cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ወርቃማ ንግግሮች

☞ ወርቃማ ንግግሮችና ምክሮች፣ አነቃቂ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻናል ነው ‼️ ▮Share and Join t.me/Golden_speeches

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
861
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አግራሞቴን በብዕር 🔰 ተሸናፊነት (ሽንፈት) ◉ በህይወታችን ውስጥ አሸናፊነት ያላስተማረንን ብዙ ነገሮች ተሸናፊነት ያስተምረናል!! በህይወቱ ውስጥ አንድ ቀን ተሸንፎ የማያውቅ፤ እሱ እንዴት አድርጎ ነው የሚያሸንፈው!! እኛ ተሸናፊ የምንሆነው በመሸነፋችን ሳያሆን፤ .... ➛ ከተሸነፍን በኋላ ሽንፈታችንን አምነን መቀበላችን... ➛ለማሸነፍ ጥረት አለማድረጋችን.... ➛ ተስፋ ቆርጠን መቀመጣችን ነው!! ▪ከተሸነፍን በኋላ በሽንፈታችን ከተማርነበት፤ ይህ ሽንፈት ሳይሆን በሉ እንደውም ስኬት ነው!! ▪ዝግጅታችን፤ለማሸነፍ መዘጋጀት.... ▪ ትግላችን፤ እራሳችንን ለማጠናከር.... ▪ሽንፈታችንን ለማሸነፍ፤ ደጋግሞ መሞከር.... ➛ይህን ሁሉ አድርገንም ብንሸነፍ፤ ተስፋ አለመቁረጥ!! ▬▬▬ ይህ ነው ስኬት የሚባለው!! ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ለአስታያየት: t.me/ReshadMuzemil
نمایش همه...
𝐑𝐞𝐬𝐡𝐚𝐝 𝐌𝐮𝐳𝐞𝐦𝐢𝐥

