cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ይህ የቤላ ፈለገ ሰላም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ፤ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት ገፅ ነው ። በዚህ ገፅ ፦ 👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ መልዕክቶች ፣ ምክሮች 👉 መዝሙሮች ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች 👉 ወቅታዊ የቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤት ጉዳዮች 👉የሰ/ት/ቤት መልዕክቶች ፣ ማስታወቂያዎች ይቀርቡበታል። ቤተ መጻሕፍትና ሚዲያ ክፍል ለመቀላቀል ➠ @felegeselam1

نمایش بیشتر
Advertising posts
588مشترکین
-124 ساعت
+17 روز
+1730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱 እንኳን ለዘብዴዎስ ልጅ ለወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ወንድም ለሆነ፤ የእንስሳና የአራዊት የሰማይ ወፎችንም ቋንቋ ያውቅ ለነበረ ለሐዋርያው ለቅዱስ ያዕቆብ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። 🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱🍀🌱 ምንጭ ውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት 👇ሙሉውን ለማንበብ👇 https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-18
نمایش همه...
አባቱም እንዲህ አለው፡- “ልጄ ሆይ፣ በየቀኑ ልክ የምትተኛበትን ቦታ ያህል አርም፣ ከዚያም ስራህ በየቀኑ እያደገ ስለሚሄድ አትዳከምም” አለው፡፡ ይህን ሲሰማ እንዲሁ አደረገ፤ በጥቂት ጊዜ ውስጥም መሬቱ ከአረሙ ጸዳ፡፡ ወንድሜ ሆይ ለአንተም እንዲሁ ነው፤ መሳነፍንና ተስፋ መቁረጥን ትተህ የምትችለውን ትንሽ ነገር ስራ ከዚያም እግዚአብሔር በቸርነቱ ወደ ቀደመው ሕይወትህ ይመልስሃል” በዚህ ምክር ያ ወንድም ተጽናንቶ ራሱን በማበርታት አረጋዊው እንደመከረው አደረገ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም በክርስቶስ ቸርነት ሰላምን አገኘ፡፡ “ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልኻል ይላል እንግዲህ እንደ ጥበበኛዎች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና፥ዘመኑን ዋጁ “ ኤፌ 5፣14~16 ምክረ አበው ፪ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ዮሐንስ ሐጺር(አጭሩ) በውስጡ ያለውን ስሜት እግዚአብሔር ሙሉ ለሙሉ ከእርሱ እንዲያጠፋለትና ነጻ ሰው እንዲያደርገው ይጸልያል። ከዚህ በኋላ ወደ አባ ጴሜን መጥቶ “ራሴን ያለ ምንም ጠላት በሰላም ውስጥ አግኝቼዋለሁ!” ብሎ ይነግረዋል። አባ ጴሜንም “ሂድና እግዚአብሔር በአንተ ላይ ውጊያ እንዲከፈትብህ ያደርግ ዘንድ አነሳሳው። ከዚህ በኋላ ሊኖሩህ የሚገቡትን የመከራ ጊዜና ራስን ማዋረድ ለማግኘት ሞክር። ምክንያቱም ነፍስ ዕድገት የምታመጣው በውጊያ ነው።” ብሎ ያሰናብተዋል። ከዚህ በኋላ ውጊያው ሲመጣበት እግዚአብሔር ውጊያውን ከእርሱ እንዳይወስድበት በጸሎት “ጌታዬ ሆይ! ከፈተና እንድወጣ አንተ ብርታቱን ስጠኝ!” ብሎ ጠየቀ። ምክረ አበው ፪ አንድ አረጋዊ ክፉ ሀሳብን በተመለከተ እንዲህ አለ፡- “ምግብና መጠጥ በሚሸጥባቸው የገበያ ቦታዎች ፊት እንደሚያልፍና ምግቡ ሲጠበስና ሲዘጋጅ ሽታው ወደ እርሱ እንደሚመጣና እንደሚሸተው ሰው ሁን፡፡ ሽታው ደስ ካሰኘውና ውስጡ ከተቀቀለው ለመብላት ወደ ውስጥ ይገባል፤ ካልሆነ ግን ሲያልፍ ብቻ ይሸተዋል፤ እርሱ ግን መንገዱን ይቀጥላል፤ አልፎትም ይሄዳል፡ ፡ ለአንተም እንዲሁ ነው፤ መጥፎውን ሽታ አትደሰትበት፤ ወደ ውስጥህም አትቀበለው፡፡ ተነስና “የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እርዳኝ” ብለህ ጸልይ፡፡ ለሌሎች ፈተናዎችም እንዲሁ አድርግ፡፡ የሰውነት ስሜቶቻችንን ነቅለን ልናጠፋቸው ሳይሆን ልንቋቋማቸውና ልንቆጣጠራቸው ይገባናል፡፡ የአንድ ታላቅ አባት ረድእ በፍትወት ጾር ተጠቃ፡፡ አረጋዊውም በጸሎቱ ጊዜ ይህን ሁኔታ አየና “ከዚህ ውጊያ እንዲገላግልህ እግዚአብሔርን እንድጠይቅልህ ትፈልጋለህ?” አለው፡፡ ያም ወንድም “አባ፣ እየተሰቃየሁ እንደሆነ ግልፅ ነው፣ ነገር ግን ይህ መፈተኔ በእኔ ውስጥ ፍሬ እያፈራ አያለሁ፤ ስለዚህ እችለው ዘንድ ጽናቱን እንዲሰጠኝ እግዚአብሔርን ለምንልኝ” አለው፡፡ አባቱም “አንተ በፍፁምነት እንደበለጥከኝ ዛሬ ተገነዘብኩ” አለው፡፡
نمایش همه...
፫. ልዩ ልዩ ምክረ አበው ፩ አንድ ወንድም በፈተና ወደቀና ከመበሳጨቱ የተነሳ የምንኩስና ተግባሩን አቋረጠ፡፡ እንደገና ሊመለስና ሊጀምር ቢፈልግም በውስጡ ያለው ትካዜና ቀቢፀ ተስፋ እንዲያ ለማድረግ አላስቻለውም፡፡ በውስጡም እንዲህ ሲል አሰበ፡- “ቀድሞ ወደ ነበርኩበት ሕይወት የምመለሰው መቼ ይሆን?” በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ አንድን አረጋዊ ለመጎብኘት ሄደና ያለበትን ሁኔታ ነገረው፡፡ አረጋዊው ይህ ወንድም ያለበትን የብስጭት ሕይወት በተረዳ ጊዜ የሚከተለውን ምሳሌ ነገረው፡- “አንድ ሰው የእርሻ መሬት ነበረው፣ ሆኖም ሳያርሰው ለብዙ ጊዜ ስለተወው በስንፍናው ምክንያት መሬቱ ጠፍ ሆኖ በአረምና በአቃቅማ ተመላ፡፡ ከጊዜ በኋላ ሊያርሰውና ሊዘራበት ፈለገና ልጁን “ሂድና ከዚያ መሬት ላይ አረሙን ንቀል” አለው፡፡ ልጁ ሊያርም ሲሄደድ የአረሙንና የአቃቅማውን ብዛት ተመልክቶ “ይኽን ሁሉ አረም እስከ መቼ ድረስ አርሜ እዘልቀዋለሁ?” በማለት ተስፋ ቆርጦ ዝም ብሎ እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ ይውልና ያድር ጀመር፡፡ “ለብዙ ቀናት እንዲህ ምንም ሳይሰራ ከቆየ በኋላ አባቱ ልጁ የሰራውን ለማየት ሲመጣ ምንም ነገር ሳይጀምር አገኘው፡፡ እርሱም “እስካሁን ምንም ነገር ያልሰራኸው ለምንድን ነው?” ሲለው “አባቴ፣ ልጀምር ስል የአረሙንና በመሬ ላይ የበቀለውን ልዩ ልዩ ነገር ባየሁ ጊዜ ይኽንስ መቼም ላልጨርሰው ባልጀምረው ይሻለኛል ብዬ ሃሳቤን ለወጥኩና ውስጤ ተዳክሞ ዝም ብዬ ቁጭ አልሁ” አለው፡፡
نمایش همه...
نمایش همه...
ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፲፭

