cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Natinael Mekonnen

ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21 Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21

Больше
Рекламные посты
7 927
Подписчики
-624 часа
-297 дней
+3930 дней
Архив постов
እንኳን 1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ/አረፈ/በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን:: መልካም በዓል! 🕌
Показать все...
👎 2 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለመጀመሪያ ግዜ የውጭ ሀገራት ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚፈቅደው ረቂቅ በዛሬው እለት በሚኒስቴሮች ምክርቤት ተወስኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ተላልፏል።
Показать все...
👍 3 1
ፑቲን ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጡ ይህን የሩሲያ ቅድመ ሁኔታ መቀበል እንደ "እጅ መስጠት" ይቆጠራል ያየችው ዩክሬን ወዲያውኑ ነው ውድቅ ያደረገችው። https://am.al-ain.com/article/put-set-terms-ceasefire
Показать все...
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የሶማሌላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ ኢትዮጵያ በቅርቡ ምትረከበውን የባህርበር ትክክለኛ ቦታ ይፋ አድርገዋል ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ለእውቁ የመረጃ ተቋም The Economist በሰጡት ዘለግ ያለ ማብራሪያ ለኢትዮጵያ ለማስረከብ ተዘጋጅተናል ሲሉ የጠቀሱት የኤደን ባህረ ሰለጤ ላይ የሚገኘው ጥልቅ የባህር አካል አከባቢ የሆነው በቡሎ-ሃር እና በሎግሃያ መሃከል የሚዘረጋ 20 ኪ.ሜ የባህር ደጅ ነው። ይህ የቀይ ባህር መግቢያ ላይ የሚገኘው ስፍራ ከጅቡቲ 130 ኪ.ሜ ቅርበት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከየመኗ 2ኛ ትልቅ ከተማ ኤደን 265ኪ.ሜ ፣ ከስትራቴጂካዊውና ዓለም ከሚራወጥበት ቀጭን የባህር ማነቂያ ባብ ኤል-መንደብ 200 ኪ.ሜ ፣ ከታሪካዊው የአሰብ ክፍለ ሀገር 300ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ድርጅትና የዋና ስራ አስኪያጁ የባንክ አካዉንት መታገዱን ተከትሎ ድርጅቱም የሰራተኞቹን ደሞዝ መክፈል አለመቻሉን ገልጿል። በዚህ ሁኔታ ድርጅቱ ህልዉናዉን ለማቆየት የጥቂት ሳምንታት እድሜ ብቻ እንደሚቀረው ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ድርጅቱ ምንም አይነት የህግ ጥሰት እንዳለፈጸመ ገልጾ በዚህ ዉሳኔ በህዝብና በባለአክሲዮኖች ሀብት ላይ ለሚደርስ ጥፋት ሀላፊነት እንደማይወስድ ገልጿል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍሰሀ “አሁን ላይ ማንንም አካል እየከሰስን አይደለም” ያሉ ሲሆን “ዉሳኔ የሚያሳልፉ አካላት ችግራችንን ቀርበዉ እንዲያሳዉቁን እንፈልጋለን” ብለዋል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የት ይደርሳል የተባለውን ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው አለ አንድ የኛ ሰፈር ቀልደኛ የፋሲል እንዲህ ተራ ጋዜጠኛና መሆኑና ብሽሽቅ ውስጥ የገባ በመሆኑ አዝናለሁ:: #FactCheck ይህ ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር ልማት ወቅታዊ ይዞታን አያሳይም በፌስቡክ ከ160 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ‘ፋሲል የኔዓለም’ የተባለ ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራት ላይ ከሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መካከል የአንዱን ወቅታዊ ይዞታ ያሳያል ያለውን ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል። ቪዲዮው ከቲክቶክ የተወሰደ ሲሆን “ዛሬ ያለቀው 1ኛው የኮሪደር ልማት በአራት ኪሎ” የሚል ጽሁፍ ይነበብበታል። ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ቪዲዮ የኮሪደር ልማቱ ከመጀመሩ በፊት የተቀረጸ መሆኑን አረጋግጧል። ቪዲዮው የሚያሳየው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 4 ኪሎ ግቢ ዋና በር ፊት ለፊት ያለው አካባቢ ሲሆን በቪዲዮው ላይም የ4 ኪሎ-ፒያሳ የኮሪደር ልማት በተጀመረ የመጀመሪያዎቹ ቀናት የፈረሱ ህንጻዎች ይታያሉ። ከነዚህም መካከል በቀይ ቀለሙ ጎላ ብሎ የሚታየውና ‘ኮርዲያል ካፌ’ ይገኝበት የነበረው ህንጻ ይገኝበታል። በተጨማሪም ከቀዩ ህንጻ ጎን የነበረው አባድር ሱፐር ማርኬትም በተመሳሳይ ወቅት መፍረሱ ይታወቃል። ኢትዮጵያ ቼክ በወቅቱ የህንጻዎቹን ፈረሳ መታዘብ ችሎ ነበር። ይህም ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ አካውንት ያጋራው ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር ልማት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የተቀረጸ መሆኑን ያረጋግጣል። በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራት ላይ ከሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መካከል አንዱ የሆነው የ4 ኪሎ-ፒያሳ ፕሮጀክት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
Показать все...
👍 6😁 1
በኦጋዴን ከ21 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ተረጋገጠ_ የማዕድን ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል ኦጋዴን 19 ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ዳሰሳ "21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ" መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ፤ በሌሎች ስድስት ቦታዎች ላይም ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መኖሩን ኢፕድ ተናግረዋል፡፡ #ኦጋዴን፣ #መቀሌ፣ #መተማ፣ #ደቡብ_ኦሞ እንዲሁም #ጋምቤላ አካባቢዎች በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡ እንደ አቶ ሚሊዮን ገለጻ፤ በክልሉ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በቅርብ ዓመታት ወደ ምርት ለማስገባት ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ ሌሎች በፍለጋ ምዕራፍ ላይ ያሉትም በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበት አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡     
Показать все...
