cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሸገር NEWS

የሚያምኑት መረጃ!! እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ አሁኑኑ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ #ሸገር የናንተ #ሸገር የኛ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
24 317
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
የህክምና (Medicine) የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ! ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ የህክምና (Medicine) ተመዛኞች ከሚያዚያ 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple/ ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት እንደምትችሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0115324185 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በመላ ሀገሪቱ ህብረተሰቡ የፋሲካ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲያከብር በቂ ዝግጅት መደረጉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በበዓሉ ወቅት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑንም ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማክሰም ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የህግ የበላይነትን የማስከበር ዘመቻ እያካሄደ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በዚህም የጁንታውን ርዝራዦች፣ የኦነግ ሸኔ አባላት እና በመተከል ዞን የመሸጉ ሽፍቶችን ከተደበቁበት ስፍራ ሙሉ በሙሉ አድኖ ለፍትህ ለማቅረብ ሌት ተቀን እየሰራ እንደሚገኝም አስታውሰዋል። በሌላ በኩል ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ለማድረግ ፖሊስ በብቃትና በገለልተኝነት በማገልገል ላይ ነው ብለዋል። ኮሚሽነሩ እንዳሉት ሰራዊቱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ሌሎች ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን በመጠበቅ ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች በጀግንነት እየታደጋት ነው። ህብረተሰቡ በመላ ሀገሪቱ የሚከበረውን የፋሲካ በዓልን ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲያከብር ኮሚሽኑ በቂ ዝግጅት ያደረገና የፖሊስ አባላትም በወትሮ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @shegernewsbot @shegernwsETH
نمایش همه...
አዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማበህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 115 የቀበሌ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ለ22 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ሼድ አስረከቡ፡፡ በተጨማሪም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በክፍል ከተማው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች እና ለፖሊስ አባላት የበሬ እና ሌሎች የምግብ በቁሳቁስ ስጦታ አበርክተዋል። በዛሬው እለት ቀበሌ መኖሪያ ቤት ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታ ዜጎች መካካል ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ይገኙበታል ። የከተማው ሀብት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በፍትሃዊነት ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ። ዛሬ የመስሪያ ቦታ ሼድ የወሰዱ ኢንተርፕራይዞች በተሰጣቸው ቦታ ስራ ፈጥረው ሌሎች ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለከተማዋ እድገት እና ብልጽግና መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል ። በተያያዘም ምክትል ከንቲባዋ ለ71 ሴክተር ተቋማት እና በ11 ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚሰሩ ከ1ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች ለትንሳኤ በዓል የሚሆን ስጦታ ማበርከታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅድመና ድህረ ምርጫ ወቅት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቀረት ዜጎች የማይተካ ሚና እንዳላቸው መዘንጋት የለበትም አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። እንዲሁም በተለይ በምርጫ ወቅት ዜጎች በልዩ ልዩ መንገዶች ተሳትፎአቸውን ሊያረጋግጡ እንደሚችሉም ጠቅሰዋል። ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት በዘለለ፣ በሲቪክ ማኅበራት አማካኝነት የምርጫው ሂደት ግልጽና ተአማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካርድ አሰጣጡ ዙሪያ፣ የምርጫ ቅስቀሳን በተመለከተ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ሀሰተኛ ሰነድን ተጠቅሞ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ብዛቱ 186,240 የእጅ ገጀራ ተያዘ:: ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጋር በጋራ በተደረገው ማጣራት ሀሰተኛ ሰነድን ተጠቅሞና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራት ባለ20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ መያዙን የገቢዎች ሚኒሰቴር አሰታወቀ። እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ከፍሎ እቃው ከተለቀቀ በኃላ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢንተለጀንስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛና ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው በመሆኑ መያዙን የገቢዎች ሚኒሰቴር አስታውቋል። በተጨማሪም በጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኛ የእጅ ገጀራው ተገቢውን የጉምሩክ ስነ-ስርዓት በመፈጸም እንዲስተናገድ የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማውጣት የተሞከረ ሲሆን ይህም ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት መረጃዉን በመስጠት በተደረገው ክትትል የእቃው ባለቤትና ትራንዚተሩ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል:: ገጀራ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች አንዱ ሲሆን ከፌደራል ፖሊስ ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ማስገባት አይቻልም።በማህበራዊ ሚዲያ በጉምሩክ ኮምሽን ባለሙያ እቃው እንዲወጣ የተፈቀደበት ደብዳቤ በማስመሰልና ሐሰተኛ የደብዳቤ በመጠቀም አስመጪው ሕጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሰታውቋል። @shegernewsETH
نمایش همه...
