cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Albetre

@Albetre21 . . Contact👉0913617275 and 0923336489 or @Albetredeinstein

Больше
Рекламные посты
5 927
Подписчики
-524 часа
-377 дней
-15930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🌿#ግራ_የሚያጋባ_ግን_እውነት_የሆነ_አንድ_ታሪክ_ልንገርህታላቁ አስማተኛ (Magician) ሃሪ ሁዲኒ፤ በሆነ ወቅት ላይ ከየትኛውም እስርቤት ማምለጥ እንደሚችል ምሎ ተናገረ። ማድረግ የሚጠበቅበትም ሱፉን እንደለበሰ መታሰርና በአንድ ሰዓት ውስጥ ያለምንም ችግር ከእስርቤት ማምለጥ ብቻ ነው። እናም ብዙ አመታትን ያስቆጠረ አንድ በምዕራብ የሚገኝ እስርቤት የሁዲኒን ጥያቄ ተቀበለ። ሁዲኒ በሚታሰርበት እለት ሰዎች መጨረሻውን ለማየት በእስርቤቱ ቅጥር ማዶ ተሰበሰቡ። ሁዲኒ በራስ በመተማመን ስሜት እንደተሞላ ወደ እስር ቤቱ ገባ። የእስር ቤት ጠባቂዎችም በብረት በር በተዘጋ ክፍል ውስጥ አስቀመጡት። ሁዲኒ ኮቶን አወለቀ። ቀበቶውንም ፈታ። በሁዲኒ ቀበቶ ውስጥ የተሸሸገ፤ እንደ ሽቦ የሚተጣጠፍ እና ሃያ ሳንቲ ሜትር የሚሆን ብረት ነበር። ሁዲኒ ስራውን ጀመረ። ለሰላሳ ደቂቃዎች ያህል በሩን በያዘው ብረት ለመክፈት ታገለ። ይዞት የመጣው በራስ መተማመን አሁን ላይ ከእርሱ የለም። አንድ ሰዓት ሆነው። በላብ ተጠምቋል … ሁለት ሰዓታትን ከበሩ የቁልፍ ሽንቁር ጋር ሲታገል አሳለፈ። ደከመው … ሁዲኒ በተሸናፊነት ስሜት ጭንቅላቱን በበሩ ላይ አስደገፈው… በሩ በቀስታ ወደ ውጪ ተገፋ… ተከፈተ። ይህ በር በጭራሽ አልተቆለፈም። ሆኖም በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ይህ በር ተቆልፎ ነበር። በሁዲኒ ጭንቅላት ውስጥ ከአለም ካሉ ሁሉ ጋኖች በሚበረታ ጋን ተቆልፏል። ማንም ቁልፍ ሰሪ እንደዚህ አይነት ጠንካራ ቁልፍ አልሰራም። አእምሮ ሃይል አለው! ምን ያህል በሮችን በራስህ ላይ ቆልፈሃል? ምን ያህል ጊዜስ ራስህ በሰራኸው የአእምሮ እስርቤት ታስረሃል? በቀላሉ የሚፈቱ ግን አንተ በራስህ ላይ ያወሳሰብካቸው ምን ያህል ችግሮች አሉብህ? አንድ የአፍሪካውያን አባባል አለ "በውስጥህ ጠላት ከሌለ፤ ከውጭ የሚመጣ ጠላት አንተን መጉዳት አይችልም።" በአለም ሁሉ ካሉ ውሸታሞች በላይ የአንተ አእምሮ አንተን ይዋሽሃል። ይህን ማድረግ አትችልም… እንዲህ መሆን አትችልም… አቅሙም ብቃቱም የለህም… ምክንያቱም ልክ እንደ ሁዲኒ የተቆለፈውን በር ብቻ ነው የሚያሳየን። ከፍተህ ውጣ… አእምሮህ የሚልህን አትመነው። 🌼 ነገ መልካም ይሆናል ! 🌼
Показать все...
