cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

نمایش بیشتر
Advertising posts
60 190مشترکین
-1924 ساعت
+377 روز
+3 70330 روز
آرشیو پست ها
እስካሁን ስንዳስስ የቆየነው ይህ የ1966ቱ የሙስሊሞች መብት የማስከበር ሰልፍ ለህዝበ ሙስሊሙ የተለያዩ ጥቅሞችን ማስገኘት ችሏል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ መነቃቃትን ከመፍጠሩ በተጨማሪ ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር በጋራ አጀንዳ ላይ አብረው መቆም እንደሚችሉ በማሳየት ፈር ቀዳጅ ነበር። ስልጣን ላይ የሚወጣው ቀጣዩ መንግስትም የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄዎችንና ብዛቱን እንዲረዳ ከማድረጉ በተጨማሪም የሚቋቋመው መንግስትም ሐይማኖታዊ ያልሆነ፣ ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተናግድና ዓለማዊ መንግስት (Secular State) መሆን እንዳለበት አመላክቷል። የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ሌላ ሽፋን ቢሰጠውም በዋናነት እስልምናን እና ሙስሊሞችን ለማዳከም የተቋቋመውን የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ሚኒስቴር መስሪያ ቤትን ቀጣዩ መንግስት ፀረ-ኢስላም ዓላማውንና ድብቅ ተግባሩን በመቀልበስ ‹‹ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር›› በሚል እንደገና እንዲቋቋም አግዟል። በንቅናቄው ማግስት ስልጣን ላይ የወጣው የደርግ መንግስት የእምነት እኩልነትን ሕግ እንዲያውጅ በማድረጉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ባህሉንና እምነቱን ሳይሸማቀቅ እንደ ሌሎች ዜጐች እንዲተገብር አስችሎታል። ከዚህ በተጨማሪም በንቅናቄው ንቃተ ሕሊናቸውን ያዳበሩ የተለያዩ ግለሰቦች ሰልፉ ያነሳቸውን ጥያቄዎች በማንሳት ሕዝቡ ይበልጥ ተነቃቅቶ ለመብቱ እንዲታገል እንዲያነሳሱ አስችሏቸዋል። ለአብነትም በአዲስ አበባ ከተማ ከተክለሃይማኖት በታች በስልጤ ሰፈር የሚገኘው የሐጂ አሕመድ መሒሊ መስጊድ ከሰልፉ ከሁለት ዓመታት በኋላ መስጊዱ የተመሰረተበትን 27ኛ ዓመት በነሐሴ 9 ቀን 1968 ዓ.ል ባከበረበት ጊዜ የመስጊዱ ኮሚቴ አመራር ያደረገውን ንግግር እንመልከት። በዕለቱ የመስጊዱ ኮሚቴ በጽሁፍ ያደረገው ንግግር የወቅቱን የንቃተ ሕሊና ደረጃ እንድንረዳ ዘንድ ስለሰልፉና ስለሙስሊሙ ጥያቄ የሚያወሳውን እንይ፡- ‹‹ከዚህ በቀር ትዝታው ከማይጠፋንና እያንዳንዱ ምእመናን ከፍተኛ በሆነ አንክሮዋዊ ስሜት ሲያስታውሰው የሚኖር የእስላሙ ህብረተሰብ ለሀይማኖቱ እኩልነት ያደረገው ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ጭቁኖች የጋራ ጠላታቸውን ለመቋቋም እንዲተባበሩ የሕብረተሰብ ዕድገት ሕግ ነውና አመፁ በሥርዓቱ ላይ ነውና ተራማጅ የሆኑ የህብረተሰብ አባሎችና ክርስቲያን ወንድሞችም በዚህ ሰልፍ መካፈላቸው ሌላው ትዝታ ነበር። በሰልፉ ወቅት ከቀረቡት መፈክሮች ውስጥ ‹ሃይማኖት ከመንግስት አስተዳደር ይገንጠል›፣ ‹በዓላችን በብሔራዊ ደረጃ ይከበር›፣ ‹እስልምና ወንጀል አይደለም›፣ ‹የሃይማኖት እኩልነት ይኑር›፣ የሚሉ ይገኙበታል። በዚያን በወቅት ነበር የአክሊሉ ካቢኔ አይንህን ላፈር የተባለው። በዚያን ጊዜ ነበር ጭቁኖች ቢተባበሩ አንድም ኃይልሊቋቋማቸው እንደማይችል የታወቀው። ያኔ ነበር ያንድን ሕብረተሰብ ስንኩል አስተዳደር የግለሰብ መለዋወጥ ሊለውጠው እንደማይችል ያሳወቀው። ከዚያን በኋላ ነበር እኩልነት እስካልተመሠረተ ድረስ ሰላም እንደማይኖር፣ ያንዲት ሴኮንድ እፎይታ እንደሌለ፣ ጭቁኑ ከትግሉ የተማረበት፣ በአንፃሩም ለአድርባዮች፣ ለባንዳዎችና፣ ለአሽቃባጮች፣ ለመሳሰሉትም ሁሉ የትግል ሚናውን፣ የእኩልነት መርሆውን፣ የአንድነት አርማውን፣ የታሪክ ባለ አደራነቱን ያስተማረበት ወቅት። ከዚያ በኋላ የእስላሙ ሕብረተሰብ ካቀረባቸው ባለአሥራ ሦስት ነጥብ ጥያቄዎች ውስጥ መልስ ያገኘው አንዱ ብቻ ነው። ይኸውም የእስልምና በዓል በብሔራዊ ደረጃ በማክበሩ ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበት እያንዳንዱ ምእመናን መገንዘብ ሲኖርበት ይህንንም የሚወሰነው የራሱ ንቃትና የአንድነት ክንዱ ነው።›› (ዐብዱልፈታህ ዐብደላ፣ የአዲስ አበባ መስጂዶች ታሪክ፣ ቁጥር 2፣ ግንቦት 2002፣ አማን ኘሮሞሽን፣ ድሬ ማተሚያ ቤት፣ ገጽ 21) ይህ የመስጊድ ኮሚቴ አመራር ንግግር የወቅቱን የንቃት ደረጃ፣ንቅናቄው ሁሉንም ጥያቄዎች ሊያስመልስ አለመቻሉንና የሰልፉን ትዝታ በማንሳት ሙስሊሞች የተቀሩትንም ጥያቄዎቻቸውን ማስመለስ የሚችሉት በተባበረ ትግላቸው እንደሆነ ለማስገንዘብ እንደነበረ ያስረዳናል። ጥያቄዎቹ በሙሉ ሊመለሱ ላለመቻላቸው በርካታ ምክንያቶችን መዘርዘር እንችላለን። በዋናነት የትግሉ አለመቀጠል፣ የሙስሊሙ በትንሽ ነገር ተደስቶ የመዘናጋት ባህሪና መብቱን ሌሎች እንዲሰጡት አልያም ታግለው እንዲያስከብሩለት ከመፈለግ ዝንባሌ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ያለመቻሉ ችግር ተጠቃሽ ናቸው። አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስታቸው በሕዝባዊ ማዕበል እየተንገዳገደ በነበረበት ጊዜም ሆነ ሥርዓቱ ከተወገደ በኋላ ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደሌላው ሁሉ ራሱ ጥያቄዎቹን ለማስመለስ ተደራጅቶ ከመታገል ይልቅ የመረጠው አዲሱ መንግስት መብቱን እንዲሰጠው እየጠየቀ በተስፋ መቀጠልን ነበር። በርግጥ ያ ንቅናቄ ጠንካራ፣ ማደራጀት የሚችል፣ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው እና ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ አመራር ቢያገኝ ኖሮ ሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄውን ከማስመለስ አልፎ በሀገሪቱ ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ፣ ተደማጭ እና የፖለቲካ ኃይልያለው ህብረተሰብ ሊያደርገው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች ነበሩ። ከነዚህ መካከል ሕዝበ ሙስሊሙ ከንግድ መስክ ውጭ ሀገራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የተሳትፎ ልምድ ማጣት፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ አግላይ ፖሊሲ የተነሳ በሁሉም ዘርፍ በቂ ሊባል የሚችል ልሂቃን (Elites) አለማፍራት እና የትምህርት እድል ያገኙትም ብዙዎቹ ተመልሰው ወደ ንግዱ መስክ መመለሳቸውን በዋናነት መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ የተነሳ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በጦር ሠራዊቱ እና በሌሎች ወሳኝ መስኮች የሙስሊሙ ቁጥር እጅግ በጣም አናሳ ከመሆኑ የተነሳ ከግምት የሚገባ አልነበረም። በአዲሱ የደርግ መንግስትም ወሳኝ ቦታዎችን የያዙት አፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት ውስጥ በተለያዩ መስክ እድል ያገኙት ነበሩ። ለምሳሌ ከጦሩ የተለያየ ክፍለ ጦር ተወጣጥቶ ከፍተኛውን የሀገሪቱ ሥልጣን ከዚያው የደርግ ምክር ቤት አንድ መቶ ሀያ አባላት መካከል ሙስሊም አንዱ ብቻ ነበር። ይህ ግለሰብም ሆነ ኋላ ላይ በተለያየ የታችኛው እርከን ደርግን የተቀላቀሉ ጥቂት ሙስሊሞችም ቢሆኑ ሙስሊምነታቸው ከስም በዘለለ በእምነታቸው ሳይሸማቀቁ የወገኖቻቸውን አጀንዳ ለማንሳት የሚደፍሩ ነበሩ ለማለት ያስቸግራል።በመሆኑም የነርሱ በሥርዓቱ ውስጥ መታየት ለሙስሊሙ ያስገኘው ጥቅም ይህ ነው ብሎ ለማስቀመጥ ያዳግታል። በወቅቱ በሀገሪቱ በተፈጠረው መነቃቃት ምክንያት የተለያዩ አካላት የራሳቸውንና የወገናቸውን አጀንዳዎች በማንሳት ተደራጅተው በይፉም ሆነ በሕቡዕ ሲንቀሳቀሱ ሕዝበ ሙስሊሙ ግን የራሱን አጀንዳ ይዞ የሚታገልለት ለአዲሱ መንግስት አጋርም ሆነ ተቃዋሚ ድርጅትም ሆነ ፖርቲ አልነበረም። በወቅቱ እንደ መኢሶን ያሉት ገዢውን መንግስትከመቃወም ይልቅ አጋር ፓርቲ ሆነው ለተሻለ ለውጥ መሥራትን ሲመርጡ እንደ ኢህአፓ ያሉት ደግሞ ወታደራዊው መንግስት ከስልጣኑ ወርዶ ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም በሚል ተቃዋሚ ሆነው በሕቡዕ ይታገሉ ነበር። ከዚህ አንፃር የሙስሊሙ ለሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ከመሳተፍ ወደኋላ መቅረቱ ብቻ ሳይሆን እንቅስቃሴውም በሃይማኖትታዊ አጀንዳ ላይ እየተገደበ ሄደ። በወቅቱ ሙስሊሙ ከራሱ የእምነት ጥያቄ በተጨማሪ ‹‹መሬት ላራሹ››፣ ‹‹ሃይማኖት ከመንግስት አስተዳደር ይገንጠል››፣ ‹‹እኩልነት በተግባር ይተርጎም›› እና መሰል ጥያቄዎችን እንዳላነሳ ሁሉ ገፍቶ ባለመሄዱ እና ሂደቱ ሁሉ ዳግም
نمایش همه...
👍 35
በመስጊድ ብቻ በመወሰኑ ከበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ወደ ኋላ ተመለሰ። በርግጥ እውነታውን ካየነው የሀገሪቱ አጠቃላይ ችግሮች ሳይቀረፉ የሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ብቻውን ተለይቶ ሊመለስ የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ በመረዳት በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችም ላይ ከሌሎች ዜጐች ጋር በጋራ መታገል ነበረባቸው። የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደተጨቆኑ፣ እንደተገፉና በስርዓቱ ውስጥ ተገቢ መብታቸው እንዳልተከበረ በማመናቸው ተደራጅተው ሲታገሉ ለዘመናት ሲጨቆን የነበረው፣ መብቶቹ ያልተከበሩለት እና ከብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ወደ ኋላ የቀረው ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበርና እኩልነቱን በሁሉም ዘርፍ በተግባር ለማረጋገጥ የሚታገልለት አካል መፍጠር አልቻለም።በጣት የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በወቅቱ ከተቃዋሚ ጐራ ተሰልፈው የነበሩ ቢሆንም የሙስሊሙን አጀንዳዎች የፖርቲዎቹ አጀንዳ ማድረግ አልቻሉም። ቁጥሩ ከሌሎች አንፃር እጅግ አናሳ ቢሆንም ከተቃዋሚዎቹ ይልቅ በደርግ ውስጥ በመጠኑ የተሻለ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ነበሩ። ይህ የሆነው ተቃዋሚነት ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ዋጋ በመክፈል ለአጀንዳቸው ለመቆም የተዘጋጁ ባለመሆናቸው ሳቢያም ሊሆን ይችላል። በነኝህና መሰል ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው መነቃቃት እየቀዘቀዘ የሚገባውን ያህል ውጤት ሳያስመዘግብ ቀርቷል። ይህ ሊሆን የቻለው የዓለም ታሪክ እንደሚያስገነዝበው የትኛውም ሕዝብ መብቱንና እኩልነትን በልመናና ተማጽኖ ሊያገኝ የቻለበት ሁኔታ ያልታየ በመሆኑ ነው። ሂደቱን ስንመለከት የ1966ቱ የሙስሊሙ ንቅናቄ መሪዎች የላቀ ባይሆንም በተግባር ግን ካነሷቸው 13 የመብት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሹ የነበሩበት በዋናነት መንግስትን በመማፀን፣ በመለመንና ምላሽ እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕዝበ ሙስሊሙ ልሂቃንን በማፍራት እና በማብቃት ሥራ ላይ በቀጣይነት ሲንቀሳቀሱ አናይም። እነኝህን በመተግበር እንደሌሎቹ የመብት አስከባሪ ታጋዮች ሁሉ በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ጉዳዮች ውስጥ በተለይም በፖለቲካው በመሳተፍ ትግል ቢያካሂዱ ኖሮ የተሻለ ለውጥን ማምጣት በቻሉ ነበር። ምክንያቱም በሀገሩ ፖለቲካ ላይ እኩል ተሳታፊ ያልሆነ አካል ሁሌም በሀገሪቱ እጣፈንታ ላይ እኩል የመወሰን እድል አይኖረውም። ይህ ሲሆን ደግሞ በሀገሩ እጣፈንታ ላይ ሚናው አነሳ ከመሆኑም በተጨማሪ የራሱ እጣፈንታ ጭምር በሌሎች መዳፍ ስር ይወድቃል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ የቱንም ያህል ቅንና ፍትሓዊ ጥያቄዎች ቢኖሩትም እኩል ተጠቃሚ የመሆን ዕድሉ ሩቅ ነው። በርግጥ የደርግ መንግስት የአፄ ኃይለ ሥላሴን ሥርዓት በማስወገድ ለኢስላም እና ለሙስሊሞች በብሔራዊ ደረጃ እውቅና በመስጠቱ አንፃር ብቻ ስናየው ሥርዓቱ ለሙስሊሞች ባለውለታ ነበር። ይሁን እንጂ በቀድሞ ሥርዓቶች የማግለል ፖሊሲ ምክንያት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሀገሪቷ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት በመገለሉ ምክንያት የተፈጠረበትን በደልና በብዙ መልኩ ወደ ኋላ የመቅረቱን እውነታ የሚያካክስ አዎንታዊ እርምጃዎችን (Affirmative Actions) ባለመወሰዱ ልዩነቱ በብዙ መልኩ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም በደርግ ስርአት ውስጥ አብዛኞቹ የመንግስት አስተዳደር፣ የፖለቲካ ተቋማት እና በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ እንደሆነ ዘልቋል። ያም ሆነ ይህ በደርግ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመናት ሕዝበ ሙስሊሙ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጣት ሊቆጠሩ የሚችሉ አንኳር ጥቅሞችን አግኝቷል። በዝርዝር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትና በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ ሲደርሱ የነበሩትን ጭቆናዎች አብዛኛዎቹን ያስወገደው የደርግ መንግስት ነበር። የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች መሪ ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጉባኤ (መጅሊስ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው በዚሁ በደርግ ዘመን በመጋቢት 4 ቀን 1968 ዓ/ል ነበር። ህዝበ ሙስሊሙም በካድሬዎች ሳይሆን እንደነ ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ባሉና ቁርኣንን ወደ አማርኛ በተረጎሙ ስመጥር ሊቃውንት እንዲመራ የደርግ መንግስት ፈቅዷል። የሃይማኖት እኩልነትን እሳቤ በሕዝቡ ውስጥ ለማስረፅም ጥሯል። ኋላ ላይም ሥርዓቱ ከተከተለው የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም ፍልስፍና አንፃር ሁሉንም ሃይማኖት በጥርጣሬና በስጋት ቢያይም እንደ መንግስት ሙስሊሙን ብቻ ነጥሎ የሥርዓቱ እና የሀገሪቷ ስጋት አድርጎ ባለመፈረጁና የማግለል ስልትን ባለመከተሉ ለሙስሊሙ የደርግ ሥርዓት ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት በእጅጉ የተሻለ መሆኑን አሳይቷል። አክሱምን ጨምሮ በአንዳንድ ሰሜናዊው የሀገሪቷ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊሞች ሕጋዊ የሙስሊሞች መካነ መቃብር እንኳን ማግኘት የቻሉት በአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ውድቀት ማግስት ነበር። በነኝህና በሌሎች በርካታ ቆራጥ እርምጃዎቹ የደርግ መንግስት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት የአገዛዝ ዘመኑ ለሙስሊሞች ውለታ ቢውልም ኋላ ላይ ግን በሙስሊሙም ሆነ በሌሎች በርካታ ጉዳዮች የሚያስወቅሱ በርካታ ተግባራትን ፈጽሟል። ይህን ርዕስ ስናጠቃልልም ያኔ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ሙስሊሞች የተቻለንን ያህል ስማቸውን መጥቀስ ያሻል ብለን ስላሰብን በዚሁ መሰረት ዝርዝራቸውን እነሆ ብለናል፡- እነ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱረሕማን፣ ዐብዱ በሽር፣ ዐብዱ አደም፣ ሐጂ ሻሚል ኑርሰቦ፣ ጀማል ዐሊ፣ ዐብደላ ሐሰን፣ ዐብደላ ዐብዱልቃዲር፣ አሕመድ ሸኽ አወል፣ ሲራጅ ሱለይማን፣ አሕመዲን ዩሱፍ፣ ዐብዱሶመድ ሰመረዲን፣ ሰዒድ ዩሱፍ፣ አሕመድ ዋሴ፣ ሲቲሚያ ሙሐመድ /ሴት/፣ አቶ ዐሊ አሕመድ፣ አቡበክር ሱለይማን፣ ሙሐመድ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ፣ ዒዘዲን ሙሐመድ /የአል ቁድስ አዘጋጅ የነበረው/፣ በድሩ ሡልጣን /የቃጥባሬ ሸኽ ልጅ/፣ አባቢያ አባጆቢር፣ አቶ አሕመድ ሰዒድ ዐሊ፣ አቶ ሙሐመድ አሕመድ ሸሪፍ እና ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ወዘተ ለሙስሊሙ መብት መከበር ከታገሉት መካከል ይገኙበታል። በሕይወት የሌሉትን አላህ ይማራቸው! ያሉትንም ያቆያቸው! በወቅቱ የታገሉት ከላይ የተጠቀሱት ብቻ ናቸው ማለት አይደለም። ሥማቸው እዚህ ያልተጠቀሱትም በርካቶች አሉ። ***************************** ደካማ ይልቃል ኃይለኛ ሲዋረድ ቡቃያ ይበቅላል ያፈራው ሲታጨድ ሰፊው ይቀንሳል ጠባቡ ሲስፋፋ ጨረቃ ታምራለች ፀሐይ ስትጠፋ ከንቅልፉ ሲነቃ ደግሞ የፈዘዘ የሞቀው ይሄዳል እየቀዘቀዘ እንደሕልም ታይቶ ያልፋል እንደጥላ ለዚህ ዓለም ነገር ምንም የለው መላ መታወቅ መረሳት ማርጀት መታደስ ይህ ሁሉ ልማድ ነው አይደለም አዲስ፡፡ (ዶ/ር ከበደ ሚካኤል)
نمایش همه...