👍 5😁 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ህዋሓት ከፍቶት በነበረው ጦርነት በሳምሪዎች ንፁህን ከተጨፈጨፉበት ማይካድራ መነሻዉን ያደረግ ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሰር መዋሉን ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ መነሻውን ማይካድራ መዳረሻዉን ደግሞ ሳንጃ በሚባል ስፍራ ያደረገ አንድ የቤት ተሸከርካሪ አውቶሞቢል ውስጥ በድብቅና በስውር 3 ብሬኖች አንድ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ለማጓጓዝ የሞከሩ አዘዋዋሪዎች ገና ከጅምሩ የንስር ዓይን ባላቸው ሳላዮች ክትትል ስር ስለነበሩ ለፀጥታ አካላት በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ በፀጥታ አካላት እጅ የወደቁት እና በቁጥጥር ሰር የዋሉት ሁለት ህግወጥ አዘዋዋሪዎቹ ደብቀው ለማስተላለፍ ከሞከሯቸው መሳሪያዎች ጋር መሆኑን ታማኝ ምንጮች ከስፍራው በላኩት መረጃ አረጋግጠዋል
Показать все...
👍 4 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኦቪድ ሬል ሰቴት የሁለተኛ ዙር የሽያጭ ፕሮግራም አስጀመረ አድዋ ሙዚየም አቅርበን የነበረው እድል አምልጦት ነበር? በቀረበልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት የሁለተኛ ዙር የሽያጭ ፕሮግራም ከ ሰኔ 6-11 በሚሊንየም አዳራሽ ማዘጋጀታችንን ስናበስራቹ በታላቅ ደስታ ነው! ከቦሌ አየር መንገድ በ8 ኪ.ሜ. ርቀት ከቦሌ ቡልቡላ ጀርባ እጅግ ዘመናዊ በ ሁለት ዓመት የሚጠናቀቅ ቤት መግዛት የሚያስችል ዕድል ተዘጋጅቶሎታል:: ለዚህኛው ዙር ያዘጋጀናቸው ልዩ ቅናሾች እንዲሁም አማራጮች እንዳያመልጥዎ! ዛሬውኑ በመመዝገብ ቀድመው ቦታ ይያዙ! የሚያልሙት ቤት እየጠበቅዎት ነው! ከ ሰኔ 6-11 በሚሊኒየም አዳራሽ በ መገኘት የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ! ቀድመው ይመዝገቡ: https://bit.ly/OVID ለበለጠ መረጃ /0904157715/0904152215/0904151115 ይደዉሉ!
Показать все...
👍 2
ዛሬ ሰኔ 06/2016 ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን በራያ አላማጣ ወረዳ የዋጃና የጥሙጋ ነዋሪዎች በአጠቃላይ በራያ ህዝብ ላይ የTPLF ሠራዊት እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ዘረፋና ውድመት የሚያወግዝ ሠላማዊ ሠልፍ በምሬት ገልፀዋል።
Показать все...
👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአዲስ አበባ ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት ክፍያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ተስብስቧል ባለፉት አስራ አንድ ወራት በአዲስ አበባ ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት ከፍያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ገለፀ። ባለስልጣኑ በማዕከልና በ12 ቅርንጫፎች ከ55 በላይ የአሽከርካሪና የተሽከርካሪ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከአገልግሎቶቹ ውስጥ 49ኙ በዲጅታል የሚሰጡ መሆኑን ያስታወቀው ባለስልጣኑ ይህን ተከትሎ ባለፉት አስራ አንድ ወራት አንድ ሚሊዮን አካባቢ የተሽከርካሪ አገልግሎት መሰጠቱ ተጠቋሟል፡፡ የባስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ለሌሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ አስራ አንድ ወራት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተገልጋዮች አገልግሎት ማግኘት ችለዋል። ይህን ተከትሎ ከተሰጠው አገልግሎት በክፍያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልፀዋል፡፡ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታውሰው፤ የዘንድሮው ከፍተኛ ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል፡፡ በዋናነት የአሽከርካሪና የተሽከርካሪ አገልግሎቶች በባለስልጣኑ እንደሚሰጡ ገልጸው በበጀት አመቱ ከተያዘው ዕቅድ አንጻር 80 በመቶውን ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረጉ፣ ከተሽከርካሪ ሽያጭ፣ ስም ዝውውር፣ ከተሽከርካሪ ሽያጭ ግምት የሚፈልጉ ደንበኞች ቁጥር መጨመር ለገቢው ማደግ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም የሰራተኞች የአገልጋይነት መንፈስ ማደጉ ለገቢው መጨመር የራሱን አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በባለስልጣኑ ይታዩ የነበሩ ብልሹ አሰራሮች እየቀነሱ መምጣታቸውን ተከትሎ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደ ባህል እየተለመደ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ህብረተሰቡ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት አስፈላጊውን መረጃ ማሟላት በቂ መሆኑን አውቆ ራሱን ከህገ ወጥ ጉዳይ አስፈጻሚዎች እንዲጠበቅም አሳስበዋል::
Показать все...
