cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Tribune sport ትሪቡን ስፓርት የኮከቦች ገፅ

ትሪቡን ስፖርት ስፖርትን ለመከታተል ትክክለኛው ቦታ በ ኤፍሬም የማነ እና ፍቅር ይልቃል

نمایش بیشتر
Advertising posts
1 818مشترکین
-124 ساعت
-17 روز
-2930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Ten out of zero 10/0 Erick Ten hag ? ቴን ሃግ ከተስፋ ጅማሮ ወደ ዜሮ እንደ ታሪኩ ውሎ ማደር በተሳነው ማንቸስተር ዩናይትድ ... በዩናይትድ የውጤት አዙሪት መጥፎ ዓመታት ሂደት በጊዚያዊ አሰልጣኝነት ኦልድትራፎርድ ደረሰው ከተመለሱ አሰልጣኞች አንዱ የሆኑት ራልፍ ራኝክ 6 ወር በሚያውቁት ዝነኛ ጓዳ ገብተው ከወጡ በኋላ ይህንን ተናገሩ ... ማንቸስተር ዩናይትድ ዘለቄታዊ ለውጥ ዳግም ማንሰራራት ከፈለገ የታይ ታይ የይስሙላ ዕድሳት ሳይሆን የማያዳግም ቀዶ ጥገና ያውም የልብ ያስፈልገዋል ሲሉ በአንድ ወቅት ተደመጡ ። የግሌዘሮች አሻንጉሊት ከሆነ በከረመው ክለብ ስር ነቀል ለውጥ እንደሚያስፈልግ መሠከሩ ። ለወደቀው የላንክሻየር ገናና የይስሙላ ጥገና እንደማይሆንም ከጋዜጠኞች ሞገቱ ። ሰውየው አልተሳሳቱም ። ከውጤት የጡት አባቱ ፈርጉሰን ጡረታ በኋላ ከታይታኒክ በፈጠነ እየሰጠመ ያለው ዩናይትድ ከቁልቁለት ህመሙ ለመነሳት ዕውነተኛ ሰርጀሪ ያስፈልገዋል ያውም የልብ ... አልያ ከከሸፈ የሰነበተው ክለብ ሚስጥራዊ የመሠለ ውስብስብ የውድቀት ፍፃሜ ለሚሊዮኖች ግራ የሚያጋባ ነው ። የዘንድሮው ደግሞ በክለቡ የዓመታት ታሪክ የበሳ ሆኗል ። ዩናይትድ ከ17 የሲዝኑ ጨዋታ በ9ኙ ተሸንፎ ከተስፋ ቢስ እንቅስቃሴው ጋር ደጋፊዎቹን ሁሉ ተስፋ አስቆርጧል ። ለዘመናት የደቆሷቸው ተቀናቃኞቹ ሁሉ መሣለቂያም ሆኗል ። ኤሪክ ቴንሃግም ከ400 ሚሊዬን በላይ ያፈሰሱበት ቡድንን የበለጠ አፈራርሰው ወደ ኤርዲቪዚዬ ሊመለሱ ሌት ተቀን እየተጉ ነው ። ከልብ ቀዶ ጥገናም በላይ ለለውጥ ሌላ አቢዬት የሚያሥፈልገው ማንቸስተር ዩናይትድ መጨረሻ ዘንድሮ ተናፋቂ ነው ። በቻምፒየንስ ሊግ ባየር ሙኒክ ከሃሪ ኬን ጎሎች ጋር ሲቲ ኢንተር ሪያልማድሪድ ሌፕዚግ የመሣሠሉት ወደ ሁለተኛ ዙር ገና ሁለት ቀሪ ጨዋታ እየቀራቸው ሲያልፉ የsuper mike Arteta ወጣት መድፈኛም የአንዳሉሺያኑ ሲቪያን በsaka class ተፅእኖ ረቶ መንገዱን አስተካክሏል ። ትሪቡን ሪቪው ዛሬ ምሣ ሰዐት ከስድስት እስከ ስምንት ብስራት fm 101.1 ላይ በቻምፒዬንስ ሊግ ሪቪው ዳሰሳ ጋር ይጠብቃችዃል ። ከዛ ውጭ በተለመደ የትሪቡን ተወዳጅ አንደበት ካሜሮናዊ ቡጢኛ ዣቪየር ፍራንሲስ አስገራሚ የህይወት ፈተና ያልበገረው በፅናት አልሸነፍ ባይነት በመጨረሻ እጅ የሰጡ ዛሬ ሆሊውድን ደጅ የሚያስጠና ስኬታማ የዚህ ዓለም የህይወት መንገድ በኮኮቦች ገፃችን ይዳሰሳል ። በመፅሐፍ አምዳችን በv በልብ በተጨዋችነት በቡናማው ቀለም በአሰልጣኝነት ደምቋል ። ስዩም አባተ ይባላል ። ዛሬ በህይወት የሌለው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ አንጋፋ ውጤታማ ሙያተኞች አንዱ ነበር ። ዕጅግ የተከበረ ስም ካተረፉ የካምቦሎጆ ዝነኞች ... እናም ስዬም አባተ ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ይናገራል ። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ሞተ ይላሉ መቼ ኖሮ ያውቅና ነው ሞተ የሚባለው ሲል ስለ ኳሳችን ዘመናት የዘለቀ ፈተና ይተርካል ። በመፅሐፍ ገፃችን ይቀርባል ። ሀሳብ አስተያየት አድርሱን ... በዩቲዩብ , face book , tik tok, ቴሌግራም ዲጂታል ሚዲያችን ተሳተፉ ። ዋና ዋና ደንበኞቻችን የታላቁ ሩጫ ቲሸርት ተሸላሚ እናደርጋለን ።
نمایش همه...
