cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

TIKVAH-Ethiopia

Tikivia Ethio የሚያተኩረው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፣ኢኮኖሚያዊ፣ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የInformationእና የቴሌግራም ቻናል ነው። - አላማው ጋዜጠኝነት መተግበር ብቻ ነው። -ግቡ ድምፅ አልባ የሆኑ እውነቶችን ድምፅ እንዲኖራቸው አድርጎ ለህዝብ ማድረስ ነው።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
10 588مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ውጤቱን አልቀበልም " - ኦዲንጋ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት አልቀበለም ብለዋል። ትላንትና ሰኞ የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዊልያን ሩቶ ማሸነፋቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም። በቦማስ በተደረገው ስነስርዓት ወቅት ጭራሽ በማዕከሉ ያልተገኙት የሩቶ ተፎካካሪ ኦዲንጋ እስከ ዛሬ ከሰዓት ድረስ ስለ ምርጫው ምንም ሳይሉ ቆይተዋል። ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ የምርጫውን ውጤት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንደሌለውና እሳቸውም እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ሰው እንዲረጋጋ እና ህግ እንዲያከብር አሳስበዋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ራይላ ኦዲንጋ በመግለጫቸው ምን አሉ ? የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና በወቅቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚደገፉት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱ ሕጋዊ ያልሆነ እና ተፈጻሚ የማይሆን ነው ብለዋል። ኦዲንጋ በመግለጫቸው ፦ • ውጤቱን አልቀበልም ብለዋል። • ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል። • የኮሚሽኑን ዋና ሰብሰቢ ዋፉላ ቼቡካቲን " አምባገነን " ሲሉ በመጥራት ተችተዋቸዋል። ይፋ ያደረጉትንም ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ አንቀበለውም ሲሉ ገልፀዋል። • የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ የምርጫ ውጤቱን ይፋ ሲያደርጉ የአገሪቱን ሕገ-መንግሥት በመተላለፍ ትልቅ የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል ብለዋል። በኮሚሽነሮች መካከል ልዩነት እያለ ዋፉላ ቼቡካቲ የምርጫ ውጤቱን ይፋ ማድረጋቸው ስህተት ነው ሲሉ ገልፀዋል። NB. የኬንያን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ያስፈጸመው ገለልተኛ የድንበር እና ምርጫ ኮሚሽን 7 ኮሚሽነሮች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ መካከል 4ቱ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ አለመስማማታቸውን ትላንት መግለፃቸው ይታወሳል። ከፍተኛ ደጋፊ ያላቸው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ማለታቸው በአገሪቱ ምርጫውን ተከትሎ ግጭት እንዲቀሰቀስ ሊያደርግ ይችላል የሚሉ ስጋቶች ከአሁኑ አይለዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-MAGAZINE
በአዳማ ከተማ በኮንትራክተርነት ብቻ በሚንቀሳቀሱ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ። የአዳማ ከተማ የትራንስፖርት ባለስልጣን ከአቅም በላይ በሚጭኑ፣ ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ፣ ከተሰማሩበት መስመር ውጪ በሚሰሩና በኮንትራክተርነት ብቻ በሚንቀሳቀሱ ባጃጅ እና ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የትራንስፖርት አገልግሎትን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባጃጅ አሽከርካሪዎች እና ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርጓል። በዚህ ወቅት፥ የትራንስፖርት አገልግሎት መመሪያን አክብረው በማይሰሩት ላይ ያለምንም መደራደር እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የባለስልጣኑ ኃላፊ አቶ አደም ፋቆ ገልጸዋል። Via @tikvahethafaanoromoo @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-MAGAZINE