99👍 63
"አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ይህ ጥያቄ ያንተ አይደለም ወይ?" ክፍል 7 (የመጨረሻው ክፍል) 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የትግሉ ውጤት 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 በአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ላይ ሕዝባዊ የተቃውሞ ማዕበል ተጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ሥርዓቱን ይፈራ የነበረው ሁሉ በድፍረት ለመብቱ መነቃነቅ ቀጠለ፡፡ ይህ እየሆነ ባለበት ጊዜ እንኳ ንጉሡ ሕዝቡ ይህን ማድረግ መብቱ እንደሆነ አምነው ተቀብለው ችግሩን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ሕዝቡን በንቀት ይመለከቱ ነበር፡፡ ሕዝቡ ለመብቱ መታገሉን እንደመባለግ የቆጠሩት አፄ ኃይለ ሥላሴ እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር፡- ‹‹በርግጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ጊዜ ለከቱን መክፈት ሲጀምር ባቄላ የቋጠረ ስልቻ ቁልቁል ዘቅዝቆ መቋጠሪያውን መፍታት እንደማለት ስለሆነ መናገሩን አያቆምም፡፡ ሕዝቡ ከልክ በላይ እንደባለገ ይታያል፡፡›› (ኮለኔል ቃለ ክርስቶስ ዓባይ፣ የ1953ቱ የመንግስት ግልበጣ ሙከራና ከ1908-1966 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ሂደት፣ የመጀመሪያ ዕትም፣ ነሐሴ 1997፣ አዲስ አበባ፣ ገጽ 399) ሕዝባዊው አመፅና ተቃውሞ ከየአቅጣጫው ተጠናክሮ ቀጠለ። ደርግም ሕዝቡ በከፊል ሥልጣኑን የነጠቀውን የአጼ ኃይለ ሥላሴን አስተዳደር ገርሥሶ ለመጣል የሙስሊሙ ሰልፍም አጋዥ ሆኖታል። የሕዝቡ ጸረ-ኃይለ ሥላሴ አቋም የልብ ልብ ሰጠው። ሚያዚያ 18 ቀን 1966 ዓ.ል ደርግ ‹‹አገርንና ሕዝብን በድለዋል›› ያላቸውን የአፄ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናትን ከያሉበት እየለቀመ በቁጥጥር ሥር አዋለ። በሐምሌ 15 ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስተር እንዳልካቸው በደርግ ከሥልጣኑ ተወገደ። ነሐሴ 15 ቀን 1966 ዓ.ል የዙፋን ችሎት፣ የዘውድ ምክር ቤት እና የፍርድ አጣሪ ጉባዔ እንዲፈርስ ተደረገ። በሲ.አይ.ኤ ባለሙያዎች አማካኝነት የሰለጠነውና የተቋቋመው የኃይለ ሥላሴ ‹‹ልዩ ኤታማዦር›› /የሥለላም ጭምር ነው/ ተጠሪነቱ ለመከላከያ ሚኒስትር እንዲሆን ተደረገ። ጳጉሜ 4 ቀን 1966 ቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ ከዙፋናቸው እንዲወርዱ በደርግ ተወሰነ። መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ል ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ አፄው ከሥልጣናቸው ተወገዱ። በቮልስ ዋገን መኪና ከቤተ መንግሥት ቅጥር ጊቢ ወደ 4ኛ ክፍለ ጦር ተወሰዱ። ተበዳዩ ሕዝብም እንደዚያ በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ከፍርሃት የተነሳ ይሰግድላቸው የነበረውን ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን በድፍረት ‹‹ይሰቀል! ሌባ! ይሰቀል! ሌባ!›› እያለ ሸኛው። ታሰሩም። (ዘነበ ፈለቀ፣ ነበር፣ ነሐሤ 2000፣ አዲስ አበባ፣ ገጽ 60-80) ታኅሳስ 14 ቀን 1967 በብሔራዊ ደረጃ ስለሚከበሩ በዓላት ዝርዝር መግለጫ ወጣ። የሙስሊሙ ትግል በከፊል ፍሬ ማፍራት ጀመረ። ኢስላማዊ በዓላትም ብሔራዊ በዓላት ሆነው ተቆጠሩ። ‹‹የሕዝብ በዓላት አዋጅ›› የተሰኘ አዋጅ ወጣ። ቀደም ብሎ በ1948 የወጣው አዋጅ ቁጥር ‹‹151/19481/15/9/1948 አ.151›› ተሻረ። በአዋጁ እውቅና ከተሰጣቸው አሥራ ሁለት በዓላት መካካል ሦስቱ የሙስሊሞች በዓላት ነበሩ። እነሱም ዒድ አል ፊጥር፣ ዒድ አል አድሃና የመውሊድ በዓላት ነበሩ። (የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ማኅደር ቁጥር 3432) ታኅሳስ 15 ቀን 1967 የዐረፋ /ዒደል አደሃ/ በዓል የሙስሊሙ የመጀመሪያው በዓል ሆኖ በብሔራዊ ደረጃ ተከበረ። ለአዲሱ መንግስት መመሪያነት ሕገ መንግስት ለማርቀቅ የሕገ-መንግሥት አርቃቂ ኮሚቴ ተቋቋመ። ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱረሕማን፣ ሐጂ ሱለይማን ወዘተ… አባል ሆኑ። በሐሳብ የሚረዷቸው የወጣት ምሁራን ኮሚቴ አቋቋሙ። ኮሚቴው የሌላን አገር ተሞክሮ ከታሪክ አኳያ፣ እንዲሁም ስለ ሕገ-መንግሥት እና ሃይማኖት ከቤተ-መጽሐፍት በማንበብ በሐሳብና በምክር ከበስተጀርባ ሆኖ ያግዛቸው ጀመር። ለስድስት ወራትም በዚሁ ሁኔታ ቀጠለ። ለክርስትና ብቻ እውቅና የሚሰጠው ሕገ-መንግሥትም ተሻረ። ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም የሙስሊሙ መብት መከበር ጀመረ። ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ለረጅም ጊዜ የታገሉለትና የደከሙበት ‹‹መጅሊሰል አዕላ›› (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባዔ) በ 1968 ተቋቋመ። የአፄው ሥርዓት በሕዝቦች አብዮት ተገርስሶ የደርግ መንግሥት ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ ሲረከብ በ1966 ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኑ አከተመ። የመንግሥትና ቤተ-ክህነት የጋብቻ ሰማንያ ተቀደደ። የሙስሊሙ በዓላት በራሱ በሙስሊሙ ትግል እውቅና አግኝተው ብሔራዊ በዓል ሆኑ። ‹‹በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች›› የሚለው አጠራር ‹‹ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች›› በሚል ተተካ። ከፊል የሕዝበ-ሙስሊሙ ጥያቄዎች በትግሉ ተረጋገጡ። ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ደረጃ የሙስሊሙ በዓል ተከበረ። በሙስሊሙ በዓልም እንደ ክርስትያኑ በዓል ሥራ ተዘጋ። ተማሪው ዒድን አክብሮ ዋለ። እንደ ከዚህ ቀደሙ በዒድ ቀን ፈተና መሰጠቱ አከተመ። የመጀመሪያው የደርግ ሊቀመንበር ጄኔራል ሚካኤል አማን አንዶም በዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ጉባዔ ላይ በሰጠው የፕሬስ መግለጫ የኢትዮጵያ ሙስሊም ኅብረተሰብ ከአጠቃላይ የአገሪቷ ሕዝብ ውስጥ 55 (ሐምሳ አምስት) በመቶ መሆኑን አምኖ ልዩ እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ይፋ ማድረጉን አዲስ ዘመን ጋዜጣ በመስከረም ስድስት 1967 እትሙ ማስፈሩን ሙሐመድ ዩሱፍ ያዕቁብ ‹‹የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመከራና የስቃይ ታሪክ›› በተሰኘው መጽሐፉ አስፍሯል። ያ ታሪካዊ ሰልፍ ሙስሊሙ አንገቱን ቀና ያደርግ ዘንድ አስችሎታል። ወኔውን አዳብሮለታል። ከሰልፉ በፊት አንድ ተራ ፖሊስ ሠላሳና ሐምሳ ሙስሊሞችን እንደከብት ነድቶ ያስር ነበር፤ ያ ሁሉ ቀረ። ዛሬ ላይ ላገኘነው ነጻነት ትልቁ ባለ ድርሻ ያኔ የታገሉት አባቶቻችን ናቸው። ይህ የሙስሊሙ የመብት ትግል የአንድ ጀንበር ብቻም አይደለም። የዘመናት ብሶትና በደል፣ እንዲሁም ማነቃቃት ውጤት ነበር። ምንም እንኳን በወቅቱ የተነሱት ጥያቄዎች ሙሉ ለሙሉ ባይመለሱም ክስተቱ ሙስሊሙ አንገቱን ቀና እንዲያደርግና ለመብቱ መታገል እንዳለበት እንዲያውቅ አድርጓል። ሙስሊም መሆን መዋረድን ያስከትል የነበረው ያኔ አክትሟል። መብትም በትግል እንጂ በልመና እንደማይገኝ አሳይቶ አልፏል።
نمایش همه...
👍 39 3
ት ሳያስመዘግብ ቀርቷል። ይህ ሊሆን የቻለው የዓለም ታሪክ እንደሚያስገነዝበው የትኛውም ሕዝብ መብቱንና እኩልነትን በልመናና ተማጽኖ ሊያገኝ የቻለበት ሁኔታ ያልታየ በመሆኑ ነው። ሂደቱን ስንመለከት የ1966ቱ የሙስሊሙ ንቅናቄ መሪዎች የላቀ ባይሆንም በተግባር ግን ካነሷቸው 13 የመብት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሹ የነበሩበት በዋናነት መንግስትን በመማፀን፣ በመለመንና ምላሽ እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕዝበ ሙስሊሙ ልሂቃንን በማፍራት እና በማብቃት ሥራ ላይ በቀጣይነት ሲንቀሳቀሱ አናይም። እነኝህን በመተግበር እንደሌሎቹ የመብት አስከባሪ ታጋዮች ሁሉ በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ጉዳዮች ውስጥ በተለይም በፖለቲካው በመሳተፍ ትግል ቢያካሂዱ ኖሮ የተሻለ ለውጥን ማምጣት በቻሉ ነበር። ምክንያቱም በሀገሩ ፖለቲካ ላይ እኩል ተሳታፊ ያልሆነ አካል ሁሌም በሀገሪቱ እጣፈንታ ላይ እኩል የመወሰን እድል አይኖረውም። ይህ ሲሆን ደግሞ በሀገሩ እጣፈንታ ላይ ሚናው አነሳ ከመሆኑም በተጨማሪ የራሱ እጣፈንታ ጭምር በሌሎች መዳፍ ስር ይወድቃል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ የቱንም ያህል ቅንና ፍትሓዊ ጥያቄዎች ቢኖሩትም እኩል ተጠቃሚ የመሆን ዕድሉ ሩቅ ነው። በርግጥ የደርግ መንግስት የአፄ ኃይለ ሥላሴን ሥርዓት በማስወገድ ለኢስላም እና ለሙስሊሞች በብሔራዊ ደረጃ እውቅና በመስጠቱ አንፃር ብቻ ስናየው ሥርዓቱ ለሙስሊሞች ባለውለታ ነበር። ይሁን እንጂ በቀድሞ ሥርዓቶች የማግለል ፖሊሲ ምክንያት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሀገሪቷ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት በመገለሉ ምክንያት የተፈጠረበትን በደልና በብዙ መልኩ ወደ ኋላ የመቅረቱን እውነታ የሚያካክስ አዎንታዊ እርምጃዎችን (Affirmative Actions) ባለመወሰዱ ልዩነቱ በብዙ መልኩ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም በደርግ ስርአት ውስጥ አብዛኞቹ የመንግስት አስተዳደር፣ የፖለቲካ ተቋማት እና በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ እንደሆነ ዘልቋል። ያም ሆነ ይህ በደርግ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመናት ሕዝበ ሙስሊሙ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጣት ሊቆጠሩ የሚችሉ አንኳር ጥቅሞችን አግኝቷል። በዝርዝር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትና በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ ሲደርሱ የነበሩትን ጭቆናዎች አብዛኛዎቹን ያስወገደው የደርግ መንግስት ነበር። የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች መሪ ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጉባኤ (መጅሊስ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው በዚሁ በደርግ ዘመን በመጋቢት 4 ቀን 1968 ዓ/ል ነበር። ህዝበ ሙስሊሙም በካድሬዎች ሳይሆን እንደነ ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ባሉና ቁርኣንን ወደ አማርኛ በተረጎሙ ስመጥር ሊቃውንት እንዲመራ የደርግ መንግስት ፈቅዷል። የሃይማኖት እኩልነትን እሳቤ በሕዝቡ ውስጥ ለማስረፅም ጥሯል። ኋላ ላይም ሥርዓቱ ከተከተለው የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም ፍልስፍና አንፃር ሁሉንም ሃይማኖት በጥርጣሬና በስጋት ቢያይም እንደ መንግስት ሙስሊሙን ብቻ ነጥሎ የሥርዓቱ እና የሀገሪቷ ስጋት አድርጎ ባለመፈረጁና የማግለል ስልትን ባለመከተሉ ለሙስሊሙ የደርግ ሥርዓት ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት በእጅጉ የተሻለ መሆኑን አሳይቷል። አክሱምን ጨምሮ በአንዳንድ ሰሜናዊው የሀገሪቷ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊሞች ሕጋዊ የሙስሊሞች መካነ መቃብር እንኳን ማግኘት የቻሉት በአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ውድቀት ማግስት ነበር። በነኝህና በሌሎች በርካታ ቆራጥ እርምጃዎቹ የደርግ መንግስት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት የአገዛዝ ዘመኑ ለሙስሊሞች ውለታ ቢውልም ኋላ ላይ ግን በሙስሊሙም ሆነ በሌሎች በርካታ ጉዳዮች የሚያስወቅሱ በርካታ ተግባራትን ፈጽሟል። ይህን ርዕስ ስናጠቃልልም ያኔ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ሙስሊሞች የተቻለንን ያህል ስማቸውን መጥቀስ ያሻል ብለን ስላሰብን በዚሁ መሰረት ዝርዝራቸውን እነሆ ብለናል፡- እነ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱረሕማን፣ ዐብዱ በሽር፣ ዐብዱ አደም፣ ሐጂ ሻሚል ኑርሰቦ፣ ጀማል ዐሊ፣ ዐብደላ ሐሰን፣ ዐብደላ ዐብዱልቃዲር፣ አሕመድ ሸኽ አወል፣ ሲራጅ ሱለይማን፣ አሕመዲን ዩሱፍ፣ ዐብዱሶመድ ሰመረዲን፣ ሰዒድ ዩሱፍ፣ አሕመድ ዋሴ፣ ሲቲሚያ ሙሐመድ /ሴት/፣ አቶ ዐሊ አሕመድ፣ አቡበክር ሱለይማን፣ ሙሐመድ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ፣ ዒዘዲን ሙሐመድ /የአል ቁድስ አዘጋጅ የነበረው/፣ በድሩ ሡልጣን /የቃጥባሬ ሸኽ ልጅ/፣ አባቢያ አባጆቢር፣ አቶ አሕመድ ሰዒድ ዐሊ፣ አቶ ሙሐመድ አሕመድ ሸሪፍ እና ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ወዘተ ለሙስሊሙ መብት መከበር ከታገሉት መካከል ይገኙበታል። በሕይወት የሌሉትን አላህ ይማራቸው! ያሉትንም ያቆያቸው! በወቅቱ የታገሉት ከላይ የተጠቀሱት ብቻ ናቸው ማለት አይደለም። ሥማቸው እዚህ ያልተጠቀሱትም በርካቶች አሉ። ***************************** ደካማ ይልቃል ኃይለኛ ሲዋረድ ቡቃያ ይበቅላል ያፈራው ሲታጨድ ሰፊው ይቀንሳል ጠባቡ ሲስፋፋ ጨረቃ ታምራለች ፀሐይ ስትጠፋ ከንቅልፉ ሲነቃ ደግሞ የፈዘዘ የሞቀው ይሄዳል እየቀዘቀዘ እንደሕልም ታይቶ ያልፋል እንደጥላ ለዚህ ዓለም ነገር ምንም የለው መላ መታወቅ መረሳት ማርጀት መታደስ ይህ ሁሉ ልማድ ነው አይደለም አዲስ፡፡ (ዶ/ር ከበደ ሚካኤል)
نمایش همه...
