cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ye fikr nuro tuber

Bezhi chinal Yefikr zefen Ye fikr gitim Ye fikr mininet Yeteleyayu voicich Achachir ye fikr tarikoch Liboledoch Ena leloch ye fikr tarikochi beyegizewuna beyeseatu tikus merejawochi enastelalifalen Feta zena yibelubet..... @yefikrnuro

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
165
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

❤️የፍቅር መድረክ❤️ ፀጋ..... እባላለው......ቃል የማላውቀው ስልክ ከማላውቀው ስም ጋር ተዳምሮብኝ አላወቅኩሽም ለማለት ተገደድኩኝ .... አዎ አታውቀኝም ..... ብላ የሆዷን ትዘረግፍልኝ ያዘች ... እንደ የትኛዋም ኢትዬጲያዊት ሴት ፀጋም በቤተሰቦቿ በከፍተኛ ቁጥጥር ያደገች ጨዋ የጨዋ ልጅ መሆናን ድፍን የሰፈሯ ሰዎች ይመሰክሩላታል .... ብዙ የፍቅር ጥያቄ ቢቀርብላትም ትምህርቴን ከጫፍ ሳላደርስ ፍንክች የለም እንዳለች የዩኒቨርሲቲ ፈተናዋን አልፋ አርባምንጭ ተመድባ ገባች ...... በትምህርት ላይ ሳለች መሰል የፍቅር ጥያቄዎች ይዥጎደጎዱላት ነበር .... ፀጋ ወይ ፍንክች ልቧ ውሃ እንደማይገባው እንደባልጩት ድንጋይ ደድሯል ...... ትምህርቷንም በጥሩ ውጤት ተመርቃ ስራ ጀመረች..... በውበቷ የተማረኩ የስራ አጋሮቿ ጭምትነቷ ሲታከልበት ለትዳር ይመኛት ጀመር የተወሰኑት ደፍረው ጠየቋት..... ፀጋ በጠየቋት ላይ ቁጣዋ አየለ እንዴት ለፍተው እዚህ ያደረሱኝን ቤተሰቦቼን ሳልጦር አገባለው ..... ከጥቂት አመታት በሃላ ማስተርስ ለመማር እድል ደርሷት ወደ ውጪ ሀገር ሄደች መሰስተርሷን ተምራ ስትመለስ እደሜዋ ሰላሳን ዘሎ ነበር .. ነገር ግን ፀጋ አሁንም ድንግል ናት አሁንም ሀሳቧ ቤተሰቦቿ ብቻ እና ብቻ ነበሩ.... በማስተርስ መመረቋ የነበራትን ቦታ ከፍ አደረገው ደምዟም ምቅ ተደርጎ ተጨመረላት.... ቤተሰቦቿንም በጥሩ ሁኔታ መጦር ጀመረች ..... በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለች የገንዘብ ክፍል የበላይ ሀላፊ ሆና ከምትሰራበት መስሪያ ቤት የክስ ደብዳቤ ደረሳት..... ፀጋ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ከ389 ሚሊዬን ብር በላይ በማጭበርበር ወንጀል ተከሳ በማታውቀው ሁኔታ ለፍርድ ቤት ቀረበች ..... እንደተለመደው ግራ ና ቀኙን የተመለከተው ፍርድቤትም 9 አመት ፈረደባት.... ፀጋ ተስፋዋ ተሟጠጠ አንዳች ልጅ እንኳን ሳትወልድ አንድ እንኳ የፍቅር አጋር ኖሯት ደስታዋን እንኳን ሳታጣጥም ከነድንግልናዋ ከእስር ቤት ውስጥ ታጅላ ለመቀመጥ ተገደደች ..... ያኔ የገፋቻቸው ወንዶች በአይኖቿ ይርመሰመሱ ጀመር ..... 4 አመታት አለፉ .... ሀናን 35 አመት ሆናት ልጅ መውለጃዋ ማብቂያው ላይ ሲደርስ እድሜዋ ይሮጥ ጀመር 3 አመታት ተጨመሩ 38 ሲሆናት ተስፋ ቆርጣ እዛው እስር ቤት ውስጥ ካሉት ችግኞች አንዱ ልጄ ማለት ጀመረች ትንከባከበውም ያዘች....... ከ አመት በሃላ በ39 አመቷ ከእስር ተፈታች አለም ሁሉ አዲስ ሆና ጠበቀቻት ያ ሁሉ ያሳድዳት የነበረ ወንድ ብታሳድደው እንኳ ምኗ ሴት አሰዳቢ ናት እያለ እንደ ሸርሙጣ ያያት ጀመር..... ፀጋ ግን ድንግል ናት የልጅ መውለጃዋ እድሜ እንዳያልፍ ወንዱን ለማሳሳት ብትምክር እንኳ ሁሉም አሻፈረኝ .... አልፈልግም ምን አስባ ነው...... ኤች አይቪ ሳይኖርባት አይቀርም እንዲ የምትሆነው እያለ ተዘባበተባት...... ፀጋ ቅስማ እንደተሰበረ አይኗን በአይኗ ለማየት እንደጓጓች አሁንም አለች ..... ጥቂት ጊዝያቶች ብቻ ነው የቀሩኝ እባክህን ከኔ መውለድ የምትፈልግ ወንድ ካለህ .... አይኔን በአይኔ ሳላይ እንደልምት እርዳኝ .....አባትነቱን መቀበልም አለመቀበልም መብትህ ነው ትላለች....... ꧁༺༒༻꧂ 🥰የፍቅር ቃና🥰 ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
نمایش همه...
Share share
نمایش همه...
نمایش همه...
