cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቶጳዝዮን

በብዕራችን ጥበብን እናነግሳለን። የብዙ ገጣሚያን ስራዎች የሚቀርቡበት ምርጥ ቻናል ነዉ። @topazionnn @topazionnn for any comment👇👇 @ediwub @Tirrubel @balageru_1

نمایش بیشتر
Advertising posts
695مشترکین
+124 ساعت
+67 روز
+4230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ድንቅ መንፈሳዊ ግጥም❤️ በዔደን እና ዕሌኒ ተፅፎ እንደቀረበ @ediwub & @eluuu2112 @topazionnn @topazionnn
نمایش همه...
🥰 3
Repost from ቶጳዝዮን
እሷን ይመስለኛል . . በብሩሽ ቢቀለም የሴትነት መልኩ፤ ተለክቶ ቢሰፈር የቀሚሷ ልኩ፤ እሷን ይመስለኛል......... በጥለቷ እራፊ እንባዋን ሸፍና፤ የልቧንን እህታ በሳቋ አፍና፤ ራሷ በርትታ 'ምታበረታዋን፤ ራሷ ጀግና 'ምታጀግነዋን፤ የዘወትር አመስጋኝ ደጃፉን ናፋቂ፤ አድባር የመረቃት ጠበኛ አስታራቂ፤ ቃሏ 'ማይታበይ እዉነተኛይቱን፤ የእግዚአብሔር ወዳጅ ባለማተቢቱን። እሷን ይመስለኛል........እ'..ሷ'..'ን ✍✍ኤደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
نمایش همه...
እንኳን መጣህልኝመጣህልኝ.... ፧ ፧ ለምን ሄድክ አልልም፤ እንዲህ አደረገኝ ብየም አልወቅስህም፤ እንኳን መጣህልኝ፤ እንካንም አወከኝ፤ እንኳንም አቀፍከኝ፤ አንኳንም ዳበስከኝ። በቅንጭብጭቡ ትርክት፤ በደራሲያ መፀሀፍት፤ ፍቅርን ላወቀችው ፍቅርን ላጠናችው፤ ለእደእኔ አይነቷ ሴት፤ መምጣት ሀሴት ናት። ተለያዩ እያለ ሀገሬው ተረተ፤ ፊደል ያወኩ ባንተ፤ ፍቅርን ያየሁ ባንተ፤ ጣት አየጨበጠ ቃል ያስደረደረ፤ አድስ ማንነትን ሰብኮ የፈጠረ፤ መጥፌየን ከጥሩ ለይቶ የሳየኝ፤ የህይወቴን ቅመም ትዝታ የሰጠኝ፤ የልብህ ብራና ቢሰርዘኝ እንኳን። የመውደድ ልኩ፤ የመኖሬ መልኩ፤ ፍቅርህ ዘላለሜ፤ መኖርህ አለሜ። የትም ሁን ግደለም፤ ብትሄድም ብትቀርም፤ ቃሌን እኔ አላጥፍም፤ ያዳም ዘር ቢሞላም፤ እመነኝ መውደድ፤ ካንተ ሌላ አላቅፍም። ✍️ዕሌኒ @eluuu2112 @topazionnn @smetoch12
نمایش همه...
1
አርጅቼልሽ የለ🥰 ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን @topazionnn @topazionnn @topazionnn
نمایش همه...
🔥 3
ወደ ግሩፑ በመግባት ግጥሙን ላይክ አድርጉልኝ🙏
نمایش همه...
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 . 11 ኛ ዙር ግጥም ውድድር 🎤ኢትዮጵያዊነት ነው                                    አሼንድዬን ላከብር ትግራይ ተሻግሬ መጣሁ ወደ ደቡብ አክሱም ላይ አድሬ ቀናትን ቆጥሬ... የማከብርበትን ደማቅ በዓል ፍቼ ጨምበላላ ሲሉ ዝናውን ሰምቼ ሸገር ላይ አድሬ ሲነጋ ሲዳማ ወግና ባህሉን ለዓለም ላሰማ፤ ለምን እቀራለሁ ኦሮሞስ መጓዜን ልሻገረው እንጅ ሸካክፌ ጓዜን ለማክበር ኢሬቻን። መስቀል ደረሰና ሄድኩኝ ከጉራጌ ኢትዮጵያዊነት ነው ባህልና ወጌ ገና'ን ላሊበላ ጥምቀትን በጎንደር አማራ ተጉዠ በአላቱን ሳከብር ትዝ አለኝ በድንገት ቁልቢ ገብርኤል አሁን ደግሞ ሀረር ጉዞዬን ልቀጥል እሄዳለሁ አፋር ቤንሻጉል ሶማሌ ኢትዮጵያዊነት ነው ወግና ባህሌ ናዝሬት ድሬደዋ ወላይታ ጋምቤላ ከሀበሻ ምድር... የሚወደድ እንጂ የለም የሚጠላ በነጻነት ምድር በሰሜን በደቡብ ከጽንፍ እስከ አጽናፉ በምስራቅ በምዕራብ ሁሉንም አያለሁ ኢትዮጵያን በሙሉ መገለጫዬ ነው ወግና ባህሉ።              ✍ በ ናሆም ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት 🏆🏆🏆 ለመቀላቀል 👇👇👇 t.me/zemaritnsae 🏆🏆🏆🏆🏆 ግጥም ለመላክ . 👇👇👇 . @Tins7
نمایش همه...
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ 2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