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ የዙምራ ፊልም፣ የሰው ለሰው እና የዘመን ድራማ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲና ተዋናይ የነበረው አርቲስት መስፍን ጌታቸው ህይወት አልፏል። ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዋሽ 7 ማሰልጠኛ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ 600 የመጀመሪያ ዙር ከፍተኛና መካከለኛ የአድማ ብተና አመራሮችና መሰረታዊ የ4ኛ ዙር የፀረ-ፈንጅ ሰልጣኞችን አስመረቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ለተመራቂዎቹ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴርና የክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በከፍተኛ መስዋእትነት እየሰራ ባለበት ወቅት ለምረቃ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ በተቋሙ እየተካሄዱ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን መሰረት በማድረግ የሰራዊቱን ህይወት ለማሻሻልና ሰራዊቱ ከተቋሙ በጡረታ በክብር  ሲሰናበት የማያርፍበትና ሰርቶ የሚኖርበት የፖሊስ ፋውንዴሺን የማቋቋም ስራ ተጀምሯል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ለሀገሩ ሰንደቅ ዓላማና ክብር ሲል ከገንዘብ በላይ የሆነውን ውድ ህይወቱን መስዋእት እያደረገ ያለውን ሰራዊት ጥያቄዎች ለመመለስ ሁሉም የተቋሙ አመራሮች ጊዜያችንን በሙሉ በመስጠት እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡ ቀጣዩ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ፖሊስ ከማንኛውም የፖለትካ ፓርቲ ገለልተኛ በመሆን ለሁሉም የፖለትካ ፓርቲዎች ሰላምና ጸጥታን የማስከበር አገልግሎቱን በመስጠት ህብረተሰቡ የሚፈልገውን መርጦ ወደ ስልጣን እንዲያመጣ የሚጠበቀውን መወጣት ይገባል ነው ያሉት። እስካሁንም ባለው ሂደት የምርጫ ጣቢያዎችን በመጠበቅና መራጩ ህብረተሰብ ያለምንም ተፅእኖ እንዲመዘገብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሀገሪቱ በአራቱም ማዕዘን የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ፀረ-ሰላም ሀይሎችን በመደምሰስ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የበለጠ መስራት እንደሚገባ ኮሚሽነር ጄነራሉ አሳስበዋል፡፡ ተመራቂዎቹ በማሰልጠኛ ቆይታቸው የፖሊስ ባህልና ጨዋነት፣ በተቋሙ የለውጥ ስራዎች፣መሪነትና የመሪነት ሚና፣ሰብዓዊ መብትና የፖሊስ እርምጃ አወሳሰድ፣በምርጫ ሂደት የፖሊስ ሚና፣የፀረ-ሽብር ትምህርት፣የአድማ ብተና፣የኮምፓስ፣የካርታ ንባብና የ‘ጂፒኤስ’ (GPS)፣የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር፣የፀረ-ፈንጅ፣የመጀመሪያ የሂክምና እርዳታ ትምህርቶችን የወሰዱ ሲሆን በመስክ የተለያዩ የአካል ብቃት ስልጠናዎች መውሰዳቸውን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተርና የትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሰማሀኝ ይደነቅ መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የአድማ ብተና አመራሮቹ በጽንሰ ሐሳብ ከተማሩት በተጨማሪ ተግባር ተኮር የሆኑ የአድማ ብተና ስልጠናዎችን በከፍተኛ የውድድር መንፈስ ማጠናቀቃቸውን ምክትል ኮማንደር ሰማህኝ ይደነቅ አብራርተዋል፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ በነጻነት የመልማት መብት በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ አንድነት እና መግባባት ሊኖረው እና በጋራ በመቆም ከዳር ሊይደርሰው እንደሚገባ የውሃ፣መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ክቡር ስለሺ በቀለ ገለፁ። በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትብብር ለህዳሴ ግድብ ከካናዳ ጋር በመተበባበር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል። በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ አንድነት እና መግባባት ሊኖረው እና በጋራ በመቆም ግደቡን ከዳር ሊይደርሰው እንደሚገባ እንዲሁም ዳያስፖራው የግድቡ አምባሳደር በመሆን የሀገሩን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እና መብት ለማሳወቅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል። በሀገር ውስጥ በሚደረገው የቦንድ ግዢን በተመለከተ ዳያስፖራው አመቺ በሆነ እና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን ባቃለለ መልኩ የተዘጋጁትን የቦንድ መግዣ መንገዶችን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሃላፊ የሆኑት አቶ ለማ ዋቀዮ ገለጻ ማድረጋቸውን በካናዳ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው፤ የዚህ ትውልድ አድዋ የሆነው ግድብ የኢትዮጵያውያንን ህይወት የሚቀይር በመሆኑ ሁሉም ተረባርቦ መጨረስ እንደሚገባና ሁሉም በእውቀት፣ ተፅዕኖ በማሳደር፣ በገንዝብ፣ በጉልበት እንዲሁም ባለው ነገር ሁሉ አስተዋጾ በማድረግ አሻራን ማኖር እንደሚገባ አሳስበዋል። @shegernewsbot
نمایش همه...
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በስፋት የሚንቀሳቀሱበትን የምስራቅ እና የምዕራብ ወለጋ ዞኖችን በመሻገር ወደ ምዕራብ ሸዋ (አምቦ) እና ወደ ጅማ ዞን ይዞታቸውን በማስፋት የተለያዩ ቀበሌዎችን መቆጣጠር ጀምረዋል። በጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ጋሌሳ ከሚሴ ቀበሌን ከወር በፊት ተቆጣጥረው ሲያስተዳድሯት የቆዩ ቢሆንም በትናንትናው እለት ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ከ25 ሰዎች በላይ ገድለው ፤ ቤት እና ንብረት አቃጥለው ፤ በከተማዋ ውስጥ ካምፕ መስርተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታውቋል። በምዕራብ ሸዋ ዞን (አምቦ) ዳኑ ወረዳ አጅላ ዳሌ ቀበሌ አምስት ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ሁለቱ የተገደሉት መስጂድ ውስጥ ነው። መንግስት እርምጃ እየወሰድኩ ነው ሲል በተደጋጋሚ ይገልጻል። ነዋሪዎች ግን ከታጣቂዎች ጋር የሚተባበር እንጂ እርምጃ የሚወስድ የጸጥታ ኃይል አላየንም ሲሉ ይናገራሉ። ምንጭ ኢሳት @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የብሔራዊ ደህንነትን በሚፈታተኑ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ! መንግስት ሀገራዊ ለውጡ እንዳይቀለበስ እንዲሁም የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ካለው ፅኑ ፍላጎት አኳያ እያሳያ ያለውን ሆደ ሰፊነትና ታጋሽነት ብሄራዊ ደህንነትን የሚፈታተን በመሆኑ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል። ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፤ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፤ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ የተውጣጣው የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ ፣ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ እያካሄደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በጽንፈኞቹ የህወሓትና የኦነግ-ሸኔ ቡድኖች እንዲሁም በሌሎች ታጣቂዎች ላይም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ብሏል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታለመለት ጊዜ ለማካሄድና በመጀመሪያው ዙሩ ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ መንግስት በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህ አዎንታዊ ተግባሮች እየተከናወኑ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን ወደ ግጭትና ትርምስ ውስጥ ለመክተት ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲፈጥር የውስጥና የውጭ ሃይሎች ተጣምረው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ መሆኑ በበቂ መረጃና ማስረጃ መረጋገጡን ከደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ አመልክቷል፡፡ ሀገራዊ ትርምስ ለመፍጠር የተዘጋጁ ሰነዶችና የጥፋቱን ተዋናይ አካላትንም የሚገልፅ መረጃ በደህንነትና በጸጥታ መዋቅሩ እጅ መግባቱንም ተጠቁሟል፡፡ መንግስት መጪው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ካለው ፅኑ ፍላጎትና ከተጣለበት ሀገራዊ ሃላፊነት የተነሳ የጽንፈኛ ሃይሎችን ተግባር በሆደ ሰፊነትና በትዕግስት ሲከታተልና በአንዳንዶቹም ላይ የእርምት እርምጃ ሲወስድ መቆየቶን ያመለከተው መግለጫው፤ ይሁንና እነዚህ ፅንፈኛ ሀይሎች በማህበራዊ ሚዲያው የሚታየውን ልቅነት ለእኩይ ሴራቸው በቅስቀሳ መሳሪያነት በመጠቀምና የእነሱ ግብረ አበሮች ከሆኑ የጥፋት ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ሰሞኑን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሞትና መፈናቀል ፈፅመዋል፡፡ ይህም መላውን የሀገራችንን ህዝቦች አሳዝኗል፤ አስቆጥቷልም፡፡ መንግስትንም በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረስብ አስተዳደር ዞኖች ከውስጥና ከውጭ የተደራጁ የጥፋት ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ንጹኃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ንብረት ወድሟል ፤ እንዲሁም በርካታ ሰዎች ከቀዬቻው ተፈናቅለዋል፡፡ በዚሁ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቅማንት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃትም የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፏል፡፡ ንብረትም ወድሟል፡፡ በሌላም መልኩ በአፋርና በሱማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የንፁሃንን ሕይወት የቀጠፉ ግጭቶች አጋጥመዋል፡፡ በተመሳሳይ በቅንጅት የሚሰሩት የውስጥና የውጭ ጸረ ሰላም ሀይሎች የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታለመለት ጊዜ እንዳይካሄድና እንዲስተጓጓል ለማድረግ የጉሙዝ ታጣቂዎችን አሰልጥነውና አስታጥቀው በአካባቢው በማሰማራት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰሩ ቢሆንም ድርጊታቸው ከመንግስት እውቅና ውጭ ባለመሆኑ ሴራቸውን ለማክሸፍ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የደህንነትና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ፀጥታን ለማስከበር እየተወሰደ ባለው እርምጃም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ያለው የኦነግ-ሸኔ ታጣቂ ቡድን የመንግስትን ትኩረት ለመበተን በማለም በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈፅማቸውን ጥቃቶችና ግድያዎች ሙሉ በሙሉ ለማስቆም በቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም ተጠናክሮ መቀጠሉን የጋራ ግብረ ሃይሉ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ የውስጥና የውጭ ሀይሎች ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራቸውን ለማሳካት በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን እንዲሁም በዚሁ እኩይ ኣላማቸው የተጠለፉ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ አካላትንም ጭምር በመጠቀም፤ ንጹሃንን በግፍ እየገደሉና እያፈናቀሉ ህዝባዊ ቁጣ እንዲቀሰቀስ በማድረግ የሀገርን ህልውና እንዲሁም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል እየተረባረቡ መሆኑን መላው ህዝባችን ሊገነዘብ ይገባዋልም ነው ያለው፡፡ መንግስት ሀገራዊ ለውጡ እንዳይቀለበስ እንዲሁም የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ካለው ፅኑ ፍላጎት አኳያ እያሳያ ያለውን ሆደ ሰፊነትና ታጋሽነት ብሄራዊ ደህንነትን የሚፈታተን በመሆኑ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የጋራ ግብረ ሃይሉ አስታውቋል። መንግስት ሀገራዊ ህልውናን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሞክሩ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎችን በምንም አይነት ሁኔታ የማይታገስ በመሆኑ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ የፀረ ሰላም ኃይል ታጣቂዎችን እንቅስቃሴ በመረጃ፣ በደህንነትና የፀጥታ መዋቅሩ አማካኝነት በመከታተልና በመቆጣጠር፣ አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ የገለጸው ግብረ ኃይሉ፤ የሀገሪቱን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ፣ እየተወሰደ ያለው መጠነ ሰፊ ህግን የማስከበር እርምጃ ስኬታማ እንዲሆን፤ ህብረተሰቡ የጥፋት ሀይሎችን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ጥቆማ በመስጠትና በማጋለጥ እንዲተባበር የጋራ ግብረ ኃይሉ ጠይቋል። Via Al ain @Shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የመራጮች ምዝገባ ለሁለት ሳምንት ተራዘመ:: የመራጮች ምዝገባ ለሁለት ሳምንታት መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ የመራጮች ምዝገባ መራዘምን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መርሃግብር መሰረት የመራጮች ምዝገባ ቀን ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል። እስካሁን በተከናወነው የመራጮች ምዝገባ ሂደትም በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የምዝገባው ሂደቶች በተለያየ ደረጃ ሲከናወኑ ቆይተዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ሀሰተኛ የሌላ ክልል መታወቂያን በማውጣት ወደ ሱዳን ሊሸሹ የነበሩ የቀሩ ርዝራዥ የጁንታው ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ፡፡ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ እነዚህ የጁንታው አባላት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የሌላ ክልል መታወቂያ በመያዝ ከሀገር ሊሸሹ ሲሉ ሰራዊቱ በደረገው ከፍተኛ ጥረት ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ የዚህ ድርጊት ዋነኛ አላማ እነዚህን አባላት ወደ ሱዳን በማሸሽ ከዚያ ሆኖ ሀገር ውስጥ ያሉትን ተጣቂ ሀይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት ሀገር ለመበጥበጥ የታቀደ እንደነበር ሌ/ጄነራል ባጫ በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ እርምጃ በተወሰደባቸው ሁሉም የጁንታው አባላት እጅ ላይ ይህ ሀሰተኛ መታወቂያ መገኘቱንም አስታውቀዋል፡፡ በጌትነት ተሥፋማርያም Via (ኢ.ፕ.ድ) @shegernewsbot @shegernewETH
