cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Sefa Ghazi || ሰፋ ጋዚ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
211
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

❤ ውድ ቤተሰቦቻችን አንድ በጣም የምትወዱትን ግሩም ቻነል ልጋብዛችሁ በርግጠኝነት ትወዱታላችሁ 👇👇👇👇👇👇 @wede_desta @wede_desta @wede_desta 👆👆👆👆👆 ሁላቹም ገብታቹ እዩት በጣጣጣጣም ትወዱታላቹ
نمایش همه...
▱መንታ መንገድ▱ ክፍል 1 ተለቀቀ👆👆👆
نمایش همه...
​ም ካለች በኋላ "ዉይ አኩሻ እናትህ እኮ የባሏ ዘመዶች ቤቷ ሲመጡ እያስቀየመቻቸዉ አሁን ማንም እናንተ ቤት ድርሽ አይልም። አባትህን የስራ ቦታዉ ሄደን ነዉ የምንዘይረዉ!" አለችኝ። ለእናቴ ያለኝ ጥላቻ ከፍ ሲል ተሰማኝ። ኢሙን ተሰናብቼ ስልኩን ዘጋሁት እና አባቴ ጋር ደወልኩ። ሰላም ከተባባልን በኋላ "አባ ዘመዶቻችን ቤት የማይመጡት እማዬ አስቀይማቸዉ ነዉ እንዴ?" አልኩት። "አይ አክረሜ የሷንስ ነገር ተወዉ መላ ጠፍቶለታል። ባይሆን አንድ ምክር ልምከርህ እኔ መልኳን አይቼ አግብቼ ነዉ እንዲህ የምቃጠለዉ አንተ ስትደርስ አደራህን እምነቷ ላይ ያላትን ጥንካሬ ሳታይ ስነ ምግባሯን ሳትመዝን እንዳታገባ።" አለኝ። የእናቴ ነገር ቢያናድደኝም የአባቴ ምክር ፈገግ አስባለኝ። እኔ ለትዳር ደርሻለሁ ማለት ነዉ? አባዬ እንደትልቅ ነዉ የሚያስበኝ? ደስ ሲል። ልብሴን ላወልቅ የሸሚዜን ቁልፍ ስፈታ ስልክ ተደወለልኝ። አየሁት ራሄል ናት። ምነዉ ያለመደባትን በዚህ ሰዓት? "ኧ እብዷ ህልም እናዋጣልሽ?" አልኩ ስልኩን አንስቼ "አንተ ያለህበት ከሆነ ደስ ይለኛል" አለች እየሳቀች። "ምነዉ እንቅልፍ እንቢ አለሽ እንዴ?" አልኳት ሳቋ እየተጋባብኝ። "አዎ ባክህ ካላስቸገርኩህ ብትመጣና ትንሽ አምሽተን ብንለያይ ደስ ይለኛል።" አለችኝ። "ልተኛ ነበር በቃ እሺ መጣሁ የት እንገናኝ?" አልኳት። "ላቭ ስትሪት እንገናኝ መግቢያዉ ጋር እጠብቅሀለሁ።" ብላኝ ስልኩን ዘጋችዉ። ላቭ ስትሪት ግቢያችን ዉስጥ ያለ ረዥም መንገድ ነዉ። መብራት ስለሌለበት እና በዛፎች የተከበበ ስለሆነ ብዙ ጥንዶች ዎክ ያደርጉበታል። ሹራብ ለብሼ ራሄል ወደ ቀጠረችኝ ቦታ ለመሄድ ተነሳሁ። የራሄልን እንቅልፍ ከራሄል ጋር ላቭ ስትሪት ላይ ልንጠብቀዉ። ይቀጥላል...... ❤️❤️🙏መልካም ቆይታ🙏❤️❤️ ታሪኩ ይቀጥል👍 @sefa_ghazi @sefa_ghazi
نمایش همه...