Scott Fergi Time በሰውየው የሀዘን ሳምንት ለጨነቀው ዩናይትድ ! ስኮት ማክቶሞናይ ከታይታኒክ በፈጠነ እየሰጠመ ያለው ገናናን ከውድድር ዓመቱ 7ኛ ሽንፈት የማታ ማታ ታድጓል ። ቅርፅ ያጣው በዘፈቀደ የሚንቀሳቀሰው ከአጣብቂኝ ለመውጣት የገፏቸውን አማራጮች ሁሉ መጠቀም የጀመሩት ኤሪክ ቴንሃግ ድንገት እያመለጣቸው ባለው የህይወት ዘመን ታላቁ እንጀራቸው የዕድሜ ማራዘሚያውን በscott fergi time magic አግኝተዋል ። ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ዕዱሉን ምን ያህል አስተባብረው በሽንፈት ስነ ልቦና አረንቋ የተዘፈቀው ቡድናቸውንም እራሳቸውንም ነፃ ያወጣሉ ቀጣዩ አጠራጣሪ ግን በጉጉት የሚጠበቀው ጥያቄ ሆኗል ? አድማጮች ሰውየው ከ12 ዓመት በፊት ለህይወት ዘመን አጋራቸው ጊዜ ለመስጠት ሲሉ ነግሰው ያነገሱትን ክለብ ለቀቁ ። ያቺ የኦጉየሮ ተዓማርን ከጩኸታም ጎረቤት ሲመለከቱ ለአንድ ዓመት ባለቤታቸው ካቲን አስፈቅደው የጡረታ ዘመናቸውንም አራዝመው ከሲቲ መንጋጋ የተነጠቁት ዋንጫን ቫንፐርሲን ከአርሰናል አስፈርመው መልሰው ነጠቁ ። ከዚያም በክብር ተሸኙ ። ዩናይትድም የኋይል ሚዛን አሳዳጊ አባቱን ካጣ ማግስት በጩኸታም ጎረቤቱ የድል ማዕበል የተዋጠ ዳግም እንደ ታሪኩ ውሎ ለማደር የስኬት ቁልፉ የጠፋው ብኩን ሆኖ 12 ዓመታት ተሻገሩ ። ካቲ ፈርጉሰን ከጆቫና ግላስኮ የጀመረው ለ 57 ዓመታት የዘለቀው የፍቅር የትዳር የህይወት ዘመን ጓደኝነት ጉዞም በዚህ ሳምንት በሞት ተቋጨ ። ለእነዛ ሁሉ የድል ዓመታት ስኬቶች ከሰውየው ገናና ታሪክ በስተጀርባ ዋና ተዋናይ የነበሩት ሴት በ84 ዓመታቸው በዚህ ሳምንት Sir Alexander Chapman Fergusonንን ተለዩ ። Learning from Masters ከግላስኮው ጃክ ስቴይን የስለጠና ጥበብን የተማሩት ሰው ፈርጉሰን አሁን በ3 ዓመት የምትበልጣቸው ውዷ ባለቤታቸውን አጥተዋል ። በውጤት በአሸናፊነቱ በማያባራ የድል ዘመን የዋንጫ ታሩኩ ዓለም አቀፍ ገናና ያደረጉት ክለባቸው ማንቸስተር ዩናይትድም እርሳቸውን በጡረታ ካጣ በኋላ ከውጤት ቁልቁለት አዙሪቱ መላቀቅ ተስኖት 12 ዓመታት አለፉ ። Super Sunday 12:30 አርሰናል ከሲቲ ተጠባቂው የመምህሩ እና ደቀ መዝሙሩ ፍጥጫ ከኤምሬትስ ? " ከአበይት ስፖርታዊ ጉዳዮች ጋር ከ4-6 ረፋድ አለን ብስራት ላይ ...
نمایش همه...
🎆 ድልድሉ ተጠናቋል!💥
نمایش همه...