نمایش همه...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 138 ሄክታር መሬት ለአልሚዎች አስተላልፏል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመሬት አጠቃቀምና አያያዝ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላትና ከባለሃብቶች ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይቱ በመዲናዋ ዓመታትን ያስቆጠሩ የመሬት ጥያቄዎችን ለመመለስና በዘርፉ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ካለው እድገት ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣውን የመሬት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት 138 ሄክታር ለልዩ ልዩ አገልግሎች እንዲውል ለአልሚዎች ማስተላለፉ ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህገወጦች ተይዞ የነበረውን መሬት ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ለረጅም ጊዜያት ጥያቄ ሲቀርብባቸው የነበሩ እና ለከተማዋ እድገት የሚያስፈልጉ ተቋማት እንዲኖራት ለማስቻል አልሚዎችን በግልጽ መስፈርት በመለየት በልዩ ሁኔታ መሬት እንዲሰጥ በካቢኔ መወሰኑን ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል ። በከተማ አስተዳደሩ ለልዩ ልዩ አገልግሎት እንዲውል የተሰጠውን መሬትም አልሚዎች በአፋጣኝ አልምተው ለተፈለገው አላማ ማዋል ይኖርባቸዋልም ብለዋል ። የከተማ አስተዳደሩም በመሬት እና መሬት ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋለውን የመሬት ወረራ እና ሌሎች ብልሹ አሰራሮችና ማነቆዎችን በመፍታት በህገወጥ የተያዘውን መሬት ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ፣ 430 በሚሆኑ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃ በመውሰድ እንዲህም ዘርፉን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑንም አመልክተዋል። ለልማት የሚውል መሬት የተሰጣቸው ተቋማት እና ልዩ ልዩ ድርጅት ተወካዮች በበኩላቸው ለዘመናት ታጥረው የነበሩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ በማስገባት በግልጽ መስፈርት ለተቋማት እና ድርጅቶች እንዲተላለፍ መደረጉ ከተማ አስተዳደሩ ለግልጸኝነት ፣ለተጠያቂነት እና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል ። የከተማ አስተዳደሩም በሰጣቸው መሬት ለተፈለገው ልማት እንዲውል በአፋጣኝ ወደ ስራ እንደሚገቡም የተቋማት እና ልዩ ልዩ ድርጅት ተወካዮች ቃል መግባታቸውን ከፕረስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ያልተለመደ የተባለ አውሎ ነፋስ ወደ ታንዛኒያ እየተቃረበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በማደጋስካር አቅራቢያ በደቡብ ሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ ጆቦ የተባለው ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ ታንዛኒያ እየቀረበ መሆኑን የአየር ትንበያ ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡ አውሎ ነፋሱ ነፋስ ከቀላቀለና በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር ከሚነፍስና ከባድ ማዕበል ጋር ተመጣጣኝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በታሪክ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ በታንዛኒያ ዳርቻደረሱ ሁለት አውሎ ነፋሶች ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም በሃገሪቱ ከተከሰቱ አውሎ ነፋሶች አንጻር ሲታይ ጆቦ ደካማ የሚባል መሆኑንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ሆኖም አውሎ ነፋሱ በአህጉሪቱ ህዝብ በሚበዛባቸው ከተሞች የሚያልፍ ከመሆኑ አንጻር የሚያደርሰውን ጉዳት ከፍ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል፡፡ አውሎ ነፋሱ ከ6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ባሉባት ዳሬሰላም እና ዛንዚባርን ሊመታ ይችላልም ነው የተባለው፡፡ ምንጭ፡- ሲጂቲኤን @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮች በሚመለከትበት ወቅት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰቡ የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት እና ለፀጥታ ስጋት አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮችን በሚመለከትበት ወቅት ጥቆማ ለመስጠት የሚያስችሉ ስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ለፀጥታ ሀይል መረጃዎችን ማድረስ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡ ስልክ ቁጥሮቹ ከላይ በምስሉ ላይ የሚትታዩት ናቸው። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በቤኒንሻንጉል ካማሺ ዞን የሚገኘው የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን ኢሰመኮ ገለፀ:: በርካታ ነዋሪዎች፣ የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው መሸሻቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል ታጣቂ ቡድኑ ንብረቶችን ማቃጠሉ ፣ ነዋሪችን፣ አመራሮችን እና የመንግስት ሰራተኞችን መግደሉና ማገቱም ተገልጿል። በቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ከማሺ ዞን የሚገኘውና ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙበት የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ፣ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጿል።  ኢሰመኮ በመግለጫው እንዳለው ፣ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በአቅራቢያው ያለው የፀጥታ ኃይል ከአቅሙ በላይ እንደሆነና ተጨማሪ የተላከው ኃይልም ወደ አካባቢው እንዳልደረሰ ይገልጻሉ።  ይህ ክስተት በክልሉ የቆየው የጸጥታ ችግር እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት የሚያሳድር ነው ብሏል ኮሚሽኑ።  ኢሰመኮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ እና ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑንም ገልጿል።  