cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Mizan

#ለመጪው_ትዉልድ_በኩራት_የምናወርሳትን_ሀገር_ለመገንባት_የደርሻችንን_እንወጣ!!

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
649مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሸባሪው ሸኔ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ግድያ አወገዙ። አቶ ደመቀ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "በፀጥታ አስከባሪ አካላትና በህዝቡ የተባበረ እርምጃ በአሸባሪውና ፅንፈኛው ቡድን ላይ በደረሰበት ሽንፈትና ኪሳራ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎችን በአፀፋው እየወሰደ ይገኛል፡፡ በቅርብ ጊዜ በጋምቤላ አካባቢ ያደረገው ሙከራ ሲከሽፍበት በምዕራብ ወለጋ በጊምቢ አካባቢ ደግሞ በንፁሃን ዜጎች ላይ በተለይም በህጻናትና በሴቶች ላይ ያካሄደው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ እና ኢሰብዓዊ ነው" ብለዋል፡፡ "በተለያዩ አካባቢዎች ቡድኑ በወሰደው እኩይ የጥፋት እርምጃ ምክንያት በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ፤ በመንግስት በኩል ህግ የማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብለዋል፤ አቶ ደመቀ። "በቀጣይ ተጎጂ ቤተሰቦችን የማረጋጋት፣ የመደገፍ እና መልሶ የማቋቋም ስራ በትኩረት የሚሰራ ሲሆን፤ አሸባሪዎችን እና ጽንፈኞችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ሲሉም ነው አቶ ደመቀ በመልክታቸው የገለጹት። t.me/hanisje
نمایش همه...
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ። ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው፤ "በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሸባሪው ሸኔ በንጹሐን ወገኖች ላይ በፈጸመውን ግድያ የተሰማኝን ሀዘን እየገለጽኩ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁ" ብለዋል። t.me/hanisje
نمایش همه...
#update የመጀመሪያው የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉባዔው በአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና የልማት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል። ኮንፈረሱ የሚካሄደው ባሳለፍነው ወርኃ የካቲት ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግ ከሾመች በኋላ ሲሆን ጉባዔው የቀንዱ አገራት አንድነት እንዲጠናከር፣ ለረጅም ጊዜያት ግጭትና ብጥብጥ ባልተለየው ቀጣና ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ ቻይና ከአገራቱ ጋር በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎት ታላሚ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን በአጠቃላይ 8 አገራትን ያጠቃለለ የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና ነው። ቻይና በቀጣናው መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሲሆን አፍሪካን ከመካከለኛው ምስራቅ የሚያስተሳስረው የቤልትና ሮድ ፕሮጀክትም ግዙፉ ተጠቃሽ ነው። በጉባዔው የቀንዱ አገራት እና የቻይና መንግስት ልዑካን ታድመዋል። #Via_ThinkAbyssinia
نمایش همه...
