cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🇪🇹 Ministry of Science and Higher Education

@minster_of_education1 ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 Share and Support us @minster_of_education1 መረጃ እና መልዕክት መቀበያ 📧 @ministryofeducation2 @minstryofeducation2 ማስታወቂያ ለማሰራት @minster_of_education1

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
841
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በሮም፤ ጣሊያን የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ሴርጂዮ ማታሬላ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል። Photo ፦ PMOEthiopia @tikvahethiopia
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና ዉጤትን ከዛሬ ለሊት ጀምሮ መመልከት ይቻላል‼️ ለ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ • በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም • በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot መመልከት ትችላላችሁ ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡ ሚኒስቴሩ አክሎም ፤ ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቅሬታቸዉን ማቅረብ ይችላሉ ብሏል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ የተባለ ሲሆን ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ይጠንቀቁ ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን ዛሬ አስታውቋል። ከዛሬ ኅዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ይቀጥላል ብሏል። ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር @tikvahethiopia
نمایش همه...
#DrAlQaradawi የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን መስራችና ፌዴሬሽኑን ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት እውቁ የእስልምና ምሁር ግብፃዊ ዶክተር ሼክ ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል። ህልፈታቸውን ልጃቸው አብዱል ራህማን ዩሱፍ አል ቃራዳዊ አረጋግጠዋል። ዶ/ር አልቃራዳዊ ህይወታቸው ያለፈው ኳታር፤ ዶሃ ውስጥ ነው። እኤአ 2004 የተቋቋመውን (እሳቸው መስራች ነበሩ) ዓለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን ከተቋቋመበተ ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል። ዶ/ር አልቃራዳዊ ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የኳታር ዜግነት ተሰጥቷቸው ህይወታቸው እስክታለፍ ድረስ ኑሯቸውን በኳታር፣ዶሃ አድርገው ነበር። አልቃራዳዊ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ወቅት በግብፅ በ1926 ነበር የተወለዱት። ገና በለጋ እድሜያቸው እስላማዊ ትምህርትን መከታተል የጀመሩት አልቃራዳዊ በፀረ ቅኝ አገዛዛ ላይ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። በ1950 ዎቹ ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ከሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ጋር በተገናኘ ብዙ ጊዜ ለእስር ተዳርገው ነበር። ከ120 በላይ መፅሀፍትን ያሳተሙት ዶ/ር አል ቃራዳዊ ለእስልምና ባበረከቱት አስተዋፆ 8 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን መሸለም እንደቻሉ ተገልጿል። ዶ/ር አል ቃራዳዊ በክፈለ ዘመኑ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የእስልምና ሊቃውንት አንዱ እንደነበሩ ተዘግቧል። በህይወት በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ሚዲያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አመለካከታቸውን ሲያጋሩ የነበረ ሲሆን በሚያነሷቸው ሀሳቦች የሚደግፏቸው እንዳሉ ሁሉ ሀሳባቸውን የሚቃወሙም ነበሩ። የዶ/ር አልቃራዳዊን ህልፈት ተከትሎ ፤ የተርክዬ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን  ለልጃቸው አብዱል ራህማን በመደወል የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው አፅናንተዋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ሐይቅ ! የሐይቅ ከተማ አስተዳደርና የተሁለደሬ ወረዳ የጸጥታ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም ፦ -  የባለ 3 እግር ተሽከርካሪና አነስተኛና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። - የመጠጥ ግሮሰሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል። - ህግ ከሚያስከብሩ የጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። - በየጫት ቤቱና መቃሚያ ቤቶች በማንኛውም ሰዓት መሰባሰብ፤ በነዚህ አካባቢዎች መቃምና መገኘት ተከልክሏል። - ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ በዘመቻ ሰበብ ከመንግስት እውቅና ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጥ አልባሳት፣ ትጥቅ፣ የጦር መሳሪያና የመሳሰሉትን በማንኛውም ሰዓት በከተማው ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል። - ተፈናቅይም ሆነ ሌሎች ወደከተማው የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት በሚያገኙበት ተቋም ራሳቸውን የመግለፅ እንዲሁም ተቋማቱም መጠየቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። - በከተማው አሉባልታ መንዛት፣ ህዝቡን በማሸበር አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ፣ የግል ንብረት እና እቃ እንዲሰብሰብ ማነሳሳት