ኒቃቧን ትለብሳለች...ትምህርቷንም ትማራለች። አላህ የደነገገውን የዲን ድንጋጌ የሰው ሰራሽ ህግ አይሽረውም።

ስለታማ ሰይፎድ [Sharp Swords] ይቺህ ዱንያማ ምንም እኮ ነች። ትንሽ አስደስታን ብዙ ታስከፋናለች❗️ ምንነቷን ካስተነተንናት እንደ መጥፎ ጥላ ወይም ህልም ናት‼️ በዚህች መጥፎ ጥላ በሆነችው፤ በህልም የተመኘነው ሁሉ ስንባንን እንደ ሚጠፈው በሽርፍራፊ ሴኮዶች ለምትቀያየረው ዱንያ ብለን መጥፎ ነገር አንስራ። በሉ እንደውም ነገ ምን እንደሚገጥመን አናውቅምና ዛሬ ላይ አዎ አሁን በዚሁ ቅፅበት መልካም ስራዎችን እናብዛ❗️ ◆ አላህን ከማመፅ ይልቅ መታዘዝና እሱን (አላህን) መገዛት፣ ◆ ከመጎሻሸም መደጋገፍን፣ ◆ ከመገፋፋት አብሽር በአላህ ፍቃድ እኔ አለሁልህ ብለን ሰዎችን መርዳት አስፈላጊ ነው ብቻ ሳይሆን ግዴታችንም ጭምር ነው።  ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ለአስታየት: t.me/ReshadMuzemil ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 t.me/Golden_speeches
نمایش همه...
📌አሰላሙዐለይኩም ያ ዒበደሏህ  የእጁጅ ወመእጁጅ በሚል ተከታታይ የሆነ ፁሑፍ በማንበብና ሼር በማድረግ ላይ እንመክራለን‼️    አሁኑኑ ጆይን ይበሉ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥👉🏿@tewihd
نمایش همه...
አግራሞቴን በብዕር ብዙ ተወዳዳሪዎች ሜዳ ላይ ናቸው፣ አሸናፊው ግን አንድ ነው፤ ሁሉም ተወዳዳሪዎች ይህንንም እያወቁ ለውድድሩ ይቀርባሉ። በቃ የህይወት ህግ ይህ ነው! እኛ ምንደሰተው ግዴታ እኛ ስላሸነፍን መሆን የለበትም፤ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችም ሲያሸንፉ ደስታ ሊሰማን ግድ ይላል!! በዚህ መልኩ ተከባብረን እና በአንዳችን ደስታ ሌላኛችን ተደስተን መኖር ይኖርብናል። ካልሆነማ፣ የህይወት ጉዙ በጣም ግራ የተጋባ ነው፤ ህይወታችንን ለማሳመር ብለን ጉዞ ስንጀምር፣ መንገዱን ተጉዘን ጣንጨርሰውም መንገዱ ራሱ ያልቃል!!..... ያኔም ራሳችን እንጠይቃለን እንዲህ እያልን...... ምን ስህተት ሰርተን ይሁን ይህ የገጠመን!? ቆይ የቱ ጋር የው ቀመሩን(formula'ውን) የተሳሳትነው!? እያልን። ግን ያላስተዋልነው ነገር ቢኖር መጀመሪያውኑም የህይወትን ቀመር አናውቀውም!! ከኛ የሚጠበቀው አንድ ነገር ነው፣ እሱም ትክክለኛ በሆነ መንገድ ጥረት ማድረግና ቀሪውን ለፈጣሪ መስጠት!! ብዙ መፈላሰፍ እና እንዲህ ለምን ይሆናል እያልን እራሳችንን ማስጨነቅ አግባብ አደለም!! የሆነው ይሁን በቃ፤ እኛን ይጎዳናል ያልነውን፣ እየሆነ ያለውን፣ እኛ እንዳይሆን ማድረግ ከቻልንና አቅሙ ካለን እሺ፤ እቅሙ ከሌለን ግን መተው የተሻለ ይሆናል!! ይህንንማ ላስታውሳችሁ....! የህይወት ጉዙ በጣም ግራ የተጋባ ነው፤ ህይወታችንን ለማሳመር ብለን ጉዞ ስንጀምር፣ መንገዱን ተጉዘን ጣንጨርሰውም መንገዱ ራሱ ያልቃል!! ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል! ለአስታየት: t.me/ReshadMuzemil ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 t.me/Golden_speeches
نمایش همه...
👍 1
ለበይክ..... በኢብን ሙዘሚል 👉🏿@tewihd
نمایش همه...
Track-146.mp31.29 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ነገ ዙልሂጃ 1 ነው... 🤌 ይህ ማለት እሁድ በቀን 09/10/2016EC የ1445ኛው ዒድ አል-ዓድሀ በዓል ይሆናል ማለት ነው!! 👉🏿@tewihd
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ከሞትክ በሃላ ምድራዊ ህይወት ምን እንደምትመስል ለማየት ከፈለክ ፧ ሌሎች ከሞቱ በሃላ እንዴት ወዳጆቻቸው እነሱን ረስተው በራሳቸው ጉዳይ ላይ መጠመዳቸውን ተመልከት ፡፡ ያኔ አንተንም ረስተውህ በጉዳያቸው እንደሚጠመዱ አትዘንጋ ፡፡ #ስለዚህ ህይወትህን ለጌታህ ስጥ! ብቸኛው ከሞትክ በሃላ የማይረሳህ፣ ከሰውነትህም የምትቀንሰውን ነገር አዋቂ እሱ ነውና 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄👇 t.me/Golden_speeches
نمایش همه...
ወርቃማ ንግግሮች

☞ ወርቃማ ንግግሮችና ምክሮች፣ አነቃቂ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻናል ነው ‼️ ▮Share and Join t.me/Golden_speeches

