cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

እዚህ ቤት

አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም ኢትዮጵያዊ ሆነን—የሚያግባባ አናጣም! ዕወቂው ዐለሜ...! ኢትዮጵያዊ መሆን—የውርስ እንቁጣጣ በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ! |ታመነ መንግሥቴ ውቤ—አባ ወራው| ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል እና ጥበብ እናወጋለን! ጀበናዋ ተጥዳለች! ፍንጃሎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም! ክሕሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ። ትውልድ❤

نمایش بیشتر
Advertising posts
1 002مشترکین
-224 ساعت
-37 روز
-1330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አያልነህ ሙላት/ሙላቱ 📝ሰውየውን የማውቃቸው ገጠር ሳለሁ በአማራ ራዲዮ ነው።ማራኪ ተናጋሪ ናቸው።ልጅነታቸው ይጣፍጣል። 📝የ ብንያም አቡራ «ወደ ፍቅር ጉዞ»መጽሐፍ የተመረቀ 'ለት ከወመዘክር ወጣ እንዳልነ አንዱ ገጣሚ ፣ጋዜጠኛ እና አሁንም ሥነ-ጽሑፍ የሚማር ጓደኛየ እንደዋዛ «ጋሽ አያልነህ የእርስዎን ግጥሞች እኮ መምህሮቻችን 'አብዮታዊ ግጥሞች'እያሉ ነው የሚያስተምሩን፤»ብሎ አበሸቃቸው። ጨሱ።ጸያፍ ሥድብ አመለጣቸው።ልጁ ሲነግረኝ ረጅሙን የግጥም መጽሐፋቸው አንብቧል።እውነትም ሥንኞቻቸው ከኪናዊ ለዛ ይልቅ አቢዮታዊ ቃና እንደሚነበብባቸው አወጋኝ። ሳላነብ አመንኩት።ግጥም ማንበብ ላይ ሰነፍ ነኝ።ከእናቴ የሚበልጥ ገጣሚ ስላላገኘሁ ይሆናል። ለሁሉም ጋሽ አያልነህን እንዲህ ያስታወስኳቸው በጴጥሮስ ቶጃ(ርዕሰ ምሁር ናቸው፤) ግለ-ታሪክ የጀርባ ሽፋን ላይ የሚከተለውን ሥንኝ እና አሳዛኝ ሥሜቱን አጋርተው አግኝቻቸው ነው። ኑ በአባቶቻችን አብረን እንዘን፤እንፈርም፣ወይም ከተገኘ እንኩራ፦ «በ1965 ዓ.ም አውሮፓ እያለሁ አንድ አጭር ግጥም ቋጥሬ ነበር። እሳት ነደደ አሉ በአገራችን ጓዳ ጓዶች ብርድ አይምታን ገብተን እንጣዳ። እንለግስ ጭራሮ አንሁን ማገዶ እሳቱ እንዳይጠፋ ጢሶ ጢሶ ነዶ። (ጥገት ላም) ይህ ግጥም ለእኔ ማዕበል ጠሪ ወፍ🦃 ነው።እጅግ በርካታ ጓዶችን ከውጭ አገር ዩኒቨርስቲዎች ቤተ-መጽሐፍት እያበረታታ ለአብዮት የሰደድ እሳት «ጭድ»^ያደረጋቸው መስሎ ስለሚታየኝ ለግጥሙ ያለኝ ፍቅር እጅግም ነው።» 🦃አዲሱ የዓለማየሁ ገላጋይ መጽሐፍ ርዕሱ «ማዕበል ጠሪ ወፍ»ይላል።የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ነበርኩ። ^የጴጥሮስ ቶጃ ግለ ታሪክ ርዕሱ «የጭድ እሳት» ነው። ሰላም ይስጥልነ!
نمایش همه...
نمایش همه...
👏 1
ኦሮማይ መጽናኛየ ነው።ተማሪ ሳለሁ አራት ጊዜ አነበብኩት።መመረቂያ ጽሑፌም ደራሲው በኦሮማይ ጋዜጠኝነትን እንዴት እንደተመለከተው ያትታል። ትረካውን በጣም እወደዋለሁ።ፍቃዱ ተክለማርያም ፊያሜታን ሲያስመላት በቃ ሙትት እላለሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ያለ መጽሐፍ መኖሩን የጠቆመኝ እና PDF የላከልኝ ፊያሜታ ላይላ ነው። ሌላኛው የእኔ ምርጥ መጽሐፍ የ«ሐበሻ ጀብዱ» ይሰኛል።በንባብ ሁለት ጊዜ አጥንቸዋለሁ።ተርጓሚውን ተጫነ ጆብሬ መኮንን'ን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መጥተው ጠይቄያቸው አውቃለሁ።ምርጥ ሰው ናቸው። መጽሐፉ በአማርኛ ተተርኳል።ትረካውን እንደ ሙዚቃ አደምጠዋለሁ። ሶስተኛው ለልቤ የቀረበ መጽሐፍ «ሌላ ሰው»ነው። ኮቪድ ሊገባ ሳምንታት ሲቀሩት የአብርሐም አፈወርቂን እና ፀሐይቱ ባራኪን ዘፈን ማጀቢያ አድርጌ ያነበብኩት ውብ ሥራ ነው። ዘፈኖቹን በሰማሁ ቁጥር መጽሐፉ ትዝ ይለኛል። ዛሬ ዛሬ ሳነብ ለቅንጦት አይደለም።በቀጥታ ለሥራዬ ሊጠቅመኝ ይገባል። ሳድግ አንድ የሐዲስ ዓለማየሁን ፍቅር እስከ መቃብር የሚልቅ ልብወለድ የመጻፍ አሳብ አለኝ።ታዲያ ከዚያ በፊት ኑሮየ ሊደላኝ ይገባል። ገጠመኞቸ'ን የያዘው «የትውልዴ ገድል»በቅርብ ዓመታት ውስጥ መነበቡ አይቀርም። ግን አልቸኩልም።
نمایش همه...
የእሁድ መደሰቻ❤ https://vm.tiktok.com/ZMMVhjhAK/
نمایش همه...
نمایش همه...
Arts Tv World

የዓለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጠሪ ወፍ"የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ መጽሐፉ ስድስት የ20ኛው ክፍለ-ዘመን የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ሰዎች ኪናዊ ሥራ የተፈተሸበት እንደሆነ ተገልጿል። ከመድረክ ሥነ-ጽሑፋዊ ትንታኔ ያቀረቡት አርታኢው ቴዎድሮስ አጥላው ዓለማየሁ ገላጋይን "Experimental Nobelist" እንደሆነ...

ማዳንና መግደል (ሸጋው ማሬ) የዐይኖቼን ዕይታ፥ ወደ ላይ ብልከው አብ የልቤን ዐይቶ፥ ማኅፀኔን ባረከው! ደግ ልቤን ብልክ፥ በአድማስ ተስፋዬ ላይ እኔው ፀሐይ ኾኜ፥ ሠጠኝ ሌላ ፀሐይ! የፍቅሬን መገለጥ፥ በማኅፀን መዝኜ ሕይወቴን ስሠጣት- በአምላክ ተማምኜ ይኼው በመባረክ፥ ብርሃን ተገኘ። ወትሮም ልማዱ ነው፥ ፍቅር ከእናት አንጀት ትንሣኤና ፍቅር፥ ለልጇ መመኘት ገዳም ነው የ'ሷ ልብ፥ መቅደስ ነው መንፈሷ በሥጋ ስዋትት፥ ተገኘሁ በነፍሷ! *ለ“ግንቦት ፳፱”
نمایش همه...
👍 6
ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ በትዝታው መጣ! (ሸጋው ማሬ) የአአዩ ኬሚስትሪ ምሩቁ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ ደቡብ ኦሞ ጂንካ የሔደው በአስተማሪነት ነበር። በዚህ ዞን ብሔረሰቦች ፍቅር የተነደፈው ያኔ ነው። ”ከቡስካ በስተጀርባ”ን በ1987 አሳተመ። በ1990 ደግሞ ተወዳጅ መጽሐፉን ”ኢቫንጋዲ"ን ሠጠን። “የዘርሲዎች ፍቅር” (1991)፣ ”አቻሜ" (1992)፣ ”የንሥር ዐይን” (1993)፣ ‘Land of the yellow bull' (1995)፣ ”ጃገማ ኬሎ- የበጋው መብረቅ” (2001)፣ እና ”የሚሳም ተራራ” (2016) የቆንጅዬው ደራሲ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ ሥራዎች ናቸው። ፍቅረ-ማርቆስ በትውልዱ ጎጃሜ ቢኾንም፤ በሕይወቱና በፍቅሩ ሐመሬ ነው። ሐመሮችን ያወቅናቸው በፍቅረ-ማርቆስ ነው። ከፍቅረ-ማርቆስ ተወስዶም በዘፈንና በጽሑፍ ”ኢቫንጋዲ” ተለምዷል። ተወዳጁ ባሕላዊ ጭፈራ ቤተኛችን ኾኗል። ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ መጽሐፉ በእንግሊዝኛ የታተመለት ደራሲ ነው። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ደቡብ ኦሞ በተሠሩ ጥናታዊ ፊልሞች ላይ ተሣትፎ ነበረው። ጎጄው ፍቅረ-ማርቆስ፣ ሐመሩ ፍቅረ-ማርቆስ፣ ኢትዮጵያዊው ፍቅረ-ማርቆስ፣ አሜሪካዊው ፍቅረ-ማርቆስ... የዓለም ሰው ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ!
نمایش همه...
3👍 1🔥 1
ያንድ ምሽት ሓሳብ (በዕውቀቱ ሥዩም) ልማድ ኾኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ ሕልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤ ሳይጎድለኝ ለዛ ሳያንሰኝ ውበት የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ኾኜበት፥ ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት መወደዴ ብላሽ ምኞቴ ዘበት፤ የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ የፈረስ ሐውልት፥ እንደመጋለብ ሲሣይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥ የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን -ዕንባየን ልሼ ደረቴን ሠብሮ ፥ የሸሸ ልቤን ቦታው መልሼ በፍቅር ፈንታ ፥ ዕረፍት ሸመትኹኝ ቁርጤን ዓወቅሁኝ፤ ለካ ሰው ቢማር፥ ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከዕድሜ ቁርጥን ማወቅ ነው የዕውቀት ፍጻሜ፡፡
نمایش همه...
"ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" ልዩ ዐውደ ርእይ በግዮን ሆቴል | ከሚያዝያ 5 - 13 ከሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የመግቢያ ትኬትዎን በኦንላይን https://event.hamereberhan.org ላይ ይቁረጡ!
نمایش همه...
2
ዘመናት እንደቀልድ ይነጉዳሉ፤ ሥራዎች ግን ዘመናትን ይሻገራሉ። "ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" ልዩ ዐውደ ርእይ በግዮን ሆቴል ከሚያዝያ 5-13 የመግቢያ ትኬትዎን በኦንላይን event.hamereberhan.org ላይ ይቁረጡ!
نمایش همه...
1