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አልታወጀባትም፤ በርካታ ሰዎች ግን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በኋላ ከቤታቸው ከመውጣት ራሳቸውን ያቅባሉ። ለደኅንነታቸው የሚሰጉ ነዋሪዎች ጎረቤቶቻቸው በስለት እና በጦር መሳርያ ጥቃት ሲደርስባቸው እና ሲዘረፉ ቢያዩ፣ አልያም የድረሱልኝ ጥሪ ቢሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለትን ይመርጣሉ። ለዚህ ታሪክ ሲባል ቢቢሲ ያነጋገራቸው በርካታ ሰዎች በክልሉ እያጋጠመ ያለው በሕጻናት እና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው እገታ፣ በሌሎች ላይ በሚደርሰው ጥቃት እና ሞት በፍርሃት ውስጥ እየኖሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው የተቀየረው አቶ ወልደስላሰ በየቀኑ “ልጆቼ ከሚውሉበት የድንኳን ትምህርት ቤት በሰላም ይመለሱ ይሆን ወይ? ብዬ ስጨነቅ ነው የምውለው፤ ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ ጆሮዬን ክፉ እንዳያሰማው እጸልያለሁ” ሲሉ ስጋታቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሽረ ከተማ ውስጥ የሚገኙት አቶ ወልደስላሰ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተንቀሳቀሱባቸው ሌሎች የክልሉ አካባቢዎችም ቢሆን ለነዋሪዎች ደኅንነት ስጋት የሆኑ አጋጣሚዎችን መመልከታቸውን ይናገራሉ። “በሽረ፣ በዓዲ ዳዕሮ እና ሸራሮ ከተሞች ዝርፊያ እና እገታ ይፈጸማል። የፋሲካ ጾም አካባቢ በሸራሮ አንድ ሰው ከቤቱ ታግቶ ሲወሰድ አይቻለሁ። እስከ አሁን የገባበት አይታወቅም። በሽረ ከተማም መኪና ይዘው በመጡ ግለሰቦች የታገተ ሰው አለ። ሆኖም እነዚህን አጣርቶ መረጃ የሚሰጥ አካል ስለሌለ፣ ሰው በምን ምክንያት ዒላማ እየሆነ እንዳለ አይታወቅም።” ቢቢሲ በክልሉ የሚታየው የፀጥታ ስጋት በተለያዩ መንገዶች ሲከታተል የቆየ ሲሆን፣ የችግሩ ስፋት ለመገንዘብ ለሳምንታት በርካታ ኗሪዎች አነጋግሯል። ይህ መረጃ በዚህ ጽሑፍ ስማቸው ያልተገለጸ አስተያየት ሰጪዎችን ጨምሮ፣ ከአምስት የክልሉ ከተሞች ያነጋገርናቸውን 12 ሰዎች እንዲሁም እገታ እና ዝርፊያ የተፈጸመባቸው ቤተሰቦች አባላት የሆኑ ግለሰቦች ጋር የተደረጉ ቃለ መጠይቆችን መሠረት ያደረገ ነው። በክልሉ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ ይመለከታቸዋል የተባሉ የተለያዩ ኃላፊዎችን ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ እጅ ስልካቸው ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
Показать все...
👍 4
በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የምግብ ጨው ማምረት ተጀመረ! በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ባሌ ዞን ከአዲስ አበባ 783 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዳዌ ሠረር ወረዳ፣ ጎላኩርማ ቀበሌ የምግብ ጨው እየተመረተ መሆኑ ታወቀ።የምሥራቅ ባሌ ዞን የንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሚን አልዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ጨው፣ የተለያዩ የጥራት ጥናቶች ከተደረጉና አዋጭነት ያለው ምርት መሆን ከተረጋገጠ በኋላ እየተመረተ ነው። ‹‹ለወደፊቱ መንግሥት የተሻሉ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን አመቻችቶ ማሳደግ እንደሚቻል ታምኖበት ነው የተጀመረው›› ያሉት ኃላፊው፣ የጨው ምርት የሚገኝበት ሥፍራ፣ በባለሙያዎች ተጠንቶ ምርት መጀመር እንደሚቻል የተረጋገጠውና ወደ ሥራ የተገባው ከሁለት ዓመት በመስከረም ወር 2014 ዓ.ም. እንደሆነ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት ጨው የማምረት ሥራውን እያከናወነ የሚገኘው አንድ ማኅበር መሆኑን፣ በሥሩም አንድ መቶ አባላት እንዳሉት ታውቋል። ማኅበሩ ከመስከረም 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በዓመት 200 ሺሕ ኩንታል የምግብ ጨው እያመረተ እንደሚገኝም ተገልጿል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ከወጪ ቀሪ ሁለት ሚሊዮን ብር ማግኘት የቻለው ማኅበሩ፣ ከጤና ሚኒስቴር ፈቃድና አዮዲን በመውሰድ የሚያመርተውን ጨው የሚያወጣው በባህላዊ መንገድ መሆኑን አቶ አሚን ተናግረዋል።ጨው እየወጣ ያለው መሬቱን ወደ ታች በመቆፈር በጉድጓድ ውስጥ ጨዋማው ውኃ እንዲከማች በማድረግ፣ ከጉድጓዱ አጠገብ ሌላ አነስተኛ ጉድጓድ በመቆፈር ጨዋማው ውኃ ተገልብጦ እንዲረጋ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጤናማነቱ በባለሙያዎች ተፈትሾ ተረጋግጧል ሲሉ ኃላፊው አስረድተዋል። አምራቾቹ ጨው ከረጋ በኋላ ከጉድጓድ አውጥተው ፀሐይ ላይ በማስጣትና እንዲደርቅ በማድረግ አዮዲን ጨምረው ለጥቅም እንደሚያዘጋጁትም ተናግረዋል።የንግድ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ፣ ‹‹ከአዲስ አበባም፣ ከኦሮሚያም፣ ከምሥራቅ ባሌ ዞንም የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተገናኝተውና ጥናት አድርገው፣ በአካባቢው በተገኘው ጨው ላይ ምርመራ ተደርጎ መመረት እንደሚችል ዕውቅና ተሰጥቶታል፤›› ብለዋል። አሁን በሥራ ላይ ያለው ማኅበር አባላቱን በመጨመርና ሌሎችንም በማካተት የምርት መጠኑን እንዲያሳድግ ከዞኑ በኩል ፍላጎት ቢኖርም፣ የገበያ ትስስር ችግር ግን ማነቆ እንደሆነባቸው ገልጸዋል።‹‹በሥራ ላይ ያለው ማኅበር በየጊዜው ከዞኑ ንግድ ጽሕፈት ቤት የሚጠይቀው የገበያ ትስስር እንድንፈጥርለት ነው፤›› ያሉት አቶ አሚን፣ በአሁኑ ወቅት ግን ከቆላማ የኦሮሚያ አካባቢ የሚመጡ አከፋፋዮች ብቻ ምርቱን እንደሚወስዱ ጠቁመዋል። Via Reporter
Показать все...