ቄዎች በማንሳት ሕዝቡ ይበልጥ ተነቃቅቶ ለመብቱ እንዲታገል እንዲያነሳሱ አስችሏቸዋል። ለአብነትም በአዲስ አበባ ከተማ ከተክለሃይማኖት በታች በስልጤ ሰፈር የሚገኘው የሐጂ አሕመድ መሒሊ መስጊድ ከሰልፉ ከሁለት ዓመታት በኋላ መስጊዱ የተመሰረተበትን 27ኛ ዓመት በነሐሴ 9 ቀን 1968 ዓ.ል ባከበረበት ጊዜ የመስጊዱ ኮሚቴ አመራር ያደረገውን ንግግር እንመልከት። በዕለቱ የመስጊዱ ኮሚቴ በጽሁፍ ያደረገው ንግግር የወቅቱን የንቃተ ሕሊና ደረጃ እንድንረዳ ዘንድ ስለሰልፉና ስለሙስሊሙ ጥያቄ የሚያወሳውን እንይ፡- ‹‹ከዚህ በቀር ትዝታው ከማይጠፋንና እያንዳንዱ ምእመናን ከፍተኛ በሆነ አንክሮዋዊ ስሜት ሲያስታውሰው የሚኖር የእስላሙ ህብረተሰብ ለሀይማኖቱ እኩልነት ያደረገው ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ጭቁኖች የጋራ ጠላታቸውን ለመቋቋም እንዲተባበሩ የሕብረተሰብ ዕድገት ሕግ ነውና አመፁ በሥርዓቱ ላይ ነውና ተራማጅ የሆኑ የህብረተሰብ አባሎችና ክርስቲያን ወንድሞችም በዚህ ሰልፍ መካፈላቸው ሌላው ትዝታ ነበር። በሰልፉ ወቅት ከቀረቡት መፈክሮች ውስጥ ‹ሃይማኖት ከመንግስት አስተዳደር ይገንጠል›፣ ‹በዓላችን በብሔራዊ ደረጃ ይከበር›፣ ‹እስልምና ወንጀል አይደለም›፣ ‹የሃይማኖት እኩልነት ይኑር›፣ የሚሉ ይገኙበታል። በዚያን በወቅት ነበር የአክሊሉ ካቢኔ አይንህን ላፈር የተባለው። በዚያን ጊዜ ነበር ጭቁኖች ቢተባበሩ አንድም ኃይልሊቋቋማቸው እንደማይችል የታወቀው። ያኔ ነበር ያንድን ሕብረተሰብ ስንኩል አስተዳደር የግለሰብ መለዋወጥ ሊለውጠው እንደማይችል ያሳወቀው። ከዚያን በኋላ ነበር እኩልነት እስካልተመሠረተ ድረስ ሰላም እንደማይኖር፣ ያንዲት ሴኮንድ እፎይታ እንደሌለ፣ ጭቁኑ ከትግሉ የተማረበት፣ በአንፃሩም ለአድርባዮች፣ ለባንዳዎችና፣ ለአሽቃባጮች፣ ለመሳሰሉትም ሁሉ የትግል ሚናውን፣ የእኩልነት መርሆውን፣ የአንድነት አርማውን፣ የታሪክ ባለ አደራነቱን ያስተማረበት ወቅት። ከዚያ በኋላ የእስላሙ ሕብረተሰብ ካቀረባቸው ባለአሥራ ሦስት ነጥብ ጥያቄዎች ውስጥ መልስ ያገኘው አንዱ ብቻ ነው። ይኸውም የእስልምና በዓል በብሔራዊ ደረጃ በማክበሩ ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበት እያንዳንዱ ምእመናን መገንዘብ ሲኖርበት ይህንንም የሚወሰነው የራሱ ንቃትና የአንድነት ክንዱ ነው።›› (ዐብዱልፈታህ ዐብደላ፣ የአዲስ አበባ መስጂዶች ታሪክ፣ ቁጥር 2፣ ግንቦት 2002፣ አማን ኘሮሞሽን፣ ድሬ ማተሚያ ቤት፣ ገጽ 21) ይህ የመስጊድ ኮሚቴ አመራር ንግግር የወቅቱን የንቃት ደረጃ፣ንቅናቄው ሁሉንም ጥያቄዎች ሊያስመልስ አለመቻሉንና የሰልፉን ትዝታ በማንሳት ሙስሊሞች የተቀሩትንም ጥያቄዎቻቸውን ማስመለስ የሚችሉት በተባበረ ትግላቸው እንደሆነ ለማስገንዘብ እንደነበረ ያስረዳናል። ጥያቄዎቹ በሙሉ ሊመለሱ ላለመቻላቸው በርካታ ምክንያቶችን መዘርዘር እንችላለን። በዋናነት የትግሉ አለመቀጠል፣ የሙስሊሙ በትንሽ ነገር ተደስቶ የመዘናጋት ባህሪና መብቱን ሌሎች እንዲሰጡት አልያም ታግለው እንዲያስከብሩለት ከመፈለግ ዝንባሌ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ያለመቻሉ ችግር ተጠቃሽ ናቸው። አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስታቸው በሕዝባዊ ማዕበል እየተንገዳገደ በነበረበት ጊዜም ሆነ ሥርዓቱ ከተወገደ በኋላ ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደሌላው ሁሉ ራሱ ጥያቄዎቹን ለማስመለስ ተደራጅቶ ከመታገል ይልቅ የመረጠው አዲሱ መንግስት መብቱን እንዲሰጠው እየጠየቀ በተስፋ መቀጠልን ነበር። በርግጥ ያ ንቅናቄ ጠንካራ፣ ማደራጀት የሚችል፣ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው እና ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ አመራር ቢያገኝ ኖሮ ሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄውን ከማስመለስ አልፎ በሀገሪቱ ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ፣ ተደማጭ እና የፖለቲካ ኃይልያለው ህብረተሰብ ሊያደርገው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች ነበሩ። ከነዚህ መካከል ሕዝበ ሙስሊሙ ከንግድ መስክ ውጭ ሀገራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የተሳትፎ ልምድ ማጣት፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ አግላይ ፖሊሲ የተነሳ በሁሉም ዘርፍ በቂ ሊባል የሚችል ልሂቃን (Elites) አለማፍራት እና የትምህርት እድል ያገኙትም ብዙዎቹ ተመልሰው ወደ ንግዱ መስክ መመለሳቸውን በዋናነት መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ የተነሳ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በጦር ሠራዊቱ እና በሌሎች ወሳኝ መስኮች የሙስሊሙ ቁጥር እጅግ በጣም አናሳ ከመሆኑ የተነሳ ከግምት የሚገባ አልነበረም። በአዲሱ የደርግ መንግስትም ወሳኝ ቦታዎችን የያዙት አፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት ውስጥ በተለያዩ መስክ እድል ያገኙት ነበሩ። ለምሳሌ ከጦሩ የተለያየ ክፍለ ጦር ተወጣጥቶ ከፍተኛውን የሀገሪቱ ሥልጣን ከዚያው የደርግ ምክር ቤት አንድ መቶ ሀያ አባላት መካከል ሙስሊም አንዱ ብቻ ነበር። ይህ ግለሰብም ሆነ ኋላ ላይ በተለያየ የታችኛው እርከን ደርግን የተቀላቀሉ ጥቂት ሙስሊሞችም ቢሆኑ ሙስሊምነታቸው ከስም በዘለለ በእምነታቸው ሳይሸማቀቁ የወገኖቻቸውን አጀንዳ ለማንሳት የሚደፍሩ ነበሩ ለማለት ያስቸግራል።በመሆኑም የነርሱ በሥርዓቱ ውስጥ መታየት ለሙስሊሙ ያስገኘው ጥቅም ይህ ነው ብሎ ለማስቀመጥ ያዳግታል። በወቅቱ በሀገሪቱ በተፈጠረው መነቃቃት ምክንያት የተለያዩ አካላት የራሳቸውንና የወገናቸውን አጀንዳዎች በማንሳት ተደራጅተው በይፉም ሆነ በሕቡዕ ሲንቀሳቀሱ ሕዝበ ሙስሊሙ ግን የራሱን አጀንዳ ይዞ የሚታገልለት ለአዲሱ መንግስት አጋርም ሆነ ተቃዋሚ ድርጅትም ሆነ ፖርቲ አልነበረም። በወቅቱ እንደ መኢሶን ያሉት ገዢውን መንግስትከመቃወም ይልቅ አጋር ፓርቲ ሆነው ለተሻለ ለውጥ መሥራትን ሲመርጡ እንደ ኢህአፓ ያሉት ደግሞ ወታደራዊው መንግስት ከስልጣኑ ወርዶ ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም በሚል ተቃዋሚ ሆነው በሕቡዕ ይታገሉ ነበር። ከዚህ አንፃር የሙስሊሙ ለሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ከመሳተፍ ወደኋላ መቅረቱ ብቻ ሳይሆን እንቅስቃሴውም በሃይማኖትታዊ አጀንዳ ላይ እየተገደበ ሄደ። በወቅቱ ሙስሊሙ ከራሱ የእምነት ጥያቄ በተጨማሪ ‹‹መሬት ላራሹ››፣ ‹‹ሃይማኖት ከመንግስት አስተዳደር ይገንጠል››፣ ‹‹እኩልነት በተግባር ይተርጎም›› እና መሰል ጥያቄዎችን እንዳላነሳ ሁሉ ገፍቶ ባለመሄዱ እና ሂደቱ ሁሉ ዳግም በመስጊድ ብቻ በመወሰኑ ከበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ወደ ኋላ ተመለሰ። በርግጥ እውነታውን ካየነው የሀገሪቱ አጠቃላይ ችግሮች ሳይቀረፉ የሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ብቻውን ተለይቶ ሊመለስ የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ በመረዳት በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችም ላይ ከሌሎች ዜጐች ጋር በጋራ መታገል ነበረባቸው። የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደተጨቆኑ፣ እንደተገፉና በስርዓቱ ውስጥ ተገቢ መብታቸው እንዳልተከበረ በማመናቸው ተደራጅተው ሲታገሉ ለዘመናት ሲጨቆን የነበረው፣ መብቶቹ ያልተከበሩለት እና ከብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ወደ ኋላ የቀረው ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበርና እኩልነቱን በሁሉም ዘርፍ በተግባር ለማረጋገጥ የሚታገልለት አካል መፍጠር አልቻለም።በጣት የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በወቅቱ ከተቃዋሚ ጐራ ተሰልፈው የነበሩ ቢሆንም የሙስሊሙን አጀንዳዎች የፖርቲዎቹ አጀንዳ ማድረግ አልቻሉም። ቁጥሩ ከሌሎች አንፃር እጅግ አናሳ ቢሆንም ከተቃዋሚዎቹ ይልቅ በደርግ ውስጥ በመጠኑ የተሻለ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ነበሩ። ይህ የሆነው ተቃዋሚነት ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ዋጋ በመክፈል ለአጀንዳቸው ለመቆም የተዘጋጁ ባለመሆናቸው ሳቢያም ሊሆን ይችላል። በነኝህና መሰል ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው መነቃቃት እየቀዘቀዘ የሚገባውን ያህል ውጤ
نمایش همه...