Ye fikr nuro tuber

Bezhi chinal Yefikr zefen Ye fikr gitim Ye fikr mininet Yeteleyayu voicich Achachir ye fikr tarikoch Liboledoch Ena leloch ye fikr tarikochi beyegizewuna beyeseatu tikus merejawochi enastelalifalen Feta zena yibelubet..... @yefikrnuro Inb @fikriye19

​​​​┄┉✽̶🌺✿ምኞቴ🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል 9 ❁▬▬▬         ✍.... ኤዲ ለቢኒ ካላት ፍቅር  የተነሳ ስታከብረዉ ወደር የላትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ለሱ ንግግር ቦታ ትሰጣለች፡፡ በእያንዳንዷ ክንዋኔም ላይ የቢኒ ቃል ተቀዳሚ ነዉ፡፡ ... ሁለቱም በእኩል ቅጽበት "እ..." ሲሉ... ኤዲ ቀደም ብላ "ወይዬ ቢኒ ምን ልትለኝ ነበር?" አለችዉ፡፡ ቢኒም "ኤዲዬ የኔ ቆንጆ አንቺ ሁሌም እኔን ታስቀድሚያለሽ፡፡ "የኔ ፍቅር ታዉቃለሃ?" ..... "ምኑን ነዉ የማዉቀዉ ኤዲዬ?" ..... "እኔና አንተ ከተጋባን አራተኛ አመታችን ነዉ፡፡" ..... " እ... በፍቅር ክንፍ አድርገሽኝ ያበድኩልሽ ቀን! ያ ቀን እንዴት ይጠፋኛል ዉዴ!?" ..... "እሱ አይደለም ፍቅሬ" ..... "እና ምንድን ነዉ ....?" ..... "ከተጋባን ቆይተናል ግን እስካሁን...." ... "ማሬ አታስጨንቂኛ ፕሊስ ንገሪኝ?" ..... "ቢኒ የኔ ዉድ...." .... "ወይዬ ኤዲ የኔ ቆንጆ! ... ንገሪኛ!" ..... "ልጅ ልወልድልህ አልቻልኩም ቢኒ" ቢኒ በዉስጡ ያለዉን ስሜት ኤዲ አወጣችዉ፡፡ "ሁለታችንም አንድ አይነት ነገር ነበር የምናስበዉ ማለት ነዉ?" አለ በሆዱ፡፡ ትክክለኛ ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ነዉ የሚቀዱት ማለት ይሄኔ ነዉ፡፡ ቢኒ ኤዲን ሊጎዳት አልፈለገም.... ..... "ኤዲዬ ይሄኮ ታዲያ የፈጣሪ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ፈጣሪ ባለ ጊዜ ትወልጂ ይሆናል፡፡" አላት፡፡ ..... " አዎ የኔ ፍቅር ፈጣሪ ካለ እወልድ ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ አንተ ከኔ በይበልጥ ልጅ ማግኘት፤ ዘርህን መተካት ይኖርብሃልኮ ዉዴ!" ..... "እና ምን ላርግ ዉዴ? ልጅ ከመዉለድ በላይ አንቺ ለኔ እንደምታስፈልጊኝ ታዉቂያለሽ፡፡ ስለዚህ ማሬ...." ፡ ፡ ፡ ረዲኤት ስለ ቢኒ ስታብሰለስል ቆይታ ሲጨንቃት  ጋደም ባለችበት እንቅልፍ ሸለብ አድርጓታል፡፡ እማማ በለጡም የረዲ የሰሞኑን ቅብዥር አላምራቸዉ ቢል ወደ ረዲ የመኝታ ክፍል ገብተዉ ከጎኗ ቁጭ ከማለታቸዉ ነበር ... ረዲ እንደ ቅብዥር ነገር ጀምሯት "ቢኒ እወድሃለሁ" የምትለዉ፡፡ እማማ በለጡ በቆሙበት ደርቀዉ ቀሩ፡፡እስከዛሬ ልጃቸውን ምን እዲህ እንፈሚያደርጋት ገባቸው ቢኒ የኤዲ ባል...እንዴት?... እያሉ ብቻቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ምን ይበሉ? ሊቀሰቅሷት አቃታቸዉና እንደገና መለስ አሉ፡፡ "በአካል ባታገኘዉ እንኳ በህልሟ እስኪ የሷ ይሁን!" እያሉ ይመስላሉ፡፡ እማማ በለጡ በጣም ጥሩ ሴት ናቸዉ፡፡ ልጃቸዉ አንድ ከመሆኗ የተነሳ እንደ እናት ብቻ ሳይሆን እንደ እህትም፣ እንደ ጓደኛም ሆነዉ ነዉ ያሳደጓት፡፡ ረዲን ዛሬ ጫን ያለዉ ይዟት እንጂ አንድም ነገር ከእናቷ ደብቃ አታዉቅም፡፡ አሁን ግን ... የሰዉ ባል አፈቀርኩ ብትል እንኳን ለእናት ለጓደኛም ለመንገር ያሸማቅቃል፡፡ እማማ በለጡ ጉዳቸዉን ሰምተዉ በእጃቸዉ መዳፋ አገጫቸዉን ይዘዉ "ጉድ... ጉድ" እያሉ ከረዲኤት ክፍል ወጡ፡፡ እማማ በለጡ ከመዉጣታቸዉ ረዲኤት ብርግግ ብላ ስትነሳ ፊቷ በላብ ተዉጧል፡፡ በቅብዥሯ "እወድሃለሁ" ስትለዉ የነበረዉ ቢኒያም ከአጠገቧ የለም፡፡ የሞባይሏን ሰአት ስታይ ቢኒ ለስራ የሚወጣበት ሰዓት ደርሷል፡፡ በፍጥነት ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሂዳ እጇ ላይ ዉሀ በማድረግ ፊቷት ውሃ ረጨት ረጨት አደረገች፡፡ በሷ ሃሳብ መታጠቧ ነበር፡፡ እየሮጠች ወጣችና በሯ ላይ ቁጭ ብላ እየተቁለጨለጨች የነ ቢኒን ቤት በር በር ታይ ጀመር፡፡ . ....ቢኒ፡ ኤዲ መረበሿን ሲያይ አብሯት እንኳ ባይዉል ቁርስ አብሯት ለመብላት ወስኖ ነበር ማርፈዱ፡፡ ኤዲ ግን... አዳሯን ሙሉ እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ስላደረች ንጋቱ ላይ ለብዙ ቀን እንቅልፍ ያልተኛች በሚመስል መልኩ ለሽሽሽ ብላለች፡፡ ቢኒም ቶሎ እንደማትነሳ ስለተረዳ ቁርሷን ከአጠገቧ አስቀምጦ በብጣሽ ወረቀት "የኔ ቆንጆ አፈቅርሻለሁ!፡፡ ፈጣሪ ይጠብቅሽ" የሚል ፅሁፍ አኑሮ ከመዉጣቱ... በሩ ፊት ለፊት ረዲኤትን አያት፡፡ ከግቢ የመዉጫዉን በር ተወና ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡ እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡ ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ.... "ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡ እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡ አስተማሪ የፍቅር ታሪክ📒               😘✍ታርኩ ቶሎ እንዲቀጥል ካነበባቹ በኋላ #Like_SHARE ሳታደርጉ አትለፉ::    ክፍል 10 ይቀጥላል💛 ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...