👍 7 4
በጀልባዋ ላይ ከተሳፈሩት ውስጥ 145 ኢትዮጵያውያን እና 115ቱ ሶማሊያውያን ናቸው ተብሏል። ከሶማሊያ የባህር ጠረፎች ከ260 በላይ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጥማ 50 ያህል ሰዎች መሞታቸውን ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም ትናንት ማክሰኞ አስታውቋል። ከሟቾች ስድስቱ ህጻናት ናቸው። በጀልባዋ ከተሳፈሩት ውስጥ 140 ያህል ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ የሟቾችን ቁጥር በእጅጉ ሊሻቅብ እንደሚችል ይጠበቃል። ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ከሶማሊያ የተነሳችው ጀልባዋ በየመን መዳረሻ የባህር ሰርጥ የመስጠም አደጋ የደረሰባት ከትናንት በስትያ ሰኞ ዕለት ነበር። በጀልባዋ ላይ ከተሳፈሩት ውስጥ 145 ኢትዮጵያውያን እና 115ቱ ሶማሊያውያን ናቸው ተብሏል። ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ መነሻቸውን ያደረጉ በርካታ ስደተኞች በመካከለኛው ምስራቅ የተሻለ ህይወት ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሲያቀኑ በተመሳሳይ መስመር በየጊዜው በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው በተደጋጋሚ ሲዘገብ ቆይቷል። ዓለማቀፉ የፍልስተኞች ተቋም IOM እንዳስታወቀው ባለፈው የጎርጎርሳውያን 2023 100 ሺ ያህል ፍልሰተኞች የሞት መስመሩን ተሻግረው የመን ደርሰዋል።  የባህር ላይ ሞቱን አልፈው የመን የደረሱቱም ቢሆኑ  ከናፈቁት የተሻለ ህይወት ይልቅ ሞት እና መከራ እንደሚቀበላቸው ነው ስደተኞቹን ያነጋገሩ ዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በየዘገባዎቻቸው ሲያስነብቡ እና ሲያስመልክቱ የቆዩት።
Показать все...
በትግራይ ከሚገኙ ወጣቶች 81 በመቶ የሚሆኑት ስራአጥ መሆናቸውን እና 40 ከመቶዎቹ መሰደድ እንደሚፈልጉ አንድ ጥናት ጠቆመ በትግራይ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 81 ከመቶዎቹ ስራአጥ መሆናቸውና 40 ከመቶዎቹ መሰደድ እንደሚፈልጉ የትግራይ ወጣቶች ማሕበር ያደረገው ጥናት ጠቆመ። ጥናቱ እንደሚያሳየው በክልሉ ለሁለት ዓመት ከተደረገዉ ጦርነት በኋላ ያለዉ ሁኔታ ለወጣቶች ተስፋ አስቆራጭ ነዉ። ከጦርነቱ በፊት በትግራይ የስራ አጥ ወጣቶች መጠን 30 ከመቶ እንደነበረ የጠቆመው ጥናቱ የደረሰው ውድመት፣ መፈናቀል እና ሌሎች ምክንያቶች ተደምረው አሁን ላይ በትግራይ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 81 ከመቶዎቹ ስራ አጥ መሆናቸውን አስታውቋል። ስራ አጥ ከሆነው በተጨማሪ 89 ከመቶ የሚሆን በትግራይ የሚገኝ ወጣት ምንም ዓይነት ገቢ እንደሌለው የትግራይ ወጣቶች ማሕበር ስራአስኪያጅ ሰናይ ከሓሰ መግለጻቸውን ከጀርመን ድምጽ የአማራኛ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ከፖለቲካ ተሳትፎ ጋር በተያያዘ ጥናቱ ባደረገው ዳሰሳ 66 ከመቶ የሚሆኑ የትግራይ ወጣቶች በፖለቲካ ጉዳዮች መሳተፍ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል ያሉት ስራ አስኪያጁ ይህም ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ተስፋ ከማጣት የመነጨ ሊሆን ይችላል ሲሉ መላምታቸውን ማስቀመጣቸውን ዘገባው አመላክቷል። በተለያየ መንገድ በፖለቲካዊ ጉዳዮች መሳተፍ እንደሚፈልጉ የገለፁ 34 ከመቶ የሚሆኑ ወጣቶች ሲሆኑ፥ 10 ከመቶዎቹ በተቃውሞ የፖለቲካ ረድፍ መሰልፍ እንደሚፈልጉ የጥናቱ ውጤት ያመለክታል ማለታቸውንም አካቷል። በትግራይ ካሉ ወጣቶች መካከል 40 ከመቶዎቹ ትግራይን ለቀው መሰደድ እንደሚሹ የትግራይ ወጣቶች ማሕበር ጥናት ያሳያል ያለው ዘገባው ሁኔታው በትግራይ ወጣቶች ዘንድ እየታየ ያለ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ጠቁሟል።
Показать все...
👍 2
📌ቶሎ የመጨረስ ችግር  እና ህክምነው (Premature ejaculation and it's Treatment)? 👉አንድ ወንድ ቶሎ የመጨረስ ችግር አለበት የሚባለው ግኑኝነት ከጀመረ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሲጨረስ ወይንም እርሱ ወይንም አጋሩ ከምትፈልገው ጊዜ በታች  ያለምንም ቁጥጥር የዘር ፈሳሽ ሲያፈስ ነው። 👉ይህም ችግር ከ30 እስከ 40 በመቶ  በሚሆኑ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ይህም ቁጥር የችግሩን መጠኑ ሰፊነት ያሳያል። 📌 ለመሆኑ ይህ ችግር መፍትሔ አለውን? 👉 በአጭሩ መልሱ አዎ መፍትሔ አለው ነው። የህክምና አማራጮቹንም በ 3 ክፍሎ ማየት ይቻላል።     1) Behavioural therapy/ የባህሪ ህክምና    👉 ይህ የህክምና አይነት የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም  የግንኝነት ቆይታን ማራዘም ነው :: ለምሳሌ A) መጀመር ከዛ ማቆም (start and stop method ) ግኑኝነነት እያደረጉ ልክ ሊጨርሱ ሲደርሱ ለ30 second ያህል ብልቱን ከሴቷ ብልት በማውጣት ማቆየት ከዛ በኋላ መልሶ መጀመር :: ከ 3 እስከ 4 ጊዜ መደጋገም ፣ ይህንን ማድረግ ወንዱ የተሻለ  ቁጥጥር እንዲኖረው ያደርጋል።    2) መያዝ (squeeze  method)    👉 ይህ ማለት ወንዱ ሊረጭ ሲል ብልቱን  በማውጣት የብልቱን ጫፍ በመጠኑ ለ30 ሰከንድ ያክልመያዝ። ይህንንም ከ 3 እስከ 4 ጊዜ መደጋገም ።    3) በግኑኝነት ጊዜ ሌላ ነገር ለማሰብ መሞከር (diatructed thinking)     4) ኪግል የመቀመጫ ስፖርት (Kegel exercise ) B) ማማከር (Counciling) የችግሩ ምክንያት ከ ሳይኮሎጂካል ችግር ፤ ፤ከተዛባ ግንኙነት ( relationship issues ) ወይንም ከአስተሰሰብ ችግሮች ለምሳሌ ከጭንቀት ፤ ድብርት ፣ ከጥፋተኝነት ስሜት (guilt) ፣ የራስ መተማመን አለመኖር (Lack of self confidence ) የሚመጣ ከሆነ በpsycho therapy ይታከማል ። C) የመድሀኒት ህክምና የተለያዩ መድሀኒቶች ሲኖሩ እነዚህም    A) Vimax የሚባል የሚዋጥ መድሃኒት    B) በብልት ላይ የሚቀቡ እና በብልት አካባቢ የሚገኙትን ነርቮቹ በማደንዘዝ ከመጠን በላይ የብልት ቆዳዎች ሲነኩ ስሜታዊ እንዳይሆኑ  የሚያደረጉ መድሃኒትች ( Largo cream and sprays)   C) ቶሎ የመርጨት ችግር ከስንፈተ ወሲብ ጋር አብሮ የመጣ ከሆነ እንደ Vimax እና Largo ያሉ መድኃኒቶችም ይታዘዛሉ ። 📌# የነዚህን መድኃኒት Original አስመጪዎች አድራሻ ከስር አስቀምጣለው እነርሱ ጋር ታገኛላቹህ  inbox @AddisAbeba44 ስልክ tel:+251983673210 ዶክተር ሸምሴ ነኝ በወሲብ ዙርያ ላይ ማንኛውም ጥያቄ ካላቹህ በህክምናው ዘርፍ ሊደረግ የሚችለውን ሁኔታ በቴሌግራም ቻናሌና በግሩፔ ላይ እመልስላችኋለሁ https://t.me/Herbal_treatment_and_marketing
Показать все...