👍 1
ውሳኔ ፨፨፨ << አንድ የወታደር ሐኪም ነበር አሉ። የሚሰራው ጦር ግንባር ላይ ነው። ወታደሮች ሲቆስሉ እንዲታከሙ፣ ሲሞቱም እንዲቀበሩ መርምሮ የሚወስነው እርሱ ነበር። ያለ እርሱ ውሳኔ የሞቱትን መቅበር እና ቁስለኞችን ማሳከም፣ ታመምን የሚሉትንም ወደ ሆስፒታል መላክ አይቻልም ነበር። ፧ አንድ ጊዜ ጦርነቱ በጣም ኃይለኛ ሆነና የሞተው እና የቆሰለው በዛ። እያንዳንዱን እየመረመረ ይኼ ሞቷልና ቅበሩት፣ ይህም ቆስሏልና አክሙት ማለቱ ለዚያ ሐኪም ከአቅሙ በላይ ሆነ። በዚያ የጦር ግምባር ላይ ብቸኛው ሐኪም እርሱ ብቻ ነበርና ያንን ሁሉ ወታደር አንድ በአንድ እያየ መወሰን ከበደው። የጠላት ጦር እየገፋ፣ ሙትና ቁስለኛውም እየበዛ መጣ፣ ያም የወታደር ሐኪም ደከመው። ፧ በመጨረሻ አያሌ ወታደሮች ወደ ወደቁበት ቦታ ሄደና አይቶ "እነዚህ በሙሉ የሞቱ ስለሆኑ ይቀበሩ" ብሎ ብጅምላ ወሰነ። የታዘዙት ቀባሪዎችም የወደቁትን እያነሱ መቅበር ጀመሩ። በመካከል ላይ አንድን ወታደር አንስተው ሊቀብሩት ሲሉ "የት ልትወስዱኝ ነው?" ብሎ ጠየቃቸው። ቀባሪዎቹም "ልንቀብርህ ነዋ" አሉት። "እንዴት በሕይወት እያለሁ ትቀብሩኛላችሁ" ሲል ጠየቃቸው። "አይ ዶክተሩ ሞተሃል ብሎናልና መቀበር አለብህ" አሉና መለሱለት። "እንዴ በሕይወት መኖሬን እያያችሁ፣ በዓይናችሁ እያረጋገጣችሁ፣ እያነጋገርኳችሁ እንዴት ሞተሃል ትሉኛላችሁ፡ ዶክተሩ ቢሳሳት እንኳን እናንተ አርሙት እንጂ" አለ ወታደሩ ገርሞት። ፧ "አየህ" አለው አንዱ ቀባሪ "ዋናው ነገር የኛ አለመሞትህን ማረጋገጥ ወይንም ያንተ አለሁ ማለት አይደለም፡ የዶክተሩ ውሳኔ ነው። ዶክተሩ ሞተሃል ካለህ ሞተሃል፡ አለ ካለህም አለህ፡ አንተ ከዶክተሩ ልትበልጥ አትችልም፡ የተመደብነው ያለውን እና የሞተውን እየመረመርን ልንለይ አይደለም። የተመደብነው መመርያ ለማስፈጸም ነው። ውሳኔ ለማስተግበር ነው። እናም ሞተሃል ተብሎ ስለተወሰነ የግድ መቅበራችን ነው" ብሎ ነገረውና ወስደው ቀበሩት። ፧ የዶክተር ውሳኔ። ሀገር የሚገድል፡ ሀገርም ሲገድል የኖረ፣ ሀገርም እየገደለ ያለ።... ለምን እንዴት ትክክል ነው ወይ? እንደገና መመርመር አለበት ወይ? ብሎ የሚጠይቅ ኅሊና ሲጠፋ፣ "ከላይ የወረደ ሁሉ ትክክል ነው"የሚል እምነት ሲሰፋ፣ አሉሁ ማለት፣ መተንፈስ እና መንቀሳቀስ፣ የደም ዝውውር እና የሕዋሳት ንቅናቄ ብቻ መኖርን ሊያመለክት አይችልም። ዶክተሩ አድገናል ካሉ አድገናል፣ አላደግንም ካሉ አላደግንም። አሸንፈናል ካሉ አሸንፈናል፤ አላሸነፍንም ካሉም አላሸነፍንም። ከታች ያሉትም ያንኑ ከመፈጸም እና ከማስፈጸም በቀር አእምሯቸውን አይጠቀሙበትም።.... ፧ በፖለቲካው ዘንድ ብቻ ሳይሆን በዕውቀቱ መስክም እገሌ የተባለ የምዕራብ ታሪክ ዐዋቂ፣ የሥነ ልቡና ሊቅ፣ የፍልስፍና ምሁር፣ የአርኪዎሎጂ መርማሪ፣ የባሕል ባለሙያ አንድ ጊዜ ከተናገረ እርሱን ተከትሎ ማስተጋባት እና የርሱን መጽሐፍ እየጠቀሱ መከራከር እንጂ ሊሳሳት ይችላል፣ ያላወቀው ነገር ሊኖር ይችላል፣ ደግሞም እኔም ከርሱ የተሻለ ላውቅ እችላለሁ ብሎ የሚያስብ ያለ አይመስልም።...>> ፨፨፨ ምንጭ ፦ " ጠጠሮቹ እና ሌሎች...ገጽ 155-158 " ደራሲ ፦ ዳንኤል ክብረት ኅትመት ፦ 2003
Показать все...
👍 4
#ራስን_ለመግዛት_የሚረዱ_6_ነጥቦች! 1. ደካማ ጎኖችዎን ይለዩ፦ ደካማ ጎኖቻችሁን ችላ ማለት እንዲጠፉ አያደርጋቸውም። ስለዚህ ጣፋጮችን መብላት የክብደት መጨመሮ ምክንያት ነው? ማህበራዊ ሚዲያ ማዘውተር ምርታማነትዎን ቀንሶታል? ድክመቶችዎን ይወቁ። ድክመቶችዎን ማወቅ አዎንታዊ ለውጥን ለመፍጠር የመጀመሪያው እርምጃ ነው። 2. ግልፅ የሆነ ስልት ይቀምሩ፦ ከፍ ያለ ራስን የመግዛት አቅም በድንገት አይመጣም። ይልቁንም የአእምሮ ጡንቻን ለመገንባት የሚያግዝዎት ስልት ማበጀት ያስፈልግዎታል። ብዙ ጊዜ ወደ ጂም እንደመሄድ ያሉ ጥሩ ልምዶችን መጨመር አልያም ብዙ ሶሻል ሚዲያ መጠቀምን የመሰሉ መጥፎ ልምዶችን ማስወገድ ከፈለጉ እነዚህን ዓላማዎችዎን ወደ ተግባር ለመቀየር ዕቅድ ያስፈልግዎታል። በየቀኑ መውሰድ የሚያስፈልጎትን እርምጃዎችን በግልጽ ይዘርዝሩ። 3. የሚፈታተኖትን ነገሮች ያስወግዱ፦ ቤትዎ ጣፋጮች ምግብ ከተከማቹ ክብደትን ለመቀነስ ራስን የመግዛትን አቅም ያዳክማል። ይልቁን እያንዳንዱን ኩኪስ፣ ቺፕስ እና ሌሎች ጣፋቾችን ላለመብላት በመሞከር ጊዜዎን ያባክናሉ። ድክመትዎ በየሁለት ደቂቃዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን መፈተሽን የሚያካትት ከሆነ ፌስቡክን የሚያግድ መተግበሪያ ይፈልጉ። ፈተናዎችን መገደብ በጊዜ ሂደት የበለጠ ራስን የመግዛትን አቅሞን እንዲገነቡ ይረዳዎታል። 