          

✿ምኞቴ✿🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል 14 ❁▬▬▬ ብታኮርፍም ልትንሽ ሰዓታቶች እንደሆነ ስላወቀ ስልኩን ለኤዲ አቀበላት፡፡ አንብቢዉና የባልሽን ጉድ ተመልከቺ ይመስላል አሰጣጡ፡፡ ኤዲም ስልኩን ተቀበለችውና የላኪዉን አድራሻ ስታይ እማማ በለጡ ይላል፡፡ "የኔ ፍቅር እማማ ደግሞ ምን ብለዉ ልከዉልህ ነዉ?" ብላ ጠየቀችዉ፡፡ "ኤዲዬ ስልኩ እጂሽ ላይ አይደል? አንብቢዉ" አላት ..."ቢኒ ለእማዬ ነግሬያታለሁኝ ኤዲ ፍቃደኛ ትሁን እንጂ ..."ኤዲ ፊቷ እየተቀየረ ነበር፡፡ ቀጥ ብላ ቢኒያምን ተመለከተችዉ ትኩር ብላ አየችዉ፡፡ ቢኒያም የኤዲን የቁጣ አይኖች መቋቋም አልቻለምና ጎንበስ አለ፡፡ኤዲ እንደገና ወደ መልዕክቱ ትኩረቷን አደረገች፡፡ ማንበብ ቀጠለች... "...አንተ እንድታገባኝ ፍቃደኛ እንደምትሆን ነግራኛለች፡፡ ግን ደግሞ እሷ ራሷ እማዬ ለኤዲ እነግራታለሁኝ ብላለች፡፡ ቢኒ ፕሊስ እማዬ ለኤዲ ከመንገሯ በፊት አንተ ቀድመህ ንገራት፡፡" ይላል መልዕክቱ፡፡ ፊቲ ሁለት ልብ ሁናለች፡፡ ደስተኛም ግን ደግሞ የብቸኝነት ስሜት የተሰማት ባዶ እንደሆነች አድርጋ እራሷን አሰበች፡፡ ከዉስጧ ደስታ ይበልጥ ንዴቷ ፊቷ ላይ ገንፈሎ ወጣና "ቢኒ እኔን ሳትነግረኝ ከረዲ ጋር ጀምረህ ነበራ?" ብላ ጠየቀችዉ፡፡ "የኔ ፍቅር እኔ ላንተ ድብቅ ነኝ ማለት ነዉ?" ኤዲ ምን እንደምትናገር ሁሉ አቅቷታል፡፡ እምባ እየተናነቃት የምታወራዉ ሁሉ ይቆራረጣል፡፡ቢኒ የዚህን ያህል ትቆጣለች፤ እንደዚህ ትሆናለች ብሎ አላሰበም ነበር... ..."እንደሱኮ አይደለም ኤዲዬ..."እያለ ወደሷ ጠጋ አለ ..."አትጠጋኝ! ደግሞ ምንም ነገር አትንገረኝ!" አለችዉ፡፡ በሂወቱ ኤዲ እንዲህ ስታመር አይቷት አያዉቅም፡፡ ዛሬ በጣም ተለይታበታለች፡፡ ለማባባል እንኳ በሚያስቸግር ሁኔታ፡፡ ኤዲን እንዲህ እንድትሆን ያደረጋት ሁለተኛ ማግባቱ አይደለም፡፡ ይሄንን ደግሞ እራሷ ፈቅዳለታለች፡፡ እሷዉ ሴት መርጣ ልትድረዉም ተዘጋጅታ ጨርሳ ነበር፡፡ ነገር ግን... ገና ሳያገባ እንዲህ ሚደብቃት፤ ለሱ እየለፋችለት፤ ሁሉንም ነገር ለሱ እየሆነችለት እሱ ግን ልቧን መስበሩ በጣም አዘነችበት፡፡ ...ቢኒ ምን እንደሚያወራ አፉ ተያያዘበት፡፡ ተንተባተበ፡፡ ጥፋተኛ እንደሆነ አዉቆታል፡፡ ኤዲ ጎንበስ ብላ ነበር ቀና ብላ ቢኒያምን ስትመለከተዉ እሱም የመለማመጥ አይነት አንገቱን ሰብሮ አይኖቹን አቁለጨለጨ፡፡ ..."ቢኒ ... እኔ እንደፈቀድኩና መጋባት እንደምትችሉ ፃፍላት" አለችዉ፡፡ ..."ኤዲዬ መጀመሪያ ስለነበረዉ ነገር ላንቺ ልንገርሽ" ..."የኔ ፍቅር በፈጣሪ!? አሁን ምንም ነገር ለመስማት ዝግጁ አይደለሁም!" ..."እይዉልሽ ማሬ...." ብሎ ወሬ ሲጀምር ኤዲ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደ ዉጭ ወጣች፡፡ ከመዉጣቷ እማማ በለጡን ዉጭ ላይ አገኘቻቸዉ፡፡ ሰላምታ ቀድማ አልሰጠቻቸዉም፡፡ እማማ በለጡም ኤዲን ሲያይዋት "ደህና ነሽ ኤዲ" አሏት፡፡ ኤዲም ለሰላምታቸዉ መልስ ሰጠችና ከማንም ጋር ምንም ማዉራት ስላልፈለገች ተመልሳ ወደ ቤት ልትገባ ስትል        ✍"ኤዲ ስፈልግሽ ነበር...ስራ አለሽ እንዴ?" አሏት፡፡ ..."አይ ስራ የለኝም፡፡ ለምን ፈለጉኝ እማማ" አለቻቸዉ ፊቷን ሳታዞር በቆመችበት፡፡ ..."የሆነ የምነግርሽ ነበረኝ" አሉ እማማ በለጡ፡፡ ይቀጥላል....💛 ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...
