cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Meleket Tube

መንፈሳዊ መረጃዎችን እንዲሁም ዝማሬዎችና የወንጌል ትምህርቶች በየእለቱ ከዚህ ገፅ ያገኛሉ። ኢየሱስ በክብር ይመጣል! Find us on more- https://linktr.ee/meleket_tube Contact us - @LiveMeleket_Bot

Больше
Рекламные посты
12 242
Подписчики
-424 часа
-297 дней
-13430 дней
Архив постов
በልባችን ፅላት የተፃፈ፣ በመንፈሳችን በውስጥ ሰውነታችን የተቀረፀ የማይሰረቀው ታቦታችን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ...
Показать все...
ድንቅ_ስጦታ አመታዊ የዝማሬ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተከርስቲያን ተካሄደ። በላቭ ኤንድ ኬር አዘጋጅነት በየአመቱ የሚደረገው ድንቅ ስጦታ የዝማሬ ኮንሰርት እሁድ ታህሳስ 15/2015 በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ባደረገው የዝማሬ አገልገሎታቸው የሚታወቁት ተወዳጁ የክብር ዶ/ር ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ አገልግለዋል። በየአመቱ ይሄንን ዝግጅት ከላቭ ኤንድ ኬር ጋር በትጋት እያዘጋጀ ያለው ዳዊት ጌታቸው ከኪንግደም ሳውድን ጋር ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን የሃገርኛ ዝማሬን ከአለም አቀፍ የዝማሬም ምቶች ጋር በማቀናጀት ድንቅ ዝማሬዎችን የሚያቀርቡት "ሪትም ኳይሮችም" ተወዳጅ ዝማሬዎቻቸውን አስደምጠዋል። ላቭ ኤንድ ኬር ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አቅመ ደካሞችን ለማገልገል የተነሱ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ሲሆን በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ ከ20 በላይ ድጋፍ ማድረጊያ እና ወላጅ አልባ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል እንዳላቸው ታውቋል። በዕለቱም የተደረገውድንቅ_ስጦታ የተሰኘው ይህ ልዩ የመዝሙር ኮንሰርት በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ድጋፍ ማሰብሰቢያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል።
Показать все...
የዘማሪት መክሊት ግርማ የአስክሬን ሽኝት ስነስርዓት እየተካሄደ ነው።🕊
Показать все...
የ እህታችን ዘማሪት መክሊት ግርማ እሬሳ ዛሬ ሀዋሳ ገብቷል የቀብር ስነስርዓት የሚከናወንበትን ጊዜ እና ቦታ በቅርቡ እናሳውቃለን። እግዚአብሔር  መፅናናትን ለሁሉም ይስጥ አሜን።
Показать все...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓስተር ዮናታን አክሊሉ በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን ፣ ነቢይ ኢዩ ጩፋ በክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን ላይ ክስ መሠረተች። በመ/ር አቤል አሰፋ (ኢኦተቤ ቴቪ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሕግ አገልግሎት መምሪያ በኩል ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ፩. ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ፪. የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን ፫. ነቢይ ኢዩ ጩፋ ፬. ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን አድራሻቸው ክስ መሥርታለች። የአቤቱታው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግርና አደገኛ የሆነ የሃይማኖትን ክብር የሚነካ የአምልኮ ሥርዓትና እምነትን የሚያንቋሽሽ የዘለፋ እና ሐሰተኛ ንግግር በመፍጠር ለሁከትና ብጥብጥ መነሻ የሚሆን ድርጊት በፈጸሙ ግለሰቦችና ተባባሪ ተቋማት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጣራ ጠይቃለች። ሙሉ ክሱን ለማንበብ ከላይ ያሉትን ምስሎች ይጫኑ።
Показать все...
