cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ዜና Ethiopian coffee FC™

በቴሌግራምና በፌስ ቡክ ስለ ኢትዮጲያ ቡና √ ዝውውሮች √ የጨዋታ ውጤትና √ የቀጥታ ስርጭቶች √ መልዕክቶች በተገቢው ሰዓትና ቦታ የበለጠ መረጃ ለማግኘት; መረጃ ለማስተላለፍ እና ጠያቄ ለማቅረብ

نمایش بیشتر
Advertising posts
1 135مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#አውቶ_ቅምሻ ተሽከርካሪ ላይ የሚፃፉ የእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃላት ምንነትና ትርጉማቸው! (V8, D-4D, GDI, SRS Airbag, 4WD, 2WD) በሳሙኤል አማረ ተሽከርካሪ ላይ በአጭሩ ስለሚፃፉ ፅሁፎች አብዛኛው ሰው በቂ ግንዛቤ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት የሞተር አይነቶችን ለተሽከርካሪው ስያሜ ሲጠቀሙት ይስተዋላል:: በዛሬው የአዉቶ ቅምሻ ዝግጅታችን የነዚህን ቃላት ትክክለኛ ትርጉም እናስቃናችሁአለን:: V8 👉ቪ ኤት 8 ሲሊንር ያለዉ እና ቅርፁ V የሆነ ሞተር ነዉ። V የሞተሩን ቅርፅ ማለትም የሲሊንደሮችን አቀማመጥ 8 ደግሞ የሲሊንደሮችን ብዛት ይወክላሉ (የሲሊንደሮችን አቀማመጥና ብዛት ከፎቶው ይመልከቱ!) 👉ሲሊንደሮቹ ሞተር ላይ በሁለት ረድፍ እኩል ብዛት ኑሯቸዉ (አራት አራት) ትይዩ ሆነው ይቀመጣሉ። በተመሳሳይ V6 ኢንጅን 6 ሲሊንደሮች ያሉት ሲሆን አቀማመጣቸዉ ከ V8 ኢንጅን ጋር ተመሳሳይ ነዉ። ስለዚህ V8 የሞተር አይነት እንጂ የመኪና መጠሪያ ስም (ብራንድ) አይደለም:: D-4D ዲ ፎር ዲ በተመሳሳይ የመኪና ብራንድ ስያሜ ሳይሆን የሞተር አይነት ነው:: 👉ዲ ፎር ዲ የናፍጣ ሞተር ሲሆን D-4D የሚለው የእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ሲተነተን - (Direct Injection 4 Cylinder Common Rail Diesel Engine) የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ ይህ ሞተር (ኢንጅን) አራት ሲሊንደሮች ያሉትና በሲሊንደሮች ውስጥ የገባው አየር ከታመቀ በኋላ ሰዓቱን ጠብቆ በእያንዳንዱ ሲሊንደር በቀጥታ ናፍጣ በመርጨት ኃይል ማምረት የሚችል የሞተር አይነት ነዉ:: GDI ዘመናዊ የቤንዚል መኪኖች ላይ GDI የሚል ፅሁፍ አለ። 👉GDI ማለትም ጋዞሊን ዳይሬክት ኢንጀክሽን ማለት ሲሆን የነዳጅ አረጫጭ ስርዓት ነዉ። ይህን የነዳጅ አረጫጭ ዘዴ የሚጠቀሙት ዘመናዊ የቤንዚን መኪኖች ናቸዉ። 👉በብዛት በቤንዚን ሞተር ነዳጅና አየር በካርቡሬተር አማካኝነት ተቀላቅሎ ወደ ሲሊንደር የሚገባና በስፓርክ ፕለግ (ካንዴላ) አማካኝነት የሚቀጣጠል ሲሆን ይህ GDI ሞተር ግን ካርቡሬተር የለዉም። ነዳጅና አየር በአንድ ላይ ተቀላቅሎ ወደ ሲሊንደር አይገባም:: እንደ ናፍጣ ሞተር መጀመሪያ አየር ወደ ሲሊንደር ከገባ እና ከታመቀ በኋላ ቤንዚን በጉም መልክ ወደ ሲሊንደር ይረጭና የመቀጣጠልና ሀይል የማምረት ስራ ይካሄዳል። ጂ ዲ አይ ኢንጅን ነዳጅ የሚረጨዉ በከፍተኛ ግፊትና በቀጥታ በያንዳንዱ የሲሊንደር ኮምበስሽን ቻምበር ላይ ነዉ። ይህም ሰዓቱን የጠበቀ የነዳጅ አረጫጭ እና የተመጠነ ነዳጅ እንዲረጭ ያደረገዉ ሲሆን ነዳጅ ቆጣቢ እንዲሆንም አድርጎታል። በካይ ጋዝ ልቀትንም እንዲቀንስ አስችሎታል። SRS Airbag 👉ኤር ባግ መሪ እና ዳሽ ቦርድ ላይ የሚገኝ የአየር ከረጢት ሲሆን ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ በአየር በመሞላት እና ተስፈንጥሮ በመዉጣት አሽከርካሪ እና ተሳፋሪ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ከባድ ጉዳት ይከላከላል። 