#አንጎልና
#አዕምሮ
***********
በማህበረሰቡ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላት ናቸው፥ አንጎልና አዕምሮ። አንዳንዴም ቦታ በመለዋወጥና በተቃራኒው ጥቅም ላይ ሲውሉ ይታያል። በተለይ ድግሞ በአዕምሮ ቦታ፤ “ፈጣሪ ልቦና ይስጠን! …….,” አላህ ቀልብ ይስጠን!...... ህሊና የተለገሱ……! አቅልን መጠቀም ያስፈልጋል.,……. !” እያልን በየእለት ተለት ውሏችን የምንጠቀማቸው ዓረፍተ ነገሮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አዕምሮን ያመላክታሉ። እኔም በአንጎልና በእዕምሮ መካከል ያለውን ልዩነት እንደሚከተለው ለማጠናቀር ሞክሪያለው።
#አንጎል(brain)
1)አንጎል 171 ቢሊዬን በሚደርሱ የተለያዩ ሴሎች የተገነባ
ውስብሱ የነርቭ ሥርዓታችን ማዕከል ነው።
2) በዋነኛነት ወደ 86 ቢሊዬን ከሚደርሱ የነርቭ ሴሎች የተገነባ ሲሆን ሌሎች አጋዥ ሴሎችና የደም ስሮችንም ያካትታል።
3) የተወሰነ ቅርጽ እና መዋቅር ስላለው የሚታይ የሚዳሰስና
የትኛው ክፍል ለምን እንደሚያገለግል ይታወቃል።
4) አንጎል የሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎችን የመረጃ መለዋወጥ ስርዓትንበመዘርጋትና በማስተናበር ህልውናችን እንድትቀጥል ያደርጋል።
#አዕምሮ(mind)
1) የሰው ልጅ ሲወለድ ለመማር ዝግጁ ከሆነ ባዶ አዕምሮ ጋር ነው። ከዛ ቦኋላ ነው ከወላጅና ከአከባቢው በሚያገኙት ግብዓት አዕምሯቸው እየተቀረጸ በአዕምሮ ተግባራቶች እራሱን የሚገልጸው። አዕምሮ የሚያዝ የሚጨበት አካል ባለመሆኑ፤ በማስተዋል፣ በእሳቤ፣ በሚሰማን ስሜት፣ በማመዛዘን፣ በማስታወስና በመሳስሉት የአዕምሯዊ ተግባራት እራሱን ይገልጻል።
2) እንዲያውም አንዳንድ የስነ አዕምሮ ባለሞያዎች ኢነርጂ ነው ይላሉ። እንደዛ ከሆነ ደግሞ ለምን ከአንጎል ጋር ብቻ ተጣመረ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ከሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛውን ኢነርጂ የሚያመነጨው ልባችን ነው።
#ልባችን፥ አንጎላችን ከሚያመነጨው ከ40% የሚበልጥ የኤሌክትሪክ ኢነርጂ የማመንጨት አቅም እንዳለው ተረጋግጧል። በዚህም የተነሳ የልባችን የሃይል መስክ(energy field) ከሰውነታችን ከተወሰነ ርቀት ላይም እንደሚገኝ ተረጋግጧል። ይህ ማለት ደግሞ ከአንጎል በተጨማሪ ልባችንም በልቦና በኩል ግብዓት ያቀርባል ማለት ነው።
3) አዕምሮ አንጎልን ይጠቀማል፤ አንጎል ደግሞ ከአዕምሮ የሚመጣለትን መረጃ በመጠቀም እራሱን የመለወጥ ሂደት ሊያካሂድ ይችላል። ሰዎች ተግባራቸውን ይመርጣሉ፤ ያለ አእምሮ ምንም አይነት የንቃተ ህሊና ተሞክሮ አይኖረንም፤ ነገር ግን ሁሉም ተሞክሮ የአንጎል ተግባር ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም። ምክኒያቱም በልባችንና በሆዳችን የሚሰማን ስሜቶች ከአዕምሯችን ጋር እንደሚገናኝ በተለምዶ ብናውቅም ይህን የሚያመላክቱ ጥናቶችም ብቅ እያሉ ይገኛሉ።
ባጠቃላይ አዕምሮ ከየት መጣ ከተባለ ከአንጎል ማለት ይቻላል። ነገር ግን ከአንጎል ብቻ ከተባለ አይ ልብና ሌሎች አካላትም … … አስተዋፆ ያደርጋል።
#ማሳሰቢያ፥ ርዕሱ አሁንም ከፍተኛ ጥናት የሚፈልግና አሁንም እየተጠና ያለ
ادامه مطلب ...