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግንቦት 20 ከአሁን በኋላ አይከበርም - የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል። አዋጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን ይችላሉ ተብሏል። ይህ የሚመለከተው እንደ ኢሬቻ፣ ጊፋታ፣ ጨምባላላ፣ አሸንዳ ፣ ሻደይ ፣ አሸንድዬ ፣ ...ሌሎችንም ሲሆን ክልሎች በራሳቸው አዋጆችን አውጥተው አከባበሩን መወሰን እንደሚችሉ ተመላክቷል። ➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን “ ግንቦት 20 “ ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡ ➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ። ➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ። ➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል። ➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል። በዚህም ፦ ° የውሃ ° የመብራት ° የስልክ ° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ) ° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች ° መከላከያ ° ፖሊስ ° ደህንነት ° የእሳት አደጋ መከላከል ° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ° ነዳጅ ማደያዎች ° ሙዝየሞች ፣ ° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።
Показать все...
👍 13
ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመመርመር ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን መጥለፍ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ወንጀል ጋር በተያያዘ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን እና ደብዳቤዎች ለመጥለፍ ለመርማሪዎች ፈቃድ የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። አዲሱ ረቂቅ በሥራ ላይ ያለውን በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ የሚሽር ነው። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መርማሪ አካል “አስቸኳይ ሁኔታ ካጋጠመው” የሚመለከተውን የዐቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመገናኛ እና የደብዳቤ ልውውጦችን መጥለፍ ይችላል። መገናኛዎችን እና የደብዳቤ ልውውጦችን መጥለፍ ከወንጀሎቹ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ከሚደረጉ የምርመራ ዘዴዎች መካከል ናቸው። በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ ክትትል ማድረግ፣ የኮምፒውተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችን ሰርቨሮችን መለየትም በተመሳሳይ ሌሎች የምርመራ ዘዴዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራም (undercover operation) በተመሳሳይ በአዋጁ የተጠቀሰ የምርመራ ዘዴ ነው። ረቂቅ አዋጁ “መርማሪ አካል አስቸኳይ ሁኔታ ካጋጠመው በአካባቢው ያለውን እና የሚመለከተውን የዐቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስረጃ ሊሰበስብ ይችላል” ይላል። በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዐቃቤ ሕግ ይሁንታ ብቻ የምርመራ ዘዴዎችን ማከናወን ለመርማሪ አካል አይፈቅድም። በመርማሪ አካል ጠለፋውን ለማካሄድ የሚጠየቅ የመገናኛ የአገልግሎት አቅራቢ፤ “ጠለፋው በፍርድ ቤት ወይም በዐቃቤ ሕግ የበላይ ኃላፊ የተፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ” ትብብር የማድረግ ግዴታ በረቂቅ አዋጁ ተጥሎበታል። “የገንዘብ ቅጣት አነስተኛ በመሆኑ አስተማሪ ቅጣት መስጠት የሚያስችል ይዘት አለመኖሩ[ን]” የጠቀሰው የአዋጁ ማብራሪያ የወንጀል ጥፋቶች እና ቅጣቶች ላይ ማሻሻያ እንደተደረገባቸው ያትታል። በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ በማስመሰል ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ ላይ ይጣል የነበረው የገንዘብ መቀጮ ጣሪያ ከ100 ሺህ ወደ 500 ሺህ ከፍ እንዲል ተደርጓል። በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ የሚባል ግለሰብ ላይ ይጣል የነበረው የእስር ቅጣት ግን ከዚህ በፊት በነበረበት ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጥል ተደርጓል። ሽብርተኝነት በገንዘብ መርዳት ወንጀልም ተመሳሳይ የገንዘብ እና የእስራት መቀጮ የሚጣልበት ሆኖ ተሻሽሏል። በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ተቀጽላ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ይጣል የነበረው ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተሻሽሎ ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሆኗል። የእስራት ቅጣቱ ግን ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት ከሦስት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ እስራት ሆኖ ቀጥሏል። ረቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ወደ ሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ከተመራ በኋላ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተግባራዊ እንዲሆን ይጸድቃል።
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የመጭው 2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 971.2 ቢሊየን ብር ሆኖ ለፓርላማው ቀረበ፡፡ ይህም ከ2016 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ የወጪ በጀት ውስጥ 451.3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ በጀት፣ 283 .2 ቢሊየን ለካፒታል እንዲሁም 236.7 ቢሊየን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍሆኖ መደልደሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ለክልሎች ከተመደበው በጀት ውስጥ 14 ቢሊየን ብር የሚሆነው የዘላቂ ልማቶችን ለማስፈፀም ለክልሎች የተመደበ ድጋፍ እንደሆነ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ ከቀረበው የፌዴራል መንግስት የወጪ በጀት ውስጥ ከፍተኛውን በጀት፤ ለመደበኛው የተያዘው በጀት እንደሆነ የተናገሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ ይህም የጠቅላላውን በጀት 46.5 በመቶ ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡ ሰኔ 30 ከሚጠናቀቀው ከ2016 በጀት ዓመት ጋርም ሲመሳከር የ21.9 በመቶ እድገት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ከመደበኛ በጀት ውስጥ 128.2 ቢሊየን ብር ወይንም 28.2 በመቶ ለመደወዝ፣ ለአበል እና ለልዩ ልዩ ክፍያ ሲሆን 321.4 ቢሊየን ወይም 71.8 በመቶ ለስራ ማስኬጃ ተደግፎ የቀረበ መሆኑን አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡
Показать все...
👍 2
ከንቲባነት የገባቸው ከንቲባ…..!! ሰውየው አሜሪካዊ የህግ ባለሙያ እና ፖለቲከኛም ነው፤ የቀድሞው የማያሚ ከንቲባ ዣቪየር ሱአሬዝ ልጅ ነው፤ የአባቱን ፈለግ ተከትሎ ሚያሚን ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በከንቲባነት እያገለገለ ይገኛል፤ የፓርቲ ውክልናው ከሪፐብሊካን የሆነው ከንቲባ ፍራንሲስ ዣቪየር ሱዋሬዝ ልምደ ብዙም ነው፤ ይህ ሰው በአንድ ወቅት ከንቲባነትን በዚህ መልኩ ገልፆታል፡፡ I believe the best type of mayor is one who seeks to uplift people and make their quality of life better and sometimes that requires tough decisions. /Francis X. Suarez/ እንደው በቀላሉ እንዲህ ብለን ከላይ የቀረበውን ለመረዳት ብንሞክር …በጣም ጥሩው የከንቲባ አይነት ሰዎችን ከፍ ለማድረግ፣ የአኗኗር ዘይቤያቸውን የተሻለ ለማድረግ እና አንዳንድ ጊዜ ከባድ ውሳኔዎችን መወሰንን የሚጠይቅ ነው ብዬ አምናለሁ። ከላይ የቀረበውን ፍሬያማ ገለፃ ይዤ የከተማዬን ከንቲባ ማሰብ ጀመርኩ…..!! አዲስ አበባ ከንቲባዋን ካገኘች ሰነባብታለች፤ ያውም በታሪክ ብቸኛዋ እንስት ከንቲባዋን….. ፤ በእረፍት የለሽነት የሚያቅዱ ፣ስራን የሚመሩ፣ የተሰራውን በቅርበት የሚከታተሉ ፣ወሳኝ ለውጥ አምጪ ውሳኔዎችን ከጠንካራ የካቢኔ አባላት ጋር በመሆን በጋራ ውሳኔ ለተጨባጭ ለውጥ የሚተጉና የሚያተጉ በገቡት ቃል ልክ የሚገኙ፣ እንባ አባሽ የብዙ ደማቅ ስኬቶች አሻራን እያሳረፉ የሚገኙ ከንቲባ ናቸው….የከተማዬ ከንቲባ ፡፡ ከንቲባነት ከገባቸው የብዙ ሀገራት ከንቲባዎች መካከልም በተጨባጭ ሚዛናዊ መለኪያ ከሰሩት እና እየሰሩ ካሉት ስራ በመነሳት ትልቅ አክብሮት እና ምሰጋና ሊሰጣቸው ከሚገባቸው ከንቲባዎች መካከል የከተማዬን ከንቲባ አንዷ በመሆናቸው ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ስራዎቻቸው በተለያዩ ሀገራት ዕውቅና ተሰጥቷቸው ሲያሸልማቸው ከማሸለምም በላይ በተሞክሮነት ሲወሰድ አይቻለሁና ማመስገኔ ተገቢ ነው፡፡ የከተማዬ ከንቲባ ለሚመሩት ህዝብ የተሻለውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ የማይሉ ለመሆናቸው በተለይም ፈፅሞ ለኑሮ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ለዓመታት በጉስቁልና ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች እንባቸው ታብሶ ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ እንዲሻገሩ አድርገዋል ፤ብዙ እናቶቻችንን እና እህቶቻችንን የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻሉበት ሁኔታ ምስክር ነው፡፡ ከንቲባዋ ከንቲባነት የገባቸው ናቸው የምልበትን ሌላ ማሳያ ልጨምር ተወልጄ ያደኩባትን፣ አሁንም እየኖርኩባት ያለሁባትን ከተማዬን አዲስ አበባን በደንብ አውቃታለሁ፤ ጓዳ ጎድጓዳዋን ምን ይመስል እንደነበር ፤ አሁን ላይ እየሆነች ያለችውን ለእናንተ ልተወው…. ፤ ብቻ ግን የሚያሚው ከንቲባ እንዳለው ከንቲባነት አንዳንዴ የተሻለውን ለማድረግ ቆራጥ ውሳኔ መወሰን የግድ ይላልና ከንቲባዋ በተለይም ከተማዋን ለመምራት ሲረከቧት ማለትም ስሟን በሚመጥን ልክ ሊያስውቧት፣ ሊያለሟት፣ለትውልድ የምትተርፍ ቆሻሻና ስንፍና የሌለባት ከተማ ሊያደርጓት የገቡትን ቃል እያሳኩ ለመሆኑ በኮሪደር ልማት ስራዎቻቸው የመጣውን ተጨባጭ ውጤት ማየት ይቻላል ፡፡ በሶስት ወር ጊዜ ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ እና የአራት ኪሎ የኮሪደር ልማት ስራዎች መጠናቀቅን ስታይ ቀጣዩን መገመት አይከብድም፤ የመወሰን ልክ ይልሃል ይሄ ነው፡፡ የከተማዬ ከንቲባ ልምደ ብዙ ለውጥ የሚሹ ናቸው ፤ ያውም ሰው ሰው የሚሸቱ ፤ በተናጠል ስኬት የማይኮሩ የተሻለውን ሁሉ ለማድረግ እንቅልፍ አልባ የሆኑ ድንቅ መሪ ናቸው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአመለካከት ለውጥ በከተማችን የስራ ባህል እና ሁለንተናዊ አገልግሎት እንዲመጣም አድርገዋል ያውም እሳቸው ግንባር ቀደም ሆነው፡፡ የተለወጠ አመለካከት የሚያመጣውን ውጤት ለመረዳት ጥሩውን የማየት ብቃት ሊኖር ይገባልና ልክ እንደ ከተማዬ ከንቲባ ጥሩውን የማየት ብቃት ተላብሶ ለጋራ ዕድገትና መለወጥ ልንተጋ ይገባል፡፡ የምርጥ አመለካከት ባለቤት መሆን መታደል ነው ፤ ጉዳት የለውምና ፡፡ … ይህቺን ምሳሌ እንያት እስኪ…. /የምሳሌዋ ምንጭ የሺቭ ኬኸራ ፣ YOU CAN WIN ከምትል መፅሀፍ የተገኘች ናት / …. አንድ ሰው በቅርቡ በስጦታ ያገኘውን አዲስ መኪና እያጠበ እያለ ጎረቤቱ ብቅ ብሎ“ ደግሞ ይቺን መኪና መቼ ገዛህ?” ይለዋል፤ ሰውየውም “ ወንድሜ ሰጥቶኝ ነው ባክህ” አለው፤ ጎረቤትየውም በቁጭት እንደው ምነው እኔም እንዲህ አይነት መኪና በኖረኝ ሲለው ባለ መኪናውም ቀበል አድርጎ እንዲህ ሲል መለሰለት ወዳጄ ይልቅስ እንደኔ ወንድም አይነት ወንድም እንዲኖርህ ብትመኝ ጥሩ ነበር አለው ፤ ይህንን ምልልሳቸውን የሰማችው የጎረቤትየው ሚስት ጮክ ብላ እንዲህ ስትል ተናገረች “እኔ የምመኘው ሰጪውን መሆን ነው !” … እንዴት አይነት ድንቅ ምኞትና ምርጥ አስተሳሰብ ነው ወዳጄ….