4. ምቾት ማጣትን ይለማመዱ፦ ምቾት ማጣትን ለማስወገድ መሞከር ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን የአጭር ጊዜ ምቾትን መሻት ብዙውን ጊዜ የረጅም ጊዜ ችግሮችን ያስከትላል። እናም በተሸነፉ ቁጥር ጭንቀትን መቋቋም እንደማይችሉ ለራስዎ ያሳምናሉ። ምቾት ማጣትን ይለማመዱ፤ ያ ማለት እርስዎ ከሚያስቡት በላይ ለተጨማሪ ደቂቃ መሮጥ ወይም ጣፋጭ ምግቦችን የመብላት ፍላጎትን መቃወም ባጠቃላይ ምቾት ማጣት ጠላት አለመሆኑን እንዲያምን አዕምሮዎን ያሰልጥኑ። 5. ግቦቾን ያስታውሱ፦ ፈተናን ሲጋፈጡ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውን ነገሮች ለራስዎ ያስታውሱ። ከግቦችዎ ጋር ሲጣበቁ የሚያገኟቸውን ነገሮች ሁሉ ዝርዝር ይፃፉ፤ ተስፋ ለመቁረጥ በሚፈተኑበት ጊዜ ዝርዝሩን ያንብቡ። 6. ለውድቀት ያለዎትን አመለካከት ይቀየሩ፦ መሻሻል ብዙውን ጊዜ በቀጥታ መስመር ላይ አይመጣም። ስህተት ሰርተዋል ማለት ከዚህ በኋላ አይሳካሎትም ማለት አይደለም። ስህተት የመሻሻል ሂደት አካል ነው። ከእነዚህ ስህተቶች የሚመለሱበት መንገድ ነው በጣም አስፈላጊው ነገር፤ ከተሳሳቱት እርምጃዎችዎ በመማር በሚቀጥለው ጊዜ የተሻለ ለማድረግ ቁርጠኛ ይሁኑ።
Показать все...
" አንድ ነገር ' እንዴት ' እንደሚደረግ የሚያውቅ ሰው ሁልጊዜ ስራን ያገኛል ፤ ያ ነገር ' ለምን ' እንደሚደረግ የሚያውቀው ግን ሁልጊዜ የርሱ አለቃ ይሆናል ። " #ዲያኔ ራቪትች
Показать все...
#ወደ_ውስጥህ_ቆፍር!
"ሁሉም ነገር ሁለት ጊዜ ይፈጠራል መጀመሪያ አእምሮ ውስጥ ከዚያም በእውኑ ዓለም ላይ" -ሮቢን ሸርማ ከመሬት ስር የተቀበረው ነው ከመሬት በላይ ያለውን የፈጠረው። የማይታየው የሚታየውን ፈጠረ። እና ይህ ምን ማለት ነው? ፍሬህን መቀየር ከፈለግክ መጀመሪያ ስርህን ቀይር፤ የሚታየውን ለመቀየር መጀመሪያ የማይታየውን መቀየር ይኖርብሃል። በእያንዳንዱ ጫካዎች፣ በእያንዳንዱ ገበሬ ማሳ፣ በእያንዳንዱ የአትክልት ስፍራ… ከመሬት በታች ያለው ከመሬት በላይ ያለውን ይፈጥራል። ትኩረትህንም በተበላሸው ፍሬ ላይ ስታደርግ ለውጥን አታመጣም። የነገ ፍሬህን ዛሬ ላይ መለወጥ ትችላለህ፤ ሆኖም ይህን ለማድረግ ወደታች በደንብ መቆፈር ይኖርብሃል።
#ቁምነገሩ_ ዛሬ ወደ ውስጥህ በደንብ እንድትቆፍር አበረታታሀለሁ፡፡ ስርህን ቀይር… ፍሬው በአስደናቂ ሁኔታ ይቀየራል፡፡


🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊
Показать все...