በህንድ እና በባንግላዲሽ በጎርፍ መጥለቅለቅ የተነሳ ቢያንስ የ59 ሰዎች ህይወት አለፈ በህንድ እና ባንግላዲሽ በከባድ ዝናብና አውሎ ንፋስ በተከሰተ የመብረቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የ59 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተጎዱት ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል ተብሏል። የጎርፍ አደጋው በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሊባባስ እንደሚችል የአየር ንብረት ትንበያ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ይገኛል። የባንግላዲሽ መንግስት ባለስልጣናት የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ እ.ኤ.አ በ2004 በሀገሪቱ ከደረሰው አደጋ በኃሏ የከፋ ነው ሲሉ ገልፀውታል። ትምህርት ቤቶች ወደ ጊዜያዊ መጠለያነት የተቀየሩ ሲሆን ከውሃው መጨመር የተነሳ ከአጎራባች ነዋሪዎች ጋር የተቆራረጡ አባወራዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ወታደሮች ተሰማርተዋል።በህንድ አጎራባች አሳም ግዛት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ የተጎዱ ሲሆን በግዛቲቱ ለአምስት ቀናት ያለማቋረጥ ከፍተኛ ዝናብ ጥሏል። #Via_ዳጉ_ጆርናል t.me//hanisje
نمایش همه...
በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ኳስ ለማወጣት ወደ ወንዝ የገቡ ሁለት ታዳጊዎች ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አስር በተለምዶ ቀይ አፈር በሚባለእ አካባቢ አደጋው ከቀኑ 9ሰዓት ላይደርሷል። የዘጠኝ እና የአስራ አራት ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎቹ ኳስ እየተጫወቱ ሳለ ኳሱ ወደ ወንዝ ሲገባባቸው ለማውጣት በሚያርጉት ጥረት በውሃው ታፍነው መወሰዳቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። አንዱ ታዳጊ ወዲያው ህይወት ሲያልፍ ሁለተኛው ደግሞ ሆስፒታል ከገባ በኃላ ህይወቱ ማለፉን ተነግሯል፡፡ምክትል ኢንስፔክተር ማርቆስ የተያዘው የክረምት ወቅት በርካታ ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ መሆናቸውን እና የወንዞች ዳርቻ ጥንቃቄ ካልተደረገባቸው በርካታ ችግር ሊፈጥሩ እንሚችል በመግለፅ ወላጆች እና ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡ t.me//hanisje
نمایش همه...
በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ሁለት ታዳጊዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ኳስ ለማወጣት ወደ ወንዝ የገቡ ሁለት ታዳጊዎች ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አስር በተለምዶ ቀይ አፈር በሚባለእ አካባቢ አደጋው ከቀኑ 9ሰዓት ላይደርሷል። የዘጠኝ እና የአስራ አራት ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎቹ ኳስ እየተጫወቱ ሳለ ኳሱ ወደ ወንዝ ሲገባባቸው ለማውጣት በሚያርጉት ጥረት በውሃው ታፍነው መወሰዳቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። አንዱ ታዳጊ ወዲያው ህይወት ሲያልፍ ሁለተኛው ደግሞ ሆስፒታል ከገባ በኃላ ህይወቱ ማለፉን ተነግሯል፡፡ምክትል ኢንስፔክተር ማርቆስ የተያዘው የክረምት ወቅት በርካታ ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ መሆናቸውን እና የወንዞች ዳርቻ ጥንቃቄ ካልተደረገባቸው በርካታ ችግር ሊፈጥሩ እንሚችል በመግለፅ ወላጆች እና ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡ #Via_ዳጉ_ጆርናል t.me//hanisje
نمایش همه...
Mizan