የነዳጅ ድጎማ ከተጀመረበት ከሰኔ 29 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የቀረቡ የቁጥር መረጃዎች፦ ⛽️ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ለማስጀመር እንደ ሀገር 1ሺ 93 ማደያዎችን በቴሌ ብር ለመመዝገብ ታቅዶ 1ሺ 14 ማደያዎችን መመዝገብ ተችሏል፤ 📲 በቴሌ ብር ከተመዘገቡት መካከል 716 ማደያዎች ማለትም 70 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ማደያዎች ወደ ሥራ ገብተዋል፤ 💵 የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ኪሣራ ማዳን ተችሏል፤ 🤳 በቴሌ ብር ሥርዓት ውስጥ ከገቡ 144ሺ 730 ተሽከርካሪዎች መካከል የድጎማ ነዳጅ ተጠቃሚ መሆን የቻሉት 40ሺ 147 ወይም 27 ነጥብ 7 በመቶ ብቻ ናቸው፤ ⛽️ በደቡብ ክልል 132 የነዳጅ ማደያዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 130ዎቹን መመዝገብ ተችሏል። ከዚህም መካከል 103 ወይም 79 ነጥብ 2 በመቶዎቹ በሥራ ላይ ይገኛሉ ተብሏል። * ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከደቡብ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተወያየበት ወቅት የቀረበ ሪፖርት @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-MAGAZINE
ፎቶ 📸: ነሐሴ 10፤ 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የተለዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አምስተኛው ፓትርያሪክ እንዲሁም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትን ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣ የዓለም የሰላም አምባሳደር የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀደማዊ ኅልፈት 10ኛ ዓመት መታሰቢያ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ውሏል። @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-MAGAZINE
የአዋሽ 90.7 ኤፍኤም ሬድዮ ሥርጭት ተቋረጠ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አዋሽ ኤፍኤም ራዲዮ ጣቢያ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች የሆኑ አራት የንግድ ቤቶችን ከ10 ወራት በላይ ወርሐዊ ኪራይ ከፍያ ሊከፍል ባለመቻሉ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ካስታወቀ በኋላ ዛሬ የአዋሽ 90.7 ኤፍኤም ሬድዮ ሥርጭት መቋረጡንና ቤቱም መታሸጉ ተገልጿል። ኮፕሬሽኑ፥ አዋሽ ኤፍኤም ራዲዮ ጣቢያ በንግድ ሕጉ መሰረት በ‘‘ንግድ ድርጅት ሽያጭ’’ ከኮርፖሬሽኑ የቀድሞው ተከራይ ከዛሚ ሬዳዮ ጣቢያ ‘‘መልካም ስም’’ በመግዛት ቀድሞ ዛሚ ራዲዮ ጣቢያ ሲጠቀምባቸው የነበሩ አምባሳደር ሕንጻ ላይ የሚገኙ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች የሆኑ አራት የንግድ ቤቶችን አዋሽ ኤፍኤም ራዲዮ ጣቢያ በሚል ስያሜ ሁለቱ ድርጅቶች የፈጸሙትን የ‘‘ንግድ ድርጅት ሽያጭ’’ ውል በውልና ማስረጃ አጽደቀው ለኮርፖሬሽኑ በማቅረብ ጣቢያው ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሷል። በትላንትናው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ባወጣው መግለጫ ''የራዲዮ ጣቢያውን በተመለከተ በመመሪያው መሰረት ሕጋዊ አሰራሮችን ተከትሎ ሕግ የሚያስከብርም ይሆናል፡፡'' ብሎ ነበር። በተጨማሪም ጣቢያው የብሮድካስት አዋጁን በጣሰ መንገድ ያለአግባብ የኮርፖሬሽናችንን መልካም ስም ለማጉደፍ እንቅስቃሴ ላይም ነበር ሲል ወቅሷል። ያልተገቡ እንቅስቃሴዎችን ኮርፖሬሽኑ በሕግ አግባብ ክስ በመመስረት እንዲታዩ ለማድረግ እንደሚገደድ አሳስቦ ነበር። @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-MAGAZINE
#YALI2023 የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎ ሺፕ ፕሮግራም የ2023 (Mandela Washington Fellowship) ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል። በአህጉሪቱ ያሉ ወጣት መሪዎች ተወዳድረው በአሜሪካ በሚደረግ ሥልጠና ላይ እንዲሳተፉ እድሉ ተመቻችቶላቸዋል። ከዚህ ቀደም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወጣት መሪዎች እድሉን ተጠቅመው ይህንን ሥልጠና ወስደዋል። በዚህ ሥልጠና ለመሳተፍ የሚናስፈልጉ መስፈርቶችን ለማየትና ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👉 https://www.mandelawashingtonfellowship.org/apply/ @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
نمایش همه...
በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት ፖሊሲ ከቅድመ 1ኛ እስከ 8ተኛ ክፍል ድረስ ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ እንደሚሆን ተገለጸ‼️ በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የሚሰጥ ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ እንደሚደረግ፤ በሚኒስቴሩ የሥርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ ለኢቢሲ ገልጸዋል። ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው፤ መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልፀዋል። በጥናቱ ሂደት ላይ ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር በተለየ ከውጭ በመጡ ባለሙያዎች ጥናቱን ከማሰራት ይልቅ፤ በአገር ውስጥ ባሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናቱ እንዲከናወን መደረጉን ተናግረዋል። በስድስት ዘርፎች ተከፋፍሎ በተካሄደው በዚህ ሰፊ ጥናት፤ በመሰረታዊነት ቅድመ መደበኛና የአንደኛ ደረጃ፣ ኹለተኛ ደረጃ፣ የመምህራን ሥልጠና፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት፣ የከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚያካትተው የትምህርት ሥርዓት በተለያየ ቡድን እንዲጠና መደረጉን ኃላፊው ገልፀዋል። በጥናቱ መሰረት በነባሩ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ የጥራት ችግር፣ የሰው ሀብት ስብዕና ግንባታ ጉድለቶች፣ ከገበያው ፍላጎት ጋር አለመጣጣም፣ የመምህራን ብቃት ማነስ፣ በቴክኖሎጂ አለመደገፍ እና ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት የዘርፉ ቁልፍ ችግሮች ሆነው መለየታቸውን አስረድተዋል። በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ አንድ አካል በሆነው ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የተዘጋጀውን የአሰራር ማዕቀፍ መሰረት በማድረግ፤ ከ2014 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴርና በክልል የትምህርት ቢሮዎች ትብብር የመማሪያ ማስተማሪያ መፀሃፍት በማዘጋጀት ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የሙከራ ትግበራ መካሄዱንም ኃላፊው ተናግረዋል። በዚህ መነሻነት የሙከራ ተግባሩን መሰረት በማድረግ በ2015 ወደ ሙሉ ትግበራ ለመሻገር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ዶ/ር ቴዎድሮስ ጠቁመዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
نمایش همه...
ሼር/share
በአዳማ ከተማ በኮንትራክተርነት ብቻ በሚንቀሳቀሱ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ‼️ የአዳማ ከተማ የትራንስፖርት ባለስልጣን ከአቅም በላይ በሚጭኑ፣ ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ፣ ከተሰማሩበት መስመር ውጪ በሚሰሩና በኮንትራክተርነት ብቻ በሚንቀሳቀሱ ባጃጅ እና ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የትራንስፖርት አገልግሎትን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባጃጅ አሽከርካሪዎች እና ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርጓል። በዚህ ወቅት፥ የትራንስፖርት አገልግሎት መመሪያን አክብረው በማይሰሩት ላይ ያለምንም መደራደር እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የባለስልጣኑ ኃላፊ አቶ አደም ፋቆ ገልጸዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
نمایش همه...
ሼር/share
Repost from Top Mereja
ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል በሚል ምክንያት የሦስት ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የገደለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣች‼️ ትዕግስት አዘዘው የተባለቸው ግለሰብ ወንጀሉን የፈፀመችው መስከረም 10 ቀን 2014 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አንቆርጫ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ተከሳሿ በዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የ3 ልጆቿ አባት የሆነው ባለቤቷን ሟች አወቀ ይርዳውን "ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል፤የተለያዩ ሴቶችንም በስልክ ታናግራለህ" በሚል ምክንያት ሶፋ ላይ በተኛበት ጭንቅላቱን በመጥረቢያ ደጋግማ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጓን በአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ከሰው መግደል ወንጀል ምርመራ ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ግለሰቧ በፈፀመችው ወንጀል በቁጥጥር ሥር ውላ ምርመራ ከተጣራባት እና ክስ ከተመሰረተባት በሗላ፤ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የከባድ ውንብድና እና ግድያ 1ኛ ወንጀል ችሎት በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ጥፋተኛ መሆኗን በማረጋገጥ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 @TopMereja @TopMereja
نمایش همه...