የሆኑ ሴቶች በምጥ እና በወሊድ ጊዜ ውስብስብ ችግሮች ሊያጋጥማቸው ስለሚችል የተለየ ክትትል ይፈልጋሉ። 2. እድሜያቸው ከ 18 አመት በታች የሆኑ ሴቶች የሰውነታቸው እድገት ለእርግዝና ገና ያልደረሰ ስለሆነ በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት የተለያዩ ችግሮች ሊያጋጥሟቸው ይችላል። 3. ሳያረግዙ 35 አመት የሞላቸውና አሁን ያረገዙ ሴቶች 4. ደም ግፌት፡ ስኳር፡ የልብ፡ የኩላሊትና ሌሎችም ችግር ያለባቸው 5. ተላላፊ በሽታ እንደ HIV አይነት ያለባቸው 6. ቀድሞ ተደጋጋሚ የውርጃ ታሪክ ያላቸው ሴቶች 7. መንታ ያረገዙ ሴቶች 8. በዘር የሚተላለፍ ችግር ያለባቸው እና ሌሎችም ናቸው። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 5
ነፍሰጡር ነሽ? እንግዲያውስ እነዚህን ነገሮች ማወቅ አለብሽ። 1. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ማግኘት አለብሽ: የተመጣጠነ ምግብ ለአንቺ ጤና እንዲሁም ለፅንሱ ጤናማ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። ስለዚህ እንዳቅምሽ ምግብሽ ውስጥ የበሰሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን፣ ወተት፣ ጉልበት ሰጪ እና ሰውነት ገንቢ ምግቦችን በማካተት መመገብ ይኖርብሻል። 2. በቂ እንቅልፍ እና እረፍት ማግኘት ሰውነትሽ እንዲያገግም እና እራሱን እንዲያድስ ስለሚረዳ አስፈላጊ ነው። 3. የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ: በእርግዝና ወቅት ብዙ ጫና የሌላቸውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ባለሙያ አማክረሽ እንድትሰሪ ይመከራል።  4. የቅድመ ወሊድ ክትትልሽን ሳታቋርጭ በየቀጠሮው እየተገኘሽ ማድረግ ለአንቺም ሆነ ለፅንሱ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። 5. በቂ ፈሳሽ መዉሰድ 6. በግራ ጎን መተኛት 7. ውፍረትን መቆጣጠር 8. በእርግዝና ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ አደገኛ ምልክቶችን ማወቅና ካሉ ቶሎ በካኪም መታየት መታየት 9. ክትባት መከታተልና መጨረስ 10. የፅንስ እንቅስቃሴ መከታተል *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 17
በተደጋጋሚ ከሚደርሱን ጥያቄዎች ውስጥ ጥያቄ: ዶ/ር ከማህፀኔ የሚወጣ ነጭ ሽታ ያለው ፈሳሽ እና ማሳከክ አለ ምን ይሆን መፍትሄው? መልስ: ከማህፀን የሚወጣ ያልተለመደ ነጭ ፈሳሽ ካስተዋልሽ የተለያዩ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ይችላል። ከነዚህም ውስጥ በዚህ ፅሁፍ ስለ የብልት ፈንገስ ኢንፌክሽን(Vaginal Candidiasis) እናወራለን። ይህ የኢንፌክሽን አይነት የሴት ልጅ የውጨኛው መራቢያ አካል ላይ የሚከሰት መታከም የሚችል በሽታ ሲሆን ብዙ ሴቶች በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ህክምና ሳያገኙ ይቀራሉ። 📌 የዚህ ኢንፌክሽን መንስኤ Candidia Albicans የተባለ የፈንገስ አይነት ነው። የተለያዩ አጋላጭ ምክንያቶች አሉ ከነዚህም ውስጥ 📌 እርግዝና 📌 የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም መቀነስ እንደ ኤች አይ ቪ 📌 የስኳር በሽታ 📌 የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ተጠቃሽ ናቸው። ይህ ኢንፌክሽን ያለባቸው ሴቶች * የብልት ማሳከክ * ከብልት የሚወጣ ነጭ ሽታ ያለው ፈሳሽ * ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም አይነት ምልክቶች ይኖራቸዋል። 📌በምርመራ በሽታው እንዳለብሽ ከታወቀ ቀጣዩ ሂደት የሚሆነው የፀረ ፈንገስ መድሃኒት ህክምና ነው። ይህ መድሃኒት በሚቀባ ወይም በሚዋጥ መልኩ ሊታዘዝልሽ ይችላልም ነፍሰጡር ከሆንሽ ህክምናው የሚሆነው የሚቀባ ፀረ ፈንገስ መድሃኒት ነው። 📌ይህ የህመም አይነት የአባላዘር አይነት በሽታ አይደለም፣ የግብረስጋ ግንኙነት አድርገው ማያውቁ ሴቶች ላይ ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ከላይ የጠቀስናቸውን ምልክቶች ካስተዋልሽ መዳን የሚችል ህመም ስለሆነ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