👉SRS;- ሰፕለመንታሪ ሬስትሬንት ሲስተም ማለት ሲሆን ትርጉሙም ተጨማሪ ማገጃ ስርዓት ማለት ነዉ። ይህ የተባለበት ምክንያት ኤር ባግ ከደህንነት ቀበቶ በተጨማሪነት አደጋን ለመከላከል የተገጠመ በመሆኑ ነዉ። 4WD 4WD - ሲተነተን Four wheel drive (ፎር ዊል ድራይቭ) የሚል ትርጉም ይሰጣል:: ፎር ዊል ድራይቭ ተሽከርካሪዎች በምቹ አነዳድ ጊዜ በኋላ ጎማዎች እንቅስቃሴ ተሽከርካሪው የሚንቀሳቀስበት የፊት ጎማዎች በነፃ የሚሽከረከሩበት ስርዓት ያላቸው ሲሆን በአስቸጋሪ ወይም ኃይል በሚያስፈልግበት የአነዳድ ሁኔታ ኃይል ለአራቱም ጎማዎች እንዲደርስ በሚፈለግበት ጊዜ አሽከርካሪዉ የማርሽ እጀታዉን በማንቀሳቀስ የሞተር ኃይል ለሁሉም ጎማዎች እንዲደርስ የሚያስችልበት ስርዓት አላቸው። 2WD 2WD - የሚለው የእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል Two wheel drive (ቱ ዊል ድራይቭ ) የሚል ትርጉም ይሰጣል:: በ ቱ ዊል ድራይቭ መኪኖች (Two wheel drive) ኃይል ወደ ሁለቱ ጎማዎች ብቻ የሚደርስ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ጎማዎች በነፃ በመሽከርከር አጠቃላይ መኪናዉ የሚንቀሳቀስበት ስርዓት አላቸው። FWD እና RWD የተሰኙ የቱ ዊል ድራይቭ አይነቶች ደግሞ Front wheel drive (ፍሮንት ዊል ድራይቭ) እና Rear wheel drive (ሬር ዊል ድራይቭ) የሚል ትርጉም አላቸው:: (Walta)
نمایش همه...
የአቡበከር ናስር ጉዳት ወቅታዊ ሁኔታ… የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ጎል አግቢ በመሆን ባለታሪክ የሆነው አቡበከር ናስር ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ካቀና በኋላ ጎሎችን በማስቆጠር መልካም የሚባል ጅማሮ አሳይቶ ነበር። ሆኖም ከዚህ ቀደም ባጋጠመው ከበድ ያለ ጉዳት ምክንያት ለወራት ከሜዳ ለመራቅ ተገዶ ቆይቷል። አቡኪ ባሳለፍነው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ አገግሞ ክለቡ ሰንዳውንስ ከኦርላንዶ ፓይረስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ዳግም ወደ ሜዳ ቢመለስም ሜዳ ላይ መቆየት ችሎ የነበረው ለአርባ አምስት ደቂቃ ብቻ ነበር። የኦርላንዶ ፓይረሱ የግብ ዘብ ቁርጭምጭሚቱ ላይ ባደረሰበት ከበድ ያለ ጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ሊወጣ ችሏል። ጉዳቱ ከገጠመው በኋላ የኤም አር አይ ምርመራ ለማድረግ እብጠቱ እስኪቀንስ የተወሰኑ ቀናት መቆየት የነበረበት አቡኪ አሁን ላይ ምርመራውን አድርጎ ውጤቱን አውቋል። በዚህም መሰረት የደረሰበት ጉዳት ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ከተጨዋቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም የቁርጭምጭሚት ስፔሻሊስት ዶክተር ጋር ቀርቦ እንደሚታይም ጨምሮ ነግሮናል። t.me/Ethiopiancofee
نمایش همه...