🔰 የውድቀት ፍርሃት ስኬት የህይወትህ አንድ አካል ሊሆን የሚችለው በአላህ ፍቃድ እችላለሁ ብለህ ሁሌም የምትሞክር ከሆነ ነው። ◆ ሰዎች ውዳቂነትን ማንነታቸው የሚያደርጉት መውደቅን በመፍራት ደጋግሞ ባለመሞከራቸው ነው። መውደቅን ፈርተን የማንሞክር ከሆነ መቼም ሊያልፍልን ወይም ሊሳካልን አይችልም። ሳንሞክር ደግሞ ከፍ ማለትም አንችልም!! ◎ ከኛ የሚጠበቀው አንድ ነገር ነው እሱም በወደቅን ቁጥር ለመነሳት መሞከር። አንዳንዴ እኮ ውድቀት በራሱ ደስታን፣ እርካታንና ስኬትን ይሰጣል። ለምን ቢባል ያልወደቀ ሰው የማሸነፍን ዋጋ ሊያውቅ አይችለም። ስንወድቅ ነው የውድቀታችንን መነሻና የምናሸንፍበትን ደግሞ መንገድ የምንረዳው። ➤ ውድቀት ከተማርንበት ውድቀት ሳይሆን ስኬት ነው። ውድቀት "ውድቀት" ነው የምንለው ያኔ ነው ከወደቅን በኋላ ዳግም ለመነሳት ያልሞከርን ከሆነ ነው። ወድቀን ዳግም ከተነሳንማ ይህ ውድቀት ሳይሆን ስኬትን ለመጎናፀፍ የሚደረግ የየህይወታችን አስደናቂውና አስደሳቹ ፊልሚያ ነው። ● እኔ ይህን እያልኳችሁ አደለም ለማሸነፍ የግድ መውደቅ አለብን። እኔ ይህን እያልኳችሁ ነው መውደቅን እየፈራን መኖርን አናቁም ነው። ▮አዎ መውደቅን ፈርተን የተለያዩ ጥረቶችንና ሙከራዎችን አቆምን ማለት በህይወት መኖርን ተውን ማለት ነው፣ ምክንያቱም ህልም የሌለው ሰው በቁሙ የሞተ ሰው ነውና። ነብር እኮ ዋሻን ለመዝለል በፈለገ ጊዜ ብዙ የሆኑ እርምጃዎቹን ወደኋላ ይሄዳል። ያኔም ነው ያለ የሌለ ኃይሉን ሰብስቦ ዋሻውን መዝለል የሚችለው። አያችሁ⁉️፣ ነብሩ ዋሻውን በስኬትና በድል ለመዝለል (ለማለፍ) መጀመሪያ ወደኋላ መመለስን (መውደቅን) ምርጫው ያደርጋል። ምን ማለት ፈልጌ መሰላችሁ፦ ስንወድቅ ያ! ውድቀታችን ለስኬት እያዘጋጀን፣ እያለማመደን መሆኑን እናስተውል። ◉ቱርኮች፡ ከፈለክ ህይወትህን እጣ፣ ነገር ግን ተስፋህን እንዳታጣ ይላሉ። ▮ የስኬት ጎዳና የሆነው ተስፋ ሲሆን፣ የውድቀታችን መነሻ የሚሆነው ደግሞ ተስፋ ማጣታችን ነው። እናም ወዳጆቼ ተስፋን ባለመለመ ጉልበት ደጋግመን ብንወድቅ እኳን ደጋግመን ለመነሳት ሙከራ እናድርግ። እመኑኝ በአላህ ፍቃድ ይሳካልናል። ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ለአስታየት: t.me/ReshadMuzemil ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 t.me/Golden_speeches
نمایش همه...
𝐑𝐞𝐬𝐡𝐚𝐝 𝐌𝐮𝐳𝐞𝐦𝐢𝐥

ኒቃቧን ትለብሳለች...ትምህርቷንም ትማራለች። አላህ የደነገገውን የዲን ድንጋጌ የሰው ሰራሽ ህግ አይሽረውም።

3
ይህ ሁሉ ለምንድነው በእኔ ላይ የሚሆነው? የሚለውን ቃል "ነገሮች እኔን ምን ለማስተማር እየጣሩ ነው?" በማለት እስካልቀየርክ መቼም አሸናፊ መሆን አትችልም። 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄👇 t.me/Golden_speeches
نمایش همه...