#ለመጪው_ትዉልድ_በኩራት_የምናወርሳትን_ሀገር_ለመገንባት_የደርሻችንን_እንወጣ!!

የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ:: በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና መተዳደሪያን ማውደም ተቀባይነት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች፥ ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በሆነ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊትን መንግስት እንደማይታገስ አስታውቀዋል። ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደህንነትን መመለስ አሁንም ቅድሚያ የሚሰጠው ተግብር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። #Via_Ethio_fm t.me//hanisje
نمایش همه...
መግለጫ! ኢሰመኮ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመዘዋወር ላይ የሚገኘውን እና በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ በማድረግ በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ሁኔታ መርምሯል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየው ከሕግ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት ኢሰመኮ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ የአፋርና የአማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶችና የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ ምርመራ ሪፖርት” ላይ ከተዘረዘሩት ክስተቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ተረድቷል።  በዚሁ የኢሰመኮ የምርመራ ሪፖርት ከምስክሮች እና በስፍራው በመገኘት በመስክ ምልከታ ያሰባሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ፣ ድርጊቱ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ልዩ ቦታው እንቶሊ አካባቢ በታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት (ቀኑ በትክክል ያልታወቀ) መፈጸሙን፤ እንዲሁም በወቅቱ በነበረው መረጃ መሰረት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሁለት የጭነት መኪኖች ጭነው ያመጡዋቸውንና ወደ 30 የሚጠጉ የኦነግ ሸኔ አባሎች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች በጅምላ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን ይገልጻል።  ኢሰመኮ ተንቀሳቃሽ ምስሉን ከተመለከተ በኋላ ባደረገው ተጨማሪ ማጣራትና የቴክኒክ ምርመራ፣ በመስክ ምርመራ በለየው ስፍራና በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ያለውን ስፍራ በቴክኒክ ምርመራ በማነጻጸር፣ እንዲሁም ምስሉ የተቀረጸበትን ቦታ ለማነጻጸርና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቴክኒክ ምርመራዎችን በማድረግ፤ ከዚህ በላይ የተገለጸው በኢሰመኮ ምርመራ የተዘገበው ከፍርድ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት የሚያመለክት ተጨማሪ ማስረጃ ስለመሆኑ በምክንያታዊ አሳማኝነት አረጋግጧል ስለሆነም ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሟላ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በድጋሚ ያሳስባል።
نمایش همه...
ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ። በትላንትናው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ የሸሹ ስለመኖራቸውን ገልፀዋል። ከሟቾች መካከል ህፃናት እና ሴቶች እንደሚበዙ ፤ ቤቶች መንደዳቸውንም ፤ ጥቃቱ ሲፈፀም የነበረው በከባድ መሳሪያ ጭምር እንደነበር አመልክተዋል። ለሚመለከተው የወረዳው አካል በሰዓቱ ጥቃት መኖሩን ጥቆማ ቢያደርሱም በቶሎ የደረሰ አካል እንዳልነበረ አስረድተዋል። የትላንቱን እጅግ አሳዛኝ ጥቃት ክልሉም አምኖ አረጋግጧል። ጥቃቱን ጭካኔ የተሞላበትም ነበር ብሏል። ክልሉ ባወጣው መግለጫ " የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ባደረሰው ጥቃት በንጹሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል" ብሏል። "ቡድኑ መንግሥት እየወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት አድርሷል" ሲል ገልጿል። በቡድኑ ላይ የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉም ብሏል። ክልሉ ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ እንዲሁም ታፍነው ስለተወሰዱ ሰዎች ምንም ያለው ነገር የለም። #Via_tikvahethiopia t.me/hanisje
نمایش همه...
#AddisAbaba ነገ የሚዘጉ መንገዶች ! ( ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ድረስ) ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በመሰቀል አደባባይ ባዘጋጀው ስፖርታዊ ዝግጅት እና መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በሚያደርገው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ምክንያት ነገ እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ከ30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወሰዱ መንገዶች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የሚዘጉት መንገዶች ፦ 🛣 ከወሎ ሰፈር መገንጠያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ 🛣 ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን በሰዓት 50 እና 80 ኪ.ሜ በተፈቀደባቸው በሁለቱም አቅጣጫ 🛣 ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያአትር የሚወስደው የቀድሞ ደሳለኝ ሆቴል 🛣 ከንግድ ማተሚያ ቤት በኦርማ ጋራዥ በፍል ውሃ ወደ መስቀል አደባባይ ኦርማ ጋራዥ መስቀለኛው ላይ ከ4 ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ኮንሰን ወይም ወደ ሸራተን ሆቴል የሚወስደው መንገድ ላይ፡፡ 🛣 ከሳር ቤት አካባቢ ለሚመጡ አሸከርካሪዎች አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት 🛣 ከፒያሳ አካባቢ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ፖስታ ቤት ትራፊክ መብራት ላይ 🛣 ከካዛንቺስ በፍል ውሃ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ እና በተመሳሳይ ካዛንቺስ የትራፊክ መብራት በባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ የትራፊክ መብራት ላይ 🛣 ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ 🛣 ከቄራ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ጠማማ ፎቅ አካባቢ 🛣 ከጦር ኃይሎች ፣ በልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወሰደው መንገድ ባልቻ ሆስፒታል መስቀለኛ 🛣 ከመርካቶ በበርበሬ በረንዳ ወደ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው አረቄ ፋብሪካ አካባቢ 🛣 ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሸከርካሪዎች አጎና ሲኒማ አካባቢ 🛣 ከጎተራ በመሿለኪያ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ መንገዱ ይዘጋል ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል። ውድ ቤተሰቦቻችን ነገ እሁድ የሚያንቀሳቅሳችሁ ጉዳይ ካለ ከላይ በተገለፀው መረጃ መሰረት እንዳትጉላሉ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ። t.me/hanisje
نمایش همه...
Mizan

#ለመጪው_ትዉልድ_በኩራት_የምናወርሳትን_ሀገር_ለመገንባት_የደርሻችንን_እንወጣ!!