ኮሚሽኑ መንግስት በአፋጣኝ የአካባቢው እና የክልሉን የፀጥታ ኃይል እንዲያጠናክርና እና ተጨማሪ የሰዎች ሞት እና የከፋ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰት እንዲከላከልም ጥሪውን አቅርቧል። ©አልአይን @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የጤና ቀውስ የሚያስከትሉ መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰራጩ ነው:: ከፍተኛ የጤና ቁውስ የሚያስከትሉ መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ ህብረተሰቡ በተሳሳተ ግንዛቤ ከውጭ የሚገቡትን መድኃኒቶች ጥራታቸው ሃገር ውስጥ ከሚመረቱት የተሻሉ ነው ብሎ እንደሚያምን ጠቅሰው እውነታው ግን ከዚህ ይለያል ነው ያሉት። በዓለም አቀፍ ደረጃ በአደገኝነት የተፈረጁ ምንም ፈዋሽ ንጥረ ነገር የሌላቸው ወይም የተሟላ ፈዋሽ ንጥረ ነገሮች የሌሏቸው መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ ጭምር እየተሰራጩ መሆናቸውን አመልክተዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በተደረገው ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ ንጥረ ነገሮቻቸው ከደረጃ በታች የሆኑ መድኃኒቶች በሃገሪቱ ስምንት በመቶ መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች በድንበርና በአየር መንገድ በኩል በህገ ወጥ መንገድ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡ ነጋዴዎቹ ህገወጥ መድኃኒቶች በድብቅ በስልክና በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚስጥር እያሰራጩ በመሆናቸው ለመቆጣጠር ከባድና ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ዳይሬክተሯ አሳስበዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ኢትዮጵያ የስፖርት ውርርድ ከተስፋፋባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ሆነች። የስፖርት የኦንላይን ውርርድ በአፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገቢ እያስገኘለት እንደሆነ ይህንን ስራ በበላይነት የሚያስተዳድረው ኤን ሶፍት አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ገቢ እያገኘ ያለው ከደቡብ አፍሪካ እንደሆነ የገለፀው ድርጅቱ ሌሎች አገራት ውስጥ ይህ ቁማር በመስፋፋቱ ዘንድሮ ሌሎች አገራት ደቡብ አፍሪካን ሊበልጡ እንደሚችሉ አስረድቷል፡፡ ኔን ሶፍት ለዘንድሮ ማለትም የ2021 ገበያው አምስት አገራት ላይ እንዳነጣጠረም ገልጿል፡፡ እነዚህ አምስት አገራትም ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ዚምቡዋዌ፣ ሌሶቶና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ የድርጅቱ የአፍሪካ ገበያ ሴልስ ማኔጀር ማርኮ ዶዚች በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ‹‹የገበያ ጥናት አድርገንና ያለውን አቅም ተረድተን በኢትዮጵያ ውስጥ ወኪሎችን ማሰራት የጀመርነው ከሴፕቴምበር 2019 አንስቶ ነበር፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ግንኙነት ደካማ መሆኑን በመረዳታችን ለወኪሎቻችን በጣም አስገራሚ የድረ ገፅ ኮድ ሰጥተን እንዲሰሩ ለማድረግ ችለናል፡፡ ይህ ደግሞ ውጤታማ ያደረገን ከመሆኑም በላይ አሁን አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለማስተዋወቅ እየሞከርን እንገኛለን›› ብለዋል፡፡ Via Fidel Post @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ለስድስተኛ ጊዜ ምርጫ ያሸነፉት የቻድ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ተገደሉ! ፕሬዝደንቱ በአማጺያን ጥቃት መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ በብሔራዊ ቴሌቪዥን አስታውቋል፡፡ ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በሶማሌ ክልል በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረው አምስተኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (psnp 5) በዛሬው እለት በይፋ ተጀመራል ። መርሃግብሩን የሶማሌ ክልል የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ከፌደራል የግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጅግጅጋ ከተማ አዘጋጅቷል፡፡ 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራም (psnp 5) ማስጀመሪያ ስነስርአት ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፤ የተለያዩ የክልሉ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮና የግብርና ሚኒስቴር ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል። በስነስርአቱ ላይ ተገኝተው በክልሉ በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረውን 5ኛውን ዙር የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራምን በይፋ ያስጀመሩት የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ናቸው:: በክልሉ ባለፉት አምስት አመታት የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የአፈርና የውሀ ጥበቃ ስራዎች በማከናወን ፤ የመንገድ ጥገናና የተለያዩ አገልግሎት መሰጫ ማዕከላትን በመስራት መርሀግብሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል። ባለፉት አምስት አመታት ተግባራዊ ሲደረግ በቆየው 4ኛው ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራም አፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል በቀጣይ ፕሮግራሙን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ለቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ የሚደረገው 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሁም ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላቶች በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል። በስነስርአቱ ላይ የ4ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈፃፀምና ቀጣዩ 5ኛው ዙር የፕሮግራሙ እቅድ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የትራፊክ ቅጣትን በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክትር አቶ ጅሬኛ ሂርጳ የትራፊክ ቅጣት መተግበሪያው የደንበኞችን እንግልት የሚቀንስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህም በከተማው ያለውን የትራፊክ እንቅሰቃሴ ፍሰት ሰላማዊ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡ የቅጣት መተግበሪያው በኢ-ብር አማካኝነት በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚከፈል መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የአገልገሎት አሰጣጡ ላይ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በዓመት ከ700 ሺህ በላይ የትራፊክ ቅጣቶች እንደሚመዘገቡም ኤጀንሲው አስታወቋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ናርሲክ ጋር መከሩ፡፡ በውይይታቸው በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳይ ማንሳታቸው ተገልጿል፡፡ የአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር በክልሉ እየተሻሻለ ስለመጣው ሰብዓዊ አቅርቦት አበረታተዋል፡፡ እንዲሁም በክልሉ ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሰብዓብዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋራ ለመመርመር የወሰዱትን እርምጃ አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እንዲወጡ የተወሰደው ውሳኔም የሚበረታታ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ደመቀ በበኩላቸው በክልሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም ቢሆን ተግዳሮቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡ Via fbc @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