👍 1
"ስዎች ከአንገት በላይ ከአላደጉ ከአንገት በታች ነው የሚኖሩት ::ከአንገት በታች ድግሞ ምንም ማሰብ የሚችል ነገር የለንም። ሰሜትንም መግዛት የሚችል ነገር የለንም! ዶ/ር ምህረት ደበበ
Показать все...
2
የብርሀን ፀዳል💥 🌿"ሰዎች ከህይወታችሁ ሊወጡ ሲወስኑ መጀመርያ የሚሰማችሁን ነገሮች ሁሉ እንዳከተሙ አለም እንደተፈፀመች የሚሰማችሁን ያንን ስሜት አትፍሩት። የቻላችሁትን ያህል እዘኑ አልቅሱ። ነገር ግን በውስጠ ህሊናችሁ ነገሮች እንደሚያልፉ የሚነግራችሁን ጥቂት ጥንካሬ በውስጣችሁ ያዙት። ስሜቱ ተመላልሶ ተመላልሶ ይመጣል። እራሱን ይገልፅ ዘንድ ፍቀዱለት። እንደ ጥንካርያችሁ መጠን ጊዜው አንድ ቀን አንድ ሳምንት አንድ ወር አንድ አመት ሊወስድ ይችላል . . ነገር ግን ከሩቅ የብርሀን ፀዳል ሲወጣ ታያላችሁ። በርግጥ ሁሉም ነገር መጨረሻ ላይ መልካም ይሆናል። ተዛንፎ የሚቀር ፤ ወድቆ የማይነሳ ሰው ተስፋ የቆረጠ ብቻ ነው።" 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾
Показать все...
👍 1 1
🌿ቢ.ኤል ነኝ ህይወቴ እንደማይቀየር አውቀዋለሁ! ሦስት ዓመት አብረን የቆየኝ ፍቅረኛ አለኝ፡፡ በጣም ይወደኛል፡፡ ለእኔ የማይሆነው ነገር የለም፡፡ እኔም እወደዋለሁ፡፡ ግን በገንዘብ በኩል ያለው አይደለም፡፡ አንድ ድሮ ከሰፈር ጀምሮ የማውቀውና አሁን ውጭ የሚኖር ጓደኛዬ ደግሞ ሁሌም እንደሚወደኝ ይነግረኛል፡፡ እኔ ግን እንደተራ ጓደኛ ካልሆነ በቅጡ እንኳን አዋርቼውም አላውቅም፡፡ እንደቀልድ እያደረገ ግን አንቺን አግብቼ እዚህ ማምጣቴ አይቀርም ይለኛል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ሊመጣ እያሰበ ነው፡፡ እናም ሰሞኑን በደንብ እንዳስብበትና ይዞኝ መሄድ እንደሚፈልግ ፃፈልኝ፡፡ ፍቅረኛዬን ለገንዘብ ብዬ ባልተወው ደስ ይለኛል፡፡ ግን እዚህ ብኖር ህይወቴ እንደማይቀየር አውቀዋለሁ፡፡ ከፍቅረኛዬ ጋር ብንጋባ እንኳ የድህነት ኑሮ እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ፡፡ እኔ ደግሞ ተምሬና ሰርቼ የራሴንና የቤተሰቦቼን ህይወት መቀየር እፈልጋለሁ፡፡ ውጭ ላለው ጓደኛዬ ምንም የሰጠሁት ምላሽ የለም፡፡ ነገር ግን ዕድሉን አለመጠቀም ትልቅ ስህተት መስሎ ይታየኛል፡፡ 😒ምን ልወስን ⁉️ 👇 መተንፈስ ማጋራት የምትፈልጉ ታሪካችሁን ያጋሩን👇 🎖 @albetre26🎖 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 💫https://t.me/albetre26💫 🎖@albetre26🎖
Показать все...
‼️‼️‼️ተጀመረ‼️‼️‼️ 🌿እንደሚታወቀው አዲስ ፕሮግራም ጀምረናል እሱም 😔ጭንቆታችሁን የማጋራት እና የመተንፈስ አገልግሎት መጀመራችን ነው። 🌿በጣም እንደወደዳችሁት ከምትልኩልኝ መልህክት ተረድቻለውኝ! ‼️ምንድነው የሚያስጨንቃችሁ? ‼️ምንድነው ለመወሰን ያቃታችሁ? ‼️ምንድነው መተንፈስ ማጋራት የምትፈልጉት? ⚡️ስለፍቅር ስለ ሱስ ስለ ትዳር ስለ ህይወት!⚡️ 👇 መተንፈስ ማጋራት የምትፈልጉ ታሪካችሁን ያጋሩን👇 🎖 @albetre26🎖 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 💫https://t.me/albetre26💫 🎖@albetre26🎖
Показать все...

1
🌿#አሁን_ነገሮች_መልካም_ሳሉ_አድርጋቸው! የአእምሮህን ቁርጠኝነት የመፈተን ትምህርት ይኸውልህ፤ ከሳምንቱ ውስጥ በቂ ያልሆነና በጣም ርካሽ የሆነ ምግብ ብቻ የምታገኝበትን ክፍል ውሰድ፣ ትንሽ ቡቱቶ የሆኑ ልብሶች ልበስና የእውነት የምትፈራው መጥፎ ነገር ይህ መሆኑን ራስህን ጠይቅ፡፡ ራስህን ከፊት ለሚመጡ ከባድ ጊዜያት ማዘጋጀት የሚገባው ጊዜው መልካም ሲሆን ነው፡፡ ምክንያቱም እድል መልካም ሲሆን፣ ነፍስ ከጥፋቶቿ በተቃራኒ መከላከያ መገንባት ትችላለች፡፡ ስለሆነም፣ ወታደሮች ጊዜው ሲደርስ እንዳይደክሙ፣ ስልጠና የሚወስዱት በሰላም ጊዜ ነው፤ ምሽግ የሚገነቡት ገና ጠላት ሳይመጣ ነው፤ ራሳቸውን የሚያደክሙት ጥቃት ሳይኖር ነው፡፡” #ሴኔካ ከወሩ ውስጥ አንዱን ቀን የችግር፣ የረሃብ፣ ሙሉ በሙሉ የመገለል ወይም ልትፈራ የምትችለውን ሌላ ነገር የምትሞክርበት ብታደርገውስ? በመጀመሪያ ከሚያጋጥምህ መደንገጥ በኋላ፣ የተለመደ እንደሆነ ሊሰማህ ይጀምራል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ በጣም አስፈሪ አይሆንም፡፡ አንድ ሰው ሊለማመዳቸው አስቀድሞ መፍትሔ ሊያገኝላቸው የሚችላቸው ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ የኪስ ቦርሳህ እንደተሰረቀብህ አስመስል፡፡ ከሚመቸው ፍራሽህ ርቀህ ወለል ላይ ተኛ፡፡ ወይም መኪናህ በመወሰዱ ሁሉም ቦታ በእግርህ መሄድ እንዳለብህ ሁን፡፡ ስራህን እንዳጣህና አዲስ ስራ ማግኘት እንደሚያስፈልግህ አስመስል፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች ማሰብ ብቻ ሳይሆን ኑራቸው፡፡ አሁን ነገሮች መልካም ሳሉ አድርጋቸው፡፡ ሴኔካ እንደሚያስታውሰን፣ “ነፍስ አስቀድማ ለጭንቀት ጊዜ ራሷን የምታጠነክረው ከሀሳብ የመከላከል አቅም ባላት ጊዜ ነው… ቀውስ በመጣ ጊዜ ወደ ኋላ የሚያፈገፍግ ሰው እንዳይኖር፣ ከመምጣቱ በፊት አሰልጥነው፡፡” #ጠቃሚ_መልእክት ●•• ◉ Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾
Показать все...
1