cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቶ mereja🇪🇹🇪🇹

ምን ጊዜም ኢትዮጲያ ትቅደም🇪🇹 🇪🇹 @Onemereja @Onemereja

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
235مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

https://t.me/ethiomerja21 ውድ የቶ mereja ወይም የEthio Mereja ተከታታዮች በሙሉ አሁን የለንበት የቶ Mereja ቻናላችን እይታ እና Subscribers እየቀነሰ በመሆኑ እይሄን ቻናል ልንደልተው ስለሆነ አሁን በአዲስ መልክ የከፈትነውን👇👇👇 channel join/Subscribe በማድረግ ፈጣን እና ታማኝ መረጃዎቻቸንን መከታተል ትችላላቹ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉https://t.me/ethiomerja21 👉ከውድ ምስጋና ጋር 👉Ethio Mereja Management Group
نمایش همه...
Ethio Mereja🇪🇹🇪🇹🇪🇷

🇪🇹ኢትዮጰያና 🇪🇹ኢትዮጵያዊነት ይቅደም 🇪🇷

ሊደለት ነው ☝️1
نمایش همه...
https://t.me/ethiomerja21 ውድ የቶ mereja ወይም የEthio Mereja ተከታታዮች በሙሉ አሁን የለንበት የቶ Mereja ቻናላችን እይታ እና Subscribers እየቀነሰ ስለሆነ እይሄን ቻናል ልንደልተው ስለሆነ አሁን በአዲስ መልክ የከፈትነውን👇👇👇 channel join/Subscribe በማድረግ ፈጣን እና ታማኝ መረጃዎቻቸንን መከታተል ትችላላቹ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/ethiomerja21 ከውድ ምስጋና ጋር Ethio Mereja Management Group
نمایش همه...
Ethio Mereja🇪🇹🇪🇹🇪🇷

🇪🇹ኢትዮጰያና 🇪🇹ኢትዮጵያዊነት ይቅደም 🇪🇷

ሰበር ዜና ‼️ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው። የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው እውን መሆኑን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። እንኳን ደስ አላችሁ ! 🇪🇹 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
نمایش همه...
#NationalExam የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል። የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል። የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል። የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም። ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው። @tikvahethiopia @tikvahuniversity
نمایش همه...
ምድረ ቀዳዳ ተቃጠል እንግዴ My Hero is come back ዋካንዳ for ever ይላታል አንድ ጀለሴ✌️✌️👌👌
نمایش همه...
በአዳማ 330 ተሽከርካሪዎች በመታሰራቸው የትራስፖርት መስተጓጎል ተፈጠረ። ከሐምሌ 23 ቀን ጀምሮ በአዳማ የታክሲ አገልግሎት ችግር የተከሰተ ሲሆን የአዲስ ዘይቤ የአዳማ ሪፖርተር በከተማዋ ባደረገው ቅኝት የሚኒባስ ታክሲዎች እንቅስቃሴ ከወትሮው የቀነሰ መሆኑን ታዝቧል። ከትላንት ሐምሌ 23 ቀን ጀምሮ በአዳማ የሚገኙ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ። ከ330 በላይ ሚኒባስ፣ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እና ጋሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበርና ከማጣራት ሂደት በኋላ እየተለቀቁ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በአዳማ ከተማ አስተዳደር የአዳማ ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት፣ በአዳማ ትራንስፖርት ኤጀንሲ፣ በአዳማ ፖሊስ መምሪያ እና በአዳማ ሚሊሻ ጽ/ቤት በጋራ በተቋቋመ ግብረ ሀይል በከተማው ተሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር በመደረግ ላይ ይገኛል። ቁጥጥሩ በዋነኝነት ትኩረት ያደረው በወንጀል የተሰማሩ ተሽከርካሪዎች፣ ታርጋ በመገለባበጥ የተጠረጠሩ፣ መንጃ ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚያሽከረክሩ፣ የቅጣት ወረቀት ከፍለው እና በሌሎች የህግ ጥሰት ጉዳዮች የተጠረጠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ እንደሆነ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ አስረድተዋል። ከተፈጠረው የታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች እጥረት የተነሳም መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች የታክሲ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ መመልከት ተችሏል።
نمایش همه...
ጠሚ አብይ አህመድ የት ነው ያሉት? ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በፓርላማ ላይ ኦነግ/ሸኔን በተመለከተ ምርር ያለ ንግግራቸውን ካሰሙ በኋላ በቀጥታ ወደ ወለጋ እንዳመሩ እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ የሚካሄደውን ኦፕሬሽን እየመሩ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በአሸባሪው ህወሀት ላይ ግንባር ድረስ በመሄድ ድል ያስመዘገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም ይህንን የህዝብ ጠላት የሆነውን አሸባሪው ኦነግ ሸኔን ለማጥፋት የሚካሄደውን ኦፐሬሽን ከሲቹዌሽን ሩም ሳይሆን እዛው ወለጋ ላይ ሆነው ኦፕሬሽኑን እየመሩ መሆኑ ከውስጥ ያገኘነው መረጃ አረጋግጦልናል፡፡
نمایش همه...
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመዳከም አልፎ ወደ ጎረቤት አገራት በመሸሽ መደበቁን መንግሥት አስታወቀ፡፡ በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸበሪ ቡድኑን ማዳከም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ ቡድኑ እየተወሰደበት ባለው እርምጃ እየተዳከመ ቢሆንም የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ለጥፋት ሀይሉ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ሁኔታው በሕዝብ ዘንድ መጠራጠርን ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በወለጋ አሸባሪው ቡድን ጥቃት ላደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ አላማ ከውጭ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቆም የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
نمایش همه...
የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የወጣው እጣ ውድቅ ተደረገ‼️ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውድቅ አደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ25 ሺሕ 491 ያወጣው የ20/80 እና 40/6 ላይ እጣ የወጣበት ሲስተም ላይ የተአማኒነት ጉድለት እንደነበር በመረጋገጡ ነው የወጣውን ዕጣ ውድቅ ያደረገው፡፡ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ የጀመረው ከተማ አስተዳደሩ በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች መገኘታቸውን መግለጹ ይታወሳል:: @Esat_tv1 @Esat_tv1
نمایش همه...