ባሕርዳር በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የተቀናጀ ሽብር አውግዛለች! እንዲሁም በተመሳሳይ ደብረማርቆስ ላይ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን ግድያ አውግዘዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በኩባ ብቸኛውና አድራጊ ፈጣሪው የኩባ ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚጉኤል ዲያዝ ካኔልን ዋና ፀሐፊው አድርጎ መረጣቸው፡፡ ዋና ፀሐፊነቱ በፖለቲካ ማህበሩ ከፍተኛው የመሪነት ደረጃ ነው፡፡ የኩባ አብዮት መሪ የፊደል ካስትሮ ታናሽ ወንድም ራውል ካስትሮ የፓርቲውን ዋና ፀሐፊነት ሀላፊነት እንደሚያስረክቡ የተናገሩት ባለፈው አርብ እንደነበር ሬውተርስ አስታውሷል፡፡ ከ60 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ የኩባ ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበሩ መሪነት ከካስትሮ ቤተሰብ እጅ ወጥቷል ተብሏል፡፡ ራውል ካስትሮ ከእንግዲህ በአረጋዊ መካሪነቴ እቀጥላለሁ ያሉት በ89ኛ ዓመታቸው ላይ በሚገኙበት ወቅት ነው፡፡ ፕሬዝዳንትነቱን ወደ ማጉኤል ዲያዝ ካኔል ካስተላለፉ 3 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ የኩባ ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ዋና ፀሐፊ የሆኑት ካኔል በፖሊሲ ጉዳይ ራውል ካስትሮ እንዲያማክሩኝ አደርጋለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በአዲስአበባ የሚገኙ አንዳንድ የግል ሆስፒታሎች የኮሮና ሕክምና ለማግኘት ለአልጋ መያዣ ብቻ እስከ ኹለት መቶ ሺሕ ብር ድረስ እንደሚጠየቁ ታካሚዎች እና የታካሚ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የኮሮና ሕክምና ወደሚሰጥባቸው የግል የሕክምና መስጫ ተቋማት ሄደው የታከሙ እና ቤተሰቦቻቸውን ያሳከሙ አስተያየት ሰጭዎች ሲገልጹ፣ ወደ ሆስፒታሎቹ ለሕክምና ሲያመሩ አልጋ ይዞ ለመታከም 95 ሺሕ ብር ዝቅተኛ የማስያዣ ክፍያ ሲሆን 200 ሺሕ ብር ደግሞ ከፍተኛው አልጋ ይዞ ለመታከም የሚጠየቁት የማስያዣ ገንዘብ መሆኑን ነው። የተጠቀሰው ገንዘብ እጃቸው ላይ ከሌለ የቤት ካርታ ወይንም የመኪና ሊብሬ ጭምር ለማስያዣነት እንደሚጠየቁ ተናግረዋል። ታካሚዎቹ እና የታካሚ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ካስያዙት የመታከሚያ ገንዘብ በተጨማሪ ለመድኃኒት መግዣ ማለትም አንድ ጊዜ ለሚወጋ መድኃኒት እስከ 35 ሺሕ ብር አውጥተው መግዛታቸውን ጭምር ተናግረዋል። ታካሚዎቹ ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል (ICU) ገብተው ሕክምናቸውን የሚከታተሉ ከሆነ ደግሞ የሕክምና ክፍያው እንደሚጨምር ገልጸዋል። በዚህ የሕክምና ሂደት እሰከ አንድ ነጥብ ኹለት ሚሊየን ብር ያወጡ የኮቪድ ታካሚ እንዳሉም አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች። በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ሕክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር ለሕብረተሰቡ በእጂ ስልክ የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ጭምር እያስታወቁ እንደሚገኙ ይታወቃል። ኢንስቲቲዩቱ በተጨማሪም የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት ያለበት ሲሆን የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ የኮቪድ ታማሚዎች ቁጥር የሕክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። ይህንን ተከትሎ በመንግሥት ሆስፒታሎች ሕክምና ለማግኘት ባለመቻላቸው ወደ ግል ሆስፒታሎች እየሄዱ የሚታከሙ የኮቪድ ታማሚዎች አልጋ ለመያዝ ብቻ በትንሹ ከመቶ እስከ መቶ ሀምሳ ሺሕ ብር ድረስ እንደሚጠየቁ ታካሚዎቹ ተናግረዋል። አዲስ ማለዳ ለሥራ በተዘዋወረችባቸው ቦታዎች ኅብረተሰቡ በኮሮና ላለመያዝ የሚያደርገው ጥንቃቄ የበሽታውን አስከፊነት እንዲሁም በበሸታው ከተያዙ በኋላ ሕክምና ለማግኘት ያለውን ውጣ ውረድ ያላገናዘበ መሆኑን ታዝባለች። የኮሮና ሕክምና መስጫ የሆኑ ተቋማት አካባቢ ያለው የሰው መጨናነቅ እና በሕክምና መስጫ ስፍራው ደግሞ በእርግጠኝነት የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ታካሚዎች መኖራቸው እየታወቀ የሚደረገው ጥንቃቄ ቸልተኝነት የተሞላበት መሆኑንም አዲስ ማለዳ ታዝባለች። በኢትዮጵያ ይህ ዜና እስከተሰራበት ሐሙስ ሚያዝያ ሰባት ድረስ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 236 ሺሕ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 3 ሺሕ 285 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 የበለጠ እንዳልሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ። በጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዮርዳኖስ አለባቸው የግል ሆስፒታሎች ኮቪድን ለማከም ስለሚያስከፍሉት ክፍያ ምንም መረጃ እንዳልነበራቸው ገልጸው፣ አገራችን ግን በነጻ ገበያ ኢኮኖሚ መመራቷን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል ብለዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ልዩ የጸጥታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ገለጸ፡፡ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በንጹሐን ላይ ሞት፣ በንብረት ላይ ውድመት እና በክልሉ ሰላም ላይ ስጋት አጥልቶ ሰንብቷል፡፡ ከጥቃት ያመለጡትም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሸሽተዋል፡፡ ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ በየአካባቢው የጸጥታ መዋቅር ተሰማርቷል ያሉን የክልሉ ሰላም እና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በሰሜን ሽዋ ዞን አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር ከክልሉ እና ከፌደራሉ የጸጥታ ኀይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ ተጨማሪ የክልሉ የጸጥታ ኀይል ወደ ቦታው አቅንቷል ያሉት አቶ ሲሳይ ትናንት ግጭቶች ቢኖሩም የጸጥታ ኀይሉ ችግሩን እየተቆጣጠረው ነው ብለዋል፡፡ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ እና በከተማዋ አካባቢ የመሸጉ ሥርዓት አልበኞችን ከሕዝቡ ጋር እየለዩ መሆኑን አቶ ሲሳይ ዛሬ ለአሚኮ በሰጡት መረጃ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ የገጠመው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር በሽብር ቡድኖች ክልሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዳይቀጥል ታስቦበት የሚሠራ በመሆኑ ሕዝቡ ይህንን በመረዳት ከጸጥታ ኀይሉ ጎን በመቆም የአካባቢውን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ አቶ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ Viaአሚኮ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጠ በዚህም በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት በንጹሃን ዜጎች ላይ የህይወት እና ንብረት አደጋ ባደረሱ የጥፋት ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን መከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ በመግለጫውም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይ ክልል ውጤታማ ህግ የማስከበር ተልእኮውን በጀግንነት በመፈጸም ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጸጥታ ችግሮች እየተስተዋሉ ይገኛል ብሏል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ የሰራዊቱን ህገ መንግስታዊ ተልእኮ ለማስተጓጎል ታስቦ የተሰሩ የጥፋት ሴራዎች በሰላም ወዳዱ ህዝባችን እና በመከላከያ ሰራዊታችን የተቀናጀ ስራ ሊከሽፍ ችሏል ነው ያለው። 