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

መምህር ሆይ! መሆንህን አውቆ እውነተኛ ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ›› ስትለው ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው… የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይቻለው›› ምሥጢሩ ባይገባው ‹‹ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው›› ብለህ አስረዳኸው፡፡ ‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› ብሎ ኒቆዲሞስ ቢጠይቅህ ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም?.... ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤… የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡›› ብለህ አስተማርከው፡፡ አሁንስ ገባው፤ እውነቱንም አውቆ ጌታውን ዘመናት አልፈው ሲደርስ ጠብቆ ተራውን ቢኖርም ተብሎ መምህር፣ በሌላ ሕግ ተደብቆ ያለ አንተ ሲኖር ከአይሁድ ተደባልቆ አሁን ግን ሰጠኸው የእውነት ሕይወት በመስቀል ላይ ገልጸህ ፍጹም አፍቅሮት ክብርንም አገኘ በአንተ ስቅለት ገንዞ እንዲቀብርህ በዓርብ ዕለት!
نمایش همه...
نمایش همه...
ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፲፫

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያዘጋጀው የምክክር መድረክ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል። ሚያዝያ 12/ 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ / አዲስ አበባ) "ዘመኑን እንዋጅ ፤ የቤተክርስቲያን የመሬት ሀብትን ከብክነት ማዳን የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የምክክር መድረኩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የአፋርና ምዕራብ ሀረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የሀገረስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ በተገኙበት በጸሎት ተከፍቷል። በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ "ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው።” — ዘፍጥረት 26፥12" ን መነሻ በማድረግ የመክፈቻ ንግግር እና የእንኳን ደኅና መጣችሁ ንግግር አስተላልፈዋል። የሀገረ ስብከቱ የዕቅድና ልማት ክፍል ኃላፊ ባስተላለፉት መልእክት "ቤተክርስቲያን ያላትን መሬት በአግባቡ በመጠቀም እና በማልማት ካሉባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንድትላቀቅ ማድረግ ዋነኛ ዓላማችን ስለሆነ ሁላችንም በጋራ ሆነን በመሥራት ቤተክርስቲያንን ማልማት ለነገ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል" በማለት አስተላልፈዋል ፤ በመቀጠልም የተደረጉ ጥናታዊ ጽሑፎች ለምክክር መድረኩ ቀርበዋል። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የክፍላተ ከተማ ኃላፊዎች ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ምክትል ሊቃነ መናብርት የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ናቸው። © Tewahedo Media Center
نمایش همه...
نمایش همه...
ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፲፪

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን