cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የዕለቱ ምርጥ ነገር (MADKING ENTERTAINMENTz)

በየቀኑ የተደረጉ፣የተከናኑ፣የተሰሙ፣ አዝናኝ፣ አስቂኝ እንዲሁም አስገራሚ ምርጥ ምርጥ ዜናዎች እውነታዎች እና ክንውኖች MEMEz & FUNNY PICz😘 😆 STOONERz🔥 AWESOME HOT & LATEST MUSICS 🎶🔊 DAILY AMAZING QUOTES 🗣️ ETHIO PROVERBS AWESOME COUPLE PICz 😉 የሚቀርቡበት ያለማጋነን ምርጡ ቻናላችን ይህ ነው !

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
149مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✅ የኢትዮሳት ብቸኛ ጥቅሞች ✅ Ethiosat Exclusive Benefits ➧⓵/የሳተላይት ክፍያ የሳተላይት ቻናሎች ክፍያ በሚይዙት ባንድዊድዝ የሚወሰን ቢሆንም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙት ቻናሎች ክፍያ ከሌላ ሳተላይት ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ይቀንሳሉ። ይህ ደግሞ ሌላ ሳተላይት ላይ በSD ጥራት ያስተላልፉ ከነበረ በHD እንዲያደርጉት እድል ይፈጥርላቸዋል። በተጨማሪም ለሌሎች የፕሮዳክሽን ሥራዎች ትርፍ ይኖራቸዋል። ➧⓶/የቻናሎች ይዘት በሌሎች ሳተላይቶች የሚገኙ ቻናሎች የአገራቸውን ጥቅም ከማስጠበቃቸው የተነሳ በርካታ ቻናሎች ከፍላጎታችን ውጭ ይገባሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ተፈላጊ ኢትዮጵያዊ ቻናል የተለያየ ፍርኩየንሲ ያለው ከመሆኑ እንፃር ቻናሎችን ፈልጎ ቅደም ተከተል ለማስያዝ ብዙ ሰዓት ይወስዳል። ኢትዮሳት ላይ ያሉ ፍሪኩየንሲዎች ግን ለጊዜው ሶስት ብቻ ናቸው ሰርች በሚደረግበት ሰዓትም የሚገቡት ጠቃሚዎቹና የተመረጡ ኢትዮጵያዊ ቻናሎች ብቻ ናቸው። ➧⓷/ የቻናሎች ጥራት እኛ ኢትዮጵያዊያን ጥራት ይገባናል። ስለሆነም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቻናሎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው (HD) ናቸው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች SD ሪሲቨር ያላቸው መሆኑንም በመገንዘብ ለ6 ወራት የሚቆዩ የተወሰኑ ቻናሎች በSD ይሰራሉ ። ነገር ግን በዘላቂነት ቻናሎቹን በጥራት ለመመልከት HD ሪሲቨር ያስፈልጋል። ➧⓸/ በዛፍ እና በግንብ የመከለል ሁኔታ ይህ ሳተላይት 57°E እንደመሆኑ መጠን ከፊት ለፊት በሚኖር ዛፍ ወይም ግንብ የመከለል ሁኔታው ዝቅተኛ ነው። በተለይ ኮንዶሚኒዬሞች ላይ ሀገርኛ ቻናሎችን ለማግኘት ሲቸገር ለነበረ ሰው ችግሩን ያቃልልለታል። በዛፍ የተከበቡ መኖሪያ ቤቶችም እንዲሁ። ➧⓹/ ኳስ የማግኘት ሁኔታ ከዚህ በፊት ብዙ የእግርኳስ ተጠቃሚ ያለው ቫርዚሽ ቲቢ ከኢትዮሳት የሚርቀው 4.5° ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ ዲሽ ሳያስፈልግ በቀላሉ አንድ LNB እና ስዊች በመጨመር ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ምናልባት ሌሎች ሳተላይቶች ላይ የማናገኛቸው የፊልም ቻናሎችንም እዚሁ ሳተላይት ላይ እናገኛለን። ➧⓺/ የቀጣይነት ሁኔታ የዚህ ሳተላይት ባለቤት በቀመጫውን ሉግዘንበርግ ያደረገው SES ካምፓኒ ሲሆን ኢትዮሳት በብቸኛነት የተከራየው ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ሳተላይት ነው። ሆኖም የሳተላይቱ "Orbital Position" ኢትዮጵያ አናት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያ የራሷን የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ከ3 ዓመት በኋላ ስታመጥቅ 58.3°E ላይ ያርፋል። ስለሆነም ምንም አይነት ተጨማሪ የዲሽ እንቅስቃሴ ሳይደረግ ፍሪኩየንሲ ብቻ በመሙላት ኢትዮጵያዊ ቻናሎችን በቀጣይነት መጠቀም ይቻላል። ➧⓻/ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ቻናሎች በዚህ ሳተላይት የሚተላለፉ ቻናሎች ሐይማኖታዊም ይሁን ፖለቲካዊ ይዘት ይኑራቸው ገደብ የለባቸውም። ነገር ግን ሀገርን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቻናሎች ላይ እንደስከዚህ በፊቱ በ"Jaming" የሚዘጉ ሳይሆኑ ስርዓት ባለው መንገድ ኢትዮሳት ከሳተላይት ካንፓኒው ጋር የሚደራደርባቸው እና ማስተካከያ የሚደረግባቸው ይሆናል። በዚህ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው። #umer t.Me/Mkentertainmentz