፤ ከላይ በምሳሌ የተነሳውን ሀሳብ እንዲህ አድርጎ ማየትም ተገቢ ይመስለኛል ፤ ልክ እንደ ጎረቤትየው ሚስት ምኞት ፣ ሰጪውን መሆን መመኘትን ማለትም ወደ ርዕሰ ጉዳያችን መለስ ስናደርገው ደግሞ ከንቲባነት የገባት ከንቲባ መሆንን፣ ለመረጠው ህዝብ ታማኝ ሆኖ ሌት ተቀን ማገልገልን ፣ ከተማው የሁላችንም ነው ብሎ በጥሩ አመለካከትት እና በጎ አሳቢነት በገቡት ቃል ልክ ሆኖ መገኘትን፣ ብቁ መሪነትን እና ተአማኒ ተቀባይነትን ከነ ውጤታማነት መሆንን ልክ እንደ ከተማዬ ከንቲባ ሆኖ መገኘትን መመኘት ጥሩ ነው ….፡፡ … በቅርቡ ከሀገር ውስጥም ከውጪም የተለያዩ ሀገራት ከተሞች ከንቲባዎች እና ልዑካኖች ይህንን የከተማዬን ከንቲባ ድንቅ የአመራር አቅም እና በተጨባጭ የሚታይ የስራ ውጤት ለማየት ወደ ከተማዋ ጎራ ብለው ነበር፡፡ ባዩት ነገር እና በወሰዱት ተሞክሮ መደነቃቸውን ከሰጡት ምስክርነት መረዳት ይቻላል፡፡ እኔ ግን ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ከንቲባነት በገባቸው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከተማዬ ስለምትመራ እና እየተለወጠች ስለምትገኝ…፡፡ ከምስጋና ጋር አበቃሁ!
Показать все...
👍 3 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢትዮጵያ ከዓመታት በኃላ በታሪኳ ከፍተኛ ነዉ የተባለውን ገቢ በቡና ምርት ማግኘት መቻሏ ተነገረ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እንዳስታወቀው ሀገሪቱ በቡና ምርት ከዓመታት በኃላ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት መቻሏን በመግለፅ በግንቦት ወር ብቻ 209.54 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት የእቅዱ 107 በመቶ አሳክቷል ብሏል። ከ 2013 እስከ 2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተላከው ምርት አኳያ ከፍተኛ መሆኑን የገለፀው ባለስልጣኑ በተጠናቀቀው ወር 43 ሺህ 481 ቶን ቡና መላክ መቻሉን በሪፖርቱ ገልጿል። በ11 ወራቱ ደግሞ ከ1.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በማግኘት ሪከርድ መስበሩን የገለፀዉ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ ( ዶ/ር) በበጀት ዓመቱ 252 ሺህ 466 ቶን የቡና ምርት መላኩን አስታዉቀዋል።     
Показать все...
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የኮሪደር ልማት ስራዎቻቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በህጋዊ የመንገድ ተጠቃሚነት ለመንገድ መሠረተ ልማቶች ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ የእያንዳዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ከአምስቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውስጥ • ከአራት ኪሎ እስከ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን መታጠፊያ • ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት እንዲሁም • ከቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም በደጎል አደባባይ እስከ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን አቅጣጫ መንገዱ በትናንትናው ዕለት ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በህጋዊ የመንገድ ተጠቃሚነት ራስንና ሌሎችን ከመንገድ ትራፊክ አደጋ ስጋት በመጠበቅና ለመንገድ መሰረተ ልማቶች ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ የእያንዳዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቦ ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሔድ ክልክል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
Показать все...
👍 3 2
07:19
Видео недоступноПоказать в Telegram
ጀምረን የማንጨርሰው አንዳችም ፕሮጀክት የለም! ጠሚ ዶር አቢይ
Показать все...