1
ጥያቄ: ሠላም ዶክተር ጥያቄ ነበረኝ እባካችሁ መፍትሄ ካለዉ? በወርአበባ ጊዜ ከተለመዶ ቦታ ዉጭ በእምብርቴ ደም ይፈሠኛል ያለሁት ሥደት ላይ ነው መፍትሄ ካለዉ እባክችሁ ተባበሩኝ። መልስ: አንዳንድ ሴቶች ላይ በወር አበባ ወቅት ደም ከማህፀን ውጭ በሌሎች የሰውነት አካላት ሊፈስ ይችላል።  📌ይህም ችግር ኢንዶሜትርዮሲስ(Endometriosis) ተብሎ ይጠራል። ይህ ችግር የሚከሰተው የማህፀን ግድግዳ የውስጠኛው ክፍል(Endometrial tissue)በተለያዩ ምክንያቶች ከማህፀን ውጭ ወደሌሎች አካላት በሚሄድበት ጊዜ ነው። 📌ይህ ችግር የሚከሰትበት ትክክለኛ መንስኤው አይታወቅም። 📌ይህ ችግር ያለባቸው ሴቶች: በወር አበባ ወቅት ሌላ የሰውነት ክፍል ላይ ደም መፍሰስ፣ በተደጋጋሚ የሚኖር የህመም ስሜት፣ እንዲሁም ለማርገዝ መቸገር ወይንም መካንነት ሊኖራቸው ይችላል። 📌ይህ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ የተለያዪ ምር መራዎች ይታዘዛሉ ከነዚህም ውስጥ: የአልትራሳውንድ፣ ኤምአርአይ(MRI) እንዲሁም ላፓራስኮፒ ምርመራ ተጠቃሽ ናቸው። 📌አንድ ሴት ኢንዶሜትርዮሲስ እንዳለባት በምርመራ ከታወቀ በኋላ የተለያዩ የህክምና አማራጮች አሉት እነዚህም: የመድሃኒት ህክምና ወይም ቀዶጥገና ናቸው። ስለዚህ የማህፀን ስፔሻሊስት ያለበት የጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ እና ህክምና ማግኘት አስፈላጊ ነው። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 11👌 1
ጥይቄ: ሰላም ዶ/ር አንድ ጥያቄ ነበረኝ እኔ 8ወር ነፍሰጡር ነኝ በእርግዝናዬ ሰአት መሀጸኔ ተቋጥሯል ምጤ ሲመጣ ነዉ ሚፈታዉ ወይስ ቀደም ተብሎ ነዉ የሚፈታው? መልስ: በእርግዝና ወቅት የማህፀን መላላት(cervical insufficiency) በእርግዝና ወቅት ለተደጋጋሚ ውርጃ እና ካለግዜ መውለድ(preterm birth) የሚዳርግ ችግር ነው። 📌በብዛት ይህ ችግር የሚከሰተው በሁለተኛው የእርግዝና መንፈቅ(14-26 ሳምንታት) ነው። 📌ለዚህም ችግር ህክምናው የማህፀን መቋጠር ህክምና ሲሆን ይህ ህክምና የሚደረገው እናቲቱ ነፍሰጡር እያለች ባሉት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ሲሆን፣ ምጥ ከመምጣቱ በፊት ከ 36-37ኛ የእርግዝና ሳምንታት ውስጥ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተፈቶ እናቲቱ በምጥ እንድትወልድ ይደረጋል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
👍 1
ጥያቄ: ሰላም ዶ/ር ጥያቄ አለኝ ሁለት ልጆች አሉኝ አሁን ደሞ፡ የአምስት ወር እርጉዝ ነኝ፡ ከአሁን በፊት አይቼ የማላዉቀዉ፡ ከማሕፅን የሚወጣ ቢጫ ፈሳሽ አለ ጠረኑም ብዙም ጥሩ ያልሆነ በፈሣሹ ምክንያት እየተረበሽኩ ነው ። ምን ማድረግ አለብኝ? መልስ: የማህፀን ፈሳሽ ከማህፀን ጫፍ እና በዙሪያው ከሚገኙ ህዋሳት የሚሰራ በውስጡ ውሃ፣ የተለያዩ ባክቴሪያዎች እንዲሁም ዝልግልግ(mucus) የሚይዝ ፈሳሽ ነው። 📌ጤናማ የሆነ ወይም ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ አለ። 