የሰልፉ ንዝረት ክፍል 6 ⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️⚫️ ቤተ-ክህነት በሰልፉ ክፉኛ ደነገጠች። ወደ መቃብር እየወረደ የነበረው የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት ውድቀቱ ተፋጠነ። ሙስሊሙ ራሱ ‹‹ለካስ ይህን ያህል እንሆናለን?›› ሲል ተገረመ። በእምባ የተሞሉ ሙስሊሞች በርካቶች ነበሩ። ከቤተ ክህነት በተበተነው ወረቀት የሙስሊሙን ሰልፍ ለማክሸፍ የተወጠነው ሤራ ራሱ ከሸፈ። በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ክርስቲያን ተማሪዎች የቤተ ክህነትን ጥሪ ወደ ጎን ትተው ከሙስሊሙ ጎን ቆሙ። ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድ “Islam and Islamic Discourse in Ethiopia; 1973-1993” በሚለው ጽሑፋቸው ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን አገር እንደሆነችና ሙስሊሙ ከቁጥር የሚገባ እንዳልሆነ በአፄው ሲነገር የነበረውን ቅዠት ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ እርቃኑን አስቀርቶታል›› ሲሉ ጽፈዋል። ( Hussien Ahmed, Islamic and Islamic Discourse in Ethiopia, 1973-1993, P.779) በሰልፉ ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ሙስሊም ተሳትፎ ብሶቱን አሰማ። የተለያዩ ሚዲያዎች ዜናውን ለዓለም አሠራጩ። የሕዝቡን ቁጥር ቢቢሲ በሁለት መቶ ሺህ ገምቶ ዜናውን ለዓለም አሠራጨ። የኢትየጵያዉያን ሙስሊሞች ሰልፍ በተለያየ ሚዲያ ተዘገበ። አዲስ ዘመን በማግስቱ በሚያዚያ 13/1966 ዓ.ል እትሙ ‹‹ኢትዮጵያዉያን እስላሞች በአዲስ አበባ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ›› በሚል ርዕስ ዜናውን ጽፏል። እንዲህ ሲልም ገልጿል፡- ‹‹የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑት ኢትዮጵያዉያን የሃይማኖት እኩል መብት እንዲኖራቸው በማሳሰብ ትናንት ከቀትር በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከአንድ መቶ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ተካፋይ ሆነዋል። … በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሽማግሌዎች፣ ባልቴቶች፣ ጎልማሶችና ወጣቶች ሳይቀሩ ተካፋይ ሆነዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ታይቶ የማይታወቅ የሕዝብ ብዛት ቢገኝም አንድም የፀጥታ መታወክ አለመድረሱን ብዙዎቹን አስደንቋል። ይሁን እንጂ የፀጥታውን ሁኔታ ለመቆጣጠር የፖሊስ ሠራዊት አባሎች ከሰላማዊ ስልፈኞች ፊትና ኋላ በመሆን ሁኔታውን ተከታትለዋል።› (አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ሚያዚያ 13፣ 1966 ) ይህ ሁሉ ሲሆን አፄ ኃይለ ሥላሴ በከፊል ሥልጣናቸው በደርግ እየተነጠቀ ነበር። ሚያዚያ 1 ቀን 1966 የቀረቡት ጥያቄዎች በአፋጣኝ እንዲመለሱ አሳስቦ ያለ ፀጥታ ችግር በሰላም ተበተነ። የቤተ-ክህነት አመራሮችም በሙስሊሙ ሰልፍ የተሰሙት መፈክሮች ቅር እንዳሰኛቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታቸውን አሰሙ። በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 42 አብያተ ክርስትያናት ሙስሊሙ ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ሳትሆን የኢትዮጵያዉያን ደሴት ናት!›› በሚል በሰልፉ ያሰማውን መፈክር ተቃውመው የአብያተ ክርስትያናቱን ተወካይ በመምረጥ ወደ ፓትሪያርኩ ጽ/ቤት ላኩ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ ‹‹ምእመናንና ካህናት ለፓትሪያርኩ ተቃውሞ አሰሙ›› በሚል ርዕስ እንዲህ ሲል ዜናውን ጽፏል፡- ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት 42 አብያተ ክርስትያናት የተወከሉ ካህናትና ምእመናን ትናንት ጧት በመንበረ ፓትሪያርክ ተገኝተው ባለፈው ቅዳሜ ኢትዮጵያዉያን እስላሞች ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የሠነዘሯቸውን አንዳንድ ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች የሚቃወሙ መሆናቸውን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ገልጠዋል። በዚሁ ጊዜ ካህናቱና ምእመናኑ ለብጹእነታቸው ባቀረቡት የተቃውሞ ሐሳብ፣ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የክርስቲያኖች ደሴት መሆኗን ጠቅሰው፣ እስላሞቹ ‹ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት አይደለችም› ያሉትን ተቃውመዋል። እንዲሁም ‹ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት› የተባለው ከአክሱም፣ ከጎንደርና ከሸዋ ነገሥታት ሲያያዝ በመጣው የአገሪቱ ጽኑ ሃይማኖት መሠረት መሆኑን አስገንዝበው ይህን ለመሻር የሚደረገው ጥረት የመንግሥቱንም አቋም የሚያናጋ መሆኑን ገልጠዋል። ካህናቱ ውሳኔውን በተግባር ላይ ሆነው የሚጠባበቁ መሆናቸውን ገልጠዋል። ቀጥሎም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ለካህናቱ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖቱ ፅኑ፣ ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝ ለመሆኑ ታሪክ ምስክር ነው› ብለዋል። (አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ሚያዚያ 15 ቀን 1966) ከሁለት ቀናት በኋላ ሚያዚያ 14 ቀን 1966 ዓ.ል ቤተ-ክህነት በመላ አገሪቱ የሙስሊሙን ሰልፍና ጥያቄዎች ለመቃወም ሰልፍ ጠራች። ሙስሊሞች የአፄውን ሥርዓት ለመናድ ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡና እንደድሮው ‹‹አርፈው መኖር እንዲቀጥሉ›› አሳሰበች። ጭራሽ ሙስሊሙ በሃይማኖት ምክንያት ምንም በደል እንዳልደረሰበት ተናገረች። አፄ ኃይለ ሥላሴ የሃይማኖት ነጻነትን አክብረዋል የሚል ወረቀትም ተበተነ። የወረቀቱ ሙሉ ይዘት የሚከተለው ነበር፡- ‹‹ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን እስላሞች! እኛ ኢትዮጵያዉያን ክርስቲያኖች ወንድሞቻችሁና እኅቶቻችሁ እስከ ዛሬ ድረስ ሲፈጸም የኖረውን አገልግሎታችንና ሥራችን፣ እንዲሁም ትብብራችን የሃይማኖት ልዩነት ሳናሳይ መኖራችን የታወቀ ነው። እኛ አሁን የተነሣንበት ዋናው ዓላማ አብዛኛው የዓለም ክፍል እንዳለው ሁሉ የመንግሥቱ ሃይማኖት በዲሞክራቲክ ሕግ መሠረት የሕዝብ ሃይማኖት መሆኑ አያጠራጥርም። ከዚህም በቀር ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ‹ሃይማኖት የግል አገር የጋራ› ብለው ሙሉ መብት መስጠታቸውና ማወጃቸው በኢትዮጵያ የሃይማኖት ነጻነት መኖሩን ለመመስከር እንደሆነ ለማንኛውም የተሠወረ አይደለም። ይህን ዲሞክራቲካዊ አስተያየታችን ለመብት፣ ለፍትሕ፣ ለአንድነትና ለዕድገት ተቆርቋሪ በሆነው ሁሉ በኅብረትም ሆነ በግለሰብነት በመደገፍ በሰላም ያደረግነውንና የምናደርገውን ጥረት እንድታውቁልን እንጠይቃችኃለን። ሥጋችሁ ከሥጋችን፣ ደማችሁ ከደማችን፣ መልካችሁ ከመልካችን፣ መቼም ቢሆን ሊለያይ እንደማይችል እምነታችን ሲሆን በእምነት አስተሳሰብ ብቻ ብንለያይም በመሠረቱ አንድ ሕዝብ፣ አንድ ዜጋ መሆናችንን ሊፍቀው የሚችል የለም። ስለዚህ ይህንኑ ለአንድነታችን ማጠናከሪያ፣ ለውዲቱ አገራችን መገንቢያ ዓይነተኛ መሣሪያ የሆነውና የነበረውን ጥንታዊ ክርስቲያናዊ እምነታችን፣ ጥንታዊና ብሔራዊ ለሆነው ቅርሳችን ጠባቂ፣ የፊደልን ቅርጽና የአጻጻፍን ሥልት፣ የባህልን አቋምና የታሪክን መሠረት ጠብቆ የቆየውን ለመናድ የምታደርጉትን ፕሮፓጋንዳ በመቃወም ሚያዚያ 14 ቀን 1966 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማና በአጠቃላይ ግዛቶች ሁሉ ሰላማዊ ሰልፍ የምናደርግ መሆናችንና እንድትተባበሩን በቅድሚያ እናሳውቃለን።››(የኢት/ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2396/01/7) የአዲስ አበባ አብያተ ክርስትያናት ፊርማ አሰባስበው ለጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው አቤቱታ አስገቡ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 15 ቀን 1966 እትሙ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክርስቲያንን ተወካዮች አቤቱታ ተቀበሉ›› በሚል ርዕስ ሥር እንዲህ ሲል ዘግቧል፡-
نمایش همه...
👍 51 23
‹‹ክቡር ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያዉያን እስላሞች ባለፈው ቅዳሜ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉትን ሰላማዊ ሰልፍ መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ የክርስትያን ተወካዮች ያቀረቡትን አቤቱታ ትናንት ጧት ተቀበሉ። በዚሁም ጊዜ ተወካዮቹ በዚሁ ሰልፍ የታየውን ሁናቴ መሠረት በማድረግ የክርስትያንን ሃይማኖት አቋም የሚመለከቱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አቤቱታዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ስላቀረቡት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ከተወካዮቹ ጋር በሰፊው ተነጋግረዋል። ተወካዮቹም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰሙት በዚሁ አቤቱታ ኢትዮጵያዉያን እስላሞች ሰላማዊ ሠልፍ ባደረጉበት አንዳንድ ሰሌዳዎች ላይ የሠፈሩት ጽሑፎች የአገሪቷን ታሪካዊ አቋም የሚያቃውሱ፣ በብዙም ድካም ተመሥርቶ የተገነባውን ጽኑ አንድነት የሚያናጉና ዝንባሌያቸውም ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚያመሩ መሆናቸውን ገልጠው ይኸው አድራጎታቸው የከተማውን ክርስትያን ቅር ማሰኘቱንና ማሳዘኑን አስገንዝበዋል።›› (አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 15 ቀን 1966 እትም) የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ለአገሪቷ አደገኛና ለኢትዮጵያ አንድነት አሥጊ እንደሆነ ተደርጎ ተወሰደ። የሙስሊሙን ሰልፍ ቤተ- ክህነት እንዳልወደደችውና ነገር ግን ቁጥብነትና ታጋሽነትን መምረጣቸውን ተወካዮቹ አስረዱ። አዲስ ዘመን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡- ‹‹ይሁን እንጂ የከተማው ሕዝበ ክርስትያን የአገሪቷን ፀጥታ ለመጠበቅና ሰላምን ለማክበር በሰላማዊ ሠልፍ የታየውን መንፈስ በፍቅር፣ በትዕግሥት ያሳለፈው መሆኑን ተወካዮቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገለጡ በኋላ፣ ሕዝቡ በከተማው በሚገኙት አብያተ ክርስትያናት ተሰብስቦ ፀሎት ምሕላ በማድረስ ሁናቴውን በዚሁ ማሳለፉን አስረድተዋል።› (አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 15 ቀን 1966 እትም) በሳምንቱ የሙስሊሙን ሰልፍ የሚቃወም ሰልፍ ቤተ-ክህነት መጥራቷ ታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም የቤተ-ክህነት አመራሮችን አግባብተው ሐሳብ አስለወጡ። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ክርስቲያኖች ታጋሽና ቁጥብ መሆናቸውን አመስግነው በሳምንቱ የሙስሊሙን ሰልፍ በመቃወም የጠሩትን ሰልፍ ለርሳቸው ጥያቄ ፈቃደኛ በመሆን ስለ ሰረዙ አመሰገኗቸው። አዲስ ዘመን እንዲህ ሲል ዘግቧል፡- ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ጊዜ ለተወካዮቹ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያዉያኑ እስላሞች ያደረጉትን ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት በማድረግ የከተማው ክርስትያን ለማድረግ ያቀደው ተመሳሳይ ሰልፍ እንዲቀር ያስተላለፉትን የአደራ መልእክት ሕዝቡ የተቀበለውና ያከበረው በመሆኑ፣ ያለውንም የጨዋነትና የአስተዋይነት ባህሉን አክብሮ በመገኘቱ ከልብ አመስግናለሁ ብለዋል። ከዚህም በማያያዝ በተናገሩት ቃል የአገሪቷን አንድነት፣ ዕድገትና ብልፅግና በይበልጥ ለማስከበርና ለማረጋገጥ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ የሃይማኖት ትብብርና ፍቅር ለወደፊቱ በይበልጥ እየጠነከረ እንዲሄድ ለመረዳት የተለየ ኃላፊነትና ጥረት ማሳየት አለባቸው በማለት አሳስበዋል።›› (አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 15 ቀን 1966 እትም) በአማኞች መካከል መቻቻልና መተባበር እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለክርስቲያኑ ተወካዮች አሳስበዋል። በአ/አበባ የሚገኙ አርባ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ለኦርቶዶክሱ ጳጳስ አቡነ ቴዎፍሎስ ደብዳቤ አስገብተዋል። በደብዳቤዎቻቸውም የሙስሊሙን ሰልፍ አውግዘዋል። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት አለመሆኗን ሙስሊሙ በመፈክሩ ማሰማቱን ኮንነዋል። (Islam and Islamic discourse in Ethiopia p. 782) አብያተ ክርስቲያናቱን ይበልጥ ያበሳጫቸው ከክርስቲያኑ ወገን ሙስሊሙን ደግፈው በሰልፉ የተገኙት ነበሩ። ክርስቶፎር ክላፋም የተባሉት ምሁር “Transformation and Continuity in Revolutionary Ethiopia” በሚለው ጽሑፋቸው ገጽ 107 ላይ ‹‹ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ጎን ለጎን ሆነው መፈክር እያሰሙ መሰለፋቸው ለትምክተኛው ክርስቲያን ወገን ከጥቃቶች ሁሉ የላቀው ጥቃት ነበር›› ሲሉ ጽፈዋል። ሰልፉ የሙስሊሙ መብት ተከብሮ ኢስላምም እንደ ክርስትና ቦታ ካገኘ አገሪቷ እንደምትበጣበጥና አንድነቷ እንደሚናጋ ተደርጎ በአፄውና በግብረአበሮቹ የተንፀባረቀው ዕይታ ከንቱና ደካማ አስተሳሰብ መሆኑን አሳይቷል። ጥንካሬ ከአንድነት እንደሚመጣ፣ ኃይል ከእኩልነት እንደሚነሳ የሕዝበ-ሙስሊሙ ሰልፍ አስተምሯል። (ሙሐመድ ዩሱፍ የዕቁብ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሥቃይና የመከራ ታሪክ፣ 1987፣ ገጽ 21) ይቀጥላል………
نمایش همه...