1ኛ በመተማ መስመር ለዘመናት አብረው በኖሩ የቅማንት እና የአማራ ተወላጆች መካከል የተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ሃይሎች ከህብረተሰቡ እና ከአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የተቀናጀ ስራ በመስራት የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል ፡፡ በወለጋ ቡሬ መስመር በጊዳ አያና አንገር ጉቴ አዋሳኝ አካባቢዎች ለረዥም ጊዜ አብሮ በኖሩ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎችን ሆን ብሎ ለማጋጨት ታስቦ የተደረገው ሙከራ በአካባቢው ህብረተሰብ ትብብር ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ ተችሏል ብሏል መግለጫው። እንደዚሁም የኢትዮጵያን የገቢ እና ወጪ የንግድ እንቅስቀቃሴን ለመገደብ በማሰብ በሱማሌ እና የአፋር ኢሳ ህዝቦችን ለማጋጨት የተሰራው ሴራ በሰላም ወዳዱ ህዝባችን የተቀናጀ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ለመዋል ተችሏልም ነው ያለው፡፡ ሌላው ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን ወረዳዎች በተለይም በዚህ ሁለት ሶስት ቀን በአጣዬ ከተማ እና በአካባቢው በታጠቁ ሃይሎች በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ በደረሰው ውድመት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ በዚህ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች መጽናናትን ይመኛል ብሏል፡፡ በዚህ የጸጥታ ችግር ተሳታፊ የሆኑ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና መሳርያ ይዘው በጸጥታ አካላት ላይ ተኩስ የከፈቱ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ የገደቡ ጸረ ሰላም ሃይሎች ላይ ሰራዊታችን እርምጃ መውሰድ መጀመሩን እየገለጽን÷ መንገድ መዝጋትን ጨምሮ የህብረሰተቡን ሰላም በማወክ ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሚኒስቴሩ በጥብቅ ለማሳሰብ ይወዳልም ብሏል መግለጫው፡፡ በዚህም መሰረት በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን ወረዳዎች ከተከሰተው የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ከክልል እና ከፌዴራል የጸጥታ ተቋማት ጨምሮ ሶስቱንም ዞኖች ያካተተ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ሚኒስቴሩ አመላክቷል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ጸጥታ በማደፍረስ ስራ ላይ በተሰማሩ የጥፋት ቡድኖች ላይ እርምጃ በመውሰድ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራን ይሰራልም ነው ያለው፡፡ በዚህም መሰረት የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲባል የሚከተሉት ክልከላዎች የተደረጉ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ይገልጻል፡፡ 1ኛ ከደብረ ሲና እስከ ኮምቦልቻ አዋሳኝ ወረዳዎች መንገድ ላይ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ እስከ 20 ኪ/ሜ ውስጥ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ 2ኛ መንገድ መዝጋትን ጨምሮ አብያተ ክርስቲያናትን እና የመንግስት ተቋማትን የግለሰብ መኖርያ ቤትን እና ንብረት ማውደም ወይም ለዚህ ተግባር በተናጥልም ይሁን በቡድን መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን እና ቀጣይ በኮማንድ ፖስቱ ለህብረተሰቡ የሚገለጹ ክልከላዎችን ተላልፎ የተገኘ የፖለቲካ ድርጅት የመንግስት መዋቅር እና በድኖች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን መታወቅ አለበት ብሏል፡፡ በመጨረሻም መላው ህብረተሰባችን እንደወትሮው ሁሉ ከጸጥታ ተቋማት ጎን በመሰለፍ ለገሀራችን ሰላም እና ደህንነት የበኩሉን ገንቢ ሚና እንዲጫወት ጥሪያችንን እናቀርባለን ፡፡ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈፀመ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ተገለጸ:: የዞኑ የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ መኮንን ለቢቢሲ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመው በዞኑ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ውስጥ ነው። ኃላፊው ጨምረውም "በጣም ከፍተኛ" ቁጥር ያለው የታጠቀ ኃይል "ወረራ" መፈፀሙን ተናግረዋል። የታጠቀው ኃይል " ቤቶችን ያቃጥላል፤ ሰዎችን ይገድላል" በማለትም ወደ አካባቢው የገባው የፌደራል የጸጥታ መዋቅርና የመከላከያ ሰራዊትም "ከአቅሙ በላይ" መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። የአማራ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለክልሉ ሚዲያ በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑን ገልፀዋል።ለጥቃቱም 'ኦነግ ሸኔ እና ሌላ 'ተከታይ' ያሉትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።በጥቃቱ የፀጥታ አካላት መዋቅርም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አክለዋል። ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ማታ ጀምሮ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና ሰሜን ሸዋ መካከል በሚገኙ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር መኖሩን ገልፀው፤ ይህ ግን ጋብ ብሎ እንደነበር ኃላፊው አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ትናንት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የታጠቀ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባት ጥቃት በመግባት በአጣየ፣ አንጾኪያና ኤፍራታ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተናግረዋል። ©BBC @Shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በተለያዩ ጉዳዮች የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በሰለጠነ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ የተጀመሩ ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን የሠላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የሠላም ሚኒስትሯ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተቋማቸው ባለፉት ሶስት ዓመታት በሃገሪቷ ዘላቂ ሠላም ማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። “ለዘመናት የተከማቸ ችግርን በአንድ ጀምበር መፍታት