📌ጤናማ የሆነ የማህፀን ፈሳሽ መጠኑ ትንሽ እና ነጣ ያለ መልክ ያለው፣ እንዲሁም ሽታ የሌለው አይነት ፈሳሽ ነው። ይህም የወር አበባ በየወሩ የሚያዪ ሴቶች ላይ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች፣ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚጠቀሙ ሴቶች ላይ ይታያል።  📌ብዙ ጊዜ ጤናማ የማህፀን ፈሳሽ ከማረጥ (menopause) በዃላ አይታይም።  እንዴት ነው ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽን መለየት የምንችለው? በተለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት ለምሳሌ እንደ የማህፀን ኢንፌክሽን፣ የአባላዘር በሽታዎች፣ የፈንገስ ኢንፌክሽኖች እንዲሁም በማህፀን ጫፍ ካንሰር ምክንያት ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ ሊከሰት ይችላል። 🚨 ከወትሮው የተለየ መጠኑ የበዛ የማህፀን ፈሳሽ 🚨 መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ 🚨 ቀለሙ አረንጓዴ፣ ቢጫ ወይም እርጎ የሚመስል ነጭ የማህፀን ፈሳሽ 🚨 ከማህፀን ፈሳሹ በተጓዳኝ የሚኖር ሽንት ቶሎ የመምጣት፣ ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል ስሜት እንዲሁም የህመም ስሜት 🚨 ደም የቀላቀለ የማህፀን ፈሳሽ  🚨 ከወር አበባ ውጭ የሆነ ወይም በግንኙነት ወቅት የሚከሰት ደም መፍሰስ ካለ  ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶችን ካስተዋልሽ ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ ምልክት ስሆኑ ችላ ሳትይ ምርመራ ማድረግ እና ህክምና ማግኘት አስፈላጊ ነው። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
Показать все...
6👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለተጨማሪ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE በሴቶች ጤና ዙርያ በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
በእርግዝና ወቅት እንድታስወግጃቸው የሚመከሩ ምግቦች 📌 በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ስጋ እና ጥሬ የአሳ ስጋ የተለያዩ በሽታ አምጭ ፓራሳይቶች በደንብ ባልበሰለ ወይም በጥሬ ስጋ ላይ መኖር ስለሚችሉ እነዚህን ምግቦች አብስለሽ መመገብ ይኖርብሻል። 📌በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ እንቁላል       ያልበሰለ እንቁላል መመገብ ሳልሞኔላ(salmonella) ለተባለ ባክቴሪያ የማጋለጥ እድል አለው ስለዚህ እንቁላልን ሳታበስዪ በጥሬው መጠቀም የለብሽም። 📌የአልኮል መጠጥ በእርግዝናሽ ወቅት አልኮል መጠጣት Fetal Alcohol syndrome ለተባለ ችግር እንዲሁም የፅንሱ እድገት ላይ ችግር ይፈጥራል። ስለዚህ ማንኛውንም አይነት የአልኮል መጠጥ(ባህላዊ ወይንም ዘመናዊ) በእርግዝና ወቅት መጠቀም የለብሽም። 📌ሲጋራ ማጨስ የፅንሱ እድገት እና ጤንነት ላይ ችግር ስለሚፈጥር ሲጋራ ከማጨስ እንዲሁም ከሚጨስበት አካባቢ መራቅ ይኖርብሻል። 📌ቫይታሚን ኤ የበዛባቸው ምግቦች እንደ ጉበት ይህ ንጥረ ነገር በብዛት ከተወሰደ የፅንሱ አፈጣጠር ላይ እክል ስለሚፈጥር ጉበት በእርግዝና ወቅት አዘውትረሽ መመገብ የለብሽም። 📌ያልተፈላ ወተት ወተት ለፅንሱ አካላዊ እድገት እንዲሁም የአጥንት እና ጥርስ ጥንካሬ አስፈላጊ ነው ስለዚህ ወተት ስትጠጪ አፍልተሽ ወይም ፓስቸራይዝድ መሆን አለበት። 📌በፅዳት ያልተሰራ ሰላጣ ጥሬ አትክልት መብላት ሲያስፈልግሽ በጥንቃቄ፣በፅዳት የተሰራ እና ያልቆየ መሆን አለበት። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE በሴቶች ጤና ዙርያ በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
👍 13 2