👍 173 87
"አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?" ክፍል አምስት ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★ የሕዝቡ ስሜት ያስደነግጣል፤ ብዛቱ ያስገርማል። ‹‹ይህን ያህል ሙስሊም እስከ ዛሬ የት ነበር?›› አስባለ። የሰልፉ ጫፍ አራት ኪሎን አልፎ ቤተ መንግሥቱን ቁልቁል ቢወርድም የኋለኛው ጫፍ ገና ከአንዋር መስጂድ ንቅንቅ አላለም ነበር። ሌላው አካል ቀርቶ አዘጋጆቹ እንኳ በሕዝቡ ብዛት ተገርመዋል። መፈክሩ ቀጠለ፡- ‹‹ሕጉን ውስጣዊ ደንብ አይጫነው! አንድነት የሚገኘው በእኩልነት ነው! እኩልነት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ! የአትዮጵያ ችግር ለመላው ኢትዮጵያዉያን ችግር ነው! ኢትዮጵያ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ! እኩልነት የዕድገት መክፈቻ ቁልፍ ነው! የሃይማኖት ልዩነት የአንድነት እንቅፋት ነው! ፍትሕ በኢትዮጵያ ይስፈን! ተባብረን እንሥራ! የሃይማኖት ልዩነት ይቅር! ሃይማኖት ከመንግሥት አስተዳደር ይገለል! እኩልነት ከሌለ ብልጽግና አይኖርም! የሰላም መሠረት እኩልነት ነው! በአስተዳደር ፍትሕ ይስመር! የእኩልነት መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም! አንድ ነው ደማችን! ኃይላችን አንድ ይሁን! አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ! የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?›› (የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁ. 2400/01/4) ከአማርኛ መፈክሮች በተጨማሪ የእንግሊዘኛ መፈክሮችም ቀጠሉ፡- “Equality is the basis of unity! We can not afford to remain second class citizens! We demand for equal participation in administration! Out of 14 Enderases none of them is a Muslim! Out of 20 Ministers only two are Muslims! No Muslim is a General! Our demand is for equality, not superiority! The constitution discriminates against the majority of the population! Ethiopia is not only a “Christian Island!” we too are Ethiopians! Go away with religious discrimination! Ethiopia can not afford to have second class citizens! Declare secular state! Liberty, equality and fraternity! Men are born free and equal in rights!” ( የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2396/02/5) የነዚህ መፈክሮች ትርጉም እንደሚከተለው ነው፡- ‹‹እኩልነት የአንድነት መሰረት ነው! ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆነን መቀጠል አይቻለንም! በአስተዳደር ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዲኖረን እንጠይቃለን! ከ14ቱ እንደራሴ ውስጥ አንዱም ሙስሊም አይደለም! ከ20ዎቹ ሚኒስትሮች ውስጥ ሙስሊሞች ሁለት ብቻ ናቸው! አንድም ሙስሊም ጄኔራል የለም! ጥያቄያችን እኩልነት እንጂ የበላይነት አይደለም! ሕገ መንግስቱ አብዛኛውን ሕዝብ ያገለለ ነው! ኢትዮጵያ ‹የክርስቲያን ደሴት› ብቻ አይደለችም፤ እኛም ኢትዮጵያዉያን ነን! ከሃይማኖት አድሎ ጋር አብራችሁ ተወገዱ! ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ እንዲኖራት አትታገስም! ዓለማዊ መንግስጥ ይታወጅ! ነፃነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት! የሰው ልጆች የተወለዱት ነፃ ሆነውና እኩል መብት ኖሯቸው ነው!›› የሙስሊሙ ሰልፈኛ ስሜት እየተጋጋለ ነው። መፈክሩ ቀጠለ። መዝሙርም ተስተጋባ፡- 1. መብታችን ይሰጠን የእምነት መብታችን እኩልነታችን ይጠንክር ኃይላችን ከወገኖቻችን! 2. አንድ ይሁን ደማችን ከወንድሞቻችን ተባብረን እንገስግስ ከገዛ ሕዝባችን ልዩነቱም ይጥፋ ከሥር መሠረቱ አጥንት ደማችን አንድ ነው በውነቱ 3. አገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው የሚለው መሪ ቃል ይሠራበት ምነው? 4. ከአንድ አባትና ከአንድ እናት ነው! በምን ነገር ነው የተለያየን አስተካክሉን አስተካክሉን! ከአንድ ባንዲራ አትነጣጥሉን! 5. ክርስቲያኑ ወገናችን ተጠብቆ መብታችን እንድንሠራ ላገራችን ተሰለፉ ከጎናችን! 1. ኢትዮጵያ የሁላችን እኩል ይሁን መብታችን እንድንሠራ ላገራችን ይጠበቅ መብታችን! 2. እኩል ነው ልፋታችን እኩል ነው ግብራችን እኩል ነው መሞቻችን እኩል ይሁን ድጋፋችን! የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መፈክር በመያዝ ሚያዚያ 27 አደባባይ ላይ ሰልፉን ተቀላቀሉ። (አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ሚያዚያ 13፣ 1966 ዓ.ል) ከሙስሊሙ ሰልፍ የተቀላቀሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበኩላቸው ሙስሊሞችም ክርስቲያኖችም በጋራ ሆነው ድምጻቸውን ያሰማሉ። ከያዟቸው መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- ‹‹ሕዝባዊ መንግሥት ይቋቋም! ለእስላም ሴቶች የሃይማኖት ጭቆና ይቅር! መሬት ላራሹ! የፖለቲካ ፓርቲዎች ይቋቋሙ! ባላባታዊ መንግሥት ይውደቅ! አትነሳም ወይ! አትነሳም ወይ! የግፍ አገዛዝ! አይበቃህም ወይ! ምርጫ ለሕዝብ! እንዳልካቸው ይውረድ! እኛ ክርስቲያኖች በሃይማኖት እየከፋፈሉ መግዛትን እናወግዛለን! የሃይማኖት መብታችን ይጠበቅና በኢትዮጵያዊነታችን እንኩራ!›› የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የራሳቸው መፈክሮችን ይዘው ሰልፉን ተቀላቅለዋል። እነርሱም መፈክራቸውን ጮክ ባለ ድምጽ ያስተጋባሉ፡- ‹‹የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጥያቄዎች ይሟሉ! የሕዝብ ጥያቄዎች በአስቸኳይ ይፈጸሙ! የመሬት ይዞታ በፍጥነት ይሻሻል! የዘርና የሃይማኖት አድልኦ ይውደም! ኢትዮጵያ የእስላምና የክርስቲያን አገር ናት! አይገባም ማድረግ እንደጋሻ ሃይማኖት! በእውነት ተነስተን አገርን ለማልማት! አንድነት ኃይል ነው! ተነስ! ነጻነት! እኩልነት! ወንድማማችነት! ‹አስተዳደርና ሃይማኖት ይለያዩ› የሚለው ጥያቄ የእኛም የክርስቲያኖች ነው! ሃይማኖት የፖለቲካ መሣሪያ አይደለም! ሃይማኖቶች ሁሉ በዴሞክራታዊ መንገድ ይከበሩ! ሠራተኛ ባሪያ አይደለም! መሬት ላራሹ! የመናገርና የጽሑፍ ነጻነት ለሕዝብ ይሰጥ! ሃይማኖት የፖለቲካ መሣሪያ መሆን የለበትም!›› ከአማርኛው በተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተማሪዎች በጋራ ሆነው የእንግሊዝኛ መፈክሮችን ያስተጋባሉ። ካሰሙት መፈክሮቻቸው መካከል፡- “Secularize the state! Ethiopia is not only to the Christians! We Christians support this democratic demand of our Muslim brothers! No state interferes in religion! Unity is the basis of equality! Separate the church and the state!” በእንግሊዘኛ የተሰሙት የነዚህ መፈክሮች ትርጉም እንደሚከተለው ነው፡- ‹‹መንግስቱ (ሥርዓቱ) ዓለማዊ ይደረግ! ኢትዮጵያ የክርስቲያኖች ብቻ አይደለችም! የሙስሊም ወንድሞቻችንን ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን እኛ ክርስቲያኖችም እንደግፋለን! በሃይማኖት የመንግስት ጣልቃ ገብነት አይኑር! አንድነት የእኩልነት መሰረት ነው! መንግስትና ቤተ-ክርስቲያን (ሃይማኖትና መንግስት) ይነጠሉ!›› ‹‹በሌሎች ገበታ የሚተማመን ሁሌም ዘግይቶ ይመገባል።›› (ጣልያኖች) ይቀጥላል....
نمایش همه...
128👍 77
“ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሶደቃ ይሆንለታል” ረሱል ﷺ (ነሳኢ 1787ና ኢብኑ ማጀህ 1344)
نمایش همه...
👍 217 116
በድንገት ከሁሉም ለየት ያለ ሰው ወታደራዊ ልብሱን እንደለበሰ መትረየሱን ደግኖ ወደ ሰልፉ ጠጋ አለ። የአስተባባሪዎቹ ዓይን በቅጽበት በርሱ ላይ ዐረፈ።የባሕር ኃይል ምክትል ኃላፊ የነበረው ኮማንደር ዘካርያ ይባላል። ሙስሊም ነው። የእምነት ጭቆና አንገሽግሾታል። ብዙ በደሎች ደርሰውበታል። ሌላ ምንም ጥፋት አላጠፋም፤ወንጀሉ ሙስሊም መሆኑ ብቻ ነበር! ጠጋ ብሎ ወደ ሰልፉ ተቀላቀለ። መትረየሱን ደግኖ የመጣው ‹‹ከመንግሥት ኃይል ጥቃት ይፈጸምብናል›› በሚል ሥጋት ነበር። ዶ/ር አሕመድ ቀሎ ጠጋ ብሎ ‹‹ይህ ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀው። ‹‹ዛሬ ቀናችን ነው! ብናልቅም ጨርሰን ነው የምንሞተው!›› ሲል መለሰ። በርግጥ ሰልፉ የተጠራው ያለፈቃድ ነው። ሆኖም መንግሥት ሳይወድ በግድ ሰልፉ እየተካሄደ ነው። ዶ/ር አሕመድ ቀሎ አግባብተው ሰይፉን ብቻ ታጥቆ ከነወታደራዊ ልብሱ በሰልፉ እንዲሳተፍ አደረጉት። ሙስሊሙ ለመብቱ ሲል እንዲያ ሲሆን ለጥቅም ብለው ከመንግሥት ጋር የወገኑ ሙስሊሞችም አልጠፉም። ከሙስሊሙ መብት መከበር ይልቅ ለነሱ የበለጠባቸው ዓለማዊ ጥቅም (ከመንግሥት የሚገኝ ጥቅም) ነበርና። የሙስሊሙ ስሜትና ብሶቱን የሚያሰማበት አኳኋን አስደንጋጭ ነበር። ማንም ‹‹እንደዚህ ያለ ሰልፍ ይደረጋል›› ብሎ አልጠበቀም ነበር። ‹‹ሙስሊሙ እንዲህ ይበዛል›› ብሎ የገመተም አልነበረም። ሰልፉን ለማክሸፍ ሲራወጡ የነበሩት የደህንነት አባላትም ጥረታቸው ከሽፎ ከፖሊስ ጋር ፀጥታ ለማስከበር ጥግ ጥጉን ይዘዋል። ሰልፉ ተጀመረ። እየዘመረ፣ መፈክር እያሰማና ተክቢራም እያለ ከአንዋር መስጂድ ተንቀሳቀሰ። ሐብተ ጊዮርጊስ ድልድይን ተሻገረ። ፒያሳን አቋርጦ ራስ መኮንን ድልድይን አለፈ። አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ ትንሽ ግርግር የሚጀመር መስሎ ነበር። ግና ወዲያው ተረጋጋ። ጉዞውንም በሰላም ቀጠለ። በየመንገድ ዳር የቆሙና በየፎቅ በረንዳ ላይ በመስኮት በኩል በሚመለከቱት ጭብጨባ ደመቀ።መፈክሮች ተስተጋቡ፡- ‹‹ሀገር የጋራ ነው! ሃይማኖት የግል ነው! እስላማዊ በዓላት ብሔራዊ በዓላት ይሁኑ! ‹ኢትዮጵያዉያን እስላሞች› ተብለን እንጠራ! የሃይማኖት ልዩነት በየትም ቦታና መሥሪያ ቤት ይቅር! የእስልምና ሃይማኖት የመንግስት ድጋፍ ይኑረው! ኢትዮጵያ በሃይማኖት መከፋፈል የለባትም! ኢትዮጵያዉያን እስላሞችና ክርስቲያኖች ወንድማማቾች ናቸው! በኢትዮጵያዉያን መካከል አንድነት ለዘለዓለም ይኑር! ኢትዮጵያ በልጆቿ አማካይነት ወደፊት ትራመድ! አንድነት ኃይል ነው! ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ደሴት ናት! ነቀፌታ የማይቀበል መንግሥት ዘለቄታ የለውም! (የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2396/02/5) ይቀጥላል....
نمایش همه...
👍 165 79
ሰላማዊ ሰልፉ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 የዛሬ 50 አመት በዛሬው እለት ነበር ይህ ክስተት የተፈፀመው 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ክፍል 4 የሙስሊሙ ሰልፍ ማድረግ አይቀሬ ሆነ። በአንድ በኩል የመንግሥት የደህንነት አባላት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ ክህነት ሰልፉን የማክሸፍ እንቅስቃሴ አደረጉ። ቤተ ክህነት የሙስሊሙን ሰልፍ የማክሸፍ ዓላማ እንዳላትም ለሰልፉ አስተባባሪዎች ግልጽ ሆነ። በመሆኑም ለቤተ ክህነት አባላትና ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሙስሊሙን ሰልፍ ዓላማ የሚያስረዳ ወረቀት ተበተነ። የተበተነው ወረቀት ያዘለው ሙሉ መልዕክት የሚከተለው ነበር፡- ‹‹ለክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን! በእኛ በኢትዮጵያዉያን እስላሞች ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ሲፈጸም የኖረው ያልተስተካከለ የሃይማኖትና የአስተዳደር አመራር ምን ያህል አራርቆን እንደቆየ ሳትገነዘቡት አትቀሩም። እኛ የተነሳንበት ዋናው ዓላማ በአብዛኛው የዓለም ክፍሎች እንዳለው ሁሉ መንግሥት ከሃይማኖት የተለየ /ሴኩላር/ አመራር እንዲኖረው፣ ይህ ሳይቻል ደግሞ የኛ ሃይማኖትም የመንግሥቱ ሙሉ ድጋፍ የሚደረግለት ለመሆኑ በሕግ እንዲረጋገጥልን ነው። ይህን ዲሞክራቲካዊ ጥያቄያችንን ለመብት፣ ለፍትሕ፣ ለአንድነትና ለዕድገት ተቆርቋሪ የሆነ ሁሉ በኅብረትም ሆነ በግለሰብነት በመደገፍ በሰላም በምናደርገው ትግል ተካፋይነቱን እንዲያስተባብርልን ነው። ኢትዮጵያ አገራችን በአሁኑ ጊዜ በኢኮኖሚና በሶሻል አቋሟ ላይ የደረሰው ችግር ተባብረን ለመወጣት እንድንችል በሃይማኖትና በአስተዳደር በኩል ያለውን የልዩነት መንፈስ እንዲወገድ በምናደርገው ጥረት ሁሉ እናንተም እንድትተባበሩን እንጠይቃችኃለን። ከደማችሁ ደማችን፣ ከሥጋችሁ ሥጋችን፣ ከመልካችሁ መልካችን እስካልተለየና በመሠረቱ አንድ ሕዝብ መሆናችን እስካልቀረ ድረስ በሃይማኖት ምክንያት ብቻ ያለውን መነጣጠል ብናስወግድ ለአገሪቱ ዕድገትና ለሕዝቧም አንድነት የበለጠ የሚጠቅም መሆኑ ጥርጥር የለውም። ስለዚህ ይህንኑ ለአንድነታችን ማጠናከሪያ፣ ለውዲቷ አገራችን መገንቢያ ዓይነተኛ መሣሪያ የሆኑትን ዲሞክራቲካዊ ጥያቄዎቻችንን ለመንግሥት በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ሚያዚያ 12 ቀን 1966 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ትዕይንተ ሕዝብ /ሰላማዊ ሰልፍ/ ስለምናደርግ በዚህን ጊዜ ለምታደርጉልን ትብብር ምስጋናችንን በቅድሚያ እንገልጻለን። ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ኢትዮጵያዉያን እስላሞች!›› (የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2396/01/7) ከወረቀቱ በተጨማሪ ‹‹የቤተ ክህነትንና አንዳንድ ክርስቲያን ምሁራንን በአካል ቀርቦ ማሳመን ይገባል›› የሚል ሐሳብ ቀረበ። ወደቤተ ክህነት አባቢያ አባጆቢር ተላኩ። ሌሎች ደግሞ ክርስቲያን ምሁራንን ለማናገር ተላኩ። ‹‹ዓላማችን በእናንተ ላይ ጦርነት ለመክፈት አይደለም። ሁላችንም ወንድማማቾች ነን፤ ይህችን አገር ለማሳደግ ውህደታችንን ማጠናከር አለብን፤ እናንተ ከኛ ጎን መቆም አለባችሁ›› በማለት ሊያስረዱ ብዙ ሞከሩ። ቤተ ክህነት ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት›› ብላ ስለምታምን አባቢያ ሳይሳካላቸው ተመለሱ። (Badr Magazine Annual Edition, 2008, USA, p. 21-23) ሁሉም ነገር ከቁጥጥሩ ውጪ እየሆነ መሆኑን የተረዳው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው ሰልፉን የማክሸፍ የመጨረሻ ሙከራ አደረገ። በቴሌቪዥን ‹‹የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ እንደሚታይና ሰልፍ እንዳያደርጉ›› በሚል ጥሪ አደረገ። ሐሙስ ሚያዚያ 10 ቀን 1966 ዓ.ል በሚቀርቧቸው ሙስሊሞች በኩል የሰልፉን አስተባባሪዎች በማግባባት ለማስቆም ቤተ መንግሥት ጠራቸው። ሙስሊሞቹም ከሥፍራው ተገኙ። ሰልፉን ማስቆም እንደማይቻልና እነርሱም እንደማይችሉ አስረግጠው ተናገሩ። የሙስሊሙን ሐሳብ ዶ/ር አሕመድ ቀሎ ‹‹ከእጃችን ወጥቷል። ይህ የሕዝቡ ሰልፍ ነው። እናስቁመው ብንል ድጦን ነው የሚሄደው። ማስቆም አይቻልም!›› ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማጠቃለል ነገሯቸው። የሙስሊሞቹን ሁኔታ ያስተዋለው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው ‹‹ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም›› ሲል ከተረተ በኋላ ‹‹በሰላም እንዲጠናቀቅ አደራ!›› ሲል ተማፀነ። ሙስሊሞቹ ሰላም አስከባሪ የፖሊስ ኃይል እንዲመደብ ጠየቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተስማማ። ሰልፉ አንድ ቀን ሲቀረው አቶ ሙሐመድ አወል በአንዋር መስጂድ በጁምዓ ሶላት ላይ በመገኘት የኮሚቴውን መግለጫ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈውን ደብዳቤና የሰልፉን ጥሪ ወረቀት አነበቡ። በኒ ሰፈር በሚገኘው ኑር መስጂድ ተመሳሳይ ወረቀት በወጣት ሙሐመድ ሐሰን ተነበበ። የሰልፉ አስተባባሪዎችም ‹‹ሰልፉን ሊያከሽፉብን ይችላሉ›› ብለው ያሰቧቸውን ሁሉ ለማለዘብ ሞከሩ። ሙስሊም ያልሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም የሙስሊሙ ሰልፍ ድምጻቸውን ለማሰማት ጥሩ አጋጣሚ ሆነላቸው። አብዛኛው ተማሪም የቤተ-ክህነትን ጥሪ በመጻረር ከሙስሊሙ ጋር ቆመ። በወቅቱ በጌታቸው በጋሻው የሚመራው የተማሪው እንቅስቃሴ ሙስሊም ያልሆኑትን ከሙስሊሙ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አደረገ። መለስ ተክሌ፣ ለገሰ ዜናዊ፣ ባንቴ ሁዋላ፣ ገላሳ ዲልቦ፣ ጀዛኖ፣ መረራ ጉዲና፣ እሸቱ ጮሌ፣ ፕሮፌሰር ፍሬ መርዕድ፣ አቦማ ምትኩ፣ ጌታቸው በጋሻው፣ ገለታ ዲልቦ፣ ሽመልስ ማዘንጊያ፣ ያዕቆብ ወልደማርያም ወዘተ በወቅቱ ሙስሊሙን በሐሳብ የረዱ ነበሩ። በተለይም ለገሰ ዜናዊ መፈክር ለሙስሊሞቹ ያፈልቁ ከነበሩት መካከል ነበሩ። (Badr Magazine Annual Edition, 2008, p.20-23) ሙሐመድ ሐሰን፣ ዐብደላ፣ ሰዒድ አሕመድ፣ ዒዘዲን ሙሐመድ (የአል ቁድስ ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረው) ያኔ በወጣቶች ክበብ ውስጥ የሥነ-ጽሑፍ ክፍል አባል ነበሩ። ሌሎች ከዩኒቨርሲቲ የመጡ ሙስሊሞች መፈክር ሲጽፉና መዝሙር (ዜማ) ሲለማመዱ በአንዋር መስጂድ አደሩ። የተጠበቀው ቀን ሚያዚያ 12 ቀን ዕለተ ቅዳሜ 1966 ደረሰ! ጎህ ሲቀድ ሱብሂ ሶላትን እንደሰገደ ሰዉ ወደ አንዋር መስጂድ ይጎርፋል። ጭቆናው አማርሮታል። የመብቱ መረገጥ አብግኖታል። በአገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ ከንክኖታል። ሴቱ፣ ወንዱ፣ ተማሪው፣ ወጣቱ፣ አዛውንቱ፣ ሕፃናት፣ አሮጊቶች… ሁሉም ወደ አንዋር! በአዲስ አበባው ሰልፍ ለመሳተፍ ጥቂት ግለሰቦች ከባሕር ዳር፣ ናዝሬት፣ ጎጃም፣ ደብረ ማርቆስ፣ ድሬዳዋ፣ ጅማ፣ አክሱም ወዘተ. በመምጣት በአንዋር አቅራቢያ አድረዋል። ተክቢራው ከየአቅጣጫው ይስተጋባል። ‹‹ዛሬ ነው ቀናችን!‹‹ በሚል ስሜት ሁሉም ሙስሊም ብሶቱን፣ ቁጭቱን፣ መናቁን እያሰበ በወኔ ወደ አንዋር ይተማል። ፍትሕና እኩልነት በመሻት ከሙስሊሙ ጎን የቆሙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም የየራሳቸውን መፈክር ይዘው የሰልፉን መጀመር ይጠባበቃሉ። በመንግሥት ላይ ካላቸውም ተቃውሞ ሰልፉን የተቀላቀሉትም እንዲሁ። ዘር፣ ፆታ፣ እድሜ ሳይለይ ሙስሊሙ ነቅሎ ወጥቷል። ከቤተ ክህነትም ሆነ ከማንኛውም ወገን ችግር እንዳይከሰት የኮሚቴው አባላት ቦታ ቦታቸውን ይዘው ያስተባብራሉ።
نمایش همه...