💞መንታ መንገድ ▱▱▱▱▱▱▱▱ ➢ ክፍል አንድ ከልጅነቴ ጀምሮ ቤት ዉስጥ ጭቅጭቅ እያየሁ ነዉ ያደግኩት። ትንሽዬ የጦርነት ሜዳ ውስጥ! እናቴ ምላሷ አይጣል ነዉ። አባቴ ደግሞ የእናቴ ምላስ ይመስገንና ሳይደበድባት ነግቶ አይመሽም። በርግጥ አባቴ ከእናቴ ጋር ለመጋጨት የእሷ ነገረ ስራ አስገድዶት እንጂ ሳትደርስበት ደርሶባት አያዉቅም። እኔም ድብድቡን ወንበር ስር መሽጌ እየተመለከትኩ አደግኩ። ፀባቸዉ ገና ሲጀመር እንባዬ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ እያለ ወንበር ስር ተደብቄ አያለሁ። ሁሌም ሰላም የለኝም። አንዳንዴ የእናቴ ተግባር እኔን ራሱ በጣም ያበሳጨኝ ነበር። እንግዳ በሚመጣበት ጊዜ አሊያም ከጓደኞቿ ጋር ስትሆን የአባቴን የግል ሚስጥር ሳይቀር ትለፈልፋለች። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ እና ነገሮችን ላቅ ባለ እይታ ማገናዘብ ስጀምር የእናቴ ተግባር ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ስለተረዳሁት የአባቴ ድብደባ ሲያንሳት ነዉ ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ። ምንም እናት ብትሆንም በፍፁም ለልጆቿ አርዐያ መሆን እንደማትችል ከስነ ምግባር ዝቅጠቷ ተረዳሁ። ቤት ዉስጥ ያለነዉ ሶስት ልጆች ነን። ሁለቱ እህቶቼ ናቸዉ። ታዲያ እናቴ ለእህቶቼ ስለ አባቴ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲኖራቸዉ የሆነ ያልሆነዉን እየነገረች ቤት ዉስጥ ትርምስ መፍጠር ጀመረች። እህቶቼ የእናቴ ኮፒ ሆኑ። በዚህም ምክንያት ከቤታችን ዉስጥ ሰላም ጓዙን ጠቅልሎ ወጣ። አባቴ በእህቶቼ ሳይቀር በጣም መናቅ ጀመረ። እኔ እናቴ እያደረገች ያለችዉ ነገር ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ላስረዳት ብሞክርም "አንተ የአባትህ ኮፒ ነህ!" እያለች ምክሬን አልቀበልም አለች። እናቴ ለአባቴ ልክ እንደ ልብስ ሆና ሚስጥሩን መሸሸግ እና ክፍተቱን መሙላት ሲገባት የሱን ስም ለማጥፋት መቅጠፍ ድረስ ሄደች። ስግደት ለሰዉ ተገቢ ስላልሆነ እንጂ እንድትሰግድለት ልትታዘዝለት የነበረችዉ ሚስት ባሏን በጣም መናቅና ዉሳኔዎቹን አለማክበር ጀመረች። የትዳር መሰረት ተናጋ! ህፃናት ልጆች በእናትና በአባት መካከል ጣልቃ ሲገቡ የትዳር መሰረት መናጋቱ የማይቀር ነዉ። እኔ ግን የሚገርመኝ የአባቴ ትዕግስት ነዉ። ለምን አይፈታትም? እኔ ብሆን የሱን ያህል የምታገስ አይመስለኝም። እድሜዬ ከፍ ብሎ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ስሆን ቤት መግባት የሚባል ነገር አስጠላኝ። ጠዋት ከቤት የወጣሁ ማታ አራት ሰዓት ወደ ቤት ብመለስ ነዉ። ማታ ወደ ቤት ስመለስ ልክ ወደ መገደያዉ ስፍራ እንደሚወሰድ እስረኛ እየቀፈፈኝ ነዉ። ወደ ቤት ላለመመለስ ስል ቀኑን በተቻለኝ መጠን ራሴን በተለያዩ ነገሮች ቢዚ በማድረግ አሳልፋለሁ። ከቤተሰቤ ያጣሁትን ፍቅር ፍለጋ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ክበቦች ላይ እንዲሁም የኪነ ጥበብ ማህበሮች ላይ መሳተፍ ጀመርኩ። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ቤታቸዉ ዉስጥ ያላቸዉ ሰላም እና የቤተሰብ ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ፀጋ እንደሆነ አይረዱትም። እኔን በተለያዩ ክበቦች ላይ በንቃት ተሳታፊ እንደሆንኩ ሲመለከቱ በጥንካሬዬ ይገረማሉ። እኔ ከቤቴ ያጣሁትን ፍቅር እና ሰላም ፍለጋ እነዚህ ክበቦች ዉስጥ መመሸጌን አያዉቁም። ቤተሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነዉ። መልካም ባልሆነ ቤተሰብ ዉስጥ ያደገ ልጅ መጥፎ ቢሆን አይገርምም። ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ የምሳተፍባቸዉ ሀይማኖታዊም ሆኑ የኪነ ጥበብ ቡድኖች ለጊዜዉ ያለሁበትን ጭንቀት ከማስረሳት በዘለለ ግላዊ ፍላጎቴን ማርካት እንዳልቻሉ ተገነዘብኩ። እያንዳንዱን ጉዳዬን የማማክረዉ ሰዉ ሊኖር ይገባል። በሰዓቱ የነበርኩበት የእድሜ ደረጃ እንደተራ ሰዉ ፍቅረኛ መያዝ የሚል አማራጭን ቢያቀርብልኝም ከሴት ጋር ያን ያህል ቀረቤታ ስላልነበረኝ ከወንድ ጓደኞቼ ጋር ያለኝን ትስስር ለማጠናከር ወሰንኩ። በሰርግ ምክንያት ከተዋወቅኩት አንድ ጓደኛዬ ጋር የወንድም ያህል ተቀራረብን ሚስጥሬን ሁሉ የማካፍለዉ ለሱ ሆነ። ጭንቄንም ቢሆን ከፈጣሪዬ ጋር በግንባሬ ተደፍቼ ከመከርኩበት በኋላ ከሱ ጋር እወያይበታለሁ። ጓደኛዬ ሰዒድ ይባላል። እሱን ከተዋወቅኩ በኋላ ትንሽ ጭንቀቱም ቀለል አለልኝ። ከጎንህ የሚያማክርህ አንድ ታማኝ ወንድም እንደማግኘት የሚያስደስት ነገር የለም። እድሜዬ አስራዘጠኝ ሲሆን ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ ተመድቤ ቱሪዝም እና ሆቴል ማኔጅመንት ማጥናት ጀመርኩ። ባህር ዳር በጣም ዉብ ከተማ ነች። መንገዶቿ በአረንጓዴ ልማት ያጌጡ እና ፅዱ ናቸዉ። ኑሮ ከሸገር ጋር ሲነፃፀር በጣም ርካሽ ነዉ። አየሯ ከአዲስ አበባ ጋር ሲወዳደር ትንሽ ሙቀታማ ከተማ ናት። የጣና ሀይቅ አይን አይቶ ማይጠግበዉ ... ብቻ ምንልበላችሁ በጣም ብዙ ዉበቶች በአንድነት የሰፈሩባት ለምለም ምድር ናት። የተመደብኩበት ፔዳ ካምፓስ ደግሞ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ካሉት ካምፓሶች ትልቁ ካምፓስ ነዉ። የተፈጥሮ ሳይንስናየማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ይሰጡበታል። ግቢዉ ዉስጥ ብዙ ካምፓሶች አሉ። ግቢዉም እንደ ከተማዋ አረንጓዴ ነዉ። የፔዳ ካምፓስ እንደኔ ሰላም ከሌለዉ ቤተሰብ ለመጣ ሰዉ ትልቅ ሰላም ያለዉ ቦታ ነዉ። ትምህርት ተጀምሮ ጥቂት እንደተማርን ከክፍል ተማሪዎች ጋር መግባባት ጀመርን። ትንሽ ቆንጆ ነገር ነኝ በዚህ ምክንያት ወንዶቹ "አክረም ቺኳ" እያሉ ይጠሩኛል። ሲጀመርም የትምህርት ዘርፋችን አምሮ መታየት እንደ መስፈርት የሚታይበት ነበርና የሴቶቹ አለባበስ እና አኳኋን ቀልብ የሚያስት ነበር። ከአለባበስ ጀምሮ እስከ ፀጉር ስታይል ሁሉም ራሳቸዉን መኳል ስራቸዉ ነዉ። ወንድ ሆኖ እኛ ክፍል ዉስጥ መማር የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም። ወንዶች ትንሽ ስለሆንን በሴቶቹ ተከበን ነዉ የምንማረዉ። ብዙዎች የኛን የትምህርት ዘርፍ የሴቶች ነዉ ይሉታል። ከአዲስ አበባ ከ500 በላይ ኪሎ ሜትሮችን ርቄያለሁ በዚህ ሰዓት ቤተሰብ አጠገቤ የለም። ፈጣሪዬን ካልፈራሁና ለራሴ ክብር ከሌለኝ የፈለግኩትን ማድረግ እችላለሁ። ጓደኛዬ ሰዒድ ከአዲስ አበባ ሆኖ አሁንም በስልክ ያማክረኛል። ሀያት ፣ ሀጅራ እና ራሄል የቅርብ ጓደኞቼ ሆኑ። በዩኒቨርሲቲ ካገኘኋቸዉ ልጆች በሳል ብዬ የቀረብኳቸዉ እነሱን ነዉ። ከእህቶቼ ጋር መልካም ቅርርብ ስላልነበረኝ የእህትነት ፍቅርን ከነሱ ለማግኘት ብዬ በደንብ ቀረብኳቸዉ። ሀጅራ ረጋ ያለችና ምክር የምታበዛ ጠይም የኮምቦልቻ ልጅ ናት። ሀያት ሲፈጥራትም ሳቂ ብሎ የፈጠራት ይመስል ከፊቷ ላይ ፈገግታ ከንግግሯ መሀል ሳቅ የማይጠፋ የሸገር ቆንጆ ናት። ራሄልን በቅፅል ስሟ ፋሽንሾዉ ብለዉ ይጠሯታል። ሁሌም የምትለብሳቸዉ ልብሶች ድግስ የምትሄድ ኮረዳ እንጂ ለሌክቸር የምትሄድ ተማሪ ልብስ አይመስሉም። በጣም ቆንጆ ከመሆኗ የተነሳ ብዙዎቹ የክፍል ልጆች ስለሷ ሳያወሩ ስብስባቸዉ አይበተንም። እሷም እንደኔዉ የሸገር ልጅ ናት። የፍሬሽማን ሙድ እየለቀቀን ግቢዉንም እየተላመድን ስንመጣ በመካከላችን ያለዉም ትስስር በጣም እየጠነከረ መጣ። ራሄል እና ሀያት ምግብ ከኔ ጋር ካልሆነ አይበሉም። ሀጅራ ካፌ ተጠቃሚ ስለሆነች የምግብ ሰዓት ላይ አንገናኝም። እኔ ፣ሀዩ እና ሪቾ ከግቢያችን በር ላይ ካሉት ምግብ ቤቶች ኮንትራት ይዘን እንመገባለን። የግቢያችን በር አራት ሰዓት ሲሆን ስለሚዘጋ በጊዜ ወደ ግቢ ገብተን በተለምዶ ሜንላዉንጅ የሚባለዉ ቦታ ላይ ትኩስ ነገር እየጠጣን ስንጨዋወት እናመሻለን። ብዙ ጊዜ የዶርም ጓደኞቼም ይቀላቀሉናል ሀሙስ ማታ ከነሀያት ጋር ተለያይተን ወደ ዶርም እንደገባሁ የአክስቴ ልጅ ደወለች። ከእህቶቼ በላይ በጣም ነዉ የምወዳት። ኢማን ትባላለች። ብዙ ከተጨዋወትን በኋላ "ኢሙ እንዴት ነዉ እነማማን ዘይራችኋቸዉ ታዉቃላችሁ?" አልኳት። ኢሙ ትንሽ ዝረ
نمایش همه...
❤ ውድ ቤተሰቦቻችን "መንታ መንገድ" የተሰኘዎ እጅግ ውብና ማራኪ እስላማዊ ልብ-ወለድ በቅርቡ ወደናንተ ማድረስ እንጀምራለን ይጠብቁን @sefa_ghazi @sefa_ghazi
نمایش همه...