አይቻልም” ያሉት ሚኒስትሯ፥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በሰለጠነ መንገድ በውይይት የመፍታት ልምድ ማዳበር አንደኛው መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ረገድ በሚኒስቴሩ የሚዘጋጁ ስልጡን የውይይት መድረኮች ውጤት እያስገኙ መሆኑን ነው የገለጹት። በእነዚህ የምክክር መድረኮች ምሁራንን ጨምሮ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞችና በሁሉም የሃገሪቷ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ናቸው። ሚኒስትሯ በውጤታማነቱ ስምንት የሙያና የብዙሃን ማኅበራት የሚሳተፉበትና የሚያስተባብሩትን የውይይት መድረክ ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌላ መልኩ ከሃገራዊ ለውጡ በኋላ በውጭ የሚኖሩ የታጠቁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲወዳደሩ የማሳመኑ ስራ ሌላው ውጤት መሆኑን አንስተዋል። መሰል ውይይቶች አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ ከመፍታት ባለፈ ለዘላቂ ሠላም ግንባታና ለዴሞክራሲ ምህዳሩ መስፋት ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸውም ነው የተናገሩት። @Shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
በአጣዬ በካራ ቆሬና በቆሬ ከተሞች በተከፈተ ውጊያ ከፍተኛ የሰው እና የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡ ችግሩ አሁንም አልተቃለለም፡፡ እሸቴ አሰፋ @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መሰረታዊ የምግብ ፍጆታዎች ያለውጭ ምንዛሬ ፈቃድ እንዲገቡ መፈቀዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሩ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ስኳር፣ምግብ ዘይት፣ስንዴ፣ሩዝ፣የዱቄት ወተት ከውጭ ሀገር እንዲገቡ መወሰኑን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ በዚህም 250 ሺህ ዶላር (የውጭ ሀገር ገንዘብ) ያላቸው ምንጩን በብሔራዊ ባንክ እያረጋገጡ ማስገባት ይችላሉ ነው ያሉት፡፡ Via fbc @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅማ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ገልጿል። አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው የጂማ አውሮፕላን ማረፊያ ለ ሁለት ቀናት [ሚያዝያ 11 እና 12 ቀን 2013 ዓ.ም] እድሳት ስለሚደረግለት ነው ብሏል። እድሳቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መደበኛ በረራው ከሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል። Via EthiopianAirlines @shegernewsbot @shegernewsETH
نمایش همه...
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሬቤካ ሞቲን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት፣ የጤናና የሰላም ጥብቅ ቁርኝት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሯ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጤናን ጨምሮ እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ገለጻ አድርገዋል። አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት፣ ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ፕሮግራሞች እና በአጠቃላይ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ አዳጋች ሁኔታዎች በገጠማት ጊዜ ሁሉ ለሚያደርጉት እገዛ ከልብ አመስግነዋል። ዳይሬክተሯ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የመሰረታዊ ጤና አጠባበቅ አገልግሎት ሽፋን ለበርካታ አመታት ሲከታተሉት የቆየ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ ዘርፍ መሆኑ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ እንደሆነም ተናግረዋል። በመጨረሻም በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች የኮቪድ-19 ክትባት እንዲደርስ በመደረጉ በተባበሩት መንግስታት እና በሰራተኞቹ ስም ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
نمایش همه...
የኢትዮጵያ የወቅቱ አቋም በግድቡ ውሃ ሙሌት እና በሙሌቱ አስተዳደር ላይ ብቻ መነጋገር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ባሳለፍነው ሳምንት የግድቡ ተደራዳሪ ሶስቱ ሃገራት ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በማቅናት ያደረጉት ድርድር በፍላጎት መለያየት ሳቢያ ያለስምምነት መጠናቀቁን አስታውሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለድርድሩ ወደ ኪንሻሳ የሄደችው እንደተለመደው “የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን ብቻ ይቀረፋል” በሚለው የዲፕሎማሲ መንገድ ማመኗን ለማረጋገጥ ነውም ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ “ወንዙም የአፍሪካውያን ነው” ከሚል የጋራ እሳቤ የሚመነጭ ነው ያሉት ቃል-አቀባዩ፥ ጉዳዩን ከአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ለማራቅ የሚደረገውን ጫና ኢትዮጵያ ፈፅሞ እንደማትቀበል ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ግብፅ ራሷ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ አሁን ህብረቱ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሊቀመንበርነት እስከሚመራበት ጊዜ ድርድሩን ወደራሷ ወደጅ ሃገራት ለማሸሽ እና የግል ጥቅሟን ለማስከበር ወደሚያግዟት ተቋማት ለመሳብ ያልሞከረችው መንገድ አልነበረምም ነው ያሉት አምባሳደር ዲና፡፡ ኢትዮጵያም ይህን አመለካከት ብቻ ሳይሆን “ሌሎች ወገኖችም የአፍሪካን ያህል በግድቡ ድርድር ላይ ሚና ይኑራቸው” የሚለውን ፍላጎት እንኳን እንደማትቀበል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ከሱዳን ጋር በተያያዘም በተለይም የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሯ አብደላ ሃምዶክ በኩል የቀረበውን “በዝግ የእንነጋገር” ጥያቄ ኢትዮጵያ በአንክሮ እንደምትመለከተውም ጠቅሰዋል፡: ሱዳን ከድንበር ግጭት ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመችውን የመሬት ወረራ እና የንብረት ጉዳት በተመለከተ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ወዳጅ ሃገሮቿ ተፅዕኖ በመፍጠር ወደ ቀደመው የግንኙነት መንገዷ እንድትመለስ እንዲያደርጉ ኢትዮጵያ ጥሪ እያስተላለፈች መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ በትግራይ ክልል ካለው ሰብዓዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘም ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው፥ “መንገድ ክፈቱልን” ሲሉ የነበሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መንገድ ሲከፈት ከአሜሪና ከተወሰኑ ሃገራት ውጪ ባዶ እጃቸውን መሆናቸውን መመልከት እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡ በሶዶ ለማ @shegernewsbt @shegernewsETH
نمایش همه...