نمایش همه...
ባይደን የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ። ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ትላንት ምሽት የኮቪድ-19 ክትባት ተከትበዋል። ተመራጩ ፕሬዜዳንት ክትባቱን ሲወስዱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለህዝብ ተላልፏል። ከጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በተመሳሳይ የኮቪድ - 19 ክትባት መከተባቸው የሚታወስ ነው። #tikvahethiopia t.Me/Mkentertainmentz
نمایش همه...
የዩኒቨርስቲዎች ጥሪ እስካሁን ድረስ ለተመራቂ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች 👇👇👇👇👇👇👇 1. AASTU ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 26 - 27 2. ASTU ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 10 3. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 1 - 2 4. አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከህደር 24 - 25 5. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 23 6. መቱ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 28 - 29 7. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26 8. ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26 9. ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 3 - 4 10. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 3 - 4 11. ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26 12. ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 21 - 23 13. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 24 - 25 14. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 29 - ታህሳስ 01 15. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 24 - 27 16. ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 30 - ታህሳስ 1 17. ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 29 - 30 18. መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 5 - 6 19. ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 26 - 28 20. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 3 - 4 21. ሰላሌ ዩንቨርሲቲ ህዳር 23 22. ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 28 - 30 23. ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26 24. ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 1 - 2 @gondarnewsmedianetwork
نمایش همه...
📍ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው በ ‘ኤሌክቶራል ኮሌጅ’ ተረጋገጠ❗️ ✒️ባይደን በአውሮፓውያኑ ጥር 20 ቃለ መሓላ ፈጽመው ስልጣናቸውን ይረከባሉ። በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከተካሔደ በኋላ በየግዛቱ በጥቂት ተወካዮች በሚካሔደው የውክልና ድምጽ ምርጫ ከ538 የውክልና ድምጾች 306 ድምጽ በማግኘት ጆ ባይደን ትናንት ምሽት በይፋ 46ኛ ፕሬዝዳንትነታቸው ተረጋግጧል፡፡ ✒️‘ኤሌክቶራል ኮሌጅ’ የሚል ስያሜን በያዙት በእነዚህ የውክልና መራጮች ከሚሰጠው ድምጽ ውስጥ 270 እና ከዚያ በላይ የሚሆነውን ማግኘት ለአሸናፊነት የሚያበቃ ሲሆን ባይደን በዋናው ምርጫ ያገኙትን ያክል 306 ድምጽ አግኝተዋል፡፡ ✒️‘ኤሌክቶራል ኮሌጁ’ ማሸነፋቸውን ካረጋገጠላቸው በኋላ ጆ ባይደን ባደረጉት ንግግር “የሕግ የበላይነት ፣ ህገ-መንግስታችን እና የህዝብ ፍላጎት አሸንፈዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ©CNN @Mkentertainmentz
نمایش همه...