          

✽̶🌺✿ምኞቴ✿🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል 13 ❁▬▬ ረድኤት እናቷን ፈራቻቸዉ፡፡ ንግግራቸዉ ወደ ቁጣ እየተቀየረ ይመስላል፡፡ ..."አይ አታዉቅም" አለች ..."የኔ ልጅ!" አሉ እማማ "ባለፈዉ ያባትሽ ሚስት በእኔ ምክንያት እንደሞተች ነግሬሻለኃ?" ..."አዎ እማዬ ነግረሽኛል" ..."ስለዚህ የኔ ልጅ ኤዲም ባንቺ ምክንያት መጎዳት የለባትም፡፡ አንቺና ቢኒያም እንደሆናችሁ ሳጨርሱ አቀሩም፡፡ እኔ ለቢኒያም የምድርሽ የእናንተን መስማማት አይቼ ሳይሆን የኤዲን ፍቃደኝነት ጠይቄ ነዉ!"አሉት፡፡ ረድኤት ደስም አላት ግራ ተጋባችም፡፡ ቢኒያምን ልታገባዉ ነዉ ግን ደግሞ ኤዲ ባትፈቅድስ ..."እና ለኤዲ  ልትነግሪያት ነዉ እማዬ?" ..."አዎ ቀስ ብዬ እነግራታለሁ፡፡ አንቺ አታስቢ የኔ ልጅ" ብለዋት ከተቀመጡበት ተነስተዉ ወደ ዉስጥ ገቡ፡፡ አባባ ሀብታሙ ከዘራቸዉን ይዘዉ ዉጭ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ እንደ አጋጣሚ ኤዲ ከቤት ስትወጣ ፊት ለፊት አየቻቸዉና "አባባ ሀብታሙ ሰላም ኖት" አለቻቸዉ፡፡ እርሳቸዉም "ደህና ነኝ ፈጣሪ ይመስገን ሰላም ነሽ ወይ ኤዲ" ብለዉ መለሱላት፡፡ ከዚያም አጠገባቸዉ ቀረበችና ስለ ረዲ አንዳንድ ነገር ለማወቅ "አባባ ረዲን አትድሯትም እንዴ እድሜዋኮ እየሄደ ነዉ፡፡"አለቻቸዉ፡፡አባባ ሀብታሙም የሷን ጥያቄ ወደ ጎን አሉና "አንቺና ቢኒያም ከተጋባችሁ ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡ኤዲ ይሄን ጥያቄ ከመለሰች ቡኋላ ቀጣዩ ጥያቄ ምን እንደሚሆን አዉቃለች፡፡ ለጥያቄያቸዉ መልስ መስጠት ስላለባት ብቻ "አራተኛ አመታችንን ይዘናል" አለቻችዉ፡፡"ታዲያ ልጃችሁን ቤተሰቦችሽ ዘንድ አርጋችሁት ነዉ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡ ..."አይይ አባባ..." አለቻቸዉ በረጅሙ የብሶት ትንፋሽ እየተነፈሰች፡፡ ተራርቀዉ መቀመጣቸዉ እንጂ ትንፋሿ እንደ በርሃ ወበቅ ይጋረፋል፡፡ ..."ምን ነዉ? የኔ ልጅ?" አሏት ጭንቀቷን ሲያዩ ..."አይ ምንም" አለችና አቀረቀረች ኤዲ፡፡ አባባ የሆነ ነገር እንዳለ ጠረጠሩ፡፡እሳቸዉም የልጅ ፍቅር ስላላቸዉ ጭንቀቷ ይገባቸዋል፡፡ "ልጅ አልወለድኩም አባባ..." አለቻቸዉ፡ አባባ ሁኔታዋን ሲያይዋት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይባታል፡፡ እሷ ግን እንደምንም እየታገለች ፈገግ ለማለት ትሞክራለች፡፡ ምክንያቱም ልጃቸዉን ለባሏ ልትጠይቃቸዉ ነዉና፡፡ ከረጅም ዝምታና ፀጥታ ቡኃላ አባባ ተንፈስ አሉና "ባልሽ ቢኒያም ግን በጣም ጎበዝ ነዉ አደነቅኩት" አሏት፡፡ እሷም ለምን? እንዴት? በምን ምክንያት አደነቁት? ብላ አልጠየቀቻቸዉም፡፡ ቢኒ የሚደነቅ ጥሩ ሰዉ እንደሆነ ታዉቃለችና፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ እየሆነች ነዉ፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያም ረድኤትን ለትዳር ቢጠይቅ እምቢ እንደማይሉና በደስታ እንደሚድሩት ከአባባ ሀብታሙ ሁኔታ መረዳት ችላለች፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያምን ይወዱታል፡፡ ደስ አላት፡፡ ባሏን እሷዉ ልድረዉ ነዉ፡፡...ቢኒ ከስራ እንደመጣ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም፡፡ "ቢኒ ለረድኤት ቤተሰቦች ሽማግሌ መላክ አለብህ" አለችዉ፡፡ ..."እንዴ ፈጠንሽሳ?" አላት ቢኒ ..."አዎ ፍቅሬ ሌላ የኔን ቢጤ ደሃ ካገባህኮ እኔን መፍታትህ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ አንተ እንድትፈታኝ አልፈልግም፡፡ ሁሌም በፍቅርህ መኖር እፈልጋለሁ" አለችዉ እየተቅለሰለሰች፡፡ ይሄን ከማለቷ ብዙም ሳይቆዩ የቢኒያም ስልክ መልዕክት (ሜሴጅ) ገባ "ጢጢጥ ጢጢጥ" ሜሴጁ ሲገባ የቢኒ ስልክ ያሰማዉ ድምፅ ነበር፡፡ ቢኒ ስልኩን አነሳና የላኪዉን ስም ሲያይ በማማ በለጡ ስልክ ነዉ የተላከዉ "ረድኤት መሆን አለባት" አለ በዉስጡ፡፡ ኤዲ እያየችዉ ነበር፡፡ ደንገጥ ብሎ ስታየዉ ፊቷ ክስም ይላል፡፡ እንደገና ፈገግ ሲል እሷም አብራ ትፈካለች፡፡ ኤዲ ሁሌም ቢሆን በቢኒያም ደስታ ደስ ይላታል፡፡ "የኔ ፍቅር ምንድን ነዉ መልዕክቱ?" አለችዉ....ኤዲ ቢኒ ፈገግ ስላለበት ጉዳይ ለማወቅ ጓጓች፡፡ ቢኒ አሁንም እንደፈገገ ነዉ፡፡ " ንገረኛ ዉዴ?" አለችዉ፡፡ በአይኖቿ እየተማጸነች፡፡ ቢኒያም ሊነግራት ነበር ነገር ግን ከረድኤት ጋር ከዚህ በፊት እንደተደዋወሉና በስልኩ መልዕክት እንደላከችለት ቀድሞ ለኤዲ አልነገራትም ነበር፡፡ ትቆጣ ይሆን እንዴ? ፈራ፡፡ ከሷ መደበቅ ስላልፈለገና ኤዲ ብትቆጣም ብታኮርፍም ልትንሽ ሰዓታቶች እንደሆነ ስላወቀ ስልኩን ለኤዲ አቀበላት፡ ይቀጥላል....💛 ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...