ከገይስ ገጠመኞች (ክፍል 11) ተርጓሚ Bint Redi 1000 ፕሮጀክት ቢስሚላህ በአዲስ ደስታ እንጀምራለን : ሙህሲን ይባላል አይነ በሲር እና ምንም ገቢ የላቸውም። ገይስ ዛሬ ከአንድ ደከም ካለ ቤት እያንኳኳ ነው ።በሩ ተከፈተ… ገይሰ: አሰላሙአለይኩም እንዴት ኖት ሸኽ ሙህሲን: ወአለይከ ሰላም ወራህመቱላህ ገይስ: አንዴ ወደ ውጪ ይወጡልኛል? እዚህ ቤት ማነው ሚኖረው? ሙህሲን: እሺ።ሙህሲን ማህሙድ : ገይስ: እዚ አካባቢ ማርፍበት ቦታ ካገኘሁ ፈልጌ ነበር ? ሙህሲን: ምን ችግር አለው እዚ ትቆያለህ ።እንግዳ ነህ? ገይስ: አዎ ሙህሲን: ና ግባ ለይላ ( ባለቤታቸው ነች) ገይስ: ችግር የለውም አጎቴ ።አንተ ለእራስህ ማየት አትችልም።አንተን ማስቸገር አልፈልግም ።ሌላ ቦታ እሄዳለው። ሙህሲን: አይሆንም ወላህ ሁላችንም አላህ ዘንድ አንግዶች ነን ። ገይስ: የአላህ ችሮታ። የሆነ ነገር ፈልጌ ነበር? ሙህሲን: ምን ንገረኝ? ምትፈልገውን? ገይስ: ውሀ ነገር ካገኘሁ ብዬ ነበር ሙህሲን: ችግር የለውም።ለይላ ውሀ ይዘሽ ነይ ። : ገይስ: አስቸገርኩ ይቅርታ አጎቴ ሙህሲን: አብሽር ምንም አይደል። ገይስ: እዚህ ነው ምትኖረው? አጎቴ ሙህሲን: አዎ ከባለቤቴ ጋር ገይስ: ሁለታቹም ማየት አትችሉም? ሙህሲን: አዎ የአላህ ኒዕማ ነው ። ገይስ: ስትወለዱም እንደዚህ ነው? ሙህሲን: እኔ ስወለድም አይነ በሲር ነበር አልሀምዱሊላህ። ገይስ: አመሰግናለው አክስቴ ( ውሀ መጥቶለት ነው) ሙህሲን: በእድላችን ደስ ተሰኝተናል።አላህ ይወደናል። ገይስ: እንዴት ነው ኑሮ? ሙህሲን: ወደ ውስጥ ግባ? ገይስ: አይ ውጪ እሆናለው። ሙህሲን: ወላሂ አይሆንም( ድርቅ ብለው አስገቡት) ገይስ: ቤትህ ሀለት ክፍል ነው? ሙህሲን: የኔ አደለም የሚሸጥ ነው። ገይስ: ላደረክልኝ ነገር አመሰግናለው አጎቴ ሙህሲን: ለሁሉም ነገር አላህን እናመሰግናለን።ከእግር ጥፍሬ እስከ ራሴ ፀጉር ድረስ።ለምበላው ምግብ፣ለወተቱ፣ለስኳሩ… ሁሉም ነገር ከአላህ ነው ። ገይስ: እውነት ተናገርክ አጎቴ : ገይስ: ስንት ዓመትህ ነው? አጎቴ ሙህሲን: ወላሂ ትልቅ ነኝ ረሱል( ሠ ዐ ወ) ትደርሱበታላቹ ያሉት ዕድሜ ልደርስ 2 ይቀረኛል። ገይስ: 58 ዓመት ማለት ነው ።ባለቤትህስ ሙህሲን: አዎ እሷ ከ45–50 ትሆናለች። ገይስ: ማነው ሚረዳቹህ? ሙህሲን: በቀጥታ ሚረዳን የለም ግን ብዙ ሰዎች ያግዙናል። ገይስ: ትንሽዬ ስራ አላሰብክም አልሞከርክም? ሙህሲን: አስቤ ነበር ብቻ ብዙ ችግር ተከሰተ አልሆነም። ገይስ: አብሽር አላህ አለ።ላመሰግንህ እፈልጋለው ለመልካምነትህ።እኔ ድሀ ነኝ።አላህ መልካም ሰዎችን በአጋጣሚ ያገናኛል።እኛ ካገኘሀቸው መልካም ሰዎች እንደምንሆን አልጠራጠርም። አላህ ይባርክህ በጣም ጥሩ ሰው ነህ። ሙህሲን: አንድ ነገር ልንገርህ።ሰው እስከሆንን ድረስ መረዳዳት አለብን ።