በእርግዝና ወቅት አተኛኘቴ እንዴት መሆን አለበት? 📌በእርግዝና ወቅት በተለይም ጽንሱ እያደገ በሚሄድበት ሰዓት በግራ ወይም በቀኝ ጎንሽ እንድትተኚ ይመከራል። 📌 በተለይም ከ 5 ወር በኋላ በጀርባ መተኛት ጽንሱ የሰውነትሽ ዋና ደም መላሽ ቱቦ(IVC) በመጫን 10% የሚሆኑ እናቶች ላይ postural hypotension syndrome የተባለ ችግር ያመጣል። 📌ይህም ችግር ወደ ፅንሱ በቂ ደም እንዳይደርስ በማድረግ ጉዳት ያስከትላል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን የአተኛኘት ዘዴዎች በመጠቀም ይህ ችግር ከመፈጠሩ በፊት መከላከል ይቻላል። *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE በሴቶች ጤና ዙርያ በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
5👍 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለጥምቀት በአል አደረሳችሁ! @tenaseb
Показать все...
10👍 7
ጥያቄ: እርጉዝ ነኝ ቡና መጠጣት እችላለሁ? መልስ: ቡና በውስጡ ካፊን የተባለ ንጥረነገር የሚይዝ ሲሆን ይህም ንጥረ ነገር የመነቃቃት ስሜትን ይፈጥራል። ነገርግን ከመጠን በላይ ከተወሰደ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ✍️በእርግዝና ወቅት ከመጠን በላይ ቡና መጠጣት ፅንሱ ላይ መቀንጨር እና የእድገት ችግር፣ ውርጃ እንዲሁም ካለጊዜው መወለድ አይነት ችግሮችን ያስከትላል። ከመጠን በላይ የምንለው መቼ ነው? ✍️እንደቡናው አይነት እና እንደምንጠቀመው መጠጫ ይዘቱ ቢለያይም፣ በእርግዝና ወቅት ከ 200 ሚሊግራም(ወደ 2 ሲኒ) በላይ ቡና በቀን ውስጥ መጠቀም አይመከርም።  *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE በሴቶች ጤና ዙርያ በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
👍 6 3
ጥያቄ: እርገዝ ነኝ ቡና መጠጣት እችላለሁ? መልስ: ቡና በውስጡ ካፊን የተባለ ንጥረነገር የሚይዝ ሲሆን ይህም ንጥረ ነገር የመነቃቃት ስሜትን ይፈጥራል። ነገርግን ከመጠን በላይ ከተወሰደ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ✍️በእርግዝና ወቅት ከመጠን በላይ ቡና መጠጣት ፅንሱ ላይ መቀንጨር እና የእድገት ችግር፣ ውርጃ እንዲሁም ካለጊዜው መወለድ አይነት ችግሮችን ያስከትላል። ከመጠን በላይ የምንለው መቼ ነው? ✍️እንደቡናው አይነት እና እንደምንጠቀመው መጠጫ ይዘቱ ቢለያይም፣ በእርግዝና ወቅት ከ 200 ሚሊግራም(ወደ 2 ሲኒ) በላይ ቡና በቀን ውስጥ መጠቀም አይመከርም።  *** ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE በሴቶች ጤና ዙርያ በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
የማህፀን መውጣትን(Uterine Propapse) እንዴት መከላከል ይቻላል? 1) ለዚህ ችግር ከሚያጋልጡ ነገሮች መቆጠብ። እነዚህ አጋላጭ ነገሮች ምንድን ናቸው? √ የሆድ ውስጥ ግፊት የሚጨምሩ ሁኔታወች(የሆድ ድርቀት፣ለረጅም ጊዜ የቆየ ሳል፣ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሆድ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት) √ ብዙ ልጅ በምጥ መውለድ √  ከመጠን ያለፈ ውፍረት √ ሲጋራ ማጨስ √ ማረጥ √ የማህፀን ቀዶጥገና √ የምጥ መርዘም √ የጅማት በሽታወች √ የስኳር በሽታ 📌ስለዚህ ጫና የሚፈጥሩ ስራወችን(ለምሳሌ ከባድ እቃ መሸከም፣ ለረጅም ሰዓት መቆምን) መቀነስ 📌ክብደት መቀነስ እና ሲጋራ አለማጨስ አስፈላጊ ነው። 2) የመቀመጫ አካባቢ እንቅስቃሴ (Kegel's exercise) ይህን እንቅስቃሴ የሚሰራው በቀን ለ3 ጊዜ ሲሆን 📌ይህም ለ 3 ሴኮንድ ያህል ሽንትና ፈስ ሊያመልጠን ስንል እንደምንይዘው አፍነን መቆየት እንደገና ለ3 ሴኮንድ እረፍት መውሰድ ለ10 ጊዜ ያክል ደግሞ መስራት። ይህንን በቀን ለ3 ጊዜ ቢያንስ ለ3 ወር ያክል መስራት ይኖርብናል። 📌ይህንን እንቅስቃሴ የወለዱ ሴቶች ቢሰሩት ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የማህፀን መውጣት ይከላከላል። ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE በሴቶች ጤና ዙርያ በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