          

┉✽̶🌺✿ምኞቴ✿🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል 11 ❁▬▬▬ ..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት ረድኤትም ..... "ኤዲዬ አንቺምኮ አምሮብሻል ምን ተገኝቶ ነዉ?" ....."እኔማ የዉበቴም የድምቀቴም ምክንያት ባሌ ነዉ፡፡......" ብላ ስለ ቁርሱ፤ ስለ ወረቀቱ ምንም ሳታስቀር ለረዲ ነገረቻት፡፡ ኤዲና ረድኤት በደንብ ተግባብተዋል፡፡ ብዙ ሚስጥሮችን አብረዉ እየተጋሩ ነዉ፡፡ ረዲ ለኤዲ 'ባልሽን ልቀማሽ ነዉ ተዘጋጂ!" የሚለዉ ሲቀር፡፡ .....ኤዲም "አንቺስ የዚህ ዉበት ምንጭ ማን ይሆን ረዲ?" አለቻት፡፡ ባልሽ ቢኒያም ነዉ አትላት ነገር... እ እ እያለች ስትደናገጥ የረድኤት አባት ከቤት ዉስጥ ወጡና "እንዴት አደርሽ ኤደን" ብለዉ ጨዋታቸዉን አቋረጧቸዉ፡፡ ...... "ደህና አደሩ አባባ" ብላ መለሰችላቸዉ፡፡ አባባ  ትንሽ ቀለድለድ ካደረጉ ቡኃላ ... "ኤዲ" አሏት፡፡ ..."አቤት አባባ" አለቻችዉ፡፡ ..."ኧረ እቺን ጓደኛሽን ምከሪያት እስኪ" ..."ማንን? ረድኤትን?" ስትላቸዉ ..."መቼም በለጡን ምከሪያት አልልሽ የኔ ልጅ" ሲሉ ሁሉም ተሳሳቁ፡፡ አባባ ቀልዳቸዉና ምራቸዉ አያስታዉቅም፡፡ ቁም ነገር እያወሩ በመሃል ይቀልዳሉ፡፡ በቀልዱም መሃል ያመራሉ፡፡ ሁሌም ፀባያቸዉ እንዲህ ነዉ፡፡ ቀጠል አደረጉና.... ..."ባል እየተንጋጋ ይመጣል እሷ ግን አሻፈረኝ አለች፡፡ ሁሌም ልማር ነዉ የምትለዉ፡፡ አግብቶስ ትምህርት የከለከላል እንዴ የኔ ልጅ?" ብለዉ ጠየቋት ኤዲን፡፡ ረድኤት አንዴ ኤዲን፤ አንዴ አባቷን እያየች የሚሉትን ትሰማለች፡፡ ..."አይ አይከለከልም፡፡ እንደዉም ሴት ልጅ በጊዜ ስታገባ ነዉ ጥሩዉ" አለቻቸዉ ..."ተባረኪ የኔ ልጅ" አሏት ደስ ብሏቸዉ "...እንደዉም እንደ ቢኒያም አይነት ባል ፈልጊማ ኤዲ፡፡ ሳልጠይቃት ነዉ የምድራት" ሲሉ ሁሉም ተሳሳቁ፡፡ ረዲ "እሱ እራሱ ቢኒ በመጣ"አለች በዉስጧ፡፡ ..... ጨዋታዉ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ እማማ በለጡም አራተኛ ተጨምረዉ ወሬዉን አድምቀዉታል፡፡ . ቢኒ በንግግሩ ኤዲን እንዳስደሰታት አዉቋል፡፡ ይበልጥ ወደ እሱ እንድትቀርብ ያደረገዉም ዘዴ ነዉ፡፡ ከኤዲ ጋር በተነጋገሩት መሰረት ሁለተኛ ማግባት እንዳለበት ወስነዋል፡፡ ሌላ ሴት ፍለጋ መኳተን አልፈለገም፡፡ እዚሁ እፊቱ በሱ ፍቅር የተራበችዉን ረድኤትን ሊያገባት ነዉ፡፡"ግን... በምን መልኩ? አባቷስ እሺ ብለዉ ይድሩልኝ ይሆን?" እያ ያስብ ጀመር፡፡... . ......"ረዲዬ..." አሏት እማማ በለጡ ልጃቸዉን ..."ወይዬ እማዬ...." ቤት አብረዉ ቁጭ ብለዉ ነበር፡፡ አባባ ስለሌሉ ረድኤትን የሚያዋርባት ምቹ ጊዜ አግኝተዋል እማማ በለጡ፡፡ ... "አባትሽ ሁለት ሚስት እንደነበረዉ ታዉቂያለሽ?" ረድኤትም "ኧረ እማዬ አላዉቅም፡፡" አለች መልሱን ለማሳጠር ያክል፡፡ ምክንያቱም ወደ እሷ ቀስ እያሉ እንደሚመጡ አላጣችዉም፡፡ .... "ይሄዉልሽ የኔ ልጅ! አባትሽ መጀመሪያ ሌላ ሚስት ነበረችዉ..." "ካንቺ በፊት?" ብላ ሊቀጥሉት የነበረዉን ወሬ አቋረጠቻቸዉ፡፡ በዚያም ላይ ደንግጣለች፡፡ረድኤት እስካሁን ድረስ እናቷ የአባቷ ሁለተኛ ሚስት እንደነበረች አታዉቅምና፡፡ ...."አዎ ከኔ በፊት ሌላ ሚስት ነበረችዉ" ...."እና ምን ሆነች ማሚ? ፈቷት ነዉ ወይስ...?" ...."አይ አልፈታትም ነበር፡፡ ሙታ ነዉ ፈጣሪ ነብሷን ይማራትና" አሉ ...."እንዴት?... ለምን?... ማለቴ ...በምን ምክንያት ሞተች ክፍል 12 ይቀጥላል አስተማሪ የፍቅር ታሪክ📕               😘✍ታርኩ ቶሎ እንዲቀጥል ካነበባቹ በኋላ #Like_SHARE ሳታደርጉ አትለፉ::    ይቀጥላል💛....... ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...