IMG_7543.MP4160.31 MB
የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 129.7 ሚሊዮን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። ኢትዮጵያ የሚገኘው የተመድ የሥነ ሕዝብ ፈንድ ድርጅት እ.ኤ.አ. የ2024 የኢትዮጵያን የሥነ ሕዝብ ሪፖርት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተመድና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋጥር ዘንድሮ 129.7 ሚሊዮን መድረሱንና ቁጥሩም በ28 ዓመት ውስጥ ራሱን እጥፍ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከ0 እስከ 14 ዕድሜ 39 በመቶ፣ ከ10 እስከ 19 ዕድሜ 23 በመቶ፣ ከ10 እስከ 24 ዕድሜ 32 በመቶ፣ እንዲሁም ከ15 እስከ 64 ዕድሜ ክልል 55 በመቶ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ዓመታዊ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ከአገሪቱ ሕዝብ ሦስት በመቶው 65 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ዜጎች ሲሆኑ፣ የአገሪቱ የውልደት መጠን 3.9 በመቶ እና የመኖሪያ ዕድሜ ጣሪያ ወንዶች 64 እንዲሁም ሴቶች 70 መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡(ሪፖርተር)
Показать все...
👍 3
ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ልዑካንን አነጋገሩ። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) የኦዲት ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ በውይይታቸው፣ የኢትዮጲያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በተቋማዊ ሪፎርም ሂደት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የተቋሙን አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማዘመንም፣ “የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ ናቸው” ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት የሚያዘጋጃቸውን የጉዞ እና የይለፍ ሰነዶችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከፍ ያለ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል፡፡ ተቋሙ፣ በቅርቡ ጠንካራ የደህንነት ባህሪ ያላቸው የይለፍና የጉዞ ሰነዶች እንዲሁም አይዲዎች ማዘጋጀት እንደሚጀምርም ገልፀዋል። ለዜጎች የሚሰጠው ፓስፖርት ይበልጥ ጠንካራ የደህንነት ባህሪ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት፣ የኢ-ፓስፖርት የመስጠት አገልግሎት እንደሚጀመር ጠቅሰዋል።     ከድንበር ቁጥጥር ስራዎች ጋራ በተያያዘም፣ ዘመናዊና የተቀናጀ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የመንገደኞችን ቅድመ በረራ መረጃ (API) ልውውጥና ሌሎች አለም አቀፍ ዘመናዊ አሰራሮች ለመተግበር የሚያስችል የህግ ማእቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
Показать все...
👍 3 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የምሽት በጎ ዜና : የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አክሱም በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ ከነገ ጀምሮ ወደ ታሪኳዊቷ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀምር የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ ተናግረዋል፡፡ በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡ የበረራው መጀመር በአክሱም ከተማ ቀደም ሲል የነበረውን የቱሪስት ፍሰት ለመጨመር እና ማኅበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር እንደሚያስችል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Показать все...
2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ15 ዓመቷን ታዳጊ የደፈሩ ሁለት ወንድማማቾች ላይ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ታዳጊዋ በተፈፀመባት ወንጀል ልጅ ወልዳለች፡፡ በዲኤንኤ ወይም በዘረመል ምርመራ ከደፋሪዎቿ መካከል አንዱ የፅንሱ አባት መሆኑ መረጋገጡን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ የዘረመል ምርመራው በራሱ አቅም ማድረግ መጀመሩ ለምርመራው ስራ መፋጠንና ለፍትህ መስፈን ከፍተኛ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ተገልፆል፡፡ የግል ተበዳይ ሀምዚያ አባረሻድ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ የ15 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ቴዎድሮስ አለሙ እና ኤርሚያስ አለሙ የተባሉ ወንድማማቾች የግል ተበዳይ በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራባቸው ሰዎች ጎረቤት ናቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የአስገድዶ መድፈሩ ወንጀል ከመፈፀማቸው በፊት ጾታዊ ጥቃት ሲያደርሱባት እንደነበረ የግል ተበዳይ ሀምዚያ አባረሻድ ገልጻ አሰሪዎቿ ቤት ውስጥ አለመኖራቸውን እየጠበቁ በተለያየ ወቅት ለየብቻ በተደጋጋሚ ጊዜ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባት ለፖሊስ በሰጠችው ቃል አስረድታለች። የግል ተበዳይ ከደፋሪዎቿ ተደጋጋሚ ማስፋራት ስለሚደርስባት ጉዳዩን ለማንም ሳትናገር ብትቆይም የህመም ስሜት ሲሰማት አሰሪዎቿ ወደ ህክምና ወስደዋት በተደረገላት ምርመራ ታዳጊዋ ነፍሰጡር መሆኗ እንደታወቀና አሰሪዎቿ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹን ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ መጀመሩን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ድርጊቱን እንዳልፈፀሙ ለፖሊስ ቃል የሰጡ ቢሆንም በሁለቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በተደረገ የዘረ መል/DNA/ ምርመራ የህጻኑ አባት 99.99% ኤርሚያስ አለሙ መሆኑን የምርመራ ውጤቱ ያስረዳል። ተጠርጣሪዎቹ ተገቢው ምርመራ ተጣርቶባቸው ክስ እንደተመሰረተባቸው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሴቶችና ህጻናት ወንጀል ምርመራ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ለውጡን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ የፈሮረንሲክ ምርመራ ክፍል በዘመናዊ መልክ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ ክፍሉ የዘረመል /ዲኤንኤ/ ምርመራ መጀመሩ ቀደም ባለ ጊዜ ወደ ውጭ ሀገር ተልኮ ውጤት ይጠበቅ የነበረውን አሰራር ሊቀርፍ በመቻሉ ለፖሊስ የምርመራ ስራ መቀላጠፍና ለፍትህ መስፈን የራሱን እገዛ እያደረገ እንደሆን ተገልፆል፡፡ አዲስ አበባ ፖሊስ በህፃናት ፣ በሴቶችና ልዩ ድጋፍ በሚሽ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳይ የሚከታተሉ በአስራ አንዱም ፖሊስ መምሪዎች የስራ ክፍሎችን አደራጅቶ እየሰራ መሆኑ አስታውቆ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲያጋጥም ህብረተሰቡ ፈጥኖ ለፖሊስ ሪፖርት የማድረግ ልምዱን ሊያዳብር እንደሚገባ አሰታውቋል፡፡ በህፃናት እና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል
Показать все...
👍 3 1
Good news : የአክሱም አየር ማረፊያ ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀመረ‼️ የአክሱም አየር ማረፊያ ፤ በፌደራል መንግስት ተጠግኖ በዛሬው ዕለት ሰኔ 1 /2016 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ሰላም ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን
Показать все...
4👍 1