👍 75 31
የሐጅ ምዝገባ በዛሬውእለት በድጋሚ እንደሚጀምር መጅሊስ አስታወቀ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ተቋርጦ የነበረው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ምዝገባ ከዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 12/2016 ጀምሮ በድጋሚ ይካሄዳል ሲል ያስታወቀው ዛሬ ነው። ምክር ቤቱ ተመዝጋቢዎች ሁጃጆች ለምዝገባ ሲመጡ የታደሰ ፓስፖርት፣ መታወቂያና ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው እንዲመጡ አሳስቧል። መጅሊስ ፓስፖርት የሌላቸውና እድሚያቸው ከ50 በታች የሆነ ተመዝጋቢዎች የልደት ሰርተፊኬት እንዲያቀርቡ የጠየቀ ሲሆን፣ እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ ለሆናቸው ደግሞ መታወቂያና ጉርድ ፎቶ ግራፍ ብቻ ይዛችሁ መገኘት አለባቸው ብሏል። ጥቂት ተመዝጋቢዎችን እንደሚቀበል ያስታወቀው ምክር ቤቱ፣ ከነገ ጀምሮ የሐጅ ምዝገባ እንደሚቀጥል ቢያሳውቅም የሚጠናቀቅበትን ቀን አልገለፀም።
نمایش همه...
119👍 59
ም ቅዳሜ በ 3 ሰዓት ከመስጂደል አንዋር ይጀምራል። ኢትዮጵያዉያን እስላሞች! (የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2396/02/5) ይህ ሁሉ ሲሆን የመንግሥት የደህንነት አካላት ሰልፉን ለማሰናከል አስተባባሪዎችን፣ በተለይም ወጣቱን ክፍል ያሳድዱ ነበር። ከወጣቱ መካከልም በዋናነት በእነ ዶ/ር አሕመድ ቀሎ እና ጉልህ ሚና ባላቸው ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ በተጋጋሚ ይፈጸም ነበር። ሰፈር በመቀያየር፣ ራሳቸውን በመለዋወጥ እና ከደህንነት ለሚደርስባቸው ዛቻና ማስፈራሪያ ‹‹የፈለጉትን ያምጡ›› ሲሉ ራሳቸውን አሳምነው በተግባራቸው ገፉበት። ስለ ሰልፍ የሰማ ሙስሊም ሁሉ ‹‹አንዳች ይነገር ይሆን?›› እያለ አንዋር መስጂድን ማዘወተሩን ቀጠለ። ሰልፉ ፈቃድ ባይኖረውም ‹‹የመጣው ይምጣ›› በሚል ሁሉም ተረባረበ። አቶ ዐብዱ አደም የተባሉ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ባለሐብት ወደ ሰልፉ አቀናባሪ ዶ/ር አሕመድ ቀሎ በመምጣት የሰልፉን ሙሉ ወጪ ለመሸፈን እንደሚፈልጉ እንዲህ ሲሉ ገለጹ፡- ‹‹አሕመድ! እኔ ሕዝቡ ጋር ሄደህ ገንዘብ እንድትሰበስብ አልፈልግም። አትቸገር፤ እኔ አለሁ! ለሰልፉ የሚያስፈልገውን የፈለግከውን ያህል ገንዘብ ይኸው ባዶ ቼክ። ከባንክ አውጥታችሁ ተጠቀሙበት። እኔ በምን አወጣኸው ብዬ አልጠይቅህም። እኔ አለሁ! የፈለጋችሁትን ገንዘብ ተጠቀሙበት! ይህ በእኔና ባንተ መሐል ይሁን።››(ከዶ/ር አሕመድ ቀሎ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ) አቶ ዐብዱ አደም እንዳሉትም የሰልፉን ሙሉ ወጪ ሸፈኑ። ገንዘባቸውንም ለሙስሊሙ መብት መከበር ትግል አዋሉ! ይቀጥላል……….
نمایش همه...
102👍 59
የዛሬ 50 አመት በዛሬው እለት ነበር ይህ ክስተት የተፈፀመው 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ‹‹አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ! ይህ ጥያቄ ያንተ አይደለም ወይ?" ክፍል 3 📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 ጥያቄዎቹ ለመንግሥት ከቀረቡ በኋላ ምላሹን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማሳወቅ በአባድር ኢንስቲትዩት (ት/ቤት) ሰብሰባ ተጠርቷል። በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ከሐምሳ ያልበለጡ ሙስሊም ግለሰቦች ተቀምጠዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠውን ምላሽ ተወካዮቹ አብራሩ። ተወካዮቹ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ ዶ/ር አሕመድ ቀሎ፣ አሕመድ ሰዒድ ዐሊ፣ጧሃ፣ ዐብዱልዋሲዕ መንዲዳ፣ ዐብዱ አደም፣ወዘተ…፤ ሪፖርት ሲያቀርቡ ሁሉም በጥሞና ያደምጣል። የምላሹ ድምዳሜ ‹‹ጉዳያችሁ ይታይላችኋል ጠብቁ›› የሚል ነበር። በሥፍራው ከተገኙት መካከል ወጣቶቹ ምላሹ እጅግ አበሳጫቸው። ይበልጥ ደግሞ የአንዳንድ ተወካዮች ‹‹ብንጠብቅ ይሻላል›› የሚለው አስተያየት አናደዳቸው፤ አዘኑ፤ ቁጭት ገባቸው። አንዳንዶቹ ‹‹አይሆንም! የሆነ ነገር መደረግ አለበት›› ሲሉ በምሬት ተናገሩ። ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ፋታ ስጡኝ! ጠብቁ!› ምላሽ ልንቀር ነው?›› በማለት አሳሰቡ። ከፊሎቹ ‹‹‹ችግራችሁ ይታይላችኋል፤ ጊዜ ስጡኝ!› መባሉ በራሱ አዎንታዊ ምላሽ ነውና እንጠብቅ›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰነዘሩ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ የ30 ዓመቱ ወጣት አሕመድ ቀሎ (ዛሬ ዶ/ር ናቸው) እጅ አወጡ። እንዲናገሩ እድል ተሰጣቸው። እንዲህ ሲሉም ሀሳባቸውን ገለጹ፡- ‹‹እንዲህማ አይሆንም! ማንም ገዢ የሆነ ሰው ይህንኑ ነው የሚለው። የሙስሊሞችን ጉዳይ ቀላል አድርገን ‹ጊዜ ስጡኝ› ስላለ ጊዜ አንሰጠውም! እስካሁን ሲጨቁነን የቆየ መንግሥት አሁን አንድ ደብዳቤ ስለጻፍንለት ብቻ ለውጥ ይመጣል ብለን መጠበቅ የለብንም። ወደሚቀጥለው እርምጃ መሄድ አለብን፡፡›› (በ2001 ከዶ/ር አሕመድ ቀሎ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ - በደራሲው) ሞራላቸው ተነክቶ የነበሩት ወጣቶች ከምሁራኑ ዶ/ር አሕመድ ቀሎ ስለደገፏቸው ደስ አላቸው። ክፍሏን በጭብጨባ አሞቋት። ከዚያ በኋላ ‹‹እንጠብቅ›› በሚሉትና ‹‹ወደሚቀጥለው እርምጃ እንሂድ›› በሚሉት መካከል ጠንካራ ክርክር ተደረገ።ሆኖም ስብሰባው ያለስምምነት ተቋጨ። በማግስቱ በምሽት በዚያው ሥፍራ ‹‹ያስታርቁን›› በማለት እነፊታውራሪ አመዴ ለማና ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦችን ‹‹እንጠብቅ›› በሚሉት ወገን ጥሪ ተደርጎላቸው በሥፍራው ተገኙ። ሁለቱም ወገኖች ሐሳባቸውን አቀረቡ። ክርክሩ ጦፈ። ሽምጋዮቹ የሁለቱንም ወገኖች ሀሳብ አደመጡ። ፊት አውራሪ አመዴ ለማ የወጣቶችን ሐሳብ ደግፈው ‹‹ፈራ ፈራ እያሉ አብዮት አይካሄድም! መጠበቅ የለብንም!››› ሲሉ ተናገሩ። ወጣቶቹ በጭብጨባ ተቀበሏቸው። ልክ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ ‹‹ጊዜ ይሰጠው፣ እንጠብቅ›› የሚለው ሐሳብ ውድቅ ሆነ። በአሜሪካን አገር ተምሮ የመጣው አሕመድ ቀሎ በዚያ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ያገኘውን ልምድ ተጠቅሞ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ በራሪ ወረቀት በመበተን ይሳተፍ የነበረው በሙስሊሙ እንቅስቃሴ የመሪነቱን ሥፍራ ያዘ። በሙስሊሙ እንቅስቃሴ ውስጥ ከዚያ በፊት ጉልህ ሚና ባይኖረውም ከተቀመጠበት በመነሳት ‹‹ከአሁን በኋላ እዚህ አባድር ኢንስቲትዩት የተዘጋ ቤት ውስጥ ሳይሆን የምንሰበሰበው በግልፅ መስጂድ መሆን አለበት። ነገ በአንዋር መስጂድ ስብሰባ ጠርተናል›› ሲል ተናገረ። በማግሥቱ ጠዋት ከ 500 እስከ 1000 ሙስሊሞች በአንዋር ቅጥር ግቢ ተገኙ። ከሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ቢሮ ፊት ለፊት ሙስሊሙ ሊያደምጥ ታደመ። የእስከ ዛሬው ሂደት ተብራራ። ሙስሊሙ በተክቢራ ግቢውን አቀለጠው። ለቀጣዩ ትግል ሀምሳ ተወካዮች ተመረጡ። ተወካዮቹም በተራቸው አመራራቸውን መረጡ። የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችን፣ ምሁራንን፣ መሻኢኾችን፣ ነጋዴዎችን እና ሌሎች ግለሰቦችን ያቀፈው ኮሚቴ ሥራውን ጀመረ። የኮሚቴው ውክልና እንዴት መስፋት እንደሚችል መምከር ያዙ። እንቅስቃሴያቸውን ሕዝባዊ መሠረት ማስያዝ እንዳለባቸውም ወሰኑ። በሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ቢሮ እየተገናኙ ውይይታቸውን ቀጠሉ። ‹‹መንግሥት ባይፈቅድም ሰልፍ መወጣት አለበት›› የሚል ሐሳብ ተነሳ። ‹‹ልታስጨርሱን ነው?›› ሲሉ የተደመጡም ነበሩ። ‹‹እንዴት ሙስሊሙን ማስወጣት ይቻላል? ከባድ እኮ ነው›› ወዘተ. የሚሉ ሐሳቦችም ተንሸራሸሩ። ሥጋት ለገባቸው ወገኖች ዶ/ር አሕመድ ቀሎ ‹‹መቶ ሺህ ሰው አስወጣለሁ!›› ሲሉ ገለጹ። የማይሆን ነው ከማለት በመነጨ ስሜት ‹‹መቶ ሰውም ከወጣ ትልቅ ነገር ነው›› ያሉም ነበሩ። ውይይቱ ጦፈ። ‹‹ሰልፍ ይወጣ›› የሚለው ሐሳብ ረታ። ውይይቱም ‹‹እንዴት ሰልፍ እናካሂድ?›› ወደሚለው ተሸጋገረ። ግና ‹‹እንዴት ያን ያህል ሕዝብ ማሰባሰብ ይቻላል?›› የሚለው ጥያቄ ፈታኝ ሆነ። የኮሚቴው አባላት፣ ምሁራኑ፣ ዑለማው፣ ነጋዴው፣ የመስጂድ ኮሚቴው… ሁሉም ያስባል። የመፍትሄው ሀሳብ ግን ጠብ አልል አለ። ግና ባልተጠበቀ ሁኔታ መላ ጠፍቶት የነበረውን ኮሚቴ ከጭንቀት የሚገላግል አንድ ግሩም ሐሳብ ቀረበ። ሐሳቡ የቀረበው ከምሁራኑ አልያም ከዓሊሞቹ አልነበረም፤ ከአንድ ተራ የቀን ሠራተኛ ሚስኪን ሙስሊም እንጂ። ግለሰቡ ‹‹አዲስ አበባ ውስጥ ያሉትን የእስላም እድሮች ዝርዝር ተዟዙረን እንለይ። ከዚያም የየእድሩን ሊቃነ መናብርት ስብሰባ ጠርተን እናወያያቸው። እነሱ ሕዝቡን ሁላ ሊጠሩልን ይችላሉ›› ሲል ሐሳቡን ገለጸ። ሁሉም የኮሚቴው አባላት በሐሳቡ ተደመሙ። ወዲያውኑ ስብሰባውን አቋርጠው የሙስሊሞችን ዕድር ለመመዝገብ በየአቅጣጫው ተበተኑ። ሀምሳ የሙስሊም እድሮችን ሥም ዝርዝር ይዘው ተመለሱ። ሊቃነ መናብርቱም ስብሰባ ተጠሩ። መጡም። ጉዳዩም ተብራራላቸው። ሐሳቡን ደገፉ። ሕዝቡንም ለመጥራት ቃል ገቡ። ከወጣቱ አካባቢ የመነጨው ሰልፍ የመውጣት ሐሳብ (አጀንዳ) የሁሉም ሆነ። የተቃወሙት ራሳቸው ይቅርታ ጠይቀው ከዝግጅቱ ተቀላቀሉ። ሰልፉን ለመጥራትና ለእንቅስቃሴው ሕዝባዊ መሠረት ለማስገኘት የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማማከሩ ቀጠለ። ከሽማግሌዎቹ አካባቢ ‹‹በፍፁም ሴቶች ሰልፍ ላይ መሳተፍ የለባቸውም!›› የሚል ሐሳብ ቀረበ። ሐሳቡ አጨቃጨቀ። ወጣቶቹ ተሳክቶላቸው የአዛውንቶቹን ሐሳብ አስቀለበሱ። የሰልፉ የአወጣጥ ስትራቴጂ ተነደፈ። ሕዝቡም በቀኑ እንዲገኝ የሚገልጽ የሰልፍ ጥሪ ወረቀት ተበተነ። በወረቀቱ ላይ የሰፈረው የጥሪ መልዕክት የሚከተለው ነበር፡- ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ ለምትገኙ ኢትዮጵያዉያን እስላሞች! ሰሞኑን በሕዝቡ መራጭነት የተቋቋመው ኮሚቴ በሕዝቡ ፍላጎት መሠረት ትዕይንተ ሕዝብ (ሰላማዊ ሰልፍ) የሚያደርግበትን መንገድ ካጠና በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል። ይኸውም፤ ምንም እንኳን እናት አገራችን በአሁኑ ጊዜ በኢኮኖሚና በሶሻል ችግር ላይ ያለች መሆኗ ቢታወቅም በኛ ኢትዮጵያዉያን እስላሞችና በአገሪቱም ላይ ያለውን ችግር የጋራ መፍትሄ ያስገኛል ብለን ያመንበትን ጥያቄ ለማቅረብ ጊዜውና ሁኔታው አስገድዶናል። ስለዚህ በአዲስ አበባ ከተማ የምትገኙ ነጋዴዎች፣ የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች፣ ተማሪዎችና በልዩ ልዩ የሥራ መስክ ላይ ያላችሁ ሁሉ ፆታን ሳይለይ ለዚሁ ለተቀደሰ ዓላማ እንድትሰለፉ ይሁን። ትዕይንተ ሕዝቡ ሚያዝያ 12 ቀን 1966 ዓ.