          

┉✽̶🌺✿ምኞቴ🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል 12 ❁▬▬▬ ✍...."እንዴት?... ለምን?... ማለቴ ...በምን ምክንያት ሞተች?" እየተንተባተበች ነበር የጠየቀቻቸዉ፡፡ ...."ይሄዉልሽ ልጄ አባትሽና ሚስቱ በጣም ነበር የሚዋደዱት፡፡ ፍቅራቸዉ እጅግ ያስቀና ነበር፡፡ ግን ምን ይደረግ ልጅ መዉለድ አልቻለችም፡፡ ከዚያ አባትሽ ሀብታም ስለነበር ሁለተኛ እኔን አገባኝና አንቺን ወለድኩለት፡፡ ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር የነበረዉ ፍቅር ቀነሰ፡፡ ዉሎዉ፤ አዳሩ ከእኔና ካንቺ ልጁ ጋር ሆነ፡፡ የመጀመሪያ ሚስቱን ፈታት እንዴ? እስከሚባል ድረስ ረሳት፡፡ እሷም በፍቅር ተጎዳች፡፡ እኔ በመዉለዴ ቅናት አብሰከሰካት፤ ብቸኝነት አጠቃት ይሄን ሰበብ አድርጎ ነዉ መሰለኝ በጣም ታመመች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ሞተች፡፡አባትሽም ከሞተች ቡኃላ ነበር የመሞቷ ስበብ እሱ መሆኑን ያወቀዉ፡፡" በሀዘን ተዉጠዉ ነበር የሚነግሯት በፈጣሪ" አለች ረድኤት "እንዴት እስከዛሬ ሳላዉቅ ግን ማሚ?ይሄን ያክል ድብቅ ነሽ ማለት ነው...ጊዜዉ እየነጎደ ነዉ፡፡ ረድኤትም የዩንቨርሲቲ መግቢያዋ ቀርቧል፡፡ ቀናቶች ናቸዉ የቀሩት፡፡የቢኒ ጉዳይ አልተቋጨም፡፡ አሁንም ቢሆን እሱን ከማሰብ ስለሱ ከማለም አልቦዘነችም፡፡ ከጭንቅላቷ ጋር አብሮ የተሰራ ይመስል ሁሌም ስሙን ትደጋግማለች፡፡ ልቧ ላይ ግን ላይለቅ፤ ላይገፈፍ ታትሟል፡፡... ኤዲና ቢኒ እያወሩ ነዉ፡፡ በባለፈዉ ምሽት ሁለተኛ ማግባት እንዳለበት ተስማምተዋል፡፡ኤዲ የሆነ ነገር አስባለች ግን ደግሞ ለቢኒያም መንገር ፈራች፡፡ከስንት ፍርሃትና ትግል ቡኃላ ..."ቢኒ" አለችዉ ..."ወይዬ ፍቅሬ🌺" አላት፡፡ አቤት አጠራር ፤ አቤት ፍቅር ..."ለምን እኔ እራሴ አልድርህም" ..."እንደዉም ከአንቺ ጋር የምትስማማዋን አምጭልኝ" አላት፡፡ እየቀለደ ነበር፡፡ ..."ቢኒ አትቀልዳ...ከምሬኮ ነዉ፡፡ እኔዉ ልዳርህ ፍቅሬ" አለችዉ፡፡ ቢኒያም ግራ ገባዉ፡፡ በዉስጡ "ይቺ ልጅ ከምሯ ነዉ እንዴ?" እያለ ..."ማንን ነዉ የምትድሪልኝ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ ኤዲም ፈራ ተባ እያለች..." በጣም ቆንጅዬ ልጅ ናት በዚያ ላይ ስርዓቷ ጥግ ድረስ ነዉ፡፡ እንደዉም ላንተ የምትሆንህ እሷ ናት፡፡"ቢኒ ተደናገጠ፡፡ ነገሩ እሱ ብቻ ሳይሆን ንግግራቸዉን የሚሰማ ሰዉ ቢኖር ይደነግጣል፡፡እንዴት ተቀናቀኟን እሱዋለዉ ትመርጣለች፡፡ በዚያ ላይ ቆንጆ ብላ እያሞገሰች፤ ስለ ፀባይዋ እየመሰከረች፡፡ ..."ማን ናት እሷ😘 ኤዲዬ" ..."ረድኤት!" አለችዉ፡፡ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ ምላሱ ተሳሰረበት የሚናገረዉ ጠፋዉ፡፡ ..."እዉነትሽን ነዉ?" አላት፡፡ በመጠራጠር አይነት ስሜት..."አዎ! ደሞኮ በጣም ምርጥ ልጅ ናት ፍቅሬ" አለችዉ፡፡ በዉስጡ 'አንቺ ሳታዉቂ መጀመራችንን አታዉቂ?" አሞግሻት' እያለ ..."እሷስ እሺ የምትል ይመስልሻል?" አላት ወሬያቸዉ ቀጥሏ ረድኤት ተክዛ በሃሳብ ተዉጣ ቁጭ ብላለች፡፡ ዛሬም መንታ መንገድ ላይ ነች፡፡ ቢኒን ልተወዉ ወይስ እንደምንም ብዬ ላግባዉ፡፡ እማማ በለጡ የረድኤትን በሀሳብ መዋጥ ተመለከቱና ጠጋ ብለዉ "ልጄ ምን ሁነሽብኝ ነዉ? ሰሞኑን ሁኔታሽ ልክ አይደለም" አሏት ረዲም "ምንም አልሆንኩምመ እማዬ" ብላ መለሰችላቸዉ፡፡"የሆነ ነገርማ ደብቀሽኛል፡፡ በፊትኮ እንዲህ አልነበርሽም የኔ ልጅ" እንደ መንቃት እያለች ተንጠራራችና ወገቧን ነቅነቅ አድርጋ"ያዉ እማዬ አሁንስ እንደ በፊቱ ሆንኩልሽ?" አለቻቸዉ፡፡ እማማ በለጡ ጣታቸዉን አገጫቸዉ ላይ ጣል አድርገዉ ..."የኔ ልጅ በህልምሽ ቢኒያም፣ ቢኒ የምትይዉ ማንን ነዉ?"..."ምን?... ማ እኔ?... ኧረ እኔ አላልኩም እማዬ" አለች፡፡ ተደናግጣ ነበር፡፡ እማማ በለጡም ቀስ እያሉ ሊያዉጣጧት ፈልገዉ ..."አንድ ቀን'ኮ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ነዉ የምትይዉ" አሏት ..."እኔንጃ እማዬ ግን..." ..."ግን ምን የኔ ልጅ?" ይበልጥ ለማወቅ ጓጉተዋል ..."ቢኒያም የሚባል ልጅ ሳልወድ አልቀርም!" ..."ምን?" አሉ እማማ በለጡ ያላወቁ በመምሰል "የኤዲን ባል ቢኒያምን ነዋ?" ..."አይ..." ብላ ንግግሯን ሳጨርስ ረዲ ..."አዎ እሱኑ ነዉ፡፡ አትዋሺኝ የኔ ልጅ፡፡ ባለፈዉም እንዳማረብሽ ሲነግርሽ ሰምቻለሁ፡፡ ለመሆኑ ኤዲ ታዉቃለች?"ብለወ ጠየቋት፡፡ ረድኤት እናቷን ፈራቻቸዉ ክፍል 13 ይቀጥላል💛.... ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...