👍 10🙏 2 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 1
ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚከሰቱ አስቸኳይ ህክምና የሚሹ የህመም ምልክቶች የጨቅላ ህፃናት ህመም ለወላጅ ከባድ ነገር ነው። ጨቅላ ህፃናት እንደ ትልቅ ሰው ይሄ አመመኝ ብለው ባይናገሩም በሚያሳዩት የባህሪ ለውጥ ምክንያት የህመም ምልክቶችን ቀድሞ ማወቅ ይቻላል። ስለዚህ ወላጆች የትኞቹ ለውጦች የህመም ምልክት መሆናቸውን ቀድመው መለየት እና ወደ ጤና ተቋም መውሰድ ይኖርባቸዋል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች ልጅሽ ላይ ካስተዋልሽ ቶሎ ወደህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። 📌 ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ ጡትሽን በደንብ የማይዝ ከሆነ፣ 📌በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ ከሆነ እንዲሁም እያባበልሽውም ካለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ 📌በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ እንዲሁም ምንም ነገር ባፉ አልወስድ ካለ። 📌ቆዳው እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ እንደሆነ ካስተዋልሽ። ይህንንም ለማረጋገጥ ብርሃን ወዳለበት ክፍል በመውሰድ ቆዳው፣ መዳፋ እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ ከሆነ 📌ከተወለደ በ 2 ቀናት ውስጥ ምንም ካካ ነገር ከሌለው፣ ሆዱ እየተነፋ የሚሄድ ከሆነ፣ በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ፣ 📌እትብቱ የተቆረጠበት ቦታ ያለማቋረጥ የሚደማ ከሆነ እንዲሁም ሌላ አይነት ፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ፣ 📌ጡት ሲጠባ የሚያቆራርጥ ከሆነ፣ አተነፋፈሱ ፍጥን ፍጥን የሚል ከሆነ፣ ከንፈሩ እንዲሁም እጆቹ የሚጠቁሩ ከሆነ፣ 📌በተለይ በመሳሪያ እገዛ የተወለዱ ህፃናት ጭንቅላት ላይ ለብቻው፣ እየጨመረ የሚመጣ እብጠት ካስተዋልሽ፣ 🚨እነዚህን ምልክቶች ችላ መባል የሌለባቸው አስቸኳይ ህክምና የሚሹ ምልክቶች ስለሆኑ ልጅሽን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። *** በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
👍 10
ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚከሰቱ አስቸኳይ ህክምና የሚሹ የህመም ምልክቶች የጨቅላ ህፃናት ህመም ለወላጅ ከባድ ነገር ነው። ጨቅላ ህፃናት እንደ ትልቅ ሰው ይሄ አመመኝ ብለው ባይናገሩም በሚያሳዩት የባህሪ ለውጥ ምክንያት የህመም ምልክቶችን ቀድሞ ማወቅ ይቻላል። ስለዚህ ወላጆች የትኞቹ ለውጦች የህመም ምልክት መሆናቸውን ቀድመው መለየት እና ወደ ጤና ተቋም መውሰድ ይኖርባቸዋል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች ልጅሽ ላይ ካስተዋልሽ ቶሎ ወደህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። * ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ ጡትሽን በደንብ የማይዝ ከሆነ፣ * በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ ከሆነ እንዲሁም እያባበልሽውም ካለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ * በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ እንዲሁም ምንም ነገር ባፉ አልወስድ ካለ። * ቆዳው እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ እንደሆነ ካስተዋልሽ። ይህንንም ለማረጋገጥ ብርሃን ወዳለበት ክፍል በመውሰድ ቆዳው፣ መዳፋ እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ ከሆነ * ከተወለደ በ 2 ቀናት ውስጥ ምንም ካካ ነገር ከሌለው፣ ሆዱ እየተነፋ የሚሄድ ከሆነ፣ በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ፣ * እትብቱ የተቆረጠበት ቦታ ያለማቋረጥ የሚደማ ከሆነ እንዲሁም ሌላ አይነት ፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ፣ * ጡት ሲጠባ የሚያቆራርጥ ከሆነ፣ አተነፋፈሱ ፍጥን ፍጥን የሚል ከሆነ፣ ከንፈሩ እንዲሁም እጆቹ የሚጠቁሩ ከሆነ፣ * በተለይ በመሳሪያ እገዛ የተወለዱ ህፃናት ጭንቅላት ላይ ለብቻው፣ እየጨመረ የሚመጣ እብጠት ካስተዋልሽ፣ እነዚህን ምልክቶች ችላ መባል የሌለባቸው አስቸኳይ ህክምና የሚሹ ምልክቶች ስለሆኑ ልጅሽን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። *** በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
የቅድመ ወሊድ ክትትል አስፈላጊነት አንድ እናት በወሊድ ወቅት ሊያጋጥሟት ከሚችሉ ችግሮች ለመከላከል እንዲሁም ጤነኛ ህፃን ለመውልድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። መቼ ነው የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ የሚያስፈልገው? 📌ለማርገዝ ስታስቢ ጀምሮ ሃኪም ብታማክሪ እና ምርመራ ብታደርጊ ይመከራል። ምክንያቱም በዚህ ወቅት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ስኳር፣ ደምግፊት፣ ለሚጥል በሽታ የምትወስጃቸው መድሃኒቶች ካሉ አንዳንዶቹ ፅንሱ አፈጣጠር ላይ ችግር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ከማርገዝሽ በፊት ወደ ሌላ አይነት መድሃኒቶች እንዲቀየሩ ይደረጋል። እንዲሁም እርግዝና አስቸጋሪ የሚሆንባቸው የጤና ችግሮች ካሉም ቀድሞ ምርመራ በማድረግ እና ህክምና በማግኘት በእርግዝና ወቅት ከሚደርሱ ውስብስብ ችግሮች መከላከል ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ ከማርገዝሽ ወራት በፊት ጀምሮ ፎሊክ አሲድ እንድትወስጁ በማድረግ ፅንሱ ላይ ከሚፈጠሩ የስርዓተ ነርቭ ችግሮች መከላከል ይቻላል። * ማንኛውም ነፍሰጡር የሆነች ሴት ነፍሰጡር እንደሆነች ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በጤና ተቋማት የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ አለባት። የቅድመ ወሊድ ክትትል ምን ምን ያካትታል? * ስለ እርግዝናው እና ህክምና ታሪክሽ ሙሉ መረጃ ይወሰዳል * ሙሉ አካላዊ ምርመራ * የደም ምርመራ(የኤችአይቪ፣ ሄፓታይትስ፣ የደም አይነት፣ የሲፊሊስ ምርመራ) * የሽንት ምርመራ * የስኳር በሽታ ምርመራ * እንዳስፈላጊነቱ የሾተላይ መከላከያ መርፌ ሊሰጥሽ ይችላል። * እንዳስፈላጊነቱ የአልትራሳውንድ ምርመራ * ከዚህም በተጨማሪ የወሊድ እቅድሽን ከሃኪምሽ ጋር ትወያያለሽ። *** በግል ሀኪም ለማማከር - https://t.me/tenaSebBot ይጠቀሙ።
Показать все...
👍 4 1