cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Injibara University

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
11 452
مشترکین
+124 ساعت
+167 روز
+11730 روز
آرشیو پست ها
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ ያዘጋጀው ልዩ የበዓል መስተንግዶ። መልካም በዓል! ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን አደረሳችሁ። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የእስልምና ተከታዮች በሙሉ   እንኳን  ለ1445ኛ ዓመት ኢድ-አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል። መልካም በዓል!
نمایش همه...
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
نمایش همه...
የተሻሻለ የድንች ምርጥ ዘር የማባዛት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተሻሻለ የምርጥ ዘር ድንችን የማባዛት ሥራ እያከናወነ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ክንዴ ብርሃን ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ክንዴ ባለፈው ዓመት የድንች ዘሩን ከሌላ ቦታ በማስመጣትና በማባዛት ለምግብ ፍጆታ እና ለዘር ብዜት አገልግሎት ላይ እንደዋለ ጠቅሰው ከዚህ ምርጥ የድንች ዘርም የግል ድርጅቶችም(NGO) ጭምር በመግዛት ለአርሶ አደሮች ያሰራጩበት ሁኔታ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ በዛሬው እለትም ይህንን ምርጥ ዘር ድንች በአካባቢው ለማባዛት እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የድንች ዘር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ሳይንስ ት/ት ክፍል ኃላፊ የሆኑት መምህር ዘላለም ካሳ በበኩላቸው 1.5 ሄክታር ለድንች ተስማሚ በሆነ መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ባለፉት በሦስት ዓመታት የተለያዩ ወረዳዎች ላይ “ጉደኔ” እና “በለጠ” የሚባሉ የድንች ዝርያዎች ላይ የምርምር ስራ ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡ በተሰራው የብዜት ሥራም አመርቂ ውጤት የተገኘበት እና ለዘር ብዜት፣ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም ለአካባቢ ለፕሮጀክት በመሸጥ ገቢ እንደተገኘበት አስረድተዋል፡፡ ለወደፊቱም ከዩኒቨርሲቲው አልፎ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
نمایش همه...
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት መድሃኒት ድጋፍ አደረገ፡፡ -------- የኒቨርሲቲው ከ172 ሽህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የእንስሳት መድሃኒቶችን ለአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እንስሳት እና አሳ ሀብት ልማት ተጠሪ ጽህፈት ቤት ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ያስረከቡት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) እንደገለጹት ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች ግብርናና አረንጓዴ ልማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ የእንስሳት እርባታን እና ጤናን ለማገዝ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው በአስቸጋሪ ወቅትም ቢሆን የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው በዛሬው ዕለት የእንስሳትን ጤናን ለማሳደግ የሚያገለግሉ ከ172 ሽህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የተለያዩ መድሃኒቶችን ድጋፍ ማድረጉንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡ https://www.facebook.com/share/p/y99d1i9auRVhgoZV/?mibextid=oFDknk
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጆርናል (Injibara Journal of Social Science and Business/IJSSB) ላይ ያላችሁን የምርምር ሥራ ማሳተም የምትፈልጉ አመልካቾት የምርምር ሥራዎችቻችሁን  ከታች በተቀመጠው ሊንክ እና መረጃ መሰረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ https://www.inu.edu.et/ijssb-author_guideline/
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ------ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከታች በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ከታች በተገለጸው አግባብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
نمایش همه...
#ማስታወቂያ ለኤክስቴንሽን ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቅዳሜና ዕሁድ (Weekend Extension) መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከየካቲት 15 - 30/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች እና የመግቢያ መስፈርቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡
نمایش همه...
የልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡ 6ኛ ዓመት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የሰላም ኮንፈረንስ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡  በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የሰላም ኮንፈረንሱ ዓላማ የተቋሙን እና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ግንኙነት ለማጠናከርና በጥናት ተመስርቶ የልማት ተነሺዎችን ችግር ለመፍታት እና ድጋፍ ለማድረግ ነው ብለዋል። ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/share/p/xAbtFtMzPznWTfr3/?mibextid=ZbWKwL
نمایش همه...