          

✽̶🌺✿ምኞቴ✿¶🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ክፍል 10❁▬▬▬ .... ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡ እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡ ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ.... "ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡ እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡✍... እማማ ሚረዱ፤ ኮሽታ ሰምተዉ የሚነቁ በአሁኑ አባባል አራዳ የሚባሉ ሴት ናቸዉ፡፡ እስከዛሬም ልጃቸዉን አላጤኗትም እንጂ ቅዠት ከመስማታቸዉ ቀድመዉ ያዉቁባት ነበር፡፡ ይሄዉ አሁን ደግሞ ስሙ ቢላቸዉ በራቸዉ ስር መጥቶ ቢኒያም ልጃቸዉን ረድኤትን እያዋራት ነዉ፡፡ ..... "ቢኒ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላዉቅም፡፡ ግን... ትቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም አንተን ላገኝህ አልችልም፡፡ ኤዲንም ላሳዝናት አልፈልግም፡፡" አለችዉ ረዲ ቢኒም....."ረዲ እሱን ላወራሽ አልነበረም፡፡ በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር አመጣጤ! በይ ደህና ዋይ" ብሏት መልሷን ሳይሰማ ጥሏት ሄደ፡፡ ረድኤት በህይወቷ እንደዚች ሰዓት የተደሰተችበት ቀን የለም፡፡ ደስታ ቢገል ኑሮ ቢኒ "በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር አመጣጤ" ካላት በኃላ ትንፋሿ ፀጥ ብሎ ትሞት ነበር፡፡ ከበር እስከሚወጣ በአይኗ ከሸኘችዉ ቡኃላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መስተዋት ፍለጋ እየሮጠች ስገባ እናቷ የመስኮቱን መስተዋት ከፍተዉ እንደማፅዳት እያደረጉ ነበር፡፡ ደነገጠች፡፡"እማዬ ስናወራ ሰምታን ይሆን እንዴ?" ብላ አሰበች፡፡ የእናቷ ነገር ደስታዋን እንዳያከስምባት ቶሎ ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ መስተዋቱ ፊት ተገተረች፡፡ 'እዉነትም ቆንጆ ነኝ!" ስትል ለራሷ አሰበች፡፡ረዲን በጣም ብዙ ወንዶች ግማሹ ለትዳር፣ ግማሹ ለአዳር፣ ሌላዉ ደግሞ ለፍቅር ጓደኝነት ሲጠይቋት አላማና ኢላማ ያላት ስነ-ስርዓት ያላት ልጅ ስለነበረች ሁሉንም ገፍታ አባራቸዋለች፡፡ ለቁጥር የሚያዳግቱ ብዙ ወንዶች ለዉበቷ ቋምጠዉላታል፤ በጣም ዉብ ነች፡፡ብዙ ሰዎች የቁንጅናዋን ልክ ለመናገር ቃላት ደርድረዋል፡፡ እሷ ... ግን ለጊዜያዊ ስሜት የምትረታ የዋዛ አልነበረችምና አሻፈረኝ ብላለች፡፡ የቢኒ አንዷ ቃል ግን ዉስጧ ገብቷል፡፡ ልትተወዉ የነበረችዉን ሴት እንደገና የልቧን ፍም ጭሮባታል፡፡ "ቢኒንማ አልተወዉም!!" የረዲኤት ዉሳኔ ነበር፡፡ ... ኤዲ ከእንቅልፏ እንደነቃች በባሏ እጅ የተከሸነዉን ጣፋጭ ቁርስ ማጣጣም ይዛለች፡፡ ቁርሷን በልታ ሳጨርስ ተኝታበት ወደነበረዉ አልጋ ዘወር ስትል ከትራሷ ስር ብጣሽ ወረቀት አየች፡፡ አነሳችዉና ስትገልጠዉ "የኔ ፍቅር አፈቅርሻለሁ፡፡ ፈጣሪ ይጠብቅሽ!" የሚል ፅሁፍ አነበበች፡፡ ደስታ ልቧን ፈነቀለዉ፡፡ ቢኒ እዉነትም ፍቅር ነዉ፡፡ ቁርስ ሰርቶ አካሏን ከመጠገኑም በላይ 'አፈቅርሻለሁ' ብሎ የመንፈስ ምግብ ሰጣት፡፡ ባዲስ ንጋት ከቁርስ ጋር ፍቅር መገባት፡፡ኤዲ አዳሯን እንቅልፍ ማጣቷን ሁሉ እረሳችዉ፡፡ በደስታ ተፍነከነከች፤ በሀሴት ጮቤ እረገጠች፡፡ በዚህ ልዩ ጧት፤ በዚህ ልዩ ቀን የጧቷን ፀሐይ ልትሻማ ከቤቷ ወጥታ ለፀሐይ ጀርባዋን ሰጥታ ቁጭ አለች፡፡ ...... ረድኤት ቆንጆ መባሏ ሳያንስ ሌላ ዉበት፤ ሌላ ድምቀት ተላብሳ፤ ንጋቷን በፍቅር አድሳ እሷም እንደ ኤዲ የፀሐይን ሙቀት ልትኮመኩም ወጣች፡፡ ከመዉጣቷ ኤዲን ስላየቻት ወደሷ ሄደች፡፡ ረድኤት ላይ ዉበት ጎልቷል፤ ኤዲ ላይ ደግሞ ደስታ ነግሷል፡፡ ሁለቱም ለጨለማ ድምቀት እንደሆነችዉ ጨረቃ ደምቀዋል፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ ቡኃላ ኤዲ፡ ረዲን... ..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት ይቀጥላል...💛 ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...