አንድ ወንድሜ የሆነ ነገር እርዳታ ከጠየቀኝ መርዳት አለብኝ።ሱዳናዊ አትመስለኝም በአንተ አክሰንት ላስረዳህ አልቻልኩም። : ገይስ: ከየት እመስላለው? ሙህሲን: ከግብፅ ነህ? ገይስ: አይደለሁም ሙህሲን: የገልፍ ሀገራት ነው ምትሆነው።እሺ ከዱባይ ነህ? ገይስ: አዎ ከኢማራት ነኝ።አንድ ነገር እፈልጋለው አጎቴ? ሙህሲን: ምን? እንዴት እረዳሀለው? ገይስ: ምኞትህ ምንድን ነው? ሙህሲን: ምኞቴ አላሁመሰሊ ዓላ ሙሀመድ የሆነ ነገር ልነግርህ ብዬ ጠፋብኝ።ወንድ ልጅ የለኝም ሁሉም ሴት ናቸው።እስፖንሰርሺፕ ባገኝ ደስ ይለኛል።ለምን ይሄን እንዳልኩህ ታውቃለህ? እኔ በህይወቴ ምንም አልፈልግም።ልጆቼ ግን ደስተኛ እንዲሆኑ እፈልጋለው።እኔ ከሞትኩ በኋላም እንዲሰቃዩ አልሻም። ገይስ: እሺ።እዚህ የመጣነው የእናንተን ደስታ ፍለጋ ነው።ውሀ ፈልጌ አይደለም።እናንተን አስደስቼ ለመሄድ እንጂ።አጎቴ ሙህሲን ወደ እዚህ ጠጋ በል።ይሄን ኪዎስቅ(ሱቅ) አምጥተን እዚህ አስተካክለነዋል።ስሙንም የደስታ ኪዎስክ ብለነዋል።ሁሉንም እቃ እናሞላልሀለን።ከቤትህ ሳትርቅ ትሰራላቹ። ሙህሲን: ከባለቤቴ ጋ አብረን መስራት እንችላለን። ገይስ: በአረብ ሀገራት ላይ 1000 ፕሮጀክት አስበናል።ሱዳን ላይ መቶ እናንተ የመጀመሪያ ናቹህ። ሙህሲን: ያሰላም እንዴት ያማረ ስራ ነው።ዱዓውን አዘነቡት ። ገይስ: አንድ ጓደኛዬ ያለውን ልንገርህ "የማይቻል ነገር የለም " ሙህሲን: እሱ እንዳለው ከፀሀይ በታች የማይቻል ነገር የለም ። ገይስ: የአንተ አባባል ያምራል።ስጦታ አለኝ።በዚህ የፈለግከውን ማድረግ ትችላለህ።ከፈለክ ቤትህን አድስበት ብቻ የፈለግከውን።ወጣቶች መጥተው እቃውን ይሞሉልሀል። ሙህሲን: ስምህን ገይስ: ገይስ እባላለው ሙህሲን: እውነትም አንተ እንደ ዝናብ ነው የመጣህው። ገይስ: ከመሄዴ በፊት ልቀፍህ? አቅፈውት ዱዓውን አዘነቡለት ገይስም መንገዱን ቀጠለ… ቤተሰቡም በደስታ አነቡ ። Join & share ቻናላችንን ለመቀላቀል👇👇👇👇 @sefa_ghazi @sefa_ghazi
نمایش همه...
ሰበር መረጃ❗ የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል። የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል። የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ) #ሼር በማድረግ መረጃውን ያዳርሱ ➢ @sefa_ghazi @sefa_ghazi ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን 👆 👆
نمایش همه...