ለ11 ዓመት የተናፈቀው የዶርቱሙንድ ዳንኪራ ሳይሳካ ቀረ ። በቢጫ ለባሹ ፍቅር የከነፉ የሲግናል ኢዱና ፓርክ የደጋፊ ክዋክብቶችም ከማይነጥፍ ድባብ ጋር ታምነው ሌት ተቀን የቆሙለት ክለባቸው ዛሬም ከዳቸው ። ቦሩሱያ ዶርቱሙንድ በእጁ የያዘውን ዕድል በዓለማችን ምርጡ ደጋፊው ፊት መጠቀም ተስኖት ቡንደስሊጋውን ለባቫራያኑ ሸለመ ። ባየር ሙኒክ ለ11 ተከታታይ ዓመት ሻምፒዮን ሆነ ። አድማጮች ይህ ቀድሞ የተፃፈ የሚመሥለው የጀርመን ቡንደስሊጋ ህይወት ዕጣ ፈንታ ነው ። በየውድድር ዓመቱ በጃምቦ ድራፍት ለሚቀልጠው የሙኒክ የመጨረሻ የሻምፒዮንነት ፌሽታ one man show ቲያትር ዘንድሮም እንደታመነ የቀጠለው የቡንደስሊጋው የባቫሪያኑ ቀይ ምንጣፍ የድል ዓለም ነው ።
نمایش همه...
በወሳኝ ሰዓት ዳገቱ ላይ ፊያቶ የጨረሰው ደካማው ዩናይትድ ! ከመድፉ ኮኮቦች ተደናቂ የኒውካስል ድል በሃላ ከሴንት ጄምስ ፓርክ የወጣለትን ሎተሪ ያልተጠቀመው ደካማው ዩናይትድ ከምስራቅ ለንደን ዌስትሃም ! አሁን ጥያቄው ከባከነው አጋጣሚ በላይ በውድድር ጫና የለዘበው ቅርፅ አልባው የቴንሃግ ዩናይትድ ከtop four ምኞቱ ጋር አሁንም ከእጁ ያልወጣው የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታውን ለማስጠበቅ በወሳኝ የውድድር ምዕራፍ ዳገቱ ላይ ፊያቶ ጨርሶ በፅኑ ካንቀላፋው ስብስቡ ጋር ቀሪ ጨዋታዎችን እንዴት ይፈፅማል ሆኗል ። የማግፓይሶች ሽንፈት የዩናይትድ የቀጠለ መንሸራተት ለመርሲሳይዱ ገናና ሊቨርፑል ታላቅ የtop four ተስፋ ይዞ መጥቷል ።
نمایش همه...
Top City ተርምኔተር 35 ደርሷል ። የአንዲ ኮል አለን ሺረር 34 የፕሪሚየር ሊግ የጎል ሪከርድ ተሰብሯል ። የጎል ማሽኑ በሲዝኑ የ51 ጎል Count Down መድረሻ ፍፃሜው አይታወቅም ። ሲቲም ወደ መሪነት መጥቷል ። የኢትሃዱ ቢሊየነር በጋርዲዮላ ዘመን 1000 ሺህ ጎል አስቆጥሯል ። ዕሮብ ሽንፈት ካባው የሆነው ሚሰተር ቼልሲ ከMister loser ፍራንክ ላምፓርድ ጋር ቁልቁለቱን ቀጥሏል ። Act Like Roman በሰመያዊ ቀለም እንደ አብራሃሞቪች ሊተውኑ የሞከሩት አሜሪካዊ ቢሊየነር ቦኽሊ በቢሊዮን ፓውንድ ባፈሰሱበት ዓመት ቼልሲን ይዘው ከMister loser እንዳይወርዱ ተሰግቷል ። የአርሰናል ወጣቶች ተደናቂ ሲዝንም የNorth london forever መድፉ መንደር በሻምፒዮንነት ትውስታ የታጀበ ውጤታማ ጉዞ አድናቆት ውዳሴ ጀምሯል ። ዩናይትድ ነገ ምሽት 4:00 በዴዘርቢው መልከኛ ቡድን ብራይተን ይፈተናል ። ጨዋታው ለቀያይ ሰይጣናቱ ለtop four ዐይን የበዛበት የውጤት ዓለማ ወሳኝ ነው ። በገናናው ሊግ Big sam ጉደኛው ሊድስ ደርሰዋል ። የዮርክሻየሩ ዝነኛ ሊድስን ሊያድኑ የወራጅ ቀጠና ኤክስፐርቱ Big sam ጋርዲዮላ ብትሉ ክሎፕ ወይ አርቴታ ከሁሉም በእግር ኳስ ዕውቀቴ እና ልምዴ እኔ አበልጣለሁ አንዳቸውም አጠገቤ አይደርሱም ሲሉ በአነጋጋሪ አስተያየታቸው ስራቸውን ጀምረዋል ። በ4 ቀሪ ጨዋታ Big sam ሊድስን ከመውረድ ያተርፉ ይሆን ? ከእኔ አይበልጥም ካሉት የጋርዲዮላ Top city በመፋለም ጉደኛው ሳም አላርዳይስ ስራቸውን ቅዳሜ በኢትሃድ ይጀምራሉ ።
نمایش همه...