نمایش همه...
👍 72 34
‹‹አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ!የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?›› ክፍል ሁለት 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የዛሬ 50 አመት በ1966ዓል ልክ በዚህ ሳምንት እንዲህ ሆነ! 📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 13ቱ ጥያቄዎችና የሰልፉ መታሰብ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ‹‹ኢትዮጵያ ምን አደረገች? እንዲያውም ከሥር መሠረቱ በነብዩ ሙሐመድ ጊዜ የእስልምና ስደተኞችን ተቀብላ ለእስልምና ሃይማኖት መስፋፋት ምክንያት የሆነችው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ምን አድርጊ ብለው ነው የሚጨቀጭቋት?›› (ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ******************************************* የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ክርስትናን በግልጽም በሥውርም በየዘርፉ ሲደጉም እስልምናን መግፋቱ ሙስሊሙን አሳርሮታል። የአገሪቱ ሐብት ሢሶው ለቤተ ክህነት ሲታወጅ ሙስሊሙ ባይተዋር መደረጉ ከንክኖታል። ክርስትና በመገናኛ ብዙኃን ሲሰበክ ሙስሊሙ ሰብዓዊ መብቱ መነፈጉ ቆጭቶታል። ክርስትና በየ ት/ቤቱ በትምህርት መልክ ሲሰጥ ኢስላም መናቁ አሳዝኖታል። ከሁሉ በላይ በሕገ-መንግሥቱ የመንግሥት ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ክርስትና ሆኖ መደንገጉ የእግር ውስጥ እሳት ሆኖበታል። ሙስሊሞች እትብታቸው በተቀበረበት አገራቸው የርስት ባለቤት መሆን መነፈጋቸው ብግን አድርጓቸዋል። ክርስቲያን ሚሺነሪዎች ሙስሊሙን እምነት ያስለውጡ ዘንድ ከየአቅጣጫው ሲጎርፉ ሙስሊም ሚስዮናዉያን ላይ መግቢያው ተከርችሞባቸዋል። ይህን ሁሉ በደል ሙስሊሙ ላይ እያደረሰ የአፄው መንግሥት ‹‹የሃይማኖት ነጻነት አከበርኩ፤ ኢትዮጵያዉያን ያለ ልዩነት ተቻችለን የምንኖር ነን፤ ኢትዮጵያ የነጻነትና የዲሞክራሲ አገር ናት›› ወዘተ ሲል ያፌዝ ነበር። መንግሥት የሃይማኖት ነጻነት እንዳከበረ የሚገልጽ “Religious Freedom in Ethiopia” የተሰኘ መጽሐፍም በእንግሊዝኛና በዐረብኛ አሳትሞ ለዓለም አሰራጨ። ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ በሥውር ሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ሚኒስቴር እና ደህንነት መሥሪያ ቤት ከጸረ-ሙስሊም ሤራቸው አልተቆጠቡም ነበር። ሙስሊሙ ላይ በሚሆነው ነገር የተቆጩትና ከተለያዩ ት/ቤቶች የተውጣጡት ወጣቶች በአ/አበባ በአባድር ኢንስቲትዩት መዋለ ሕፃናት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠዋል፤ የሙስሊሙ መብት የሚከበርበትን ዘዴ ለመማከር ስብሰባ የተቀመጡት በሕቡዕ (በምስጢር) ነበር። (ከዶ/ር አሕመድ ቀሎ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ፣ 2001፣ አ/አ፣ ኢትዮጵያ) የሙስሊሙን መብት ለማስከበር ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይመክራሉ። የተለያዩ ሙስሊም ግለሰቦች እየተጨመሩበት ለተከታታይ ቀናት ስብሰባው ቀጠለ። በወቅቱ ‹‹ለጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው ደብዳቤ እንጻፍ›› በሚል ሐሳብ ላይ ከስምምነት ይደርሳሉ። ይህ የመብት ትግል በአንዋር መስጂድ በወጣት ክበቡ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ይፋ ሆነ። ‹‹ችግሮቻችንን ለመቅረፍ ለመንግሥት አቤቱታ እንጻፍ እና ትግል እንጀምር›› የሚለውን ሐሳብ ያደመጠው የዝግጅቱ ታዳሚ ‹‹አላሁ አክበር!›› እያለ ብሶቱን አስተጋባ። ‹‹የግድ አንድ ነገር አሁኑኑ መደረግ አለበት›› ተባለ። በቁጣና በወኔ የተነሳውን ሙስሊም ወጣት አሕመድ ቀሎ እና ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ አረጋጉ። ሐጂ ሙሐመድ ኢብራሒም ዐብዱሰላምም በመምከር ሙስሊሙ ተረጋግቶ ጉዳዩ ፈር እንዲይዝ አደረጉ። ጉዳዩን የሚያስተባብር አንድ ኮሚቴ ተዋቀረ። ኮሚቴውም ‹‹የሙስሊሙን ችግሮች አጥንቶ በጽሑፍ ከነመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርብ›› ተብሎ ተወሰነ። ኮሚቴው የሚከተሉትን ግለሰቦች ያቀፈ ነበር፡- 1. አቶ ሙሐመድ አወል ከቴሌ ኮሚውኒኬሽን 2. አቶ አሕመድ ቀሎ (ዶ/ር) ከአውራ ጎዳና መሥሪያ ቤት 3. አቶ ዐብዱ አደም - የግል ኩባንያ ባለቤት 4. አቶ ዩሱፍ አሕመድ ዐሊ - የኢንዶ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሀላፊ 5. አባቢያ አባጆቢር አባዱላ አባጂፋር - የሕግ ጠበቃ 6. ወጣት ኸሊል ዐብዱ - ከወጣቶች ክበብ 7. ወጣት ሙሐመድ ሐሰን - ከወጣቶች ክበብ የኮሚቴው አባላት በተለያዩ ግለሰቦች ቤት ውስጥ በድብቅ ስብሰባ ጀመሩ፤ በተደጋጋሚ በመገናኘት ከአሥር ጊዜያት በላይ ተሰበሰቡ። ‹‹የሙስሊሙ አበይት ችግሮች ናቸው›› የሚሏቸውን ጥያቄዎች የያዘ ረቂቅ አዘጋጁ። ረቂቁም ከአባት ኮሚቴዎች ዘንድ ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት። የመጨረሻው ረቂቅም ተዘጋጀ። ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው ቢሮም ቀጠሮ ተያዘ። አሥራ ሦስት ጥያቄዎች የሠፈረበት ባለ አራት ገጽ ጽሑፍ ሚያዚያ 1 ቀን 1966 ዓ.ል ቀረበ። ውይይትም ተካሄደበት። በወቅቱ አንገብጋቢ የነበሩት 13ቱ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ፡- 1. በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠው የሃይማኖትና የሞራል ትምህርት የአንዱን ክፍል ሃይማኖት የተከተለ እንደመሆኑ እስላሞች ልጆቻቸው ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ በመፍራት ወደየት/ቤቶች ሳይልኳቸው በመቅረቱ በዘመናዊ ትምህርት ያለንን ተካፋይነት አዳክሞታል። 2. በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍለ አገሮች የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲኖረው ስለማይፈቀድለት ኢትዮጵያዉያን በሕግ ፊት እንዲኖራቸው የተወሰነው በእኩልነት የንብረት ማፍራት መብት በከፊል ተነፍገዋል። 3. በሕገ መንግሥቱ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ‹‹ማኅበር የማቋቋም መብቱ የተጠበቀ ነው›› ቢባልም በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የተቋቋመው ማኅበር ባለመፈቀዱና ከዚህም የተነሣ ኢትዮጵያዉያን እስላሞች በኢንተርናሽናል ደረጃ በሚካሄዱ የእስላም ሃይማኖት ተከታዮች በስብሰባዎች እንዳንካፈልና ከጊዜው አስተሳሰብ ጋር እንዳንራመድ አድርጎናል። 4. እንግዲህ የመንግሥቱ አመራር መሠረቱ ከሃይማኖት የታበለ እንዲሆን ይህ ሁሉ ችግራችንና ቅሬታችን መፍትሄ እንደሚገኝለት እናምናለን። (መንግሥት እና ሃይማኖት እንዲለይ) 5. ምናልባት የመንግሥቱ አመራር ሃይማኖትን መሠረት ከማድረግ የማይታበል የሆነ እንደሆነ ከላይ እንደተጠቀሰው ጉዳዩ የሚመለከተው የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆችና ሌሎችም ከዚሁ ጋር የተያያዙ ድንጋጌዎች የማይለወጡ ከሆነ በኢትዮጵያ ዜጎች መካከል ልዩነት በማይፈጥር ሁኔታ የኛም ሃይማኖት የመንግሥቱን ድጋፍ የሚያገኝ ለመሆኑ በሕጉ ይረጋገጥልን ዘንድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲፈጸሙልን እንጠይቃለን፡- 1. የእስልምና ሃይማኖት የመንግሥቱ ድጋፍ እንዲኖረው በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ በጽሑፍ ሠፍሮ በሥራም ተገልፆ እንድናይ እንዲደረግልን። 2. ኢትዮጵያዉያን እስላሞች በእስልምና ሃይማኖት የሊቃውንት ጉባዔ በጠቅላላውም የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መራጭነት የእስልምና መሪዎች ሙፍቲዎቹና ረዳቶቹ የመንፈሳዊውን ጉዳዮች እንዲመሩ በንጉሠ ነገሥቱ እንዲፀድቅልንና የአስተዳደሩም ድርጅት በሕግ እንዲመራልን፣ ለዚሁም መተዳደሪያ መንግሥት በጀት እንዲመድብልን። 3. የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በ 1936 ዓ.ም በቁጥር 62 በወጣው አዋጅ ለብዙ ዘመናት ሲሠራበት ቆይቶ ባላወቅነው ምክንያት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 33447 ንዑስ ቁጥር አንድ (1) በመለወጡና አሠራሩም የሕግ ድጋፍ የተነፈገው ስለሆነ አሁን የሸሪዓ ፍርድ ቤት ቅዱስ ቁርኣናችን በሚያዘው መሠረት አንድ ራሱን የቻለ አቋም ኖሮት በመንግሥት በጀት እየተዳደረ፣ ሕግጋት ተደንግገውለት፣ ወግና ሥርዓት ባለው አኳኋን በእምነቱ ተከታዮች እንዲመራ ተሻሽሎ በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ ተጠቅሶ እንዲወጣልን። 4. የእስላም ሃይማኖት ተከታዮች በዓላት የሕዝብ በዓላት ሆነው እንዲከበሩ እንዲታወጅልን። 5.
نمایش همه...
👍 108 46
ወጣት ወንዶች እስላም ማኅበር (ወ.ወ.እ.ማ) እና ወጣት ሴቶች እስላም ማኅበር (ወ.ሴ.እ.ማ.)፣ ሌሎችም የመሳሰሉትን ማኅበሮች ለማቋቋም እንድንችል በነጋሪት ጋዜጣ እንዲታወጁልን። 6. በጠቅላላው የመሬት ሥሪት መሻሻል አለበት ብለን እናምናለን። አሁን እንደተያዘው የመሬት ይዞታው በሚሻሻልበት ደረጃ ሥሪቱም አብሮ መሻሻል ይኖርበታል። እዚህ ላይ እንደምሳሌ አድርገን ልንጠቅስ የምንፈልገው ኢትዮጵያዉያን እስላሞች በአንዳንድ ሥፍራዎች ላይ ባለርስት መሆን ቀርቶ ከሌላ ባዕድ አገር የመጡ ይመስል ለመኖሪያቸው ያህል እንኳን በግል ሐብታቸው ገዝተው ለመሥራት አይፈቀድላቸውም። ስለዚህ እንደዚህ ያለውን ሥሪት ፈጽሞ መቅረት አለበት። 7. ይህ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው የመሬት ሥሪት መኖር የሚያመራን ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ምን ጊዜም ከልሳናቸው የማይለዩትን ‹‹አገር የጋራ ነው፤ ሃይማኖት የግል ነው›› የሚለው አነጋገር ትርጉም እንደሌለው አባባልና በሥራም እንደማይገለጽ ስለሚያደርገው የንጉሠ ነገሥታችንን መሪ ቃልና ጥቅስ በሥራ የመገለጹ ጉዳይ ጊዜው አሁን ስለሆነ አዲሱ ካቢኔ በተለይ በዚሁ አባባል ተመርቶ እግብር (ተግባር) ላይ እንዲያውለው እንጠይቃለን። 8. በብዛት በንግድ፣ በእርሻና በመሳሰሉት የሥራ ዘርፎች ተወስነን የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን እስላሞች በመንግሥቱ ሥራ በመሳተፍ ለውዲቱ አገራችን ያለንን የሥራ ድርሻ እንድናበረክት፡- ሀ) በአገር አገዛዝ ለ) በፍርድ ሐ) በዲፕሎማቲክ መ) በወታደርና በጠቅላላው በመንግሥቱ የሥራ መስኮች ሁሉ በይበልጥ እንድንካፈል እንቅፋት የሚሆኑት ነገሮች እንዲወገዱልን፣ አዲሱ ካቢኔ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስድልን እንጠይቃለን። 9. ለእስልምና ሃይማኖት መስፋፋት መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን። ከሚደረጉልን ድጋፎችም አንዱን ለመጥቀስ ያህል የእስላም ሚሲዮን እንዲገባ ሙሉ ፈቃድ እንዲሰጥልን ነው። (እንደ ክርስቲያኑ ማለት) የሰበካም ባጀት እንዲመደብልንና ለስብከቱ የሚሠማሩ ሰዎች የሚሠለጥኑበት የኮርስ ዝግጅት እንዲደራጅልን። 10. በማንኛውም የመገናኛ ዘዴዎች ለምሳሌ እንደሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና በመሳሰሉት መገናኛዎች ሁሉ /እንደ ክርስትያኑ/ የእስልምና ሃይማኖት ስብከት ለማሠራጨት እንዲፈቀድልን። 11. ‹‹በኢትዮጵያ የሚገኙ እስላሞች›› እየተባለ በሬዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን፣ ወይም በማንኛውም የመገናኛ ዘዴዎች የሚነገረውን አነጋገር በኛ በኢትዮጵያዉያን እስላሞች ላይ እንደውጭ አገር ኮሚኒቲዎች በገዛ አገራችን የባዕድነትን ስሜት ስለሚፈጥርብን ይህ ዓይነቱ አነጋገር ፈፅሞ እንዲቀርና ምናልባትም ስለኛ የሚነገር ነገር ቢኖር በነዚሁ የመገናኛ ዘዴዎች ‹‹ኢትዮጵያዉያን እስላሞች›› ተብሎ እንዲነገር እንፈልጋለን። ይህም ለማለት ካሰኙን ምክንያቶች አንዱ ኢትዮጵያ ማንኛውም ሃይማኖት ከመግባቱ በፊት ኑራ፣ ዜጎችም ‹‹ኢትዮጵያዉያን›› ተብለው ሲጠሩ የቆዩባት አገር እንደመሆኗ መጠን የተለያዩ እምነቶች ስለገቡ ብቻ በኢትዮጵያዉያን መካከል ልዩነት ማድረግ ስለማይገባ የልዩነት መንፈስ ሊያሳድሩ የሚችሉትን የቃልም ሆነ የሥራ ድርጊቶች እንዲቀሩ ጨምረን ለመጠየቅ ነው። 12. በየትምህርት ቤቶቹ ሁሉ የሃይማኖት ትምህርት በፕሮግራም ውስጥ ገብቶ ይሰጣል። የሚሰጠውም ትምህርት የአንድ ወገን የሃይማኖት ትምህርት ብቻ ስለሆነ የእስልምና ሃይማኖት ትምህርቱም በካሪኩለም ውስጥ ገብቶ ከሌሎች የትምህርት ፕሮግራሞች ጋር ተያይዞ እንዲሰጥልን እንፈልጋለን። 13. /እንደ ክርስትናው ሁሉ/ መንግሥት በመላ የኢትዮጵያ ክፍለ ግዛቶች መስጊዶች ሊሠሩባቸው ከሚገቡ ሥፍራዎች ላይ መስጊዶችን እየሠራ ከነመተዳደሪያቸው እንዲያደራጅልን ስንለምን፣ እስከ አሁን በነበረው የመስጊዶች ይዞታ ሲሠራባቸው እንደቆየው ሁሉ በጠቅላላው መስጊዶች የሚተዳደሩት ከእምነቱ ተከታዮች ከሚገኘው መዋጮና ስጦታ ስለሆነ አገልግሎታቸውም ለምእመናኑ ከመሆኑም በቀር ሌላ የገቢ ምንጭ ስለሌላቸው ንብረታቸው ሁሉ ከማናቸውም ግብር ነጻ እንዲሆኑና ከውጭ ለሚያስመጡትም እቃ ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ እንዲደረግልን እንጠይቃለን። (የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2400/01/4) ይቀጥላል……..