📍ህዳር 29 ቀን 1965 ✒️የዛሬ 48 አመት ህዳር 29/1965 ዓ.ም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 708 ከአዲስ አበባ አስመራ በመብረር ላይ እያለ ምድር ለቆ መንሳፈፍ በጀመረ 13ኛ ደቂቃ ላይ መጠለፉ ተነገረ ። ♦️7 ጠላፊዎችም 2 ሴቶችና እና 5 ወንዶች ነበሩ ። እነሡም 1/ ዋለልኝ መኮንን 2/ ማርታ መብራህቱ (የዋለልኝ መኮንን ፍቅረኛ) 3/ በላይ ታደሰ (መሐመድ ዑስማን መሐመድ) 4/ ጌታቸው ሀብቴ 5/ ታደለች ኪዳነ ማሪያም 6/ ዮሐንስ ፈቃዱ 7/ ተስፋዬ ቢረጋ ✒️ጠላፊዎቹ የአውሮፕላኑን መጠለፍ ተናግረው ወደ ኮክፒቱ ለመግባት ሲሞክሩ ከጠለፋ አክሻፊዎች (anti hijackers) ጋር ግብግብ ጀመሩ ። አውሮፕላኑ በቶክስና በቦንብ ፍንዳታ ድብልቅልቁ ወጣ ። በቶክስ ልውውጡም ጠላፊዎቹ አንድ በአንድ እየተመቱ ወደቁ ። ✒️በውጤቱም ከጠላፊዎቹ ወገን ዋለልኝ መኮንን ጨምሮ 6 ጠላፊዎች ተገደሉ ፤ ታደለች ኪዳነማርያም ቆሰለች ። ከተሣፋሪና ከአየር መንገድ ሠራተኞች በኩልም 5 መንገደኞች እና 2 የበረራ አስተናጋጆች ቆሰሉ ። ከጠለፋ አክሻፊዎች በኩልም 2 መኮንኖች ቆሠሉ ። ✒️በወቅቱ አለምን ያስደነቀው የጠለፋ ድራማ ሂደት በብቃት ያከሸፉት የያኔው ሻምበል የቀኃላው ብ/ጀ ተስፋዬ አረሩ ቡድን መሪነት በረራው ውስጥ የነበሩት ግዳጃቸውን በብቃትና በጀግንነት የተወጡት የበረራ ደህንነት ጠባቂ ወጣት መኮንኖች እንደነበሩ ይታወሳል ። ✒️በጌዜው አውሮፕላኑን ያበሩት የነበሩት ዋና አብራሪ ካፒቴን ቀፀላ ብርሃኑ ከረዳት አብራሪያቸው ጋር በመሆን በነበረው የፍንዳታና ቶክስ ሁኔታ ሳይረበሹ 3 ሞተሮቹ ጠፍተው በአንድ ሞተር ብቻ ይበር የነበረውን አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ መልሰው በያኔው አጠራር ቀ.ኃ.ሥ. በአሁኑ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም አሳረፋት ። ✒️በ1960ዎቹ መጀመሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጠለፋ የሽብር ወንጀል ምክንያት ከፍተኛ የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ነበር ። በወቅቱ በጀብሃና ሻእቢያ አሸባሪዎችና ሀገራቸውን በካዱ ተላላኪዎቻቸው ይካሄድ የነበረውን የአውሮፕላን ጠለፋ የሽብር ድርጊት ለመቋቋም ይረዳ ዘንድ ከአለም ከእስራኤል ቀጥሎ ጠንካራና ብቃት ያለው የበረራ ደህንነት መቆጣጠሪያ መስሪያ ቤት ማቋቋም አስፈልጎ ነበር ። ✒️ይህንንም ትልቅ ሀገራዊ ሀላፊነት በመቀበል መስርያ ቤቱን በማቋቋምና ለበረራ ደህንነቱ ብቁ ባለሞያዎችን በመመልመልና በስፔሻል ፎርስ ስልጠና በማሠልጠንና በማብቃት የሀገር ኩራት የሆነውን አለማቀፍ ተቋም በመታደግ ለአሁን የከፍታ ደረጃው ያደረሡትን ጀግናው #ኮሎኔል_ካሣ_ገብረማርያምን ማንሳትና ማመስገን ግድ ይለናል ። እናመሠግናለን ኮሎኔል !!! @lupet @Mkentertainmentz @Mkentertainmentz
نمایش همه...