👍 1 1
ሞት . ያ....ክፉ ነጣቂ፤ ከሥጋ ለይቶ እስትንፋስ ፈልቃቂ፤ ወሳጅ መልአከ ሞት በሰዎች ጀርባ ላይ፤ ተንጠልጥሎ ሚኖር በእድሜ ገደብ ጣይ፤ ቀናትና ወራት በቀመር ሲለኩ፤ ወራትና አመታት ፈጥነዉ ሲተካኩ፤ የሰዉ ልጅ ማለፊያዉ፤ የእስትንፋሱ ማብቂያው ፤ ከአይን ጥቅሻ እጅጉን ይቀርባል፤ ከአፈር እንደመጣ ከአፈር ይከተታል። ..................................................... በዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
نمایش همه...
2🔥 2🕊 1
🙏ገብርሔር🙏 ልክ እንደ ገብርሔር ወገብር ምዕመን መክሊትን ሰጠኸኝ ላንተው እንድታመን እኔም በተቸርኩት አቅሜ በሚፈቅደው የሰጠኝን መክሊት ከቤቴ ብወስደው አትርፌና አብዝቼ እንድገኝ አስቦ ጠብቆኝ ነበር መንግስቱን አስውቦ እኔ ግን...ኃጥኡ ስንፍናን አብዝቼ መክሊቴን ቀባሪ መታመኔን ትቼ ገብረ ሀካይ ሆኘ ከመሬት ቀበርኩት አትርፌ አልሰራሁም የሰጠኝን መክሊት ከከበረች ገነት ብርሀን ከምትሰጥ የጩኸቷን ባዕት ጨለማን የምመርጥ ዳግም ስጠኝና መክሊትን በልኬ እጥፍ እንዳደርገው አግዘኝ አምላኬ @topazionnn @topazionnn @balageru_1
نمایش همه...
👍 1🙏 1
ገብርኄር . የክርስቲያን ወጉ፣ የክርስቲያን ህጉ፣ ነፍስን በዘራበት በአምላኩ አምኖ፣ መክሊቱን አትርፎ በጥቂቱ ታምኖ፣ ሞገስን አግኝቶ በብዙ መሾም ነው፣ ከሀጢአት ርቆ በፅድቅ መኖር ነው። ................................................. በዔደን_ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
نمایش همه...
🥰 1
# ተወዳጇ # ገጣሚ ህሊና ከግጥሙቿ ይበልጥ የምትወደውን ግጥም እነሆ ተጋበዙልኝ ... @smetoch12 @smetoch12
نمایش همه...