نمایش همه...
206👍 103
👍 33 9
“ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሶደቃ ይሆንለታል” ረሱል ﷺ
نمایش همه...
258👍 59
ታላቁ አሊም ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በጠና መታመማቸው ተገለፀ! 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን ፣በመዲና ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁና በወሎ ከሚሴ እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዳአዋ በርካቶችን በማስተማር እና በሀገር ሽማግሌነት ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው ታላቅ አሊም ናቸው። ... ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ወቅት ህዝቡን በማሰተባበር ለተቸገሩ ወገኖች መሰረታዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ህዝቡን በጦርነት ውስጥ ሲታደጉ የቆዩ ቢሆንም ለሁለት አመታት በአዋሽ አርባ እና በከሚሴ እስር ቤት ታስረው እንደነበር ይታወሳል። ... እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ሰአት ህመሙ የጀመራቸው ሲሆን ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሀገረ በቱርክዬ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን፣አሁን ላይ የህክምና ወጪው ከቤተሰብ አቅም በላይ በመሆኑ በአሊሞች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተዊቀረ ኮሚቴ በተከፈተ አካውንት ድጋፍ እንድታደረግላቸው ጥሪ ቀርቧል። ... ድጋፍ ለማድረግ፦ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአካውንት :-1000392652788 የአካውንት ስም፦የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮምዩኒቲ ሰፖርት አካውንቱን የሚከታተሉ ኮሚቴዎች ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን ...
نمایش همه...
👍 162 75
“አምስቱ ሰላቶች፣ ከጁምዓ እስከ ጁምዓ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው ያሉትን ኃጢአቶች ያብሳሉ ታላላቅ ወንጀሎችን ሲቀር፡፡” ረሱል (ﷺ)
نمایش همه...
87👍 20
‹‹አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ! የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?›› 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 📌 የዛሬ 50 አመት በ1966 ዓል ልክ በዚህ ሳምንት እንዲህ ሆነ! 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ክፍል አንድ በእምነቱ ምክንያት መገፋቱ ሙስሊሙን አብግኖታል። የስውርና የግልጽ ሴራ ተጠቂነቱ ከንክኖታል። በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ የእግር እሳት ሆኖበታል። ኢትዮጵያ ለሙስሊሙ ከክፉ ከእንጀራ እናት በላይ ከፋችበት። ‹‹አገር የጋራ ሃይማኖት የግል›› በሚል የሽንገላ ቃላት ሊያሞኙት እየሞከሩ በተግባር ግን የሃይማኖት ነጻነት መነፈጉ አብግኖታል። ከትምህርት አራቁት። ሙስሊም በመሆኑ ብቻ በአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ድርብ ጭቆና ቀመሰ። አንድነቱን በማሳጣት እርስ በርስ እየተጠራጠረ እንዲኖር መደረጉ ቆጭቶታል። የዘመናት ብሶትና ቁጭት ለመብቱ ሊታገል ሙስሊሙን ግድ አሉት። ከትግል ሥልቶቹ አንዱ ሕዝባዊና ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ቁጣውንና ብሶቱን በማሰማት የመብት ጥያቄውን ሊገፋበት ወሰነ፤ ይህም በዕለተ ቅዳሜ ሚያዚያ 12 ቀን 1966 ዓ.ል በመዲናችን አዲስ አበባ በዓይነቱና በስፋቱ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ትዕይንተ-ሕዝቡ በኢትዮጵያም ሆነ በሙስሊሙ ታሪክ ጉልህ ሥፍራ ነበረው። ግና ተዘነጋ። በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉት ፈር ቀዳጅ ሆኖ ሳለ ቸል ተባለ። በሰልፉ ሙስሊሙ ብሶቱንና ቁጭቱን ገልጾ መብቱን ለማስከበር ነቅሎ ወጣ። መብቱንም መንግሥት ያረጋግጥለት ዘንድ አስገደደ። ‹‹የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነውና የግድ ልናውቀው ይገባል›› በሚል ታሪኩ ሰፋ ባለ መልኩ እንደሚከተለው ቀርቧል። የሰልፉ አቀነባባሪዎች እነማን ነበሩ? ለምን እና እንዴት ሊደረግ ቻለ? የወጣቱና የሙስሊሙ ተማሪ ሚና ምን ነበር? መነቃቃቱስ እንዴት ሊመጣ ቻለ? የሙስሊሙ ጥያቄዎችስ ምን ነበሩ? የወጣቶች ክበብ እና የዒድ ፓርቲ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ‹‹እስላሞች ተጨቁነዋል እየተባለ በኢትዮጵያ ብጥብጥ እንዲነሳ ብዙ ጊዜ በመገናኛ ብዙሃን ወቀሳ ይነገራል፡፡›› (ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) በአፄው ዘመን የመማር ዕድል ያገኙ ጥቂት ሙስሊም ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከ 1950ዎቹ ጀምሮ ‹‹የዒድ ፓርቲ›› በሚል በዒድ ቀን ይገናኙ ነበር። በዚያው ዝግጅት ላይ ስለ ኢስላም የሚያስተምራቸው ግለሰብ እየፈለጉ፣ እየተማማሩና እየተዝናኑ ዒድን ያከብሩ ጀመር። በጥቂት ሙስሊሞች የተጀመረው ይህ ሂደት ቀስ በቀስ ስለሙስሊሙ ተጨባጭ ሁኔታ እና መብት ወደመወያየት ገባ። የእርስ በርስ ግንዛቤያቸውን ማዳበሪያ መድረክ ሆኖ ቀጠለ። ይህ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) የተጀመረው የተማሪዎች የግንኙነት መድረክ ቀስ እያለ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ቀልብ ሳበ። ዐብዱ መስዑድና ሙሐመድ ሐሰን ከመድኃኒዓለም ትምህርት ቤት፣ ሙሐመድ ዩሱፍ ከልዑል መኮንን ት/ቤት እና አበጋዝና ዐብዶ በሽር ከተግባረ-ዕድ ትምህርት ቤት በጋራ በመሆን በ1964 ዓ.ል ‹‹የሙስሊም ወጣቶች ክበብ››ን አቋቋሙ። ብዙም ሳይቆይ የክበቡን ዓላማ የተረዱ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ከተለያዩ ት/ቤቶች ወደ ክበቡ በአባልነት ተቀላቀሉ። ክበቡም ከዒድ ፓርቲ ልምድ በመቅሰም በሙስሊም በዓል ቀናት ሙስሊሙ ተማሪ የሚገናኝበትንና የሚማማርበትን መድረክ ማዘጋጀቱን ተያያዘው። ከበዓል ቀናት ውጪም መገናኘትና መማማር እንዳለባቸው ተመካከሩ። ቋሚ የሚማሩበትንና ስለሙስሊሙ በደል፣ ስለመንግሥት ግልጽና ስውር ጸረ-ኢስላም ተግባራት፣ እንዲሁም የሙስሊሙ መብት የሚከበርበትን ቋሚ መንገድና አጠቃላይ መፍትሄ የሚገኝበትን ዘዴ ሊማከሩ ግድ ሆነ። ለመገናኘት የሚሆናቸው ስፍራ ሲታሰብ አንዋር መስጂድ ምቹ ሆኖ ታያቸው። የአንዋር መስጂድ አስተዳዳሪ የነበሩትን ሐጂ ዐብዱረሕማን ሸሪፍን ጠየቁ። እሳቸውም ወጣቶችን የሚያቀርቡ ነበሩና የመስጅዱን ቅጥር ግቢ ፈቀዱላቸው። ተማሪዎች በዚያ መገናኘት ጀመሩ። ሥፍራዋም ለክበቡ አባላት የስብሰባና የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎትን መስጠት ጀመረች። የስፖርት፣ የሥነ-ጽሑፍ፣ የሴቶች፣ የደዕዋና መሰል ንዑስ ኮሚቴዎችን አዋቀሩ። በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ቁጥር ያለው ሙስሊም ወጣት አንዋርን አጥለቀለቀ። በኢስላማዊውም ሆነ በዓለማዊው ትምህርት እውቀት ያላቸውን ግለሰቦች በየሳምንቱ መጋበዙን ተያያዙት። ሸኽ ሐሚድ ዩሱፍ፣ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ እና ሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሷዲቅ ዲናዊ ትምህርቶችን ለወጣቶች ያስተምሩ ጀመር። ሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ከዲናዊ ትምህርት ጎን ለጎን ስለመብታቸውና ስለሙስሊሙ ጭቆና ወጣቶቹን ማስገንዘቡን ተያያዙት። አባቢያ አባጆቢር ስለ ሕግ ሲያስተምሩ ጋዜጠኛ ሐጂ በሽር ዳዉድና ሙሐመድ ኢድሪስ የተለያዩ አርእስቶችን እየመረጡ ወጣቱን ያነቃቁ ጀመር። ሐጂ ዐብዱልከሪም ኑር ሑሴን እና ሐጂ ዑመር ሑሴንም የየራሳቸው ፕሮግራሞች ነበሯቸው። በሂደት የወጣት ክበቡ ከአንዋር መስጂድ ወጣ እያለ መድረክ ለመፍጠር ሙከራ አደረገ። አባቶች ግን ሥጋት ነበራቸው። ምክንያቱም እነሱ ‹‹የሰላም ማኅበር›› በሚል ሥያሜ አቋቁመውት የነበረው ድርጅታቸው በኃይለ ሥላሴ ደህንነቶች በሐሰት ተወንጅሎ መዘጋቱ ይቆጫቸው ነበርና ነው። የወጣት ክበቡ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ‹የዒድ ፓርቲ› አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በመተባበር አዳራሽ እየተከራየ ፕሮግራም በጋራ ማዘጋጀት ጀመሩ። መሰል የወጣት ክበቦች (ስብስቦች) በየአካባቢው ብቅ ብቅ አሉ። የወጣቱም ንቃተ-ሕሊና እየዳበረ ሄደ። የሕግ ባለሞያና ጠበቃ የነበሩት አባቢያ አባ ጆቢር (የጅማው አባጂፋር የልጅ ልጅ ልጅ ናቸው) በየቲያትር ቤቱ በሚዘጋጀው መድረክ በግልጽ ስለ ሙስሊሙ መብት መቀስቀሱን ተያያዙት። በዚህ ጊዜም ከደህንነት አባላት ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርስባቸው ነበር። የሙስሊሙ መብት መጣሱ እጅግ ይቆጫቸው ነበርና የደህንነትን ዛቻና ማስፈራሪያ ከቁብ አልቆጠሩትም። በደህንነት አባላት እንዳይታፈኑ በመሥጋት ወጣቱ እያጀባቸው ቤት ድረስ ይሸኛቸው ነበር። በ1964 ዓ.ል በሲኒማ ራስ በተዘጋጀው መድረክ ‹‹የእስልምና ማኅበራዊ ግዴታዎች ምንድናቸው?›› በሚል ርዕስ ንግግር አድርገዋል። ‹‹ኢስላም ሕግም፣ ንግድም፣ ፖለቲካም፣ ባህልም፣ ሥልጣንም፣ ማኅበራዊ ኑሮም፣ ሳይንስም፣ ሁሉንም ነው። አንዱን ነገር ብቻ ነጥለን የምንመራበት ሳይሆን ሁለንተናዊ ነው›› ሲሉ አስተምረዋል። ወጣቱ ስለ መብቱና እምነቱ፣ ስለ ሕልውናው እና አገሩ ይጨነቅ ዘንድ፣ እንዲሁም ለሙስሊሞች መብት መከበር መታገል እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል። ሌሎችም በተለያዩ አርእስቶች ሥር የየራሳቸውን ትምህርት ሰጥተዋል። በ1965 የዒድ ፓርቲና የወጣቶች ክበብ በጋራ በመሆን የአገር ፍቅር አዳራሽን ተከራይተው የትምህርት መድረክ አዘጋጁ። በመሰል መድረኮች ንቃተ-ሕሊናው የዳበረው ወጣት ስለሙስሊሙ መብት መጣስና አጠቃላይ ጭቆና ይማከር ያዘ። ዑለሞችንም ያማክር ቀጠለ።በመስጂድ መገናኘትና መወያየትን አዘወተረ። የመድኃኒዓለም፣ ተግባረ ዕድ፣ ኮሜርስ ት/ቤት እና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በይበልጥ ብርቱና ንቁ ተሳታፊ ነበሩ። ይቀጥላል……..
نمایش همه...
👍 370 149
44👍 17
ታላቁ አሊም ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በጠና መታመማቸው ተገለፀ! 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን ፣በመዲና ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁና በወሎ ከሚሴ እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዳአዋ በርካቶችን በማስተማር እና በሀገር ሽማግሌነት ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው ታላቅ አሊም ናቸው። ... ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ወቅት ህዝቡን በማሰተባበር ለተቸገሩ ወገኖች መሰረታዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ህዝቡን በጦርነት ውስጥ ሲታደጉ የቆዩ ቢሆንም ለሁለት አመታት በአዋሽ አርባ እና በከሚሴ እስር ቤት ታስረው እንደነበር ይታወሳል። ... እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ሰአት ህመሙ የጀመራቸው ሲሆን ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሀገረ በቱርክዬ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን፣አሁን ላይ የህክምና ወጪው ከቤተሰብ አቅም በላይ በመሆኑ በአሊሞች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተዊቀረ ኮሚቴ በተከፈተ አካውንት ድጋፍ እንድታደረግላቸው ጥሪ ቀርቧል። ... ድጋፍ ለማድረግ፦ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአካውንት :-1000392652788 ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን ...
نمایش همه...
10ሩ የቁርኣን ዓላማዎች 🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯 https://youtu.be/NwdPL6EJIms?si=1Kr8e21qN4u4MoUn
نمایش همه...
👍 82 67
“አትቆጣ ጀነት ይኖርሃል።” ረሱል (ﷺ)
نمایش همه...
482👍 126
“ሰዎች ቢያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህን ስትሆን አትስራው።” ነቢዩ (ﷺ)
نمایش همه...
567👍 186
“ከፆም፣ ከሰላት፣ ከሰደቃ በላጭና ደረጃው ከፍ ያለውን ተግባር አልነግራችሁምን? እንዴታ! ይንገሩን አሉ ሶሃቦች፦ ‘በሰዎች መካካል ማስታረቅ’ ነው አሉ።” ረሱል (ﷺ)
نمایش همه...
575👍 165
📌 ለወንድምህ ዱዐ አድርግለት “ወንድም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ አይመለስም። (ተቀባይነት አለው)።” ረሱል (ﷺ)
نمایش همه...
557👍 151
ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ! 🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢 በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ። እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት። እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል። እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት.... ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?! ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ። አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ ተጨባጫችንን እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?! ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።" [ሐሳቡ (አላህ ይዘንላቸውና)የዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ነው።] ©️ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን
نمایش همه...
395👍 177
🔴 የመንግስት ቢሮዎች ላይ የሙስሊሙ ቁጥር ለምን አናሳ ሆነ? 📌 T.me/ahmedin99
نمایش همه...
381👍 117