ዛሬ የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቦርድ ደረጃ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰሞኑን ባቀረበች ጥያቄ ዙሪያ ስብሰባ አድርገው ነበር። በስብሰባው ላይ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኒቱን ያስተማረው ትምህርት ላይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፥ ካልጠየቀ ግን፦ - ከሰላም ሚኒስቴር ላይሰንሱ እንደሚሰረዝ - ሚዲያው እንደሚዘጋ - እስር እንደሚጠብቀው የተወያዩ ሲሆን የዛሬው ዋናው አጀንዳ በዋናዎቹ አመራሮች ታይቶ የሚወሰን ለነገ ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል። አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የእምነት ተቋምን ሰደበ የሚል ክስ ቀርቦበታል። በእውነት ተሳድቧልን? ቪዲዮውን መመልከት ይቻላል። የጠቀሰው ከቤተ እምነቱ እዕዋልድ መጽሐፍት ነው። መጽሐፍ የእነርሱ ካልሆነ ስም አጥፍቷልና በዚያ ሊጠየቅ ይችላል። ከዚያ ውጪ በየ አደባባዩ የሚሸጥና በቤተክርስቲያኒቱ አሳታሚነትና አከፋፋይነት የታተመን መጽሐፍ ላይ ምላሽ መስጠት በምንም መንገድ ወንጀል አይደለም። የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች በዚህ ጉዳይ የመጨረሻውን ውሳኔ ከማስተላለፋቸው በፊት ሊያስቡበት ይገባል። የወንጌል አማኞች ከ ሰላሳ ሚሊዮን በላይ ናቸው ነገሩ በአንድ አገልጋይ ዮናታን ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን መላውን የወንጌል አማኞች ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል። በሌላ መረጃ እንገኛለን። አገራችንን ሰላም ያድርግልን።
Показать все...
ዜና እረፍት 🕊🕊🕊 ለእህታችን ዘማሪት መክሊት ግርማ ሁሉም የሚቻለውን ሁሉ አድርጓል፤ ለህክምና የሚያስፈልገው ትብብር ሁሉ በቀና መልኩ ተሳልጧል። እግዚአብሔር የፈቀደው ሆነና ወደ ህንድ ለህክምና አቅንታ ህክምናዋን ለመጀመር ጥረት ሲደረግ ሕይወቷ አልፏል። በልጅነቷ ወዳገለገለችው አምላኳ ሄዳለች። ለቤተሰቧና ለወዳጅ ዘመዶቿ ሁሉ እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን!!
Показать все...
#ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #ምህረትአብ_አሰፋን_መጀመሪያ_መቅጣት_የለባትምን??? ምህረትአብ 30 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለውን ሃይማኖት ፕሮቴስታንትን(የወንጌል አማኞችን) ትልቁ ጋንጩር ሰይጣን ናቸው በማለት በግልጽ ተሳድቧል። በሁለተኛ ደረጃ ምህረትአብ መጽሐፍ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ነው ያለውን የልሳን ስጦታ ላይ አላግጧል፣ ተሳልቋል መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "“እግዚአብሔርም #በቤተ_ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ #የልዩ_ልዩ_ዓይነት_ልሳኖችንም አድርጎአል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥28 “በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤” 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥2 ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ልሳን የሚናገረው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም ፣ በሰው ቋንቋ ሳይሆን በሰማይ ቋንቋ ለእግዚአብሔር የሚነገር በውስጣችን በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የሚሰጥ የፀጋ ስጦታ ነው።ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱ በልሳን እንደሚፀልይ ግን በአእምሮ ምንም ሊረዳው እንዳልቻለ ጠቅሷል ፕሮቴስታንትን(የወንጌል አማኝ) እና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለማጋጨት ቀን ከሌት የሚሰራውን ምህረት አብ አሰፋ ለምን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ለምን ዝም አሉት?
Показать все...
#ከዘፈኑ አለም ወደ ጌታ ዘወር ያለችዉ ተወዳጇ #ቸሊና ባለፈዉ አመት ጌታን እንደግል አዳኝዋ ተቀብላ መጠመቋ ይታወቃል። አሁንም በክርስታና ህይወቷ ስር በመስደድ በእናት ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ማገልገል ጀምራለች። እንኳን ጌታ እረዳሽ በአለቱ በክርስቶስ ላይ ፈጽመሽ ተተክለሽ ኑሪ ስለ አንቺ እግዚአብሔር ይመሰገናል። መለከት Tube
Показать все...
ባዕድ 2 - ሌላ ኢየሱስ || Documentary Film https://www.youtube.com/watch?v=ZE4A_HAmlcU
Показать все...