ከገይስ ገጠመኞች (ክፍል 10) ተርጓሚ Bint Redi 16 ዓመት ቢስሚላህ በአዲስ ደስታ እንጀምራለን ኡሙ ራሚ የኢራቅ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ነው ምትኖረው ።ባልዋ የሞተ ሲሆን ምንም አይነት ስራም ሆነ ገቢ የላቸውም።አንድ ልጆ ታስሮባታል።ገይስ ወደ ካምፑ አንደ መጠለያ ጠጋ አለ… : ገይስ: አሰላሙ አለይክ እንዴት ናቹህ? የራሚ አጎት: ወአለይከ ሰላም አልሀምዱሊላህ ገይስ: መኪናችን ተበላሸብን ውሀ ትሰጡናላቹ? አጎት: እሺ ችግር የለውም ።ልጆች ውሀ አምጡ ገይስ: የቤቱ ባለቤት ነህ? አጎት: አይ እኔ ዋርሳ( የባል ወንድም) ነኝ።ባለቤቷ ሴት ናት። ገይስ: አፉ በሉን አስቸገርናቹህ አጎት: አብሽሩ ቤት ግቡ? ገይስ: አይ መኪናችን ሞቃብን ነው አሁን እንሄዳለን። አጎት: ለመኪናው ውሀ አምጡለት ገይስ: አስቸግርናቹህ ።የቤቱን ባለቤት ልናገኛት እንችላለለን እናመስግናት።ካምፕ ከገባቹህ ስንት ጊዜ ሆናቹህ? አጎት: መውሱል ጦርነት ከተነሳ ወዲህ ነው።5 ዓመት ይሆነዋል። ገይስ: አልተመለሳችሁም? እዚ ነገራት ጥሩ ነው? አጎት: አይ! ከባድ ነው እዚህ ( ውሀ መጣላቸው) : ገይስ: አሰላሙ አለይኪ እናቴ እንዴት ነሽ ? ኡሙ ራሚ: ወአለይከ ሰላም አልሀምዱሊላህ ገይስ: አፉ በይን መኪናችን ተበለሽቶ በር ላይ አቆምነው። ኡሙ: አብሽር ትልቅ ነገር አደለም። ገይስ: ሀጂያ ወደዚህ ቀረብ በይልኝ ።ውሀቹ ይጣፍጣል ቀዝቃዛ ነው።የፍሪጅ ነው? ኡሙ: አይ ፍሪጃችን ተሰብሮዋል።ከታንክ ነው ያቀዘቅዛል እሱም። ገይስ: አፉ በይን እናታችን ኡሙ: ችግር የለውም ገይስ: ተባረኪ ትንሽ ጊዜ ስጭን።እንዴት ነው ምትኖሩት ከእናንተ ጋርስ ማን አለ? : ኡሙ: እኔና ልጆቼ እና ዋርሳዬ አብረን ነን። ገይስ: ኦ ጥሩ ሰው ነው።አንድ ጥያቄ አለኝ።ካምፕ ውስጥ መኖር እንዴት ነው? ኡሙ: አልሀምዱሊላህ እነሱ በሚሰጡን እየኖርን ነው። : ገይስ: ሚሰራ ሰው የለም? ኡሙ: ማንም የለም ትንሹ ልጄ ይሰራ ነበር ታሰራ።አንደኛው ልጄ ወታደር ነው ።ሚስቱ እና ልጁ ከእኔጋ ናቸው።በጎ አድራጎት ድርጅት ከ300–500 ብር በ2 ወር እናገኛለን።አልሀምዱሊላህ አንዳንዶች ምግብ ልብስ ይልኩልናል። ገይስ: አልሀምዱሊላህ ሁሉም ጥሩ ይሆናል።ልጄ ታስሮዋል አልሽኝ? ምን ተፈጥሮ ነው? ኡሙ: አዎ ችግር ውስጥ ወደቀብኝ ።እዚህ ከመጣን 6 ዓመት ምንም ወስዶ አያውቅ ። ማንም መጠየቅ ትችላለህ አጎቱን ጠይቅ ከፈለግክ።ሞተር ሳይክል ግዢልኝ አለኝ ገዛሁለት።ከዛ ትንሽዬ ፒክ አፕ አለኝ ገዛሁለት።ባጃጅ አይነት ነው።ከካምፕ ውጭ ያሉ ሰዎች ይጠሩታል ለስራ።ሸክላ ድንጋይ ያጓጉዛል። ገይስ: ይረዳሽ ነበር? ኡሙ: አዎ ።ነግሬህ የለ የእርዳታ ድርጅቶቹ ከሚሰጡን ብር ቆጥቤ ገዛሁለት።አንዱ ልጄ ከካምፕ ውጭ ነበር ።ክራዩ ሲከብደው ወደ እኔ ተመለሰ ከነ ቤተሰቡ ከኔ ጋር ነው። : ገይስ: ስንት ሰው ይኖራል? እዚ ቤት ኡሙ: 6 ገይስ: ሁላቹም ምትኖሩት በእርዳታው ድርጅት ብር ነው? ኡሙ: አዎ አንዱ ልጄም ስራ የለውም። ገይስ: ልጅሽን ለማስወጣት አልሞከርሽም ? ኡሙ: ወላሂ ብዙ ሞክርያለው 16 ዓመቱ ነው ።ከባድ ነው።