#ቀበሮ_ገዳይ ( በእውቀቱ ስዩም) . ድሮ ልጅ እያለን ደብረማርቆስ ውስጥ ቀበሮ ገዳይ የሚባል የመቶ ሜትር ሩዋጭ ነበር፤እናቱ ያወጣችለትን ስም የሚያውቅ የለም፤ ከለታት አንድ ቀን ፤ቀበሮ በሩጫ አባርሮ ጅራቱን ይዞ በርግጫ ደቅድቆ ገድሉዋል እየተባለ ይወራለት ነበር፤ ደብረማርቆስ ስቴድየም ውስጥ ውድድር ላይ የሚያደርገው ነገር ትዝ ይለኛል፤ ገና ሩጫው ሊጀመር ሲል ከጎረቤት አውራጃ ከመጡ ተወዳዳሪዎች ተነጥሎ ወደ ደጋፊዎቹ ዞሮ እጁን ያውለበልባል! ረጅም ስለነበረ የምስራቅ ጎጃምን ሰማይ በፎጣ የሚወለውል ነው እሚመስል! ከዚያ ፤በአክሮባት ወደ ሁዋላ ይገለባበጣል ! ያባ ታምሩ ወፍጮ መዘውር ራሱ እንደዛ አይገላበጥም፤ ይቀጥልና ወደ ሌሎች ተወዳዳሪዎች ዞሮ ይገረምማቸዋል፤ “ አሁን ቢቸግር እንጂ እናንተን ከመሰለ ውርጋጦች ጋር መሽቀዳደም ነበረብኝ “ የሚል ይመስላል፤ ልክ ሩጫ ሲጀመር ቀድሞ ይወጣና ይፈተለካል፤ በጣም ከመፍጠኑ የተነሳ ፎቶግራፍ ለማንሳት እንኩዋን አይመችም! ሁለት ካሜራማኖች ከጎ ከጎኑ ተከትለን ፎቶ እናነሳለን ብለው በልብ ድካም ሞተዋል ባጭሩ፤ ልጁ ቀበሮ ገዳይ ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኛ ገዳይም ነበር! ግን ችግሩ ምን መሰላችሁ? ቀበሮ ገዳይ ሩጫውን ለማጠናቀቀ አስር ሜትር ሲቀረው አቁዋርጦ ይወጣና ተመልካቹን ከሩዋጮች እሚለየውን የሽቦው አጥር ተደግፎ ያስመልሳል! እና አሁን ሳየው በህይወታችን ውስጥ ያሉት ብዙ ነገሮች እንደ ቀበሮ ገዳይ እንጂ እንደ ሃይሌ አይደሉም ፤ ነገሮችን ስንጀምርና ያለን ጉልበት እስከመጨረሻው አይቆየንም ፤ ኮረና የጀመረ ሰሞን፤ የዳንቴል ማስክ ሰርቼ በነፍስ ወከፍ ለህዝብ ካላዳረስኩ ብላ ስትገለገል የነበረች ሴትዮ፤ ዛሬ ዶክተር ሊድያ ገፅ ስር “ ይሄ ነገር ዛሬም አለ እንዴ ?’ የሚል ኮመንት ታስቀምጣለች፤ ጦርነትም እንዲሁ ነው፤ ውጊያ የተጀመረ ሰሞን የወኔ ችግር አይኖርም ባንድ ቀን ውጊያ ሁለት የጠላት ወታደር ገድለህ ፤ አምስት ማርከህ ሶስቱን ደግሞ እንዳይለመዳችሁ ብለህ ራሳቸውን ዳብሰህ ታሰናብታለህ፤ ጦርነቱ ካመት በላይ የሚቀጥል ከሆነ ግን ሌላ ጣጣ ይመጣል ፤ ወኔ በወይኔ ይተካል፤ በጥላሁን ገሰሰ ዘፈን ቀርቶ፤ ቂጥህን ራሱ በሳንጃ ብትወጋ ወደፊት መንቀሳቀስ ታቆማለህ፤ በሳንጃ የተወጋ ቂጥህን እንደ ሃብሃብ ፈንክተህ ጥለህ ፤ የተረፈ ቂጥህን አስከትለህ፤ ወደ ቤትህ መመለስ ነው የምትፈልገው! የፍቅርም ነገር እንደዚያ ይመስለኛል፤ ሲጀምር በነበረው ጉልበት የሚቀጥል ፍቅር ያለን ሰዎች የታደልን ነን ንዋይ ደበበ አፍላ ሳለ፤ ባንድ ብርጌድ ማሲንቆ መቺ ታጅቦ የሚዘፍነው ዘፈን ነበር” ያላንቺ እኖራለሁ እኔ መች ወጣኝ’ ይላል፤ መላው የሰው ዘር ለኦክስጂን ሲጠቀምበት የኖረውን አገላለፅ ነው ንዋይ ለፍቅረኛው የሰጠው፤ ንዋይ በሌላ ዘፈን “አትጥፊ በብዙ ከልቤ እንዳትወጭ እንደዛም ስላልኩሽ ቶሎ ቶሎ አትምጭ” ብሎ አረፈ፤ የመጀመርያው አገላለፅ ፍቅር የተጀመረ ሰሞን የነበረውን ስሜት ሲያንፀባርቅ ፤ ሁለተኛው ግጥም የሰነበተ ፍቅርን ይወክላል . . @Mkentertainmentz
نمایش همه...
🛩🛩🛩🛩✈️ በዓለም ላይ በጣም አጭር የንግድ በረራ በስኮትላንድ ነው የተካሄደው ፡፡ በረራው በስኮትላንድ ኦርኪኒ በሚገኙ ሁለት ደሴቶች መካከል የሚሄድ ሲሆን ከ 47 እስከ 90 ሰከንድ ብቻ ይወስዳል ፡፡
نمایش همه...
ከጀርባህ የሚያወሩት አንተ ከፊታቸው ስለሆንከ ነው... Keep going forward 🚶🚶 #Daily_Quotes t.Me/Mkentertainmentz
نمایش همه...
ትናንት እኮ ነው ! 😃 ሌባ ቤት ገብቶ ሚስረቅ ነገር ሲፈልግ ቲቪዉን አየው ከዛ አብይ እየተናገረ ነበር ፈዞ ሲያዳምጥ ተያዘ😜🤣 @Mkentertainmentz
نمایش همه...
‌‌‌SUBSCRIBE OUR CHANNEL👇👇👇👇 t.Me/Mkentertainmentz
نمایش همه...
وارد شوید و به اطلاعات مفصل دسترسی پیدا کنید

ما این گنجینه ها را پس از تأیید هویت به شما نشان خواهیم داد. ما وعده می‌دهیم که سریع است!