          

​​​​┄┉✽̶🌺✿ምኞቴ ✿🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬❁ ክፍል 15 ❁▬▬        የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እሁድ እሄዳለሁ" ስትላቸዉ እማማ በለጡ ደንገጥ አሉና..."እንግዲያዉስ ከመሄድሽ በፊት በዚህ ሳምንት ዉስጥ ቀለበት ማሰር አለብሽ!" አሉ፡፡አባትና ልጅ ሁለቱም ድንግጥ ብለዉ "እ..." አሉ፡፡ የረድኤት አደነጋገጥ እንዴት ብለዉ ካወጡ ቡኃላ ይሄዉልህ ሀብታሙ ብለዉ ለማስረዳት ሊሞክሩ ሲሉ "ማንን ነዉ የምታገባዉ? እ!" ብለዉ መልሱን ለመስማት ጓጉ... እማማ በለጡም ቀስ አሉና... "ረድኤት እንግዲህ ደርሳለች፡፡ ህፃን ልጅ የምትባል ልጅ አይደለችም፡፡ ለማፍቀርም ለመፈቀርም፤ ለማግባትም ለመዉለድም ደርሳለች፡፡" ...የጋሽ ሀብታሙን አይን አይን እያዩ ነበር የሚያወሩት "አይደለም እንዴ ሀብታሙ?" ብለዉ የረድኤትን መድረስ ለማረጋገጥ ባለቤታቸዉን አባባ ሀብታሙን ጠየቁ፡፡ ..."አዎ ደርሳለች ግን...ለማን ነዉ የምትድሪያት? ማንን ነዉ የምታገባዉ?" ብለዉ ጠየቁ የምታገባዉን ሰዉ ይበልጥ ለማወቅ እየጓጉ፡፡ "...እኔ አይደለሁም የምድራት፡፡ ልጄ ረዲ የምታገባዉን ሰዉ ራሷ መርጣለች" አሉ እማማ በለጡ ረድኤትን እንደ ማቀፍ እያረጉ፡፡ ረድኤት አባቷን ለማየት ተሳናት፡፡ ..."አትፍሪ የኔ ልጅ ንገሪኝ ማንን ነዉ የመረጥሽዉ? እኔምኮ አባትሽ ነኝ ለናትሽ ብቻ ነዉ እንዴ የምትነግሪያት" አሉ አባባ ሀብታሙ፡፡ ረድኤት ደፈር ብላ እንድትነግራቸዉ እየገፋፏት፡፡ ረድኤትም አባቷን በፍርሃት ቀጥ ብላ እያየች "አባዬ... ቢኒያምን ነዉ!" አለቻቸዉ፡፡ ይሄ አባቷን ድፍረቷ ሳይሆን አሰተዳደጓ ነዉ፡፡ ምንም ነገር አጥብቀዉ ከጠየቋት አትዋሽም፡፡ እማማ በለጡም ስሙን ከረድኤት አፍ ነጠቅ አደረጉና "አዎዎ ቢኒያም ነዉ፡፡ የኤዲን ባል" ..."ምን?በስመአብ" ብለዉ ከተቀመጡበት ብድግ እንደገና ቁጭ አሉና....፡፡አይሆንም?አታደርጉትም። ...ኤዲና ቢኒ አንድ ላይ ተኝተዉ እየተንሾካሾኩ ያወራሉ፡፡ ኤዲም ንዴቷን እረስተዋለች፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ረድኤትን በጣም ወዳታለች፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ከሜሴጁ ላይ ረድኤት ለኤዲ እጅግ በጣም አሳቢ እንደሆነች ነዉ የተረዳችዉ፡፡ "ለኤዲ አንተ ቀድመህ ንገራት"..."ኤዲ ትፍቀድ እንጂ" ... ይሄ የረድኤት ንግግር ዉስጧ ገብቷል፡፡ እኔ የማልፈቅድ ከሆነኮ ረድኤት ቢኒያምን አታገባዉም ማለት ነዉ እያለች ታስባለች፡፡ እንደ እዉነቱም ረድኤት ለኤዲ ታዝንላታለች፤ ታከብራታለች፡፡ ፍቅር ሆኖባት እንጂ የኤዲን ባል ልትቀናቀናት አትፈልግም ነበር፡፡ ..."የኔ ፍቅር እማማ በለጡ ሁሉንም ነግረዉኛል" አለችዉ ቢኒያምን፡፡ ቢኒም እቅፉን ይበልጥ እያስተካከለ ..."ምን ነገሩሽ የኔ ቆንጆ!" ብሎ ጠየቃት፡፡ ..."ረድኤትም በጣም እንደምትወድህና ልታገባህ እንደምትፈልግ እና ሌላም ብዙ..." ብላ በቁጭት አይነት ወሬዋን አቋረጠችዉ፡፡ ትንፋሿ ይጋረፍ ነበር፡፡ ቢኒያም በዚሁ ርዕስ ወሬ ከቀጠሉ ወደ ማኩረፍ እንደምትሄድ ስለተረዳ ወሬ ለመቀየር ያክል... ..."ኤዲዬ ..." አላት ..."ወዬ ቢኒ" ..."ስትተኚ ይበልጥ የምታምሪዉ ለምንድን ነዉ? በጣም ዉብብ ሆነሻልኮ" አላት፡፡ ጉንጯን እንደመሳም እያረገ ነበር፡፡ ኤዲም ... ..."እሺ የኔ ፍቅር እንቅልፍ ሲወስደኝ ደግሞ ይበልጥ ስለሚያምርብኝ ልተኛ" አለችዉና እሷም ሳም አድርጋዉ ራሷን ከእቅፉ አዉጥታ ጀርባዋን ሰጥታዉ ተኛች፡፡ ...ኤዲና ቢኒ ሰሞኑን በረድኤት ጉዳይ የተነሳ አልተኙም  ቢኒ  በለሊቱ ተነስቶ ወደ ስራ ለመሄድ ወደ ስራ ይዟቸዉ የሚሄደዉን እቃዎች እያዘጋጀ ነጋ፡፡ አስተማሪ የፍቅር ታሪክ📕               😘ክፍል 16 ይቀጥላል💛.... ⁠⁠⁠⁠⁠
نمایش همه...