የጋሽ ጫን ያለው ተኮላ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ቡናማዎች ማልያችሁን አድርጋችሁ ዛሬ 9 ሰዓት በብሔረ-ፅጌ ማርያም ቤ/ክርስቲያን ተገኙ
نمایش همه...
ዜና እረፍት ☕️ኢትዩጵያ ቡና ከምስረታው 📅1968 ጀምሮ ለአመት ታሪኩ ውስጥ ታማኝና ባለ ውለታ ደጋፊው ከሆኑት ውስጥ ከወጣትነት እስከ ጡረታ ያገለገሉትን አቶ ጫንያለው ተኮላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ:: 🏟 በአዲስ አበባ ስታድየም የመጀመሪያ የቡና ባንዲራ ስታድየም ውስጥ ያውለበለቡት ምን ይሄ ብቻ ኤሴሳቦ የሚለውን ዜማ ስታድየም ውስጥ አሄ ኤሴሳቦ የኛ ቡና ገበያ አደገኛ እያሉ በማዜም የኢትዩጵያ ደጋፊዎች መዝሙር ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቁት እኒው አቶ ጫንያለው ተኮላ ነበሩ ፡፡ ጋሼ ነብሶት በሰላም ትረፍ ለወዳጅ ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን!!
نمایش همه...
ተሰናባቹ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ክለቡ ያቀረበለትን በስምምነት እንለያይ ጥያቄ ውድቅ አደረገ። ከደቂቃዎች በፊት አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እንደተናገረው” ከኢትዮጵያ ቡና የቀረበልኝ በስምምነት የመለያየት ጥያቄን ብቀበለውም የስምምነቱ ይዘት ላይ ጥያቄ በማንሳት የስንብት ደብዳቤውን ሳልቀበል ወጥቻለሁ ውሉ ላይ ከመጀመሪያ ዙር 30 ጨዋታ 75 በመቶ ወይም ከ1-3 ማሳካት ይላል በ15ቱ ጨዋታ ላይ ባላሳካም ከ1-3 የሚለውን አሳካለሁ ብልም አልተቀበሉኝም እኔም በስምምነት የሚለውን ጥቅማ ጥቅሜና ደመወዜ ላይ ያለውን ባለመቀበሌ የሰጡኝን ደብዳቤ ሳልወስድ ወጥቻለሁ” ብሏል። አሰልጣኙ እንዳለው ” በውል መቋረጡ ላይ ፍቃደኛ ነኝ ነገር ግን በውሌ መሠረት ያለኝ ክፍያና ጥቅማ ጥቅም ዙሪያ ላይ ከጠበቃዬ ጋር ተነጋግሬ አሳውቃለሁ” ብሏል። አሰልጣኙ ግን ደብዳቤውን ተቀብሎ ምላሽ መስጠት እየቻለ አልቀበልም ማለቱ ለሌላ ውዝግብ በር እንዳይከፍት ስጋት ፈጥሯል። በጉዳዩ ዙሪያ የተጠየቁት የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ግን ” በውላችን መሠረት አሰናብተነዋል። ውሉ ከጨዋታው 75 በመቶ ድል ማሳካት አለበለዚያ ከ1-3 መውጣት ከሚለው አንዱን ካላሳካ የማሰናበት መብት አለን ለዚህም ነው ያሰናበትነው” ሲሉ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት “በውሉ መሠረት ከሁለቱ ተዋዋዮች አንዱ ውል ማቋረጥ ከፈለገ ከአንድ ወር በፊት አሳውቆ ውሉን ማቋረጥ ይችላል ይላል እኛም በውላችን መሠረት ከታህሳስ 30/2015 ጀምሮ ውላችንን አቋርጠናል ብለን ነግረነዋል ደመወዙን ይከፈለዋል ቡድኑ ጋር መሄድ ግን አይችልም” በማለት የክለቡን አቋም አሳውቀዋል።
نمایش همه...