በጥብቅ ተከልክሏል። ነዋሪዎች ማንኛውም ጥቆማ ካላቸው በ 033 222 0481 ፣ 033 222 0955 ፣ 0333 222 0006 በመደወል መጠቆም ይችላሉ ተብሏል። (ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia #DireDawa ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ ፣ ለአየር ሰዓት እና ልዩ ልዩ የደንበኞች አገልግሎት ከ3ቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከላት (ከዚራ፣ መስቀለኛ፣ ኮኔል ከሚገኙት) በተጨማሪ ብራንድድ በሆኑ በሁሉም የከተማው ሱቆች #ሲም_ካርድ እና #አየር_ሰዓት ማግኘት እንደሚቻል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል። #SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#KOBO የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ። የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል። በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል። የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል። ምንም እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሰላም እንዲሰፍን እና መሳሪያ ወርዶ ንግግር እንዲጀመር ጥሪዎች ቢቀርቡም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopiaAirlines ኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET343 አውሮፕላን ነሀሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አየር ትራፊክ ቁጥጥር ጋር ያለው ግንኙነት ለጊዜው ተቋርጦ እንደነበር የሚጠቁም ሪፖርት እንደደረሰው አመልክቷል። ሆኖም ግንኙነቱ ከተመለሰ በኋላ አውሮኘላኑ በሰላም እንዳረፈ ገልጿል። ተጨማሪ #ምርመራ እስከሚያጠናቅቅ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሠራተኞች ከሥራ ታግደው ይቆያሉም ብሏል። በምርመራው ውጤት መሰረት ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነትን ማስጠበቅ  የሁልጊዜም የመጀመሪያው ተግባሩ ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጧል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ ችግር ውስጥ ናቸው " - የሶማሌ ክልል የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ አካባቢዎች ላይ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል። ክልሉ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። ከመኖሪያ ቀዬአቸው የተፈናቀሉት ዜጎች በአሁኑ ወቅት በሲቲ ዞን ኤረር ወረዳ አስቡሊ እና በድዌይ በሚባል አካባቢ የተሰባሰቡ ቢሆንም በክረምቱ ከባድ ዝናብ ምክንያት መንገዶች በመቆራረጣቸውና ወደ አካባቢው ተሽከርካሪ ሊገባ ባለመቻሉ ምንም አይነት የእለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረብ አልተቻለም ብሏል። በአሁኑ ወቅት ተፈናቃዮቹ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ ያለው የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት አፋጣኝ እርዳታ ለማቅረብ ጥረትና ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል። ለዚህም የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ እና ም/ርዕሰ መስተደድር ኢብራሂም ኡስማን የተካተቱበት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልኡካን ቡድን ተፈናቃዮች በሚገኙበት በሲቲ ዞን በመገኘት ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ በማስተባበር ላይ ይገኛሉ ሲል ክልሉ አሳውቋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የተሰራጨው ሀሰተኛ ወሬ ነው " - የሶማሌ ክልል መንግስት የሶማሌ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ላይ "የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው" በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል። የክልሉ መንግስት " በትላንትናው እለት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ ተብሎ የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን " ብሏል። በትላንትናው ዕለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደርን የሚመለከቱ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር። አንደኛው ይኸው "የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው" የሚለው ሲሆን የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው የተባለው ለስራ ጉዳይ "ቢኪ" የሚባል ቦታ በሄዱበት ወቅት ነው። ሌላኛው ደግሞ፤ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ወደዚሁ "ቢኪ" የተባለ ስፍራ በሄዱበት ወቅት ወጣቱን ጨምሮ፤ ህብረተሰቡ በመቆጣቱ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበር፤ ድንጋይም እስከመወርወር የደረሰ ክስተት እንደተፈጠረ የሚገልፅ መረጃ ተሰራጭቷል። የክልሉ መንግስት፤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ላይ "የግድያ ሙከራ አልተደረገባቸውም ውሸት ነው" የሚል መግለጫ ቢሰጥም በተመሳሳይ ሰዓት ስለተሰራጨው የ "ቢኪ" ከፍተኛ ተቃውሞ በተመለከተ እንዲሁም ርዕሰ መስተዳደሩ ወደ ተባለው ስፍራ አቅንተው እንደሆነ፤ ሄደውስ ምን እንደተፈጠረ የገለፀው ነገር የለም፤ ማስተባበያም አልሰጠም። ዘግየት ብሎ ከሲቲ ዞን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በደረሰን መልዕክት ትላንት ፕ/ት ሙስጠፌ ቢኪ ላይ ተቃውሞ ገጥሟቸው እንደነበር፤ በዚህም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት እንደነበር፤ በኃላም ሁኔታውን እንደተቆጣጠሩ፣ የግድያ ሙከራ የተባለው ግን ትክክል እንዳልሆነ ገልፀዋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...