ሞተር ሳይክሉ ስጡኝ ስላቸው ፖሊስ እስቴሽኑ በህግ ተይዞዋል አሉ። ገይስ: ስንት ጊዜው ነው? ኡሙ: 5 ወሩ እሱ ጋ እሄዳለው ።ካልሄድኩ ያለቅሳል ለምን አልመጣሽም ብሎ።እንዳልቻልኩ እነግርሀለው።እዚህ ያለ ሰው ማንንም መጠየቅ ትችላለህ እሱ ምንም አይወስድም።ካርቶን ፋብሪካ ይሰራ ነበር ትንሽ አጠራቀመ እኔ ጨመርኩለትና ሞተር ሳይክል ገዛ።እራሱን ከሰው ጋ እያወዳደደረ ከሰው በታች እንደሆነ እንዲሰማው አልፈልግም።ያለኝን በሙሉ አውጥቼ ገዛሁለት ።ከዛ ስራ ይሄዳል ያገኘውን ይዞ ይመጣል አልሀምዱሊላህ። : ገይስ: ምኞትሽ ምንድነው? ኡሙ: ምኞቴ ልጄን ነፃ ማድረግ ነው። ገይስ: መቼ ይወጣል? ኡሙ: አላውቅም።ጠበቃው ከትንሽ ወር ቡሃላ ይለኛል እኔን ለማስደሰት ብሎ ይሁን እውነትቱን ይሁን አላውቅም።በሳምን 2 ጊዜ እሄዳለው አሁን 1 ። ገይስ: ምን ይልሻል? ኡሙ: እዚህ ስላሉ ስዎች ይጠይቀኛል።ስለ እኔ ምን አሉ ይላል።እኔም ችግር ውስጥ ያለን ሰው ማን ያስታውሳል እለዋለው ።እናት ምንም ሁኔታ ላይ ብትሆን ትንከባከብሃለች። ገይስ: ትምህርት ነው። ኡሙ: አዎ ትልቅ ትምህርት ።ድጋሚ አይሳሳትም። ገይስ: ናፍቀሽዋል? ኡሙ: አዎ በጣም ልቤ ያመኛል ስለእሱ ሳስብ። ብዙ ያግዘኝ ነበር ።ጋዝ ሲለኮስ ራሚ ጋዙን አጥፋው እለዋለው።ሲሊንደሩን አስሞላ እለዋለው።ለመጨረሻ ጊዜ ባለፈው ሳየው እያለቀሰ ነበር እኔን ማን ይረዳታል ብሎ ( ታለቅሳለች ) : ገይስ: ትግስት ስጦታ ነው እናቴ ።አንድ ጓደኛዬ ያለውን ልንገርሽ "ማለምህን አታቁም፣አንድ ቀን እውነት ይሆናል "።ምኞትሽ እውነት ይሆናል… ( ከጀርባ ራሚ እቅፍ አበባ ይዞ ሲመጣ ይታያል) ኡሙ: ለአላህ ሰጥቸዋለው ገይስ: ምኞት እውነት ይሆናል።ራሚ መጥቶዋል። ኡሙ: ዞር ስትል አሰላሙአለይኪ ሚል ድምፅ ሰማች አላመነችም ተጠምጥማበት አለቀሰች ደስታዋ እጥፍ ድርብ ሆነ። ገይስ: አላህ አይለያያቹ።እንኳን ደህና መጣህ ያራሚ አፉ በለን ።እማዬ ነይ ወደዚህ ።እዚህ የመጣነው የእናንተን ደስታ ለማየት ነው።ራሚ ሁለተኛ አይመለስም ኢንሻአላህ።ስራ አጊንተንለታል።ስራው እዚው ካምፕ ውስጥ ያለ ዳቦ ቤት ነው ራሚ ነው ሚያስተዳድረው።ለካምፑ ሰዎች ሙሉ ነው ሚያገለግለው። እናንተ ለካምፑ ሰው ሙሉ ደስታ ትሆናላቹ ሁሉም ተጠቃሚ ነው ።ሰው ለሰው ነው ቻው… መንገዱን ቀጠለ… የአካባቢው ሰዎች ዱፋቸውን እየመቱ እልልታውን አቅልጠውት ወደ እነ ራሚ ቤት ሲመጡ ይታያሉ… : ማጠቃለያ ዛሬ በስደት ምክንያት እዚህ ካምፕ ውስጥ ያሉ ሰዎችን በሙሉ ደስታ እናያለን።የእነ ራሚ ቤተሰብ የሚሰራበት ዳቦ ቤት ከ300 ሰዎች በላይ በቀን ይመግባል።በተጨማሪም የተለያዩ ግላዊ እቃዎችን እናቀርባለን ኢሻአላህ። JOIN & SHARE ቻናላችንን ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇 @sefa_ghazi @sefa_ghazi
نمایش همه...