ሰዉነት ቢሻዉ ወደ አሰልጣኝነት........ ⚡️ የአሰልጣኝ ለዉጥ እንደሚያደርግ የተነገረዉ ኢትዮጵያ ቡና ቀጣዩን አሰልጣኝ ምርጫ ዉስጥ የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ እንደተካተቱበት ተሰምቷል ፤ አሰልጣኙ ከሀገራችን ቀደምት የእግር ኳስ ሊቆች መካከል አንዱ ሲሆን ለምርጫዉ ከታጩት ሶስት አሰልጣኞች አንዱ ናቸዉ። ⚡️ ከተመስገን ዳና ጋር ሊለያይ መሆኑ የተሰማዉ ክለቡ ከሰዉነት ቢሻዉ ዉጪ ሁለት አሰልጣኞችን እያናገረ መሆኑ ሲሰማ በገንዘብ ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ንግግር ላይ ናቸዉ ፤ ከእነርሱ በተጨማሪ ሁለት አሰልጣኞች ገና ካሁኑ ሲቪያቸዉን ማስገባታቸው ተሰምቷል። #yonasamare
نمایش همه...
ሰዉነት ቢሻዉ ወደ አሰልጣኝነት........ ⚡️ የአሰልጣኝ ለዉጥ እንደሚያደርግ የተነገረዉ ኢትዮጵያ ቡና ቀጣዩን አሰልጣኝ ምርጫ ዉስጥ የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ እንደተካተቱበት ተሰምቷል ፤ አሰልጣኙ ከሀገራችን ቀደምት የእግር ኳስ ሊቆች መካከል አንዱ ሲሆን ለምርጫዉ ከታጩት ሶስት አሰልጣኞች አንዱ ናቸዉ። ⚡️ ከተመስገን ዳና ጋር ሊለያይ መሆኑ የተሰማዉ ክለቡ ከሰዉነት ቢሻዉ ዉጪ ሁለት አሰልጣኞችን እያናገረ መሆኑ ሲሰማ በገንዘብ ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ንግግር ላይ ናቸዉ ፤ ከእነርሱ በተጨማሪ ሁለት አሰልጣኞች ገና ካሁኑ ሲቪያቸዉን ማስገባታቸው ተሰምቷል። @yonasamare
نمایش همه...
ኢትዮጵያ ቡና ውጤታማ አልሆነም በሚል ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር መለያየቱ ይፋ ሆኗል። አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ቡድኑን ውጤታማ እንደሚያደርግ ቃል ቢገባም የተመዘገበው ውጤት በዝውውሩ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ቡና አመራሮችን ያስደሰተ አልሆነም። በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ በተመሳሳይ በአራቱ ተሸንፎ ሁለት ጨዋታ ብቻ አቻ የወጣው አሰልጣኙ በተለይ በሀድያ ሆሳዕና 1ለ0 መሸነፉ ለስንብቱ ትልቁን ሚና መጫወቱ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ቡና የዛሬ 12 ቀን ከአዳማ ከተማ ጋር ቀሪ ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን በ12ኛው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ወደ አዳማ ከተማ በመዞሩ ከተስተካካይ ጨዋታው በኋላ በ13ኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ መድን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በማከናወን ለቻን ውድድር ዝግጅት ውድድሩ ሲቋረጥ በቂ የማገገሚያ ጊዜ እንደሚኖረው ተገምቷል። ከድሬዳዋ ባገኘሁት መረጃ ደግሞ አሰልጣኙ ከክለቡ በመሰናበቱ ከክለቡ ሆቴል በመልቀቅ ወደ ኤርፖርቴት እየሄደ መሆኑ ታውቋል። አመራሮቹ በቀጣዩ 11 ቀን አዲሱን አሰልጣኝ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የውጪ ሀገር አሰልጣኝና የአገር ውስጥ አሰልጣኞችን በማነጋገር ስራ ላይ መጠመዳቸውም እየተነገረ ነው። በእስካሁኑ የአስረኛ ሳምንት ውጤት መሠረት ኢትዮጵያ ቡና በ14.ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
نمایش همه...
11ኛ ሳምንት ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ 👉 #የኢትዮጵያ_ቡና_ከ_ሀድያ ሆሳዕና 🗓 ህዳር 29/2015 ዓ.ም 🕚 ቀን 10:00 ሰዓት 🏟 በድሬዳዋ ስታዲየም
نمایش همه...
وارد شوید و به اطلاعات مفصل دسترسی پیدا کنید

ما این گنجینه ها را پس از تأیید هویت به شما نشان خواهیم داد. ما وعده می‌دهیم که سریع است!